Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 124

የገጠርና የከተማ መሬትን የሚመለከቱ

ህጐችና

አፈጻጸማቸው በኢትዮጵያ

ለረዥም ጊዜ የስራ ላይ ስልጠና


የተዘጋጀ የስልጠና ሞጁል
በፌዴራል የፍትህ አካላት ባለሙያዎች
ስልጠና ማዕከል የተዘጋጀ

2004 ዓ.ም

0
ማውጫ ገፅ

መግቢያ…………………………………………………………………………………………5

ክፍል አንድ፡ የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈጻጸማቸው………………7

ምዕራፍ አንድ፡ የገጠር መሬት ስሪት በኢትዮጵያ……………………………………………..8

1.1 የቅድመ 1967 ዓ.ም የገጠር መሬት ስሪት (በዘውዳዊ ስርዓት)………………………..9

1.2 የገጠር መሬት ስሪት በደርግ ስርዓት………………………………………………….12

1.3 የገጠር መሬት ስሪት በሽግግር ወቅት…………………………………………………14

1.4 የገጠር መሬት ስሪት በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት………………………………………15

1.4.1 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የማውጣት ሥልጣን……………………16

1.4.2 የፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ህግ…………………………….17

1.4.3 የክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ህጎች……………………………22

1.4.4 የፌዴራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ በክልሎች ላይ ያለው


ተፈፃሚነት…………………………………………………………………………….23

የመወያያ ጥያቄዎች……………………………………………………………………27

ምዕራፍ ሁለት፡ የገጠር መሬትን የማግኘት፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብቶች በክልል የሕግ
ማዕቀፎች………………………………………………………………………………….29

2.1. የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብት …………………………………………….29


2.1.1. የይዞታ መብት ትርጉምና የይዞታ አይነቶች…………………………………………..30

2.1.2. የገጠር መሬት የይዞታ መብት የሚገኝባቸው መንገዶች………………………………32

2.2. በገጠር መሬት የመጠቀም መብት……………………………………………………..36

2.3 የገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብት የሚታጣባቸው /ቀሪ

የሚሆንባቸውሁኔታዎች…………………………………………………………………..36

2.3.1 በሕግ…………………………………………………………………………36
2.3.2 በባለይዞታው ፈቃድ……………………………………………………………39

1
2.4. የገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብቶች የሚተላለፉባቸው መንገዶች………….41

2.4.1. ውርስ………………………………………………………………………………..41

2.4.2. ስጦታ………………………………………………………………………………..45
2.4.3. ኪራይ………………………………………………………………………………..47
2.4.4. የመጠቀም መብትን በዋስትና ማስያዝ………………………………………………50
2.4.5. የይዞታ መሬትን ስለመለዋወጥ………………………………………………………51
2.4.6. የመሬት ሽግሽግ………………………………………………………………………52
2.4.7. አግባብ ያልሆነ የመሬት ማስተላለፍ………………………………………………….54
2.5. የገጠር መሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ እና ማስተላለፊያ ፎርማሊቲ………………..57

የመወያያ ጥያቄዎች…………………………………………………………………………..60

ምዕራፍ ሶስት፡ የገጠር መሬትን በመጠቀምና በማስተዳደር ረገድ ስለተጣሉ ግዴታዎችና


ኃላፊነቶች……………………………………………………………………………………62

3.1 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች………………………………………………..62

3.2 ግዴታን አለመፈፀም በባለይዞታው ላይ ስለሚያስከትለው ኃላፊነት……………………..64

3.3. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች……….66

የመወያያ ጥያቄዎች…………………………………………………………………….69

ምዕራፍ አራት፡ የገጠር መሬት ይዞታን ለሕዝብ አገልግሎት ስለማስለቀቅና ስለካሳ

አከፋፈል……………………………………………………………………71

4.1. የህዝብ ጥቅም እና የካሳ ፅንሰ-ሀሳብ………………………………………………72

4.2. ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የገጠር መሬት ይዞታ በሚለቀቅበት ጊዜ የባለይዞታውና


የባለስልጣን መ/ቤቱ ስለሚኖራቸው መብትና ግዴታ……………………………..74

4.2.1. የባለይዞታዎች መብትና ግዴታ………………………………………………..74

4.2.2. የባለስልጣን መ/ቤቱ መብትና ግዴታ…………………………………………75

2
4.3. የገጠር መሬት የካሣ አከፋፈል ስሌት……………………………………………..76

4.4. ካሣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች ስለሚፈቱበት ስርዓትና የሚስተዋሉ


ችግሮች…………………………………………………………………………….78

4.4.1. ክርክሮች ስለሚፈቱበት ስርዓት………………………………………………..78

4.4.2. የሚስተዋሉ ችግሮች…………………………………………………………..78


የመወያያ ጥያቄዎች………………………………………………………………………80

ምዕራፍ አምስት፡ የገጠር መሬት ይዞታ መብት መከበር ዋስትና እና ክርክሮች የሚፈቱበት
አግባብ………………………………………………………………….......81

5.1. ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ ክርክሮች አፈታትና አወሳሰን…………………………82

5.2. በፍ/ቤት ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች……………………………………………..85


5.3. የመሬት ክርክር አፈታት ሥርዓትና ችግርቹ ………………………………………...87
የመወያያ ጥያቄዎች ……………………………………………………………………89

ክፍል ሁለት፡ የከተማ መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈጻጸማቸው…………..90

ምዕራፍ አንድ፡ የከተማ መሬትና ሕገ-መንግስቱ……………………………………………..91

1.1 የከተማ መሬት አጠቃቀም ታሪካዊ አመጣጥ ቅድመ 1987 ዓ.ም /የኢፌዴሪ ሕገ-
መንግስት ከመውጣቱ በፊት/…………………………………………………………..91

1.2 የከተማ መሬት የማግኘት መብት እና የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት……………………...94


1.3 የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የሚያገለግል ሕግ የማውጣት ስልጣንና የወጡ ህጎች…96

የመወያያ ጥያቄዎች………………………………………………………………………99

ምዕራፍ ሁለት፡ የከተማ መሬት በሊዝ የማግኘት፣ የማስተላለፍ መብት እና ይዞታ

የሚታጣባቸው ምክንያቶች………………………………………………..100

2.1 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለማግኘት………………………………………………………..101

3
2.1.1 የመተላለፊያ መንገዶች………………………………………………………………101

2.1.2. የሊዝ ውል አመሠራረት፣ የሊዝ ተመንና የሊዝ ዘመን…………………………….103

2.2. የሊዝ ተዋዋይ ወገኖች መብቶችና ግዴታዎች ……………………………………….105

2.2.1. የሊዝ ውል ሰጭ መብቶችና ግዴታዎች…………………………………………….106

2.2.2. የሊዝ ውል ተቀባይ መብቶችና ግዴታዎች………………………………………….107

2.3. የሊዝ መብትን ማስተላለፍ እና በዋስትና ማስያዝ ……………………………………108

2.4. የሊዝ ይዞታ የሚታጣባቸው ምክንያቶች እና ይዞታን የማጣት ውጤቶች……………110

2.4.1. ቦታውን ለተፈቀደለት አላማ አለማዋል፣ በጊዜ ገደቡ አለመገንባት………………….111

2.4.2. መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ለሌላ አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን……………….112


2.4.3. የሊዝ ይዞታ ዘመኑ አብቅቶ ሳይታደስ ሲቀር………………………………………….113
የመወያያ ጥያቄዎች……………………………………………………………………113
ምዕራፍ ሶስት፡ የከተማ ቦታን አስመልክቶ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸው
መንገዶች…………………………………………………………………..114
3.1. አግባብ ያለው አካል……………………………………………………………………..114
3.2. ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ……………………………………………………………………..116
3.3. የከተማ ነክ እና መደበኛ ፍ/ቤቶች……………………………………………………...116

የመወያያ ጥያቄዎች………………………………………………………………………….118

ማጠቃለያ…………………………………………………………………………………….119

የስልጠና ፕሮግራም አባሪ……………………………………………………………………121

ዋቢ መጽሐፍት እና ሕጎች…………………………………………………………………..122

4
መግቢያ

መሬት በተፈጥሮ የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑም በላይ ሌሎች የሚንቀሳቀሱና


የማይንቀሳቀሱ ንበረቶችን ለማፍራት አስፈላጊ የሆነ መተኪያ የሌለዉ ሀብት ነው፡፡ በአገራችን
የመሬት ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዘውዳዊው ስርዓት ጋር
ከፍተኛ ትግል በማድረግ የጭሰኛና የባላባት ግንኝነት ለዘለቄታው በማሰቀረት መሬት
የመንግስትና የሕዝብ ሀብት እንዲሆን አድርገዋል፡፡

ደርግም የከተማና የገጠር መሬትን የመንግስት እና የህዝብ ሀብት በማድረግ ሥር ነቀል


እርምጃ በመውሰድ የሰፊውን አርሶ አደርና የከተማ ኗሪ የመሬት ባለይዞታነትና ተጠቃሚነት
ፍትሀዊና ዋስትና ባለው ሁኔታ ለማረጋገጥ የሞከረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ውጤታማ
አልነበረም፡፡ ከደርግ ወድቅት ቀጥሎ የተቋቋመው የሽግግር መንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብት
የህዝብና የመንግስት መሆኑ እንደሚቀጥልና አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮችና አርብቶ
አደሮች ህጋዊ ዋስትና ያለው የመሬት ይዞታና የመሬት ተጠቃሚነት መብት የሚኖራቸዉ
መሆኑን ግልፅ በማድረግ በአንዳንድ አካባቢዎች ፍትሀዊ የመሬት ድልድል በማድርግ
እርምጃዎችን ወስዷል፡፡

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሬት የመንግስት አና የህዝብ ሀብት ሆኖ ግለሰቦች የከተማም ሆነ


የገጠር መሬት ባለይዞታና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ህገ መንግሰታዊ ስርዓት የዘረጋ በመሆኑ
የፌደራል እና የክልል መንግስታት በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ሀላፊነት
ለመወጣት የተለያዩ የህግ ማዕቀፎቸን በማውጣትና አስፈፃሚ አካላትን በማደራጀት በተግባራዊ
ሂደት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በመቀመር የህግ ማዕቀፎቹን የተሟሉና ችግር ፈች
ለማድረግ ህጎቹን በማሻሻል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም የፍትህ አካላት ባለሙያዎችም ህጎቹን በማስፈጸም ረገድ ቀላል የማይባል ሚና


ያላቸው በመሆኑ በገጠርና በከተማ መሬት ህግ አፈጻጸም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ ይህ
የስልጠና ሞጁል በሁለት ክፍል ተከፍሎ ተዘጋጅቷል፡፡ የመጀመሪያው ክፍል የገጠር መሬትን
የሚመለከቱ ህጎችና አፈፃፀማቸውን የሚመለከት ሲሆን ክፍል ሁለት ደግሞ የከተማ መሬትን
የሚመለከቱ ሕጎችንና አፈፃፀማቸውን ይዳስሳል፡፡

ይህ ፅሁፍ በገጠር እና በከተማ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም በኩል የሚታዩ ችግሮችን፣


የችግሮቹን መንስኤና የመፍትሄ ሀሳቦ ች ን በተሟላ ሁኔታ ለመዘርዘር ታስቦ የተዘጋጀ

5
አይደለም፡፡ የፍርድ ውሳኔዎችንም በበቂ ሁኔታ ይዟል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በተለይ የገጠር
መሬትን በተመለከተ ክልሎች የእየራሳቸው የህግ ማዕቀፍ ያላቸው በመሆኑ ፅሁፉ የሚዳስሰው
መሰረታዊ ነገሮችን ብቻ እንጅ ስለእያንዳንዱ ክልል ህግ በጥልቀት ይተንተን ቢባል ከጊዜ
አንፃርም ሆነ ከማቴሪያል አጥረት የማይቻል ነው፡፡ በመሆኑም የፅሁፍ ዓላማ ለውይይት መነሻ
የሚሆኑ መሠረታዊ ነጥቦችን በማቅረብ ሠልጣኞች በየአካባቢያቸው ያለውን ችግር፣ የችግሩን
መንስኤና ችግሩ ሊፈታ ስለሚችሉበት ሁኔታ ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ተለዋውጠው የጋራ
ግንዛቤ እንዲይዙ ለማነሳሳት መሆኑን በመገንዘብ ሠልጣኞች ንቁ ተሣትፎ በማድረግ ፅሁፉን
ለማዳበር ለማሻሻልና ለማስተካከል የሚረዳ ተሞክሮችን እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡ የስልጠና
ማንዋሉ በዋናነት የተዘጋጀው ለረዥም ጊዜ የስራ ላይ ሰልጣኞች በመሆኑ እና ሰልጣኞቹም
በስራው አለም ረዘም ላለ ጊዜ የሰሩ ስለሚሆኑ በውይይታቸው በእየአካባቢያቸው የሚነሱ
የፍርድ ጉዳዮችን እንዲያነሱ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም ጽሑፉ የተዘገጀው ለመነሻ ያክል በመሆኑ
ሰልጣኞች የክልላቸውን ህግና ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲወያዩ እና የበለጠ
እንዲያዳብሩት እጋብዛለሁ፡፡1

በሪሁን አዱኛ(LL.B, LL.M) የፅሑፉ አዘጋጅ ቀደም ሲል በአማራ ክልል የፍትህ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ እና
1

የህግ ምርምር ኢኒስትቲዩት አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የምዕራብ ጎጃም
ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ ነው፡፡

6
ክፍል አንድ
የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ሕጎችና አፈጻጸማቸው

በክፍል አንድ የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈፃፀማቸውን የምንመለከት ሲሆን በስሩ
አምስት ምዕራፎችን ይዟል፡፡ ምዕራፍ አንድ የገጠር መሬት ስሪት በኢትዮጵያ የነበረውን
ታሪካዊ ዳራና አሁን ያለውን ህገመንግስታዊ ይዘት ይዳስሳል፡፡ በምዕራፍ ሁለት የገጠር
መሬትን የማግኘት፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብቶች በክልል የሕግ ማዕቀፎች
እንመለከታለን፡፡ በምዕራፍ ሶስት የገጠር መሬትን በመጠቀምና በማስተዳደር ረገድ
በባለይዞታዎች እና በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን ላይ ስለተጣሉ ግዴታዎችና
ኃላፊነቶች እንዳስሳለን፡፡ በምዕራፍ አራት ደግሞ የገጠር መሬት ይዞታን ለሕዝብ አገልግሎት
ስለማስለቀቅና ስለካሳ አከፋፈል እናያለን፡፡ በመጨረሻም ምዕራፍ አምስት የመሬት ይዞታ
መብት መከበር ዋስትና እና ክርክሮች የሚፈቱበትን አግባብ እና የሚታዩትን ችግሮችና
መፍትሔዎችን እንቃኛለን፡፡

7
ምዕራፍ አንድ
የገጠር መሬት ስሪት በኢትዮጵያ

በአንድ ሀገር ያለው የመሬት ስሪት ዓይነት የመሬት ባለይዞታዎችን መብት በማስፋትም ሆነ
በማጥበብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ለንብረት መብት ዋናው
መሠረት መሬት በሆነባቸውና አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በባህላዊ የግብርና ስራ
በሚተዳደርባቸው ሀገሮች የመሬት ስሪቱ የመሬት ባለይዞታዎችን የንብረት መብትም ሆነ
የእያንዳንዱን ባለይዞታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ በመወሰን ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ
ይኖረዋል፡፡

ስለሆነም የመሬት ባለይዞታነት፣ የመሬት ስሪትና የመሬት ባለይዞታነትና አጠቃቀምን


በተመለከተ በተለያየ ጊዜ አገሪቱ ስትከተለው የነበረውን መሠረታዊ የፖሊሲ ሀሳብና አሠራር
ለመረዳት ይቻል ዘንድ የዘውዳዊ እና የደርግ ስርዓተ መንግስታት ይከተሉት የነበረውን
የፖሊሲ ሀሳብና ተግባራዊ ያደርጉት የነበረውን አሠራር የኢፌዲሪ መንግስት እየተከተለው
ካለው የፖሊሲ ሃሳብና አሰራር ጋር በማነፃፀር በአጭሩ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች

ሰልጣኞች የዚህን ምዕራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-

 በዘውዳዊ ስርዓት ስለነበረው የመሬት ስሪትና አጠቃቀም እንዲሁም ስለአስከተላቸው


ችግሮች ማብራራት ይችላሉ፡፡

 በደርግ ስርዓት ስለነበረው የመሬት ስሪትና አጠቃቀም እንዲሁም ስለአስከተላቸው


ችግሮች እውቅና ይኖራቸዋል፡፡

 የገጠር መሬት ስሪትን በተመለከተ የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት የወሰደውን አቋም


ማብራራት ይችላሉ፡፡

 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን የሚመለከት ሕግ የማውጣት ስልጣን


የተሰጠውን አካል ለይተው ያውቃሉ፡፡

8
 የፌዴራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ አስገዳጅና ፈቃጅ
ድንጋጌዎች በክልሎች ላይ ያለውን የተፈፃሚነት ወሰን ያውቃሉ፡፡

1.1 የቅድመ 1967 ዓ.ም የገጠር መሬት ስሪት (በዘውዳዊ ስርዓት)

Land tenure is the relationship, whether legally or customarily defined,


among people, as individuals or groups, with respect to land. (For
convenience, “land” is used here to include other natural resources such as
water and trees.) Land tenure is an institution, i.e. rules invented by societies
to regulate behaviour. Rules of tenure define how property rights to land are
to be allocated within societies. They define how access is granted to rights to
use, control, and transfer land, as well as associated responsibilities and
restraints. In simple terms, land tenure systems determine who can use what
resources for how long, and under what conditions.2

በቀላሉ ለመረዳት የመሬት ስሪት (Land Tenure) ማለት አርሶ አደሮችና ሌሎች የመሬት
ተጠቃሚዎች መሬት የሚይዙበትን ሁኔታና የአጠቃቀሙን ስርዓት የሚገልጽ ጽንሰ ሀሳብ
3
ነው፡፡ ይህ ትርጉም የመሬት ስሪት መሬት ከማግኘት መብት የሰፋና የመብቱን ደረጃም ሆነ
መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ተቋማትን የሚያካትት መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡
ስለዚህም በአንድ ሀገር ያለው የመሬት ስሪት ግንኙነት በመሬት መጠቀምን በተመለከተ አንድ
ሰው ከሌላው ሰው ጋር እንዲሁም ግለሰቦች ከመንግስት ጋር ያላቸውን ማህበራዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የሚገለፅበት ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡

በተለያዩ ሀገሮችና በተለያዩ ጊዜያት የሚኖሩት የመሬት ስሪት ግንኙነቶች ሊያመሳስሏቸው


የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ ቢችሉም በጣም በርካታ የየራሳቸው የጎሉ አካባቢያዊ ልዩ ታሪኮች

2
What is Land Tenure available at www.fao.org/DOCREP/005/Y4307E/y4307e05.htm (Date of Use 23 February
2012)

3
Kenneth H. Parsons, Land Tenure, the University of Wisconsin press, Wisconsin (1963) P. 44

9
አሉአቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የቅደመ 1967 ዓ.ም ኢትዮጵያ የገጠር መሬት ስሪትም የራሱ
የሆነ ባህሪይ የነበረውና በውስጡ በርካታ ስሪቶችን ያካተተ ነበር፡፡4

የኢትዮጵያን የገጠር መሬት ስሪት እጅግ ሩቅ ወደ ሆነው ዘመን ወደ ኋላ ሄዶ ለማጥናት


በተበታተነ የመንግስት አሠራርና በየአካባቢው ባህል ላይ በመመስረቱና በመብዛቱ ምክንያት
በዚህ ፅሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የማዕከላዊ መንግስት
አሠራር እየተጠናከረ ከመጣበት ከ17ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ያለውን ስሪት ነው፡፡ ከዚህ ዘመን
ጀምሮ ከነገስታት ነገስታት ለውጦች እየተደረጉበትና የተለያዩ ገጽታዎች እየታየበት የመጣው
የገጠር መሬት ስሪት የጋራ ይዞታ፣ የግል ይዞታና የመንግስት ይዞታ በሚል ሊከፈል
ይችላል፡፡5 በእነዚህ ስሪቶች ስር ሊካተቱ የሚችሉ የመሬት ይዞታና አጠቃቀም አይነቶች ደግሞ
በርካታ ነበሩ፡፡ እነዚህም ለምሳሌ፡- የቤተክርስቲያን ይዞታ፣ የጉልት ይዞታ፣ የርስት ጉልት
ይዞታን የሚያካትቱ ናቸው፡፡ እነዚህ የመሬት ስሪት ዓይነቶች ከተመሠረቱበት ዘመንም ሆነ
ለባለይዞታዎች ከሚሰጡት መብት አንፃር የተለያዩ ቢሆኑም ቢያንስ ስሪቱን ከመወሰን አንፃር
በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የመንግስታት ወሳኝነት ወይም ተፅዕኖ የነበረበት መሆኑ ግን
የሚያመሳስላቸው ባህሪይ ነው፡፡

የወል(ርስት) ይዞታ የሚባለው በሰሜኑና በመካከለኛው ኢትዮጵያ በከፊል የነበረ የመሬት ስሪት
ሲሆን የሚገለጸውም የርስት ይዞታ በሚል ነው፡፡6 የዚህ ስሪት መለያ ባህሪው ዘራቸውን ወደ
ላይ ቆጥረው የስሪቱ ቆርቋሪ ሰው የጋራ ተወላጆች መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ሰዎች የጋራ
ይዞታ መሆኑ ነው፡፡ የርስት ይዞታ መሬትን በተመለከተ አንዳንድ ፀሐፊዎች ይዞታው ከአንድ
ሰው ወደ ሌላ ሊተላለፍ የሚችል ነው7 ሲሉ ሌሎች ፀሐፊዎች ደግሞ የማይተላለፍ ነው8
ይላሉ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ፀሐፊዎች ትኩረታቸው ስለሚለያይ ነው እንጅ ሁለቱም ልክ ናቸው፡፡
ምክንያቱም የርስት ይዞታ መሬት የወል ባለይዞታ በሆኑት ርስተኞች መካከል መሬቱ ያለምንም

4
Aberra Jembere, Legal History of Ethiopia 1434-1974: Some Aspects of Substantive and Procedural Law, Lieden
Arika-studie centrum (1998) P. 123
5
Ibid
6
የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈጻጸም በፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕከልለ ረጅም ጊዜ ስራ
ላይ ስልጠና ፕሮግራም የተዘጋጀ (ያልታተመ)፣ገፅ 8
7
Richard David Green Field, Ethiopia, A New Political History, Pallmale press, London (1965) P.323
8
Abera Jembere cited at note 2

10
ገደብ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ይሁን እንጅ የርስት ይዞታ የርስተኞቹ
የጋራ ይዞታ በመሆኑ ከርስተኞቹ ውጭ ለሆነ ሰው ግን ሊተላለፍ አይችልም፡፡

የርስት ስሪት ሰዎችን በአንድ አካባቢ የሚገኝ መሬት የጋራ ግለ ይዞታ የሚያደርገው የዘር
ሀረግን ከአንድ የጋራ አባት ግንድ መሆን በመቁጠር በመሆኑ በአንድ በኩል በቁጥጥር
ዝምድናም መካከል ቤተሰባዊ ግንኙነትን ስለሚያጠናክር ለህ/ሰቡ ሰላማዊ ኑሮ መሠረት
የመሆን ከፍተኛ ማህበራዊ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ በሌላ በኩል ግን ከተለያየ የቤተሰብ ግንድ
በሚወለዱ ሰዎች መካከል ርስቱ የእኔ አባት ያቀናው እንጅ የእናንተ አባት ያቀናው አይደለም
ስለዚህም የርስተኝነት መብቱም የእኛ ነው በሚሉ የተለያዩ ቤተሰቦች መካከል ረጅም ዘመን
የሚፈጅ ክርክሮች ምክንያት የነበረና አንዳንድ ጊዜም በዚህ ዓይነት ቤተሰቦች መካከል
መጋደልን በማስከተል ከፍተኛ ጠላትነትን ሲፈጥር የነበረ ስሪት መሆኑ በታሪክ ይነገራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የዘራቸውን ጥንታዊ አባት ቆጥረው ከአቅኝው ርስተኛ አባት ጋር በዝምድና
መገናኘት የማይችሉ ሰዎችም የመሬት ባለይዞታነት መብት አያገኙም፡፡ ይህ በመሆኑ ደግሞ
የመሬት ይዞታ መብት ማግኘት የማይችሉ የህብረተሰብ ከፍሎች ሁሉ የርስተኞች የመሬት
ተጠማኝ ከመሆናቸውም ሌላ የሰዎች ማንነት የሚገለፀው ከርስተኝነት ጋር ተያይዞ ስለነበር
በህ/ሰቡ ውስጥ በዝቅተኛ ደረጃ እንዲታዩ አድርጓቸው ነበር፡፡

የጉልት ይዞታ ለተፈፀመ ውለታ ለመንግስት ባለመሬቶች የሚከፍሉትን ግብር ተቀብሎ ለግል
ለመጠቀም እንዲቻል የሚሰጥ መብት ነው፡፡ ባለፈው ለተፈፀመና ወደ ፊትም ሊፈፀም የሚችል
የአንድን አካባቢ የማስተዳደርና ፀጥታ የማስከበር ተግባር ለሚፈጽም ሰው በግል የሚሰጥ
“የመሬት ይዞታ” መብት በመሆኑ ለልጅ የሚተላለፍ ይዞታ አይደለም፡፡ መንግስት ከፈለገ
ጉልተኛው ተግባሩን አልተወጣም ብሎ ሲያምን መልሶ ሊወስደው ይችላል፡፡ ይህ ይዞታ ከርስት
ይዞታ ጋር ትስስር ስለሌለው የርስት ስሪት በሌላቸው የሀገሪቱ ክፍሎችም የነበረ ይዞታ ነው፡፡9

የርስት ጉልት ይዞታ ደግሞ በርስት ስሪት አካባቢዎች ከርስት ይዞታ በተጨማሪ በግል ይዞታ
አካባቢ ደግሞ ከግል ባለቤትነት በተጨማሪ ከመሬቱ የሚሰበሰበውን ግብር ሰብስቦ ለግል
ለመጠቀም ከመንግስት የሚሰጥ መብት ሲሆን መብቱ የሚሰጠውም ለመንግስት ለተሰጠ
አገልግሎት ነው፡፡ በመሬቱ ላይ ካሉ የርስተኝነት ይዞታ ወይም ከግል ባለቤትነት በተደራቢነት

9
Aberra Jembere cited at note 2, P.141

11
የሚሰጥ በመሆኑም መልሶ ሊወሰድ የማይችልና ለተወላጅ ሁሉ በማንኛውም ሁኔታ ሊተላለፍ
የሚችል ይዞታ ነው፡፡10

የግል የመሬት ስሪት በአብዛኛው በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረ ሲሆን ለእያንዳንዱ ባለይዞታ
ሙሉ የመሬት ባለቤትነት መብት የሚሰጥ ስሪት ነበር፡፡ በመንግስት በግዴታ የተጣለ ስሪት
ስለነበርም ስሪቱ ለሁሉም ዜጎች መሬት በግል ባለቤትነት የመያዝ መብት የሚሰጥ ቢመስልም
የተወሰኑ ለመንግስት ልዩ ቅርበት የነበራቸው ግለሰቦች ብቻ መሬቱን ሰብስበው ይዘው
አብዛኛውን ህዝብ ግን መሬት አልባና የመሬት ተጠማኝ ያደረጉበት ስርዓት ነበር፡፡ የግል
የመሬት ስሪት የግል ባለቤትነት መብት ያለበት ስሪት በመሆኑም መሬቱ በባለቤቱ ውሳኔ ሊሸጥ
ወይም በሌላ ሁኔታ ለማንኛውም ሰው ሊተላለፍ የሚችልበት የይዞታ ዓይነት ነበር፡፡11

የመንግስት ይዞታ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የነበረ ስሪት ሲሆን መሬቱን መንግስት
ለሚፈልገው የራሱ ተግባር የሚያውልበት አለዚያም ለባለሟሎቹ እንደማደሪያ የሚሰጥበት
ወይም ለመንግስት ለሚገብር ተጠማኝ የሚሰጥበት የይዞታ ዓይነት ነበር፡፡12

ለማጠቃለል በዘውዳዊ ስርዓት የነበረው የመሬት ስሪት ለአርሶ አደሩ የመሬት ባለቤትነትም ሆነ
የመሬት ባለይዞታነትና ተጠቃሚነት ምንም ዓይነት ዋስትና የማይሰጥ የሀገሪቱን የእርሻ መሬት
በእጣት ለሚቆጠሩ ሰዎች ባለቤትነትና አዛዥነት ስር ያደረገና ሰፊውን አርሶ አደር ለጭሰኝነት
እና ለባርነት የዳረገ እንደነበር ይህም በ1966 ዓ.ም ለተደረገው ህዝባዊ ቁጣና አብዮት
መሠረታዊ ምክንያት የነበረ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

1.2 የገጠር መሬት ስሪት በደርግ ስርዓት


በ1967 ዓ.ም የተደረገው የመሬት ስሪት ለውጥ በ1966 ዓ.ም የተካሄደው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ
በሀገሪቱ ያስከተለው አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ውጤት አካል ነበር፡፡ ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን
ተከትሎ የደርግ መንግስት የዘውድ አገዛዙን ተክቶ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የሀገሪቱ
የፓለቲካ ስርዓት ሶሻሊስታዊ ርዕዮተ ዓለምን እየተከተለ በመምጣቱ የኢኮኖሚ ስርዓቱም አብሮ
በመለወጡ የመሬት ስሪት ለውጥ እንዲከተል አደርጓል፡፡ የገጠር መሬት ስሪት ለውጡ በህግ

10
Ibid.
ማህተመሥላሴ ወ/መስቀል ስለ ኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ግብር ጠቅላላ አስተያየት (1970,
11

ያልታተመ) ገጽ 14
12
Desalegn Rahmatto, Agrarian Reform in Ethiopia, Scandinivian Institute of African Studies, uppsala (1984) P. 20

12
ሲታወጅም በመጀመሪያ አጽንኦት የሰጠው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በእርሻ የሚተዳደሩ ሀገሮች
አንድ ሰው በህ/ሰቡ ውስጥ ሊኖረው የሚችለው የኑሮ ደረጃ፣ መብት፣ እንዲሁም ክብርና
ማዕረግ የሚወሰነው ከመሬት ጋር ባለው ግኑኝነት በመሆኑ የዜጎችን እኩልነት ለማስከበር
የመሬት ስሪቱን መለወጥ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡13

የፓለቲካ ስርአቱየሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም ተከታይ በመሆኑም መሬትን የመሳሰሉ ሀብት


ማፍሪያዎች የግል ባለቤትነት መብት በስርዓቱ ተቀባይነት ስለማይኖረው የመሬት ስሪቱ
በሀገሪቱ አንድ ወጥ ሆኖ “የሕዝብ ይዞታ” ተብሎ ታወጀ፡፡14 የመሬት ስሪቱ የህዝብ ይዞታ
እንዲሆን በመታወጁ መሬት ሊሸጥ ሊለወጥ የማይችል የህዝብ ሀብት እንዲሆን ተደረገ፡፡
ስለዚህም በርስት፣ በግል ወይም በመንግስት ይዞታ ስር የነበረው የገጠር መሬት ሁሉ የህዝብ
ይዞታ በመደረጉ ማንኛውም በእርሻ ለመተዳደር የሚፈልግ ሰው መሬት የማግኘት እኩል
መብት እንዳለው ህጉ ደነገገ፡፡

ይሁን እንጅ የመሬት ስሪቱ መሠረታዊ መርህ በዚህ መልኩ የታወጀ ቢሆንም አንድ አርሶ
አደር በመሬት ላይ ያለው የመጠቀም መብት ግን እንዲሁ ከላይ ስናየው ከሚመስለው እጅግ
የጠበበ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የመሬት መብት ውሱንነት የሚታየው የይዞታ መሬትን በሽያጭ፣
በለውጥ፣ በማውረስ፣ በማስያዝ፣ በወለድ አገድ፤ በስጦታ ወይም በሌላ መንገድ ማስተላለፍ
በመከልከሉ ነው፡፡15 ባለይዞታው ሲሞት/ስትሞት ብቻ የትዳር ጓደኛው ወይም አካለ መጠን
ያላደረሰ ልጅ እነዚህ ከሌሉ ደግሞ አካለ መጠን ያደረሰ ልጅ ተተክቶ በመሬቱ የመጠቀም
መብት እንደሚኖረው በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 5 ተደንግጓል፡፡ በዚህ ክልከላ ምክንያትም የመሬት
ባለይዞታ ያለው መብት ከአንድ የመሬት ተከራይ ያላለፈ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ሁለተኛው ውስንነት ማከራየትን ጨምሮ በሌላ ሁኔታ የመሬት ይዞታ መብትን መገልገልንም
መከልከሉ ነው፡፡ አዋጁ ከዚህ ጋር ተያይዞ በእርጅና ወይም በህመም ወይም አካለ መጠን
ባለማድረስ ወይም ለሴቶች ካልሆነ በቀር በይዞታ መሬት ላይ ሌላ ሰው ቀጥሮ ማሳረስም16

የገጠር መሬትን የህዝብ ሀብት ለማድረግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 31/67 መግቢያ
13

ዝኒከማሁ አንቀጽ3(1)
14

ዝኒከማሁ አንቀጽ 5
15

ዝኒከማሁ አንቀጽ 4(1)


16

13
መከልከሉን ስንመለከት በሕግ የተሰጠውን መሬት የማግኘት እኩል መብት በተግባር ለመጠቀም
ያለውን የመብት ጠባብነትና አስቸጋሪነት እንረዳለን፡፡

በ1980 ዓ.ም የወጣው የኢሕድሪ ሕገ-መንግስትም የገጠር መሬት ስሪትን በተመለከተ ቀደም
ብሎ ከታወጀው ስሪት የተለየ ምንም ያስከተለው ለውጥ አልነበረም፡፡ ስለዚህም አዲሱ የገጠር
መሬት ስሪት በአንድ በኩል ለአብዛኛው የህ/ሰብ ክፍል መብት የሚነፍገውን ነባሩን የመሬት
ስሪት በማስወገድ መልካም ገጽታ ያለው ቢሆንም በሌላ በኩል ግን የመሬት ባለይዞታዎችን
መብት በማጥበቡና የመሬት አስተዳደሩንም በመንግስት አካላትና የፓለቲካ አመራሮች ስር
በማድረጉ ከንብረት መብት አንፃር ይህ ነው የሚባል ለአርሶ አደሮች ከድሮው የመሬት ስሪት
የተሻለ የመሬት የተጠቃሚነት ለውጥ ሳያስከትል ቀርቷል፡፡

1.3 የገጠር መሬት ስሪት በሽግግር ወቅት


የደርግን መንግስት በ1983 ዓ.ም ከስልጣን ያስወገደው ኢሕአዴግ እንደመታገያ ያነሳቸው
ከነበሩ ጥያቄዎች አንዱ የደርግ መንግስት የገጠር መሬት ጥያቄን በአግባቡ አልመለሰውም
የሚለው ነበር፡፡ በዚህና በተለይም በአርሶ አደሩ በነበረው የመሬት አስተዳደር መከፋት ምክንያት
ከመሬት ስሪት እስከ መሠረታዊ የመሬት አስተዳደር ለውጥ ከአዲሱ መንግስት የሚጠበቅ
ተግባር ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ቀደም ብሎ የነበረውን የሶሻሊስት ስርዓት ውጤት የሆነውን
አጠቃላይ የኢኮኖሚ ግንኙነት በተመለከተ ብዙም ሳይቆይ በአዲሱ መንግስት በግል ባለቤትነት
ላይ ወደተመሠረተው የገበያ ስርዓት ለውጥ የተደረገ ቢሆንም በገጠር መሬት ይዞታው ላይ ግን
ዝምታው አጭር ለማይባል ጊዜ ሰፍኖ ቆየ፡፡ ሐምሌ 15 ቀን 1983 ዓ.ም የወጣው የሽግግር
መንግስት መተዳደሪያ ቻርተርም አንዳንድ መሠረታዊ የፓለቲካ አቅጣጫዎችን ከመጠቆሙ
በስተቀር17 ቻርተሩ በሕገ-መንግስት እስኪተካ ድረስ የገጠር መሬት ስሪቱ በነበረበት በመቀጠሉና
የመሬት አስተዳደሩም የእለት ከእለት ችግሮችን በማቃለል ላይ ተወስኖ በመቆየቱ ስለመሬት
ስሪትም ሆነ የአስተዳደር ለውጥ ከሚወጣው አዲስ ሕገ-መንግስት ድንጋጌ ሲጠበቅ ቆይቷል፡፡

የሽግግሩ መንግስት ቻርተር ቁጥር 1/1983 አንቀጽ 10


17

14
1.4 የገጠር መሬት ስሪት በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት
የመሬት ይዞታ ጥያቄ በአጠቃላይ በተለይም የገጠር መሬት ይዞታ ቀደም ብሎ በተደጋጋሚ ሲነሳና

ሲያከራክር እንደነበረው ሁሉ የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት ከመውጣቱ በፊትም በየስብሰባዎችም


ሆነ በየግል ውይይቶች የመነጋገሪያ ነጥብ ሆኖ ነበር፡፡ የመሬት ስሪቱ ምን መሆን አለበት
የሚለው ነጥብ ላይም ያሣምናሉ የተባሉ ምክንያቶች እየተሠጡ የተለያዩ አቋሞችም ሲገለፁ
የቆዩ ቢሆንም ሕገ መንግስቱ ቀደም ብሎ በነበረው መንግስት ከነበረው በተለየ ሁኔታ የሀገሪቱ
የንብረት ባለቤትነት መብት ሥርዓት በግል ባለቤትነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በአጠቃላይ
ደንግጐ የገጠር መሬት ይዞታ መብትን በተመለከተ ግን የገጠር መሬት እና የተፈጥሮ ሀብት
የባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው ተብሎ ታወጇል፡፡18

የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(3) የገጠር መሬትን በተመለከተ የሚደነግገው ሁለት


መሠረታዊ ነጥቦችን ነው፡፡ እነዚህም አንደኛው የመሬት ባለቤትነት የመንግስትና የሕዝብ ነው
የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መሬት ሊሸጥ ሊለወጥ አይችልም የሚለው ነው፡፡ ሁለቱም
ነጥቦች ለገጠር መሬት ባለይዞታዎችና ተጠቃሚዎች መብት የሚሰጡ ሣይሆኑ በተጠቃሚዎች
መብት ላይ የተጣሉ ገደቦች ናቸው፡፡ በአጠቃላይም ሕገ መግስቱ የመረጠው በመሬት ላይ
የተፈቀዱ መብቶችን በሙሉ ዘርዝሮ በመደንገግ ፈንታ አንድ የንብረት ባለመብት ሊኖሩት
ከሚችሉት መብቶች መሬትን በተመለተ የተከለከሉትን በዝርዝር ማስቀመጥን ነው፡፡ ስለዚህ
በኢትዮጵያ የገጠር መሬት ሥሪት መሠረት አንድ የመሬት ተጠቃሚ ከአንድ የንብረት ባለቤት
ከሚኖረው መብት በተለየ የከለከለው መሸጥና መለወጥን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ
ሕገ-መንግስቱ የይዞታ ወይም የመጠቀም መብትን በሌላ ሁኔታ ማስተላለፍን ፈፅሞ መከልከለ
አለመፈለጉን የሚያሣይ ነው፡፡ የመሬት ይዞታ ወይም የመጠቀም መብት ሊተላለፍ የሚችለው
ደግሞ በሽያጭና በልውውጥ ብቻ ሣይሆን በኪራይ፤ በስጦታ ወይም በውርስ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለዚህም የማስፈፀሚያ የበታች ህጐች ይህን ጥያቄ እንዴት እንደመለሱት ወደፊት የምናየው
ይሆናል፡፡

የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 4ዐ(1) ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብት እንዳለው
18

ሲደነገግ የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ግን ከንዑስ አንቀጽ 1 በተለየ ሁኔታ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት
ባለቤትነት መብት የመንግስትና የሕዝብ ብቻ መሆኑን ደንግጓል፡፡

15
በሌላ አገላለፅ የገጠር መሬት ሥሪት የመሬት ባለቤትነቱ የመንግስትና የህዝብ መሆኑንና አርሶ
አደሮች19 ከሚያገኙት መሬት ያለመነቀል መብት እንዳላቸው መደንገጉ የሚያስገነዝበው
በመሬት ላይ የሚኖረው መብት የይዞታ መብት መሆኑን ነው፡፡ የመሬት የይዞታ መብት ደግሞ
በይዞታ መብቱ ላይ ተመሥርቶ ከሚገኘው የመጠቀም መብት የተለየ ነው፡፡ ይህን ሥንልም
የባለቤትነት መብት፣ የይዞታ መብትና የመጠቀም መብት የተለያዩና ከመጀመሪያው ወደ
መጨረሻው ቅደም ተከተል እየጠበቡ የሚመጡ መብቶች ናቸው ማለታችን ነው፡፡ ምክንያቱም
የባለቤትነት መብት መሸጥን ጨምሮ ማንኛውንም በንብረት ላይ ሊኖር የሚችል መብት ሁሉ
የሚያካትት ከመብቶች ሁሉ የሰፋ መብት ሲሆን የይዞታ መብት ደግሞ በኢፌዲሪ ሕገ
መንግስት መሠረት የገጠር መሬትን በተመለከተ አንድ የመሬት ባለቤት ሊኖረው ከሚችለው
መብት ላይ በመሸጥ ወይም በመለዋወጥ መሬትን ለሌላ ማሥተላለፍን ብቻ ለይቶ በመከልከል
ሌሎችን መብቶች ግን የጠበቀ መብት ነው፡፡ የመጠቀም መብት ደግሞ አንድ የገጠር መሬት
የይዞታ መብት ያለው ሰው በመሬቱ የመጠቀም መብቱን ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ የተላለፈለት
ሰው የሚኖረው መብት ነው፡፡20 ስለዚህም የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው የይዞታ መብቱን
እንደጠበቀ ሆኖ የመጠቀም መብቱን ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን መብቱ ለተላለፈለት ሰው
የሚሠጠው መብት በመሬቱ የመገልገል መብት ብቻ ነው፡፡

1.4.1 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የማውጣት ሥልጣን

የብሔራዊ ፓሊሲ መርሆዎችና ዓላማዎች በተዘረዘሩበት የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት ክፍል


አንቀጽ 89(5) መሰረት መንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር
በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን እንደ
አንድ የኢኮኖሚ ነክ ዓላማ አስቀምጦታል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሀገራችን በምትከተለው
ፌደራላዊ ቅርፀ መንግስት መሠረት መሬትና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ
ሕግ የማውጣት ሥልጣን የፌደራል መንግስት ሥልጣን እንደሆነ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ
51(5) ላይ ተደንግጓል፡፡ የዚሁን ሕገ መንግስት አንቀጽ 52(2)(መ) ድንጋጌ ደግሞ ክልሎች
የፌደራሉ መንግስት የሚያወጣውን ሕግ መሠረት አድርገው መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን
የማሥተዳደር ሥልጣን እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡ በሌላ መልኩ የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 50(9)
የፌደራል መንግስቱ በዚሁ ሕገ መንግስት አንቀፅ 51 ከተሠጡት ሥልጣንና ተግባሮች መካከል

አርሶ አደሮች የሚለው አገላለፅ ከዚህ በኋላ ከፊል አርብቶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ያካትታል፡፡
19

ለምሳሌ በኪራይ ለተወሰነ ጊዜ ቢያስተላልፍ


20

16
እንደ አስፈላጊነቱ ለክልሎች በውክልና ሊሠጥ እንደሚችል ደንግጓል፡፡ ስለዚህ በሕገ መንግስቱ
አንቀጽ 51 ለፌደራል መንግስቱ ከተሠጡት ሥልጣንና ተግባሮች መካከል አንዱ የሆነው
መሬትና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ የማውጣት ሥልጣን በመሆኑ
ሕገ መንግስቱ የፌደራል መንግስቱ የአርሶ አደሮችን በነፃ መሬት የማግኘት፣ የመሬት ባለይዞታ
የመሆንና ከይዞታ ያለመነቀል መብትን ወጥ በሆነ ሁኔታ ለማረጋገጥ በሚችል የመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ እንዲያወጣና ክልሎች ደግሞ የፌዴራል መንግስት ያወጣውን ሕግ
መሠረት በማድረግ ሌሎች የሕግ ማዕቀፎችን በማውጣትና አስፈፃሚ አካላትን በማደራጀት
በክልላቸው ውስጥ ያለውን መሬት የማስተዳደር ስልጣን ያላቸው መሆኑን በግልጽና በማያሻማ
ቋንቋ ይደነግጋል፡፡

1.4.2 የፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ህግ

የፌደራሉ ሕገ መንግስት መሬትን በተመለከተ ስለ ስሪቱ፣ ስለመብቱ ወሠንና ስለአስተዳደሩ


በአጠቃላይ የደነገገውን ተፈፃሚ ለማድረግም በፌደራል ደረጃ ቀደም ሲል የነበረው አዋጅ ቁጥር
89/89ን እና እሱን በመሻር ታውጆ አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ ቁጥር 456/97 ወጥቷል፡፡
አዋጅ ቁጥር 89/89 የአርሶ አደሮችን የገጠር መሬት መብት በተመለከተ ብዙም ዝርዝር
ድንጋጌን ያላካተተና ክልሎች እንዲያወጡ ለሚጠበቀው ዝርዝር ህግም እንደመመሪያ ሆኖ
ለማገልገል ግልፅነት የጎደለው ህግ ነበር፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የሀገሪቱ የገጠር ልማት ፖሊሲና
ስትራቴጅ ከተነደፈ በኃላ ፖሊሲውንና ስትራቴጅውን በአግባቡ ሊያስተገብር በሚችል መልኩ
አዋጁን ማሻሻል በማስፈለጉ የገጠር መሬት አጠቃቀምን በተመለከተ የተሻሻለውን የፌደራል
አዋጅ ቁጥር 456/97 ወጥቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የፌደራል መንግስት በሚያከናውናቸው የመሠረተ ልማት ስራዎች


ምክንያት ከይዞታቸው ለሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች ካሣ አከፋፈል የሚደነግግ የህግ ማዕቀፍ
አዋጅ ቁጥር 455/99 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስችል ደንብ ቁጥር 135/99ን
በማውጣት ስራ ላይ አውሏል፡፡

