Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 27

ጥናትና ምርምር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


ክፍል አንድ
1.1 መግቢያ

በመግቢያ ውስጥ የጥናት(የምርምር) ትምህርትን አስፈላጊነትና ዓላማውን እንዳስሳለን፡፡

1.1.1 የጥናት ትምህርት አስፈላጊነት


በቤተ-ክርስቲያናችን ውስጥ ስራውንና የስራውን ባለቤት በግልፅ ባለማወቃችን ጥናታዊ ፅሁፎች በብዛት ሲሰሩ አይታዩም፡፡ ለዚህም ችግር
እንደምክንያት የሚጠቀሱት፡-
ሀ) ጥናትን የተወሰኑ ሰዎች ስራ በቻ አድርጎመውሰድ
ለ) በቤተክርስቲያን ዙሪያ የጥናትን አስፈላጊነት አለመረዳት
ሐ) የምርምር ስራ ከየት ተነስቶ የት እንደሚድርስ አለማወቅ
መ) አጠቃላይ በሀገራችን የጥናት ስራ ባህል አነስተኛ መሆኑ ዋናዋና ችግሮች ናቸው፡፡
ከላይ የተገለፁት ዋናዋና ችግሮች ለመቅረፍም በየሰንበት ት/ቤቶች የጥናታዊ ፅሁፍ ስራን ለማጠናከር የጥናታዊ ትምህርት መሰጠቱ
አስፈላጉ ሆኗል፡፡

1.1.2 የጥናት ትምህርት ዓላማ


 ስለጥናት ምንነት፤ጠቀሜታውን እና ባህርያቱን ማስረዳት
 በጥናት ሊፈቱ የሚችሉ የቤተክርስቲያን ችግሮችን በዘመናዊ የጥናት ዘዴ ዕገዛ ማድረግ
 በሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች የሚዘጋጁ ጥናታዊ ስራዎችን ተጨባጭና ዘመናዊ በሆነ የጥናት ስራ መደገፍ
 በቤተክርስቲያን የሚጠኑ ጥናቶች ወጥነት እንዲኖራቸው ማድረግና ተማሪዎች አንድ ጥናት ለማጥናት ማካተት የሚገባውን
መሰረታዊ ይዘቶች በያዙ መልኩ እንዲዘጋጁ ማድርግ

1.2 የጥናት ትርጉምና ባህርያት


1.2.1 የጥናት ትርጉም
ጥናት ማለት አንድን የታወቀም ሆነ ያልታወቀ ችግር አጥንቶ መፍትሄውን ለማግኘት ሳይንሳዊ ዘዴዎችንና ልዩልዩ ቅድመ ተከተሎችን
ተጠቅሞ በትዕግስት የሚሰራ ተግባር ነው፡፡

1.2.2 የጥናት ባህርያት

 የጥናት መሰረታዊ ባህርያት የሆኑት፡-


 ጥናት ለአንድ ችግር መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ተግባር ነው፡፡
 ጥናት የሚካሄደው ችግር ሲኖር ብቻ ነው፡፡
 ጥናት በሚታዩና በሚጨበጡ ነገሮች የሚመሰረት ተግባር ነው፡፡
 ጥናት ለማድረግ መረጃ አስፈላጊ ነው፡፡
 ጥናት ከመጀመሪያና ከሁለተኛ ደረጃ ምንጮች መረጃዎችን የመሰብሰብ፤ የመተንተንና የማጠናቀር ሂደት ነው፡፡
 ጥናት የተለየ ዕውቀት የሚጠይቅ ስራ ነው፡፡
1.3 የጥናት ጥቅም
ጥናት በቤተክርስቲያን ዙሪያ ማድረግ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥቅሞች ያስገኛል፡፡
 ቤተክርስቲያንን ያስተዋውቃል
 ቤተክርስቲያን ገቢ እንድታገኝ ያደርጋል
 ለመናፍቃን መልስ ለመስጠት ይረዳል
 በቤተክርስቲያናችን ለሚገኙ ችግሮች መፍትሄ በመዘጋጀት ችግሮች እንዲቀረፉ ይረዳል፡፡
1
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 ለቤተክርስቲያን ኩራት ለአጥኚዎች ደግሞ በረከት ያስገኛል፡፡

1.4 የጥናት ርዕሶ ችምንጭ


በቤተክርስቲያን ዙሪያ ለሚጠኑ ጥናቶች የሚሆኑ ርዕሶችን የምናገኘው ከምናየውና ከምንሰማው ከምናነበው ነገረ-ቤተክርስቲያን ሲሆኑ
የሚከተሉት ጉዳዮችም ለጥናቶች የአርዕስት ምንጮች ይሆናሉ፡፡

 በሰንበት ት/ቤት ዙሪያ ከሚታዩ ችግሮች


 በቤተክርስቲያን ዙሪያ ከሚታዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች
 በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ዙሪያ ከሚታዩ ችግሮች
 በህይወታችን ዙሪያ ከሚከሰቱ ችግሮች
 በሀገር-አቀፍ ደረጃና በዐለም-አቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ለጥናት የሚሆን ርዕስ
ሊመነጭ ይችላል፡፡

1.5 ከአንድ አጥኚ ምን ይጠበቃል?

ለአንድ አጥኚ(ተመራማሪ) የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝ ናቸው፡፡


ሀ) የንባብ ልምድ
በየትኛውም የጥናት ዘርፍ ጥናት የሚያጠና ሰው ብዙ ማንበብ ይጠበቅበታል፡፡
 በሚያጠናው ርዕስ ዙሪያ ምን እንደ ተሰራ ለማወቅ
 የምርምሩን የትኩረት አቅጣጫ ለመወሰን
 በየወቅቱ ያሉትን ክስተቶች ለመረዳት
 በቤተክርስቲያን ዙሪያ ለተወረወሩ የቃላት ድንጋዮች መልስ ለመስጠት ያስችው ዘንድ ለአንድ አጥኚ ሰው በመንፈሳዊም
በዓለማዊም ዙሪያ የተፃፉ መፅሐፍትን፤ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን ማንበብ ግድ ይላል፡፡
ለ) ንቃት
ቤተክርስቲያን ከዘመኑ ጋር እንዴት መራመድ እንዳለባት ለመግለፅ አካባቢያችንን ሁልጊዜ በንቃትና በማስተዋል መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡

ሐ) ትዕግስት
ጥናት ከብዙ ሰዎች ጋር የሚያገናኝ ስራ ነው፡፡ ስለሆነም በተገቢው መልኩ ትዕግስትን ገንዘብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

መ) ወኔ
አንድን ሰው በአንድ ነገር ላይ በባለቤትነት እንዲጨነቅ ለማድረግና መፍትሄም ለማምጣት እንዲረዳው ብርቱ ወኔ ወይም ተቆርቋሪነት
(ተነሳሽነት) ሲኖረው ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ያሉ አጠቃላይ የችግሮችዋን መንስዔዎች ስንመለከት ወኔ ከማጣት ወይም ተቆርቋሪ ካለመሆን
የሚመነጩ ናቸው፡፡

