Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የአየር ንብረት ለውጥ

የአየር ንብረት ለውጥ ጠቆሚዎች የሙቀት መጠን መጨመር የዝናብ እጥረት፣ ድርቅን፣ የሰብል
አለማፍራትንና ረሀብን ያጠቃልላል የስው ልጅ የተፈጥሮ ሚዛንን በማዛባቱ የተነሳ እፅዋትና የዱር እንሰሳት
ከአካባቢያቸው ጋር ያላቸው ቁርኝት ተቆርጧል ይህም በአለማችን የሙቀት መጠን መጨመር የጎርፍ
መጥለቅለቅ የበረዶ መቅለጥ አውሎነፋስቨ መከሰት እለታዊ ችግሮች እንዲሆኑ ያደርጋል | ይህ የአየር ንብረት
ለውጥ የተለያዩ ዕፅዋትና የዱር እንሰሳት መላመድ ስላልቻሉ ከአካባቢው ይሰደዳሉ ፡፡

ለአደጋ የተጋለጡ የዱር እንሰሳት


የተፈጥሮ ሚዛን ሲዛባ እፅዋትና እንሰሳት ላይ አደጋ ይከሰታል በምስራቅ አፍሪካ ለአደጋ የተጋለጡ የዱር
እንሰሳት ዝሆን፣ጎሪላ፣አቦሸማኔ፣ነብር፣የመሳሰሉት ናቸው

የአለም አቀፍ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ድርጅት


የአለም አቀፍ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ድርጅት (አዱጥድ)ከዱር እንሰሳት ጥበቃ ድርጅት አንዱ ነው፡፡ይህ ድርጅት
የየሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ድርጅት ነው ፡፡በነዚህ ቢሮዎች ስር በመመራት ላይ ያሉት የእንክብካቤ
ፕሮጀክቶች ከ 100 የሚበልጡ ሀገሮች ስር የነቃ ተሳትፎ ያደርጋሉ ፡፡

የሰዎች በተፈጥሮ አካባቢ ጣልቃ ገብነት መንስኤውና ውጤቶች


በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት ተጨማሪ የሬት ፍላጎት እንዲኖር ምክንያት ሆኗል
፡፡በዚህ የተነሳ ሰዎቸች ወደ ጥብቅ አካባቢዎች በመግባት የደን ሽፋን እንዲመናመን ያደርጋል ማነንኛውም
አግባብ የሌለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም በረዥም ጊዜ ውስጥ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ ያስከትላል ሰዎች
ቤት ለመስራት የቤት ቁሳቁስ ለመስራት እንዲሁም ምግባቸውን ለማብሰል የደን ዛፎችን ይቆርጣሉ ዛፎችን
መቁረጥ የአካባቢ ስነ̄̄ ̄ምህዳርን ይጎዳል ፡፡

የአፈርና የውሀ ሀብትን የመንከባከብ ዘዴዎች


የአፈር ሀብት አጠባበቅ ዘዴዎች ፡አፈር በጥንቃቄ ካልተያዘ ወደ ጠፍነት ይቀየራል
ምርታማነቱም ይቀንሳል ስለዚህ አፈር ለምነትን ለመጠበቅ ተፈጥሮአዊ ዘዴዎችን ተጠቅመን መጠበቅ
ያስፈልጋል ፡፡

ዳግም ድነና ፡-ቀደም ሲል በደን ተሽፍኖ የተራቆተ መሬትን እንደገና መልሶ በደን መሽፈን ማለት ነው ፡፡

ድነና ፡- ድነና ዛፍ ባልነበረበት መሬት ወይም ቦታ ይ የዛፍ ችግኞችን መትከል ማለት ነው ፡፡

ጣምራ እርሻ ፡- ገበሬዎች ከእርሻና ከብት ከማርባት እርባታ ጎን ለጎን ዛፎችን መትከል በርካታ ጥቅም አሉት
አህዱ ጥቅም ገቢን ማሳን ነው ፡፡ ሌላው ደግሞ የአካባቢን ሚዛን መጠበቅ ነው፡፡
የእርከን ሥራ ፡- አፈርን ለመንከባከብ ጥቅም ላይ ከሚውሉ ዘዴዎች አንዱ ነው ፡፡እያንዳንዱ መደብ መስል ሆኖ
በከፍተኛ ስፍራ ጎኖች ላይ የሚሰራና በዝናብ ወቅት አፈር በጎርፍ እንዳይጠረግ ይረዳል፡