አዋጅ ቁጥር 456/97 የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስትና ይህን መሠረት በማድረግ የወጡ የኢኮኖሚ
ልማት ፓሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ የወጣ ህግ ነው፡፡
ከአዋጁ መግቢያ መረዳት የሚቻለውም በርካታ የገጠር ልማት ዓላማዎችን የያዘ መሆኑን
ነው፡፡ እነዚህንም በአጭሩ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

17
1. ዘላቂ ልማት (Sustainable Development)
የገጠር መሬት አስተዳደርንና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 በመግቢያው ላይ በተለያዩ
የሀገሪቱ የስነ-ምህዳር ቀጠናዎች ላይ ተመስርቶ ዘላቂ ሀብቶችን በዘላቂ ሁኔታ በመጠቀምና
በልማት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ በማስፈለጉ ነው ሲል ይገልፃል፡፡ የዚህ አዋጅ
መግቢያ መሠረተ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃና ልማት ኮሚሽን “sustainable
development” ለሚለው ሐረግ ከሰጠው ትርጉም ማለትም “Development that meets the
needs of the present without compromising the ability of the future generation to meet
their own needs” ከሚለው ጋር የሚስማማ ከመሆኑም በላይ ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ
የአሁኑና የወደፊቱን ትውልድ ፍላጎት አጣጥሞ አሁን ያለውን ንፁህ ውሃ፣ አየር፣ አፈር፣
እፅዋት በአጠቃላይ በዓለማችን የሰው ልጅ በሕይወት ለመኖር አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች
በሚገባ ይዘን ስርዓት ባለው አስተዳደርና አጠቃቀም ተገልግለንባቸው ከትውልድ ትውልድ
የማስተላለፍ ግዴታ የአሁኑ ትውልድ ግዴታ መሆኑን መገንዘብ የሚጠይቅ ነው፡፡

በመሆኑም የዘላቂ ልማት ፅንሰ ሀሳብ ታሳቢ የሚያደርገውን የአሁኑ ትውልድ የልማት ፍላጎት
ሳይገታ ግን ደግሞ የመጪው ትውልድ የልማት ፍላጎት ሳይጎዳ ልማትን እንዲያፋጥን
ከተፈለገ ለዚህ ተስማሚ የሆነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግዴታችን መሆኑን ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር
456/97 ይህን የዘላቂ ልማት ፅንሰ ሀሳብ እንደ ዓላማ ይዞ ሲታወጅ አርሶ አደሩም ሆነ
ኢንቨስተሩ የተረጋገጠ ይዞታ (tenure security) እንዲያገኝ እና በተሰጠው መብት ተጠቅሞ
መሬትን ሲያለማ ሊከከተላቸው ስለሚገባ የመሬት አጠቃቀም ስርዓቶች የሚደነገግ በመሆኑ
በርካታ ፋይዳዎች ያሉት ነው፡፡

2. አርሶ አደሩ በመሬት ላይ ያለውን የንብረት መብት ማጠናከር

ከአዋጁ መግቢያ ለመረዳት እንደሚቻለው የንብረት መብት መነሻና መድረሻ በባህል ደንቦች
ወይም መንግስት በሚያወጣቸው ህጎች እንደሚወሰን ነው፡፡ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስትም ሆነ
በአዋጅ ቁጥር 456/97 መሠረት አርሶ አደሮች በመሬት ላይ የሚኖራቸው መብት የይዞታ
መብት ሲሆን በዚህ መሬት በሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ላይ ግን የባለቤትነት መብት
እንደሚኖራቸው ነው፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለውም በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት መሠረት መሬት
የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የህዝብ ንብረት መሆኑ በራሱ የመሬት ባለይዞታዎችን የልማት
ዋስትና እንዲያጡ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡ ለምን ቢባል በህገ-መንግስቱና ሌሎች ህጎች

18
ከባለቤትነት በመለስ በመሬቱ የመገልገልና የፍሬው ባለቤትነት እስከተረጋገጠላቸው ድረስ
እንዲሁም በይዞታ መብቱ ላይ ችግር ሲፈጠር የሚተዳደሩበት ህግ እስካላቸው ድረስ አርሶ
አደሩ በመሬት ላይ ያለውን የንብረት መብት የሚያጠናከር ነው የሚሆነው፡፡ የመብቱ
ማጠንጠኛና ዋና ሀሳብ ያለው እዚህ ላይ በመሆኑ የመሬት ስርዓቱ ፍትሐዊነት መመዘኛ
መሆን ያለበት መሬትን መሸጥ መፈቀዱና አለመፈቀዱ ሳይሆን ለህብረተሰቡ የሚሰጠው ጥቅም
ወይም የሚያስገኘው ፋይዳ መሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

3. የምግብ ዋስትና

አዋጅ ቁጥር 456/97 በአንቀፅ 2(10) ላይ አነስተኛ የይዞታ መጠን ማለት ምርታመነቱ የአንድ
አርሶ አደር ቤተሰብ የምግብ ዋስትና ሊያረጋግጥ የሚችል የገጠር መሬት ይዞታ ወይንም
ለሰብል እርሻ፣ ለቋሚ ሰብል፣ ለግጦሽ፣ ለመኖሪያ ቤትና ለጓሮ የሚበቃ የገጠር መሬት ይዞታ
መጠን መሆኑን ይገልፃል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘት እንደሚያሳየን አዋጅ ቁጥር 456/1997
የወጣው የኢትዮጵያ መንግስት በጽናት ይዞ እየሰራበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ
ስትራቴጅን ታሳቢ በማድረግ አርሶ አደሮች ያለባቸውን የመልካም አስተዳደር እጦት ደረጃ
በደረጃ እየፈቱ ተረጋግተው በልማት ስራ ላይ ጠንክረው በመስራትና ከድህነት በመላቀቅ የተሳካ
ኑሮ እንዲኖሩ የሚያደርግ የልማት ፖሊሲ ይዞ ነው፡፡

4. ሴቶች በመሬት ላይ ያላቸውን መብት ማረጋገጥ

እንደሚታወቀው ሴቶች አሁን ባለው የህዝብ ብዛት ቁጥራቸው ከግማሽ በላይ ቢሆንም እስቅርብ
ጊዜ በኢትዮጵያ ሴቶች የመሬት ባለይዞታነት መብት ተጠብቆላቸው የመብቱ ተጠቃሚ
አልነበሩም፡፡ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት በወጣበት ጊዜ ሴቶች የልማቱ ግማሽ ኃይል እንደሆኑ
በማመን እነዚህን የህብረተሰቡ ክፍሎች ለዓመታት ሲታገሉለት የቆየውን የመሬት ባላይዞታነት
መብት እውን ለማድረግ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 35(7) “ሴቶች ንብረት የማፍራት፣
የማስተዳደር፣ የመቆጣጠርና የማስተላለፍ መብት አላቸው፡፡ በተለይ መሬትን በመጠቀም፣
በማስተላለፍ፣ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት አላቸው፡፡
እንዲሁም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት አላቸው፡፡” በማለት ይደነግጋል፡፡
አዋጅ ቁጥር 456/97 ደግሞ የህገ-መንግስቱን የሴቶች የእኩልነት መርህን በመከተል በአንቀጽ
6(4) ለይ “መሬቱ የባልና ሚስት የጋራ ከሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በሁሉም የጋራ
ባለይዞታዎች ስም መዘጋጀት አለበት” ሲል ይደነግጋል፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች የምንረዳው

19
ሴቶች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን በተመለከተ ከወንዶች ጋር እኩል መብት እንዳላቸውና
በዚህ መብታቸው ተጠቅመው እንደ ወንዱ ባለይዞታ መሆንና በፍቺ ጊዜም ድርሻቸውን ይዘው
የመሄድ መብት እንዳላቸው ነው፡፡ ይህ ከአሁን ቀደም ይገጥማቸው የነበረውን የኢኮኖሚ
ተፅእኖ በማስቀረት ብዙሃኑን የሴት አርሶ አደሮች ጉልበት ለልማት በማዋል ዜጎች በየደረጃው
ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዘላቂና ፈጣን ልማት ተግባራዊ በማድረግ ሴቶች በየደረጃው ተጠቃሚ
እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡

5. ማህበራዊ ደህንነት ማረጋገጥ

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97 የዜጎችን
ማህበራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ በአንቀጽ 5(1) (ለ) ላይ ዕድሜአቸው ከ18 ዓመትና ከዚያ በላይ
የሆነና በግብርና ሙያ ሊተዳደር የሚፈልግ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በገጠር መሬት የመጠቀም
መብቱ የተረጋገጠ ሆኖ እናትና አባታቸውን በሞት ወይም በሌላ ሁኔታ ያጡ በገጠር መሬት
የመጠቀም መብት አላቸው ሲል ይደነግጋል፡፡ ከዚህ ህግ መገንዘብ የሚቻለው የገጠር መሬት
ለማግኘት 18 ዓመት የሞላው ሆኖ በግብርና ስራ ለመተዳደር የወሰነ ሰው መሆኑን
እንደመስፈርት የሚጠቀምና በልዩ ሁኔታ ከ18 ዓመት በታች ሆነው ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች
ግን ያለአሳዳጊ እንዳይቀሩ ህጉ ልዩ ማህበራዊ ዋስትና እንደሚሰጣቸው ነው፡፡ ይህ ማህበራዊ
ደህንነት በሀገራችን በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ወላጅ አልባ
እየሆኑ ካሉበት ሁኔታ አንፃር ሲታይ እንደዚህ ያለ የመሬት ተጠቃሚነት መብት ከ18 ዓመት
በታች ላሉ ህፃናት በልዩ ሁኔታ መፈቀዱ ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

አዋጁ ከዚህ በተጨማሪ በአንቀጽ 5(4) ላይ ለአርሶ አደሮች ቅድሚያ በመስጠት በግብርና
ልማት ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፖሊሲውንና ህጎችን መሠረት በማድረግ የገጠር
መሬት ሊሰጣቸው እንደሚችል መደረጉ በራሱ ለአርሶ አደሮች ቅድሚያ መሰጠቱ የቱን ያህል
የመሬት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህ ህግ ግብርና መር
እንዱስትሪያዊ ልማት ስትራቴንጅን መሠረት በማድረግ ለእነዚህ ማህበረሰቦች ከፍተኛ
የማህበራዊ ደህንነት ዋስትና በመስጠት የስትራቴጅው ግብ መምታት በሰፊ ሕዝባዊ መሠረት
ላይ እንዲጣልና አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡

20
6. አጥጋቢ የገጠር መሬት መረጃ ስርዓትን ማረጋገጥ

የገጠር መሬትን መሠረት በማድረግ የእያንዳንዱ ባለይዞታ ስም፣ አድራሻ፣ የመሬቱን ስፋትና
አዋሳኝ ለይቶ ግዴታውን በመመዝገብ አንዱ ባለይዞታ ከሌላው ባለይዞታ ተለይቶ እንዲታወቅ
በሚያስችል መልኩ የገጠር መሬት አስተዳደር ማህደር አያያዝ ስርዓትን መዘርጋት አላማ
ያደረገ አደረጃጀት ነው፡፡ እንደዚህ ያለ አሠራር የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ
መዘርጋት በርካታ ፋይዳዎች ያሉት ሲሆን ከብዙ በጥቂቱ ወስደን ብናይ አሁን ያሉ የይዞታ
ግጭትና እሰጥአገባ በማስወገድ አርሶ አደሮችና በገጠር ልማት ኢንቨስትመንት የተሰማረው
ባለሃብት በሰላም ጊዜያቸውን ለልማት በማዋል ምርታማነት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ መንግስትንና ባለጉዳዮችን ካላስፈላጊ ወጭ ያድናቸዋል፤ በመንግስት የተመዘገበ
መረጃ በመሆኑ የፍትህ አካላት ከመረጃ ምዘና ችግር ተላቀው በቀላሉ ፍትህ የሚሰጡበት
ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ የገጠር መሬት መረጃ ስርዓት ባለው መንገድ እንዲመራና
መንግስትም ሆነ ተጠቃሚዎች በበቂ መረጃ ላይ ተመስርተው የትኛው አካባቢ ምን ቢያመርቱ
የበለጠ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግንዛቤያቸውን እያሰፉና እየተበረታቱ
እንዲሄዱ የሚያስችላቸው በመሆኑ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

7. ቀልጣፋ የገጠር መሬት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት

አዋጅ ቁጥር 456/97 በትርጉም ክፍሉ አንቀጽ 2(2) ላይ “የገጠር መሬት አስተዳደር ማለት
ምን ማለት እንደሆነ ሲተረጉም፡- በገጠር መሬት ይዞታ ላይ ዋስትና የሚሰጥበት የገጠር
መሬት አጠቃቀም ዕቅድ የሚተገበርበት ፣በገጠር መሬት ተጠቃሚዎች መካከል የሚነሱት
ግጭቶች የሚፈቱበትና ማንኛውም የገጠር መሬት ተጠቃሚ መብትና ግዴታዎች
የሚተገበሩበት እንዲሁም የባለይዞታዎች ማሳዎችንና የግጦሽ መሬትን መረጃ በመሰብሰባ እና
በመተንተን ለተጠቃሚዎች እንዲዳረሱ የሚደረግበት ሂደት ነው” ይላል፡፡

ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው የመሬት አስተዳደር ለማከናወን በርካታ ስራዎችን መስራት
እንደሚጠይቅና እነዚህን ስራዎች ለመስራት የራሱ ተቋማዊ አደረጃጀትና ምርምርን
እንደሚጠይቅ ነው፡፡ ስለሆነም የገጠር መሬት አስተዳደር መኖር በራሱ ግብ ባይሆንም የዘላቂ
ልማት ፖሊሲና ስትራቴጅዎች የሆኑትን እንደ የገጠር መሬት ዋስትና ማረጋገጥ፣ የገጠር
መሬት ክርክርን መቀነስ፣ የመሳሰሉትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል በመረጃና በእውቀት

21
የዳበረ አሰራርን ተከትሎ ለበለጠ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ልማትና መልካም አስተዳደር ስኬታማነት
ያላሰለሰ ጥረት ማድረግና በሂደት የገጠር መሬት ፖሊሲውንና ስትራቴጅውን የራስ ማድረግ
የሚጠይቅ መሆኑን ነው፡፡

ስለዚህ አዋጅ ቁጥር 456/97 በርካታ ዓላማዎችን በመያዝ የገጠር ልማት ፖሊሲውንና
ስትራቴጅውን እውን ለማድረግ በሚያስችል መልኩ የወጣ አዋጅ እንደመሆኑ መጠን የክልል
መንግስታት እና በየደረጃው ያሉ የፍትህ አካላት ለተፈፃሚነቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ
ይገባል ማለት ነው፡፡

1.4.3 የክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ህጎች

የፌዴራል መንግስት የሚያወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ መሠረት


በማድረግ የክልል መንግስታት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን ለማስተዳደር ስልጣን እንዳላቸው
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 52(2)(መ) ሥር ተደንግጓል፡፡ የፌዴራል መንግስት በኢፌዴሪ
ሕገ-መንግስት በተሰጠው ስልጣን መሠረት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ
አዋጅ ቁጥር 456/1997ን ያወጀ ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 17(1) ድንጋጌ መሰረት ክልሎች
ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚስፈልጉ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የያዘ የገጠር መሬት አስተዳደር እና
አጠቃቀም ሕግ ያወጣሉ በማለት አስቀምጧል፡፡

በዚህ መሠረትም የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመጀመሪያ አዋጅ ቁጥር 23/89ን
በመቀጠልም 55/94ን እና 97/98 እንዲሁም አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር
136/2000ን፤ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመጀመሪያ አዋጅ ቁጥር 56/94ን
በመቀጠልም 70/95ን እና 103/97 እንዲሁም አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር
130/99ን፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በመጀመሪያ አዋጅ ቁጥር
53/95ን እና በመቀጠልም አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር 110/99ን፣ የአማራ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግስት ደግሞ በመጀመሪያ አዋጅ ቁጥር 16/89ን፣ በመቀጠልም አዋጅ ቁጥር 46/92
እና አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር 133/98ንና የዚህን አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር
148/99ን፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትም አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅ
ቁጥር 85/2002ን (ከዚህ አዋጅ በፊት የወጡትን ማግኘት አልተቻለም) በየምክር ቤቶቻቸው
በማውጣት የገጠር መሬትን በማስተዳደር ረገድ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

22
በመሆኑም በአምስቱ ብሔራዊ ክልሎች ምክር ቤቶች የወጡ አዋጆችን ለማሰባሰብ የተሞከረ
ሲሆን በክልሎች ፀድቀው እየተሰራባቸው ያሉ ደንቦችና መመሪያዎችን ግን በተሟላ ሁኔታ
ለማግኘት አልተቻለም፡፡ በተጨማሪም የፌዴራል መንግስት አባላት የሆኑት አፋር፣ ሱማሌ፣
ጋምቤላ እና ሐረሪ ብሔራዊ ክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች ለመፈለግ
የተሞከረ ቢሆንም ለማግኘት አልተቻለም፡፡ በመሆኑም ሰልጣኞች የየክልሎቻቸውን የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች በማፈላለግ መሠረታዊ ይዘትና ገጽታቸውን በማየት
ለስልጠናው ውጤታማነት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

1.4.4 የፌዴራል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ


በክልሎች ላይ ያለው ተፈፃሚነት

ህገ መንግስቱ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የግብርና ሥራውን ለማከናወን በቂ የሆነ የእርሻ


መሬት በነፃ የማግኘት መብት እንዳለቸው የሚደነግግ ሲሆን ዝርዝሩ በህግ እንደሚወሰን
ይገልፃል፡፡ አሁን ባለው ህገመንግስታዊ ሥርዓት አገሪቱ በፌደራል ቅርፅ መንግስት የተዋቀረች
ናት፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ኢትዮጰያዊ አርሶ አደር በነፃ መሬት የማግኘት መብት እንዴትና
በምን ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚሆን ዝርዝሩ የሚወሰነው በፌደራል መንግስት በሚያወጣው
ህግ ነው ወይስ ክልሎች የሚያወጡት የህግ ማዕቀፍ ለሚለው መሰረታዊና ቁልፍ ጥያቄ ህገ
መንግስቱ መሠረታዊ መርሆችን በመደንገግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ህገ መንግስቱ የፌደራሉ መንግስት የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና ጥበቃ ህግ


የሚያወጣ መሆኑንና ክልሎች የፌደራል መንግስት በሚየወጣው ህግ መሠረት የመሬትና
የተፈጥሮ ሀብት የማስተዳደር ሥልጣን እንዳላቸው በአንቀፅ 51(5) በአንቀፅ 55(2)(ሀ) እና
በአንቀፅ 52(2)(መ) ይደነግገል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፌደራሉም ሆነ የክልል መንግስታት
መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታቸው ሥር በማድረግ ለሕዝብ የጋራ ጥቅምና
እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑ ህገ መነግስቱ የኢኮኖሚክ ነክ
አላማዎች አበይት መርህ መሆኑን በአንቀፅ 89(5) ይደንግጓል፡፡

የህገ መንግስቱን ድንጋጌ ተግባራዊ ለማድረግ በፌደራል መንግስት የወጡ የህግ ማዕቀፎች
በተመሳሳይ ጉዳይ ክልሎች በሚያወጡት ህግ ላይ የበላይነት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለው
ነጥብ እነዚህን ህገመንግሰታዊ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ንደፈሀሳባዊ ምላሽ መሰጠት

23
ለህግ ባለሙያዎች የሚከብድ አይደለም፡፡ ሆኖም የፌደራል መንግስት ካወጣቸዉ የህግ
ማዕቀፎች ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 456/97 ድንጋጌዎች የትኞቹ አስገዳጅና ወጥነት ባለዉ ሁኔታ
በሁሉም ክልሎች ያለምንም የይዘት ለውጥ ማሻሻያ ሊከበሩና ሊተገበሩ የሚገባቸው የትኞቹ
ድንጋጌዎች ናቸው እንዲሁም ፈቃጅነት ያላቸዉና ክልሎች ነባራዊ ሁኔታዉን መሰረት
በማድረግ ይዘታቸውን በመለወጥና በማሻሻል ሊተገብሯቸው ይችላሉ የሚሉትን ጥያቄዎች
በተሟላ ሁኔታ ምላሽ መሰጠት ቀላል እንዳልሆነ የሚከተሉትን ነጥቦች በማንሳት ማየት
ይቻላል፡፡

የመጀመሪያው በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ 2 የተደነገጉ የትርጉም ድንጋጌዎች አስገዳጅነት


ያላቸው ናቸው ወይስ ፈቃጅነት ያላቸው ናቸው የሚለው ጥያቄ የትግራይ ክልል የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ 2(5) ለቤተሰብ አባል
የተሰጠዉን ትርጉም አለማካተቱ ምን ዉጤት ይኖረዋል የሚለዉ ነዉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ
ለቤተሰብ አባል የሰጠውን ትርጉም መሰረት በማደረግ በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ5(2) እና
አንቀፅ 8(5) የተደነገገዉን በውርስና በስጦታ የእርሻ መሬት የማግኘትና የማስተላለፍ መብት
በሚለዉጥ በሚያጠብ ወይም በሚያሰፋ መንገድ በትግራይ በአማራ በኦሮሚያ በቤንሻጉል
ጉሙዝ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጆች የተደነገጉ ድንጋጌዎች በፌደራሉ
የወጣዉን አሰገዳጅ ድነጋጌዎች ስለሚቃረኑ ተግባራዊ ሊሆኑ አይገባም የሚል ክረክር ቢነሳ ምን
አይነት የህግ አተረጓጎም መከተልና ችግሩን መፍታት ይቻላል የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ
ጥያቄ የሚያስነሱ ድንጋጌዎች አሉ፡፡ ስለሆነም የፌደራል መንግስት አሰገዳጅነት ያላቸውንና
ፈቃጀነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ግልፅ በማድረግ ማወጅና በዚህ ምክንያት የሚፈጠሩ
ችግሮችንና ክፍተቶችን ለማቃለል ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሆኖም ለዚህ ስልጠና አላማ ሲባል በህገ መንግስቱ ከተረጋገጡት መብቶች በመነሳት የፌዴራል
የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ በማናቸውም የገጠር
መሬት ላይ ተፈፃሚነት ያለው የሕግ ማዕቀፍ ስለሆነ ሁለት አይነት ባህሪይ ያላቸው
ድንጋጌዎችን የያዘ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እነርሱም፡-

 ሁሉም ክልሎች ሊያከብሯቸውና ሊተገብሯቸው የሚገቡ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌዎች፣


 ክልሎች እንዳላቸው ነባራዊ ሁኔታ ውሳኔ ሊሰጡባቸው የሚገቡ ፈቃጅ የሕግ
ድንጋጌዎች ናቸው፡፡

24
ሀ. ክልሎች ሊያከብሯቸውና ሊተገብሯቸው የሚገቡ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌዎች

በአዋጅ ቁጥር 456/97 መሠረት ሁሉም ክልሎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ዝርዝር
የሕግ ማዕቀፎችን ሲያወጡና የሕግ ማዕቀፎችን ሲያስፈፅሙ የሚከተሉትን መሠረታዊ
መብቶች የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡

 በግብርና ስራ የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የገጠር መሬት በነፃ የማግኘት መብትን


ማረጋገጥ (አንቀጽ 5(1)(ሀ)))፣
 ወላጅ አልባ ሕፃናት አካለ መጠን እስኪያደርሱ በሞግዚታቸው አማካኝነት የገጠር
መሬት የመጠቀም መብታቸውን ማረጋገጥ (አንቀጽ 5(1)(ለ)))፣
 የሴቶችን የገጠር መሬት በነፃ የማግኘት መብትና ከወንዶች በእኩልነት የመጠቀም
መብትን ማረጋገጥ (አንቀጽ (5(1)(ሐ)))፣
 የአርሶ አደሮችን በገጠር መሬት የመጠቀም መብት ያለምንም ጊዜ ገደብ ማረጋገጥ
(አንቀጽ 7(1))፣
 የማንኛውም አርሶ አደር የቤተሰብ አባል ከቤተሰቡ በስጦታ ወይም በውርስ ወይም
አግባብ ካለው አካል የገጠር መሬት በይዞታ የማግኘት መብቱን ማረጋገጥ (አንቀጽ
5(2))፣
 አርሶ አደሮች በማይፈናቀሉበት መልኩ በይዞታ የያዙትን መሬት የማከራየት መብት
ማረጋገጥ፣ የኪራይውም አግባብ ባለው አካል መጽደቅ ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ
(አንቀጽ 8(1-3))፣
 ማንኛውም ባለይዞታ የገጠር መሬት የመጠቀም መብቱን ለቤተሰቡ አባል የማውረስ
መብት ያለው መሆኑ (አንቀጽ 8(5))፣
 ማንኛውም አርሶ አደር መሬቱን በአግባቡ የመንከባከብ ግዴታ ያለበት መሆኑና
በመሬቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ በመሬት የመጠቀም መብቱን ሊያጣ የሚችል መሆኑን
(አንቀጽ 10(1))፣
 ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሊሠጠው የሚገባ
መሆኑን፣ መሬቱ በባልና በሚስት በጋራ የተያዘ ከሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ
በሁለቱም የጋራ ባለይዞታው ስም መዘጋት ያለበት መሆኑ (አንቀጽ 6(3)(4)))፣

25
 ቅድሚያ ለአርሶ አደሮች በመስጠት ኢንቨስተሮችና ሌሎች ድርጅቶች የገጠር
መሬትን በሊዝ ወይም በሌላ መልኩ በማግኘት የመጠቀም መብትን ለማረጋገጥ
የሚችል አሠራር መከተል (አንቀጽ 5(4))፣
 የገጠር መሬት ባለይዞታ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬቱን በመንግስት እንዲለቅ
ሲደረግ በመሬቱ ላይ ላደረገው ማሻሻያና ላፈራው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ የማግኘት
መብቱን ማረጋገጥና ተለዋጭ መሬት እንዲያገኝ ማድረግ (አንቀጽ 7(3))፣
 የገጠር መሬት ሽግሽግ ለማድረግ መሠረት የሚሆኑ ደንቦችን መከተል (አንቀጽ 9)፣
 የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ማውጣትና ማስፈፀም (አንቀጽ 13)፣

ለ. ክልሎች እንዳላቸው ነባራዊ ሁኔታ ውሳኔ ሊሠጡባቸው የሚገቡ ፈቃጅ የሕግ


ድንጋጌዎች፣

በአዋጅ ቁጥር 456/97 መሠረት ክልሎች የራሳቸውን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ ሕግ


ሊያወጡባቸውና በተለያየ መንገድ ሊያስፈፅሟቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ እነርሱም፡-

 መሬት በነፃ የማግኘት መብት ያለው ሰው ምን መስፈርቶችን እንደሚያሟላ


መወሰን፣
 በገጠር የሚገኝ መሬት በግል ይዞታ የመያዝ፣ የወልና የጋራ መሆናቸውን
መለየትና መከለል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የወልና የጋራ መሬት ይዞታዎችን ወደ
ግል ይዞታ ማዛወር የሚቻልበትን ስርዓት መዘርጋት፣
 የገጠር መሬትን በሊዝ የያዙ ኢንቨስተሮች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ
ተቋማት የመሬት ባለይዞታነትና መሬት የመጠቀም መብት ፀንቶ የሚቆይበትን
ጊዜ መወሰን፣
 አርሶ አደሮች በኪራይ ሊያስተላልፉ የሚችሉት የይዞታ መጠንና ኪራዩ ፀንቶ
የሚቆይበትን ጊዜ መወሰን፣
 የኪራይ ውል የሚመዘገብበትን ሁኔታ መወሰንና ማመቻቸት፣
 የመስኖ መሬት ሽግሽግና የመሬት ሽግሽግ ለማካሄድ የሚያስችሉ ደንቦችን
ማውጣት፣
 የገጠር መሬትን አነስተኛ እና ከፍተኛ የወለል መጠንን መወሰን፣
 የመሬት ይዞታን አስመልክቶ የሚነሳ ክርክር የሚፈታበትን ሁኔታና ስልጣን
ያላቸውን አካላት በሕግ መደንገግ፣

26
 የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ሕግን የሚያስፈፅሙ አካላትን ማደራጀት ናቸው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በአንዳንድ አገሮች መሬት በግል ባለሀብቶች የሚያዝ የግል ንብረት ሲሆን እነዚህ ሰዎች
የመሬት ባለቤቶች ይሆናሉ፡፡ መሬት በሀገራችን የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ መሰረታዊ አጀንዳ
መሆኑ እንዲሁም ካሳለፍናቸው ታሪካዊ የመሬት ስሪቶች አንፃር በኢፌዴሪ ህገ-
መንግስት መሬት የመንግስት እና የሕዝብ ንብረት እንዲሆን መደንገኑ (መሸጥ መለወጥ
መከልከሉ) ፋይዳው ምንድን ነው?
2. አንዳንዶች ክልሎች የፌደራል መንግስት በሚያወጣው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ህግ መሰረት መሬትን ማስተዳደር እንጅ ህግ የማውጣት ስልጣን የላቸውም የሚል
መከራከሪያ ያነሳሉ፤ እንዴት ታዩታላችሁ?
3. መሬትን በተመለከተ የፌዴራል መንግስት ህግ ባላወጣበት ሁኔታ ክልሎች መሬትን
ለማስተዳደር የራሳቸውን ህግ ቢያወጡ የክልሎች ነዋሪዎች ይህንን ህግ በመጥቀስ
መብታቸውን ለማስከበር ክርክር ቢያነሱ በየፍ/ቤቶች ተፈፃሚነቱ ምን መሆን አለበት?
4. በሕገ-መንግስቱ ለአርሶ አደሮቹ የተረጋገጠውን የገጠር መሬት በነፃ የማግኘት መብት
እውን ከማድረግ አንፃር የክልሎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ የማውጣት
ስልጣን (Inter state legislation power) ከቦታ ቦታ በመብቶች አጠቃቀም ላይ ልዩነት
አያመጣም ወይ? በመሬት ባለይዞታ የመሆንና የመጠቀም መብቶችን ውስብስብ
አላደረገውም ወይ? የክልሎችን ስልጣን መኖር ጥቅምና ጉዳት ተወያዩበት?
5. የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደርን በተመለከተ ቀደም ሲል በነበረው ስርዓት
የፍትሐብሔር ህጉ ቀጥሎ በደርግ ዘመን በአዋጅ ቁጥር 31/67 በኋላ ደግሞ በፌዴራል
ደረጃ የኢፌዴሪ መንግስት የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 89/1989 እና አሁን ያለው
456/1997 ወጥቷል፡፡ ክልሎችም የእየራሳቸውን ህጎች በማውጣትና በማሻሻል አሁን
ስራ ላይ ያለ የክልል የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር አዋጆች እንዳሏቸው
ተመልክተናል፡፡ ለምሳሌ የአማራ ክልልን ብንወስድ አዋጅ ቁጥር 16/1989 (የመሬት
ሽግሽግ የተደረገበት አዋጅ)፣ አዋጅ ቁጥር 46/1992፤ አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ
ቁጥር 133/1998 እና ማስፈፀሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999 ወጥተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ
ህጎች እንደየዘመናቸው ለመሬት ባለይዞታዎች የተለያየ መብት ይሰጣሉ፡፡ በክልሉ
ተጨባጭ ሁኔታ በተለይ የወረዳ ፍ/ቤቶች በ1991 ዓ.ም ወይም በ1995 ዓ.ም የሞተ

27
ሰው ቢኖር ውርሱን በአዋጅ ቁጥር 133/1998 መሠረት ሲያስተላልፉና ሲወስኑ
ይስተዋላሉ፡፡
5.1. ለመሆኑ በ1987 ዓ.ም የሞተ ሰው ቢኖር እና ወራሾቹ በ2000 ዓ.ም
የውርስ ይገባኛል ጥያቄ ቢያቀርቡ በየትኛው ህግ መሠረት ይወሰናል?
5.2. በ1991 ዓ.ም የሞተ ቢሆንስ?
5.3. በ1995 ዓ.ም ቢሆንስ?
5.4. በመጨረሻ 1999 ዓ.ም የሞተ ቢሆንስ? (የሁሉም ክስ የቀረበው በ2000 ዓ.ም
ነው ብለን እንውሰድ)
5.5. አሁን ባለው ሁኔታ አዋጅ ቁጥር 31/67 ተጠቅሶ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል?
5.6. በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት ሽግሽግ ባለመደረጉ ምክንያት መሬቱን ይዘው
የቆዩ ሠዎች የይገባኛል ጥያቄ ቢያነሡ እንዴት ይስተናገዳል? በየተኛው ህግ?

28
ምዕራፍ ሁለት
የገጠር መሬትን የማግኘት፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብቶች በክልል የሕግ
ማዕቀፎች፣
የፌዴራሉ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 52(2) (መ) ክልሎች መሬትን የሚያስተዳድሩት የፌዴራሉን
የመሬት ሕግ መሠረት አድርገው መሆን እንዳለበት በደነገገው መሠረት አዋጅ ቁጥር 456/97
ለገጠር መሬት መብት አተገባበር ለክልሎች እንደ መመሪያ የሚያገለግል ህግ ነው፡፡ ክልሎች
የሚያወጡአቸው የገጠር መሬት ህጎችም ይህንኑ አዋጅ መሠረት እንዲያደርጉ ይጠበቃል፡፡
አዋጅ ቁጥር 456/97 አንድ የመሬት ባለይዞታ ያሉትን መብቶች በበቂ ሁኔታ ባይዘረዝርም
መጠቀም፣ ማከራየትና ማውረስ እንደሚችል ግን በጥቅሉ ይጠቁማል፡፡ በዚህ ምዕራፍ የገጠር
መሬትን የማግኘት፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብቶች በክልል የሕግ ማዕቀፎች ያላቸውን
ሽፋን እንመለከታለን፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች
ሠልጣኞች የዚህን ምዕራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-
 የገጠር መሬት የይዞታ መብት አይነቶችን፣
 የገጠር መሬት በነፃ የማግኘት መብት ያላቸው ሰዎችን፣
 የገጠር መሬትን በነፃ ለማግኘት ያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን፣
 የገጠር መሬት መብቶች የሚገኙባቸውንና የሚታጡባቸውን እንዲሁም
የሚተላለፉባቸውን መንገዶች ለይተው ያውቃሉ፣
 የገጠር መሬት የማግኘት፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብትን በተመለከተ
በክልሎች ህጎች መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት ማስረዳትና ማብራራት
ይችላሉ፡፡

2.1 የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሆን መብት


መሬት የማግኘት መብትን በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት በመጀመሪያ ደረጃ የይዞታ መብትን
ትርጉምና ዓይነቶችን ማየት ያስፈልጋል፡፡

29
2.1.1 የይዞታ መብት እና የይዞታ አይነቶች

በኢትዮጵያ የፍ/ር/ህ/ቁ 1140 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ይዞታ አለ ማለት የሚቻለው


ባለይዞታ የሆነው ሰው ንብረቱን በእጁ ሲያደርግና በእጁ ባደረገው ንብረት ላይ የመጠቀም ሃሳብ
ሲኖረው ነው፡፡ በኢትዮጵያ የህግ ሥርዓት በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ አንድ ሰው የአንድ
ንብረት ባለይዞታ መሆን እንደሚችል በፍ/ር/ህ/ቁ 1140 እና 1141 የተደነገገ ሲሆን
ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ልዩ የባለቤትነት ሰነድ የማያስፈልጋቸውን የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ይዞ
መገኘት የንብረቱ ባለቤት ነው ተብሎ በህግ የመገመት መብት ያጎናፅፋል፡፡ ይህም ማለት ልዩ
ተንቀሣቃሽ ከሚባሉት ንብረቶች ውጭ የሆኑ የሚንቀሣቀስ ንብረት በእጅ ይዞ የተገኘ ሰው
የንብረቱ ባለቤት ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ንብረቱን በእጅ የያዘው ሰው ሣይሆን
የእኔ ነው የሚለው ወገን የማስረዳት ግዴታ እንዳለበት የፍ/ር/ሕ/ቁ 1190 ይደነግጋል፡፡

በሌላ በኩል በፍትሐብሔር ህጉ መሰረት ባለቤትነት የሚገኝባቸው አራት መንገዶች ያሉ ሲሆን


አንዱ በፍ/ር/ህ/ቁ 1168 የሚገኘው ነው፡፡ ይህ የህግ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው በማይንቀሳቀስ
ንብረት ላይ ነው፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚባሉትም መሬትና ህንጻዎች እንደሆኑ
በፍ/ር/ህ/ቁ1130 ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ሰው በመሬቱ ላይ ወይም
በህንጻው ላይ ለ15 ዓመታት በተከታታይ ሳይቋረጥ በስሙ ግብር ከከፈለ የመሬቱ ወይም
የህንጻው ባለቤት መሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ድንጋጌ አዋጅ ቁጥር 31/67 ከታወጀ ማግስት
በመሬት ላይ ተፈጻሚ መሆኑ ተቋርጧል፡፡ አሁንም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ላይ በግልጽ
እንደተመለከተው መሬት የመንግስትና የህዝብ በመሆኑ አንድ ሰው ለ15 ዓመት ቀርቶ ለ50
ዓመትም እንኳን በተከታታይ በስሙ ግብር ቢከፍል የመሬት ባለቤት መሆን አይችልም፡፡
ስለዚህ አሁን ባለው መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ስርዓት መሰረት የፍ/ር/ህ/ቁ 1168
የመሬት ባለይዞታ የመሆን መብት አይሰጥም፡፡

በኢትዮጵያ የህግ ሥርዓት የይዞታ መብት አድማስ በመሬትና በሌሎች ንብረቶች ላይ የተለያየ
መሆኑን መገንዘብ ይጠይቃል፡፡ ለምሳሌ ይዞታ በፍ/ር/ህ/ቁ 1140 እና 1141 እና ተከታይ
ድንጋጌዎች የተሰጠው ትርጉምና ጥበቃ እና ይዞታ በፌዴራል የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 እና ክልሎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን በሚመለከት
ባወጧቸው አዋጆች ከተሰጠው ትርጓሜና ጥበቃ የተለያዩ ናቸው፡፡

30
ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእዉነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነዉ
በማለት የፍ/ር/ህ/ቁ 1140 የተሰጠዉ ትርጉም እጅግ በጣም ጠባብ ሲሆን የፌደራል የገጠር
የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ 2(4) “የይዞታ መብት ማለት
ማንኛውም አርሶ አደር ፣አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የገጠር መሬትን በግብርናና
በተፈጥሮ ሀብት ልማት ተግባር ላይ የማዋል፣ የማከራየት፣ ለቤተሰቡ አባልና ለሌሎች በህግ
መብት ለተሰጣቸው ወራሾች ለማውረስ የሚኖረው መብት ሲሆን በመሬቱ ላይ በጉልበቱ
ወይም በገንዘቡ ንብረት የማፍራትና ይህንንም በመሬቱ ላይ ያፈራውን ንብረት የመሸጥ
የመለወጥና የማውረስንም መብት ይጨምራል” በማለት ደንግጓል፡፡ አንዳንድ ክልሎችም ይህንን
ትርጉም እንዳለ በመቀበል ባወጡት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ ውስጥ
አካትተዋል፡፡21

የገጠር መሬት በግል፣ በጋራ፣ በወል ወይም በመንግስት ሊያዝ ይችላል፡፡ የግል ይዞታ ማለት
በማንኛውም አርሶ አደር ወይም በክልሎች የገጠር መሬት አዋጆች መሠረት የመጠቀም መብት
በተሠጠው ሌላ አካል እጅ ሆኖና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ወጥቶለት በግል ይዞታ ስር
የሚገኝ መሬት ነው፡፡22 የጋራ ይዞታ ማለት ደግሞ ቁጥራቸው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ
የሆኑ ሰዎች በአንድ መሬት ላይ ያልተከፋፈለ የይዞታ ባለመብቶች ሆነው መሬቱን ሳይከፋፈሉ
ከዚሁ ከመሬቱ የሚገኘውን ጥቅም እየተጋሩ የሚጠቀሙበት መሬት ነው፡፡23 የወል ይዞታ
ማለት ደግሞ ከመንግስት ወይም ከግል ይዞታነት ውጭ የሚገኝና የአካባቢው ነዋሪዎች
በህብረት የሚጠቀሙበት መሬት ሲሆን ለግጦሽ፣ ለደንና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች
የዋለ መሬት ነው፡፡24 የመንግስት ይዞታ ማለት ለሀገርና አካባቢ ልማትና እድገት ተብሎ
በመንግስት ይዞታ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የተያዘ መሬት ሲሆን ጥብቅ የደን
መሬቶችን፣ የዱር እንስሳት መጠለያዎችን የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን፣ ፓርኮችንና
በሀይቆችም ሆነ በወንዞች አካባቢ የሚገኙ ስፍራዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡25 በአጠቃላይ
የመሬት ባለይዞታ ማለት በአንድ የገጠር መሬት ላይ የይዞታ መብት ያለው ግለሰብ፣ የሰዎች

ለምሳሌ አማራ፣ ደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች


21

የኢፌዴሪ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/1997(ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር
22

456/1997 እየተባለ የሚጠራው) አንቀፅ 2(11)


የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር133/1998((ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር
23

133/1998 እየተባለ የሚጠራው) ፣ አንቀፅ 2 (10)(11)


አዋጅ ቁጥር 456/1997፤ አንቀፅ 2(12)
24

ዝኒከማሁ አንቀፅ 2(13)


25

31
ስብስብ ወይም ህ/ሰብ፣ የመንግስት አካል፣ ማህበራዊ ተቋም ወይም ሌላ የሕግ ሰውነት ያለው
አካል ነው፡፡

2.1.2 የገጠር መሬት የይዞታ መብት የሚገኝባቸው መንገዶች፡-


ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት ክልል ውስጥ
በግብርና ስራ የሚተዳደር ከሆነ ወይም ለመተዳደር የሚፈልግ ከሆነ የገጠር መሬት የይዞታ
መብት በነፃ በሶስትመንገዶች ሊያገኝ ይችላል፡፡26 እነዚህም በድልድል፣ በውርስ እና በስጦታ
ናቸው፡፡
1. በድልድል
የገጠር መሬት የይዞታ መብት ከሚገኝባቸው መንገዶች መካከል አንዱ በድልድል (ሽግሽግ)
ሲሆን የሚፈፀመውም የገጠር መሬትን በይዞታ እንዲሰጠው የሚጠይቀው አካል በመደበኛነት
በሚኖርበት ወይም መኖር ከሚፈልግበት ቀበሌ መሬትን ከሚያስተዳድረው አካል በሚደረግ
የመሬት ክፍፍል ይሆናል፡፡27 መሬትን በድልድል ያለምንም ክፍያ መሬትን ከሚያስተዳድረው
አካል ማግኘት የሚገባቸው አካላትን በተመለከተ ክልሎች በየራሳቸው የሕግ ማዕቀፎች ዝርዝር
መስፈርቶችን አስቀምጠዋል፡፡ መሬት በድልድል ሊያገኙ የሚችሉ አካላትንና ሊያገኙ
የሚችሉበትን መስፈርት እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
ሀ. አርሶ አደሮች
አርሶ አደሮች ምንም ዓይነት የፆታም ሆነ ሌላ ልዩነት ሳይደረግባቸው መሬትን በይዞታ
ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ያሉ ሲሆን ዋናዎቹ አርሶ አደር መሆን፤ አስራ
ስምንት ዓመትና ከዚያ በላይ መሆንና የክልሉ ነዋሪ መሆን ናቸው፡፡28 የፌደራሉ መንግስት
ባወጣው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ እድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ
የሆነና በግብርና ሙያ ለመተዳደር የሚፈልግ ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ የገጠር መሬት በነፃ
እንዲያገኝ እንደሚያደርግና የገጠር መሬት የመጠቀም መብቱ እንደሚረጋገጥ ይደነግጋል፡፡
ሆኖም የእርሻ መሬት የሚያገኘው በምን ሁኔታ ነው? መብቱን ሊያከብርና ሊያስከብር
የሚችለው አካልስ ማን ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች የፌደራሉ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
ህግ ምላሽ አይሰጥም፡፡ በመሆኑም የፌደራሉ ህግ በክልሎች ተግባራዊ ስለሚሆንበት ሁኔታ

ዝኒከማሁ አንቀፅ 5(1)(ለ)


26

ዝኒከማሁ አንቀፅ 5 እና 9 አጣምሮ በማንበብ መረዳት ይቻላል


27

ዝኒከማሁ አንቀፅ 5(1)


28

32
ክልሎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ እንዲያወጡ በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ 17
ሥልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡

በአዋጅ የተሰጣቸውን ህግ የማውጣት ሥልጣን መሠረት በማድረግ አንድ አርሶ አደር በነፃ
መሬት ሊያገኝ የሚችልበትን የተለያዩ መስፈርቶች የደነገጉት ክልሎች መብቱ ሊጠየቅና
ተፈፃሚ ሊሆንበት ስለሚችልበት ሁኔታ ወጥነት ያለዉ ግልፅ ምላሽ አይሰጡም፡፡ የትግራይ
ክልል ያወጣው ህግ በግብርና ሥራ የሚተዳደር አርሶ አደር የገጠር መሬት በነፃ እንዲያገኝ
እንደሚደረግ ከመደነግግ ውጭ የክልሉን መንግስት በነፃ የእርሻ መሬት ሊሰጠኝ ይገባል ብሎ
ለመጠየቅ አርሶ አደሩ ማሟላት ያለበትን መስፈርት በግልፅ አይደነግግም፡፡ የኦሮሚያ ክልል
ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ የሆነና እድሜው ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆነ አርሶ አደር በነፃ
የእርሻ መሬት የማግኘት መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ይህ አዋጅ አንድ ሰው
የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ ነው የሚባለው ምን ምን መስፈርቶችን ሲያሟላ እንደሆነ የማይደነግግ
ከመሆኑም በላይ “የክልሉ ነዋሪ” ለሚለው ቃል የሰጠውም የህግ ትርጉም የለም፡፡ የአማራ
ክልል በክልሉ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም አርሶ አደር በፆታም ሆነ በሌላ ማናቸውም ምክንያት
ልዩነት ሣይደረግበት መሬት በይዞታ የማግኘት እኩል መብት ያለው መሆኑን ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም አንድ ሰው በክልሉ ውስጥ ባሉ በአንደኛው ቀበሌ ነዋሪ ነው የሚባለው መደበኛ
መቀመጫውን በአንድ ቀበሌ አድርጎ መሠረታዊ አገልግሎቶችንና ማህበራዊ ጥቅሞቹን በዚያው
ቀበሌ ውስጥ የሚያገኝ ማናቸውም ሰው ማለት እንደሆነ ትርጉም ሰጥቶታል፡፡ ሆኖም አንድ
ሰው የቀበሌ ነዋሪ ነው ለመባል በክልሉ ለስንት ወራት ወይም ዓመታት መቀመጥ አለበት
ለሚለው ጥያቄ በግልፅ ምላሽ የሚሰጥ አይደለም፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ በአማራ ክልል ህግ