1.6 የጥናት ዓይነቶች

በርካታ የጥናት ዓይነቶች ቢኖሩም ለሰንበት ት/ቤታችን የትምህርት አገልግሎት የሚከተሉትን ብቻ አንመለከታለን፡፡

1.6.1. ታሪካዊ ጥናት(ምርምር) (Historical Research)

- ታሪካዊ (ጥናት) ምርምር ያለፈን ታሪክ በተመለከተ ምዝገባ፤ክትትልና ትንተና የሚከናውንበት የጥናት ዓይነት ነው፡፡
- ታሪካዊ የሚያሰኘው ባለፈ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ክትትልና ትንተና ስለሚያደርግ ነው፡፡
-ይህ ዓይነቱ ጥናት ተጨባጭ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ መረጃዎችን በጥንቃቄ መሰብሰብና መተንተን የሚተኮርበት ጉዳይ ነው፡፡

2
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
1.6.2 ገላጭ ጥናት(ምርምር) (Descriptive Research)

- ምን? ምንድን ነው? እያለ ለማብራራት ይሞክራል::


- ገለፃን፤ትንታኔንና አተረጓጐምን መሠረት የሚያደርግ ነው::
- በሁለት ተለዋዋጭ ነገሮች መካከል የሚኖረውን ተዛምዶ እያወዳደረና እያነጻጸረ ለመመልከት ይችላል::
- ትኩረቱ ግን አንዱን ተጨባጭ ሁኔታ ትክክለኛ ባህርይ መግለጽ ዌም ማሳወቅ ይሆናል::

1.6.3 ቅኝታዊ ጥናት(ምርምር) (Surveying Research)


- ትኩረቱ በተወሰኑ ቡድኖች በሚኖራቸው አመለካከት፤ አስተያትና ባህርይ ላይ ይሆናል፡፡
- ሠፊ ሽፋን ሊያካልል ሚችል የምርምር ዓይነት ነው፡፡
- አብዛኛውን ጊዜ መጠይቅን ተግባር ላይ ይውላል፡፡
- ቅኝታዊ ምርምር በጥንቃቄ ከተያዘ በርካታ መረጃዎችን ማሰባሰብ እንደሚያስችል ይታመናል፡፡

1.6.4 ተግባራዊ ጥናት ምርምር (Action Research)


- ይህ ጥናት በአንደ የተወሰነ ሁኔታ ችግር ላይ ያተኩራል፡፡
- ወዲያው ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል የምርምር ዓይነት ነው፡፡
- የተነሳበት የጥናቱ ዓላማ በአንድ የተወሰነ ችግር ላይ ስለሚሆን ግኝቱምየሚመዘነው እዚያው ችግሩ ባለበት አካባቢ በሚኖረው ተግባር
ይሆናል እንጂ ሁለንተናዊ ተግባራዊነት የለውም፡፡
- ተግባራዊ ምርምር በአብዛኛው በትምህርታዊ አውድ ውስጥ የሚከወን የጥናት ዓይነት ነው፡፡

1.6.5 የሙከራ ምርምር(ጥናት) (Experimental Research)


- የሚለዋወጡ ነገሮችን በጥንቃቄ መቆጣጠር ሲቻል ሊፈጠር የሚችለውን ሁኔታ ለመዳሰስ የሚሞክር የምርምር ዓነት ነው፡፡
- የዚህ ምርምር(ጥናት) ዋናው ትኩረት ተለዋዋጭ(የሚለዋወጡ) ነገሮች በሚኖራቸው የእርስ በእርስ ግኑኝነት ላይ ያተኩራል፡፡

1.6.6 ውሱን ጥናት (Case Study)


- ይህ ጥናት የሚያተኩረው በአንድ በተወሰነ ተቋም፤ በአንድ በተወሰነ ግለሰብ ወይም ጥቂት ግለሰቦች ላይ ነው::
- ይህ ጥናት በአብዛኛው ተራዝሞ የሚቀጥል ጥናት ነው፡፡

3
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
ክፍል ሁለት

2. የጥናት(የምርምር) ዕቅድ ቅደም ተከተል


2.1 የጥናት (የምርምር) ርዕስ መምረጥ

 ርዕስ ለአንድ ለሚጠና ጥናት አጠቃላይ ሥራውን የሚወክል ስያሜ ነው፡፡


 ርዕስ ተመራማሪው (አጥኚው) በአዕምሮው ያሰበውን ችግር በጥናት ለመፍታት የሚያስቀምጠው የመጀመሪያ ሥራ ነው፡፡
 ለጥናት (ለምርምር) የሚሆኑ ርዕስን ለመምረጥ፡-
ሀ. ርዕሱ ለሚሠራው ሥራ የሚስማማ መሆን አለበት፡፡
ለ. ርዕሱ ግልፅ የማያሻማ መሆን አለበት፡፡ (ማለትም በጥናቱ ሊካተቱ የታሰቡትን ነገሮች የሚገልፅ ከቃላት እስከ ግድፈት
የሌለበት መሆን አለበት፡፡)
ሐ. ርዕሱ የአጥኚውን ዕውቀት ፣የጊዜ ሁኔታና የገንዘብ አቅም ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡
መ. ርዕሱ ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ ችግር ዙሪያ ያልተጠና መሆን መረጋገጥ አለበት፡፡
ሠ. የጥናቱ ርዕስ ከጥናቱ (ከምርምሩ) ዓላማ ፣ አስፈላጊነት ፣አጠናን ዘዴ ፣ መዋዕለ ንዋይና የሰው ኃይል ጋር የተጣጣመ መሆን
አለበት፡፡

2.2. የጥናት መነሻ (ዕቅድ) ቅደም ተከተላዊ አዘገጃጀት


 አንድ አጥኚ ርዕሱን ከመረጠ በኋላ የጥናቱን መነሻ ሀሳብ (Research Proposal) ያዘጋጃል፡፡
 ይህም የጥናት መነሻ ሀሳብ ለአጥኚው፣ ለአስጠኚውና ለአማካሪው በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

ሀ. ለአጥኚው (ለተመራማሪው) የሚሰጠው ፋይዳ (ጥቅም)


 የሚያጠናውን ነገር በግልፅ እንዲያውቅ ያደርገዋል::
 በጥናቱ ጊዜ ሊያጋጥሙት የሚችሉትን ችግሮች በግልፅ እንዲያይ ይረዳዋል፡፡
 ዕቅዱ (የመነሻ ሀሳቡ) ተቀባይነት ካገኘ የጥናቱ መነሻ ሀሳብ እንደመመሪያ ያገለግለዋል፡፡
 የጊዜ፣ የገንዘብና የሰው ኃይል በጀትን በዕቅዱ መሠረት እንዲጠቅም ይረዳዋል፡፡

ለ. ለአስጠኚው (ለባለቤቱ) የሚሰጠው ጥቅም


 የሚያስጠናው ነገር ለተቋሙ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ በግልፁ እንዲረዳ ያደርገዋል፡፡
 የጥናቱን ዓላማ በግልፅ ያስረዳዋል፡፡
 ከአጥኚው ጋር በውይይት ለሚወሰኑ ዉሳኔዎች ይረዳዋል፡፡
 በጥናቱ መነሻ ሀሳብ ውስጥ የጥናቱን ዳራ፣ የችግሩን ትንተታኔ፣ የጥናቱን ዓላማ፣ የጥናቱን አስፈላጊነት፣
የጥናቱ ዘዴና ሌሎች በግልፅ መቀመጣቸውን ያሳየዋል፡፡

