Professional Documents
Culture Documents
21
21
21
የስምምነት ውል፣
ስምምነት የተደረገበት ቦታ፡-በማህበሩ ጽ/ቤት
የስብበሳው ቀን፡-መጋቢት 8 ቀን 2015 ዓ.ም
የስብሰባው ሰዓት፡-ከ4:00 እስከ 6:00 ሰአት
በስምምነቱ ላይ የተገኙ ባለ አክሲዮኖች ፦
1/ አቶ ነብዩ ገ/ክርስቶስ ገ/ማሪያም
2/ አቶ ይስማ አስራት ለገሰ
3/ አቶ ገ/ወልድ ዘመቻ ሱፉ
4/ አቶ መሐመድ ሁሴን ሟርሼ
5/ አቶ ተባረክ የሱፍ አህመድ
6/ ወ/ሮ ፀሀይነሽ ይማም የሱፍ
7/ ወ/ሮ አረጋሽ ሙሴ ጎጆ
8/ አቶ አ/መኑር ሁሴን ሟርሼ
9/ አቶ ቦጋለ ብሩ አገዘ
10/ አቶ አማኑኤል ቶሎሳ ጨዋቃ
11/ አቶ ዳውድ ሁሴን ሟርሼ
የስብሰባው አጀንዳ፡-ስምምነትን በተመለከተ ፦
እኛ በስብሰባው ላይ የተገኘነው የማህበሩ አባላት በፍ/ሕ/ ቁጥር 1731/1679/2005/2266 መሠረት እና
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 274 እና በተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ከዚህ በታች በዝርዝር በተጠቀሱት ጉዳዮች
ላይ ወደንና ፈቅደን የስምምነት ዉሉ ተዋውለናል ፡፡
እኛ ተስማሚዎች ቀደም ሲል ከሳሽና ተከሳሽ ሆነን በማህበሩ አጠቃላይ የስራ ሁኔታ ላይ ክስ ተመስርቶ
ከስር ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 134461 የካቲት 14 ቀን 2008ዓ /ም በተሠጠው
ውሣኔ ፣ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 160248 በቀን 17/4/2010 በሠጠው
ውሣኔ ፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 212204 በቀን 03/09/2010 ዓ/ም በሰጠው
ውሣኔ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 164008 ጥር 13/2012 ዓ/ም
በሠጠው ውሳኔ መነሻነት የቀድሞ ከሳሾች የቦሌ አየር አንባ ነጋዴዎች አንድነት ኃ/የተ/ የግል ማህበር አባላት
ናቸው ብሎ የወሰኑ ስለሆነ በእነዚህ ውሳኔዎች መሰረት ለመፈፀም እና የማህበሩ አባላት ብዛትና የአክሲዮን
ድርሻ መጠን ወደ ነበረበት ለመመለስ የማህበሩ አባላቶች በሙሉ ሰፊ ውይይት ካደረግን በኋላ ስለ አፈፃፀሙ
ከፍርድ ቤት ውጪ በስምምነት የጨረስን ሲሆን የስምምነታችን ዝርዝር ውሳኔዎች ከዚህ በታች አቅርበና ፦
1ኛ/ ከላይ ስማችን የተገለፀው አባላት በማህበሩ ውስጥ ያለን የአክሲዮን ድርሻ መጠን እኩል መሆኑ
የተስማማን ሲሆን በስምምነቱ መሰረት ከአሁን በፊት በሚያዚያ 15 /2010 ዓ/ም በሰባቱ አባላት ስም
የፀደቀው የማሻሻያ ቃለ ጉባኤ በአዲስ መልክ ተሻሽሎ እንዲፀድቅ እና በመጀመሪያው ቃለ ጉባኤ የተገለፁት
የአባላት ብዛት እንዲስተካከል እና ወደ ነበረበት እንዲመለስና እንዲሁም በሰባቱ አባላት ስም የፀደቀው
የካፒታል መጠን ከላይ ከ1- 11 የተገለፁት የማህበሩ አባላት እኩል ድርሻ እንዲሆንና ተስተካክሎ እንዲፀድቅ
በማለት በሙሉ ድምፅ ተስማምተናል ። በስምምነቱ መሠረትም የማህበሩ የአንድ አክሲዮን ዋና ብር 1000
/አንድ ሺህ ብር/ እንዲሆን እና የእያንዳንዱ አባላት የአክሲዮን ድርሻ መጠን 1916 /አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ
አስራ ስድስት/ ሆኖ በስማችን እንዲመዘገብና የማህበሩ አባላት የአክሲዮን ድርሻ ወደ ነበረበት ተስተካክሎ
እንዲፀድቅ በማለት በሙሉ ድምፅ ተስማምተናል ፡፡ በተጨማሪም በስምምነታችን መሰረት አዲሱ የማህበሩ
አባላት የአክሲዮን ድርሻ ድልድል በአዲስ ቃለ ጉባኤ ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው መስሪያ ቤት አቅርበን
ለማፅደቅ ተስማምተናል ። በመጨረሻም በዚህ ስምምነት መሰረት አዲሱ የማህበሩ አባላት ብዛት እና
የአክሲዮን ድርሻ ድልድል ከዚህ እንደ ሚከተለው ተስተካክለዋል ።
ተ.ቁ የባለአክሲዮኖች ስም የአክሲዮን የአንዱ አክሲዮን ጠቅላላ ዋጋ
ብዛት ዋጋ