የተቀመጡትን ድንጋጌዎች አገላለፅ የተጠቀመ ሲሆን ይህ የክልሉ አዋጅ አንድ አርሶ አደር
መደበኛ መኖሪያው የነበረውን ሌላ ክልል በቋሚነት ለቅቆ በመሄድ በክልሉ ውስጥ መደበኛ
መኖሪያውን አድርጓል የሚባው ምን ምን ሁኔታዎችን ሲያሟላ ነው? ለምን ያህል ጊዜ
በመደበኛነት በክልሉ ውስጥ በሚገኘ ቀበሌ ሲኖር ነው ?ለሚለው ጥያቄ ግልፅና በቂ ምላሽ
የሚሰጥ ሆኖ አናገኘውም፡፡ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የገጠር መሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ እድሜው አስራ ስምንት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ በግብርና ስራ
ሊተዳደር የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ የገጠር መሬት የማግኘትና የመጠቀም መብት እንዳለው

33
ይደነግጋል፡፡29 ሆኖም አንድ ሰው የክልሉ ነዋሪ ነው የሚባለው ምን ምን መስፈርቶችን
ሲያሟላ እንደሆነ አይደነግግም የክልል ወይም የቀበሌ ነዋሪ ለሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉም
የለም፡፡

በአጠቃላይ የፌደራል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግም ሆነ በክልሎች የወጡ የመሬት


አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ ማዕቀፎች በአንድ ክልል ተወላጅ ወይም ነዋሪ የነበሩ አርሶ
አደሮች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራቸውን በቋሚነት በመልቀቅ በሌላ ክልል ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ
/ቦታ/ በመመስረት የክልሉ ነዋሪ ናቸው የሚባሉት ምን መሥፈርት ሲያሟሉና ለምን ያህል
ጊዜ ሲኖሩ እንደሆነና በቋሚነት መኖሪያ ቦታቸውን የመሰረቱ የክልል ተወላጆች የእርሻ መሬት
በነፃ ሊሰጣቸው የሚችለው በምን መንገድ እንደሆነና እንዴት መብታቸውን መጠየቅ እና
ማስከበር እንደሚችሉ በዝርዝርና በግልፅ አይደነግጉም፡፡

በፌደራሉም ሆነ በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጆች የገጠር መሬት


በይዞታ ለማግኘት የእድሜ ገደቡን 18 ዓመት እና በላይ ብለው በመርህ ደረጃ ቢያስቀምጡም
በልዩ ሁኔታ ግን እድሜአቸው 18 ዓመት ያልሞላቸውን ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናት
የሚተዳደሩበት መሬት በሞግዚታቸው ወይም በወኪላቸው አማካኝነት እንደሚሠጣቸው
ተደንጓል፡፡30 ምክንያቱም ወላጅ አልባ የሆኑ ሕፃናትን በተመለከተ መሬት በይዞታ ሊሰጣቸው
የሚገባ መሆን እና ይህም ማህበራዊ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያ ወሳኝ መፍትሔ መሆኑን
በምዕራፍ አንድ በተመለከትነው መሰረት ያላሟላ ክልል ካለ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፡፡

ለ. መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ማህበራትና ሃይማኖታዊ ተቋማት


እነዚህን ተቋማት በተመለከተ ክልሎች የየራሳቸውን መስፈርት አስቀምጠዋል፡፡ የአማራ ክልል
የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ እነዚህ ተቋማት የገጠር መሬት የይዞታ መብት በነፃ በድልድል
እንዲሰጣቸው፡-31
 ተግባራቸውን የሚያከናውኑት ለገንዘብ ትርፍ መሆን የለበትም፣

29
የተሻሻለዉ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አሰተዳደርና
አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999 (ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር 110/1999 እየተባለ የሚጠራው) አንቀፅ 5(1)(2)
30
ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀፅ 5(1)(ለ)፤ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀፅ 6(2)፣ አዋጅ ቁጥር
110/1999 አንቀፅ 5(8)
31
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀፅ 6(4)

34
 የአርሶ አደሮችን መሬት የማግኘት መብት የሚፃረር መሆን የለበትም፣
 ይህን የገጠር መሬት ይዞታ በውርስም ሆነ በስጦታ ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ
የለባቸውም በማለት ይደነግጋል፡፡
የኦሮሚያ የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ ደግሞ እነዚህ ተቋማት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
የገጠር መሬት የይዞታ መብት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አስቀምጧል፡፡32 በሌላ በኩል የደቡብ
ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ እንዲሁም የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የገጠር መሬት
አስተዳደር ሕግ33 ተቋማቱ ከክልሉ የልማት ዓላማዎች እና አቅጣጫዎች ጋር በተጣጣመ
መልኩ የይዞታ መብት እንደሚሰጣቸው ይገልፃል፡፡34 ነገር ግን የትግራይ ክልል የገጠር መሬት
አስተዳደር ሕግ35 ስለ እንዚህ ተቋማት የሚለው ነገር የለም፡፡

ሐ. የግልባለሀብቶች /ኢንቨስተሮች
በመርህ ደረጃ የግል ባለሀብቶች /ኢንቨስተሮች የገጠር መሬት የይዞታ መብት የላቸውም፡፡
ይሁን እንጅ የገጠር መሬት የይዞታ መብት ካላቸው ከመንግስት ወይም ከማንኛውም የገጠር
መሬት ባለይዞታ በኪራይ በገጠር መሬት የመጠቀም መብትን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ይህንም
በተመለከተ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ በገጠር መሬት አስተዳደር ሕጋቸው ደንግገዋል፡፡

2. በውርስ እና በስጦታ
የገጠር መሬት የይዞታ መብት የተሰጠው ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው የይዞታውንም ሆነ
የመጠቀም መብቱን በውርስም ሆነ በስጦታ ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ምንም እንኳ አንድ ሰው
የገጠር መሬት የይዞታም ሆነ የመጠቀም መብቱን በውርስም ሆነ በስጦታ ሊያስተላልፍ

32
የተሻሻለዉ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር130/
1999 (ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር 130/1999 እየተባለ የሚጠራው) አንቀፅ 5(3)

33
የቤንሻንጕል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 85
/2002 (ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር 85/2002 እየተባለ የሚጠራው) አንቀፅ 6(4)(ለ)
34
አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 5(15)(ለ)

35
የተሻሻለዉ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አሰተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር136/
2000 (ከዚህ በኃላ አዋጅ ቁጥር 136/2000 እየተባለ የሚጠራው)

35
የሚችል ቢሆንም ሊከተላቸው የሚገባ መስፈርቶች እንደ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታዎች እና
የመሬት አስተዳደር ሕጎች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ሁሉም ክልሎች ግን የገጠር መሬት የይዞታም
ሆነ የመጠቀም መብትን በውርስ ወይም በስጦታ ማስተላለፍ እንደሚቻል ደንግገዋል፡፡ ስለዚህ
የገጠር መሬት ይዞታ በውርስ ወይም በስጦታ ማግኘት እንደሚቻል እንረዳለን፡፡

2.2 የገጠር መሬት የመጠቀም መብት


የባለቤትነት መብት፣ የይዞታ መብት እና የመጠቀም መብት የተለያዩና ከመጀመሪያው ወደ
መጨረሻው በቅደም ተከተል እየጠበቡ የሚመጡ መብቶች መሆናቸውን ከላይ ተመልክተናል፡፡
ስለዚህም የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው የይዞታ መብቱ እንደተጠበቀ የመጠቀም መብቱን
ብቻ ለይቶ (ለምሳሌ በኪራይ) ለሌላ ሰው ሊያስተላልፍ ይችላል ማለት ነው፡፡ የዚህ አይነት
የመጠቀም መብት ማስተላለፍ ደግሞ መብቱ ለተላለፈለት ሰው የሚሰጠው መብት በመሬት
የመገልገል መብት ብቻ ነው፡፡

2.3 የገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብት የሚታጣባቸው /ቀሪ


የሚሆንባቸው/ሁኔታዎች
የየክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች በየክልሉ የሚኖር ማንኛውም አርሶ አደር በፆታም
ሆነ በሌላ በማናቸውም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግበት የገጠር መሬትን በይዞታ በነፃ የማግኘት
መብት ያለው መሆኑን እንዲሁም ይህ የአርሶ አደሩ የይዞታ መብት የጊዜ ገደብ የሌለው
መሆኑን በመርህ ደረጃ ቢደነግጉም ይህን የይዞታ መብት ቀሪ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ
ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህንም ምክንያቶች ከክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች አንፃር
እንደሚከተለው እንመለከታቸዋለን፡፡

2.3.1. በሕግ
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 11(2) ድንጋጌን
ስንመለከት በገጠር መሬት የመጠቀም መብት የተሰጠው ማንኛውም ሰው የገጠር መሬት
የይዞታና የመጠቀም መብቱን ሊያጣ የሚችለው በዚህ አዋጅ ወይም ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም
በሚወጣ ደንብ በተደነገገው መሠረት እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ በየክልሎች የገጠር መሬት

36
አስተዳደር ህጎች አንድ የይዞታ ባለመብት መብቱን በህግ እንዴት ሊያጣ እንደሚችል
ያስቀመጡትን ድንጋጌ በአምስት ከፍለን እንመለከታለን፡፡

ሀ. ባለይዞታው ከግብርና ስራ ውጭ የተሠማራና ገቢ የሚያገኝበት ቋሚ መተዳደሪያ ያለው


ከሆነ፣
የትግራይ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግ የመሬት ይዞታቸውን ለሌላ አካል አከራይተው
እነርሱ ግን በሌላ ስራ ተሰማርተው የወር ገቢያቸው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በላይ
የሆኑ ይዞታቸው በቀጥታ ይወሰዳል፤ የወር ገቢያቸው ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) እና
ከዚያ በታች የሆኑት ግን በህይወት እስካሉ ድረስ በይዞታቸው የመጠቀም መብት ይኖቸዋል
በማለት ይደነግጋል፡፡36 በእርግጥ የመንግስት ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሠራተኞች
ወርኃዊ ገቢያቸው ከብር 1,000.00 በላይ ቢሆንም ከስራቸው ይልቅ በመሬት የመጠቀም
መብታቸውን ከመረጡ ምርጫቸው እንደሚጠበቅላቸው አስቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ ነጥብ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርን ሕግ ስንመለከት በዝቅተኛ መነሻ
ደመወዝነት እንዲከፈል መንግስት ከወሰነው አማካይ የወር ደመወዝ መጠን ያላነሰ ገቢ
በሚያስገኝ ቋሚ ስራ ተቀጥሮ መገኘት እንዲሁም ከግብርና ስራ ውጭ በሆነና ግብር
በሚያስከፍል የስራ መስክ ተሰማርቶ መገኘት የገጠር መሬት የይዞታ መብት ከሚታጣባቸው
መንገዶች አንዱ መሆኑን አስቀምጧል፡፡37 የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋጅም ZRZ„ bdNB
y¸wsN çñ kGBR W+ bçn |‰ §Y yts¥‰Â ገቢ y¸Ãg"bT ̸ mtÄd¶Ã
ÃlW ማንኛውም ሰው በገጠር mÊT Yø¬ ym-qM mBt$N እንዲያጣ l!wsNbT
እንደሚችል ተደንግጓል፡፡38

ይህ በዚህ እንዳለ የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች በደንብ
ወስነውት ካልሆነ በስተቀር ባለይዞታው ከግብርና ስራ ውጭ የተሰማራና ገቢ የሚያገኝበት ቋሚ
መተዳደሪያ ያለው መሆን አለመሆኑን የይዞታ መብት ቀሪ ሊሆን የሚችልበት መስፈርት
አድርገው አላስቀመጡትም፡፡

አዋጅ ቁጥር 136/1999 አንቀጽ 12(3)(ሠ-ሸ)


36

አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 12(1)(ሀ) እና ማስፈፀሚያ ደንብ ቁጥር 51/1999) አንቀጽ 14(1)(ሀ)(ለ)
37

አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 13(1)(ሀ)


38

37
ለ. ያለበቂ ምክንያት ያለበት ቦታ ሳይታወቅ፣ መሬቱን ሳያከራይ ወይም የሚያስተዳድርለት
ሰው ሳይመደብ ከመኖሪያ ቦታው ባለይዞታው ሲጠፋ
ይህን ነጥብ በተመለከተ በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች ያለውን መስፈርት
ስንመለከት የአማራ ክልል ሕግ ባለይዞታው ምን ያህል ጊዜ ከጠፋ ነው ይዞታውን የሚያጣ
የሚለውን ጉዳይ ለተከታታይ አምስት ዓመት በማለት ሲደነግግ፤ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል
አዋጅ ከሦስት አመት በላይ፤ የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልል ሕጎች ደግሞ ከሁለት ዓመት
በላይ በማለት ደንግገዋል፡፡39 ከዚህ በተለየ ሁኔታ የደቡብ ክልል ሕግ ደግሞ ይህን መስፈርት
የገጠር መሬት ይዞታ ከሚታጣባቸው መስፈርቶች ውስጥ በግልፅ አካቶ የደነገገው
አይመስልም፡፡ ሆኖም በአዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 9(1) ላይ ስለ መሬት ሽግሽግ ሲደነግግ
ባለይዞታዎች በሰፈራ ይም በፍላጎታቸው ከተወሰነ ጊዜ በላይ አካባቢውን ለቀው የቆዩ ከሆነ
ይዞታቸው መሬት አልባ ሆኖ መሬት ለሌላቸው ሰዎች እንደሚከፋፈል ገልፃል፡፡

ሐ. መሬትን ጥቅም ላይ አለማዋል /ጦም ማሳደር/


ይህን መስፈርት ባለይዞታው መሬቱ ከሚገኝበት ቦታ እያለ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት
መሬቱን ጥቅም ላይ አለማዋልን የሚመለከት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የክልሎችን የገጠር መሬት
ሕጎችን ስንመለከት የአማራ ክልል ሕግ ለማንኛውም በዝናብ ለሚለማ የገጠር መሬት ለሶስት
ተከታታይ ዓመታት ፣ በመስኖ ለሚለማ ደግሞ ከአንድ ዓመት በላይ በጥቅም ላይ አለማዋልን
ይዞታ የሚታጣበት መስፈርት አድርጎ የደነገገ ሲሆን የትግራይ ክልል ሕግ ደግሞ በመስኖ
የሚለማን የገጠር መሬት ለሁለት ተከታታይ ዓመት ጥቅም ላይ ያላዋለ አርሶ አደር የይዞታ
መብቱን እንደሚያጣ በመደንገግ በዝናብ የሚለማ የገጠር መሬትን ጥቅም ላይ ያላዋል
ባለይዞታን በተመለከተ በዝምታ አልፎታል፡፡40 የደቡብ ክልል ሕግ ግን መሬትን ጥቅም ላይ
አለማዋልን እንደ መስፈርት ቢያስቀምጠውም ለምን ያህል ጊዜ መሬቱን ጥቅም ላይ ያዋለ

በቅደም ተከተል አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 12(1)(ለ)፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 13(1)(ለ)፣ አዋጅ
39

ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 6(16)፣ አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 12(1)፡፡ የኦሮሚያ አዋጅ ቁጥር 130/1999
አንቀፅ 6(16) የመሬት ይዞታ ከሚታጣባቸው ምክንያቶች አንዱ በመሬቱ ሳይጠቀምበት ሁለት አመት እና ከዚያ
በላይ ከቆየ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ይህ ዲንጋጌ የመሬቱ ባለይዞታ ያለበት ቦታ ሳይታወቅ ይሁን ወይም መሬቱ
በሚገኝበት ቦታ እያለ የሚለውን በግልፅ ስለማያስቀምጥ በዚህ ፁሁፍ በ “ለ” ም ሆነ በ “ሐ” ለተቀመጠው ይዞታ
የሚታጣበት ምክንያት ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡
40
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 12(1)(ሐ)፣ አዋጅ ቁጥር 136/1999 አንቀጽ 23(10)

38
የሚለውን በሕግ ከመወሰን ይልቅ አግባብ ባለው አካል በሚሠጠው የጊዜ ገደብ በማለት
አስቀምቶታል፡፡41

መ. መሬቱን በእንክብካቤ ባለመያዙ መሬቱ ላይ ጉዳት የደረሰ እንደሆነ


ይህን መስፈርት በተመለከተ አምስቱም ክልሎች አንድ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን
በእንክብካቤ ባለመያዙ መሬቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ የመጠቀምም ሆነ የይዞታ መብቱ ቀሪ
እንደሚሆን ያለልዩነት በገጠር መሬት አስተዳደር ሕጋቸው አስቀምጠዋል፡፡42

ሠ. ለሕዝብ ጥቅም ሰባል መሬቱን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ


በአምስቱም ክልሎች የየክልሉ መንግስት ለአንድ አርሶ አደር በይዞታነት የተሰጠውን የገጠር
መሬት ለሕዝብ አገልግሎት ሊያስለቅቅ ይችላል፡፡ በዚህም የመሬት ባለይዞታው የይዞታም ሆነ
የመጠቀም መብቱ ቀሪ ሊሆን እንደሚችል ያለልዩነት ደንግገዋል፡፡43 ከዚሁ ጋር ተያይዞም
በዚህ መንገድ የይዞታ መብቱን ለሚያጣው ሰው መንግስት ተገቢውን ካሣ በቅድሚያ ሊከፍል
እንደሚገባ የሕግ ማዕቀፍ ተሰርቶለታል፡፡

2.3.2 በባላይዞታው ፈቃድ

አንድ የገጠር መሬት በባለይዞታ ከሚኖርበት ቀበሌ ከሚገኘው መሬትን የሚያስተዳድር አካል
በድልድል በነፃ የገጠር መሬት የማግኘት መብት እንዳለው ሁሉ ይህን የይዞታ መብቱን በራሱ
ፈቃድ መተውን መሬቱን ለሰጠው አካል ያሳወቀ እንደሆነ የይዞታ መብቱን ሊያጣ ይችላል፡፡
በመሆኑም አምስቱም ክልሎች በገጠር መሬት አስተዳደር ህጋቸው የገጠር መሬት የይዞታና
የመጠቀም መብት ቀሪ ከሚሆንባቸው መንገዶች አንዱ በራስ ፈቃድ መተው መሆኑን
ደንግገዋል፡፡44

41
አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 13(13)
42
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 12(1)(መ)፣ አዋጅ ቁጥር 136/1999 አንቀጽ 14(1)(2)፣ አዋጅ ቁጥር
110/1999 አንቀፅ 13(12)፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 6(16)፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 13(1)(መ)
43
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 28፣ አዋጅ ቁጥር 136/1999 አንቀጽ 21፣ አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ
7(3)፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 6(10)፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 33
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 12(1)(ሠ)፣ አዋጅ ቁጥር 136/1999 አንቀጽ 14(4)(5)፣ አዋጅ ቁጥር
44

110/1999 አንቀፅ 10(4)፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 6(16)፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 13(1)(ሠ)

39
ከላይ በተገለፁት ሁኔታዎች አንድ አርሶ አደር የመሬት ባለይዞታነትና በመሬት የመጠቀም
መብቱ በህግም ሆነ በፈቃድ ቀሪ ሲሆን የቀበሌው አስተዳደር መሬቱን በመረከብ መሬት
ለሌላቸው በሽግሽግ እንደሚሰጥ ተደግጓል፡፡ የህጉ ይዘት ከላይ የተገለፀው ቢሆንም በተግባር
በመሬት የመጠቀም መብት ቀሪ የሚሆንበት የጊዜ ገደብ /lapse of land use right/ ከይርጋ የጊዜ
ገደብ /period of limitation/ጋር ያላቸው አንድነትና ልዩነት በአግባቡ ሣይጤን ውሣኔ
የሚሰጥበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ስለሆነም የእርሻ መሬታቸውን በማረስ ምርት ለማካፈል
በስምምነት መሬቱን ከሁለት ዓመት በላይ ሲያርሱ የኖሩ ሰዎች፣ መሬቱን በአደራ ጠባቂነት
የያዙ ሰዎች የመሬቱ ባለይዞታ ከሁለት ዓመት በላይ የለቀቀውና ያልያዘው በመሆኑ ክሱ
በይርጋ ይታገዳል የሚል ክርክር የሚያቀርቡ መሆኑና ፍ/ቤቶችም መብቱ ቀሪ የሚሆንበትን
የጊዜ ዘመን እንደ ይርጋ ዘመን በመቁጠር ውሣኔ የሚሰጡ ስለመሆኑ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
በመሆኑም በተለይ ባለይዞታው በፈቃዱና በፍላጎቱ አካባቢውን ለቋል የሚባለው በምን ሁኔታ
ነው? ይህንን ነጥብ በባለ ይዞታዉ ላይ መከራከሪያ አድርጎ የሚያነሣው መሬት የማስተዳደርና
በማሸጋሸግ ለሌላ አርሶአደር የመስጠት ሥልጣን ያለው የመንግስት አካል ነው ወይስ
ማናቸውም የይዞታ መሬቴን አላገባብ ስለያዘ ይልቀቅልኝ የሚል ክስ የቀረበበት ሰው የሚሉት
ነጥቦች መፍትሄ የሚፈለጉ ናችዉ፡፡

ሌላው ከላይ እንደተመለከትነው በፌደራልና በክልሎች በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የህግ


ማዕቀፎች ለይዞታ መብት የሚሰጠው ጥበቃ በ1952 ዓ.ም የወጣው የፍትሐብሔር ህግ የይዞታ
መብትን ለማስከበር ከሚሰጠው ጥበቃ እጅግ በጣም የተለየና ሰፊ ነዉ፡፡ ይዞታዉን ለማስከበር
አንድ አርሶ አደር በስንት ጊዜ ውስጥ ክስ ማቅረብ እንዳለበት የይርጋ የጊዜ ገደብ ድንጋጌዎች
በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጆች ውስጥ አልተደነገጉም፡፡ በተግባራዊ አፈፃፀም
ይዞታን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ በፍ/ር/ህ/ቁ 1149 መሠረት በሁለት ዓመት አልቀረበም
የሚልና ሌሎች በፍትሐብሔር ህጉ ስለይዞታ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በመጥቀስና በመተርጎም
ፍ/ቤቶች ውሣኔ የሚሰጡ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

በመሆኑም የዚህ አይነት የህግ አተረጓጎም የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ለመሬት ይዞታ መብት ለመስጠት የሚፈለገውን ጥበቃና ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስች
አይመስልም፡፡ በአጠቃላይ የገጠር መሬት ይዞታን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ የሚያስፈልገው

40
የይርጋ የጊዜ ገደብ ተለይቶና ግልፅ ሆኖ መደንገግና በዚህ መነሻ የሚፈጥሩ ክርክሮች ለመቀነስ
ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡

2.4 የገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብቶች የሚተላለፉባቸው መንገዶች

የኢፌዴሪ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/97 የገጠር
መሬት መብት አተገባበር ለክልሎች እንደ መመሪያ የሚያገለግል ሕግ እንደሆነና ክልሎችም
መሬትን የሚያስተዳድሩት ይህንን አዋጅ መሠረት አድርገው መሆን እንዳለበት ከዚህ በፊት
በነበረው ምዕራፍ ተመልክተናል፡፡ አዋጅ ቁጥር 456/97 አንድ የመሬት ባለይዞታ ያሉትን
መብቶች በበቂ ሁኔታ ባይዘረዝርም መጠቀም፣ ማከራየትና ማውረስ እንደሚችል ግን በጥቅሉ
ይጠቁማል፡፡ በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች በዝርዝር ሲደነገጉ ሊጠቡም ሆነ
ሊሠፉ የሚችሉ እነዚህ መብቶች ናቸው፡፡ የገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብቶች
የሚተላለፉባቸውን መንገዶች ከክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች አንፃር
እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

2.4.1 ውርስ

የማውረስ መብት መከበር የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን ለመንከባከብ፣ አስፈላጊ የሆነውን
የጉልበትና የገንዘብ ወጭ አውጥቶ መሬቱን ለማልማትና አካባቢን በአግባቡ ለመጠበቅ
ምክንያትና ፍላጎት እንዲኖረው ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለይዞታው
ተወላጆች ከባለይዞታው ጋር ባሉበት ጊዜም ሆነ ራሳቸውን ከቻሉ በኋላ ወደፊት መሬቱ ለእኔ
ይተርፋል በሚል መሬቱ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ እና ጥበቃ ለማድረግ የሚያስፈልገውን
እገዛ እንዲያበረክቱ ሊገፋፋቸው ይችላል፡፡ ለአዲሱ ትውልድ ሊሰጥ የሚችል ትርፍ መሬት
በሌለበት ሁኔታ ውርስ መሬት ከወላጆች ወይም ሌሎች ቤተሰቦች ለተወላጆች የሚሰጥበት ዋና
መንገድ በመሆኑ የገጠር መሬትን ማውረስ እንደማንኛውም ንብረት በአውራሹ ፈቃድ ላይ
ተመስርቶ በሕግ ሊጠበቅ የሚገባው መብት ነው፡፡ ሆኖም የመሬት ውርስ እንደማንኛውም
ንብረት በፍ/ር ህጉ ባለው የአወራረስ ዘዴ እና ቅደምተከተል የሚከናወን ሳይሆን መንግስት
በሚከተለው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ በፌደራል መንግስቱ እና በክልሎች በወጡት
አዋጆች መሠረት የሚከናወን ነው፡፡ ይኸውም የመሬት ውርስ እራሱን የቻለ የፖሊሲ አቅጣጫ
የሚከተልና ከፍትሐብሔር ህጉ የውርስ ስርዓት አንፃር በርካታ ልዩነቶች ያሉት መሆኑ
በቅድሚያ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት፡፡

41
የመሬት ይዞታና በመሬት የመጠቀም መብትን በውርስ ማስተላለፍ እንደሚቻል የፌዴራሉ
መንግሥት ባወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 8 ላይ በግልጽ የተደነገገ ከመሆኑም ባሻገር
አምስቱም ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ባወጡአቸው አዋጆች ውስጥ ይህ መብት በግልጽ
ተደንግጓል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 6(1) መሠረት አርሶ አደሮች የይዞታ መብታቸውን
ለቤተሰብ አባላት ማስተላለፍ እንደሚችሉ የደነገገ ሲሆን በአዋጁ አንቀጽ 9(1) መሠረት
ለቤተሰብ አባላት በውርስ መልክ ማስተላለፍ የሚቻለው በህግ መሠረት ውርስ የማግኘት
መብት ለሚኖራቸው የቤተሰቡ አባላት እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ የአወራረስ ቅደም ተከተሉን
በተመለከተም በተለይ ኑሮአቸው ከመሬቱ ላይ በሚገኝ ገቢ ለተመሰረተ ወይም ሌላ ምንም

ዓይነት ገቢ ለሌላቸው የቤተሰቡ አባላት እና ወራሾች በቅድሚያ የመውረስ መብት እንደሚሰጥ


አንቀፅ 9(2) ይደነግጋል፡፡

የትግራይ ክልል ህግ አንቀፅ 17 የእርሻ መሬት ውርስን በተመለከተ አርሶ አደሩ ሲሞት መሬት
የሌለው ልጅ ሊወርስ እንደሚችል፤ ሟች ልጅ ከሌለው መሬት የሌለው ወላጅ እንደዚሁም
መሬት የሌለው ወላጅ ከሌለ መሬት የሌላቸዉ የሟች የልጅ ልጆች ሊወርሱ እንደሚችሉ
ይደነግጋል፡፡ ይህ ህግ የራሱ የመሬት ይዞታ ያለው ሰው፣ ከግብርና ውጭ ኑሮውን የለወጠ
ሰው (ከጎጆ መውጫ በስተቀር) እና በከተማ የሚኖሩ ልጆች የገጠር መሬት የመውረስ መብት
የሌላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በትግራይ ክልል ህግ የፌደራሉ ህግ(አዋጅ ቁጥር 456/1997)
የቤተሰብ አባል ለሚለው ሀረግ የሰጠው ትርጉም ያላካተተው በመሆኑ ከባለይዞታው ቤት ያደገ
ሰው የእርሻ መሬት የሚያገኘው በውርስ ሣይሆን የሟች መሬት ወራሽ የሌለው ሲሆን
በሽግሽግ ቅድሚያ ተሰጥቶት ነው፡፡45

የደቡብ ክልል ባወጣው አዋጅ በአንቀጽ 8(5) መሠረት ማንኛውም ባለይዞታ በገጠር መሬት
የመጠቀም መብቱን ለቤተሰቡ አባለት የማውረስ መብት አለው፡፡ የቤተሰብ አባል ማለት
የመሬት ባለይዞታውን የመተዳደሪያ ገቢ በመጋራት በቋሚነት አብሮ የሚኖር ማንኛወም ሰው
እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2(7) ተተርጉሟል፡፡ የአወራረስ ቅደም ተከተል ምን ይመስላል የሚለው
በማስፈፀሚያ ደንቡ ተቀምጦ ካልሆነ በስተቀር በአዋጁ በግልፅ አልተቀመጠም፡፡

አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 17(6)


45

42
የአማራ ክልል ህግ አንቀጽ 16 ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታና የመጠቀም
መብቱን በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በግብርና ሥራ መተዳዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም
አርሶ አደር በኑዛዜ ማውረስ የሚቻል መሆኑን፤ ኑዛዜው አካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቹን
የማይነቅልና የትዳር ጓደኛውን መብት የማይነካ መሆን እንዳለበት ደንግጓል፡፡ ሟች ኑዛዜ
ሳይተው የሞተ እንደሆነ የይዞታ መብቱ በግብርና ስራ ለሚተዳደር ወይም በግብርና ሥራ
መተዳደር ለሚፈልጉ የሟች ልጅ ወይም ቤተሰብ ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣ ደንብ
መሰረት በቅድም ተከተል ይተላለፋል፡፡46 ነገር ግን ሳይናዘዝ የሞተው ሰው በክልሉ ውስጥ
የሚኖርና በግብርና ስራ የሚተዳደር ወይም ለመተዳደር የሚፈልግ ልጅ ወይም ቤተሰብ የሌለው
እንደሆነ ወላጆቹ በክልሉ ውስጥ ኑዋሪዎች ሆነው በግብርና ስራ የሚተዳደሩ ወይም ለመተዳደር
የሚፈልጉ ከሆነና አስቀድሞ የያዙት የገጠር መሬት ይዞታ ከከፍተኛው የይዞታ መጠን በታች
መሆኑ ከታወቀ የሟችን የመሬት ይዞታ የመውረስ መብት ይኖራቸዋል፡፡ ሆኖም የይዞታና
የመጠቀም መብቱን ለሟች ወላጆች የሚተላለፍ ቢሆንም የሟች የትዳር ጓደኛ መሬቱ
በሚገኝበት ቀበሌ ውስጥ በህይወት የሚኖር/የምትኖር ከሆነ ሌላ ጋብቻ እስከሚመሰረት ወይም
ካላገባ/ች በመሬቱ የመጠቀም መብቱን አያስቀርበትም/ባትም፡፡47

የቤኒሻንጉል ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 16(1) መሰረት የገጠር መሬት የተሰጠው አርሶ አደር
የይዞታ መብቱን በውርስ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ በተለይ በአዋጁ አንቀጽ 17 መሰረት የመሬት
ይዞታንና የመጠቀምን መብት በውርስ ማስተላለፍ የሚቻልባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከአማራ
ክልል ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ተዘርዝረዋል፡፡

በአጠቃላይ የፌዴራል ህጉም ሆነ የክልሎች ህግ አንድ አርሶ አደር የይዞታ መሬቱን ለቤተሰብ
አባላት የማውረስ መብት ያለው መሆኑን ደንግጓል፡፡ የቤተሰብ አባል ማነው የሚለውን ነጥብ
በተመለከተ የፌደራል ህጉ የቤተሰብ አባል ማለት የይዞታ ባለመብቱን መተዳደርያ ገቢ በዘላቂነት
በመጋራት አብሮ የሚኖር ነዉ በማለት ተርጉሞታል፡፡ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች
በክልሎች የወጡ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ህግጋት ትርጉሙን በህግ ማቀፋቸዉ
አካተዋል፡፡ የፌደራል ህግ ለቤተሰብ አባል የማውረሱን መብት አለው የሚል ቢሆንም አርሶ አደሩ

የአዋጅ ቁጥር 133/1998 ማስፈፀሚያ ደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀፅ 11(7) ላይ በዝርዝር ቅደምተከተሉ
46

ተቀምጧል፡፡ ይኸውም በቅድሚያ የሟች አካለመጠን ያላደረሱ ልጆች፣ ልጅ ከሌለ የቤተሰብ አባላት፤ ቀጥሎመሬት
የሌላቸው አካለመጠን ያደረሱ ልጆች ወይም የቤተሰብ አባላት፤ቀጥሎ መሬት ቢኖራቸውም አካለመጠን ያደረሱ
ልጆች፤በመጨረሻም ወላጆች ይወርሳሉ፡፡
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 16(5) እና (6)
47

43
በኑዛዜ የእርሻ መሬቱን የማውረስ መብት ያለው መሆኑን ወይም አለመሆኑን በግልፅ
አይደነግግም፡፡ የፌደራል ህጉ ድንጋጌ ጠቅላላ አገላለፅ የተጠቀመ ቢሆንም የክልል የህግ ማዕቀፍ
የእርሻ መሬት በውርስ ስለማስተላለፍ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

የፌዴራሉ ሕግ አርሶ አደሩ በመሬት የመጠቀም መብቱን በውርስ ለቤተሠቡ ማውረስ


እንደሚችል የደነገገና የቤተሠብ አባል ለሚለው ቃል ትርጓሜ የሰጠ ቢሆንም የክልል የህግ
ማዕቀፎች የፌደራል መንግስት የቤተሰብ አባል በሚለው ትርጉም ለሚሸፈኑም ሆነ ለማይሸፈኑ
ሰዎች በመሬት የመጠቀም መብቱን ሊያወርስ እንደሚችል ይደነግጋሉ፡፡ ይህ ልዩነት አከራካሪ
ሆኖ በሚመጣበትና ህጉን መተርጎም አስፈላጊ በሚሆንበት ሠዓት የትኛው ገዥ መሆን አለበት
የሚለው ጥያቄ እንዲነሣ የሚያስገድድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ሌላው የኦሮሚያ ህግ በህግ የሚወርሱ መብት ያላቸው ከማለት ውጭ በኑዛዜ በከፊል ያለ ኑዛዜ
የሚከናወን ስለመሆኑም አይገልፅም፡፡ የደቡብ ክልል ህግም በኑዛዜ መሬት ማውረስ የሚቻል
መሆን አለመሆኑን አይደነግግም፡፡ በእነዚህ ክልሎች በኑዛዜ መሬትን ማውረስ ይቻላል ወይስ
አይቻልም የሚለዉ ነጥብ መታየት አለበት፡፡

የመሬት ይዞታና የመጠቀም መብት የማውረስ መብት በተመለከተ የሚፈጠረው ሌላው ችግር
የሟች አርሶ አደር ወራሽ ነን የሚሉ ሰዎች ወራሽ መሆናቸውን በፍ/ቤት ካረጋገጡ በኋላ በስንት
ጊዜ ውስጥ የሟች ይዞታን የያዘው ሰው እንዲለቅላቸው ወይም እንዲያስተላልፍላቸው መጠየቅ
አለባቸው የሚለው ነው፡፡ መሬቱን የያዘው ሰው የይርጋ መከራከሪያ አንስቶ መከራከርና
መቃወም ይቻላል ወይ? ፍ/ቤቶችስ የሟች የእርሻ መሬት በውርስ ይተላለፍልኝ የሚሉ ሰዎችን
ጉዳይ የይርጋ ዘመን ለመወሰን የፍ/ር/ህ/ቁ 1000(1) እና (2) ወይም የፍ/ር/ህ/ቁ 1677 እና
1845 በመጥቀስ መወሰናቸው ተገቢነት አለው ወይስ የለውም የሚሉት ነጥቦች አከራካሪ
መሆናቸውን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ከደቡብ ክልል የተነሳውና በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች
ክርክር የተደረገበት በመጨረሻም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር
38237 (ቅፅ 9) ላይ የአባቴን የውርስ መሬት ሊያካፍሉኝ ይገባል በማለት ወንድሞቹን የከሰሰው
ግለሰብ በሶስት ዓመት ይርጋ የታገደ ስለሆነ መሬቱ አይገባህም በማለት የተወሰነ መሆኑን
መመልከት ይቻላል፡፡

44
2.4.2. ስጦታ

ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የመሬት መጠቀም መብቱን ለቤተሰቡ አባል በስጦታ
የማስተላለፍ መብት ያለው መሆኑ በፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ
ተደንግጓል፡፡ በመሬት የይዞታንና የመጠቀም መብትን በስጦታ ማስተላለፍ እንደሚቻል
በአምስቱም ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የገጠር መሬት ህጎች ውስጥ ተካትቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት ህግ አንቀፅ 9(5) ላይ መሬትን በስጦታ ማስተላለፍ የተፈቀደ
ሲሆን የሚተላለፈው ይዞታው ሳይሆን በመሬቱ ላይ ያለው የይዞታ መብት ነው፡፡ ከዚህም በላይ
የይዞታ መብቱ የሚተላለፈው ኑሮአቸው በመሬቱ ላይ ለተመሰረተው ወይም ሌላ ምንም
ዓይነት ገቢ ለሌላቸው ወይም መሬት አልባ ለሆኑ ልጆች ነው፡፡

በትግራይ ክልል የገጠር መሬት ህግ አንቀፅ 5(2) መሰረት የገጠር መሬት የመጠቀም መብት
የተሰጠው አርሶ አደር ከቤተሰቡ በስጦታ የገጠር መሬት ይዞታ ማግኘት ይችላል፡፡ ነገር ግን
ስጦታው የሚፈቀደው የገጠር መሬት ይዞታ ለሌለው ልጅ ወይም ወላጅ ብቻ መሆኑን
ይደነግጋል፡፡

በደቡብ ክልል የገጠር መሬት ህግ አንቀፅ 5(11) መሰረት ማንኛውም አርሶ አደር ቤተሰብ አባል
ከቤተሰቡ በስጦታ የገጠር መሬት ሊያገኝ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ አዋጁ ላይ ምንም እንኳን
የመሬት ባለይዞታ የሆነው ሰው መሬቱን በቀጥታ በስጦታ ማስተላለፍ ይችላል ባይልም ስጦታ
አንዱ የገጠር መሬት የሚገኝበት መንገድ በመሆኑ የመሬት ባለይዞታ የሆነው ሰው መሬቱን
በስጦታ ማስተላለፍ እንደሚችል ያመለክታል፡፡

የአማራ ክልል የገጠር መሬት ህግ አንቀፅ 17 የመሬት ይዞታና የመጠቀም መብት በስጦታ
ሊተላለፍ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ደንግጓል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. ስጦታ ተቀባዩ በግብርና ስራ የሚተዳደር ወይም ለመተዳደር የሚፈልግ የክልሉ ነዋሪ


ሆኖ ምንም ዓይነት መሬት የሌለው ወይም በያዘው መሬት አነስተኛነት ምክንያት ሌላ መሬት
እየተከራየ የሚያርስ ልጅ ወይም የልጅ ልጅ ወይም ሌላ የቤተሰቡ አባል፡፡

ለ. ስጦታ ተቀባዩ ስጦታው ከመደረጉ በፊት ለነበሩ 3 ተከታታይ ዓመታት የስጦታ


አድራጊውን መሬት እያረሰ ስጦታ አድራጊውን ሲጦር መቆየቱ የታወቀ ከሆነ፡፡

45
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገጠር መሬት ህግ አንቀጽ 18 መሰረት የይዞታንም ሆነ የመጠቀም
መብትን በስጦታ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን በአንቀጽ 18(2) መሰረት የይዞታ መብቱን
በቋሚነት በስጦታ የሚያስተላልፈው በግብርና ስራ መተዳደር ለሚፈልግ የቤተሰብ አባል ነው፡፡

ከላይ የተገለፀው የፌደራል ህግና የአምስት ክልል የህግ ማዕቀፎች የመሬት ባለ ይዞታ
ተጠቃሚ የሆነ ሰው የይዞታ መሬቱን በስጦታ የሚሰጥበት ዝርዝር ሥርአት የሚደነገጉ
አይደሉም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመሬት መጠቀም መብቱን ለዘለቄታው ወይም ለተወሰነ ጊዜ
ብቻ ሊሰጥ የሚችል መሆኑን ወይም አለመሆኑን የመሬት የመጠቀም መብቱን በስጦታ
ሲያስተላልፍ ሁኔታ ማስቀመጥ የሚችል መሆን አለመሆኑና የስጦታ ውሉን ለማፍረስ
የሚችልበት ሁኔታ መኖር አለመኖሩን የሚዘረዝሩ አይደሉም፡፡

ስጦታ ሰጭውና ተቀባዩ በህይወት እያሉ ተፈፃሚነት ላላቸው ሁኔታዎች በሚሆንበት አግባብ
የሚፈፅም (donation intervavo) ወይም ሰጪው ሲሞት ስጦታው ተፈፃሚ በሚሆንበት
አግባብ የሚደረግ ‘’donation mortis causa’’ የሚደረግ ሊሆን ይችላል፡፡ በአገራችን ሟች
ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ ይሆናሉ የተባሉ ስጦታዎች ስለ ኑዛዜ በተደነገጉት ድንጋጌዎች የሚታይ
መሆኑ የፍ/ር/ህ/ቁ 2428 ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ ሟች ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን መሆኑን
ገልፆ በመሬት የመጠቀም መብቱን በስጦታ ውል አንድ አርሶ አደር ቢሰጥ ህጋዊ ውጤት
አለው ወይስ የለዉም፤ አርሶ አደሩ ከሞተ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ስጦታ ቢሰጥ የፍትሐብሔር
ህጉ ስለኑዛዜ የደነገጋቸው ድንጋጌዎች ለጉዳዩ አግባብነት አላቸው ወይስ የላቸውም የሚሉትን
ጥያቄዎች የፌደራሉም ሆነ የክልሎች ህግ ማዕቀፎች አይመልሱም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሟች በህይወት እያለ የሚደረግ ስጦታ ምንም አይነት አገልግሎት ወይም
ጥቅም ሰጪው ሣያገኝና ሣይፈልግ በነፃ የሚሰጠው Gratutious donation ሲሆን ሁለተኛው
ሰጪ ከስጦታ ተቀባዩ በአይነት ወይም በገንዘብ ጥቅም አግኝቶ የሚያደርገው onorious
donation የሚባለው ስጦታ ነው፡፡ ሦስተኛው ለአገልግሎት የሚከፈል renumrative donation
ነዉ፡፡ በፍ/ር ህጉ ስጦታ ሰጭው ከስጦታ ተቀባይ ችሮታ ለማድረግ በማሰብ ከንብረቶቹ አንዱን
የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት እንደሆነ በፍ/ር/ሕ/ቁ 2427 ትርጉም
ተሰጥቶታል፡፡ የአማራና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ህግ አንድ ሰው ለስጦታ ሰጭው ለሶስት
አመት በተከታታይ የእርሻ ወይም ሌላሥራ እየሰራ ከጦረው የመሬቱ ባለይዞታ በመሬት
የመጠቀም መብቱን በስጦታ ሊያስተላልፍለት የሚችል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ይህም ስጦታ

46
በፍ/ር ህጉ ከተሰጠው ትርጓሜ ሰፋ ባለሀሳብ renumrative donation-ን የሚፈቅድ መሆኑን
እንመለከታለን፡፡

ስለሆነም በሌሎቹ ክልሎች በመሬት የመጠቀም መብት በስጦታ የሚተላለፈው ከላይ


ከገለፅናቸው ከሶስቱ ስጦታ አይነቶች አንደኛውን በመከተል ነው ወይስ የፍትሐብሔር ህጉ
ዕውቅና የተሰጠውን Gratutious donation ብቻ በመጠቀም ነው? ሰጭው በመሬት የመጠቀም
መብቱን ሁኔታ ባለበት ስጦታ ሊያስተላልፍ ይችላል ወይስ አይችልም? ሰጭው በመሬት
የመጠቀም መብቱን በስጦታ ካስተላለፈ በኋላ ውሉ የሚፈርስባቸው ምክንያቶች አሉ?
የሚሉት ነጥቦች በገጠር መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ህግ ማዕቀፎች በግልፅና በዝርዝር
የተደነገጉ አይደለም፡፡ በመሆኑም የገጠር መሬት ባለ ይዞታነትንና የመጠቀም መብትን በስጦታ
ለማስተላለፍ የሚቻልበትን ዝርዝር ሥርዓት መደንገግና በዚህ ረገድ ያሉ ችግሮችን በማጥናት
ችግሮችን መፍታት በሚቻልበት አግባብ የህግ ማዕቀፎቹን ማሻሻልን ይጠይቃል፡፡

2.4.3 ኪራይ

የገጠር መሬት ባለይዞታ የመጠቀም መብቱን በኪራይ ማስተላለፍን በተመለከተ በክልሎች


የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች መካከል በአብዛኛው ተመሳሳይነት ቢኖርም መሬት
በኪራይ ሊሰጥበት የሚችለውን ከፍተኛ ዘመንና ሊከራይ የሚችለውን መሬት መጠን
በተመለከተ ግን ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ በመሬት የመጠቀም መብትን የማከራየት መብት በሕግ
መጠበቅ የሚገባው የተከራዮችን መብት ለመጠበቅ ብቻ ተብሎ ሳይሆን የመሬት ባለይዞታዎች
ያላቸው የመጠቀም መብት አካል ስለሆነ ነው፡፡

በኦሮሚያና በትግራይ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች መሠረት ማከራየት
የሚቻለው አንድ ሰው ካለው የይዞታ መሬት ከግማሽ ያልበለጠውን ብቻ ነው፡፡48 የሚከራየውን
የይዞታ መሬት መጠን በአከራዩ በመወሰን ፋንታ በመሬት አስተዳደር ሕጉ የተወሰነ ነው፡፡
የደቡብ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ ደግሞ መሬትን ማከራየት
የሚቻለው ባለይዞታውን በማያፈናቅል መልኩ መሆን ይኖርበታል በማለት ባለይዞታው ያለውን
የማከራየት መብት በተዘዋዋሪ ሁኔታ የይዞታ መብትን በሙሉ ማከራየት እንደማይቻል
በመደንገግ ገደብን ያስቀምጣል፡፡