በከፍተኛ ስፍራ አግድም ማረስ ፡-በከፍተኛ ስፍራ አቀበት ላይ የእርሻ ተግባር ሲካሄድ የሚፈጠሩ መስመሮች ከላይ በዚናብ
ወቅት እያሽቆለቆለ የሚወርድ ጎርፍ ይቀንሳሉ ውሀም ቀስበቀስ ወደ መሬት እንዲሰርግ ያደርጋል፡፡

ጥቅሞች ፡- የአፈር መላትን ይከላከላል ፡፡

የአፈር ለምነትን ይጠብቃል ፡፡

ሰብል አትፊ ነፍሳትን ይቀንሳል፡፡

በኬሚካል ማዳበርያ መጠቀም ይቀንሳል ፡፡

አረም ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡

ሰውሰራሽ ማዳበሪያ አለአግባብ መጠቀም


የአንድን አፈር ለምነትና ምርታማነት ለማሻሻል ሲባል ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎችን ያለአግባብ መጠቀም
የአካባቢብን ይልቅ የተፈጥሮ ማዳበሪያ የምንላቸውን እንደ ፍግና ብስባሽ የመሳሰሉትን ወደ አፈር ውስጥ
የሚገባውን የኬሚካል መጠን ስለሚቀንስ የአፈር ለምነትን ይጨምራል፡፡

የውሀ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም


ውሀ ማቆር ፡- በተለያዩ መንገዶች ውሀን መሰብሰብ ማለት ሲሆን ከነዚ ዘዴዎች መካከል

የዝናብ ውሀን ማቆር ፡፡

ከከርሰምድር የሚገኝ ውሀን ማጠራቀም፡፡

የዝናብ ውሀን ማከማቸት፡፡

ብክለትን መከላከል
ብክለት በአየርና በውሀ አማካኝነት ይከሰታል ፡፡ከኢንደስትሪ የሚወጡ በካይ ነገሮች በተሸነቆሩ ወይም ክፍት
በተተዉ ቧንቧዎች ወይም መሬት ዉስጥ ከተቀበሩ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ቀስበቀስ በመጣተ ከወራጅ ዉሀ
ጋር ይደባለቃሉ፡፡

ከፋብሪካ የሚዎጡ በካይ ነገሮች ወደ ጅረቶች በመፍሰስ የዱር እንስሳትም ሆነ የቤት እንስሳት ሲጠጡት
ሊጎዳቸዉ ይችላል፡፡ሰዎች ላይም ጉዳት ያስከትላል፡፡

ዉሃን ማጣራት፡-በተለያዩ ቆሻሻ ነገሮች ምክንያት ለመጠጥ አገልግሎት የማይዉል ዉሀን ለመጠጥ ምቹ
ማድረግ ዉሃን ማጣራት ይባላል፡፡የተለያዩ ኬሚካሎች እና ቆሻሻዎች የተደባለቁበት ዉሃ ለጤና አደገኛ ነዉ፡፡
እነዚህን ኬሚካሎች ከዉሃ ለመለየት የሚጨመሩ የፋብሪካ ዉጤቶች አሉ፡፡ለምሳሌ፡-ክሎሪን የተባለ ንጥረ-ነገር
ለመጠጥ አገልግሎት የሚዉል ዉሃን ያጣራ፡፡

የአየር በካዮች ፡-አብዛኛው የአየር ብክለት የሚመጣው ከሰዎች ተግባራት ነው ለምሳሌ ፡-የተፈጥሮ ዘይት
ወይም የድነንጋይ ከሰል ሲቃጠል እነዚ ሀይል አመንጭ ነገሮች በኢንድስትሪ የማምረቻ መሳሪያዎች በተጓዥ
መኪኖች ስራላይ ሲውሉ ይቃጠላሉ ፡፡ የአየር ድንበር የለውም ፡፡ስለዚህ በአንድ አካባቢ የተበከለ አየር
በሌላ አካባቢ በመዘዋወር ጉዳት ያደርሳል፡፡