ሐ. ለአማካሪው የሚሰጠው ጥቅም


 ሥራውን ከመጀመሪያ ጀምሮ በግልፅ እንዲያውቀው ይረዳዋል፡፡
 ለጥናቱ የዕውቀቱን አስተያየት እንዲሰጥ ይረዳዋል፡፡
 አጥኚው በመነሻ ሀሳቡ (በዕቅዱ) ሁኔታ መሄዱን እንዲቆጣጠር ይረዳዋል፡፡
2.2.1. ምሥጋና
 ምሥጋና የጥናቱ ጽሑፍ ከግብ እንዲደርስ በገንዘብ፣ በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ መረጃ በመስጠትና ረቂቁን አንብቦ በማረም፣
ዕርዳታና ትብብር ወይም ዕገዛ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት አጥኚው ሰው ምሥጋና የሚያቀርብበት ክፍል ነው፡፡
 ምሥጋና በአንድ ገፅ ላይ ገባ ብሎ ይገለፃል፡፡
 ገፁም እንደ ሮማን አሃዝ ወይም በአማርኛ ፊደል ባለ ይገለፃል፡፡(ምሳሌ፡- I ወይም ሀ)::

4
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

2.2.2. መክሰተ አርዕስት (Content)


 መከሰተ አርዕስት ማለት ማውጫ ማለት ነው፡፡ ይህም ማውጫም አጠቃላይ የጥናቱን ይዘት በርዕሳቸውና በገፃቸው
የሚጠቀስበት ነው፡፡
 አዘገጃጀቱም አበይት ምዕራፎችን፣ ክፍሎችንና ንዑስ ክፍሎችን የአቀማመጣቸውን ሥርዓት ተጠብቆ የሚገለፅበት ክፍል
ነው፡፡
 የገፁ ቁጥርም የሚገለፀው (የሚቀመጠው) በሮማን አሃዝ ወይም በአማርኛ ፊደል ነው፡፡(ለምሳሌ፡- II ወይም ለ)::
2.2.3. የሰንጠረዥ ማውጫ
 በጥናቱ ውስጥ የሚገኙ ሠንጠረዦችን ርዕሳቸውንና ገፃቸውን የምንሰራበት ክፍል ነው፡፡
 የዚህም ገፅ ቁጥር የሚሰጠው በሮማን አሃዝ ወይም በአማርኛ ፊደል ነው፡፡(ለምሳሌ፡- III ወይም ሐ)::
2.2.4. ምህፃረ ቃላት(Abrevations)
 በጥናቱ ውስጥ የሚገኙትን በምህፃረ የተጠቀምንባቸውን ቃላቶች ፍቻቸውን የምንገልፅበት ክፍል ነው፡፡
 የዚህም የገፅ ቁጥሩ የሚሰጠው በሮማን አሃዝ ወይም በአማርኛ ፊደል ነው፡፡(ለምሳሌ፡- IV ወይም መ)::

2.2.5. የጥናቱ ዳራ(Background Of The Study)


 ዳራ ማለት ጥናቱ የሚያተኩርበትን መሠረታዊ ጉዳይና ጥናቱ እንዲጠና ያነሳሳው ጉዳይ ምን እንደሆነ በአጭሩ ተብራርቶ
የሚቀርብበት ክፍል ነው፡፡
 የጥናቱን ዳራ ለመፃፍም በርዕሱ ዙሪያ ብዙ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡
 መጠኑ አጠር ብሎ በአንቀጽ በመከፋፈል ይቀመጣል፡፡
 ማንኛውንም ሰው አንቦቦ እንዲረዳው ግልፅ መሆን አለበት፡፡

2.2.6. የችግሩ ትንታኔ (Statement Of The Problem)


 አካባቢ የችግሩን ዓይነት ስፋትና ጥልቀት ተገንዝቦ የጥናቱን አስፈላጊነት እንዲረዳ ጥናቱ ችግሩን ለመፍታት የሚሞክረው
የችግር ትንታኔ በአግባቡ ሲገለፅ ነው፡፡
 የአንድ ጥናት ችግር ሲተነተን በተቻለ መጠን መጠይቃዊ ቢሆን ይመርጣል፡፡
 ይህም የሚረዳው የጥንቱ ትኩረት የሆነው ችግር እጅግ በጣም ጠቦ ጥናቱ ግልፅነት የጎደለው እንዳይሆን
ወይም ደግሞ በጣም ከመስፋት የተነሳ ወደ መነሻ ዓላማው ለመመለስ የሚያስቸግር እንዳይሆን ነው፡፡
 የችግሩ ትንታኔ ሲቀመጥም በመጀመሪያ ጥልቅ ችግሩ ከተቀመጠ በኋላ ወደ ዝርዝር ችግሩ ይገባል፡፡

2.2.7. የጥናቱ ዓላማ


 አንድ ጥናት ከመጀመሩ በፊት ዓላማ ሊኖረው ይገባል፡፡
 ዓላማ ማለት ጥናቱ ከግብ እንዲያደርሰው ወይም እንዲመልሰው የተፈለገው ጥያቄ ነው፡፡
 የጥናቱ ዓላማ ሲዘጋጅ በመጀመሪያ ጥልቅ ዓላማ በአንድ ዐረፍተ ነገር ከተቀመጠ በኋላ ዝርዝር ዓላማዎች ደግሞ በመቀጠል
ይቀመጣሉ፡፡
 ዝርዝር ዓላማው ከዋናው ዓላማ የወጣ መሆን አለበት፡፡

2.2.8. የጥናቱ መላምት (Hypothesis)


 መላምት - ማለት ሊጣራ ወይም በጥናት ሂደቱ ውስይ ሊረጋገጥ የሚችልን ነገር ከወዲሁ መተንበይ ነው፡፡
- ማለት ለአንድ ጥናት መሠረታዊ ጥያቄ ጊዜያዊ መልስ ነው፡፡
- ማለት የአንድን ጥናት የወደፊት ውጤት የሚያመለክት ነው፡፡

5
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 በአጠቃላይ መላምት በጥናት ሊረጋገጥ የሚችል እውነትን የያዘ ሃሳብ ማለት ነው፡፡
 ሁሉም ሀሳብ መላምት ሊሆን አይችልም፡፡
ለምሳሌ፡- “ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቢሆን”
ይህ ዐረፍተ ነገር ምኞት ወይም ጥሩ አስተያየት ሥለሚሆን እንደመላምት ተቀምጦ ሊረጋገጥ የሚችል ነገር
አይደለም፡፡
 የጥሩ መላምት ምሳሌ፡-
“ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ያልሆነው ስብከተ ወንጌልን በሰፊው ባለማካሄድ ነው፡፡”
 የዚህም መላምት ትክክለኛ መሆን አለመሆን ወደፊት በሃደት ከጥናቱ ውጤት የሚገኝ ይሆናል፡፡
 ለመላምት መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦች የሚገኘት፡-
 ከህብረተሰቡ የቀን ተቀን ውሎ
 ከልምድ
 የጋራ ከሆነ አስተሳሰብ ወይም አመለካከት
 ካለፈ ጥናት
 ከተለያዩ ንድፈ ሀሳብ ወዘተ