48
አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 10(1) እና አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 6(1)

47
የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ
ማንኛውም ሰው የመጠቀም መብቱን ለማንኛውም ሰው በኪራይ ማስተላለፍ ይችላል በማለት
የደነገገ በመሆኑ49 በኪራይ ሊሰጥ የሚችለው የመሬት መጠን ላይ ገደብ አለማድረጉን
እንገነዘባለን፡፡ ይህም ማለት በዚህ ሕግ መሠረት አንድ የገጠር መሬት ባለይዞታ ቢፈልግ
በከፊል አለዚያም በሙሉ መሬቱን ሊያከራይ ይችላል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሕጉ
ባለይዞታው መሬቱን ሊያከራይ ሲፈልግ ምን ያህል የመሬት መጠን ማከራየት እንዳለበት ራሱ
እንዲወስን መብቱን ጠብቆለታል ማለት ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግም
¥N¾WM ymÊT ÆlYø¬ አርሶ አደር ym-qM mBt$N l¥N¾WM sW bk!‰Y
¥St§lF XNd¸CL YdnGUL፡፡50 ከዚህ ጋር ተያይዞም አርሶ አደሮች መሬት በማከራየት
መብታቸው ውስጥ ከይዞታቸው ሊያከራዩ የሚችሉት የመሬት መጠን፣ የኪራይ ውልና
አይነት፣ የኪራይ ዘመን፣ የለምነት ደረጃ እና ዝርዝር መብትና ግዴታዎችን እንዲሁም ሌሎች
ተዛማጅነት ያላቸው ጉዳዮች መካተታቸውን በሚመለከተው አካል መረጋገጥ አለበት፤ ዝርዝር
አፈጻጻሙ በሚወጣው ደንብ አንደሚወሰን ይደነግጋል፡፡51

ከላይ ከጠቀስናቸው የክልል ሕጎች ውስጥ የተጣሉትን ገደቦች በተመለከተ ሁለት አይነት
አመለካከቶች አሉ፡፡ አንደኛው የገጠር መሬት መብትን በተመለከተ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት
በባለይዞታዎች ላይ የተቀመጠው ክልከላ በመሸጥ ወይም በመለዋወጥ ማስተላለፍ ብቻ ቢሆንም
ባለይዞታው በሚያከራየው የመሬት መጠን ላይ የክልል ሕጎች ሊለያዩ የቻሉበት ምክንያት
የፌዴራሉ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ አንቀጽ 8(1) አርሶ አደሮች “እነሱን
በማያፈነቅል መልኩ” የይዞታ መሬታቸውን ማከራየት ይችላሉ በሚለው ድንጋጌ መሰረት አንድ
የመሬት ባለይዞታ መሬቱን በሙሉ ማከራየት አይችልም የሚል መልዕክት ያዘለ በመሆኑ
ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው መሬቱን በሚያከራበት ጊዜ የሚከራየው የመጠቀም መብቱ ብቻ
በመሆኑ የይዞታ መብቱ የሚቀረው ከእርሱ ጋር ቢሆንም መሬቱን ሙሉ ለሙሉ ለረጅም
አመታት ከአከራየ በተዘዋዋሪ መልኩ ከይዞታ መፈናቀል ሊያስከተል ይችላል የሚል ነው፡፡

49
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 18(1)
50
አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 19(4)
51
ዝኒከማሁ አንቀጽ 19(3)

48
ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ አንድ የመሬት ባለይዞታ መሬቱን የሚያከራየው ለፈለገው ሰው ነው፡፡
ማከራየት ሽያጭ ወይም ልውውጥ ባለመሆኑ ደግሞ አንድ ሰው የይዞታ መብቱን እንደጠበቀ
መሬቱን በሙሉ ቢያከራይ ከሕጉ ጋር የሚቃረንበት ሁኔታ ስለሌለ በኪራይ የሚሠጠው መሬት
መጠን መወሰን ያለበት በአከራዩ በራሱ እንጅ በክልል የመሬት አስተዳደር ሕግ መሆን
የለበትም፡፡ በገጠር መሬት የመጠቀም መብት ላይ የሚከራየውን መሬት መጠን በተመለከተ
ገደብ የተደረገው ባለይዞታዎች ከመሬታቸው እንዳይፈናቀሉ ለማድረግ ነው የሚባል ቢሆን
እንኳን ከመሬት መፈናቀል የሚከተለው ይዞታ ሲተላለፍ እንጅ የመጠቀም መብት ለተወሰነ
ጊዜ በኪራይ ሲሰጥ አይደለም፡፡ ምክንያቱም መፈናቀል ማለት የይዞታ መብትን ማጣት ማለት
እንጅ የመጠቀም መብትን ለተወሰነ ጊዜ ማቋረጥ ማለት ባለመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም የገጠር
መሬት ይዞታን በሙሉ ማከራየት እንደማይቻል በሕግ በመደንገግ በባለይዞታዎች የማከራየት
መብት ላይ ገደብ ማድረጉ በቂ ምክንያት ያለው ሆኖ አይታይም የሚል ነው፡፡

የመሬት መከራየት መሠረቱ የአከራይና የተከራይ ስምምነት ቢሆንም የኪራይ ስምምነቱን


ከፍተኛ የኪራይ ዘመን በሕግ መወሰኑ ከኪራይ ዘላለማዊ አለመሆንና ከውልም በጊዜ የተወሰነ
መሆን ምክንያት የሚመነጭ ከመሆኑም በላይ ከውል ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን
ለመፍታትም አስፈላጊ ነው፡፡ እንዲሁም በኪራይ ሰበብ መሬት እንዳይሸጥ ይከለክላል፡፡ ስለሆነም
የመሬት የኪራይ ከፍተኛ ዘመንን በሕግ መወሰኑ የንብረት መብትን እንደሚያጠብ ተደርጎ
ሊወሰድ የሚችል አይደለም፡፡

የገጠር መሬት የሚከራይበት ከፍተኛ ዘመን በክልሎች ሕግ እንደሚወሰን በተደነገገው መሠረት


በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልሎች እንደ ቅደም ተከተላቸው 20
ዓመት፣ 15 ዓመት፣ 10 ዓመት፣ 25 ዓመት ነው፡፡ የቤንሻንጉል ጉምዝ ግን ከላይ

እንደተመለከትነው የኪራይ ዘመን በደንብ እንደሚወሰን ተመልክቷል፡፡ ከፍተኛው የኪራይ ዘመን

ሊለያይ የቻለበት ምክንያት የመሬት አስተዳደሩ በክልሎች ልዩ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ


የሚተገበር ስለሆነ አንድ አይነት እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ከፍተኛ የመሬት
ኪራይ ውል ዘመን ከአማራ ክልል በስተቀር በሌሎች ያለው ተፈፃሚነት መሬቱ ለአልሚ
ባለሃብት በሚከራይበት ጊዜ ብቻ ሲሆን መሬቱ ልማዳዊ የአስተራረስ ዘዴን ለሚጠቀም አርሶ
አደር በሚከራይበት ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆነው ከፍተኛ የውል ዘመን ግን ከላይ ከተጠቀሰው
እጅግ ያነሰ ነው፡፡ የአማራ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ 25 ዓመት ከፍተኛ

49
የመሬት ኪራይ ውል ዘመኑ ለማንኛውም ተከራይ በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈፃሚነት
እንደሚኖረው ደንግጓል፡፡

የመሬት ኪራይ ውል ከፍተኛ ዘመን በሕጉ መደንገግ ያስፈለገበት የውልን ዘለዓለማዊ ሊሆን
አለመቻል መሠረት በማድረግና ተዋዋዮች በውላቸው የጊዜ ገደብ ባላስቀመጡበት ጊዜ የውሉን
ክፍተት ለመሙላት እንጅ በተለይ የመሬት ኪራይን በተመለከተ የተከራዩን ማንነት መሠረት
በማድረግ የሚሆንበት ምክንያት የለም፡፡ ተከራዩ ማንም ይሁን ማን የገጠር መሬት ኪራይ
ዘመን ረጅም መሆንን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በመሬቱ ላይ ተከራዩ አስፈላጊውን ወጭ አድርጎ
በማልማት በቂ ገቢ ለማግኘት ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ምክንያት ደግሞ ተከራይ
ለሆነው አልሚ ባለሀብትም ሆነ ልማዳዊ የአስተራረስ ዘዴ ለሚጠቀመው ተከራይ አርሶ አደር
እኩል ተፈፃሚነት አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለማንም ተከራይ የዘመኑ ረጅም መሆን ተከራዩ
የመሬቱን ወደፊትም ረዘም ባለ ጊዜ እንደሚጠቀምበት በማመን እንዲንከባከበውና በማልማት
እንዲጠብቀው ለማድረግ ስለሚያስችል ለአከራዩም መሬቱ በእንክብካቤ እንዲያዝ በማድረግ
ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች አሁን ባለው ሁኔታ
የእርሻ መሬት ጥበት በመኖሩ ብዙ ልማዳዊ የአስተራረስ ዘዴ የሚጠቀሙ አርሶ አደሮች
ከሌሎች አርሶ አደሮች መሬት ተከራይ በመሆናቸው የዚህ አይነት ተከራዮች ረዘም ያለ የኪራይ
ዘመን የሚያገኙበትን የሕግ መሠረት ማስቀመጥ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

2.4.4 የመጠቀም መብትን በዋስትና ማስያዝ

አንድ ንብረት በእዳ ዋስትናነት የሚያዘው ባለዕዳው እዳውን ባይከፍል ባለገንዘቡ የተያዘውን
ነገር ለእዳው መክፈያ ለማድረግ እንዲችል ነው፡፡ አሁን ባለው የኢትዮጵያ የገጠር መሬት ስሪት
ሁኔታ ግን የግል የመሬት ባለቤትነት ባለመኖሩ ባለይዞታው የሌላውን የባለቤትነት መብት
ለሌላ ሰው በመያዣነት ሊሰጥ አይችልም፡፡ ይሁን እንጅ የገጠር መሬት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ
የይዞታና የመጠቀም መብት አለው፡፡ ባለይዞታው የይዞታ መብቱን በዋስትና ቢያስይዝ ደግሞ
ግዴታውን ባልተወጣ ጊዜ ይዞታው ለባለገንዘቡ እንዲተላለፍ ስለሚያደርግ ይህ ደግሞ በሕገ-
መንግስቱ የተከለከለውን መሬትን የመሸጥ ውጤት ስለሚያስከትል በሕግ የሚፈቀድ አይደለም፡፡
ባለይዞታው ያለው በመሬት የመጠቀም መብትን ግን በኪራይ ሊተላለፍ እንደሚችል ሁሉ
በዋስትናም ሊያዝ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የመሬት ባለይዞታው የመጠቀም መብቱን በዋስትና

50
ያስያዘበትን ግዴታ ሳይወጣ ቢቀር ባለገንዘቡ የሚኖው መብት ከመሬቱ ከሚገኘው ምርት
ገንዘቡን አስኪመለስ ድረስ ባለይዞታውን ተክቶ በመሬቱ መጠቀም ነው፡፡

የፌዴራሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ በገጠር መሬት የመጠቀም መብት
በዋስትና መያዝ የሚችል መሆኑን በመቀበል በአንቀጽ 8(4) የገጠር መሬት በሊዝ የተከራየ
ባለሀብት የመጠቀም መብቱን እንደ ዋስትና ለማስያዝ ይችላል በማለት ደንግጓል፡፡ ይሁን እንጅ
የ5ቱም ክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች አንድ የገጠር መሬት የተከራየ
ባለሀብት በመሬቱ ላይ ያለውን የመጠቀም መብት በዋስትና ሊያስይዝ እንደሚችል የደነገጉ
ቢሆንም አንድ የገጠር መሬት ባለይዞታ አርሶ አደር በመሬት የመጠቀም መብቱን ማስያዝ
እንደሚችል ግን ምንም የደነገጉት ነገር የለም፡፡ አንድ ባለሀብት መሬት ሊከራይ የሚችለው
ደግሞ ከመንግስት ወይም ከባለይዞታ አርሶ አደር ነው፡፡

በዚህ ምክንያት የመሬቱ ባለይዞታ የሆነው አርሶ አደር የመጠቀም መብቱን በዋስትና የማስያዝ
መብት ሳይኖረው ከእርሱ የተከራየው ባለሀብት ግን የተከራየውን መሬት የመጠቀም መብት
በዋስትና ሊያስይዝ ይችላል የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል፡፡ ይህም አከራዩ የሌለውንና
ሊሰጥ የማይችለውን መብት ለተከራዩ የሚሰጥ በመሆኑ በሕግ አግባብ ሆኖ አይታይም፡፡ ይህ
ከሆነ ደግሞ ከመጠቀም መብቱም በተጨማሪ ከአንድ ተከራይ የተሻለ የሆነው የይዞታ መብት
ያለው አርሶ አደር በገጠር መሬት የመጠቀም መብቱን እንደ ዋስትና ሊያስይዝ የማይችልበት
የሕግ ምክንያት የለም፡፡ በሌላ በኩል አርሶአደሮች መሬታቸውን በዋስትና አንዲያስይዙ
ቢፈቀድላቸው በተዘዋዋሪ መንገድ እዳ ውስጥ አየገቡ መሬታቸውን ገንዘብ ላለው ሰው
በማስረከብ እነሱ ለባለገንዘቦች ተገዥ እንዳይሆኑ ለመከላከል ነው የሚል መከራከሪያ ይነሳል፡፡

ስለዚህም የክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች የገጠር መሬት


ባለይዞታዎችን መብት ከማስከበር አኳያ የሚታይባቸው አንድ መሠረታዊ ጉድለት አርሶ
አደሮች የመጠቀም መብታቸውን በዋስትና ማስያዝ እንደሚችሉ አለመደንገጋቸው መሆኑን
እንገነዘባለን፡፡

2.4.5 የይዞታ መሬትን ስለመለዋወጥ

የይዞታ መሬትን መለዋወጥ እንደሚቻል የፌዴራሉ መንግሥት ባወጣው በአዋጅ አንቀጽ 11


ላይ ተመልክቷል፡፡ በተለይ የመሬት ልውውጥ እንዲደረግ የሚበረታታው አነስተኛ ማሳዎችን

51
ለማልማት እንዲያመች ሆኖ በአርሶ አደሮቹ ሙሉ ፈቃደኝነት ነው፡፡ አርሶ አደሮች የይዞታ
መሬታቸውን ለመለዋወጥ ፈቃደኛ ከሆኑ ለመለዋወጥ ያሰቡትን የማሳ ስፋትና የለምነት ደረጃ
ሌሎች በቀበሌው አስተዳደር ውስጥ የሚኖሩ አርሶ አደሮች እንዲያውቁት ለማድረግ መረጃ
በቀበሌው አስተዳደር አማካይነት እንዲሰራጭ ይደረጋል፡፡

በደቡብ ክልል የወጣው አዋጅ በፌዴራል መንግሥቱ ከወጣው አዋጅ ጋር ተመሳሰይ ነው፡፡
የኦሮሚያ መንግስት ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 6(1) መሰረት መሬት መለዋወጥ እንደሚቻል
ተመልክቷል፡፡ የአማራ ክልል ያወጣውን አዋጅና ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 51/99
አንቀጽ 8 ላይም አርሶ አደሮች በስምምነት የመሬት ልውውጥ ማድረግ እንደሚችሉ በግልጽ
የተመለከተ ሲሆን ይህ ግን የሚፈጸመው አፈጻጸሙ የመሬት መበጣጠስን እስካላስከተለ ድረስ
እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አዋጁ በሊዝ ስርዐት የተገኘን የገጠር መሬት
የመጠቀም መብት የእዳ ዋስትና አድርጐ ማሰያዝ እንደሚቻል በሚደነግገው አንቀጽ 19(3)
መሠረት አበዳሪው ሳይስማማ የአበዳሪውን ጥቅም በከፊል ወይም በሙሉ በሚጐዳ ሁኔታ
በዋስትና የተያዘውን መሬት በሌላ መለወጥ እንደማይቻል ይደነገጋል፡፡

የትግራይ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 19 መሠረት አርሶ አደሮች ለግብርና ልማት በሚመች
ሁኔታ በስምምነት መሬት መለዋወጥ የሚችሉ ሲሆን ለተለወጠው መሬትም የምስከር ወረቀት
ተስተካክሎ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዝርዝሩ በደንብ የሚወሰን ቢሆንም በተለያዩ
ወረዳዎች ወይም የተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች የመሬት ልውውጥ የማድረግ
መብት አላቸው፡፡ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 28(4) መሰረት
ለልማት አመቺ እንዲሆን በአርሶ አደሩ ሙሉ ፈቃደኝነት በአነስተኛ ማሳዎች ላይ የይዞታ
ልውውጥ እንዲያደርጉ ሊበረታቱ እንደሚችሉ ተደንግጓል፡፡

2.4.6 የመሬት ሽግሽግ

የመሬት ሽግሽግ በፌዴራል መንግስቱ በወጣው አዋጅ አንቀጽ 9 መሠረት ሊካሄድ


የሚችልባቸው ሁኔታዎች ተዘርዝረዋል፡፡ እነርሱም፡-፡-

ሀ. የመሬት ባለይዞታዎቹ በሕይዎት የሌሉና ወራሾች የሌላቸው ከሆኑ ወይም ባለይዞታዎች


በሰፈራ ወይም በፍላጐታቸው በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ህግ ከተወሰነው ጊዜ በላይ

52
ከአካባቢው ለቅቀው የቆዩ ከሆነ በአካባቢው ለሚኖሩት መሬት አልባ ለሆኑ ወይም መሬት
ላነሳቸው አርሶ አደሮች በሽግሽግ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

ለ. የመስኖ መሬትን በአግባቡ በፍትሃዊነት ለመጠቀም ሽግሽግ ሊካሄድ ይችላል፡፡

ሐ. በአርሶ አደሮች ፍላጐትና ውሳኔ መሠረት አማራጭ የሌለው ሆኖ ሲገኝ የመሬት ሽግሽጉ
ከአነስተኛ የይዞታ መጠን በታች በማይሆን የተፈጥሮ ሀብት መመናመንን በማያስከትል መልኩ
ሊፈጸም ይችላል፡፡

መ. የገጠር መሬት ይዞታቸውን ለመስኖ አውታር ግንባታ ሲባል ለሚያጡ አርሶ አደሮች
በአካባቢው ከሚዘረጋው የመስኖ ልማት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመሬት
ሽግሽግ ይደረጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ አንቀጽ 14(1) መሠረት ከመስኖ መሬቶች በስተቀር
በሌሎች የመሬት ይዞታዎች ላይ ሽግሽግ እንደማይካሄድ በአስገዳጅነት ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን
ያልተያዙ እና የመንግስት የእርሻ ልማት መሬቶች ለአርሶ አደሮች ሊከፋፈሉ ወይም
ለባለሀብቶች በሊዝ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

በደቡብ ክልል አዋጅ አንቀጽ 9 ላይ የመሬት ሽግሽግ የተካተተ ሲሆን የፌዴራል መንግስቱ
የመሬት ሽግሽግን አስመልክቶ ካስቀመጠው ድንጋጌ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ለግብርና ሥራ
ሊውሉ የሚችሉ በግል ያልተያዙ የግልና የመንግስት መሬቶች በአካባቢው ለሚገኙ መሬት አልባ
ወጣቶችና መሬት ላነሳቸው አርሶ አደሮች ሽግሽግ ሊደረግ መቻሉ ነው፡፡

በትግራይ ክልል አዋጅ አንቀጽ 22 መሠረት በፌዴራል መንግስቱ የወጣው አዋጅ አንቀጽ 9
እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በክልሉ የመሬት ሽግሽግ የሚካሄድባቸው ምክንያቶች ተገልፀዋል፡፡
ይኸውም በሰፈራ ወይም በሌላ ምክንያት በፍላጐታቸው ቀበሌአቸውን ከሁለት ዓመት በላይ
ለቀው የሄዱትን መሬታቸው በሚመለከተው አካል እንዲተዳደር ተደርጐ መሬት ለሌላቸው
ወይም ላነሳቸው በሽግሽግ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ዝርዝር አፈፃፀሙ በደንብ የሚወሰን
ቢሆንም ተራሮችና ቦረቦሮች የመሬት መሸርሸርና መራቆትን በማያስከትል መንገድ በሽግሽግ
ወይም በኢንቨስትመንት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሊደረግ ይችላል፡፡

በአማራ ክልል አዋጅ አንቀጽ 8(1) መሠረት አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በየትኛውም የክልሉ
አካባቢ የመሬት ሽግሽግም ሆነ ክፍፍል እንዳይካሄድ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን በአንድ ቀበሌ ውስጥ

53
የሚኖሩ ቢያንስ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆኑት የመሬት ባለይዞታዎች ክፍፍል እንዲካሄደ ወስነው
በጽሁፍ ጥያቄውን ለባለስልጣኑ ካቀረቡ ይህንኑ ውሳኔ ለማስፈጸም በሚወጣ መመሪያ መሰረት
የመሬት ሽግሽግ ሊካሄድ ይችላል፡፡ ይህ ሽግሽግም ተፈፃሚ የሚሆነው ውሳኔውን ባሳለፋት
ባለይዞታዎች ብቻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የመሬት ሽግሽግ ወይም ክፍፍል ክልከላው በመስኖ
የሚለማን መሬት ለተለያዩ ተጠቃሚዎች የማከፋፈልን ሥራ የሚከለክል አይሆንም፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 9(2) መሰረት የመሬት ሽግሽግ በህብረተሰቡ
ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ከሆነና በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩ ሰማኒያ ከመቶ እና ከዚያ በላይ
የሚሆኑት የመሬት ባለይዞታዎች ክፍፍል እንዲካሄድ ወስነው በጽሁፍ ጥያቄውን ለባለስልጣኑ
ካቀረቡ ይህንኑ ውሳኔ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ መሰረት የመሬት ሽግሽግ ሊካሄድ ይችላል፡፡
ሽግሽጉም የሚካሄደው ጥያቄው በቀረበበት የይዞታ ሽፋን ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጭ የመሬት ሽግሽግ
ፈጽሞ አይካሄድም፡፡ ነገር ግን የመሬት ሽግሽግ ክልከላው በመስኖ የሚለማን መሬት
የማከፋፈልን ሥራ የሚከለክል አይሆንም፡፡ በሌላ በኩል የመሬት ሽግሽግ ማካሄድ አማራጭ
የሌለው ሆኖ ሲገኝ ከአነስተኛ የይዞታ መጠን በታች በማይሆንና የምግብ ዋስትናን በማይጎዳ
እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት መመናመንን በማያስከትል መልኩ ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል፡፡

በሕዝብ ጥያቄ መሰረት የመሬት ሽግሽግ በሚካሄድበት ጊዜ መሬት ተቀንሶ የሚወሰድበት


ባለይዞታ የመሬት መበጣጠስን የማያስከትል እስከሆነ ድረስ የመረጠውን የመሬት ክፍል
የማስቀረትና በመሬቱ ላይ ላለማው አንስቶ ሊወስደው ለማይችል ንብረት መሬቱ ከሚሰጠው ሰው
ወይም ሽግሽጉ እንዲካሄድ ከሚፈልገው አካል ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ የማግኘት መብቱ
የተጠበቀ ሆኖ ዝርዝሩ በደንብ ይወሰናል፡፡

2.4.7 አግባብ ያልሆነ የገጠር መሬት ማስተላለፍ

የገጠር መሬት የባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ በመሆኑ የመሬት ይዞታን በሽያጭም
ሆነ በሌላ ንብረት በመለወጥ ለሌላ ማስተላለፍ እንደማይቻል በተደጋጋሚ ተመልክተናል፡፡
በዚህ መሠረት ማንኛውም በገጠር መሬት የይዞታ ባለመብት የሆነ አርሶ አደር በይዞታ መሬቱ
የመጠቀም መብት እንጅ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ የገጠር መሬትን እንዲሸጥ ወይም በሌላ
ንብረት እንዲለውጥ የገጠር መሬት አዋጁም ሆነ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ የሆነው ሕገ-መንግስት
አይፈቅድለትም፡፡ ነገር ግን ባለይዞታው በገጠር መሬት ይዞታው ላይ ያለማውን ወይም
ያቋቋመውን ንብረት የመሸጥ ወይም በሌላ ንብረት የመለወጥ መብት ያለው ሲሆን በመሬቱ

54
ላይ የተፈራውን ሀብት የገዙ ባለመብቶችም በይዞታ መሬቱ ላይ የተፈራውን ወይም የለማውን
ንብረት/ሀብት አንስተው የመውሰድ መብት አላቸው፡፡ በመሬቱ ላይ የተፈራው ንብረት በመሬቱ
ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ካሣ የማግኘት መብታቸው የተከበረ ነው፡፡

የፀደቀና ሕጋዊ የሆነ የመሬት አጠቃቀም ጥናትና ማስተር ፕላን ባለመኖሩ ምክንያት በእርሻ
መሬቶች ላይ የተለያዩ ግንባታዎች በመካሄድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የህግ ድጋፍን መሠረት
አድርጎ ድርጊቱም መከላከልና ህጋዊ እርምጃ ማስወሰድ አልተቻለም፡፡ በብዙ አካባቢዎች የእርሻ
መሬቶች የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡባቸው የሚገኙ ሲሆን የገጠር መሬት አዋጁንና ሕገ-
መንግስቱን በተላለፈ ሁኔታ በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎች ደግሞ የሚፈጠሩ ከተማ መሰል
ጥንስስ ከተሞች አንዳንድ ባለይዞታዎች የይዞታ መሬታቸውን ህጉ በማይፈቅደው ሁኔታ ከተማ
ለሚቆረቁሩ ግለሰቦች መሸጣቸው ለግጭት ከመዳረጉ ባሻገር ለመልካም አስተዳደር መጓደል
ምክንያት እየሆነ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት
መሰረት በተለያዩ ሽፋኖች የመሬት ሽያጭና ዝውውር የተበራከተ መሆኑን በሚከተለው መልኩ
እንረዳለን፡፡

መሬትን በተመለከተ /የገጠርም ይሁን የከተማ/ በሕገ-መንግስቱ እና ዝርዝር ሕጎች በግልጽ


ተደንግጓል፡፡ የገጠርም ይሁን የከተማ መሬት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው በምን ሁኔታ
እንደሚተላለፍ፣ ምን ምን ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ እንደሚተላለፉ እየታወቀ በበርካታ
ፍ/ቤቶች የገጠርም ይሁን የከተማ ባዶ ቦታ ለእዳና ለመያዣ ማስፈፀሚያ እንዲሆን ሲወሰን
ይታያል፡፡ በተለይም የገጠር ቀበሌ የነበሩ ወደ ከተማ ክልል የተከለሉ ነገር ግን በከተማ
አስተዳደሮች ተሸንሽነው ለተለያዩ አገልግሎቶች ያልተሰጡ ቦታዎች ላይ ችግሩ ጎልቶ ይታያል፡፡

ተከራካሪዎች የሐሰት የብድር ውል ይዋዋላሉ፣ በውሉ መሠረት ገንዘቡ ስላልተከፈለኝ


በመያዣነት የያዝኩት መሬት ስመ ንብረትነቱ ይዛወርልኝ ተብሎ ዳኝነት ይጠየቃል፣
ፍ/ቤቶችም በዚሁ መሠረት ባዶ መሬት ይተላለፍ እያሉ ይወስናሉ፡፡ ይህ በሕገ-መንግስቱ
ስለመሬት በግልጽ የተደነገገውን መርህ መጣስ ነው፡፡ የችግሩን ግዝፈት ለማየት ሁለት
አብነቶችን እናያለን፡፡

1. ላሊበላ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ እማሆይ አስላኩ ኃይሌ የተባሉ በ4 የተለያዩ
መዝገቦች ገንዘብ ተበድረው አልከፈሉም ተብሎ ክስ ቀርቦባቸው አምነው ከነበራቸው
የከተማ ቦታ 150፣ 150፣ 200 እና 300 ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ አበዳሪ ለተባሉት

55
/እውነታው ግን የመሬት ሽያጭ /ለብድሩ ማስፈፀሚያ እንዲሆን ተወስኖ ስመ ንብረት
እንዲዛወር ካርታና ፕላን ተሰርቶ እንዲሰጣቸው ጭምር ታዘዘ፣
2. ጎንደር አዘዞ እነዚህም በተመሳሳይ የሐሰት የብድር ውል ሽፋን ወደ ከተማ ክልል የገቡ
ነገር ግን ያልተሸነሸኑና አሁንም በገጠር ቀበሌዎች የሚታወቁ አርሶ አደሮች ለእርሻ
እየተገለገሉባቸው ያሉ የገጠር መሬቶች ላይ አነስተኛ ጎጂዎችን በማቆም ለብድር
ማስፈፀሚያት እንዲውሉ ፍ/ቤቱ በበርካታ መዝገቦች ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በክልሉ መንግስት የወጣው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ማስፈፀሚያ ደንቡ
አንድ የገጠር መሬት ባለይዞታ መሬቱን ለምን ለምን ጉዳይ ሊገለገልበት እንደሚችል እና
የባለይዞታነት መብቱን መቼ እና በምን ሁኔታ ለሌላ ሊያስተላልፍ እንደሚችል በግልጽ
ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን በአምስት እና አስር ቆርቆሮ ዶርም እየተሠራ እስከ 1000 ካሬ ሜትር
የገጠር መሬት በብድር ሽፋን ሲሸጥ ፍ/ቤቱም ይህንን ሕገ ወጥ ተግባር ሲያስተናግድ
ይውላል፡፡ ፍ/ቤቱ በ2003 ዓ.ም ካስተናገድናቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮ አብዛኛዎቹ በብድር
ሽፋን የገጠር መሬት ሽያጭን የሚመለከቱ ሲሆኑ በ162 መዝገቦች ከ68,000 ካሬ ሜትር በላይ
የገጠር መሬት ተሸንሽኖ ተሸጧል፡፡

ለአብነት ያህል በሁለቱም ከተሞች ያለው ቀረበ እንጂ በሁሉም ከተሞች ዙሪያ ያሉ ቦታዎች
በተለያዩ ሽፋኖች በህገ ወጥ መንገድ ይተላለፋሉ፡፡

 በፍች ሰበብ ባልና ሚስት ሕጋዊ ይዞታቸው ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ሳያቀርብ


የመንግስት ቦታ እንዲከፋፈሉና በስማቸው እንዲዞር ይታዘዛል፡፡
 ለኢንቨስትመንት የተወሰደ ቦታ በተሰጠው ፕላን እና ካርታ የተሠራ ስለመሆን
አለመሆኑ ወደ 3ኛ ወገን ሊዛወር የሚችል ስለመሆን አለመሆኑ ሳይጣራ ይወሰናል፡፡
 ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ በጊዜያዊነት ለመስሪያ ወይም ለመሸጫ የተሰጠ ቦታ
በፍች ሰበብ እንዲካፈሉና በየስማቸው እንዲዞር ይበየናል፡፡

በአጠቃላይ የመሬት አጠቃቀምን በተመለከተ በሕገ-መንግስቱ እና በዝርዝር ሕጎች በተቀመጡት


መርሆዎች መሠረት ጉዳዮችን በማስተናገድ ውስን የሆነውን ሐብት ለታሰለመለት ዓላማ
እንዲውል በማድረግ ረገድ ችግሮች ነበሩ/፡፡ ይላል የጥናቱ ውጤት፡፡52

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የ2003 ዓ.ም በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ የቀረበ ጥናት፣
52

ጥቅምት 2004 ዓ.ም ገፅ 15

56
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በአነስተኛ የገጠር ከተሞች መፈጠርና መስፋፋት ምክንያት
የሚካሄደው የገጠር መሬት ሽያጭና ህገወጥ ግንባታ ድርጊት ህጋዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት
ስለሌለው አስቀድሞ መገታትና ህጋዊ እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል፡፡ በየደረጃው የሚገኙ
የሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶችም መሬትን ለማስተዳደርና አጠቃቀሙን ለመወሰን
ስልጣን ለተሰጠው የአካባቢ ጥበቃ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መ/ቤት ተገቢውን
ድጋፍ በመስጠትና አስተዳደራዊ እርምጃዎች በመውሰድ ችግሩ ሳይባባስ ከወዲሁ እንዲገታ
ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2.5 የገጠር መሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ እና ማስተላለፊያ ፎርማሊቲ

በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 6(3) መሠረት ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ አግባብ
ባለው ባለስልጣን የሚዘጋጅና የመሬቱን ይዞታ ስፋት፣ አጠቃቀምና ሽፋን፣ የለምነት ደረጃና
አዋሳኞቹን እንዲሁም ሀላፊነትና ግዴታን የያዘ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንደሚኖረው
ይደነግጋል፡፡ መሬቱ የባልና ሚስት የጋራ ከሆነ ወይም በሌሎች በጋራ የተያዘ ከሆነ የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተሩ በሁሉም የጋራ ባለይዞታ ስም መዘጋጀት እንዳለበት የዚሁ አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ 4 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም በግል፣ በውል፣ በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ
ድርጅቶች ይዞታዎች ሥር ያሉ የገጠር መሬቶች እንደሁኔታው ባህላዊና ዘመናዊ መሳሪያዎችን
በመጠቀም የመሬት ስፋታቸውን በመለካት እንዲሁም የመሬት አጠቃቀማቸውና የለምነት
ደረጃቸው በክልልና በየደረጃው በተቋቋሙ የመረጃ ማዕከላት እንዲመዘገቡ እንደሚደረግ በግልጽ
ተደንግጓል፡፡

በዚህ መሠረት በዚህ ጽሑፍ የተካተቱ አምስቱም ክልሎች በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
አዋጆቻቸው ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ የሆነ ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር
እንደሚሰጠው እና መሬቱ የተያዘው በባልና ሚስት በጋራ ከሆነ ደብተሩ በሁለቱም ስም
እንደሚዘጋጅ ደንግገዋል፡፡53 እንዲያውም የአማራና የቡንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋጆች አንቀጽ
24(4) እና 27(5) (በቅደም ተከተል) መሠረት ተቃራኒ የፅሑፍ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ
የይዞታ ማረጋገጫ በስሙ የተሰጠው ሰው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ እንደሆነ እንደሚቆጠር
በግልጽ ይደነግጋሉ፡፡ የደቡብ አዋጅም ቢሆን ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ያለይዞታ

አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 24(1)(2)፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀጽ 15(4)(8)፣ አዋጅ ቁጥር
53

110/1999 አንቀጽ 9(4)(5)፣ አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 5(1)(ሐ) እናአዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ
27(1)(2)

57
መረጋገጫ ደብተር የገጠር መሬትን መጠቀም እንደማይቻል በአንቀጽ 13(4) ላይ ደንግጓል፡፡
ስለሆነም ከዚህ የምንረዳው የገጠር መሬት ባለይዞታነትን ለማረጋገጥ የይዞታ ማረጋገጫ
ደብተር ይዞ መገኘት ወሳኝ መሆኑን ነው፡፡ መሬት የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑም የተነሳም
በእንዲህ አይነት የሰነድ ማስረጃ ማስረዳት በህጉ መቀመጡ ተገቢነትና ተመራጭነት ያለው
ጉዳይ ነው፡፡

በአጠቃላይ የገጠር መሬት በማን ይዞታ ስር እንደሚገኝ፣ ከማን መሬት ጋር እንደሚዋሰን፣


ደረጃው ምን አይነት እንደሆነ፣ ለምን አገልግሎቴ እንደሚውልና ባለይዞታው ምን መብትና
ግዴታዎች እንዳሉበት የሚገልጽ መረጃ ተመዝግቦ አግባብ ባለው ባለስልጣን እንደሚያዝ አዋጅ
ቁጥር 456/97 አንቀጽ 6(5) ይገልፃል፡፡ በሊዝ ወይም በኪራይ የተያዘ የገጠር መሬትም አግባብ
ባለው አካል መመዝገብ እንዳበት የዚሁ አንቀጽ 6(6) ያሳያል፡፡ ስለሆነም ከዚህ አዋጅ
እንደምንረዳው የገጠር መሬት ባለይዞታ ለመሆንም ሆነ ተጠቃሚ ለመሆን (ከአንዱ ወደ አንዱ
ሲተላለፍም) መመዝገብ ያለባቸው መሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌ የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 8(2) የገጠር
መሬት ኪራይ ውል አግባብ ባለው አካል ጸድቆ መመዝገብ ያለበት መሆኑን ይገልፃል፡፡

በዚህ መሠረት ክልሎች የመሬት ይዞታና የመጠቀም መብት የሚተላለፍባቸውን ፎርም


የእየራሳቸውን እንዲስቀምጡ ይጠበቃል፡፡ ለምሳሌ፡- የአማራ ክልል አዋጅ ማናቸውም የመሬት
የስጦታ ስምምነት በፅሑፍ መደረግ ያለበት መሆኑን እና መሬቱ የሚገኝበት ወረዳ ባለው
የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ መ/ቤት መመዝገብ ያለበት መሆኑን አንቀጽ 17(5)(6) ይገልፃል፡፡
እንዲሁም ከ3 ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ የሚደረግ የመሬት ኪራይ በፅሑፍ መደረግ ያለበት
መሆኑንና መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ ያለበት
መሆኑን አንቀጽ 18(2)(5) ደንግጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ክልል አዋጅ ከመሬት ጋር
የተያያዘ ማንኛውም መብትና ግዴታን የሚመለከት ተግባር መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ ባለው
የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ መ/ቤት ቀርቦ ካልተመዘገበ በስተቀር በ3ኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ
ሊቀርብ አይችልም በማለት አንቀጽ 23(4) ይደነግጋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋጅ የመሬት ስጦታ በፅሑፍ ሆኖ በወረዳው ባለስልጣን ፅ/ቤት
መመዝገብ ያለበት መሆኑን አንቀጽ 18(5)(6) ይደነግጋል፡፡ የመሬት ኪራይም በፅሑፍ ተደርጎ
በጽ/ቤት መመዝገብ አለበት (አንቀጽ 19(5)(8)፡፡ አንቀጽ 26(4) ከመሬት ጋር ተይይዞ
ማንኛውም መብትና ግዴታን የሚመለከት ተግባር መሬቱ በሚገኝበት አግባብ ባለው ባለስልጣን
ቀርቦ ካልተመዘገበ ለ3ኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ሊሆን እንደማይችል ይገልፃል፡፡

58
የትግራይ ክልል አዋጅ አንቀጽ 10(1)(2) አርሶ አደር ከሌላ አርሶ አደር ጋር ወይም አርሶ አደር
ከባለሀብት ጋር የሚደረግ የመሬት ኪራይ በሚመለከተው የመሬት አስተዳደር አካል ተረጋግጦ
በወረዳ ወይም ንዑስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት መመዝገብ ያለበት መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የመሬት
ባለይዞታዎች መሬት ቢለዋወጡ በለውጡ መሠረት ደብተር እንደሚሠራላቸው አንቀጽ 19(2)
ይደነግጋል፡፡ ስጦታ ሲደረግ በቀበሌ መሬት አስ/ኮሚቴ ወይም በወረዳ ዴስክ ተረጋግጦ በወረዳ
ወይም በንዑስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ይመዘገባል፤ አንቀጽ 5(3)(ለ)፡፡

በደቡብ ክልል አዋጅ አንቀጽ 8(2) የገጠር መሬት ኪራይ እስከ 2 ዓመት ከተደረገ በቀበሌው
አስ/ጽ/ቤት ከ2 ዓመት በላይ ከሆነ ደግሞ ውል ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል
እንደሚመዘገቡ ይደነግጋል፡፡ የይዞታ መለዋወጥ በሚኖርበት ጊዜ አዲስ የይዞታ ማረጋገጫ
ደብተር ይዘጋጃል፤ አንቀጽ 6(9)፡፡ በሊዝ ወይም በኪራይ የሚያዝ የገጠር መሬት አግባብ ባለው
አካል መመዝገብ ያለበት መሆኑን አንቀጽ 6(11) ይደነግጋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል አዋጅ አንቀፅ 10(3) የመሬት ኪራይ በፅሑፍ ሆኖ በግብርናና ገጠር ልማት
ቢሮ ካልተመዘገበ የማይፀና መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የመሬት መለዋወጥ ሲኖርም አዲስ የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር እንደሚሠራ አንቀጽ 15(12) ይገልፃል፡፡

በአጠቃላይ በአዋጅ ቁጥር 456/97ም ሆነ በክልሎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህጎች


የመሬት ይዞታን አስመልክቶ የሚደረግ ስጦታ፣ ለውጥ፣ ኪራይ እና የመሳሰሉት የመብት
ማስተላለፊያ መንገዶች የተመዘገቡና የሚመለከተው የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አካል
ያፀደቃቸው መሆን ያለባቸው መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ስለዚህም መነሻ ምክንያቱ በአንድ በኩል
መሬት የመንግስትና የህዝብ ከመሆኑ አንፃር መሬት ከአንዱ ወደ አንዱ የይዞታ መብትም ሆነ
የመጠቀም መብት ሲተላለፍ መሬትን ለማስተዳደር ስልጣን በተሰጠው አካል፤ የማይንቀሳቀስ
ንብረት ስለሆነ በፍትሐብሔር ህጉ የተቀመጡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን አስመልክቶ የሚደረጉ
ግንኝነቶች ማሟላት ካለባቸው በፅሑፍ የመሆንና የመመዝገብ ፎርማሊቲ ጋር ተመሳሳይ
ለማድረግ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመሬት ላይ የሚነሱ አለመግባባቶችን በቀላሉ
ለመፍታት በፅሑፍ መደረጉና መመዝገቡ ወሳኝ ጥቅም ስለሚኖው ነው፡፡

ስለሆነም መሬትን በሚመለከት ባለይዞታዎች ይዞታቸውን ወይም የመጠቀም መብታቸውን


ሲያስተላልፉ ስምምነታቸውን በጽሑፍ ከማስፈራቸው በተጨማሪ በሚመለከተው አካል ፊት
ቀርበው እንዲመዘገቡ መደንገጉ ሕጉ ለመሬት ልዩ ትኩረት መስጠት መፈለጉን የሚያመለክት

59
ነው፡፡ ይህም የሕግ አውጪው ፍላጐት መሬት ለአንድ አገር በአጠቃላይም ሆነ ለአንድ
ግለሰብ በተለይ ካለው ጠቀሜታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ መሬት ካለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
ጠቀሜታ አንፃር ስምምነቶች ሥልጣን ባለው አካል እንዲመዘገቡ በመጠየቅ የማረጋገጡ ሂደት
ተስማሚዎች ትልቅ ጠቀሜታ ባለው መሬት ላይ የሚፈጽሙት ውል ፈቅደው የሚፈጽሙት
መሆኑን ከማረጋገጥ ባሻገር፣ የሚያስተላልፈው ሰው ባለይዞታ መሆኑን ለማጣራት፣ ስምምነቱ
የተፈፀመበትን ትክክለኛ ቀን ለማረጋገጥ እድል በመስጠት በመሬት ባለይዞታ መሆንን እና
የመጠቀም መብትን ለመጠበቅ፣ የስምምነቱን ዋስትና ለማረጋገጥ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች
1. በህገ መንግስቱ የተረጋገጠዉ ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋወርና የመንቀሳቀስ መብትን
ተጠቅሞ ከአንድ ክልል የነበረውን መደበኛ መኖሪያ ስፍራ በመተው ሌላ ክልል ውስጥ
በቋሚነት ኑሮውን የመሠረተ አርሶ አደር የክልሉ ነዋሪ ነኝና በነፃ የእርሻ መሬት ይሰጠኝ
ብሎ እንደ መብት የሚኖርበትን ክልል መንግስት ለመጠየቅ ይችላል ወይ? የመጠየቅ
መብት አለዉ የሚባል ከሆነ ስንት ዓመት በክልሉ ውስጥ በቋሚነት መኖር ይገባዋል?
ፍ/ቤቶች የክልሉ ነዋሪ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ጭብጥ ለመወሰን መነሻ
የሚያደርጉት ምን መሆን አለበት?
2. አንድ ሰው ከመሬት ውጭ ያሉ ንብረቶችና ሃብቶች ወራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ
የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚጠይቀው ከፍ/ቤት ነው፡፡ የመሬት ይዞታ
ወራሽ መሆኑን ለማረጋገጥስ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ያለበት
ከየት ነው?
3. የስጦታ ውል ተደርጐ በመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ከተመዘገበ በኋላ ስጦታ
አድራጊዎች ስጦታው ይሰረዝልን ሲሉ በአንዳንድ ቦታዎች የአስተዳደር አካሉ የስጦታ
ውሉን ይሰርዘዋል፡፡ ሌሎች ቦታዎች ደግሞ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ይቅረብ የሚል ውሣኔ
ይሰጣሉ ነገር ግንየስጦታ ውሉን ማነው መሰረዝ ያለበት? ፍ/ቤት ወይስ የአስተዳደር
አካሉ? የስጦታ ውሉን መሰረዝስ ይቻላል ወይ? የመሬት አዋጅና ደንቡ የመሬት ስጦታን
ስለመሻር የሚለው ነገር ከሌለ ወደ ፍትሐብሔር ህጉ መሄድ አለበን?
4. በመሬት የመጠቀም መብትን በመያዣነት ማስያዝ ይቻላል ወይ?
5. በአማራ ክልል በአዋጅ አንቀፅ 24/4/ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋጅ አንቀፅ 27
መሠረት ተቃራኒ የፁሑፍ ማስረጃ ካልመጣ በስተቀር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የያዘ

60
ሰው የመሬቱ ባለቤት ነው ይላል፡፡ ተቃራኒ የጽሑፍ ማስረጃ ማለት ምን ማለት ነው?
እንዴትስ ነው የሚመጣው? በመሬት ክርክር ወቅት የሰው ማስረጃ /ምስክር/ መስማት
ይቻላልን? ከተቻለስ በየትኛው የህግ አግባብ?
6. የቤተሰብ አባል ማን ነው? በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ላይ ያልተጠቀሱ ሰዎች የቤተሰብ
አባል ነን በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡ ጥያቄያቸውን የሚቀበለው የትኛው አካል ነው?
ማስረጃውስ በማን ይረጋገጣል?
7. የመንግስት ሠራተኞች መሬታቸው እንዳይወሰድባቸው በማሰብ መሬታቸውን በስጦታ
ለሌላ ሰው ያስተላልፋሉ፣ እንዴት ይታያል? አግባብ ነውን?
8. የገጠር መሬት ላይ የተገነባን ቤት መሸጥ ይቻላል? እንዴት? የገጠር መሬትን ወይም
በገጠር መሬት የተገነባን ቤት ለፍርድ የማስፈፀሚያ ማድረግ ይቻላል? በማደግ ላይ ባሉ
ከተሞች ላይ የገበሬው መሬት በቤት ሽያጭ ስም መሬቱ እየተሸጠ በመሆኑ መፍትሔው
ምን ሊሆን ይችላል?
9. ማንም ሠው የፈለገውን ያህል መሬት ያለገደብ መከራየት ይችላል? በአማራ ክልልስ
አርሶ አደሩ በሚያከራየው የመሬት መጠን ላይ ገደብ አለማስቀመጡ ተገቢ ነውን?
10. በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 853 መሠረት የምትክ ወራሽነት ስለሚፈቀድበት ሁኔታ
ተደንግጓል፡፡ የምትክ ወራሽነት ለመሬት ውርስ ተፈፃሚ ሊሆን ይችላል?
11. የመንግስት ሠራተኛ ከመሆኑ በፊት ያገኘውን መሬት አከራይቶ አየተጠቀመ እያለ
በመሐል ግለሰቡ የመንግስት ሠራተኛ ሆነ እንበል፡፡ በመሆኑም የዋና ይዞታ መብት
ሲቋረጥ የኪራይ ውሉ ውጤት ምን ይሆናል?
12. መሬትን ማስተላለፍ በተመለከተ (ለምሳሌ በኪራይ) በፅሑፍ የመሆንና በሚመለከተው
አካል የመመዝገብ ፎርማሊቲ ሳይሟላ ቢቀር ውጤቱ ምን ይሆናል? የፎርሙ ጉዳይ
ባይሟላ እና ተቃውሞ ባይነሳበት ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል? ሰGጣኞች ይህንን ጥያቄ
ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር መዝገብ ቁጥር 21448 (ቅጽ 4) እና 43825 (ቅጽ
10) ጋር በማገናዘብ ተወያዩበት፡፡
13. የሕዝብ ይዞታ መጠቀሚያ የሆነ መሬት (ለምሳሌ የቤተክርስቲያን) የይዞታ ማረጋገጫ
ደብተር የግድ እንዲኖረው ያስፈልጋል? ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር መዝገብ
ቁጥር 22469 (ቅጽ 6) አንፃር ተወያዩበት፡፡
14. የመሬት ባለይዞታነት በይርጋ ሊታገድ ይችላል? የአርሶ አደሮች የመሬት ባለይዞታነት
መብት የጊዜ ገደብ የለውም ከሚለው መርህ አንፃር እንዴት ይታያል?