ብክለትን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ደኖችን መንከባከብ የድነና ዳግም ድነና ስራ መስራት ታዳሽ ሀይሎችን
በሀይል ምንጭነት መጠቀምና ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም ይኖርብናል፡፡

የኢ\ያ የምስራቅ አፍሪካ ብሔራዊ ፓርኮች ጠሜታ


የኢ\ያ ብሔራዊ ፓርኮች
ብሔራዊ ፓርኮች በአንድ ሀገር የሚገኙ ልዩ የሕዝብ የመሬት ይዞታዎች ወይም የዉሐ አካላት ናቸዉ፡፡
ስፍራዎች ስነ-ምህዳር

የእፅዋት የእንስሳት ዝርያ ዉበየመሬት ገፅታዎችን የስነ-ምህዳር ሂደት ዉጤቶችን ወይም ታሪካዊ የቅሪት አካል
መገኛ አካባቢዎችን የሚያጠቃልሉ ለይተዉ እንዲጠበቁ የተከለሉ ቦታዎች ናቸዉ፡፡

ኢ/ያ ዉስጥ የሚገኙብ ብሔራዊ ፓርኮች

1. ሰሜን ተራሮች
2. አብያታ ሻላ ሐይቆች
3. አዋሽ
4. ባሌ ተራሮች
5. ጋምቤላ
6. ሚጎ
7. ነጭ ሳር
8. ኦሞ
9. ያንጉ ዲራሳ

ሀ .አብጃታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ

የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች አካባቢ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በ 200 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡የፓርኩ
ስፋት 482 ካ.ሜ በፓርኩ ዉስጥ 31 የአጥቢ እንስሳት ዝርያ ይገኛሉ፡፡እነዚህ አጥቢ እንስሳት የሚያጠቃልሏቸዉ
፡- የቆላ አጋዘን፡ የሜዳ ፍየል፡ ዝንጀሮ፡ ጦጣ፡ ጉሬዛ ፡ቀበሮ ናቸዉ፡፡በረካታ አእዋፎች ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ መካከል አምስቱ በኢ/ያ ብቻ የሚገኙ ናቸዉ፡፡

ለ .አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፡-ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 225 ኪ›ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ስፋቱ 756 ካ ›ኪ ›ሜ
ነው ሳላ፣የቆላአጋዘን፣አምባራይሌ፣ የሜዳ ፍየል፣ቆርኪ ፣አንበሳና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ፡-በደቡብ ምስራቅ ከአዲስ አበባ 400 ኪ‹ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ፓርኩ
የተቋቋመው ኒያላ ወይም የደጋ አጋዘንና ቀይቀበሮ የተባለ ብርቅየ የዱር እንሰሳትን ከአደጋ ለመከላከል ታስቦ
ነበር ፡፡በዚፓርክ በኢ\ያ ብቻ የሚገኙ 11 የዱር እንሰሳት መኖራቸው ይታወቃል ፡፡ዱኩላ፣በኸር፣
ሚዳቆ፣ከርከሮ፣አገር፣ጉሬዛ፣ ፍልፈል፣ተኩላ፣አሳማ፣የዱርአሳማ ፣አንበሳ፣ዝንጀሮ፣16 በፓርኩ ብቻ የሚገኙ
ብርቅዩ አእዋፍ ይገኛሉ፡፡

የእንሰሳት መጠበቅያና መከላከያ ስፍራ፡-እንሰሳት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የሚጠበቁበት ቦታ ነው፡፡

ሀ‹ የባሌ ዝሆን መጠበቂያ ፡-ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 570 ኪ›ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ስፋት 6982 ካ› ኪ ›ሜ

ለ›ሠንቀሌ ቆርኪ መጠበቂያ መከለያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 320 ኪ ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ስፋት 54 ካ›ኪ
›ሜ

ሐ›ያቤሎ መጠበቂያና መከላኬያ ፡- ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 550 ኪ ሜ ርቀት ላይ ወደ ሞያሌ በሚወስደው
መንገድ ላይ ይገኛል ፡፡ስፋት 2496 ካ ኪ ሜ ነው ፡፡

You might also like