1. የመላምት አስፋላጊነት (ጥቅም)


 የጥናቱን ዓላማ በትክክል ያሳያል፡፡
 ምን ዓይነት መረጃ መሰብሰብ እንዳለበት ይጠቁማል ፡፡
 ናሙናዎች እንዴት እንደሚመረጥ ይጠቅማል ፡፡
 ጥንቱ እንዴት እንደሚካሄድ ይጠቁማል፡፡
 አሃዛዊ (ቁጥራዊ) መረጃ እንደሚያስፈልግና እንደማያስፈልግ ይጠቁማል፡፡
 ጥናታችን በተሰጠን ወሰን (ክልል) ውስጥ እንዲሆን ወይም ጥናታችን እንዳይሰፋ ይረዳል፡፡
 ለማጠቃለያችን ቅርፅ ይሰጣል፡፡

2. የጥሩ መላምት ባሕርያት


 መላምቱ ግልፅ መሆን አለበት፡፡
 መላምቱ በምርምር ወይም በጥናት ሊረጋገጥ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 መላምቱ ውስን መሆን አለበት፡፡
 በተጨባጭ ካለ እውነታ ጋርም የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡
 በቀላል ቋንቋ መገለፅ አለበት፡፡

3. የመላምት አፃፃፍ ይዘት


አዎንታዊ መላምት
“በጠባብ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በሰፊ ክፍል ከሚማሩ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እያመጡ
ይመጣሉ፡፡”
አሉታዊ መላምት
“በጠባብ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ታማሪዎት በሰፊ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አያመጡም፡፡”
አሉታዊ አዎንታዊ ያልሆኑ መላምት
“በጠባቡም ሆነ በሰፊ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ከፍተኛ የሆነ የውጤት ልዩነት
አይታይባቸውም፡፡”
ጥያቄያዊ መላምት
“የክፍል መጥበብ ወይም መስፋት የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ይጎዳዋልን;$

6
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 መላምት መሠራት ያለበት መረጃ ከመሰብሰብ በፊት መሆን አለበት፡፡
 መረጃ ከተሰበሰበ በኋላ ከሆነ መላምቱ ባላሰብነው ወይም በተቃራኒ መልኩ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡

2.2.9. የጥናቱ አስፈላጊነት(ጠቀሜታ)


 ጥናቱ (ምርምሩ) በሚጠናቀቅበት ጊዜ የሚያስገኘው ጥቅም ምን ሊሆን እንደሚችል እነማን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በዚህ
ክፍል ይጠቆማል፡፡

2.2.10. የጥናቱ ወሰን (ሽፋን)


 ጥናቱ (ምርምሩ) ከየት ተነስቶ የት እንደሚደርስ ወይንም ጥናቱ የሚሸፍነው ቦታ የትድረስ እንደሆነ የሚገልፀው በዚህ ክፍል
ነው፡፡ ጥናቱ የሚሸፍናቸውና የማይሸፍናቸው የሚደስሳቸውና የማይዳስሳቸው ቦታዎችም ከነ ምክንያታቸው ይጠቀሳሉ፡፡

2.2.11. የጥናቱ ሳንካ (ጉድለት)


 ጥናቱ (ምርምሩ) በሚደረግበት ወቅት ለአጥኚው ሰው በጥናቱ ጊዜ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን የገንዘብ ወይም የጊዜ እጥረት
የሰው ኃይል ችግር ማለትም ናሙና የምንወስድባቸው ሕብረተሰብ ችግር እንዲሁም ጥናቱ የሚያተኩርባቸው የአካባቢው
ሁኔታ የመሳሰሉት የሚጠቀሱበት ክፍል ነው፡፡

2.2.12. የጥናቱ (ምርምሩ) ዘዴዎች (Methodologies)


 በዚህ ክፍለረ የሚጠቀሰው የአሰራሩን ዘዴ የሚመለክት ሀሳብ ነው
 በጥናቱ(በምርምሩ) ወቅት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎችና መተንተኛ መንገዶች በዚህ ሥር
ይጠቅሳሉ፡፡

ሀ. የጥናቱ ዓይነት
 ለጥናቱ የምንጠቀምበት የጥናት ዓይነት ምን ዓይነት እንደሆነ የምትገልፅበትና የመረጥንበትንም ምክንያትም
የምናብራራበት ክፍል ነው፡፡
ለ. የጥቅል ስብስብ ተጠያቂዎች ዓይነትና መጠን
 በጥናቱ የምንጠቀምባቸው የጥቅል ስብስብ ተጠያቂ ዓይነቶች እነማን እንደሆኑ የምንገልፅበትና የአጠቃላይ
ተጠያቂዎች መጠንም ምን ያህል እንደሆነ የማናሰፍረው በዚህ ነው፡፡
ሐ. የናሙና ዓይነትና መጠን (የአወሳሰድ ዘዴ)
 ለጥናታችን ምን ዓይነት ናሙና እንደመረጥን፣ የናሙናው መጠን ምን ያህል እንደሆነ፣ ናሙናውን እንዴት
እንደወሰድንና ናሙናውን የመረጥንበትን ምክንያት ምን እንደሆነ የምንገልፅበት ክፍል ነው፡፡
መ. የመረጃ አሰባሰብ
 በጥናታችን ወስጥ የምንጠቀምባቸውን የመረጃ ምንጭ ዓይነቶችን የምንገልፅበጽ ክፍል ነው፡፡
ሠ. የመጠየቁ ይዘት
 ለጥናታችን የምንጠቀመውን መጠይቅ የመጠየቁም ይዘት ምን እንደሚመስል የምንገልፅበት ክፍል ነው፡፡(ማለትም
ሥለ ዝግና ክፍት የመጠይቅ ዓይነቶች እንዴት እንደምንጠቀም የምንገልፀው በዚህ ውስጥ ነው፡፡)

2.2.13. የተዛማጅ ጽሑፎች ዳሰሳ


 ከርዕሱ (ከጥናቱ ርዕስ) ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ቀደምት ሥራዎች የሚሚዳሰሱበት ክፍል ነው፡፡
 በዚህ ውስጥ ቀደምት ሥራዎች በሥፋትና በጥልቀት ይዳሰሳሉ፡፡

2.2.14. የመረጃ ትንታኔ


 በዚህ ክፍል ከተጠያቂዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች በተለያዩ የአጠናን ሥልቶች ይተነተናሉ፡፡

7
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 ከተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ከተዛማጅ ጽሁፎች ጋር በማዛመድ በዚህ ክፍል ውስጥ
እየተተነተኑ ይቀርባሉ፡፡