61
ምዕራፍ ሶስት
የገጠር መሬትን በመጠቀምና በማስተዳደር ረገድ ስለተጣሉ ግዴታዎችና
ኃላፊነቶች

በዚህ ምዕራፍ ስር በፌደራል መንግስት እና በአምስቱ ብሔራዊ ክልሎች የገጠር መሬት


አስተዳደር ህጎች የገጠር መሬት ባለይዞታዎችና የገጠር መሬት አስተዳደር ባለስልጣን የገጠር
መሬትን አስተዳደር እና አጠቃቀምን አስመልክቶ የተጣሉባቸውን ግዴታዎች እና ግዴታዎቹን
አለመወጣት ስለሚያስከትለው ኃላፊነት እንመለከታለን፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች፡-

ሰልጣኞች የዚህን ምዕራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-

 የገጠር መሬትን በማስተዳደርና በመጠቀም ረገድ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች እና


የገጠር መሬት አስተዳደር ባለስልጣን ስለተጣለባቸው ግዴታዎች እና ግዴታን
አለመወጣት ስለሚያስከትለው ኃላፊነት ለይተው ያውቃሉ፡፡

3.1 የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች

በኢፌዴሪ መንግስት የወጣውን አዋጅ ቁጥር 456/97ን ጨምሮ በአምስቱ ብሔራዊ ክልሎች
በወጡ የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች ውስጥ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች
ተደንግገዋል፡፡ እነርሱም ጠቅለል ባለ መልኩ እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡54

1. በይዞታው ስር ያለውን ወይም በኪራይ የተሰጠውን መሬት የመንከባከብና አካባቢን


የመጠበቅ ግዴታ፡- የገጠር መሬትን በይዞታ ያገኘ ወይም የመጠቀም መብት ያለው
አርሶ አደር በይዞታ ወይም በኪራይ የተሰጠውን መሬት በአግባቡ የመንከባከብና
አስቀድሞ በተዘጋጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ የመጠቀም ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን፡፡
ይህ ግዴታ የሚከተሉትን ነጥቦች ያካትታል፡፡

54
በመሆኑም ከተራ ቁጥር 1-12 የተዘረዘሩት የመሬት ባለይዞታዎች ግዴታዎች የተወሰዱት ከአዋጅ ቁጥር
456/1997 አንቀፅ 10 እና 13፣ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 20፣ አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 11፣
አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 22፣ አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 10፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 18
ነው፡፡

62
 በአካባቢው ባህል በተለመደው መሠረት መሬቱን ማረስና ስለዘመናዊ የመሬት
አጠቃቀም ዘዴ በሚሠጠው የባለሙያ ምክር አገልግሎት መጠቀም፣
 የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራን ማከናወን፣
 በሰብሉም ሆነ በአካባቢው ላይ ጉዳት የማያደርሱ ዛፎችን ፈቃድ ሳያገኙ ከመቁረጥ
መቆጠብ፣
2. በመሬቱ አካባቢ ዛፎችን መትከልና በተገቢው ሁኔታ ተንከባክቦ የማሳደግ ግዴታ፡-
በሰብሉ ወይም በመሬቱ እንዲሁም በአጎራባች ማሳዎች ላይ ጉዳት የማያደርሱ ዛፎችን
በመሬቱ አካባቢ የመትከልና ተንከባክቦ የማሳደግ ግዴታን ያካትታል፡፡
3. በመሬቱ አካባቢ የሚገኙ የዱር እንስሳትና አዕዋፎች እንዳይጎዱ ተገቢውን ጥንቃቄ
የማድረግ ግዴታ፡- በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት በማያደርሱና በአካባቢው
ተጠልለው በሚኖሩ የዱር እንስሳት ላይ ሆነ ብሎ ጥቃት አለመፈፀም፣ ጉዳት
ያደርሳሉ ተብለው በሚገመቱት ላይ ደግሞ ይህንኑ ለመከላከል የሚያስችል እርምጃ
ከመውሰድ በፊት አግባብ ካለው አካል ፈቃድ የመጠየቅ ግዴታንም ያካትታል፡፡
4. የመሬት ተዳፋትነታቸው ከ30% - 60% የሆኑ መሬቶችን ለዓመታዊ ሰብሎች ልማት
ለማዋል ይቻል ዘንድ ጠረጴዛም እርከን ወይም ሌሎች ተስማሚ የአፈር ጥበቃ
ስራዎችን የማከናወን፤ እንዲሁም ተዳፋትነታቸው 60% እና ከዚያ በላይ የሆኑ
መሬቶችን ለደን፣ ለቋሚ ተክሎችና ለእንስሳት መኖ ልማት ወይም የመሳሰሉት
ተግባራት ካልሆነ በስተቀር ለእርሻም ሆነ ለልቅ ግጦሽ እንዲውል ያለማድረግ ግዴታ፣
5. ተገቢ ባልሆነ አስተራረስ ሳቢያ ምንጮች እንዳይደርቁ ጥንቃቄን የማድረግ ግዴታ፣
6. ወሰናቸው የተከለለ መሬቶችን ድንበር ያለመጋፋትና ተለይተው የሚታወቁ መንገዶችን
ያለመዝጋት ግዴታ፡፡፡ ይህ ግዴታ፡-
-ከአጎራባች ይዞታዎች ጋር የሚጋሩትን ድንበር ያለማፍረስ፣
- የወል መሬቶችን ወሰን ያለመጋፋት፣
-አግባብ ባለው አካል የተከለሉ መንገዶችን ያለመዝጋት፣
-ለራሱ፣ ለቤተሰቡም ሆነ ለሌሎች ባለይዞታዎች አጠቃቀም ይረዳ ዘንድ
እንደ አስፈላጊነቱ በመሬቱ ዳር ወይም ውስጥ በቂና ስፋት ያለው የመተላለፊያ መንገድ
የመፍቀድ፣
-በሌሎች ባለይዞታዎች ወሰን ውስጥ ሲያልፍ ንብረታቸው እንዳይጎዳ ጥንቃቄን
የማድረግ ግዴታዎችን ያካትታል፡፡

63
7. አግባብ ባለው አካል መሬቱ እንዲለካ ወይም የቅየሳ ስራ እንዲካሄድበት ሲጠየቅ በቅርብ
የመተባበር እና መሬቱን በመሬት አጠቃቀም ዕቅድ መሠረት እንዲጠቀም አግባብ ባለው
አካል በጽሑፍ ሲጠየቅ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ፡፡
8. የገጠር መሬት ባለይዞታ ከሆነ የገጠር መሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ ደብተር
በሚሰጥበት ጊዜ ይህንኑ የማውጣትና የመያዝ፤ የመሬቱ ባለይዞታነት መብቱን
በሚያጣበት ጊዜ የተሠጠውን የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አግባብ ላለው አካል
የመመለስ ግዴታ፡፡
9. መሬቱ በወንዝ ዳር ወይም ገደላማ በሆነ አካባቢ የሚገኝ ማንኛውም ባለይዞታ ከወንዙ
ወይም ከገደሉ አርቆ የማረስና ያልታረሰውን የወንዙን ዳር አካባቢ በይዞታው ስር
አድርጎ እየተካ የሚጠቀምበት ዛፍ የማልማት እና በመሬቱ ላይ ያለማውን ሰብል
በአካባቢው ከፍተኛ ጉዳት ከሚያደርሱ አረሞችና ፀረ-ሰብል ተባዩች የመጠበቅ ግዴታ
10. የመስኖ ቦዮችንና ሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮች በሚዘረጉበት ወቅት
በባለይዞታው መሬት ላይ የሚያልፍ ከሆነ ይህንኑ የመቀበል ግዴታ፡፡
11. በመሬቱ ላይ የእሳት ቃጠሎ እንዳይነሳ ተገቢ ሆኖ የተገኘውን የጥንቃቄ እርምጃ
የመውሰድ ግዴታ፡፡
12. በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ምክንያት ከላይኛው አካባቢ በመነሳት የተፈጥሮ
አቅጣጫውን ተከትሎ የሚፈሰውን ውሃ በመቀበል ወደ ታች እንዲያልፍ የማድረግ
እንዲሁም ውሃው ወደታች በሚፈስበት ጊዜ አላግባብ የውሃውን የተፈጥሮ ፍሰት
አቅጣጫ በመቀየር የታችኛው መሬት የውሃ ጫና እንዲያርፍበት ያለማድረግ ግዴታ
እና ሌሎች የመሳሰሉት ግዴታዎች፡፡

3.2 ግዴታን አለመፈፀም በባለይዞታው ላይ ስለሚያስከትለው ኃላፊነት

የኢፌዴሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅን ጨምሮ በአምስቱ ክልሎች የገጠር
መሬት አስተዳደር ሕጎች የተደነገጉትንና ከዚህ በላይ የተመለከትናቸውን ግዴታዎች
ያልተወጣ ማንኛውም የገጠር መሬት ባለይዞታ ወይም በገጠር መሬት ላይ የመጠቀም
መብት ያለው አካል እንደአስፈላጊነቱ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፡፡

64
1. አስተዳደራዊ እርምጃ (Administrative Responsibility)
ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸውን ግዴታዎች ያልተወጣ ማንኛውም የገጠር መሬት
ባለይዞታ በመጀመሪያ ደረጃ እንደቅደም ተከተሉ የቃል ወይም የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ
ይሰጠዋል፡፡ ይህ በአማራ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ የተደነገገ ተጠያቂነት
ነው፡፡55 በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት ስህተቱን ሊያርም ያልቻለ እንደሆነ
ከተሰጠው የቃልና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለይዞታው
በራሱ ድክመት መሬቱን ባለመንከባከቡ ምክንያት በመሬቱ ላይ ጉዳት ከደረሰ የመጠቀም
መብቱን መሬቱን ለመንከባከብ ግዴታ ለሚገባ ሌላ ሰው ለተወሰነ ጊዜ በኪራይ እንዲሰጥ
አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ከዚህ በላይ የተቀመጠው አስተዳደራዊ እርምጃ ተፈፃሚ
ከሆነ በኋላ ጥፋቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ከተደገመ በመሬት የመጠቀም መብቱን ለተወሰነ
ጊዜ ከማገድ ጀምሮ ካሳ ተከፍሎት መሬቱን እንዲለቅ እስከ መገደድ የሚደርስ እርምጃ
ይወሰዳል፡፡56

2. የፍትሐብሔር ተጠያቂነት (civil responsibility)


ማንኛውም የመሬት ባለይዞታ ከላይ የተመለከትናቸውን የገጠር መሬት ባለይዞታ
ግዴታዎች ያልተወጣና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበት ራሱን ካላስተካከለ
ከአስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ በመሬቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት በፍትሐብሔር ሕግ
መሠረት ካሣ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ (በአማራ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ
የተደነገገ ተጠያቂነት)፡፡57

3. የወንጀል ኃላፊነት (Criminal responsibility)


ከአስተዳደራዊ እና ፍትሐብሔራዊ ኃላፊነት በተጨማሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም ሕግን የጣሰ ወይም አፈፃፀሙን ያሰናከለ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው
የወንጀል ህግ ድንጋጌ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

55
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 21(1) እና አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 23(1) በቅደምተከተል
56
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 21(2)፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 23(2)
አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 21(5) እና አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 23(5) በቅደምተከተል
57

65
3.3 የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች

የኢፌዴሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ እንዲሁም የአምስቱን ክልሎች የገጠር
መሬት አስተዳደር ሕጎች በተመለከተ በእየክልሎቹ ጠቅለል ባለ መልኩ በባለስልጣን መስሪያ
ቤቱ የተጣለበትን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡58

1. የገጠር መሬትን መለካት


የገጠር መሬትን መለካት የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ማከናወንን ይጠይቃል፡፡
 ልኬት ከሚካሄድበት መሬት አንፃር መሬትን የመለካት ስራው በማናቸውም መንገድ
ለተጠቃሚዎች በይዞታነት የተሰጠ፣ በአንድ አካባቢ ማህበረሰብ አማካኝነት በወል
መጠቀሚያነት የተያዘ ወይም ለደን ልማት ወይም ለሌሎች መሰል ተግባራት
የተከለለ የትኛውም የገጠር መሬት ላይ ይሆናል፤
 ልኬታው ከሚካሄድበት መሳሪያ አንፃር እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ በባህላዊ
መንገድ ወይም ዘመናዊ መሳሪያን በመጠቀም መለካት፤
 የመለካት ስራ ለተከናወነበት መሬት ካርታን ማዘጋጀት፤
 እያንዳንዱ መሬቱን በግልጽ ለመረዳት የሚያስችል የመሬት ልዩ ቁጥር አሰጣጥ
ስርዓትን መዘርጋት እና ስራ ላይ ማዋል፤
 የእያንዳንዱን መሬት ድንበር (ወሰን) የሚያሳይ ምልክት በመሬቱ ላይ ማድረግ፤
 ማናቸውም መሬት በሚለካበት ጊዜ በተቻለ መጠን የሚለካው መሬት አዋሳኝ
ባለይዞታዎች ወይም ተጠቃሚዎች በስፍራው እንዲገኙና ድንበራቸውን በስምምነት
እንዲወስኑ ጥሪ ማድረግ፤
 የመሬት ቅየሳ ተግባርን የባለይዞታዎችን ማሳዎች በመነሻነት በመጠቀም ማካሄድ፤
 በመሬቱ አለካክና በድንበሩ አከላለል ረገድ ቅሬታ የተሰማቸው ባለይዞታዎች ቅሬታ
የሚያቀርቡበት ስርዓትን መዘርጋት፤
 መሬቱ ከተለካ በኋላ በልዩ ልዩ ምክንያት መጠኑ ከተለወጠ እንደገና መለካትና
አዲስ ካርታን ማዘጋጀት፤ በልኬታው ተግባር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የግል የቅየሳ
ድርጅቶች በመሬት ቅየሳ ስራው እንዲሳተፉ ማድረግ ወዘተ…
58
እነዚህ ከተራ ቁጥር 1-11 የተዘረዘሩት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን ግዴታዎች እና
ኃላፊነቶች የተወሰዱት ከአዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀፅ 6፣ አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 22-27፣ አዋጅ
ቁጥር 136/2000 አንቀጽ 20፣ አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 25-27፣ አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀፅ 7 እና
14፣ አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 15 ነው፡፡

66
2. የገጠር መሬትን መመዝገብ እና መረጃን መያዝ
በክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የሕግ ማዕቀፎች የተቀመጡት እና
የገጠር መሬትን መመዝገብ እና መረጃን የመያዝ ግዴታ የሚከተሉትን ተግባራት
ያካትታል፡፡
 በባለስልጣኑ የተለካ ማናቸውንም መሬት በገጠር መሬት መመዝገቢያ መዝገብ
ውስጥ መመዝገብ፡፡ ይህ ምዝገባም፡-
o የመሬቱን ባለ ይዞታ ሙሉ ስም
o ይዞታው የተገኘበትን ሁኔታ
o የመሬቱን አዋሳኞች
o የለምነቱን ደረጃ
o መሬቱ የሚውልበትን አገልግሎትና ባለይዞታው ያሉበትን ግዴታዎች
የሚገልጽ መረጃን ባካተተ መልኩ ይካሄዳል
o የመሬት መመዝገቢያ መዝገቡም መሬቱ በሚገኝበት ቀበሌ የመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴ ጽ/ቤት እና የባለስልጣኑ የወረዳ ተጠሪ ጽ/ቤት
ውስጥ እንዲቀመጥ ማድረግ
 መዝገቡን በአንድ መሬት ላይ ህጋዊ መብት ወይም ጥቅም እንዳላቸው ማስረዳት
የሚችሉ ሰዎች ጥያቄ ሲያቀርቡ የሚያዩበትን ስርዓት መዘርጋት ወዘተ…
3. ለእያንዳንዱ ባለይዞታ የባለይዞታውን በሕግ የተደነገጉ ዋና ዋና መብቶችና ግዴታዎች
የሚያመላክት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማዘጋጀት፤ መሬቱ የባልና የሚስት በአንድነት
ወይም ሌሎች ሰዎች በጋራ የያዙት መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ደብተሩን በሁሉም ስም
ማዘጋጀት፡፡ ይህ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በሚዘጋጅበት ጊዜም
የሚከተሉትን ዝርዝር ነገሮች ማካተት ይኖርበታል፡-
 የመሬቱን ባለይዞታ (ዎች) ሙሉ ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ እና ጉርድ ፎቶ ግራፍ
 የባለይዞታ (ዎች) ዋና ዋና መብቶችና ግዴታዎች
 የመሬቱን መለያ ቁጥርና የይዞታው ስፋት
 የደብተሩን ተራ ቁጥር
 መሬቱ የሚሰጠውን የአገልግሎት ዓይነት
 መሬቱ የሚገኝበት የለምነት ደረጃ
 ደብተሩ የተሰጠበት ቀን፣ ወርና ዓመተ ምህረት

67
 ሰነዱን ያዘጋጀው ሠራተኛና ያረጋገጠው ኃላፊ ሙሉ ስም እንዲሁም ፊርማና ማህተም
 የመሬቱን አዋሳኞች
 መሬቱ የሚገኝበትን ቀበሌ እና ልዩ ጎጥ
4. አግባብ ያላቸውን አካላት በማስተባበርና አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ በመስጠት
የየክልሉን የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕጎች የማስፈፀም ኃላፊነት፣
5. የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር መ/ቤቶች ድንበራቸው በግልጽ እንዲካለል በማድረግ ረገድ
ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስፈላጊውን እገዛ የማድረግ፣
6. በቀበሌዎች እና በንዑስ ቀበሌዎች የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኮሚቴዎችን በሕዝብ
ምርጫ ማቋቋም፤ ተግባርና ኃላፊነታቸውን አስመልክቶ ተገቢውን ስልጠና መስጠት፤
ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን በቅርብ መከታተልና መቆጣጠር፣
7. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን የሚመለከቱ መረጃዎችን በአግባቡ የመያዝና
የመጠበቅ፣
8. የመሬት ባለይዞታዎችና ተጠቃሚዎች በህግ የተጣለባቸውን ግዴታ እየተወጡ
ስለመሆናቸው የመከታተል፤ ግዴታዎችን ባልተወጡት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን
የመውሰድ፣
9. መሬት በሚመዘገብበት ወቅት በመዝጋቢው ስህተት በማንኛውም ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ
እንደሆነ ስህተቱ የሚመለከተው የመንግስት አካል በፍትሐብሔር ኃላፊነት ተጠያቂ
የመሆን ኃላፊነት፣
10. በየክልሎቹ ም/ቤቶች ያወጧቸውን አዋጆችና ደንቦች በተሟላ ሁኔታ ለማስፈፀም
የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን የማውጣት፣
11. ቢሮዎችንና በየደረጃው የተቋቋሙ መዋቅሮችን በሰው ኃይል እና በቁሳቁስ የማደራጀት
እና ሌሎች ኃላፊነቶችን ያጠቃልላል፡፡

ከግዴታዎች እና ኃላፊነቶች ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮች59

 በአንድ መሬት ላይ ሁለትና ከዚያ በላይ ደብተር የመስጠት ችግር፣


 የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሲሰጥም አዋሳኞችን በአግባቡ አለመግለጽ፣ አጠራጣሪ
ሁኔታ ሲኖር ቦታው ድረስ ሄዶ አለማየት፤ በይዞታ ላይ የተጠቀሰው አዋሳኝ
በእርግጥ በተጨባጭ ከመሬቱ ላይ ከሚገኘው ጋር ያለመጣጣም ችግር፣

እነዚህ ችግሮች ፀሐፊው በሥራ አጋጣሚ የገጠሙት እና በፍ/ቤት በሚቀርቡ ጉዳዮች የተረዳቸው ናቸው፡፡
59

68
 የመሬት ልኬታው የመሬቱን መጠን በትክክል አለማስቀመጥ፤
 የተለያዩ ሃላፊዎች በተቀየሩ ቁጥር የተሰጡ ማስረጃዎች የመቀየር ችግር፤
 የመሬት ድልድል በተካሄደበት ወቅት መሬቱ የተመዘገበበት የገጠር መሬት
መመዝገቢያ መዝገብ መጥፋት እና ሌሎች የመሳሰሉት ችግሮች ይገኛሉ፡፡

ስለዚህ እንዚህን እና ሌሎች ያልተጠቀሱ ችግሮችን ለማስወገድ ምን መደረግ አለበት የሚለውን


ሰልጣኞች በየስልጠና ማዕከላቸው እንደየክልላቸው ነባራዊ ሁኔታ በሰፊው ሊወያዩበት እና
የመፍትሔ ሀሳቦችን ሊያፈላልጉ ይገባል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች
1. በአዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀፅ 5/4/ መሰረት የአዋጁ ዋና መርህ የሆነው የህዝቦች
ተሳትፎ በመሬት አስተዳደር ረገድ እንዴት እንደሚፈፀም ከአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ ተወያዩበት፡፡

2. የአስተዳደር አካላት በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት የአስተዳደር ውሣኔ ባይሰጡ ዜጐች


መብታቸውን በምን ዓይነት ሁኔታ ነው ማስከበር ያለባቸው?

3. የገጠር መሬትን ለግጦሽ መሬት በወል ይዞታ መጠቀሚያነት የተሰጣቸው


ባለይዞታዎች አልፎ አልፎ ለእርሻ ሲገለገሉበት ይስተዋላል፡፡ ይህ ድርጊት የወንጀል
ኃላፊነትን ያስከትላል?

4. አንድ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነና በግብርና ስራ ለመተዳደር የፈለገ ሰው


በሚኖርበት ቀበሌ /ወረዳ ውስጥ መሬት በነፃ የማግኘት መብት ስላለኝ መሬት ይሰጠኝ
ብሎ ጥያቄውን የሚያቀርበው ለማን ነው? ክስ ቢመሰርትስ ጉዳዩ በፍርድ ሊታይ
የሚችል (Justiciable Matter) ነው ወይ?

5. ማንኛውም የመሬት ባለይዞታ የገጠር መሬት ባለይዞታ ግዴታዎች ያልተወጣና


አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበት ራሱን ካላስተካከለ ከአስተዳደራዊ እርምጃ በተጨማሪ
በመሬቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት በፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ካሣ እንዲከፍል ይደረጋል
በማለት በአማራ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደር እና

69
አጠቃቀም ህግ የተደነገገ ተጠያቂነት እንዳለ ተመልክተናል፡፡ ለመሆኑ ካሳው
የሚከፈለው ለማን ነው? የሚታሰበውስ እንዴት ነው? ተግባራዊ ማድረግ ይቻላልን?

6. ከአስተዳደራዊ እና ፍትሐብሔራዊ ኃላፊነት በተጨማሪ የገጠር መሬት አስተዳደርና


አጠቃቀም ሕግን የጣሰ ወይም አፈፃፀሙን ያሰናከለ ማንኛውም ሰው አግባብ ባለው
የወንጀል ህግ ድንጋጌ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ በየትኛው ዲንጋጌ ነው የሚጠየቀው?

7. በአንድ መሬት ላይ ሁለትና ከዚያ በላይ ደብተር በመስጠት ችግር ለሚከሰት ጉዳት
ትክክለኛው የመሬቱ ባለይዞታ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መስሪያ ቤትን ካሳ
መጠየቅ አይችልም ወይ?

70
ምዕራፍ አራት
የገጠር መሬት ይዞታን ለሕዝብ አገልግሎት ስለማስለቀቅና ስለካሳ አከፋፈል

የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት የገጠር መሬት ባለይዞታነትን በማስመልከት ቀደም ሲል በዚህ ጽሁፍ


እንደተመለከትነው በአንቀጽ 40 እና 89(5) ላይ ዜጎች በገጠር መሬት አጠቃቀም ላይ
ስለሚኖራቸው መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም አስተዳደሩን በማስመልከት የገጠር መሬት
የባለቤትነት መብት የሕዝብና የመንግስት መሆኑን አስቀምጧል፡፡ አሁን ከያዝነው ርዕሰ ጉዳይ
አንፃር በዚሁ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 40(8) ላይ “የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ
ሆኖ መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሣን በቅድሚያ በመክፍል
የግል ንብረትን ለመውሰድ ይችላል” በሚል ተደንግጎ እናገኛለን፡፡

የኢፌዴሪ የገጠር መሬት አስተዳደር ሕግን ጨምሮ የአምስቱንም ብሔራዊ ክልሎች የገጠር
መሬት ሕጎች ስንመለከት የገጠር መሬት ለአርሶ አደሮች በነፃ፣ ለባለሃብቶች በሊዝ የሚሰጥ
ቢሆንም መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ መንግስት ተገቢውን ካሣ በመክፈል
መውሰድ እንደሚችል ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ ስለሆነም በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የገጠር መሬት
ለሕዝብ አገልግሎት በሚለቀቅበት ጊዜ የመሬቱ ባለይዞታና መንግስት ስላላቸው መብትና
ስለተጣለባቸው ግዴታ፣ ስለካሣ አከፋፈል እና ካሣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች አፈታት
ስርዓትን እንመለከታለን፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች

ሰልጣኞች የዚህን ምእራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-

 የገጠር መሬት ለሕዝብ አገልግሎት የሚለቀቅበትን ሁኔታ ለይተው ያውቃሉ፡፡

 የገጠር መሬት ለሕዝብ አገልግሎት በሚለቀቅበት ጊዜ የመሬቱ ባለይዞታና መንግስት


ስላላቸው መብትና ስለተጣለባቸው ተነፃፃሪ ግዴታ ለይተው ያውቃሉ፡፡

 የገጠር መሬት ለሕዝብ አገልግሎት በሚለቀቅበት ጊዜ ለመሬቱ ባለይዞታ ስለሚከፈሉት


የካሣ አይነቶችና ስለካሣ አከፋፈል ስርዓት ለይተው ያውቃሉ፡፡

 ካሣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች የሚፈቱበትን ስርዓትና ስለሚታዩ ችግሮች እውቅና


ይኖራቸዋል፡፡

71
4.1 የሕዝብ ጥቅም እና የካሳ ጽንሰ-ሀሳብ

የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት በአንቀጽ 40(8) ላይ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በይዞታ መሬታቸው


ላይ ለሚያደርጓቸው ቋሚ ስራዎችና ማሻሻያዎች ባለቤት መሆን እንደሚችሉ ደንግጓል፡፡
በመሆኑም መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚወሰድበት ወቅት በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት
ተገቢው ካሣ መከፈል እንዳለበትም ሕገ-መንግስቱ አስቀምጧል፡፡

የአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 2(1) እና 2(5) ድንጋጌዎችን ስንመለከት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ
ተደጋግመው የሚነሱና በሕግ ባለሙያዎች ሳይቀር ልዩነት ሲፈጥሩ የሚስተዋሉትን “ካሣ እና
የሕዝብ ጥቅም” የሚሉትን ነጥቦች በማያሻማ መንገድ ለአፈፃፀም ካለው ፋይዳ አንፃር ብቻ
ሳይሆን አፈፃፀሙ በዜጎች መብት ላይ ከሚፈጥረው ተፅዕኖ አንፃርም ጭምር ሲመዘን የሕጉ
አቀራረፅና ዓላማ መፍትሔ ሰጭነቱ እንዲታይ በሚያደርግ መልኩ ተተርጉመው እናገኛለን፡፡
ከዚህ በመነሳትም ይኸው ሕግ “ካሣ ማለት የገጠር መሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት
ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት በዓይነት ወይም በገንዘብ ወይም በሁለቱም የሚከፈል
ክፍያ ነው በማለት ደንግጓል፡፡” ከዚህ ላይ ሶስት ዓይነት የካሣ አከፋፈል ስርዓቶች እንዳሉ
እንረዳለን፡፡ እነርሱም በዓይነት የሚከፈል የካሣ ስርዓት፣ በገንዘብ የሚከፈል የካሣ ስርዓት እና
በዓይነትና በገንዘብ የሚከፈል የካሣ ስርዓት ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ “የሕዝብ ጥቅም ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች
በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በቀጣይነት
ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል በከተማ መዋቅራዊ ፕላን ወይም በልማት ዕቅድ መሠረት
የሕዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው ነው” ሲል ደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌም ሶስት አበይት
ዓላማዎችን ይዞ እናገኛለን፡፡

1. በቅድሚያ የከተማ መዋቅራዊ ፕላን ወይም የልማት ዕቅድ መኖር፣

2. የሕብረተሰቡ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ መሆንና

3. ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን የማጎልበት ዓላማዎች ናቸው፡፡

ለአዋጅ ቁጥር 455/97 ዓላማ ካሳን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ይኸውም በመሬቱ ላይ
ለሚገኘው ንብረትና ቋሚ መሻሻል የሚከፈል ካሳ እና የመፈናቀያ ካሳ ናቸው፡፡ ለንብረቱ
የሚከፈለው ካሳ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ ለመተካት የሚያስችል ክፍያ ሲሆን በመሬቱ ላይ

72
ለተደረገው ቋሚ መሻሻል የሚከፈለው ካሳ በመሬቱ ላይ የዋለውን ገንዘብ (Capital) የጉልበት
ዋጋ (Labor) የሚተካ ይሆናል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመሬቱ ላይ የሚገኘው ንብረት ወደ ሌላ
መሬት ተዛውሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል ንብረት ከሆነ ንብረቱን ለማንሳት ለማጓጓዝና
መልሶ ለመትከል የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈንን ይጨምራል፡፡

ሁለተኛው የካሳ ዓይነት የመፈናቀያ ካሳ ሲሆን የገጠር መሬትን በሚመለከት መሬቱ በቋሚነት
ወይም በጊዜያዊነት ሲወሰድ ሊከፈል የሚገባው የካሳ መጠን ሲሆን በአዋጁ አንቀፅ 8(1) እና
(2) ላይ ተመልክቷል፡፡ እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀፅ 7(3) መሠረት የገጠር መሬት
ለህዝብ ጥቅም ሲባል ባለይዞታው መሬቱን እንዲለቅ ሲደረግ በመሬቱ ላይ ላደረገው ማሻሻያና
ላፈራው ንብረት ተመጣጣኝ ካሳ ይከፈለዋል ወይም በለቀቀው መሬት ምትክ በተቻለ መጠን
ሌላ ተለዋጭ መሬት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታው መሬቱን እንዲለቅ
የሚደረገው በፌደራል መንግስቱ ከሆነ የሚከፈለው ካሳ ተመን በፌዴራል የመሬት አስተዳደር
ህግ ይወሰናል፡፡ ነገር ግን መሬቱን እንዲለቅ የሚደረገው በክልል መንግስት ከሆነ የካሳ ተመኑ
በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር ህግ ይወሰናል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ባወጣው የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 130/1999 አንቀፅ 6(11) እና (12)
መሠረት የሚከፈለው ካሳ በይዞታው ላይ ለተፈራው ንብረትና ለተቋረጠበት ጥቅም (benefits
lost) ሲሆን በተቻለ መጠን ተመጣጣኝ (ተመሳሳይ) የሆነ መሬት በምትክ ሊያገኝ /ሊሰጠው/
ይችላል፡፡ ነገር ግን በምትክ ተመጣጣኝ መሬት መሰጠት ካልተቻለ ለማቋቋሚያ የሚሆን ካሳ
ይከፈለዋል ፡፡

የደቡብ ክልል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 7(3) መሰረት በመሬቱ ላይ ለተደረገው
ማሻሻያ እና ለተፈራው ንብረት ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ ይከፈላል፡፡ በተለቀቀው መሬት
ምትክ ተለዋጭ መሬት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ መሬቱንም እንዲለቅ የተደረገው በፌዴራል
መንግስት ከሆነ የካሳው ተመን በፌዴራል ህግ ይወሰናል፡፡ ነገር ግን መሬቱን እንዲለቅ
የተደረገው በክልሉ መንግስት ከሆነ የካሳው መጠን የክልሉ መንግስት በሚያወጣው ደንብ
መስረት እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

የትግራይ ክልል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 136/2000 አንቀፅ 21 መሰረት የካሳው የአከፋፈል
ሁኔታ የፌዴራል መንግስት ካወጣው አዋጅ ቁጥር 456/97 አንቀጽ 7 እና 8 ጋር አንድ

73
ዓይነት ነው፡፡ ነገር የካሳውን ቀመር በሚመለከት የፌዴራል መንግስቱ ካወጣው አዋጅና ደንብ
በተጨማሪ በክልሉ በሚወጣ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

የአማራ ክልል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀፅ 28 ለባለይዞታው ወይም ለተጠቃሚው
ተገቢው ካሳ በቅድሚያ መከፈል አለበት ይላል፡፡ በሌላም በኩል የገጠር መሬት ለህዝብ ጥቅም
ሲባል እንዲለቀቅ የሚወስነው የባለስልጣን ቢሮው፤ የወረዳ ጽ/ቤት ሲሆን መሬቱ የሚለቀቅበት
ምክንያት ከአካባቢው ህብረተሰብ ልማት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ሲሆን ጉዳዩ ለቀበሌው ህዝብ
ውይይት ቀርቦ የብዙሃኑን ድጋፍ ማግኘት አለበት፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባወጣው አዋጅ ቁጥር 85/2002 አንቀጽ 33 መሰረት ለባለይዞታው
ወይም ለተጠቃሚው ተገቢው ካሳ በቅድሚያ መከፈል አለበት፡፡ በሌላም በኩል የገጠር መሬት
ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቀቅ የሚወስነው የባለስልጣን ቢሮው የወረዳ ጽ/ቤት ሲሆን መሬቱ
የሚለቀቅበት ምክንያት ከአካባቢው ህብረተሰብ ልማት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ሲሆን ጉዳዩ
ለቀበሌው ህዝብ ውይይት ቀርቦ የብዙሃኑን ድጋፍ ማግኘት አለበት፡፡ ማናቸውም የወረዳ
አስተዳደር የገጠር መሬት እንዲለቀቅ ሲወስን ከባለስልጣኑ የሚያገኘውን መረጃ መሰረት
በማድረግ መሬቱ የሚለቀቅበትን ጊዜና የሚከፈለውን የካሳ መጠን ገልጾ ለመሬቱ ባለይዞታ
ወይም ተጠቃሚ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ በካሳው መጠን ቅር የተሰኘው ወገን ጉዳዩን
ለባለስልጣኑ የማቅረብና የማስመርመር መብት ይኖረዋል፡፡ የካሳው መጠንም የሚወሰነው
በአዋጅ ቁጥር 455/97 መሰረት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

4.2 ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የገጠር መሬት ይዞታ በሚለቀቅበት ጊዜ


የባለይዞታውና ባለስልጣን መ/ቤቱ ስለሚኖራቸው መብትና ግዴታ

4.2.1 የባለይዞታዎች መብትና ግዴታ

 ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ የማግኘት መብት፡- ማንኛውም ባለይዞታ መሬቱንና በመሬቱ


ላይ ያሰፈረውን ሀብት ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቅ በሚመለከተው አካል ሲወሰንና
ይህን መሠረት በማድረግ ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው ከ90 ቀን ባላነሰና ባልበዛ ጊዜ ውስጥ
ቦታውን ለሚመለከተው አካል ማስረከብ ቢኖርበትም ለንብረቱ ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ
ማግኘት ይኖርበታል፡፡ (ሕገ-መንግስት አንቀጽ 40(8) እና የአዋጁ አንቀጽ 7 እና 8፡፡

74
 የመሬት ባለይዞታ ካሣ የማግኘት መብት እንዳለው ሁሉ ካሣውን ተቀብሎ መሬቱን
የማስረከብ ግዴታም አለበት፣ ለዚህም የአዋጁ አንቀጽ 4 “አንድ ለህዝብ ጥቅም ሲባል
ከይዞታው እንዲለቅ የተወሰነበት ሰው ካሣውን ተቀብሎ በ90 ቀናት ውስጥ መሬቱን
ለወረዳው ወይም ለከተማው አስተዳደር ማስረከብ አለበት፡፡” ሲል ደንግጓል ይህም
የሚያሳየው የመብትና ግዴታን አለመነጣጠል ነው፡፡

 ካሣን መሠረት በማድረግ አቤቱታ የማቅረብ መብት፡- አንድ ለህዝብ ጥቅም ሲባል
ይዞታውን እንዲለቅ የሚደረግ ሰው የተወሰነው የካሣ መጠን ላይ አንሷል የሚል ከሆነ
ወይም ያልተገመተ ንብረት ቀርቷል ወዘተ… በሚል ምክንያት የገማቾችን ውሳኔ
በመቃወም አቤቱታውን በገጠር መሬት ነክ አቤቱታ ሰሚ አስተዳደራዊ አካል ሊያቀርብ
ይችላል፡፡ ይህ ባልተደራጀበት ሁኔታ ስልጣን ወዳለው መደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ ይቻላል፡፡
ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ማንኛውም ዜጋ ከህግ ውጭ የንብረት መብቱን እንደማያጣና
በየደረጃው ባሉ አስተዳደር አካላት በሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ በማለት ቀጥሎ
ወዳለው ይግባኝ ሰሚ መደበኛ ፍ/ቤት መሄድ እንደሚችል ነው፣ (አንቀጽ 10 እና 11)፡፡

4.2.2 የባለስልጣን መ/ቤቱ መብትና ግዴታ

በገጠር ያለ አስተዳደር ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የከተማ ቦታን ወይም የገጠር መሬትን
በሚያስለቅቅበት ጊዜ ለባለይዞታው ማሳወቅ፣ ካሣ መክፈልና ባለይዞታው ካሣውን ለመቀበል
ፈቃደኛ ባልሆነበት ጊዜም ሒሳቡን በዝግ የባንክ ሒሳብ በማስቀመጥ የሚለቀውን ዜጋ በተቻለ
መጠን እንዲቋቋም የማድረግና የሚለቀቀውን ንብረት መሠረት ያደረገ መረጃ የመያዝ
ግዴታዎች ያሉበት ሲሆን ባለይዞታው ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባልሆነ ጊዜ የፖሊስ ኃይል ተጠቅሞ
ማስለቀቅ እንደሚችል አዋጁ በአንቀጽ 4(5) በግልጽ ይደነግጋል፡፡

ስለዚህ አዋጅ ቁጥር 455/97 ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የገጠር መሬት በሚለቀቅበት ጊዜ የማሳወቅ
ስርዓት፣ የመገመት፣ የንብረት ግምትና መፈናቀያ ካሣ ስለሚከፈልበት ስርዓትና በተወሰነው
ካሣ ያልተስማማ ባለይዞታ አቤቱታውን ወደሚመለከተው አካል የማቅረብና አሁንም በተሰጠው
ውሳኔ ቅር ከተሰኘ ይግባኝ ብሎ መሄድን ባካተተ መንገድ የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 40(8)
በቅድሚያ የማግኘት መብት ተከትሎ የወጣ ሕግ በመሆኑ ዜጎች የንብረታቸው የወደፊት እጣ
ፋንታ ግልጽ የሆነ የባለቤትነት ስሜት ኑሮአቸው በልማቱ መስክ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ
የሚያደርግ ነው፡፡

75
4.3 የገጠር መሬት የካሣ አከፋፈል ስሌት

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ከይዞታው የሚለቅ ሰው በቅድሚያ ካሣ የማግኘት መብት


ሕገመንግስታዊ መብት ነው፡፡ የሕገመንግስቱን አንቀጽ 40(8) መርህ ተግባራዊ ለማድረግ
የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 7 ላይ የካሣ መሠረትና መጠን በሚል ርዕስ ስርና
አንቀጽ 8 ላይ የማፈናቀያ ካሣ በሚል ርዕስ ስር ሁለት ዓይነት የካሣ ክፍያዎች እንዳሉ
በሚገልጽ መልኩ ተደንግጓል፡፡ በአንቀጽ 7 መሠረት የካሣ መሠረት ሆኖ የሚወሰደው እንዲለቅ
በሚመለከተው አካል የተወሰነበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት እና በመሬቱ ላይ
ላደረገው ቋሚ መሻሻል የሚከፈል ካሣ ነው፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 8 መሠረት የሚከፈል የማፈናቀያ ካሣ በአንቀጽ 7 ካየናቸው የካሣ አከፋፈሎች


እና የካሣ መሠረቶች በተጨማሪ አንድ ሰው ከይዞታው በመፈናቀሉ ብቻ የሚከፈል የሁሉም
ባለይዞታዎች መብት ነው፡፡ አሠላሉ እንደሚከተለው ነው፡፡ በቋሚነት እንዲለቅ የሚደረገው
የገጠር መሬት ባለይዞታ ሲሆን እንዲለቅ ከመደረጉ በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት የነበረውን
ገቢ በአስር ተባዝቶ እና በአዋጁ አንቀጽ 7 መሠረት ማግኘት የሚገባውን ካሣ ታክሎበት ካሣ
ይከፈለዋል፡፡ በአጭሩ የካሣ አከፋፈል ቀመር፡-

ቋሚ የማፈናቀያ ካሣ = ባለፈው 5 ዓመት ያገኘው አማካኝ ዓመታዊ ገቢ x 10 + ንብረቱ


ባለበት ሁኔታ መትከያ (የሚተከል ንብረት ካለ) + የቋሚ ማሻሻያ ገንዘብና የጉልበት ዋጋ (ካለ)
+ የንብረቱ ማንሻ፣ ማጓጓዣ እና መልሶ መትከያ ወጭ (የሚጓዝ ከሆነ)

ለተወሰነ ጊዜ ከገጠር መሬት ይዞታው ለሚለቅ ባለይዞታ ወይም ለወል መሬት ባለይዞታዎች
እንዲለቁ ከመደረጉ በፊት በነበሩት 5 ዓመታት ያገኙት አማካኝ ዓመታዊ ገቢ መሬቱ
እስኪመለስ ባለው ጊዜ ታስቦ በአንቀጽ 7 የሚከፈለው ካሣ ተጨምሮበት የማፈናቀያ ካሣ
ይከፈላቸዋል፡፡ ማለትም፡-

የተወሰነ ጊዜ ማፈናቀያ ካሣ = ባለፈው 5 ዓመት ያገኘው አማካኝ ዓመታዊ ገቢ x ተፈናቅሎ


የሚቆይበት ዓመት + ንብረቱ ባለበት ሁኔታ መትከያ (የሚተከል ከሆነ) + የቋሚ ማሻሻያ
ገንዘብና የጉልበት ዋጋ (ካለ) + የንብረቱ ማንሻ፣ ማጓጓዣና መተኪያ ወጭ (የሚጓዝ ከሆነ)

ሕጉ ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ከይዞታ መልቀቅን በተመለከተ ለቋሚ መልቀቅ ከተከተለው ስሌት


ጋር ሲታይ ከተወሰነ የብዜት መሠረት ለውጥ ውጭ ሌላ ልዩነት የሌለው ቢመስልም በአንቀጽ

76
8(1) እንደተመለከተው ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ መልቀቅ ለካሣው ብዜት ለሆነው 10 ዓመት
ለሚበልጥ ጊዜ በጊዜያዊነት ከይዞታው ለቆ መቆየት የለበትም፡፡ ሕጉ ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ
መፈናቀል ከመሬቱ ለቆ የሚቆይበት ጊዜ ከ10 ዓመት በላይ ከሆነ ለተወሰነ ጊዜ ከገጠር መሬት
ይዞታ መልቀቅ መሆኑ ቀርቶ እንደቋሚ ከገጠር መሬት ይዞታ መልቀቅ ይቆጠርና የካሣ
አከፋፈሉ በቋሚ መልቀቅ አከፋፈል ስርዓትን የተከተለ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ከላይ ከተመለከትናቸው የካሣ አከፋፈል ስሌቶች በተጨማሪ አንድ ሰው ካለው የገጠር መሬት
ይዞታ ለህዝብ ጥቅም ሲባል እንዲለቅ በሚደረግበት ጊዜ ሌላ አማራጭ የካሣ አከፋፈል ስርዓት
በአንቀጽ 8(3) ላይ ተደንግጓል፡፡ ይኸውም ተመጣጣኝ ገቢ የሚያስገኝና በቀላሉ ሊታረስ እና
ምርት ሊያስገኝ የሚችል ተተኪ መሬትና መሬቱ እንዲለቀቅ ከመደረጉ በፊት በነበሩት አምስት
ዓመታት ያገኘው አማካኝ ዓመታዊ ገቢውን ያህል በካሣነት ይከፈለዋል፡፡ ስለዚህ ሕጉ የገጠር
መሬት ይዞታን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ማስለቀቅንና የካሣ አከፋፈሉን በተመለከተ በቋሚነት
ለሚለቅ በመሬት ላይ ለሚገኘው ንብረት የተደረገ ቋሚ መሻሻል ካለ ለዚህ የተደረገውን ወጭና
እንደሁኔታው የንብረት ማንሻ፣ ማጓጓዣና የንብረት መትከያ ወጭን የሚሸፍን ካሣና ከዚህ
በተጨማሪ እንደየሁኔታው የሚከፈል የማፈናቀያ ካሣን የመክፈል ስርዓትን የያዘ ነው፡፡ ይህም
ብቻ ሳይሆን በቋሚነት መልቀቅንና ለተወሰነ ጊዜ መልቀቅን መሠረት በማድረግ የተለያየ የካሣ
አከፋፈል ስርዓትን የሚከተልና ተተኪና የሚመጥን መሬት ባለበት ሁኔታ ምትክ መሬት
በመስጠት ለየት ያለ የካሣ አከፋፈል ስርዓት የሚከተል ሕግ ነው፡፡

