Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

የኮ/ቀ/ቅ/ጽ/ቤት የድን/አደ/ህ/አ/አ የስራ ክፍል

የ 2016 ዓ/ም የፕሮሰስ ካዉንስል ሪፖርት

መግቢያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንደተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራኒዮ
ቅርንጫፍ የድንገተኛ አደጋዎች ህክምናና አምቡላንስ አገልግሎት የስራ ክፍል የሚገኘው የለውጥ ቡድን
አደረጃጀት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ
ይታወቃል፡፡የዚህን አደረጃጀት ያለውንጥንካሬ በማጎልበትና የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የተሻለ የስራ
አፈፃፀም እንዲኖር ያስችላል፡፡በስራ ክፍሉ የሚገኘው የብሮሰስ ካዉንስል በተሻለ አቅም ለመንቀሳቀስ በስሩ
ለሚገኙ የአቻ ሰራተኞች ፎረም አደረጃጀቶች ሞዴል ለመሆንና በመንግስት ስራ ላይ የተቀመጡትን ዕቅዶች
ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው ይህ ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡

ክፍል አንድ

ቁልፍ ተግባር

የድንገተኛ አደጋዎች ህክምናና አምቡላንስ አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠንካራ የማስፈፀምና የመፈፀም
አቅምን በመገነባባትና ጠንካራ የሚባል የልማት ሰራዊት የአቻ ሰራተኞች ፎረም አደረጃጀት ውስጥ በመፍጠር
የህዝብ አገልጋይነት ስሜትን የተላበሰ፤በአመለካከቱና በክህሎቱ የተሻለ ዝግጅት ያለውና ተልዕኮውን በብቃት
የሚወጣ የልማት ሰራዊት መፍጠር ይሆናል፡፡

የቁልፍ ተግባሩ አላማ

የድንገተኛ አደጋዎች ህክምናና አምቡላንስ አገልግሎት የስራ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን የለውጥ ቡድን በተሻለ
አቅም በማደራጀትና አቅሙን በማሳደግ በስሩ የሚገኙ የአቻ ሰራተኞች ፎረምአደረጃጀረት አባላትን
በዕዉቀጥ፤በክህሎትና በግብዓት አጠቃቀም የተሻለ የልማት ሰራዊት በማድረግ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት
እንዲፈጠር ማስቻልና የለውጥ ቡድኑን ሞዴል እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

አጠቃላይ ግብ

የድንገተኛ አደጋዎች ህክምናና አምቡላንስ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና አገልግሎቱን


በአገልጋይነት ስሜት ሊያከናውን የሚችል የልማት ሰራዊት በመፍጠር የህዝቡን የእርካታ ደረጃ ከፍ ማድረግ
ይሆናል፡፡

ዋና ዋና የተሰሩ ስራዎች
 በየወሩ የአቻ ሰራተኞች ፎረምአደረጃጀት አፈፃፀምን በጋራ የማየት ስራ ሲሰራ ቆይቷል
 የአቻ ሰራተኞች ፎረም አደረጃጀት ውስጥ የሚገኙትን ፈፃሚዎች በእየለቱ የተገመገሙትን
የስራ አፈፃፀም(ካስኬዲንግ) ነጥብ በሳምንት በማጠቃለል ደረጃ እየሰጡ ኮር ፈፃሚ እየለዩ መሄድ
 የተገልጋዩን እና የፈፃሚዎችን የቅሬታ ምንጮች ለይቶ መያዝ እና የመፍትሄ እርምጃ በመዉሰድ
የእርካታ ዳሰሳ ጥናት መስራት ተቸሏል፡፡
 ስራዎችን በአግባቡ፤በወቅቱና በጥራት መፈፀም
 ሞርኒንግ ብሪፊንግ አደረጃጀት አጋዥ የሚሆን ችግር ፈቺ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማምጣት በወስን
አከላለል እና አስቸጋሪ ቦታዎችን በመለየት መፍትሄ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡
 በስራ ክፍሉ ያሉትን የ ሞርኒንግ ብሪፊንግ አደረጃጀት ቡድኖችን በመገምገም ክፍተት ያለበትን ቡድን
መለየት
 ክፍተት እንዳለበት የተለየውን ቡድን ከሌሎች ሞርኒንግ ብሪፊንግ አደረጃጀት ቡድኖች ጋር
በመተባበርና በመደጋገፍ ችግሩን በመቅረፍ ተሻለ የስራ እንቅስቃሴ መፍጠር
 በስራ ክፍሉ የሚገኙ ሰራተኞችን የስራ አፈፃፀማቸውንና በካስኬዲንግ እየገመገሙ እንዲሄዱ
የማብቃት ስራ በመስራት ተችሏል፡፡
 የቡድን ሰስራ ላይ ሰልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል
 በጋራ በመሆን የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን የሴቶች የማደሪያ ክፍል የማደስ ስራ ተሰርቷል፡፡
 የሪፖርት ቼክሊስት በማዘጋጀት ሪፖርቶችን መቀባበል ማቻሉ፡፡

የተገኙ ዉጤቶች

 በሰራተኛው ላይ የህዝብ አገልጋይነት ስሜት በመፍጠር የህብረተሰቡን እርካታ ከፍ ማድረግ ይቻላል


 በእቅድ አፈፃፀማችን የተሻለ ስረዎችን መስራት ችለናል፡፡
 የውድድር መንፈስ በመፍጠር የተሻለ የስራ አፈፃፀም እንዲኖር ሆኖዋል፡፡
 በስራ ላይ በሚያጋጥሙ ችግሮች አፋጣኝ የመፍትሄ ሃሳብ ለመስጠት ተችሏል
 በስራ ክፍሉ የሪፊርም ስራዎችን መስራት ተችሏል፡፡

የነበሩ ክፍተቶች

 አንዳድ ሽፍቶች ላይ የበሰለ ዉይይት አለማድረግ


 አጀንዳ የመያዝ ክፍተቶች

የትኩረት አቅጣጫዎች

 እርስ በእርስ በግልፅ ተገማግሞ የመደጋገፍ ሁኔታ እንዲፈጠር ብዙ ድጋፎችን ማድረግ


 የሳምንታዊ አፈፃፀም መሙያ ቼክ ሊሰት በጊዜው እንዲሞላ በማድረግ ስራዎችን መገምገም
 የሞርኒንግ ብሪፊንግ መዝገብ በእየ ጊዜው በመከታተል ግብረ መልስና አስተያየት መስጠት
 የፕሮሰስ ካዉንስል ግምገማ እና የአቻ ፎረም ዉይይት ባልተቆራረጠ ሁኔታ ለማስቀጠል ትልቅ ጥረት
ማድረግ
 በስራ ላይ ክፍተት ያሳዩ ፈፃሚዎችን ለይቶ በመያዝ ድጋፍ ማድረግ
 የሞርኒንግ ብሪፊንግ አደረጃጀት ኮር መሪዎች የአቅም ውስንነት ሲኖር ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

You might also like