8
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

2.2.15. የጥናቱ መደምደሚያ


 አንድ ጥናት ያተኮረበት ችግር እንዴት ሊፈታ እንደሚችልና በምን ዓይነት መንገድ ሊጠቃለል እንደሚችል የሚገለፅበት
ክፍል ነው፡፡
 ይህ ክፍል የጥንታዊ ሥራ ግብ መግለጫ ስለሆነ ዝግጅቱ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡
 የጥናቱ መደምደሚያ ክፍልም በውስጡ አራት ንዑሳን ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ እነርሱም፡ ፡-
1. መግቢያ(Introduction)
2. ግኝቶች(Findings)
2.1 ጠንካሮች ጎኖች(Strength)
2.2 ደካማ ጎኖች(Weakness)
3. ማጠቃልያ(Conclusion)
4. የመፍትሔ ሀሳብ(Recommendation)

 በመጀመሪያ ጥናቱ ያተኮረበትን ችግርንና የጥንቱን መደምደሚያ አጠቃላይ ይዘት በዝርዝር የሚፃፍበትን መግቢያን
ማዘጋጀት ፡፡
 ጠንካራና ደካማ ጎኖች የሚገለፁበት ግኝቶችን ከመረጃ ትንታኔ በመውሰድ በአጭር በአጭሩ እያጠቃለሉ መጥቀስ፡፡
 በመቀጠልም ከግተኝቶች መረጃ በመነሳት ማጠቃለያ ማዘጋጀት፡፡
 በመጨረሻም የማጠቃለያ ነጥቦችን መሠረት በማድረግ ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚመከርበትን፣ ትኩረት
እንዲደረግ የሚጠቆምበትንና እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቢያ የሚሰጥበትን የመፍትሐየ ሀሳብ ማዘጋጀት ይሆናል፡፡

2.2.16. የጥናቱ አጠቃላይ ይዘት


 በዚህ ክፍል ውስጥ ጥናቱ በአጠቃላይ የሚይዛቸው ምዕራፎች ከዓበይት ርዕሶቻቸው ጋር ይተነተናሉ፡፡

ለምሳሌ፡- ምዕራፍ አንድ - መግቢያ


ምዕራፍ ሁለት - የተዛማጅ ጽሁፎች ዳሰሳ
ምዕራፍ ሦስት - የመረጃ ትንታኔ

ምዕራፍ አራት - የጥናቱ መደምደሚያ


2.2.17. የጥናቱ በጀት
 አንድ ጥናት ሲጠና ወጪ የሚደረግ ገንዘብ፣ የሚያስፈልግ በቂ ጊዜና የሰው ኃይል ይኖረዋል፡፡
 ማንኛውም አጥኚ ሰው ጥናቱን (ምርምሩን) ከመጀመሩ በፊት የሚያስፈልገውን (የሚፈጅበትን) የወጪ መጠን፣
ጥናቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ የሚፈጅበትን ጊዜና በጥናቱ ላይ የሚሳተፍ ሰዎችን በግልፅ ማስቀመጥ ይገባዋል፡፡
(ይህም በሰንጠረዥ ቢቀመጥ መልካም ነው፡፡)
 በአጠቃላይ አንድ አጥኚ ጥናቱን ከመጀመሩ በፊት ጥናቱ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የሚያስፈልጉትን የሰው
ኃይል፣ የገንዘብና የጊዜን መጠን ይወስናል፡፡

- እያንዳንዱ ሥራ መቼ ተጀምሮ መቼ እንደሚጠናቀቅ


- እያንዳንዱ ሥራ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል
- እያንዳንዱ ሥራ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው፡፡

9
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

ክፍል ሦስት
3. የመረጃ አሰባሰብ
 ጥናት ለማካሄድ አስተማማኝ መረጃዎችን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡
 ማንኛውም አጥኚ መረጃን ለመሰብሰብ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችና ይጠቀማል፡፡
 በዚህ ዐበይት ርዕስ ውስጥ
 የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን ለማብራራት ይሞክራል፡፡
 የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖቸቻቸው ይገልፃል፡፡
 አንድ አጥኚ አንድ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ከመጠቀሙ በፊት ምን ምን ሁኔታዎችን ማጤን እንዳለበት ይረዳል፡፡

3.1. የናሙና አወሳሰድ ዘዴ


3.1.1. የናሙና ትርጉም
አንድ አጥኚ (ተማራማሪ) ለጥናቱ የሚያስፈልጉትን ጥቅል ስብስብ ወገኖች(Population) ካወቀና (ካጠናና)
ዝርዝራቸውንም በሚገባ ካስቀመጠ በኋላ ከዝርዝሩ ውስጥ ለጥናቱ ተመጣጣኝ የሆኑ ወኪሎችን ይመርጣል፡፡ ይህም
የአመራረጥ ዘዴ ናሙና ይባላል፡፡
3.1.2. የናሙና አስፈላጊነት
 የናሙና አስፈላጊነት ዋናው ምክንያት የተመጣጠነ ዋጋን (Cost Effectiveness) መሠረት ያደረገ ስለሆነ ነው፡፡
 ሁሉንም ጥልቅ ስብስብ ወገኖች በጥናቱ ውስጥ ማካተት የጥናቱ ትክክለኛነት የጎላ ቢሆንም ይህ ግን ጊዜን፣
ገንዘብንና ጉልበትን በከፍተኛ ደረጃ በማባከን አጥኚውን ችግር ላይ ይጥላል፡፡
3.1.3. የናሙና አወሳሰድ ደረጃዎች
 ይህ ዘዴ ከጥቅል ስብስብ ወገኖች መካከል ናሙና ለማውጣት የሚረዳ ዕቅድ ነው፡፡
 ይህም ዘዴ መረጃዎች ከመሰብሰባቸው በፊት የሚከናወን ነው፡፡
 ናሙና በምንመርጥበት ጊዜ ተግባራዊ መሆን ያለባቸው አራት ዋናዋና ደረጃዎች ያሉ ሲሆን እነርሱም፡-
1. ጥቅል ስብስብ ወገኖችን በሚገባ ማወቅ(ደ efeining the population)
2. የጥቅል ስብስብ ወገኖችን ዝርዝር ማውጣት (Listing the Population)
3. ወካይ ናሙናዎችን መምረጥ (Selecting Rep ረ esentatie Sample)
4. በቂ ናሙናዎችን መምረጥ(Odtaining adequate sample)
ጥቅል ስብስብ ወገኖችን በሚገባ ማወቅ
ናሙና ከመሥራታችን በፊት የመጀመሪያው ደረጃ የጥቅል ስብስብ ወገኖችን በሚገባ ማወቅ ነው፡፡ ይህንም በተገቢው
ሁኔታ ማጥናቱ (ማወቁ) አባሉ የጥቅል ስብስቡ ክፍል መሆን አለመሆኑን ለመረዳት ይጠቅመናል፡፡

የጥቅል ስብስብ ወገኖች ዝርዝር ማውጣት


የጥቅል ስብስብ ወገኖችን ሁኔታ በሚገባ ካጠኑ በኋላ የሁሉንም አባሎች ሥም ዝርዝር ማዘጋጀት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የሥም ዝርዝሩም ሁሉንም አባሎች ያካተተና ትክክለኛና ተአማኚነት ያለው መሆን አለበት፡፡
ወካይ ናሙናዎችን መምረጥ
 አጥኚው ሰው (ተመራማሪው) ጥቅል ስብስብ ወገኖችን (Population) ካጠናና ዝርዝራቸውን በሚገባ ካስቀመጠ
በኋላ ከዝርዝሩ ውስጥ ይመርጣል፡፡ ይህ የአመራረጥ ዘዴም ናሙና (Sampling) ይባላል፡፡
 ናሙና አወሳሰዱ አድሏዊነት ሊኖረው አይገባም፡፡
 አንድ ናሙና (Sample) የአንድን ጥቅል ስብስብ ወገኖች ሙሉ መረጃ መስጠት መቻል አለበት፡፡
በቂ ናሙና ማግኘት
 የአንድ የናሙና መጠን ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡
 እጅግ በጣም ትልቅ ወይም እጅግ በጣም ትንሽ ናሙና መሆን የለበትም