እስካሁን ካሣ የሚከፈልበትን ስርዓትና የምንጠቀምበትን ቀመር እያየን መጥተናል ይህ ማለት


ግን ሁልጊዜ ካሣ ይከፈላል ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በአዋጁ መሠረት መሬቱ የሚለቀቅ
ስለመሆኑ የተሰጠው ውሳኔ ለባለይዞታው ከደረሰ በኋላ ለተሰራ ወይም ለተሻሻለ ቤት፣ ለተዘራ
ሰብል፣ ለተተከለ ቋሚ ተክል ወይም በመሬት ላይ ለተደረገ ቋሚ ማሻሻያ ካሣ አይከፈልም፡፡
ስለዚህ በሕገ-መንግስቱ የተረጋገጠው ቅድሚያ ካሣ የማግኘት መብት ቀጥሎ የወጣ አዋጅና
ደንብ በዝርዝር እንዴት መፈፀም እንዳለበት ከፍ ብሎ ባየነው መልኩ የተደነገገ ቢሆንም ህግ
ከሚፈቅደው ወጭ በመሆን ማለትም ለህዝብ ጥቅም ሲባል ከቦታው እንደሚለቅ እየተነገረው
በዚህ መሬት ላይ ለሚፈራው ንብረት ካሣ የማይከፈልበት መሆኑን ከግምት ውስጥ ማስገባት
የግድ ይላል፡፡

77
4.4 ካሣን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች ስለሚፈቱበት ስርዓትና የሚስተዋሉ
ችግሮች

4.4.1 ክርክሮች ስለሚፈቱበት ስርዓት

ካሳን አስመልክቶ የሚቀርቡ አቤቱታዎችና ይግባኝ በምን መልኩ መፈታት እንዳለባቸው በአዋጅ
ቁጥር 455/97 አንቀጽ 11 በግልጽ ተደንግጓል፡፡ በቅድሚያ በአዋጁ መሰረት ይዞታው
የተወሰደው ያለአግባብ ነው በሚል መሬት እንዲለቀቅ በተላለፈው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ማቅረብ
የሚቻልበት ሁኔታ በአዋጁ ውስጥ አልተካተተም፡፡ ቅሬታ ማቅረብ የሚፈቀደው በካሳው መጠን
ይሆናል፡፡ ካሳውን አስመልክቶ ቅሬታው የሚቀርበው ስልጣን ላላው መደበኛ ፍ/ቤት ሲሆን ይህ
ስልጣን ያለው ፍ/ቤት ሊሆን የሚችለው የወረዳ ፍርድቤት ነው ወይስ ለዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤት የሚለዉ እንደንብረቱ ግምት የሚታይ መሆኑን ካለው አሰራር ለመገንዘብ ይቻላል፡፡

ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት ካሳውን አስመልክቶ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን
የከተማው የከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ካለ ለዚሁ ፍ/ቤት ይግባኙን ማቅረብ
ይችላል፡፡ ነገር ግን የወረዳው ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘው ወገን ይግባኙን ለመደበኛው
ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በግልፅ ባያመለክትም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ የይግባኝ
ቅሬታው ውሳኔው በወረዳው ፍ/ቤት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ መቅረብ
አለበት፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻው ይሆናል፡፡

በሌላም በኩል ይግባኝ የሚጠይቀው የመሬት ባለይዞታ ይግባኝ ሊታይለት የሚችለው እንዲለቅ
የታዘዘውን መሬት ለወረዳው አስተዳደር ያስረከበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (ሰነድ)
ከይግባኙ ጋር አያይዞ ካቀረበ ብቻ ይሆናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ምንም እንኳን ይግባኝ ቢጠየቅም
በይግባኙ ምክንያት የመሬት ማስለቀቅ ውሳኔው አፈፃፀም ሊዘገይ አይችልም፡፡ በሌላ አገላለጽ
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የመሬት ማስለቀቅ ውሳኔው እንዲታገድ ወይም እንዳይፈፀም ለማገድ
ወይም ለማዘዝ አይቻልም፡፡

4.4.2 የሚስተዋሉ ችግሮች

በቀጥታ አዋጁ ላይ የሚታየው ችግር ይግባኝ የሚጠይቀው የመሬት ባለይዞታ ይግባኝ


በሚጠይቅበት ወቅት መሬቱን ለወረዳው አስተዳደር ያስረከበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ከይግባኝ ቅሬታው ጋር አያይዞ እንዲቀርብ መገደዱ ነው፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ እየታየ ባለበት ሁኔታ

78
በአጋጣሚ በመሬት ላይ የተፈራው ንብረት ቋሚ መሻሻል በአስፈፃሚው አካል ከነበረበት መሬት
እንዲነሳ ወይም እንዲፈርስ ወይም እንዲነቀል ቢያደርግና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በተለቀቀው
መሬት ላይ የነበረውን ንብረትና ቋሚ መሻሻል ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ቢፈልግ
ንብረቱና ቋሚ መሻሻሉ በመሬቱ ላይ ስለሌለ ውሳኔ መስጠቱ ላይ ሊቸገር ይችላል፡፡ ምናልባት
ንብረቱና ቋሚ መሻሻሉ እንደገና በሌላ ባለሙያ መገመት አለበት ቢባልም እንኳን ንብረቱ እና
ቋሚ መሻሻሉ በቦታው ላይ ስለማይኖር ለግምትም አስቸጋሪ ይሆናል ፡፡

ከዚህም ባሻገር ጉዳዩ በይግባኝ በሚታይበት ወቅት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የመሬት መለቀቁን
አፈፃፀም ወይም ሂደት እንዳያግድ መደረጉ ምናልባት መሬቱ ለህዝብ ጥቅም የሚሰጠውን
አገልግሎት ከማፋጠንና ሙስናን ከመዋጋት አንፃር ጠቃሚ መስሎ ቢታይም የመሬት
ባለይዞታውን መብትና የይግባኝ ሰሚውን ፍ/ቤት ስልጣን በእጅጉ የሚገድብ ይሆናል፡፡

አመልካቾች /ይግባኝ ባዮች /መሬቱን ከማስረከባቸው በፊት መሬቱ ይለካል፡፡ ነገር ግን መሬቱ
ተለክቶ የሚመለከተው አካል መሬቱን ከተረከበ በኋላ የመሬቱ ስፋት መጀመሪያ ላይ ከተለካው
መሬት ያነሰ ሆኖ ቢገኝ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ መሬቱ መጀመሪያ ላይ ሲለካ 500 ካሬ
ሜትር ነው ተብሎ ነገር ግን በመሬት አስተዳደር የሚገኘው የመሬት ስፋት 200 ካሬ ሜትር
ሊሆን ይችላል ወይም ይሆናል፡፡ አመልካቹ ያስረከብው መሬት ስፋት ከፍተኛ ሆኖ እያለ በሰነድ
በመሬት አስተዳደር የሚገኘው መሬት ስፋት (መጠን) ዝቅተኛ / አነስተኛ መሆኑ በይግባኝ
ለሚታየው የካሳ አወሳሰን ያስቸግራል፡፡

አቤቱታ ለአስተዳደር ጉባኤው የሚያቀርበው አመልካች (ይግባኝ ባዩ) መሬቱን ካስረከበ በኋላ
በመሆኑ አስተዳደር ጉባኤው መሬቱን ሄዶ በሚመለከትበት ወቅት የተወሰደው ንብረት
በተባለው ቦታ ላይ አለመገኘት ካሳውን በሚመለከት ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ያስቸግራል፡፡
በተጨማሪም በምትክ የሚሰጠው መሬት ተመጣጣኝ አለመሆኑ እና የካሳው መጠን በአግባቡ
አለመሰላቱ እንደችግር የሚታዩ ናቸው፡፡

79
የመወያያ ጥያቄ

1. መንግስት አንድን የገጠር ባለይዞታ ለህዝብ ጥቅም በሚያስለቅቅበት ጊዜ የሚኖረው


የካሣ አከፋፈል ስርዓት የንብረት ግምት ካሣ እና የማፈናቀያ ካሣ ተብሎ እንደሚከፈል
በአዋጁ አንቀጽ 7 እና 8 ተደንግጓል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው የአተማመንና የቀመር
ልዩነት ምንድን ነው?

2. በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40(8) ላይ “የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ


መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሣን በቅድሚያ
በመክፍል የግል ንብረትን ለመውሰድ ይችላል” በሚል ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ የአንድ
ወረዳ አስተዳደር በአንድ ቀበሌ ውስጥ ያሉ በረካታ አርሶ አደሮችን አንስቶ ለአንድ
ኢንቨስተር ቢሰጥ ለህዝብ ጥቅም የሚውል ነው ሊባል ይችላል ወይ?

3. የወል መሬት ለልማት ስራ ቢፈለግ ካሳ ሊከፈል ይገበዋል ወይ? ካሳ የሚከፈል ቢሆን


ለማን ነው የሚከፈለው?

4. መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲነሳ የመሬት ባለይዞታው የካሳ መጠኑን በተመለከተ ይግባኝ
በሚጠይቅበት ወቅት መሬቱን ለወረዳው አስተዳደር ያስረከበ መሆኑን የሚያረጋግጥ
ማስረጃ ከይግባኝ ቅሬታው ጋር አያይዞ እንዲቀርብ ይገደዳል፡፡ ምክንያቱ ምንድን ነው?
ጉዳዩ በይግባኝ እየታየ ባለበት ሁኔታ በአጋጣሚ በመሬት ላይ የተፈራው ንብረት ቋሚ
መሻሻል በአስፈፃሚው አካል ከነበረበት መሬት እንዲነሳ ወይም እንዲፈርስ ወይም
እንዲነቀል ቢያደርግና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በተለቀቀው መሬት ላይ የነበረውን
ንብረትና ቋሚ መሻሻል ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት ቢፈልግ ንብረቱና ቋሚ
መሻሻሉ በመሬቱ ላይ ስለሌለ ውሳኔ ለመስጠት ሊቸገር ይችላል፡፡ መፍተሔው ምንድን
ነው?

80
ምዕራፍ አምስት
የመሬት ይዞታ መብት መከበር ዋስትና እና ክርክሮች የሚፈቱበት አግባብ

የገጠር መሬት ይዞታ መብት ዋስትናው የተረጋገጠ ሊሆን የሚችልባቸው በርካታ ምክንያቶች
አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ አርሶ አደሮች ያላቸው የመሬት ይዞታ መብት ራሱ በጊዜ
የተገደበ አለመሆኑን በግልጽ በሕግ መደንገጉ ነው፡፡ ይህ በሕግ ካልተጠበቀ ደግሞ ይዞታው
በማንኛውም ጊዜ እየተቆረሰ ለሌላ ሰው እንዲሰጥ ወይም ለሌላ ለተፈለገ ተግባር እንዲውል
ለማድረግ በር ስለሚከፍት በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት የተሰጠውን ከይዞታ ያለመነቀል መብት
በአተገባበር ችግር ምክንያት ዋስትና የለሽ ያደርገው ነበር፡፡ ሁለተኛው ምክንያትም በየጊዜው
የመሬት ሽግሽግ እንዳይካሄድ በሕግ መከልከሉ ነው፡፡ የገጠር መሬት ሽግሽግ ማድረግ
የሚያስፈልገው መሬት ካላቸው ቀንሶ መሬት ለሌላቸው ሰዎች ለመስጠት በመሆኑ ከተቀባዩ
አንፃር ፍትሐዊነቱ ባያከራክርም መሬት ከሚቀነስበት ባለመብት አንፃር ደግሞ የንብረት
መብትን ስጋት የተሞላበትና ዋስትና የለሽ ያደርገዋል፡፡ ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የአንድ
የገጠር መሬት ባለይዞታ መሆንን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ለባለይዞታው መስጠት ነው፡፡
ለገጠር መሬት ባለይዞታ መብት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ካልተሰጠ አንዱ የመሬት ባለይዞታ
ነኝ ባይ ከሌላው ባለይዞታ የተሻለ መብት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
በዚህም ምክንያት የፌደራሉን ጨምሮ በክልሎችም የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች የገጠር
መሬት ይዞታ መብት የጊዜ ገደብ እንደሌለው በመደንገጉ፤ የመሬት ሽግሽግም በመርህ ደረጃ
በመከልከሉ እና በክልሎች ለሚገኙ አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች የምስክር ወረቀቱ በመሰጠቱ
የመሬት ይዞታ ዋስትና የሕግ ጥበቃ አግኝቷል ማለት ይቻላል፡፡

የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መብት ጥበቃ በሕግ በበቂ ደረጃ ተደንግጓል ቢባል እንኳ መብቶቹ
በሚጣሱበት ጊዜ አጥፊዎችን ለማረምና መብቱን መልሶ ለማስከበር እንዲቻል ለማድረግ ፍትህ
የማግኘት መብት ከሌለ የሕጉን ድንጋጌ ትርጉም አልባ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ምዕራፍ
ውስጥ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች ስለሚፈቱበት ሁኔታና ስለሚስተዋሉ
ችግሮች እንመለከታለን፡፡

81
የስልጠናው አላማዎች

ሰልጣኞች የዚህን ምእራፍ ስልጠና ሲጨርሱ ከገጠር መሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ ክርክሮች
ስለሚፈቱበት ስርዓት እና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ስላላቸው የአፈጻጸም ችግሮች እውቅና
ይኖራቸዋል፡፡

5.1 ከገጠር መሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ ክርክሮች አፈታትና አወሳሰን

የገጠር መሬት ይዞታን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችን ለመፍታት (ለመወሰን) የሚያስችሉ


ስልቶች የፌዴራል መንግስቱ ያወጣውን አዋጅ ጨምሮ በአምስቱም ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስታት በወጡ አዋጆች ውስጥ ተካትቷል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ ባወጣው አዋጅ አንቀጽ
12 መሠረት የመሬት ይዞታን አስመልክቶ ክርክር ቢነሳ በቅድሚያ ተከራካሪ ወገኖች ችግሩን
ወይም ክርክሩን በውይይትና በስምምነት እንዲፈቱ ጥረት ይደረጋል፡፡ በስምምነት መፍታት
ካልተቻለ በተከራካሪ ወገኖች በተመረጡ ሽማግሌዎች አማካይነት በሽምግልና ይፈታል ወይም
በክልሉ በሚወጣው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ መሰረት ይወሰናል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 16(1) መሠረት በቅድሚያ አቤቱታው
ለቀበሌው አስተዳደር ይቀርባል፡፡ ተከራካሪ ወገኖች ሁለት አስታራቂ ሽማግሌዎችን ይመርጣሉ፣
ሰብሳቢው በተከራካሪ ወገኖች ወይም በሁለቱ አስታራቂ ሽማግሌዎች ይመረጣል፡፡ በምርጫው
ላይ ስምምነት ከሌለ በቀበሌው አስተዳደር ይሾማል (ይመረጣል)፡፡ የተመረጡት አስታራቂ
ሽማግሌዎች ውሳኔአቸውን በ15 ቀናት ውስጥ ለቀበሌው አስተዳደር ማሳወቅ አለባቸው፡፡
የአሰታራቂ ሽማግሌዎች ውሳኔ በቀበሌው አስተዳደር ከተመዘገበ በኋላ የቀበሌው ህጋዊ
ማህተም ተደርጎበት ግልባጩ ለተከራካሪ ወገኖች ይሰጣል፡፡ በዚህ በአስታራቂ ሽማግሌዎች
ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በቀበሌው ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውሰጥ
ቅሬታውን ለወረዳው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ ከቅሬታው ጋር የአስታራቂ ሽማግሌዎችን
ውሳኔ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ በወረዳ ፍ/ቤት ቅር የተሰኘ ወገን ቅሬታውን ለከፍተኛው
ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ የከፍተኛው ፍ/ቤት የወረዳው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ከለወጠው
(ከቀየረው) ቅሬታ ያለው ወገን ቅሬታውን ለጠቅላይ ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ
ፍ/ቤት ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ይሆናል፡፡

82
የደቡብ ክልል ያወጣው አዋጅ አንቀጽ 12 የኦሮሚያ ክልል ካወጣው አዋጅ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ
ለየት የሚያደርገው የአስታራቂ ሽማግሌዎች ውሳኔ በቀበሌው አስተዳደር የሚመዘገብ ስለመሆኑ
የተገለፀ ነገር የሌለ ከመሆኑም ባሻገር የአስታራቂ ሽማግሌዎች እና የሰብሳቢው አመራረጥ
እንዴት እንደሆነ አልተገለፀም፡፡ እንዲሁም የአስታራቂ ሽማግሌዎች ውሳኔ ከሰጡ በኋላ ቅሬታ
ያለው ወገን ቅሬታውን ለወረዳው ፍ/ቤት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ማቅረብ እንዳለበት
አያመለክትም፡፡ በሌላም በኩል የከፍተኛው ፍ/ቤት በይግባኝ በቀረበለት ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ
በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ቅሬታውን ለጠቅላይ ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችል ሲሆን የጠቅላይ
ፍ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ ሆኖ መሠረታዊ የህግ ስህተት ካለበት ግን በሰበር
ችሎት ሊታይ ይችላል፡፡

የትግራይ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 28 መሠረት ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች ክርክሩን
በስምምነት እንዲፈቱ ጥረት ይደረጋል፡፡ ይህም ካልተቻለ በሽማግሌዎች ወይም በእርቅ
ሊጨርሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከላይ በተገለፀው መልኩ ክርክሩን መፍታት ካልተቻለ ጉዳዩ
ለቀበሌው የገጠር መሬት አስተዳደር ኮሚቴ ቀርቦ ውሳኔ ያገኛል፡፡ በቀበሌው የገጠር መሬት
አስተዳደር ውሳኔ ቅር የተሰኘው ወገን ቅሬታውን ለወረዳው ፍ/ቤት በ15 ቀናት ውሰጥ ማቅረብ
ይችላል፡፡ የወረዳው ፍ/ቤትም በ30 ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ የወረዳው ፍ/ቤት የቀበሌው
የመሬት አስተዳደር ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ ካፀናው የወረዳው ፍ/ቤት ውሳኔ የመጨረሻ
ይሆናል፡፡ ነገር ግን የወረዳው ፍ/ቤት የቀበሌው የመሬት አስተዳደር ኰሚቴ የሰጠውን ውሳኔ
ካሻሻለው ወይም ከለወጠው በውሳኔው ቅር የተሰኘው ወገን ቅሬታውን ለዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ማቅረብ ይችላል (ቅሬታው ለዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት በምን ያህል ጊዜ እንደሚቀርብ አልተገለፀም)፡፡
የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

የአማራ ክልል ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 29 መሠረት ከመሬት ይዞታና ከመጠቀም መብት ጋር
በተያያዘ በሚነሱ የፍትሐብሔር ክርክሮች ላይ ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ወደ መደበኛ
ፍ/ቤት የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ቢሆንም በቅድሚያ አለመግባባቱ ወይም ክርክሩ በሽምግልና
ታይቶ በእርቅ እንዲፈታ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ የአስታራቂ ሽማግሌዎች አመራረጥና የእርቁ
ድርድር የሚካሄደው የአካባቢውን ባህላዊ ስርዓት መሰረት አድርጐ በተከራካሪ ወገኖች
ስምምነት መሠረት ይሆናል፡፡ ጉዳዩ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ከቀርበ ግን እንደማንኛውም
የፍትሐብሔር ጉዳይ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ሰበር ድረስ በየደረጃው ባሉት ፍ/ቤቶች ታይቶ
የሚወሰን ይሆናል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው አካሄድ ግን የመሬትን ጉዳይ አከራክሮ የመወሰን

83
ስልጣን በክልሉ ውስጥ ለማህበራዊ ፍ/ቤቶች ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 149/1999
ይህ ስልጣን ተነስቶ ለመደበኛ የወረዳ ፍ/ቤቶች የተሰጠ መሆኑን ልብ ማለት ያሻል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ባወጣው አዋጅ አንቀጽ 34 መሰረት ከመሬት ይዞታ
ወይም ከመጠቀም መብት ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማናቸውም ክርክር በቅድሚያ በሽምግልና
ታይቶ በእርቅ እንዲፈታ ጥረት ይደረጋል፡፡ የሽማግሌዎቹ አመራረጥና የእርቁ ድርድር አካሄድ
የአካባቢውን ባህላዊ ስርዓትና ህግ መሰረት አድርጎ በባለጉዳዮች ስምምነት የሚፈጸም ይሆናል፡፡
ነገር ግን ጉዳዩ ከዚህ በላይ በተመለከተው ሁኔታ የማይፈታ ከሆነ ከወረዳው የባለስልጣኑ
ተጠሪ ቅርንጫፍ መ/ቤት አስፈላጊው መረጃ ተወስዶ ጉዳዩ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ወይም
አስተዳደራዊ አካል ቀርቦ እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ በሌላም በኩል በክርክሩ የውሳኔ
አሰጣጥ ሂደት መራዘም እንዳይከሰት እና መሬቶች ፆም እንዳያድሩ፤ የሴቶችና የህጻናት መብት
እንዳይጓደል ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው አካላት ጉዳዩን የመከታተልና የተጠቀሱትን መብቶች
የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው፡፡

የሶስቱ ክልሎች ካወጧቸው አዋጆች ጋር ሲነፃፀር የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች


ባወጧቸው አዋጆች የሚከተሉትን ችግሮች መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህም፡-

ሀ. አቤቱታ ለመደበኛ ፍ/ቤት የሚቀርበው የአሰታራቂ ሽማግሌዎች በሰጡት ውሳኔ ላይ ነው


ወይስ ውሳኔ ቢኖርም እንኳን አቤቱታ እንደ አዲስ ለመደበኛ ፍ/ቤት ማቅረብ ይቻላል?

ለ. የአስታራቂ ሽማግሌዎች በሰጡት ውሳኔ ላይ ነው ከተባለ ቅሬታው ለመደበኛ ፍ/ቤት


የሚቀርበው በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ነው?

መ. የይግባኝ አቀራረብ ሂደቱ ያልተገለፀ ከመሆኑም ባሻገር ክርክሩ የመጨረሻ ውሳኔ


የሚያገኘው በክልሉ የፍ/ቤት ተዋረድ መሠረት የትኛው ላይ እንደሆነ አያመለክትም፡፡

ሠ. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባወጣው አዋጅ ላይ ጉዳዩ በሽምግልና በእርቅ ሊፈታ ካልቻለ
አግባብ ባለው ፍ/ቤት ወይም በአስተዳደራዊ አካል ቀርቦ ይታያል ስለሚል ይህ
አስተዳደራዊ አካል የሚባለው የቱ ነው? ከዚህ ላይ የትኞቹ ጉዳዮች በፍ/ቤት የትኞቹ
ደግሞ በአስተዳደራዊ አካል ይታያሉ? በተጨማሪም የአስተዳደር አካሉ የሚሰጠው ውሳኔ
የመጨረሻ ነው ወይስ አይደለም? የመጨረሻ ካልሆነ ይግባኝ መጠየቅ ይቻላል ወይስ

84
አይቻልም? ይግባኝ የሚጠየቅ ቢሆን ይግባኙ የሚቀርበው ለየትኛው ፍ/ቤት ነው?
የሚሉ ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን ችግሮች ማንሳት ይቻላል፡፡

5.2 በፍ/ቤት ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች

በፍ/ቤት ክርክር የሚደረግባቸው ጉዳዮች ሁሉ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ማስረጃን


የሚመለከቱ ጥያቄዎችን የሚያስነሱ ናቸው፡፡ ውሳኔ ሊሰጥባቸው የተፈለጉ ጭብጦች ህግን
የሚመለከቱ ቢሆኑ እንኳ ወደ ህግ ጭብጥነት ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ፍሬ ነገሮችን
የሚመለከቱት ጭብጦች የሚረጋገጡት ወይም የሚስተባበሉት በማስረጃ አማካኝነት ነው፡፡

የፍሬ ነገሮችን መኖር ወይም የመደምደሚያን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ወይም ለማስተባበል


ያስችላል ተብሎ የቀረበ ማስረጃ ሁሉ እንደተባለው ላያረጋግጥ ወይም ላያስተባብል ይችላል፡፡
ስለዚህ የቀረበው ማስረጃ በሚፈለገው ደረጃ አስረድቷል ወይስ አላስረዳም ለሚለው ጥያቄ
መልስ ለመስጠት ፍ/ቤቱ የማስረጃ ምዘና ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም የመደምደሚያን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ /ለማስተባበል


ከሚቻልባቸው ዘዴዎች እና ማስረዳት ከሚፈለገው ፍሬ ነገር ወይም መደምደሚያ ጋር
ማስረጃው የሚኖረውን ግንኙነት መሠረት በማድረግ ማስረጃን በተለያዩ መንገዶች ከፍሎ ማየት
ይቻላል፡፡ ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከምንጠቀምበት ዘዴ አንፃር ማስረጃን

 የምስክርነት ማስረጃ (Testimonial evidence)


 የሰነድ ማስረጃ (Documentary evidence)
 ገላጭ ማስረጃ (Demonstrative evidence) በሚል መከፋፈል የሚቻል ሲሆን
በማስረጃነት የሚገለፀው ፍሬ ነገር ሊያስረዳው ከተፈለገው ፍሬ ነገር ወይም
መደምደሚያ ጋር ካለው ግንኙነት አንፃር ደግሞ ማስረጃን ፡-
o ቀጥተኛ ማስረጃ (Direct evidence)
o ቀጥተኛ ያልሆነ ማስረጃ (Indirect evidence) ብሎ መከፋፈል ይቻላል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፍሬ ነገርን መኖር ወይም የመደምደሚያን ትክክለኛነት ለማስረዳት


ወይም ለማስተባበል የተፈለገው ማስረጃ በዘፈቀደ ወይም ማስረጃ አቅራቢው ስለፈለገ ብቻ
ይቀርባል ማለት አይደለም፡፡ ማስረጃው ሊቀርብ የሚችለው ተቀባይነት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡
የተቀባይነት የሌለው ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም፡፡ የመጀመሪያው ማንኛውም ማስረጃ ሊቀርብ

85
የሚችለው ያስረዳዋል ለተባለው ፍሬ ነገር አግባብነት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ ማስረጃው እንዳይቀርብ በህግ ያልተከለከለ እንደሆነ ነው፡፡ የገጠር መሬትን
አስመልክቶ በፍ/ቤት ክርክር ቢነሳ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር እንዲሁም
የመደምደሚያን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ (ለማስተባበል በፍ/ቤት ዘንድ ተቀባይነት እና አግባብ
ያላቸው ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው የሚለውን እንደሚከተለው እናያለን፡፡

በፌዴራልም ሆነ በአምስቱም ክልሎች የገጠር መሬት አስተዳደር ሕጎች ስንመለከት ሁሉም


ከሞላ ጎደል የገጠር መሬትን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮችን በሚመለከት በፍ/ቤት ተቀባይነት
ስላለው እና አግባብ ሊሆን ስለሚችለው ማስረጃ በህግ ማዕቀፎቻቸው ደንግገው እናገኛለን፡፡
ለምሳሌ የትግራይ ክልል ህግ አንቀጽ 15፣ የደቡብ ክልል ህግ አንቀጽ 6፣ የኦሮሚያ ክልል ህግ
አንቀጽ 15፣ የአማራ ክልል ህግ አንቀጽ 24 እና የቤኒሻንጉል ክልል ህግ አንቀጽ 27
ድንጋጌዎችን ስንመለከት የገጠር መሬት በይዞታ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ዝርዝር
የተመዘገበበት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ ተዘጋጅቶና ፎቶግራፍ ተለጥፎበት ባለስልጣኑ
እንደሚሰጠውና ይህ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ደግሞ የባለይዞታው በሕግ የተጠበቀ የመብት
ማስረጃ እንደሆነ ደንግገው እናገኛለን፡፡

ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግዴታዎች መካከል አንዱ መሬትን በአግባቡ መዝግቦ መያዝና


ለባለይዞታው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መስጠት አንዱ እንደሆነ ከላይ በምዕራፍ ሶስት ስር
አንስተናል፡፡ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በስሙ የተሰጠው ሰው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ
እንደሆነ ሕግ ግምትን ከወሰደ የገጠር መሬትን አስመልክቶ በፍ/ቤት ክርክር በሚደረግ ጊዜ
የአንድን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር እንዲሁም የመደምደሚያውን ትክክለናነት
ለማረጋገጥ /ለማስተባል በፍ/ቤት ተቀባይነት ያለው እና ለተያዘው ጉዳይ አግባብ የሚሆነው
ማስረጃ የሰነድ ማስረጃ እንደሆነና ይህ የሰነድ ማስረጃም የባለይዞታው የይዞታ መረጋገጫ
ደብተር እንደሆነ ከሕግ ማዕቀፎቹ ድንጋጌዎች እንረዳለን፡፡ ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር ባልተሰጠባቸው አካባቢዎች በልዩ ሁኔታ ከሰነድ መስረጃ ውጭ ያሉ
የማስረጃ አይነቶችም ተቀባይነት ሊኖራቸው እንደሚችልም ልብ ማለት ይገባል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም የይዞታ ደብተሩን ትክክለኛነት የሚያጠራጥሩ ሁኔታዎች ሲኖሩ ለትክክለኛ ፍትህ
ሲባል ፍ/ቤቶች በሌላ መንገድ ተገቢውን ማጣራት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

86
5.3 የመሬት ክርክር አፈታት ሥርዓትና ችግርቹ

በአርሶ አደሮች መካከል በመጀመሪያ በሽማግሌዎች ከዚያ በኋላ ጉዳዩን በዳኝነት አይተው
የመወሰን ሥልጣን ባላቸው አካላት ክርክሮቹ በሚፈቱበት ሂደት እውነቱን ለማወቅና ትክክለኛ
ፍትህ ላይ በመድረስ በኩል የሚታዩ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡

የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ህግ አርሶ አደሮች በይዞታ መሬት ምክንያት የሚያደርጉት


ክርክር በመጀመሪያ በስምምነት እንዲጨርሡ ይህ ካልሆነ በሽማግሌ እንዲታይ የሚደነግጉ
ናቸው፡፡ ሆኖም ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠትና እውነቱን በማስረጃ አለማጣራት፣ የመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ህጉን አለማወቅ፣ ክርክሩን በሚዛናዊነት አለመምራት ፣አልፎ አልፎም
በዘመድ አዝማድ በሙስና አድሏዊ ውሣኔ የመስጠት ችግር በሽማግሌዎች በኩል የሚፈፀም
መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡60 በመሆኑም ሽማግሌዎች ያለባቸውን ሃላፊነት ጉዳዩን ሲያዩ
ሊከተሉት የሚገባውን ሥርዓትና ሥነ ምግባር ገለልተኛና ነፃ ሆኖ ጉዳዩን አጣርተው የመወሰን
ግዴታ ያለባቸው ስለመሆኑ የተሟላ ግንዛቤ እንዲይዙ ማድረግና የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ
ጉዳዩ ለፍ/ቤት በሚቀርብበት ጊዜ የማያስቸግር ትክክለኛነቱ የማያጠራጥር በሚሆንበት አግባብ
ማስተካከልን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽማግሌዎቹ ውሳኔ በህግ ያለዉ አስገዳጅነት እና
ሽማግሌዎቹ ያጣሩትን ፍሬ ጉዳይ እንዳለ የመቀበል ግዴታ ሊጣልባቸዉ ይገባል ወይስ
አይገባም? ጉዳዩ በሽማገሌዎች እንዲታይ መደረጉ በየአካባቢዉ ተጨባጭ ለዉጥ በማምጣት
የእርሻ መሬት ክርክሮችን ቀንሷል ወይስ አልቀነሰም? የሚሉት ጥያቄዎች ለየክልሎቹ የሚተው
ይሆናል፡፡

የክልል ፍ/ቤቶች በመደበኛ፣ በይግባኝ ወይም በሰበር ጉዳዩን አይተው ሲወስኑ የፍትህ መዛባት
አልፎ አልፎ የሚከሰት ስለመሆኑ በጥናት ተረጋግጧል፡፡61 በፍ/ቤት የሚታዩ ችግሮች የህግ
ክፍተት ባሉባቸው ሁኔታዎች ለማሟላት የፍትሀብሔር ህግ ድንጋጌዎችን በሚጠቀሱበት
ወቅት የአርሶ አደሩን የመሬት ባለይዞታነት የሚያረጋግጡ ድንጋጌዎች ሣይሆን የይዞታ
መብቱን የሚያሳጡትንና መብቱን የሚያጣብቡ የይርጋ ህግ ድንጋጌዎችን ለምሳሌ የፍ/ር/ህ/ቁ
1149 እና 2143 የመሣሠሉትን ድንጋጌዎች የመጠቀም፣ ፍሬ ጉዳይን በአግባቡ አጣርቶ

60
ዓሊ መሀመድና ማሩ ባዘዘው፤ የመሬት ባለይዞታና ተጠቃሚ የመሆን መብት በኢትዩጵያ፤ ነሐሴ 2002
(ያልታተመ)

ዝኒከማሁ
61

87
ያለመወሰን እና እውነቱን የሚያስረዳ ማስረጃ በማስቀርብ ውሣኔ አለመስጠት፣ አንድ አንድ
የህግ ድንጋጌዎችን በአግባቡ አለመተርጎምና ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ያለመሰጠት ችግር ያለባቸዉ
እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከሁሉም በላይ በመሬት ጉዳይ ተቃራኒ ማስረጃ /ለምሣሌ መሬት ለማስተዳደርና መዝግቦ
የመያዝ/ ሥልጣን ባለው አካል መሰጠቱና መሬት ደልዳይ ነበርን የሚሉ ሰዎች ግማሾቹ
መሬቱን ለከሳሽ ነው የተሰጠው ሲሉ ግማሾቹ ለተከሳሽ ነው የሰጠው የሚል ምስክርነት
የሚሰጡ በመሆናቸው ፍ/ቤቶች በሥነ-ሥርዓት ህጉ በተሰጣቸዉ ፍሬ ጉዳይን የማጣራት
ሥልጣን በመጠቀም ራሳቸዉ ወይም ምትክ ዳኛ መድበዉ እውነታውን ሳያጠሩ በባለስልጣኑ
የቀረበላችውን ማሰረጃ ብቻ በማየት ወሳኔ የሚሰጡ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ከመሬት
አስተዳደር እና አጠቃቀም ባለሥልጣን ቅረንጫፍ ጽ/ቤቶች ተቀራኒ የፅሁፍ ማስረጃ በሚላክበት
ጊዜ ፍ/ቤቶች ዕውነቱን ሣያረጋግጡ ወሳኔ የሚሰጡበት ሁኔታ መኖሩ እና ይህን መስረት
በማድረግ ብቻ አርሶ አድሩ መሬቱን እንዲለቅ መወሰኑ ፍትህን ማዛባቱ አይቀርም፡፡ ስለሆነም
ፍ/ቤቶች የአረሶ አደሩን የእርሻ መሬት ይዞታና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የሙግት አመራር
ሥርዓት በመከተል ዕውነታውን በእራሳቸው በማስረጃ በማጣራት መወሰን የለባቸውም ወይ?

ሌላው ችግር በአንዳንድ ፍ/ቤቶች እና በባለስልጣን መ/ቤቱ አስተዳደራዊ እና ፍትሐብሔር ነክ


ክርክሮችን ለይቶ አለማወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ በአማራ ክልል ከቀበሌ የመ/አስ/አጠ/ኮሚቴ ውሳኔ
በመነሳት ለምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በደረሱት የመዝገብ ቁጥር 42747 እና 43722
መረዳት እንደሚቻለው ግለሰቦች የመሬቱ ባለይዞታ እኔ ነኝ እኔ ነኝ በማለት በሚከራከሩበት
ጉዳይ የቀበሌው ኮሚቴዎች ለአንደኛው ተከራካሪ ወገን ይገባል በማለት ውሳኔ በመስጠታቸው
በኮሚቴው ውሳኔ ቅር የተሰኘው ወገን ለወረዳው አካ/ጥ/መ/አስ/አጠ/ጽ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ
የፀናበት በመሆኑ አሁንም ይግባኙን ለወረዳው ፍ/ቤት ሲያቀርብ የወረዳው ፍ/ቤትም የጽ/ቤቱን
ውሳኔ እንዳለ ተቀብሎ በማፅናቱ ይግባኙ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርቦ ከፍተኛው ፍ/ቤትም ግራ
ቀኙ ተከራካሪዎች ያቀረቡት ክርክር የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ስለሆነ አስተዳደራዊ ጉዳዮች
ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ አይደለም፡፡ ስለሆነም የቀበሌው ኮሚቴዎችም ሆነ የወረዳው
አካ/ጥ/መ/አስ/አጠ/ጽ/ቤት በግራቀኙ የመሬት ባለይዞታነት ክርክር ላይ የሰጡት ውሳኔ
ከስልጣናቸው ውጭ ስለሆነ የሚፀና አይሆንም፡፡ የስር ፍ/ቤትም ቢሆን ጉዳዩን በይግባኝ ደረጃ

88
ተቀብሎ ማከራከር አልነበረበትም በማለት ውሳኔውን በመሻር በመሬቱ ላይ መብት አለኝ የሚል
አካል ስልጣን ላለው የወረዳ ፍ/ቤት ክስ ማቅረብ ይችላል በማለት ወስኗል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች
1. ፍ/ቤቶች ከመ/አስ/አጠ/ የሚመጣውን የሠነድ ማስረጃ መሠረት አድርገው ውሳኔ ሲሰጡ
የመሥሪያ ቤቱን ማስረጃ ከማፅደቅ የዘለለ ተግባር አይፈፅሙም በመሆኑም ጉዳዮ ወደ
ፍ/ቤት መምጣቱ ተገቢ ነው ወይ?
2. በድንበር ግጭት የሚነሳ ክርክርን የአካባቢ ሽማግሌዎች የወሰኑትን የወረዳው መሬት
አስተዳደር የሚያይበት ሁኔታ አለ፡፡ በቀጥታ ወደ ፍ/ቤት መቅረብ አይችልም ወይ?
3. አንድ ፍ/ቤት መሬቱ የማን ነው የሚለውን በአካባቢው ህዝብ ተተችቶ እንዲቀርብ
ሲያደርግ የሰነድ ማስረጃ ነው ማለት ይቻላል ወይ?
4. የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ፍ/ቤቶች ውድቅ ሲያደርጉት ይታያል፡፡ ይህን
ለማድረግ ስልጣን አላቸው ወይ?
5. ፍትሐብሔር ነክ እና አስተዳደራዊ ነክ የመሬት ክርክሮች መሠረታዊ ልዩነት ምንድን
ነው? መመዘኛውስ?
6. በመሬት ጉዳይ ላይ አለመግባባቶችን በግልግል የመጨረስ ሁኔታ በህጉ ላይ
የተቀመጠው በአስገዳጅ ነው ወይስ በአማራጭ?
7. የመሬት ጉዳይን ወደ ፍርድ ቤት ሳይመጣ መሬቱን እንዲያስተዳድር ስልጣን የተሰጠው
አካል በሚሰጠው ማስረጃ መሠረት የሚወሰን በመሆኑ እዚያው ሊያልቅ የሚችልበት
ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ፍ/ቤት ማስረጃውን መሠረት በማድረግ ውሳኔ የሚሰጥ
በመሆኑና ይህን የሚለውጥ ስለማይሆን ፍ/ቤት መምጣቱ ምን ጠቀሜታ ይኖረዋል?