10
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 በቂ ንሙን የባለው ተአማኚነት ያለው ጥቅል ስብስብ ወገኖችን መወከል የሚቻል ነው፡፡
 ትንሽ ናሙና የሚያስፈልገው አንድ ዓይነት አባል ለሆኑ ጥልቅ ስብስብ ወገኖች ሲሆን ትልቅ ናሙና የሚያስፈልገው
ደግሞ የተለያዩ አባላት በአንድ ጥልቅ ስብስብ ወገኖች ውስጥ ሲገኙ(ሲኖሩ) ነው፡፡

3.1.4. የጥሩ ናሙና አወሳሰድ ባሕርያት


 ጥልቅ ስብስብ ወገኖችን በሚገባ(በጥሩ ሁኔታ) መወከል መቻል አለበት፡፡
 በተቻለ መጠን አድሎአዊነትን ያስወገ ደ መሆን አለበት፡፡
 ከወሰድነው ናሙና ተነስተን ለሙሉው ጥናት ተግባራት ያለምንም ጥርጥር መሥራተወ የሚያስችል መሆን አለበት፡፡

3.1.5 የናሙና ዓይነቶች


ሁለት ዓይነት የናሙና ዓይነቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡-
ሀ. ናሙናው ውስጥ ለመግባት እኩል ዕድል ያላቸው (ፕሮባብሊቲ ሳምፕሊንግ)
ለ. ናሙናው ውስጥ ለመግባት እኩል ዕድል የሌላቸው (ነን-ፕሮባብሊቲ ሳምፐሊንግ)

ናሙናው ውስጥ ለመግባት እኩል ዕድል ያላቸው(ፕሮባብሊቲ ሳምፕሊንግ)


 በዚህ የናሙና አወሳሰድ ሁሉም አባላት ወደ ናሙና ለመግባት እኩል ዕድል አላቸው፡፡
 በዚህ ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ዘዴ በሚከተሉት ምክንያቶች ተመራጭነቱ የጎላ ነው፡፡
 የጥቅል ስብስብ አባላት በተመራማሪው ፍቃድ የሚመረጡ አይደሉም፡፡
 ናሙናዎቹ ሁሉንም የጥቅል ስብስብ አባላትን ይወክላሉ፡፡
 በዚህ ዘዴ ውስጥ አምስት(5) ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎች አሉ፡፡ እነርሱም፡፡
1. ቀላል ባየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ (Simple random sampling)
2. ሲስተማቲክ በየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Systematic random sampling)
3. ፈትጋበቃል በየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Stratigied random sampling)
4. በቡድን የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Cluster sampling)
5. ባለብዙ ደረጃ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Multi sathe sampling)

ቀላል ባየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Simple random sampling)


 በዚህ ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ሁሉም አባሎች የመመረጥ ዕድላቸው እኩል ነው፡፡
 በዚህ ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ዘዴ የሚከተሉትን ዘዴዎች ልንጠቀም እንችላለን፡፡
 ሣንቲም የማጦዝ ዘዴ
 ሣንቲም ወደ ላይ አሽከርክሮ በማጎን (በማጦዝ) ምርጫቸውን በማየት ናሙናን
ለመውሰድ ይረዳል፡፡
 ይህ ዓይነቱን ዘዴ የምንጠቀመው ትንሽ ቁጥር ያለው ጥቅል ስብስብ (Population)
ሲኖር ነው፡፡
 የሎተሪ አወጣጥ ዘዴ
 በዚህ ዓይነት ዘዴ አጥኚው ሰው በመጀመሪያ ለሁሉም የጥቅል ስብስብ አባለት ልዩ ቀጥር
ይሰጣል፡፡ ቀጥሎ ከጥቅል ስብስብ አባል ቁጥር ጋር እኩል የሆነ ትኬቶችን ያዘጋጃል፡፡
በመጨረሻም ትኬቶቹን በሚገባ በመቀየጥ ዕጣውን ያወጣል፡፡

11
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

ሲስተማቲክ ባየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Systematic random sampling)


 በዚህ ዓይነት ዘዴ በቅድሚያ ሁሉም የጥቅል ስብስብ አባላት በፊደል ቅደም ተከተል(Alphabetically)
ይዘረዝራሉ(ይደረደራሉ)፡፡ በመቀጠልም አጥኚው ሰው ደስ ካለው ቁጥር ላይ በመነሳት ናሙናዎችን ይወስዳል
ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- 100 አባሎች ቢኖሩን ከእዚህ ውስጥ 7 ናሙናዎችን መውሰድ ቢያስፈልገን አጥኚው ሰው በ 6 ኛ
ደረጃ (ተራ ቁጥር) ላይ ያለውን አባል መነሻ ቢያደርግ በየ 14 ተራ ቁጥር ልዩነት 7 ናሙናዎችን ማግኘት
ይቻላል፡፡ ይኸውም 6 ፡ 20 ፡ 34 ፡ 48 ፡ 62 ፡ 76 ፡ 90 ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
14 14 14 14 14 14 14 14

ፈትጋበቃል በየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Stratigied random sampling)


 በዚህ ዘዴ ናሙናዎችን መውሰድ የምንችለው የጥቅል ስብስብ አባላቱ በተለያዩ መስፈርቶች ውስጥ ያሉ ወይም
በመስፈርታቸው የማይገናኙ ሲሆን ነው፡፡
 ስለዚህም የጥቅል ስብስብ አባላቱ በሚመሳሰሉበት መስፈርት ከተመደቡ በኋላ በመቀጠልም ከእያንዳንዱ መደብ
ቀላል ባየሽ የናሙና እወሳሰድ ዘዴን (Simple random sampling) ወይም ሲስተማቲክ ባየሽ የናሙና አወሳሰድ ዘዴን
(Systematic random sampling) በመጠቀም ናሙናን ይወስዳል ማለት ነው፡፡
 የሚመደቡበት መስፈርትም ፡- በፆታ፣ በዕድሜ፣ በትምህርት ደረጃ፣በኑሮ ሁኔታ፣ በሃይማኖት፣ወዘተ የመሳሰሉት
ናቸው፡፡
 የሚወሰዱት ናሙናዎችም ከአጠቃላይ ስብስብ የተወጣጡ ስለሚሆን ትክክል የሆነ ሥራ ሊሠራ ይችላል፡፡
በተጨማሪም ጊዜንና ገንዘብን ይቆጥብልናል፡፡

በቡድን የናሙና አውሳሰድ ዘዴ (Cluster sampling)


 በዚህ ዓይነቱ ዘዴ ናሙና ለመውሰድ በመጀመሪያ የጥቅል ስብስብ አባላቱን በቡድን በቡድን ካስቀመጥን በኋላ
በመጨረሻ ናሙና ስንመርጥ ሁሉንም የቡድን አባላት ወይም የተወሰኑትን የቡድን አባላት ሊሆን ይችላል፡፡
 የዚህን ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ዘዴ አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀመው
1. ጥቅል ስብስብ እጅግ የበዛ ቁጥር ሲኖረው
2. ጥቅል ስብስብ የማይቆጠር ሲሆን
3. የአባላቱ ስብጥር በጣም የተራራቀ ሲሆንና
4. የአባላቱ በተናጠል ከዋናው የጥቅል ስብስቡ አባላት ለመምረጥ አስቸጋሪ ሁኔታ ሲፈጠር ነው፡፡

ለምሳሌ፡- አጥኚው በኢትዮጵያ የሚገኙ የ 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች ያገኙትን የሒሳብ ትምህርት ውጤት ማወቅ ሲያስፈልገው በተናጠል
አባላትን በማውጣት ናሙና መውሰድ ያስቸግረዋል፡፡ ስለዚህም በኢትዮጵያ የሚገኙ የ 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች በክልል፣
በዞን፣ በወረዳ ትምህርት ቤት የተቦደኑ ስለሆኑ አጥኚው ሰው ክልሎችን፣ ዞኖችን ወይም ወረዳዎችን እንደ አንድ
ቡድን ወስዶ ናሙናውን ማዘጋጀት ይችላል ማለት ነው፡፡

ባለብዙ ደረጃ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ(Multi sathe sampling)


 የዚህ ዓይነቱ የናሙና አወሳሰድ ዘዴን የምንጠቀምበት፡-
1. በቡድን የናሙና አወሳሰድ ዘዴ ከፍተኛ ደረጃ ሲሆን
2. የጥቅል ስብስብ አባላቱ እጅግ በጣም የበዛና በጣም ትልቅ የቆዳ ስፋት(ሽፋን) የያዘ ሲሆን
 ይህ ዘዴ ገንዘብንና ጊዜን ለመቆጠብ ይረዳል፡፡
ለምሳሌ፡- አንድ አጥኚ ሰው ነጋዴዎች ስለ ነፃ ገበያ ያላቸውን ሀሳብ ለመሰብሰብ ቢፈልግ ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ
ከማዕከላዊ አቅጣጫዎች 5 ክልሎችን ባየሽ ይመርጣል፡፡ ቀጥሎም በ 5 ቱ ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ ዞኖች ያሉት

12
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
ሁሉም ወረዳዎችን ይዘረዝሩና ከተዘረዘሩት ውስጥ 100 ወረዳዎች ባየሽ ይመረጣል፡፡ ከነዚህም ወረዳዎች ውስጥ
700 ነጋዴዎችን እንደ ናሙና ይወሰዳል ማለት ነው፡፡

ናሙናው ውስጥ ለመግባት እኩል ዕድል የሌላቸው (ነን-ፕሮባብሊቲ ሳምፐሊንግ)


 በዚህ ዓይነት ዘዴ ናሙናዎችን የምንወስደው የአጥኚውን ዳኝነት መሠረት ባደረገ ነው፡፡ የዚህ ዘዴ ደካማ ጎኖች፡-
- የሚወሰዱት ናሙናዎች ሁሉንም የጥቅል ስብስብ አባላት ሊወክሉ አይችሉም፡፡
- ከሚወሰደው ናሙና ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

 ጠንካራ ጎኖች፡-
 ውስብስብ አለመሆኑ
 ብዙ ወጪ አለመጠየቁ
 በቂ መረጃ ያላቸውን አባላት መምረጥ ስለሚቻል ጊዜን መቆጠብ ያስችላል፡፡

 በዚህ ዘዴ ውስጥ 4 ዓይነት የናሙና አወሳሰድ ዘዴዎች አሉ፡-


1. ኮንቬንሽናል የናሙና አወሳሰድ ዘዴ
2. ኮታ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ
3. ዳይሜንሽናል የናሙና አወሳሰድ ዘዴ
4. ፐርፐሲቭ ወይም ጀጅመንታል የናሙና አወሳሰድ ዘዴ

3.2. የመረጃ ምንጮች


 የመረጃ ምንጮች በሁለት ስፊ ምድቦች ይመደባሉ፡-
ሀ/ የመጀመሪያ ደረጃ የደረጃ ምንጮች
- አዲስ፣ ወጥ (Original) መሰል ጠባይ ያላቸው መረጃዎችን የምናገኝባቸው ናቸው፡፡
- የመረጃ ምንጮቹም ከዓይን ምስክሮች፣ ከመዋዕለ ዜና፣ ከቃለ መጠይቅ፣ ከጽሁፍ መጠይቅ፣
ከምልከታ፣ ወዘተ ከመሳሰሉት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ይካትታል፡፡
ለ/ የሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮች
- ቀድመው የተዘጋጁ፣ ቀደም ሲል የተሰባሰቡና የተመዘገቡ መራጃዎችን ያካትታል፡፡

3.3. የመጀመሪያ ደረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያዎች(ዘዴዎች)


 የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች በርካታ ቢሆኑም አጥኚው የትኛውን ዘዴ መጠቀም እንዳለበት ለመወሰን፡-
- የጥናቱ ዘዴ ወይም የተመረጠው የጥናት ዓይነት
- የጥናቱ አዋጪነት እና
- ተገቢውን መረጃ ለማግኘት ያለው አምቺነት መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው፡፡
በዚህ መሠረት በጣም አስፈላጊ የሆኑት የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች በተለይ በቅኝት ወይም በገላጭ የምርምር ዓይነት የሚከተሉት
ናቸው፡፡
1. የጽሑፍ መጠይቅ (Questionnaire)
2. የመርሐግብር መጠይቅ(Schedule)
3. ቃለ መጠይቅ (Interview)
4. ምልከታ(Observation)
5. ውሱን የቡድን ውይይት (Focus group discussion)

13
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
3.3.1. የጽሑፍ መጠይቅ
 ይህ ዘዴ ለመረጃ ማጠናከሪያ ስልት ሆኖ ብዙውን ጊዜ ያገለግላል፡፡
 ሰዎችን በግንባር ለማግኘት በማይቻልበት ሁኔታና አስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ መጠየቁን በጽሑፍ አዘጋጅቶ እንዲሞሉ
በማድረግ አስተያየታቸውን ለመሰብሰብ የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡
 የዚህ ስልት ዋና ጥቅሙ መጠይቁን ለብዙ ሰዎች አሰራጭቶ መረጃ መሰብሰብ ያስችለናል፡፡
 በጽሑፋዊ መጠይቅ ውስጥ የሚሰፍሩ ጥያቄዎች በሁለት ዓይነት መልኩ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

1. ዝግ(Closed Ended) ጥያቄና


2. ክፍት (Open Endede) ጥያቄ ናቸው፡፡
 በዝግ የጥያቄ ዓይነት ለሚዘጋጁ ጥያቄዎች መልሶቻቸው የተወሰኑ ናቸው፡፡ በምርጫ መልክ ወይም በማይሻማ መልክ
ተቀምጠውልናል፡፡
ለምሳሌ፡- ጾታ ወንድ ሴት
 በክፍት የጥያቄ ዓይነት ለሚዘጋጁ ጥያቄዎች መልሶቻቸው የመላሹን ሀሳብ ያለገደብ የሚያስበውን እንዲሞላ
ይፈቅዱለታል፡፡
ለምሳሌ፡- የትምህርት ደረጃ .....................................................