89
ክፍል ሁለት
የከተማ መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈጻጸማቸው
በክፍል አንድ የገጠር መሬትን አስመልክቶ ሰፊ ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ የከተማ
መሬትን የሚመለከቱ ሕጎችንና አፈፃፀማቸውን በመጠኑ እንመለከታለን፡፡ በመሆኑም በክፍል
ሁለት ውስጥ ሶስት ምዕራፎችን የምንመለከት ሲሆን እነዚህም በምዕራፍ አንድ በዋናነት
የከተማ መሬት እና የሕገ-መንግስቱን ግንኙነት፣ በምዕራፍ ሁለት ደግሞ የከተማ መሬትን
በሊዝ የማግኘት፣ የማስተላለፍ መብትና ይዞታ የሚታጣባቸውን ምክንያቶች ይዳስሳል፡፡
ምዕራፍ ሶስት ደግሞ የከተማ መሬትን አስመልክቶ የሚነሱ አለመግባባቶች ስለሚፈቱበት
መንገድ ይተነትናል፡፡

90
ምዕራፍ አንድ
የከተማ መሬትና ሕገ-መንግስቱ

መሬት በተፈጥሮ ውስን ሀብት እንደመሆኑ መጠን አጠቀቀሙ በተቻለ መጠን የአሁኑን
ትውልድና የመጪውን ትውልድ ጥቅም ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም
የከተማ መሬት አጠቃቀምን የተመለከቱ ህጎችና አፈፃፀማቸውን ከነበረው ታሪካዊ ዳራ በመነሳት
በአሁኑ ሰዓት ያለውን ሁኔታ መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ የከተማ መሬት
አጠቃቀምን ታሪካዊ አመጣጥና አሁን ባለው የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት ያለውን ሽፋን፣ የከተማ
ቦታን በሊዝ ለመያዝ የሚያገለግል ሕግ የማውጣት ስልጣን እና የወጡ ህጎችን የምንዳስስበት
ይሆናል፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች

ሰልጣኞች የዚህን ምዕራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-

 የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት ከመውጣቱ በፊት የከተማ መሬት አጠቃቀምን ታሪካዊ


አመጣጥ ያውቃሉ፣

 የከተማ መሬት የማግኘት መብትን ከሕገ-መንግስቱ አንፃር መተንተን ይችላሉ፣

 የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የሚያገለግል ህግ የማውጣት ስልጣን የማን እንደሆነና


የወጡ ሕጎችን ይለያሉ፣

1.1 የከተማ መሬት አጠቃቀም ታሪካዊ አመጣጥ ቅድመ 1987 ዓ.ም


/የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት ከመውጣቱ በፊት/

በኢትዮጵያ የከተሞች መቆርቆርና መስፋፋት የቅርብ ጊዜ ክስተት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ለዚህም


ምክንያቱ በሀገሪቱ ታሪክ ኢኮኖሚዋ ለረጅም ዘመናት በእርሻ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አርሶ
አደሮች ኑሮአቸውን በቀላሉ ከእርሻ በሚያገኙት ገቢ የሚገፉ በመሆኑ እንዲሁም ለረጅም
ዘመናት የኢትዮጵያ ነገስታት ቋሚ የሆነ መናገሻ ከተማ ባለመመስረታቸው መሆኑ

91
ይነገራል፡፡62 በመሆኑም ለመጀመሪያ ጊዜ የከተማ መሬትን የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት
ለማስተዳደር የተሞከረው በ1900 ዓ.ም አካባቢ በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ሲሆን በወቅቱ
በወጣው ህግ የከተማ መሬትን በግል ባለንብረትነት መያዝ ተፈቅዶ ስለነበር በአዲስ አበባ
ከተማ የውጭ ዜጎች ሳይቀሩ እስከ 10 ሄክታር መሬት ድረስ መያዝ የሚችሉበት ሁኔታ
ነበር፡፡63

ይህን ተከትሎ በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስትም በ1952 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ
ፍትሐብሔር ህግ ውስጥ የንብረት ህግን በተመለከተ በ3ኛው መጽሐፍ ከቁጥር 1126-1674
ድረስ በዝርዝር ድንጋጌዎች ማለትም የንብረት መብት ስለሚገኝባቸው መንገዶች፣ ስለንብረት
አጠቃቀምና አስተዳደር በርካታ ድንጋጌዎችን ይዞ ወጥቷል፡፡ ይህ የፍትሐብሔር ሕግ በወጣበት
ዘመን የከተማ መሬትና ቤት በግል ንብረትነት ሊያዝ፣ ሊሸጥና ሊለወጥ እንደሚችል ግልጽ
ነው፡፡ በተለይ የህጉ አንቀጽ 1535-1552 ያሉት ድንጋጌዎች የከተማ ቦታ ባለሀብቶችን
/ባለንብረቶችን/ ሙሉ መብት የሚጠብቁ እና ግዴታዎቻቸውን የሚያስቀምጡ ነበሩ፡፡

በመቀጠል በደርግ ዘመነ መንግስት የአብዮቱን መፈንዳት ተከትሎ የከተማ ቦታ እና ትርፍ


ቤትን የመንግስትና የሕዝብ ንብረት ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 47/1967 የከተማ ቦታ
የመንግስት ንብረት መሆኑንና ማንኛውም ሰው የከተማ ቦታ በግል ባለሀብትነት ለመያዝ
እንደማይችል ደንግጓል፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ዜጎች እስከ 500 ካ.ሜ ቦታ ላልተወሰነ ጊዜ
በይዞታ መያዝ እና በዚህ ቦታ ላይ አንድ ቤት ብቻ የመገንባት መብት የነበራቸው ሲሆን
ከንብረት መብት አጠቃቀም አንፃር በጣም ጠባብ መብት ብቻ ነው የነበራቸው፡፡ ስለሆነም በዚህ
አዋጅ መሠረት የከተማ መሬትን መሸጥም ሆነ መለወጥ በመያዣ ማስያዝ እና በማናቸውም
መንገድ እንዳይተላለፍ የተከለከለ ነበር፡፡64 ብቸኛው የተፈቀደው ነገር የመሬት ባለይዞታው
ሲሞት ለትዳር አጋሩ ወይም ለልጁ ማስተላለፍ ነበር፡፡65 በወቅቱ መሬት የመንግስት ስለነበር
መሬቱን መንግስት በፈለገው ጊዜ ያለካሣ ምትክ መሬት በመስጠት ብቻ ወይም ቤት ካለ ለቤቱ
ብቻ በመካስ የመውሰድ መብት ነበረው፡፡

62
Molla Mengsitu, the Ethiopian Urban Landholding System: An Assessment of the Governing Legal Regime in
Muradu Abdu eds Land Law and Policy in Ethiopia since 1991: Continuities and Challenges, Ethiopian Business
Law Series, (AAU 2009) at 150
63
Id at 153
አዋጅ ቁጥር 47/1997 አንቀፅ 4
64

ዝኒከማሁ አንቀፅ 5(1)


65

92
የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ በሽግግሩ ወቅት የከተማ መሬት ባለቤትነትና ይዞታ ወይም
ስሪት ላይ የተደረገ መሠረታዊ ለውጥ አልነበረም፡፡ ሆኖም በሽግግሩ ወቅት ወደ መጨረሻ
አካባቢ የከተማ ቦታ በኪራይ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 80/1986 በርካታ መሠረታዊ
ለውጦችን አካቶ ወጣ፡፡ አዋጁ በመግቢያው ላይ የሚከተሉትን ዓላማዎች (የወጣበትን
ምክንያት) ይዟል፡፡

1. ከተሞች ከከተማ ቦታ ኪራይና ከሌሎች ምንጮች የሚሰበስቡት ገቢ ለነዋሪው


ህዝብ አገልግሎት የሚያስፈልጉትን የመሠረተ ልማት አውታሮች ለመዘርጋትእና
የማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል የገንዘብ አቅም መፍጠር
በማስፈለጉ፣

2. ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤትን አቅርቦ ለማሟላት


የሚውል የፋይናንስ ምንጭ ማቅረብ በማስፈለጉ፣

3. የመሬት አገልግሎት ተገቢውን ዋጋ በገንዘብ መግለጽ በማስፈለጉ እና የከተማ


ቦታ የመጠቀም መብት የገበያ ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፣

4. ኢንቨስተሮች በከተሞች የኢኮኖሚ እድገት እንዲሳተፉ የሚያስችላቸው ስርዓት


መዘርጋት በማስፈለጉ የሚሉ ናቸው፡፡

የሊዝ አዋጁ ተፈፃሚነት በከተማ ክልል ውስጥ በሚገኝ ቦታ ሲሆን ቦታ በሊዝ ለመያዝ
የሚጠይቀው ሰው በሚያቀርበው ማመልከቻ መነሻነት የከተማውን የቦታ አጠቃቀም ፕላን
አመልካቾችን በጨረታ በማወዳደር እንደሚሰጥ፣ ቦታው በሊዝ ሲሰጥ የሊዝ ይዞታ ማረጋገጫ
ሰርቲፊኬት እንደሚሰጥ፣ በሰነዱ ውስጥም የሊዝ ገቢው ስም፣ ቦታው ጥቅም ላይ የሚውልበት
የአገልግሎት አይነት፣ የሊዝ ዘመን፣ የክፍያውን መጠን፣ እና የአከፋፈሉን ሁኔታ
እንደሚያካትት አንቀጽ 5 እና 6 ይደነግጋሉ፡፡ የሊዝ ዘመኑም እንደየአገልግሎቱ አይነት ከ50
ዓመት እስከ 99 ዓመት ሊደርስ የሚችል ሲሆን የሊዝ ዘመኑ ሲያበቃም ሊታደስ እንደሚችል
አንቀጽ 7 ላይ ተደንግጓል፡፡

93
መንግስት ለሚያበረታታቸው ኢንቨስተሮች፣ ለማህበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ ለቁጠባ
ቤት መስሪያ እና በቀጥታ ለህዝብ ጥቅም ለሚውሉ ሌሎች ስራዎች ለሚያገለግል የከተማ ቦታ
በነፃ መስጠት እንደሚቻል አንቀጽ 13 ደንግጓል፡፡ በመጨረሻም አዋጁን በተሟላ መልኩ ስራ
ላይ ለማዋል ክልሎች አዋጁን ለማስፈፀም ደንቦችንና መመሪያዎችን ማውጣት እንዳለባቸው
ደንግጓል፡፡

1.2 የከተማ መሬት የማግኘት መብት እና የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት

የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 40(3) “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት


ባለቤትነት መብት የመንግስት እና የህዝብ ብቻ ነው፤ መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ንብረት ነው፤” በማለት ይደነግጋል፡፡ የዚህ
ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ መሰረታዊ አላማ መንግስት በሕገ-መንግስቱ ለህዝብ የገባቸውን
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግዴታዎች ለመፈፀም የግድ በይዞታው ስር አድርጎ
የሚያዝበት መሬት ሊኖረው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ያለእንደዚህ ያለ የኢኮኖሚ መሳሪያ ዘላቂ
ልማት፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ጠንካራ ኢትዮጵያን
ሊገነባ አይችልም፡፡ ስለሆነም ይህን ሁለንተናዊ ዘላቂ የልማት መሠረት የሆነውን መሬት
በመንግስት አስተዳደር ከማድረግ ውጭ መንግስት ከባለይዞታዎች መሬት እየገዛ በከተሞች
መሠረተ ልማት የማስፋፋት ስራም ሆነ ለግል የከተማ ልማታዊ ባለሀብት መሬት በማቅረብ
በተፈለገው ደረጃ ፈጣንና ዘላቂ ሁሉም ዜጎች በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት
ማምጣት አይችልም፡፡ ስለሆነም የከተማ ቦታን የመንግስትና የህዝብ የማድረጉ ፖሊሲና ዓላማ
የሚመነጨው መንግስት በህዝብ ወኪልነቱ የህዝቦች የጋራ ሀብት የሆነውን የከተማ ቦታ
በእኩልነት ለማዳረስ፣ ለመቆጣጠር፣ ለማስተዳደር፣ ስርዓት ለማስያዝና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣
ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ተግባራትን ለማከናወን እንዲችል ከማድረግ ጋር ተያይዞ የሀገሪቱን
መፃኢ ዕድል ከሚወስኑት አባይት ጉዳዮች አንዱ አድርጎ ከሚወስድ ሕገ-መንግስታዊና ሀገራዊ
ራዕይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘት እና ከመሬታቸው


ያለመፈናቀል መብታቸው የተከበረ እንደሆነ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 4 እና 5
ይደነግጋል፡፡ ይህ አንቀጽ ዜጎች የከተማ መሬት በነፃ የማግኘት መብት የላቸውም ወደሚል
መደምደሚያ ያደርሳል፡፡ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40 ስር በግልጽ እንደሚታየው በከተማ

94
መሬት የመጠቀም መብት በነፃ ሊገኝ እንደሚችል አይደነግግም፡፡ ይኸውም የገጠር መሬትን
ብቻ በነፃ ማግኘት እንደሚቻል አሳይቶ የከተማ መሬትን በዝምታ ያለፈው ለምንድን ነው?
የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፡፡

በመሆኑም አንዳንዶች የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 40 ስለአርሶ አደርና አርብቶ አደር መሬት እንጅ
ስለከተማ መሬት አስመልክቶ በምን መልኩ ሊያዝ እንደሚገባ የጠቀሰው ነገር ስለሌለ መሬትን
በሊዝ ማስተላለፍ ሕገ-መንግስታዊ መሠረት የለውም ይላሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም አርሶ
አደሮችና አርብቶ አደሮች መሬት በነፃ በጊዜ ሳይገደብ ባለይዞታ ስለሆኑ ከመሸጥና መለወጥ
ወጭ ሰፊ መብት ሲኖራቸው በአንፃሩ የከተማ ነዋሪው ግን መሬት የሚያገኘው በጊዜ ተገድቦ
ለዚያውም ኪራይ እየከፈለ ስለሆነ የጠበበ መብት ያለው በመሆኑ መሬት የመንግስትና የህዝብ
ነው ቢባልም ቅሉ መንግስት ጠቅልሎ ብቻውን ወስዶታል የሚል መከራከሪያ ይነሳል፡፡

በመሠረቱ የመሬት ስሪቱ ምንም ይሁን ምን መሬት ከመንግስት እጅ ወደ ግለሰቦች በሊዝ


ኪራይ ማስተላለፍ በብዙ ሀገሮች የተለመደ አሠራር ነው፡- ለምሳሌ በቻይና እና በህንድ፡፡66 ዋና
ዓላማውም መንግስት ልክ እንደግብር ሁሉ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝበት ታስቦ የተቀረጸ ሲሆን
ከሊዝ ስርዓቱ የሚሰበስበው ገቢም ተመልሶ ለከተሞች ልማት ይውላል፡፡ ስለሆነም ይህን
በአለም ላይ የተለመደ አሠራር የኢትዮጵያ የሕግ ስርዓት የተቀበለው ገና ሕገ-መንግስቱ
ከመጽደቁ በፊት የከተማ ቦታን በሊዝ ኪራይ ለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 80/1986 ሲሆን
ይህ አዋጅ እንደሚያሳየንና በመግቢያው ላይ እንደተገለጸው ከተሞች ከከተማ ቦታ የሊዝ ኪራይ
የሚሰበሰቡትን ገንዘብ ለህዝቡ መሠረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ማሟያ ለማድረግ
እንዲሁም ኢንቨስተሮች በከተሞች ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚያስችል
መሆኑን ነው፡፡

66
Kala Seetharam “Innovative Sources of Development Finance: The Role of Land Financing India’s Large Cities
and Comparisons with China (2010) Available at www.depot.gdnet.org/newkb/submissions/P452-M3-
Kala%20Sridhar-Paper.pdf (Date of Use: February 25, 2012) at 6, 12; see also George E Peterson “Land Lease and
Land Sale as an Infrastructure Financing Option” World Bank Policy Research Working Paper 4043 November
2006 available at
www.worldbank.org/servlet/WDSContentServer/WDSP/IB/2006/10/25/000016406_20061025121353/Rendered/PD
F/wps4043.pdf (Date of Use February 2012)

95
በተጨማሪም አንቀጽ 89(5) በተደነገገው መሠረት መንግስት መሬትንና የፈጥሮ ሀብትን
በህዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለህዝቡ የጋራ ጥቅም እና እድገት እንዲውሉ የማድረግ
ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ከዚህ ግዴታው በመነጨ መልኩ መንግስት የከተማ መሬትን
ለመኖሪያ ቤት፣ ለኢንቨስትመንትም ሆነ ለሌላ አገልግሎት በሊዝ በማስተላለፍ ለእየከተማዎቹ
ህዝቦች የጋራ ጥቅምና እድገት የሚውሉ መሠረተ ልማት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን
የሚያሟላበት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ አገላለጽ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ እንደገና
ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 272/1994ም በመግቢያው ላይ በተጠናከረ መልኩ የከተማ
ቦታን በነፃ ሳይሆን በሊዝ ማስተላለፍ የተፈለገበት አንዱ ምክንያት በነፃ ገበያ መርሆዎች
መሠረት የከተማ ቦታን በተገቢ ዋጋ በሊዝ ማስተላለፍ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ
ልማትን ለማሳካትና የከተሞች ልማት በቀጣይነት የሚጎለብትበት አቅም እንዲፈጠር ለማድረግ
እንደሚረዳ ስለታመነበት መሆኑን ይገልፃል፡፡

ይሁን እንጅ በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም ከተሞች በሊዝ ህግ የሚተዳደሩ ባለመሆኑ አሁንም ቢሆን
በተግባር ዜጎች በግላቸውም ሆነ በማህበር የቤት መስሪያ ቦታ በነፃ የሚያገኝበት አሠራር
እስከቅርብ ጊዜ የተለመደ ነበር፡፡ ባለሀብቶችም ቢሆን በነፃ ወይም በኪራይ የመሬት ባለይዞታ
የሚሆኑበት ሁኔታ አሠራርና የሕግ ማዕቀፍ የነበረ መሆኑን እንረዳለን፡፡

1.3 የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የሚያገለግል ሕግ የማውጣት


ስልጣንና የወጡ ህጎች

መሬትና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና ጥበቃን የተመለከቱ ህጎች የማውጣት ስልጣን


የፌዴራል መንግስቱ መሆኑ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 51(5) እና 55(2)(ሀ)
ደንግጓል፡፡ ይህ ህግ የማውጣት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግስት ግዴታዎች
በተቀመጡበት የህገ-መንግስቱ ኢኮኖሚ-ነክ ዓላማዎች ውስጥ መንግስት መሬትንና የተፈጥሮ
ሀብትን በህዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለህዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ
የማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን አንቀጽ 89(5) በግልጽ ያሳየናል፡፡ በመሆኑም
በፌደራል መንግስት የከተማ መሬትን የተመለከተ ህግ የማውጣት ስልጣን የሚመነጨው
ከዚህ ግዴታው እና ከአንቀጽ 52(2)(ሀ) መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ቀደም ሲል
እንደተገለፀው የመጀመሪያው የከተማ መሬት ይዞታ በሊዝ ስርዓት እንዲተዳደር የወጣው

96
አዋጅ ቁጥር 80/1986 ሕገ-መንግስቱ ከመወጣቱ ከአንድ ዓመት በፊት የፀደቀ መሆኑን
እንረዳለን፡፡ ስለሆነም የመጀመሪያው የሊዝ አዋጅ መሠረቱ ሕገ-መንግስቱ ባይሆንም መሠረቱ
በሽግግሩ ወቅት የነበረው የመንግስት የፖሊሲ ለውጥ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

አዋጅ ቁጥር 80/1986ን የተካው የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ እንደገና ለመደንገግ የወጣው
አዋጅ ቁጥር 272/1994 ነው፡፡ በቅርቡ ደግሞ አዋጅ ቁጥር 272/1994ን የተካው የከተማ ቦታ
በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 272/1994 ሁለት ዋና
ዋና ዓላማዎች ነበሩት፡፡ እነዚህም በቂ የሆነ ገቢ ከሊዝ ኪራይ መሰብሰብና በከተማ የተያዘውን
መሬት ሁሉ ወደ ሊዝ ይዞታ መቀየር የሚሉ ሲሆኑ እነዚህን ዓላማዎች በመያዝ መንግስት
ላለፉት አስር ዓመታት ተግባር ላይ ለማዋል ጥረት አድርጓል፡፡ ነገር ግን በከተሞች ያለው
የመሬት አስተዳደር ስርዓት በመሬት አቅርቦት ሂደት ወቅት ቅልጥፍናና ግልጽነት የሌለው
በመሆኑ የመሬት ፍላጎት እና አቅርቦት ካለመመጣጠኑም በላይ በመሬት አሰጣጡ ስርዓት
የተፈጠረው ክፍተት ለሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም ለግለሰቦች መክበሪያ ሆኖ መቆየቱ
ይታወቃል፡፡

በመሆኑም እነዚህን ችግሮች ይፈታል ተብሎ የታሰበው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ሁለት ዋና
ዋና ዓላማዎችን ይዞ ወጥቷል፡፡ እነዚህም በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች እየጨመረ ከመጣው
የኢኮኖሚ እድገት ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ለመጣው የመሬት ፍላጎት ተገቢ
የሆነ የመሬት አቅርቦ ለመፍጠርና ከነፃ ገበያ ስርዓት ጋር የሚራመድ በመልካም አስተዳደር
የተደገፈ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ያለበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መፍጠር
በማስፈለጉ የሚሉ ናቸው፡፡ ዝርዝር አዋጁን ይዘት አስፈላጊም ሲሆን ከቀደመው ጋር በማነፃፀር
በቀጣይ ክፍሎች የምንመለከተው ይሆናል፡፡ (የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ የከተማ መሬት ህግ
የማውጣት ስልጣንና የወጡ ህጎን ማሳየት ብቻ ስለሆነ ማለት ነው)፡፡

እንግዲህ ሕገ-መንግስቱ ባስቀመጠው መርህ መሠረት የከተማ መሬት አዋጅ በፌደራል


መንግስቱ ከወጣ የክልል መንግስታትና የከተማ መስተዳደሮች ስልጣን ምንድን ነው የሚለውን
ጥያቄ እንመለከታለን፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን አጠቃቀምና
ጥበቃን የተመለከቱ ሕጎችን የማውጣት ስልጣን የፌደራል መንግስት ነው፡፡ ሆኖም የክልል
መንግስታትም በኢፌደሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 52(2)(መ) ላይ እንደሰፈረው የፌደራል

97
መንግስት በሚያወጣው ህግ መሠረት መሬትና የተፈጥሮ ሀብትን የማስተዳደር ስልጣንና
ተግባር አላቸው፡፡ እንዲሁም ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ የሆኑ የከተማ አስተዳደሮችም (አዲስ
አበባና ድሬደዋ) በመተዳደሪያ ቻርተራቸው ስልጣን የተሰጣቸው መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ለምሳሌ
አዋጅ ቁጥር 87/1989 የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በከተማው መስተዳደር ክልል ውስጥ
የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የማስተዳደር ስልጣንና ተግባር እንዳለው አንቀጽ
3(2)(መ) ደንግጓል፡፡ የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር
361/1995ም አንቀጽ 11(2)(ሰ) ተመሳሳይ ድንጋጌ በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን
መሬትና የተፈጥሮ ሀብት በህግ መሠረት የማስተዳደር” ስልጣን የተሰጠው መሆኑን
ደንግጓል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996
አንቀጽ 9(3) በከተማው ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት በህግ መሠረት
የማስተዳደር ስልጣን የከተማው አስተዳደር መሆኑን ደንግጓል፡፡

ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው በሁለቱም የከተማ መስተዳደሮች በቻርተራቸው ላይ


በከተማዎቹ ክልል ውስጥ የሚገኝ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት በህግ መሠረት የማስተዳደር
ስልጣንና ተግባር የእየከተማዎቹ መስተዳደር መሆኑን ይደነግጋሉ፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ
በየትኛው ህግ መሰረት ነው የሚያስተዳድሩት የሚለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ አዋጅ ቁጥር
272/1994ም ሆነ አዋጅ ቁጥር 721/2004 በግልጽ የሚደነግጉት ክልሎች እና የከተማ
መስተዳደሮች አዋጁን ለማስፈፀም ዝርዝር ደንብ የማውጣት ስልጣንና ግዴታ ያለባቸው
/ያላቸው መሆኑን ነው፡፡

በመሆኑም ቀደም ሲል በምሪት ወይም በሌላ ሁኔታ የተያዘ የከተማ ቦታ ወደ ሊዝ


የሚቀየርበት ሁኔታ፣ በአዲስ መልኩ የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀድበት፣ የሊዝ
ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚሰጥበት፣ የሊዝ ዘመን ጣራን ሳይቃረን የሊዝ ዘመን
መወሰን፣ የሊዝ ክፍያ ተመን እና ሌሎችን ዝርዝር አፈፃፀሞችን በተመለከተ ክልሎችም ሆነ
ሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች ደንብ በማውጣት ስራ ላይ እንደሚያውሉ ይገልፃል፡፡ ስለሆነም
ደንቡ ሲወጣ የእየክልሎችንና የከተሞችን የእድገት ደረጃ ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ
ሊሆን እንደሚገባ የድሮውም ሆነ አዲሱ የሊዝ አዋጅ ይገልፃሉ፡፡

98
የመወያያ ጥያቄዎች
1. የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት የገጠር መሬትን ብቻ በነፃ ማግኘት እንደሚቻል አሳይቶ
የከተማ መሬትን በዝምታ ያለፈው ለምንድን ነው? የከተማ መሬት በሊዝ እነዲተላለፍ
ማድረግ ፋይዳው ምንድን ነው? ጉዳቱስ?
2. በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 40 መሠረት የከተማ መሬት በነፃ ማግኘት አይቻልም ማለት
ነው?

99
ምዕራፍ ሁለት
የከተማ መሬትን በሊዝ የማግኘት እና የማስተላለፍ መብት እንዲሁም ይዞታ
የሚታጣባቸው ምክንያቶች

ሊዝ ማለት በጊዜ በተገደበ ውል መሠረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት የሚገኝበት ወይም


የሚተላለፍበት የመሬት ኪራይ ይዞታ ስሪት ነው፡፡67 ሊዝ ውል በመሆኑ ውሉ የሚፈፀመው
በመሬቱ ባለቤትና መሬቱን በኪራይ በሚወስደው ሰው መካከል ነው፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ
በአለው የመሬት አስተዳደር መርህ መሠረት መሬት የመንግስትና የህዝብ በመሆኑ ሊዙ /ኪራዩ
የሚደረገው በመንግስትና በተከራዩ መካከል ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የከተማ
መሬት በሊዝ የማግኘት (ባለይዞታ የመሆን)፣ የማስተላለፍ መብት እና ይዞታ የሚታጣባቸውን
ሁኔታዎች እናያለን፡፡ የአዲሱ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንቦች ያልወጡለት ስለሆነ አብዛኛዎቹን
ነጥቦች ከድሮው ጋር በንፅፅር ማየት ጠቃሚ ነው፡፡

የስልጠናው ዓላማዎች

ሰልጣኞች ይህን ምዕራፍ ሲያጠናቅቁ፡-

 የከተማ ቦታ በሊዝ የሚገኝባቸውን መንገዶች ይለያሉ፣

 የሊዝ አመሠራረት፣ የሊዝ ተመንና የሊዝ ዘመንን በተመለከተ በቂ እውቀት


ይኖራቸዋል፣

 የሊዝ ተዋዋይ ወገኖች (የሊዝ ተቀባይና የሊዝ ሰጭ) መብትና ግዴታዎችን ለይተው
ያውቃሉ፣

 የሊዝ ይዞታ መብት የሚተላለፍባቸውንና በዋስትና የሚያዝባቸውን ሁኔታዎች ይለያሉ፣

 የሊዝ መብት የሚቋረጥባቸውን መንገዶች ያውቃሉ፡፡

67
የኢፌዴሪ የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣ፤ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 2(1)

100
2.1 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለማግኘት

2.1.1 የመተላለፊያ መንገዶች

በአዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀጽ 4(1) ላይ የከተማ ቦታ በሊዝ ሊሰጥ የሚችልባቸው


ሁኔታዎች እንደሚከተለው ይገለፃል፡፡

ሀ. ከተማው ፕላን ያለው ሲሆን የፕላኑን የቦታ አጠቃቀም ድንጋጌ ወይም ከተማው ፕላን
የሌለው ሲሆን ክልል ወይም የከተማ መስተዳደር እንደእየአግባቡ የሚያወጣውን ደንብ
በመከተል እና

ለ. በጨረታ ወይም በድርድር

ሐ. ለግል መኖሪያ ቤት፣ ክልል ወይም የከተማ መስተዳድር በሚወስነው መሠረት ይሆናል
ይላል፡፡

ከዚህ አንቀጽ የምንገነዘበው እንደ እየሁኔታው፣ እንደየክልሉ የሚወስኑ የከተማ ቦታ በሊዝ


የአሰጣጥ መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ደንብ ቁጥር 6/1994 አንቀጽ 4(3) ላይ የከተማ ቦታ ለግል መኖሪያ ቤት መስሪያ በእጣ ወይም
በሽልማት ሊሰጥ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት በነበረው የህግ ማዕቀፍ
መሬት ከመንግስት ወደ ግለሰቦች በጨረታ፣ በድርድር፣ በስጦታ፣ በሽልማት፣ በሕግ ሊተላለፍ
እንደሚችል እንገነዘባለን፡፡ እንዲያውም የክልል ወይም የከተማ መስተዳድር ሊያበረታታ
ለሚፈልገው የልማት ስራ ወይም ማህበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋም፤ ለቁጠባ ቤት ለግል
መኖሪያ ቤት መስሪያ እና ለሌሎች መሰል ሥራዎች የከተማ መሬት ከሊዝ ነፃ ሊሰጥ
እንደሚችልም አዋጅ ቁጥር 272/1994 አንቀፅ 8(2) ይደነግጋል፡፡

አዲሱ አዋጅ ግን የከተማ መሬት የሚገኝባቸውን መንገዶች በተወሰነ መልኩ ቀንሶታል፡፡


በመሆኑም አንቀጽ 7 ላይ በግልጽ እንደተደነገገው የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀደው፡-
1. ከተማው ፕላን ያለው ሲሆን የፕላኑን የቦታ አጠቃቀም ድንጋጌ ወይም ከተማው ፕላን
የሌለው ሲሆን ክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ የሚያወጣውን ደንብ በመከተል እና

101
2. በጨረታ ወይም በምደባ ስልት ይሆናል፡፡ ምደባ ማለት በአዋጁ የትርጉም ክፍል
እንደተቀመጠው መሬትን በሊዝ መነሻ ዋጋ ያለጨረታ ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡

ስለሆነም ቀደም ሲል በድርድር የመስጠት ሁኔታ እንዲሁም በቀድሞው አዋጅ አንቀጽ 4(1)(ሐ)
የነበረው የክልሎችና የከተማ መስተዳደሮች ስልጣን (discretion) በአዲሱ አዋጅ አልተካተተም፡፡
ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የተወሰኑት የማስተላለፊያ መንገዶች ለምሳሌ ድርድር ለሙስናና
ላልተገባ አሠራር በር የሚከፍቱ በመሆናቸው ህግ አውጭው በቅርቡ በሀገራችን ከነበረው
የመሬት ዝርፊያ ችግር ትምህርት ወስዶ እንዲቀሩ ያደረጋቸው ለመሆኑ መገመት አያዳግትም፡፡
በመሆኑም ህጉ በተቻለ መጠን ሁሉም አካል የከተማ መሬት ተጫርቶ እንዲያገኝ የሚፈልግ
ሲሆን አንዳንድ ለህዝብ ከፍተኛ ጥቅምና አገልግሎት የሚሰጡ እንደ መንግስት መ/ቤቶች፣
የእምነት ተቋማት፣ በጎ አድራጎት ተቋማት፣ ኤምባሲዎች፤የመንግስት የጋራ ቤቶች ግንባታና
የማኑፋቸክሪንግ ድርጅቶች እና ሌሎችም ልዩ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውሉ
ቦታዎች የከተማ መሬት ያለጨረታ መነሻ ዋጋው በምደባ ብቻ እንደሚሰጣቸው የአዋጁ አንቀጽ
12(1) ላይ ተደንግጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በከተማ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ምክንያት ተነሽ የሚሆን የነባር ይዞታ
ባለመብት ምትክ ቦታ የማግኘት መብት ያለሊዝ ይኖረዋል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ የሚነሳው ሰው
በራሱ የመኖሪያ ቤት ይኖረው ስለነበር ምትክ መሬት እንዲካስ ስለሚታሰብ የሊዝ ዋጋ
እንዲከፍል አይገደድም ማለት ነው፡፡ በአንፃሩ ግን በቀበሌ ወይም በመንግስት ቤቶች
ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች በከተማ ማልማት ከተነሱ እና ምትክ ቤት የማይሰጣቸው ከሆነ
መሬት በሊዝ መነሻ ዋጋ እንዲሰጣቸው እንደሚደረግ ከአንቀጽ 12(2) እና (3) ደንግጓል፡፡

በአጠቃላይ በአዲሱ አዋጅ ከሊዝ ስሪት ውጭ የከተማ መሬት መያዝም ሆነ መፍቀድ የተከለከለ
መሆኑን አንቀጽ 5 ደንግጓል፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር በዚህ
አዋጅ ከተደነገገው ውጭ የከተማ መሬትን መፍቀድ ወይም ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ከዚህ ጋር
ተያይዞ ነባር ይዞታዎች ሳይቀር ወደ ሊዝ ስሪት የሚቀየሩበትን ሁኔታ የከተማ ልማትና
ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሚያቀርበው ዝርዝር ጥናት ላይ ተመስርቶ በሚኒስተሮች ም/ቤት
እንደሚወሰን የአዋጁ አንቀጽ 6(1) ይገልፃል፡፡ ስለሆነም ነባር ይዞታዎች (የከተማ ቦታ በሊዝ
ስርዓት መተዳደር ከመጀመሩ በፊት በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ወይም በሊዝ ተግባራዊ ከሆነ

102
በኋላ ለተነሽ በምትክ የተሰጠ) ወደ ሊዝ ተቀይረው የሚመዘገቡበት ሁኔታ ወደፊት ተግባራዊ
የሚደረግ ሆኖ ይልቁንስ ነባር ይዞታ የሆነ መሬት ከውርስ ውጭ በሆነ መንገድ (በሽያጭ፣
በስጦታ፣ በለውጥ፣) ወደ ሶስተኛ ወገን ቢተላለፍ ወይም የነባር ይዞታ መሬት በሊዝ ከተገኘ
ሌላ መሬት ጋር እንዲዋሀድ ጥያቄ ቀርቦ እንደሆነ ወይም በህገወጥ መንገድ ተይዞ የነበረ
መሬት ህጋዊ እንዲሆን ተፈቅዶ ከሆነ የስም ዝውውሩም ሆነ ሕጋዊ ምዝገባ የሚደረገው በሊዝ
ምዝገባ ስርዓት ሊሆን እንደሚገባ ይኸው አንቀጽ 6 በግልጽ ያሳያል፡፡

2.1.2 የሊዝ ውል አመሠራረት፣ የሊዝ ተመንና የሊዝ ዘመን


የሊዝ ውል እንደ ማንኛውም ውል ማሟላት የሚጠበቅበት ነገሮች ይኖራል፡፡ ስለሆነም የከተማ
ቦታ በሊዝ እንዲይዝ የተፈቀደለት ሰው አግባብ ካለው የመንግስት አካል ጋር ውል መፈራረም
ይኖርበታል፡፡ ከዚያም የሊዝ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል፡፡ የቀድሞው አዋጅ
ቁጥር 272/94 አንቀጽ 5 እና 9 ተያይዘው ሲነበቡ የሊዝ ውል እና የሊዝ ይዞታ ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀቱ የሚይዛቸው ዝርዝር ሁኔታዎች በክልል ወይም በከተማ መስተዳደር
በሚወጣ ደንብ እንደሚወሰን ነበር፡፡ ነገር ግን አዲሱ አዋጅ አንቀጽ 16(2) የሊዝ ውል የግንባታ
መጀመሪያ፣ የግንባታ ማጠናቀቂያ፣ የክፍያ አፈፃፀም ሁኔታ፣ የችሮታ ጊዜ፣ የውል ሰጭና
የውል ተቀባይ መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ዝርዝር ሁኔታዎች
ማካተት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም አንቀጽ 17(2) የሊዝ ይዞታ የምስክር ወረቀት
የውል ተቀባዩን ሙሉ ስም ከነአያት፣ የቦታውን ስፋትና አድራሻ፣ የቦታውን አገልግሎት
አይነት፣ ደረጃና የፕሎት ቁጥር፣ የቦታውን ጠቅላላ የሊዝ ዋጋና በቅድሚያ የከፈለውን መጠን
በየአመቱ የሚፈፅመውን የሊዝ ክፍያ መጠንና ክፍያውን የሚያጠናቅቅበት ጊዜ እንዲሁም
የሊዝ ይዞታ ፀንቶ የሚቆይበትን ዘመን አካቶ መያዝ ያለበት መሆኑን ይገልፃል፡፡

የሊዝ ተመንን በተመለከተ ማንኛውም የከተማ ቦታ የሊዝ መነሻ ዋጋ እንደሚኖረውና የመነሻ


ዋጋ ትመና ዘዴው በሚመለከታቸው ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በሚወጡ ደንቦች
መሠረት እና የከተማዎቹን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ እንደሚወሰን የአዲሱ አዋጅ አንቀጽ
14(1) ይደነግጋል፡፡ ይኸውም የሊዝ መነሻ ዋጋ ወቅታዊነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ለማድረግ
ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ መከለስ ያለበት መሆኑን ከዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 መረዳት
ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል የነበረው አዋጅ አንቀጽ 8(2) ላይ የክልል ወይም
የከተማ መስተዳድር ሊያበረታታ የሚፈልገው የልማት ስራ ወይም የማህበራዊ አገልግሎት

103
ሰጭ ተቋም ለቁጠባ ቤት፣ ለግል የመኖሪያ ቤት መስሪያ እና ሌሎች መሰል ስራዎች የከተማ
ቦታ ከሊዝ ክፍያ እስከ ነፃ ሊፈቀድ እንደሚችል ደንግጎ ነበር፡፡ አዲሱ አዋጅ ግን ይህን ሁኔታ
ሙሉ በሙሉ በማስወገድ በሊዝ በጨረታ ወይም በሊዝ በምደባ ብቻ መያዝ እንደሚቻል
የደነገገ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በዚህ አዋጅ ሊኖረው የሚችለው አማራጭ የችሮታ ጊዜ ብቻ
ነው፡፡ ማለትም የከተማ ቦታ በሊዝ የተፈቀደለት ሰው እንደልማቱ ወይም እንደአገልግሎቱ
አይነት የመሬቱን የሊዝ ቅድመ ክፍያ ከከፈለ በኋላ በየዓመቱ መክፈል ያለበትን መክፈል
ከመጀመሩ በፊት ግንባታ እንስኪያጠናቀቅ ከክፍያ ነፃ ሆኖ እንዲቆይ የሚፈቅድ ሕግ በክልልና
በከተማ መስተዳድሮች በሚወጣ ደንብ ሊወሰን እንደሚችል ከአንቀጽ 15 እንረዳለን፡፡

ሊዝ ውል በመሆኑ ውሉ በተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ይሆናል፡፡ የሊዝ ዘመንን በተመለከተ


የቀድሞው አዋጅም ሆነ አዲሱ አዋጅ ከተወሰኑ ነገሮች በስተቀር (ለአዲስ አበባ ከተማ
ከተቀመጠው በስተቀር) ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ በመሆኑም በአንቀጽ 18(1)መሠረት
እንደከተማው የእድገት ደረጃና የልማት ስራው ዘርፍ ወይም የአገልግሎቱ ዓይነት ሊለያይ
የሚችል ሆኖ አነስተኛው የሊዝ ዘመን 15 ዓመት ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 99 ዓመት ነው፡፡
ይህ ዘመን በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 18 ላይ የተደነገገ ሲሆን በማንኛውም ከተማ
ለመኖሪያ ቤት ፣ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ለምርመርና ጥናት፣ ለመንግስት መ/ቤት፣ ለበጎ
አድራጎት እና ለሐይማኖት ተቋማት 99 ዓመት ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ለከተማ ግብርና የሊዝ
ዘመን 15 ዓመት መሆኑን ሲደነግግ በአዲስ አበባ ከተማ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለባህልና
ስፖርት 90 ዓመት፣ ለኢንዱስትሪ 70 ዓመት፣ ለንግድና ለሌሎች 60 ዓመት መሆኑን
እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ለትምርህት፣ ለጤና፣ ለባህልና ለስፖርት 99 ዓመት፣
ለኢንዱስትሪ 80 ዓመት፣ ለንግድና ለሌሎች 70 ዓመት መሆኑን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም
ለዲፕሎማቲክ እና ለአለም አቀፍ ተቋማት በመንግስት ስምምነት መሠረት የሊዝ ዘመን ጣራ
እንደሚወሰን ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በመርህ ደረጃ እንደየከተማው የእድገት ደረጃ (በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች) እና
የልማት ስራው ዘርፍ ወይም የአገልግሎት አይነት ሊለያይ የሚችል ሆኖ የሊዝ ዘመን ከ60
ዓመት - 99 ዓመት የተወሰነ ቢሆንም በባህሪው ረዘም ያለ የሊዝ ይዞታ ዘመን ለሚጠይቅ
የልማት ስራ ወይም አገልግሎት ከተወሰነው ዘመን ጣሪያ ግማሽ ሳይበልጥ ሊጨመር

104
እንደሚችል በግልጽ ተደንግጓል፡፡68 በሌላ በኩል በልዩ ሁኔታ ለጊዜው በልማት ስራ ጥቅም ላይ
በማይውሉ የከተማ ቦታዎች ላይ ለሚቀርቡ የአጭር ጊዜ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት
የቦታ ጥያቄዎች ከ5 ዓመት በማይበልጥ በሊዝ ሊስተናገዱ እንደሚችሉና እንደአስፈላጊነቱ
ለተመሳሳይ ጊዜ ሊታደስላቸው እንደሚችል አንቀጽ 18(2) (ለ) ይደነግጋል፡፡

በቀድሞው አዋጅና በአዲሱ አዋጅ መካከል የሊዝ ዘመንን በተመለከተ ያለው አንድ መሠረታዊ
ልዩነት በቀድሞው አዋጅ አንቀጽ 6(1) ላይ ተለይተው ላልተቀመጡ ሌሎች የልማት ስራዎች
ወይም አገልግሎቶች ተገቢ ጥናት ተደርጎ በክልሉ ወይም በከተማው አስተዳደር በሚወጣ ደንብ
መሠረት ሌላ የሊዝ ዘመን ጣሪያ መወሰን እንደሚቻል የሚደነግግ ቢሆንም በአዲሱ አዋጅ
ይህን የክልሎችና የከተማ መስተዳደሮች ስልጣን ሙሉ በሙሉ አንስቶታል፡፡

የሊዝ ውል የገባ ሰው በሊዝ ዘመኑ ሁሉ ቦታውን መልስ ሳይባል ወይም ኪራይ ጨምር
ሳይባል ውል ለያዘበት ዓመታት መጠቀም ይችላል ማለት ነው፡፡ የሊዝ ዘመን ሲያበቃ ደግሞ
በወቅቱ የሚኖሩትን የቦታውን የሊዝ መነሻ ዋጋና ሌሎች መስፈርቶች መሠረት በማድረግ
ሊታደስ የሚችል መሆኑን፤ የሊዝ ዘመኑ ሊታደስ የማይችልበት ሁኔታ ካለ ግን ለባለይዞታው
ካሳ የማይከፈል መሆኑን አንቀጽ 19(1) ላይ ተገልጿል፡፡ የሊዝ ይዞታው እንዲታደስለት
የሚፈልግ ሰው እንዲታደስለት መፈለጉን የሊዝ ዘመኑ ሊያበቃ ከ10 -2 ዓመት እስኪቀረው
ድረስ ባለው ጊዜ እድሳት መፈለጉን ለሚመለከተው አካል በጽሑፍ ካመለከተ ብቻ ይሆናል፡፡
ማመልከቻው የቀረበለት አካልም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን በፅሑፍ ለአመልካች
የመግለጽ ግዴታ ያለበት ሲሆን ውሳኔውን በተባለው ጊዜ ውስጥ ካላስታወቀ በእድሳቱ
እንደተስማማ ተቆጥሮ በወቅቱ በሚኖረው የሊዝ መነሻ ዋጋና ለአገልግሎቱ የሊዝ ዘመን
መሠረት የሊዝ ውሉ ይታደሳል፤ አንቀጽ 19(2)(3)ን ይመለከቷል፡፡

2.2 የሊዝ ተዋዋይ ወገኖች መብቶች እና ግዴታዎች


የከተማ ቦታን በሊዝ ያገኘ ሰውም ሆነ የሊዝ ውሉን ሰጭው የመንግስት አካል ወይም የከተማ
መስተዳደር በከተማ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረገድ የየራሳቸው ተነፃፃሪ መብቶችና
ግዴታዎች አሏቸው፡፡

አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 18(2)(ሀ)


68

105
2.2.1 የሊዝ ሰጭ (የክልሎች ወይም የከተማ መስተዳደሮች) መብቶችና ግዴታዎች
የሊዝ ሰጭው መብቶች
 በአዋጁ እና በሚወጣ ደንብ መሠረት የሊዝ ኪራይ ከተጠቃሚዎች የመሰብሰብ
መብት፤አንቀፅ 20

 የችሮታ ጊዜ የመስጠት ወይም የመከልከል መብት፤አንቀፅ 15

 ለህዝብ ጥቅም ሲባል መለቀቅ ያለበትን የሊዝ ይዞታ ካሣ በመክፈል ማስለቀቅና


መረከብ አስፈላጊም ሲሆን የፖሊስ ኃይልን የመጠቀም መብት ፤አንቀፅ 25-27

 በሕገወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታ የማስለቀቅ መብት፤አንቀፅ 26(4)

 የሊዝ ቦታን መሠረት በማድረግ ክርክር ሲነሳ በከሳሽነትም ሆነ በተከሳሽነት


የመከራከር መብት፤አንቀፅ 29-30

የሊዝ ሰጪው ግዴታዎች


1. ለጨረታ የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎችን ለህዝብ ይፋ ከመደረጋቸው በፊት ከይገባኛል
ጥያቄ ነፃ መሆናቸውን፣ የከተማውን ፕላን ተከትሎው የተዘጋጁ መሆናቸውን፣
የመሠረተ ልማት አውታሮች የተሟሉላቸው መሆናቸውን፣ ተሸንሽነው ምልክትና
ድንበር ያላቸው መሆናቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች የተሟሉ መሆኑን
ማረጋገጥ፣ አንቀጽ 8 (1)

2. የመሬት አቅርቦት ፍላጎትንና ትኩረት የሚደረግባቸውን የልማት መስኮች መሠረት


በማድረግ በየዓመቱ ለጨረታ የሚያወጡትን የከተማ ቦታ መጠን በመለየት ዕቅዱን
ለህዝብ ተደራሽና ይፋ ማድረግ እና ወቅቱን የጠበቀ የመሬት አቅርቦት እንዲኖር
ማድረግ፣ አንቀጽ 10 (1)(ሀ)

3. የሊዝ ጨረታ ለማካሄድ የጨረታ ማስታወቂያ ከማውጣትና የጨረታ ሰነድ ከመሸጥ


ጀምሮ ጨረታው እስከሚጠናቀቅ ሂደቱን በአግባቡ በመምራት አሸናፊዎቹን መለዬት፤
አንቀጽ 11

4. የሊዝ ውል ለፈረመ ሰው የሊዝ የይዞታ ምስክር ወረቀት ማዘጋጀትና ቦታውን በመስክ


ተገኝቶ ማስረከብ፣ አንቀጽ 16(4)

106
5. በሊዝ የተያዘውን ቦታ በውሉ መሠረት እንዲለማ መደረጉንና በየዓመቱ የሚከፈለው
የሊዝ ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ እየተፈፀመ ስለመሆኑ ክትትል የማድረግና የማረጋገጥ
ኃላፊነት፣ አንቀጽ 16(5)

6. የሊዝ እድሳት ጥያቄ ሲቀርብለት በአዋጁ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ
የመስጠት ግዴታ፣ አንቀጽ 19(3)

7. ለህዝብ ጥቅም ሲባል አንድን የሊዝ ባለይዞታ በሚያስለቅቅበት ጊዜ ተመጣጣኝ ካሣ


የመክፈል ግዴታ፣ አንቀጽ 25(4) እና 26(1)

2.2.2 የሊዝ ውል ተቀባይ መብቶች እና ግዴታዎች


የሊዝ ውል ተቀባይ በአዋጁ ላይ እንደተጠቀሰው በግለሰብም ይሆን በተቋም ደረጃ
የከተማ መሬትን በጨረታ ወይም በምደባ የሚያገኝ ሰው ሲሆን የሚከተሉት መብቶችና
ግዴታዎች ይኖሩታል፡፡
የሊዝ ተቀባይ መብቶች
 በሊዝ ጨረታ የመሳተፍና አሸናፊ ሲሆንም የሊዝ ውሉን በመፈረም ተገቢውን ክፍያ
ከፍሎ ቦታውን የመረከብ መብት፣ አንቀጽ 16(3)(4)

 የሚመለከተው አካል ሲፈቅድለት የሊዝ ባለይዞታው የተፈቀደለትን የአገልግሎት


አይነት ወይም የልማቱን ስራ ዓይነት መቀየር፣ አንቀጽ 21(3)

 መብቱን ወደ ሶስተኛ ወገን የማስተላለፍ፣ በዋስትና የማስያዝ ወይም የከፈለውን


ክፍያ በካፒታል አስተዋፆነት ለመጠቀም የሚያስችል መብት፣ አንቀጽ 24

 ለህዝብ ጥቅም ተብሎ የመሬት የሊዝ ባለይዞታነቱ በሚለቀቅበት ጊዜ ካሣ በቅድሚያ


የማግኘት መብት፣ (ሕገ-መንግስት 40(8) እና አዋጁ አንቀጽ 26(1)

 የሊዝ ይዞታን አስመልክቶ አለመግባብት ሲፈጠር በአዋጁ ለተቋቋመው የአስተዳደር


አካልና በይግባኝ እስከ ከፍተኛ ፍ/ቤት የመከራከር መብት፣ ሕገ-መንግስቱ አንቀጽ
37 እና አዋጁ አንቀጽ 29-30

 የሊዝ ባለይዞታነት ዘመኑ ሲያልቅ ውሉን እንዲታደስ ጥያቄ የማቅረብ መብት፣

107
የሊዝ ተቀባይ ግዴታዎች
1. በሊዝ ውል ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለተፈቀደለት
አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል፤ አንቀጽ 21(1)

2. በሊዝ ውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታ መጀመር እና በጊዜ ገደቡ


የማጠናቀቅ ግዴታ፤ አንቀጽ 22(1) እና አንቀጽ 23(1)

3. በሊዝ የያዘውን ቦታ የሊዝ ቅድሚያ ክፍያ፣ ቀሪ ዓመታዊ ክፍያና ወለድ ወቅቱን


ጠብቆ የመክፈል ግዴታ፤ አንቀጽ 20

4. የከተማ ቦታ ጥቅም ላይ ካልዋለ፣ የሊዝ ዘመኑ ጨርሶ ካልታደሰና ቦታው ለህዝብ


አገልግሎት በመፈለጉ ምክንያት የሊዝ ውል ሲቋረጥ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ
በቦታው ላይ ያሰፈረውን ንብረት በማንሳት ቦታውን አግባብ ላለው አካል መልሶ
ማስረከብ፣ አንቀጽ 25(1) እና (5) የሚሉ ግዴታዎች ይገኙበታል፡፡

5. የሊዝ ባለይዞታው እንደማንኛውም ዜጋ የሊዝ አዋጁን ለማስፈፀም በሚደረግ


ማናቸውም እንቅስቃሴ ትብብር የማድረግ ግዴታ፤ አንቀጽ 34

2.3 የሊዝ መብትን ማስተላለፍ እና በዋስትና ማስያዝ


ሊዝ ምንም እንኳን በመሬቱ ባለቤት በመንግሥት እና በተከራዩ መካከል የሚደረግ ውል
ቢሆንም ተከራዩ (የሊዝ ባለይዞታው) መብቱን ለሌላ ሶስተኛ ወገን የማስተላለፍ መብት
ይኖረዋል፡፡ የሊዝ ባለይዞታው መብቱን ከማስተላለፍ በተጨማሪ መብቱን በዋስትና ማስያዝና
በካፒታል አስተዋጽኦነት (Capital Contribution) ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

በመሆኑም የአሁኑም ሆነ የድሮው የሊዝ አዋጆች የሊዝ መብትን ማስተላለፍ አይከለክሉም።


በእርግጥ ቀደም ሲል አዲስ አበባን ጨምሮ የአንዳንድ ከተሞች ባለይዞታዎች ባዶ መሬት ወይም
መሠረት የወጣለትን ቦታ እንዳያስተላለፉ የውስጥ መመሪያ ሲያወጡ ነበር። ከተሞቹ እነዚህ መብት
ገዳቢ የሆኑትን መመሪያዎች ማውጣት የተገደዱበት ምክንያት በከተሞቹ እየተስፋፋ የመጣውን
ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት ነበር፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ማለት በአንድ ነገር ላይ እሴት ሳይጨምሩ
ትርፍ መፈለግ ነው።69 ይህም ማለት የከተማ ደላሎችና አትራፊዎች ከመንግሥት ያገኙትንና ከሌላ

ዳንኤል ወልደ ገብርኤል፤ አነጋጋሪው የአዲሱ የሊዝ አዋጅ ይዘትና አንድምታው at www.ethiopianreporter.com 2011
69

Date of Use: November 25, 2011 ገፅ 5

108
ሰው የተላለፈላቸውን የሊዝ መሬት ምንም እሴት ሳይጨምሩበት ይልቁንም ጊዜ በመጠበቅ ብቻ
ከፍተኛ ትርፍ ያጋብሳሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የመሬት እጥረት ፈጥረዋል፡፡ በዚህ የኪራይ ሰብሳቢነት
ሂደትም ታላላቅ የተባሉ የሪል ስቴት አልሚዎችም ተሳታፊ እንደነበሩ ይታወቃል።

አዋጅ ቁጥር 721/2004ን ስንመለከት የሊዝ መብትን ለሦስተኛ ወገን በማንኛውም መልኩ
ማስተላለፍን፣ በዕዳ ማስያዝንና ለንግድ ማኅበር እንደ ካፒታል መዋጮ አድርጎ መስጠትን
እንደሚቻል ይገልጻል። ስለዚህ አዋጁ በመርህ ደረጃ የመሬት የሊዝ መብትን በነፃ ማስተላለፍን
ያለምንም ገደብ ፈቅዷል ማለት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ቢባልም አዋጁ ከዚህ በፊት የነበረውን
የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር የሚያስወግድበት ስልትም ነድፏል። የአዋጁን አንቀጽ 24 ስንመለከተው
ከላይ የተነሳውን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ አራት ስልቶችን አስቀምጧል።

አንደኛውና ዋነኛው ባዶ ቦታ (የሊዝ መብትን ብቻ) ወይም ከግማሽ በታች ግንባታ በመሥራት
ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ምንም ጥቅም እንዳይኖረው ተደርጓል። በዚህ አንቀጽ መሠረት
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ የሊዝ መብቱን ግንባታ ከመጀመሩ ወይም ግንባታውን በግማሽ
ከማጠናቀቁ በፊት ከውርስ በስተቀር ማስተላለፍ የሚችለው አግባብ ባለው አካል ቁጥጥር
የሚደረግበት ግልጽ የሽያጭ ሥርዓትን በመከተል ይሆናል፤አንቀፅ 24(2)፡፡
ሁለተኛ ግንባታ ያልተሠራለት ወይም ግማሽ ግንባታ ያለው ቦታ ሲተላለፍ ባለመብቱ የሚያገኘው
የተፈጸመው የሊዝ ክፍያና የሊዝ ክፍያው በባንክ ቢቀመጥ ያስገኝ የነበረው ወለድ፣ የተከናወነው
ግንባታ ዋጋና የሊዝ መብቱ በመተላለፉ የተገኘው የሊዝ ዋጋ አምስት በመቶ ብቻ ነው። (አንቀፅ
24(3)) ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ባዶ መሬት በሊዝ ጨረታ በካሬ ሜትር በ3000 ብር አሸንፎ 200 ካሬ
ሜትር ቢረከብ፣ ለዚህም ቅድሚያ የዋጋው 10 በመቶ 60,000 ብር ይከፍላል። ይህ ግለሰብ በመሬቱ
ላይ በ40,000 ብር መሠረት ካወጣ በኋላ መቀጠል ስላልቻለ መሠረት የወጣለትን ቦታ በካሬ ሜትር
ብር 4,000 ቢሸጥ ፤ በካሬ ሜትር 1,000 ብር በጠቅላላ ብር 200,000 ትርፍ ተገኘበት ማለት ነው።
ሻጭ የሚያገኘው ለሊዝ ቅድሚያ ክፍያ የከፈለውን 60,000 ብር፣ የዚሁ ወለድ አምስት በመቶ 3,000
ብር፣ ለመሠረት ግንባታ የተከፈለ 40,000 ብር እና በሊዝ መብቱ መተላለፍ የተገኘውን የ200,000
ብር አምስት በመቶ 10,000 ብር በድምሩ 113,000 በመሆኑ ግለሰቡ ያተረፈው 13,000 ብር
ይሆናል ማለት ነው።

ሦስተኛ ባለመብቱ ከባንክ መብቱን አስይዞ መበደር ከፈለገ የሊዝ መብቱ (ባዶ መሬት) የሚገመትለት

109
አስቀድሞ በከፈለው የሊዝ ዋጋ ክፍያ መሠረት ነው፤ አንቀፅ 24(4)፡፡ ይህም ማለት ለአብነት ከላይ
የተጠቀሰውን ምሳሌ ብንወስድ ባለመብቱ ለሊዝ የከፈለው 60,000 ብር ስለሆነ ባንኮች ለመሬቱ/ሊዝ
መብቱ ብቻ ከዚህ በላይ ሊያበድሩ አይችሉም። በእርግጥ ተጨማሪ ግንባታ ካለ የዚህን ግምትም
መያዛቸው አይቀርም። ቀደም ሲል ባንኮች ሲያበድሩ ለመሬቱ ብቻ በካሬ ሜትር እያሰቡ ይይዙ ነበር።
አሁን ግን ተበዳሪው የሚያዝለት የከፈላት ክፍያ ብቻ ናት።

አራተኛ አዋጁ ማንኛውም ሰው በመሬት የወቅት ጥበቃ የሚመጣን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ
በተደጋጋሚ ጊዜ ግንባታ ሳያጠናቅቅ የሊዝ መብቱን የሚያስተላልፍ ከሆነ፣ የሚመለከተው አካል
በማንኛውም የሊዝ ጨረታ እንዳይሳተፍ ሊከለክለው ይችላል፤ አንቀፅ 24(7) የሚሉ ናቸው፡፡

የሊዝ ባለይዞታው (ተከራዩ) መብቱን በዋስትና ካስያዘ በኋላ ምናልባት በውሉ መሰረት እዳውን
መክፈል ካልቻለ ወይም የመክሰሩ ሁኔታ በፍርድ ከተረጋገጠ አበዳሪው ወይም የሊዝ መብቱን
በዋስትናው የያዘው ሰው የሊዝ ባለይዞታውን መብት፣ በቦታው (በመሬቱ) ላይ የሚገኘውን
ህንፃውና ከህንፃው ጋር የተያያዙ መገልገያዎችን በሕግ መሰረት ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ወይም
እራሱ ሊጠቀመበት እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 24(6) ላይ ተመልክቷል፡፡

2.4 የሊዝ ይዞታ የሚታጣባቸው ምክንያቶች እና ይዞታን የማጣት ውጤቶች

በመርህ ደረጃ ሊዝ በመሬቱ አከራይና ተከራይ መካከል ለተወሰነ ጊዜ የሚደረግ ውል በመሆኑ


የውሉ ጊዜ ከመድረሱ ወይም ከመጠናቀቁ በፊት ተከራዩ (የሊዝ ባለይዞታው) ከሊዝ መብቱ
አይፈናቀልም፣ አንቀፅ 26(3):: ነገር ግን ምንም እንኳን ውሉ የተደረገው ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም
የውሉ ጊዜ ከመጠናቀቁ ወይም ከመድረሱ በፊት የሊዝ ባለይዞታው (ተከራዩ) ከይዞታው
ሊፈናቀል የሚችልባቸው ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡

ሊዝ (ኪራይ) የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች በአዋጁ አንቀጽ 25(1) ላይ ተዘርዝረዋል፡፡


እነርሱም፡- ባለይዞታው ቦታውን ጥቅም ላይ ሳያውል ሲቀር፤ ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ለሌላ
አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን፣ ወይም የሊዝ ይዞታ ዘመኑ አብቅቶ ሳይታደስ ሲቀር የሚሉ
ናቸው፡፡

110
2.4.1. ቦታውን ለተፈቀደለት ዓላማ ጥቅም ላይ አለማዋል፣ በጊዜ ገደቡ ግንባታ አለመጀመር
እና አለማጠናቀቅ

የከተማ ቦታ ሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን


ለተፈቀደለት አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል ያለበት መሆኑን አንቀጽ 21(1) ይደነግጋል፡፡
ምናልባት የሊዝ ባለይዞታው የቦታውን አጠቃቀም መለወጥ የሚችለው አግባብ ላለው አካል
አመልክቶ ከተፈቀደለት ብቻ መሆኑን የዚሁ አንቀጽ ተከታይ ድንጋጌዎች ይገልፃሉ፡፡
በመሆኑም ባለይዞታው በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለታሰበለት ዓላማ ካላዋለው እና
ጥቅም ላይ ያለዋለው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ካልተረጋገጠ እንዲሁም ተጨማሪ
ጊዜ ካልተሰጠው የሊዝ ውሉ ተቋርጦ ተገቢው ወጭና መቀጮ ተቀንሶ የሊዝ ክፍያው
ለባለመብቱ ተመላሽ እንደሚሆን ከአንቀጽ 25 (1)(ሀ) ንዑስ ቁጥር 2 እና 3 እንረዳለን፡፡

ስለዚህ የሊዝ ባለመብቱ ግንባታ የሚጀምርባቸውና የሚያጠናቅቅባቸው ጊዜያትን ተላልፎ


ከተገኘ አሁንም መሬቱ ተመልሶ በመንግስት ይወሰድበታል፡፡ ከቦታው መወሰድ ጋር ተያይዞ
የሊዝ ባለይዞታው ቦታውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሊዝ ክፍያና የጠቅላላ ውል የሊዝ
ዋጋ 7% መቀጮ ለመንግስት ተቀንሶ ገቢ ተደርጎ ቀሪ ገንዘቡ ይመለስለታል፣ አንቀጽ 25(3)፡፡
ሆኖም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12(3) መሠረት በቀበሌ መኖሪያ ቤት ሕጋዊ ተከራይ የነበረ ሰው
በከተማ መልሶ ማልማት ምክንያት ተነሽ በመሆኑ የመኖሪያ ቤት መስሪያ የከተማ ቦታ በሊዝ
መነሻ ዋጋ የተሰጠው ሰው በውሉ በተመለከተ የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ ካልጀመረ ለአቅም
ማሳያ በዝግ የባንክ ሒሳብ ከተያዘው ገንዘብ ላይ 3 በመቶ ይቀጣል፡፡ አንቀጽ 22(4)
ይመለከቷል፡፡

በሌላ በኩል በአዋጁ አንቀጽ 12(1) መሠረት ለመንግስት መስሪያ ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት፣
ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለእምነት ተቋማ፣ ለኤምባሲዎችና ለአለም
አቀፍ ድርጅቶች በሊዝ መነሻ ዋጋ በምደባ የተሰጡ ቦታዎች ቦታውን የተረከበው አካል ወይም
ተቋም በተወሰነ ጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ ካልጀመረ ያልምንም መቀጫ ቦታውን ብቻ
ይመልሳል፤ አንቀጽ 22(5)ን ይመልከቱ፡፡

በአጠቃላይ የሊዝ አዋጅ የግንባታ መጀመሪያ ጊዜን ብቻ ሳይሆን የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜም
የተገደበ እንዲሆን ያደረገ በመሆኑ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሕጉ በተወሰነው የጊዜ ገደብ

111
ውስጥ ግንባታውን ካላጠናቀቀ አግባብ ያለው አካል የሊዝ ውሉን በማቋረጥ ቦታውን መልሶ
እንደሚረከብ አንቀጽ 23(5) ይደነግጋል፡፡ የሊዝ ባለመብቱ በመሬቱ ላይ ያቆመው ወይም
የገነባው ንብረት ካለ በራሱ ወጭ እንዲያነሳ ይገደዳል፡፡ በተጠቀሰው ቀነ ገደብ ማንሳት ካልቻለ
ግን የከተማ መስተዳደሩ እንደ ሁኔታው መሬቱን ከነግንባታው ለሌላ ሰው በጨረታ ማስተላለፍ
ወይም ደግሞ በመሬቱ ላይ ያለውን ሀብት በማንሳት ወጭውን የሊዙ ባለመብት የነበረው ሰው
እንዲከፍል ማስገደድ ይችላል፣ አንቀጽ 23(7)፡፡

2.4.2 መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ለሌላ ሥራ ወይም አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን
የሊዝ ባለይዞታው ከሊዝ ይዞታው የሚፈናቀለው መሬቱ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በአዋጅ ቁጥር
455/1997 መሠረት የሚወረስ ወይም የሚወሰድ ከሆነ ነው፡፡ ስለዚህ የህዝብ ጥቅም
በሚያሻበት ወቅት ምንም አንኳን መሬቱ በሊዝ የተሰጠ ቢሆንም የሊዝ ይዞታው ሊቋረጥ
ይችላል፡፡ የህዝብ ጥቅም ምን ማለት እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 2(7) ላይ ተተርጉሟል፡፡
ትርጉሙም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሕዝቦች በመሬት ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በቀጣይነት ለማጎልበት አግባብ ያለው አካል
በከተማው ፕላን መሠረት የሕዝብ ጥቅም ብሎ የሚወስነው የመሬት አጠቃቀም ነው፡፡

የሊዝ ይዞታ ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚወረስበት ጊዜ የሊዝ ባለይዞታው በአዋጅ ቁጥር
721/2004 አንቀጽ 25(4) እና አንቀጽ 26(1) በተመለከተው እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር
455/1997 መሰረት ተገቢው ካሳ ሊከፈለው ይገባል፡፡ ካሳ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 ትርጉም
ባይሰጠውም በአዋጅ ቁጥር 455/1997 አንቀጽ 2(1) ላይ በአግባቡ ተተርጉሟል፡፡ በዚህ አዋጅ
መሰረት ካሳ የሚባለው በዓይነት ወይም በገንዘብ ወይም በዓይነትና በገንዘብ የሚደረግ ክፍያ
እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሊዝ የተሰጠው መሬት ሲወሰድ የሊዝ
ባለይዞታው የሚከተለው ካሳ ይከፈለዋል፡፡

1. በአዋጅ ቁጥር 455/97 አንቀጽ 7(1) መሠረት በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት እንዲሁም
በመሬቱ ላይ ለተደረገው ቋሚ ማሻሻል ካሳ ይከፈለዋል፡፡
2. በመሬቱ ላይ ለሚገኘው ንብረት የሚከፈለው ካሳ ንብረቱን በነበረበት ሁኔታ ለመተካት
የሚያስችል ይሆናል (አንቀጽ 7(2)) ፡፡

112
3. በመሬቱ ላይ ለተደረገው ቋሚ መሻሻል የሚከፈለው ካሳ በመሬቱ ላይ የዋለውን ገንዘብ እና
ጉልበት ዋጋ (Capital and Labour) የሚተካ ይሆናል፣ (አንቀጽ 7(4))
4. በተወረሰው የሊዝ ይዞታ መሬት ላይ የነበረው ንብረት ከነበረበት ቦታ ተነስቶ (ተነቅሎ) ወደ
ሌላ ቦታ ተዛውሮ ሊተከልና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ከሆነ ንብረቱን ለማንሳት
ለማጓጓዝ እና ለመትከል የሚያስችል ካሳ ይከፈላል (አንቀጽ 7(5))፡፡
5. ከላይ ከ1-4 ከተመለከተው ካሳ በተጨማሪ የሊዝ ባለይዞታው በአዋጁ አንቀጽ 8 መሠረት
የመናፈቂያ ካሳ ይከፈለዋል፡፡
6. በተጨማሪም የሊዝ ባለይዞታው ለቀሪው (ለቀረው) የሊዝ ዘመን የሚጠቀምበት ተመጣጣኝ
መሬት በምትክ ይሰጠዋል፡፡ በምትክ የሚሰጠው መሬት ኪራዩ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል
ከተወሰደው መሬት ከሚከፈለው ኪራይ ያነሰ ከሆነ በምትክ የተሰጠውን መሬት ረዘም ላለ
ተጨማሪ ጊዜ እንዲጠቀምበት በማድረግ ማካካስ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የሊዝ ባለይዞታው
በምትክ የተሰጠውን መሬት መረከብ ካልፈለገ ለቀሪው የሊዝ ዘመን ኪራዩ ተሰልቶ ለሊዝ
ባለይዞታው ይመለስለታል፣ አዋጁን አንቀጽ 8(6) ን ይመለከቷል፡፡

2.4.3 የሊዝ ይዞታ ዘመኑ አብቅቶ ሳይታደስ ሲቀር


በመርህ ደረጃ የሊዝ ዘመኑ ሲያልቅ ውሉ ይታደሳል። ሊታደስ የሚችለው ግን ባለመብቱ የማደስ
ፍላጎቱን አስቀድሞ በጽሑፍ አሳውቆ ከሆነ ነው። ሲታደስም የሊዝ ክፍያው እንደ አዲስ ተከልሶ
በወቅቱ ዋጋ መሠረት ይሆናል፤አንቀፅ 19(1) እና (2) ተመልከት፡፡ ነገር ግን መንግሥት ቦታው
ለሌላ የበለጠ አገልግሎት ተግባር ፈልጎት ከሆነ ወይም ቦታው በወቅቱ ማስተር ፕላን መሠረት ለሌላ
ዕቅድ የሚውል ከሆነ ውሉ አይታደስም። ውሉ ባይታደስ ባለመብቱ ያለምንም ካሳ ንብረቱን በአንድ
ዓመት ውስጥ ከቦታው በማንሳት መሬቱን ለመንግሥት ያስረክባል። በተባለው ጊዜ ንብረቱን ባያነሳ
ግን የሚመለከተው አካል መሬቱን ከነንብረቱ ይወስደዋል፣ አንቀፅ 25(5) እና (6) ይመለከቷል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች
1. ለሕዝብ ጥቅም ቦታን ማስለቀቅ ሲባል በህግ ትርጉም የሚሠጠው ወይም መመዘኛ አለ
ወይ? የካሣ አከፋፈሉ ስርዓት ቢብራራ?
2. አዋጅ ቁጥር 272/1994ን አሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 መተካት ያስፈለገበት
ምክንያት ምንድን ነው? አዲሱ አዋጅ ከቀድሞው አዋጅ የሚለይባቸው ነጥቦች ምንድን
ናቸው?

113
ምዕራፍ ሶስት
የከተማ ቦታን አስመልክቶ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸው መንገዶች

በመርህ ደረጃ የከተማ ቦታ በሊዝ የያዘ ሰው የሊዝ ውሉን ባለማክበሩ፣ የቦታ አጠቃቀሙ ከከተማው
ፕላን ጋር ሊጣጣም የሚችል ባለመሆኑ ወይም ቦታው መንግሥት ለሚያካሂደው የልማት ሥራ
አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የሊዝ ዘመኑ ከማለቁ በፊት ይዞታውን እንዲለቅ
አይደረግም፡፡ ሆኖም አግባብ ያለው አካል ከቦታው ለሚነሳው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ
እንዲከፈል በማድረግ እና ምትክ ቦታ በከተማው ውስጥ በመስጠት የከተማ ቦታ ይዞታን ለሕዝብ
ጥቅም ሲባል የማስለቀቅና የመረከብ ሥልጣን ይኖረዋል፣ (አንቀፅ 26)፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ
የከተማ ቦታን አስመልክቶ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱባቸው መንገዶች እንመለከታለን፡፡

የስልጠናው ዓላማ

ሰልጣኞች የዚህን ምዕራፍ ስልጠና ሲጨርሱ፡-

 የሊዝ መብትን አስመልክቶ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ የሚፈቱባቸውን መንገዶች ለይተው


ያውቃሉ፡፡

3.1 አግባብ ያለው አካል

“አግባብ ያለው አካል” ማለት የከተማ ቦታን ለማስተዳደርና ለማልማት ሥልጣን የተሰጠው የክልል
ወይም የከተማ አስተዳደር አካል ነው፡፡70 በህግ ስልጣን የተሰጠው አግባብ ያለው አካል በሊዝ
የተሰጠን መሬት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል እንዲወሰድ/እንዲወረስ ከወሰነ ይህ የመንግሥት አካል
ለሊዝ ባለይዞታው የማስለቀቂያ ትዕዛዝ ወይም ማስጠንቀቂያ በጽሁፍ በመስጠት የሚፈለገውን
የከተማ ቦታ ማስለቀቅና መረከብ ይችላል፡፡ በመሆኑም ይዞታው የሚለቀቅበት ጊዜ፣ ሊከፈል
የሚገባው የካሣ መጠን እና ሊሰጥ የሚችለው የምትክ ቦታ ስፋትና አካባቢ ተጠቅሶ የማስለቀቂያ
ትዕዛዝ ለባለይዞታው በጽሁፍ ይሰጣል (አንቀፅ 27(1))፡፡

አዋጅ ቁጥር 721/2004 አነቀፅ 2(6)


70

114
የማስለቀቂያ ትዕዛዝ የደረሰው ወይም ትዕዛዝ በተሰጠበት ንብረት ላይ መብቴ ወይም ጥቅሜ
ይነካብኛል የሚል ማንኛውም ሰው ትዕዛዙ በደረሰው በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ያለውን አቤቱታ
ከዝርዝር ምክንያቱና ማስረጃው ጋር አግባብ ላለው አካል (ትዕዛዙን ለሰጠው አካል) ቅሬታውን
ማቅረብ የሚችል መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 28(1) ተመልክቷል፡፡ አግባብ ያለው
አካል ማስጠንቀቂያ የሰጠው በሕገ ወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታ ለማስለቀቅ ከሆነ በዚህ አዋጅ
አንቀጽ 26 (4) መሠረት ማስጠንቀቂያ የደረሰው ሰው ማስጠንቀቅያው በደረሰው በሰባት የሥራ ቀናት
ውስጥ አቤቱታውን ከዝርዝር ምክንያቱና ማስረጃው ጋር አግባብ ላለው አካል ማቅረብ ይችላል፤
አንቀጽ 28(2):: ይኸን ተከትሎ አግባብ ያለው አካል የቀረበለትን አቤቱታ በአግባቡ በማጣራት
ውሳኔ መስጠትና ውሳኔውን ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ የቀረበው አቤቱታ
ተቀባይነት ያላገኘ ከሆነ ምክንያቱ በግልጽ በውሳኔው ውስጥ መገለጽ ይኖርበታል፡፡

በቀድሞው አዋጅ ቅሬታው የቀረበለት የመንግሥት አካል አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ በአዋጁ
አንቀጽ 17(2) መሠረት ካሣ ሊከፈለው የሚገባው መሆኑን ካመነ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈለው
ይወስናል ወይም የቀረበለትን አቤቱታ የማይቀበለው ከሆነ አቤቱታውን ያልተቀበለበትን
ምክንያት በመግለጽ ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሁፍ ያሳውቃል የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም የቀድሞ
አዋጅ የሊዝ ባለመብቱ ካሣ ይገበዋል ወይስ አይገባውም የሚለውን የሚወስነው ባለመብቱ
አቤቱታ ካቀረበ በኋላ መሆኑን ያሳያል፡፡ ጉዳዩን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ አዋጅ ቁጥር
272/1994 አንቀጽ 16(1) መሠረት አግባብ ያለው አካል ለሕዝብ ጥቅም ይውላል ብሎ
በሚወስነው መሠረት ለሚመለከተው ሰው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሚፈልገውን የከተማ ቦታ
ማስለቀቅና መረከብ ይችል ነበር፡፡ ለሊዝ ባለይዞታውም ካሣ የሚከፈለው የሕጉን አቤቱታ
አቀራረብ በመከተል አግባብ ላለው አካል ሲያመለክት መሆኑን የዚሁ አዋጅ አንቀጽ 15(3)
ይደነግጋል፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የዜጎችን በንብረታቸው ላይ ካሣ የማግኘት መብት
የሚያጣብብ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ከአዋጅ ቁጥር 455/1997 ጋር ለማጣጣምም ያስቸግር
ነበር፡፡ አዲሱ አዋጅ ግን ሲጀምር በአንቀጽ 25(1)(ለ) መሠረት የከተማ ቦታ የሊዝ ይዞታ
ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ለሌላ አገልግሎት እንዲውል ሲወሰን ባለይዞታው አግባብ ባለው ሕግ
መሠረት ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፈለው አንቀጽ 25(4) ይደነግጋል፡፡ ይህ አግባብ ያለው ሕግ
የተባለው ደግሞ አዋጅ ቁጥር 455/1997 መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም የካሣ አከፋፈልን
በተመለከተ ይህ አዋጅ መሠረታዊና አግባብ ያላቸውን ድንጋጌዎች የያዘ ልዩ ሕግ ስለሆነ ነው፡፡
የዚሁ ህግ አንቀጽ 26(1)ም አግባብ ያለው አካል የሊዝ ይዞታ የሆነን የከተማ ቦታ ለሕዝብ

115
ጥቅም ማስለቀቅ የሚቻለው ከቦታው ላይ ለሚነሳው ንብረት ተመጣጣኝ ካሣ በቅድሚያ
እንዲከፈል በማድረግ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በዚህም አዋጅ ቁጥር 455/1997 እና
አዋጅ ቁጥር 721/2004 በቅድሚያ ካሳ በመክፈል ረገድ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ በመሆኑም
የሊዝ ይዞታውን እንዲለቅ የተደረገ ሰው አግባብ ላለው አካል የሚያመለክተው ቅሬታ አንድም
መነሳት የለብኝም በማለት አልያም የተሰጠኝ ምትክ ቦታ ወይም የተከፈለው የካሣ መጠን በቂ
አይደለም የሚል ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡

3.2 ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ


የሊዝ ባለይዞታው የሊዝ ይዞታው እንዲወሰድ ትዕዛዝ ወይም ማስጠንቀቂያ ለሰጠው አካል
አቤቱታውን ካቀረበ በኋላ በዚህ የመንግስት አካል ውሳኔ ቅሬታ ካለው የይግባኙን ቅሬታ
በአዲሱ አዋጁ አንቀጽ 29(1) መሠረት ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውሰጥ
ይግባኙን ለከተማው የቦታ ማስለቀቅና የካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ ይችላል፡፡

ጉባኤው የቀረበለትን ይግባኝ በአዋጁ አንቀጽ 29(2) መሠረት ከመረመረ በኋላ በ3ዐ የሥራ ቀናት
ውስጥ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል፡፡ ውሳኔውንም ለተከራካሪ ወገኖች በጽሁፍ ማሳወቅ
ይኖርበታል፡፡ በካሣ ክርክር ላይ ካልሆነ በስተቀር ምትክ ቦታን ጨምሮ በሌሎች በሕግም ሆነ በፍሬ
ነገር ክርክሮች ላይ ጉባዔው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፣ አንቀጽ 29(3) ፡፡

3.3 የከተማ ነክ እና መደበኛ ፍ/ቤቶች

ካሳው አንሷል ወይም በዝቷል ወይም ካሳ ተከለከልኩ የሚለው ወገን አሁንም ይግባኙን ከተማ
ከሆነና የከተማ ነክ ፍ/ቤት ካለ ለከተማው የከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት
(Municipal Appellate Court) ወይም የከተማ ነክ ጉዳዮች ፍ/ቤት ከሌለ ለክርክሩ ምክንያት
የሆነው ንብረት በሚገኝበት ለሚያስችለው የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ
በ30 ቀናት ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ እንደሚቻል በአዋጁ አንቀጽ 29(4) ላይ ተደንግጓል፡፡ ነገር
ግን ይግባኙን የሚያቀርበው የሊዝ ባለይዞታ ይግባኙን ማቅረብ የሚችለው በአዋጁ አንቀጽ
29(5) ላይ በተመለከተው ሁኔታ የሊዝ ይዞታውን ትዕዛዙን ወይም ማስጠንቀቂያውን ለሰጠው
አካል ካስረከበና ማስረከቡንም የሚያረጋግጠውን ማስረጃ ወይም ሰነድ ከይግባኝ ቅሬታው ጋር

116
አያይዞ ማቅረብ ከቻለ ብቻ ይሆናል፡፡ ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ይግባኙ በቀረበለት በ3ዐ የሥራ
ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡ የፍ/ቤቱ ውሳኔም የመጨረሻ ይሆናል፤ አንቀጽ 29(6)፡፡

ከላይ እንደተገለፀው የሊዝ ይዞታው ለህዝብ ጥቅም ተብሎ ሲወሰድ ወይም ሲወረስ ካሳን
አስመልክቶ የሚነሳው ክርክር ሊታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 455/1997 እንጅ በሊዝ አዋጅ
ቁጥር 721/2004 መሰረት አይሆንም፡፡ የቅሬታውን አቀራረብ ሂደት ወይም ስርዓት አስመልክቶ
በሁለቱ አዋጆች መካከል ጉልህ የሆነ ልዩነት አይታይም፡፡ ነገር ግን በአዋጅ ቁጥር 721/2004
አንቀጽ 29(3) ላይ በግልጽ እንደምንረዳው በሊዝ የተሰጠው መሬትና በመሬቱ ላይ የሚገኘው
ንብረት የተወረሰው ወይም የተወሰደው ያላግባብ ነው የሚል ክርክር ትዕዛዙን ለሰጠው አካል
እና ለከተማው የመሬት ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ ይችላል፡፡ ነገር ግን በአዋጅ
ቁጥር 455/1997 መሰረት በሊዝ የተያዘው መሬትና በመሬቱ ላይ የሚገኘው ንብረት
የተወረሰው ወይም የተወሰደው ያላግባብ ነው የሚል ክርክር ሊነሳ አይችልም፤ሊነሳ የሚችለው
ክርክር በካሳው ላይ ብቻ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከዚህ የምንረዳው በአዋጅ ቁጥር 455/1997
ያለው የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት የዜጎችን ፍትሕ የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ71 መብት
የሚያጣብብ ይመስላል፡፡ በአንፃሩ አዋጅ ቁጥር 721/2004 ይህንን መብት ለሊዝ ባለይዞታዎች
ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደር ለህዝብ ጥቅም ሣይሆን ለሌላ ግለሰብ ለመሰጠት በሊዝ ኪራይ
የተገኘ ቦታ ለማሰለቀቅ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም የሚቀረብ ክስ ለማን ነው የሚቀርበው?
ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የከተማው የመሬት ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ አለው ወይስ
የለውም? ፍ/ቤቶች ጉዳዩን በመጀመሪያ የማየት ሥልጣን አላቸዉ ወይስ የላቸውም? ጉዳዩን
የመወሰን ሥልጣን ያለዉ የትኛው ፍ/ቤት ነው? የሚለው ነጥብም አከራካሪ ሆኖ እስከ
ፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመድረስ በመዝገብ ቁጥር 46220 (ቅጽ 10) ላይ
የከተማ ቦታ ያለአግባብ ተወስዶብኝ በሊዝ ለሌላ ተሰጥቷል በሚል የሚቀርብ አቤቱታ
የቦታውን መውሰድ ውሳኔ ለሰጠው አካል በቅድሚያ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑና በሚሰጠው

ምክንያቱም የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 37(1) በግልጽ ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍ/ቤት ወይም
71

ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው መሆኑን ስለሚደነግግ
እና የከተማ ቦታን ማስለቀቅ እና የካሣ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በሕገ-መንግስቱ አገላለጽ መሠረት በሕግ የዳኝነት ስልጣን
የተሰጠው አካል ስለሆነ በእኔ እምነት በሊዝ የተሰጠው መሬትና በመሬቱ ላይ የሚገኘው ንብረት የተወረሰው ወይም
የተወሰደው ያላግባብ ነው የሚል ክርክር በአዋጅ ቁጥር 455/1997 ለጉባኤው እንዳይቀርብ መደረጉ አግባብ አይደለም፡፡

117
ውሳኔ ቅሬታ ያለው ወገን ለቦታ ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ማቅረብ ያለበት እና ይኸውም
አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆን ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች
1. የገጠር መሬት ወደ ከተማ ከተከለለ በኋላ በመሬቱ ላይ ክርክር ቢነሣ ጉዳዩ በየትኛው

ፍርድ ቤትና በየትኛው የህግ አግባብ ይስተናገዳል? ይህን ጉዳይ በተመለከተ የአማራ ክልል
ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 12322 እና በርካታ ተመሳሳይ ውሳኔዎች
የሚከተለውን ሐተታ አስቀምጧል፡፡

“…ክርክሩ በባህር-ዳር ከተማ ክልል ውስጥ የተጠቃለለን የገጠር መሬት የሚመለከት ነው፡፡ በከተማ
ውስጥ የተጠቃለሉ የዕርሻ መሬት ይዞታዎችን በተመለከተ በአስተዳደራቸው ጉዳይ ላይ የማስተካከያ
ርምጃ ሳይወሰድ በቀድሞው ሁኔታ መተዳደራቸውን በቀጠሉበት ሁኔታ በይዞታወቹ ላይ የሚነሱ
ውዝግቦች ቢኖሩ ጉዳዮቹ ሊስተናገዱ የሚገባው ይህንኑ ለማስተናገድ ሥልጣን በተሰጣቸው የመደበኛ
ፍርድ ቤቶች ነው፡፡ የከተማ-ነክ ፍርድ ቤቶች በከተማ ውስጥ በልዩ የአስተዳደር ሥርዓት የሚተዳደሩ
ቦታዎችን ከማየት በቀር በገጠር የአስተዳደር ሥርዓት የሚመሩ ይዞታዎች ላይ የሚነሱ ውዝግቦችን
ለማስተናገድ ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡…ይህ የሚታለፍ ቢሆን እንኳ የከተማ-ነክ ፍርድ ቤቶች ለክርክሩ
ምክንያት የሆነው ቦታ በባህር-ዳር የከተማ ክልል ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ብቻ በግራ ቀኙ የተነሳውን
ክርክር ለማስተናገድ ሥልጣን ይኖራቸዋል ማለት አይቻልም፡፡ የከተማ-ነክ ፍርድ ቤቶችን ካቋቋመው
አዋጅ መግቢያ ላይ ለመረዳት እንደሚቻለው በመንግሥትና በግለሰቦች መካከል በሚደረገው ክርክር
የተነሳ የከተማ ልማት ፕሮግራሞች እንዳይሰናከሉ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ጉዳዮች በጊዜ ተቋጭተው
መንግስት የልማት ሥራዎችን መሥራት እንዲችል ለማድረግ ነው እንጂ አስተዳደሩን በቀጥታ
በማይመለከቱ በሁለት ግለሰቦች መካከል የሚነሳውን ውዝግብ ሁሉ እንዲያስተናግዱ አይደለም፡፡” በዚህ
ትንታኔ ትስማማላችሁ ወይ?

2. የስረ - ነገር ሥልጣን በተለያዬ ጊዜ በተለያዩ ሕጐች ይሠጣል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ
ከካሣ ከፍያ፣ ከቦታ ማስለቀቅና ከመሳሰሉት አንፃር የስረ - ነገር ስልጣን ከአዋጅ ቁጥር
721/2004 አንፃር የዳኝነት ስልጣን የማን ነው?
3. የከተማው የመሬት ማስለቀቅ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ቦታው ለሕዝብ ጥቅም በሚለቀቅበት
ጊዜ የከተማው አስተዳደር የገንዘብ ካሳ ከፍሎ ምትክ ቦታ ለመሰጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ
የቀረበለትን ይግባኝ ሳይወስን ቢያልፈው በዚህ ነጥብ ይግባኝ ለፍርድ ቤት ማቅረብ
ይቻላል ወይስ አይቻልም? ፍ/ቤቶች የቀረበውን ይግባኝ የማየት ሥልጣን አላቸው ወይስ
የላቸውም?

118
ማጠቃለያ

መሬት በተፈጥሮ የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከመሆኑም በላይ ሌሎች ንበረቶችን ለማፍራት
አስፈላጊ እና መተኪያ የሌለዉ ሀብት መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በአገራችን ታሪክ የመሬት
ባለይዞታነትና ተጠቃሚነት ለማረጋግጥ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከዘውዳዊው ሥረዓት ጋር ከፍተኛ
ትግል በማድርግ የጭሰጫኛና የባላባት ግኑኝነት ለዘለቄታው በማሰቀረት መሬት የመንግስትና
የሕዝብ ሀብት እንዲሆን አድርገዋል፡፡

የደርግ መንግስትም ቢሆን የከተማና የገጠር መሬትን የመንግስት እና የህዝብ ሀብት በማድረግ
ሥር ነቀል እርምጃ በመውሰድ የሰፊውን አርሶ አደርና የከተማ ኗሪ የመሬት ባለይዞታነትና
ተጠቃሚነት ፍትሀዊና ዋስትና ባለው ሁኔታ ለማረጋገጥ የሞከረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ
ውጤታማ ስላልነበር ኢህአዴግም ደርግን ለመጣል እነደመታገያ ከያዛቸው ጥያቄዎች አንዱ
መሬት እና ከመሬት የሚገኙ ውጤቶች ተጠቃሚነት ላይ ነበር፡፡ ከደርግ ወድቅት ቀጥሎ
የተቋቋመው የሸግግር መንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የህዝብና የመንግስት መሆኑ
እንደሚቀጥልና እርሶ አደሮች ዋስተና ያለው የመሬት ይዞታና የመሬት ተጠቃሚነት መብት
የሚኖራቸዉ መሆኑን ግልፅ በማድረግ በአንዳንድ አካባቢዎች ፍትሀዊ የመሬት ድልድል
በማድርግ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሬት የመንግስት አና የህዝብ ሀብት ሆኖ ግለሰቦች የከተማም ሆነ


የገጠር መሬት ባለይዞታና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ህገ መንግሰታዊ ስርዓት የዘረጋ በመሆኑ
የፌደራል እና የክልል መንግስታት በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ሀላፊነት
ለመወጣት የተለያዩ የህግ ማዕቀፎቸን አውጥተዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ የስልጠና ፁሑፍ የገጠር
እና የከተማ መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈፃፀማቸውን ከታሪካዊ ዳራው ጀምረን አሁን
ያለውን ህገመንግስታዊ ይዘት ዳስሰናል፡፡ የገጠር እና የከተማ መሬትን የማግኘት፣ የመጠቀምና
የማስተላለፍ መብቶች፤ መሬትን በመጠቀምና በማስተዳደር ረገድ በባለይዞታዎች እና በመሬት
አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን ወይም በአስተዳደር አካሉ ላይ ስለተጣሉ ግዴታዎችና
ኃላፊነቶች፤ ይዞታን ለሕዝብ አገልግሎት ስለማስለቀቅና ስለካሳ አከፋፈል፤ ይዞታ መብት
መከበር ዋስትና እና ክርክሮች የሚፈቱበትን አግባብ እና የሚታዩትን ችግሮችና መፍትሔዎችን
ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡

119
ሆኖም ህገመንግስቱን ድንጋጌና የህግ ማዕቀፎቹን መሠረታዊ ግብና ዓላማ በመረዳት ህጎቹን
በመተርጎምና በማስፈፀም በኩል የፍትህ አካላት በኩል ቀላል የማይባል የግንዛቤ፣ የክህሎትና
የአመለካከት ችግሮች ምክንያት አርሶ አደሮች የምርት ሥራቸውን በመተው በየደረጃው ባሉ
ፍርድ ቤቶች ጊዜቸውን በሙግት የሚያሳልፉበት ሁኔታ እንዳለ በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች
የሚከፈቱ መዛግብት ብዛት በማየት መረዳት ይቻላል፡፡ ሰለሆነም የመሬት ባለይዞታዎችን
በተለይም የአርሶ አደሩንና የመሬት ባለይዞታ የመሆንና መሬትን የመጠቀም መብት ለማረጋገጥ
የተደነገጉትን የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎችና በፌዴራልና በክልል የህግ ማዕቀፎች መሠረታዊ
ግብና ይዞታ ህጉን በማስፈፀምና በመተርጎም በኩል የሚታዩ ችግሮች፣ የችግሮቹን መንስኤና
ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ በጋራ በመወያየት የጋራ ግንዛቤ
በመያዝ በአመለካከትና በክህሎት ረገድ የሚታዩ ችግሮችን ማስወገድ ይገባል፡፡ ከዚህ አንፃር
የፍትህ አካላት ባለሙያዎችም ህጎቹን በማስፈጸም ረገድ ቀላል የማይባል ሚና ያላቸው
በመሆኑ በገጠርና በከተማ መሬት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ ጽሑፉ የተዘገጀው ለመነሻ
ያክል በመሆኑ ሰልጣኞች የክልላቸውን ህግና ነባራዊ ሁኔታ እነዲሁም የፍርድ ውሳኔዎችን
ግምት ውስጥ በማስገባት ሊወያዩ እና የበለጠ ሊያዳብሩት ይገባል፡፡

120
የስለጠና ፕሮግራም አባሪ
ለስልጠናው የተያዘው 7 ቀን ሲሆን ስልጠናውም በየክልሉ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህን ጽሁፍ
በሰባት ቀን ውስጥ ለመስጠት አሰልጣኞችንም ከዚህ አንጻር ለመምራት የሚከተለው
የአሰልጣኝ መመሪያ አባሪ ቀርቧል፡፡

በፀሐፊው እምነት ክፍል አንድ የአምስት ቀናት ክፍል ሁለት ደግሞ የሁለት ቀናት ስለጠና
ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ክፍል አንድ፡- ምዕራፍ አንድ በአንደ ቀን፣ ምዕራፍ ሁለት በሁለት
ቀናት፣ ምዕራፍ ሶስት፣ ምዕራፍ አራት እና ምዕራፍ አምስት እያንዳንዳቸው በአንድ ቀን
በድምሩ በአምስት ቀናት ስልጠና ይጠናቀቃል፡፡ ክፍል ሁለት፡- ደግሞ ምዕራፍ አንድ
በግማሽ ቀን፣ ምዕራፍ ሁለት በአንድ ቀን አንዲሁም ምዕራፍ ሶስት በግማሽ ቀን በድምሩ
በሁለት ቀናት ይጠናቀቃል፡፡

የስልጠናውን አሰጣጡን በተመለከተ በእያንዳንዱ ቀን ጧት ከ2፡30 እስከ 6፡30 የአሰልጣኙ


ገለፃ፤ ከሰዓት በኃላ ከ8፡00 እስከ 11፡30 የሰልጣኞች የቡድን ውይይት እና በቡድን
በተወያያዩበት ጉዳይ ላይ ከክፍል አሰልጣኞቻቸው ጋር የማጠቃለያ ውይይት ያደርጋሉ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ጧት በቡድን ውይይት ወቅት አለመግባባት የተፈጠረባቸው ነጥቦች ካሉ
አሰልጣኙ የእራሱን ማጠቃለያ ሰጥቶ የእለቱን ገለፃ ይቀጥላል፡፡

121
ማጣቀሻዎች

የገጠር መሬትን የሚመለከቱ ህጎችና አፈጻጸም በፍትህ አካላት ባለሙያዎች ስልጠና ማዕከልለ
ረጅም ጊዜ ስራ ላይ ስልጠና ፕሮግራም የተዘጋጀ (ያልታተመ)

አሊ መሀመድና ማሩ ባዘዘው፤ የመሬት ባለይዞታና ተጠቃሚ የመሆን መብት በኢትዩጵያ፤


ነሐሴ 2002 (ያልታተመ)

ዳንኤል ወልደ ገብርኤል፤ አነጋጋሪው የአዲሱ የሊዝ አዋጅ ይዘትና አንድምታው


www.ethiopianreporter.com 2011
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የ2003 ዓ.ም በጀት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ
የቀረበ ጥናት፣ ጥቅምት 2004 ዓ.ም
ገብሩ ዘነበ እና ብርሃኔ አሰፋ፣ የንብረት ህግና ሕገ-መንግስቱ፣ ለወረዳ ዳኞችና አቃቤያነ ሕግ
የቅድመ ስራ ስልጠና የተዘጋጀ (2001 ዓ.ም፣ ያልታተመ)
ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል ስለ ኢትዮጵያ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ግብር ጠቅላላ አስተያየት
(1970፣ ያልታተመ)

Molla Mengsitu, the Ethiopian Urban Landholding System: An Assessment of the Governing
Legal Regime in Muradu Abdu eds. Land Law and Policy in Ethiopia since 1991: Continuities
and Challenges, Ethiopian Business Law Series, (AAU 2009)
Daniel W/gebriel Compensation during Expropriation in Muradu Abdu eds. above
Kenneth H. Parsons, Land Tenure, the University of Wisconsin press, Wisconsin (1963)
Aberra Jembere, Legal History of Ethiopia 1434-1974: Some Aspects of Substantive and
Procedural law,

Richarel David Green Field, Ethiopia, A New Political History, Pallmale press, London (1965)
John Man Kakis etal(ed), Ethiopian: Anatomy of Tradational Polity, Oxford University Press,
Addis Ababa (1974)

Desallgn Rahmatto, Agrainan Reform in Ethiopia, Scandinavian Institute of African Studies,


Uppsala (1984)

122
ህጐች

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት፤አዋጅ ቁጥር 1/1987

የከተማ ቦታ እና ትርፍ ቤትን የመንግስት ንብረት ለማድረግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 47/1967

የገጠርን መሬት የህዝብ ሀብት ለማድረግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 31/1967

የኢፌዴሪ የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝን እንደገና ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 272/1992

የኢፌዴሪ የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣ፤ አዋጅ ቁጥር 721/2004

የኢፌዴሪ የገጠር መሬት አሰተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር456/1997

የኢፌዴሪ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን


ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 455/1997

የተሻሻለዉ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት
አሰተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 110/1999

የተሻሻለዉ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ቁጥር130/ 2000

የተሻሻለዉ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አሰተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ቁጥር133 /1998 እና አዋጅ ቁጥር148/99 እና ማስፈፀሚያ ደንቡ ቁጥር 51/1999

የተሻሻለዉ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አሰተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ቁጥር136/ 2000

የቤንሻንጕል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
ቁጥር 85 /2002

123

You might also like