3.3.1.1. የዝግ ጥያቄዎች ጠንካራ ጎን


 መልሶቹ መሠረታዊ (መደበኛ) ስለሆኑ መልስ ሰጪዎችን ለማወዳደር ያስችላል፡፡
 መልሶቹን ለመመደብ ለትንታኔ ቀላል ናቸው፡፡ ገንዘብና ጊዜንም ይቆጥባል፡፡
 መልሶቹ በቀላሉ እንዲመለሱ ስለሚያደርግ ብዙ መጠይቆች ተሞልተው እንዲመልሱ ይረዳል፡፡
 የመላሾቹን ፍራቻ ይቀንሳል፡፡ ማለትም “አላውቀውም” የሚለው ሀሳብ ይቀንሳል፡፡
 መልሶቹ በአንፃራዊ መልኩ የተጠናቀቁ ይሆናሉ፡፡
 ለመላሾች መልስ ለመስጠት ቀላል ነው፡፡

3.3.1.2. የዝግ ጥያቄዎች ደካማ ጎን


 መላሾች የማያውቁትን መልስ እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡ ማለትም ግምታዊ መልስ ሊሰጡ ስለሚያስችል፡፡
 መላሾች አንድን ጥያቄ በሚገባ ተረድተው የመለሱት መሆኑ ላየረታወቅ ይችላል፡፡
 መላሾች መልስ በሚመርጡበት (በሚሞሉበት) ጊዜ ስህተት ሊሠሩ ይችላሉ፡፡
3.3.1.3. የክፍት ጥያቄዎች ጠንካራ ጎኖች
 የዚህ ዓይነት ጥያቄዎች አማራጭ መልሶች በዝርዝር በማይታወቁበት ጊዜ የሚጠቅሙ ናቸው፡፡
 ለመላሾች በበቂ ሁኔታ መልሱን እንዲመለሱ ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
 ለአንድ ጥያቄ እጅግ በርካታ የሆኑ መልሶች በሚኖሩበት ጊዜ ጥያቄውን ክፍት ጥያቄ ማድረጉ ይጠቅማል፡፡ ምክንያቱም
ዝግ ጥያቄ ብናደርገው አማራጭ መልሶቹን ለመዘርዘር አድካሚና አሰልቺ ይሆናል፡፡
 ውስብስብ የሆኑ ጥያቄዎችን ወደ አነስተኛ የጥያቄ ቅርፅ ለመቀየር የሚያስቸግሩ የጥያቄ ዓይነቶችን ክፍት ጥያቄ
አድርጎ ማቅረብ ተመራጭ ይሆናል፡፡

3.3.1.4. የክፍት ጥያቄዎች ደካማ ጎን


 አጥኚው ከሚገምተው ውጪ ከርዕሱ የወጡና አስፈላጊ ያልሆኑ መልሶችን እንዲሰበስቡ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
 የዚህ ዓይነት ጥያቄ ከፍተኛ የመፃፍ ችሎታን፣ የተሻለ የመግለፅ ችሎታንና በአጠቃላይ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃን
ይጠይቃል፡፡
 ጥያቄዎቹ ለመላሹ በጣም ጥቅልል ያሉ ከሂኑ ለመረጃ አዳጋችና ከባዶች ይሆናሉ፡፡
 የዚህ ዓይነት ጥያቄዎች የመላሹን ጊዜና ኃይል ስለሚወስዱ መጠይቆቹ ሳይሞሉ ሊመልሱ ይችላሉ፡፡

14
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
3.3.1.5. የጽሑፍ መጠይቅ መሙያ(መመለሻ) ቅጽ
ሀ/ የክፍት ጥያቄዎች መመለሻ
 ለክፍት ጥያቄዎች መመለሻ መላሹ የሚሞላበት ክፍት ቦታ ይኖረዋል፡፡ አጥኘው ይህን ክፍት ቦታ የሚተወውም
መልስን ለመስጠት የሚፈጀውን የቦታ መጠን በቂ ነው ብሎ በሚገምተው ልክ ይሆናል፡፡

ለ/ የዝግ(የውሱን ምርጫ) ጥያቄዎች መመለሻ


 ለዝግ ጥያቄዎች መልስ መስጫ ብዙ ዓይነት አማራጮች ይኖራሉ፡-
1. ኖሚናል
2. ኦርዲናል
3. ኢንተርቫል
4. ሬሽዎ
ኖሚናል
 ለጥያቄዎቹ መልስ መሰጫ ባዶ ቦታ በመተው ወይም ምልክት የሚደረግበት ሳጥን በመተው ወይም የሚከበብ
ቁጥር በመፃፍ አማራጮችን መዘርዘር የተለመደ ነው፡፡
ለምሳሌ  ተገቢው ባዶ ቦታ ላይ ምልክት ያድርጉ
1. ፆታ ወንድ ሴት
 ተገቢውን ቁጥር ያክብቡ
1. ፆታ ወንድ ፡ 1 ሴት ፡ 2
ኦርዲናል
 የዚህ የአመላለስ ቅርፁ በሚከተሉት ምሳሌ ዓይነቶች ሊገለፅ ይችላል፡-
ለምሳሌ፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለሁሉም ቀሳውስት አስፈላጊ ነው፡፡
በጣም እስማማለሁ እስማማለሁ እርግጠኛ አይደለሁም
በጣም አልስማማም አልስማማም
 ከላይ በምሳሌ እንደተቀመጠው በዚህ መልክ ለተዘጋጁ ተመሳሳይና ተከታታይ ጥያቄዎች በሚከተለው ሁኔታ
የመመለሻውን (መልስ መስጫውን) ቅፅ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
ተ.ቁ እስማማለሁ አልስማማም
1 ........... ..............
2 ........... ..............

 የዚህ ዓይነት ቅፅ ጠቀሜታ ድግግሞሽን ያስወግዳል፡፡

 ሌላው የአመላለስ ቅርፅ ደግሞ በደረጃ መመለስ ሲሆን ይኸውም ነጥቦችን በመዘርዘር መላሾች በመልስ ቦታው
ላይ ደረጃ እንዲሰጡአቸው ማድረግ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- እባክዎ ከዚህ በታች የገጠር ገዳማትን ህልውና ለመጠበቅ ከተዘረዘሩት የገንዘብ ምንጮች የምንጭነታቸውን መጠን
ደረጃ በመስጠት ያስቀምጧቸው፡፡(1 ኛ, 2 ኛ, ወዘተ በማለት)
....................... በምዕመናን የማሰባሰብ ዕርዳታ
........................ በመነኮሳት የልማት እንቅስቅሴ
........................ በብድር
........................ በልመና
........................ በገዳሙ አነስተኛ እንቅስቃሴ
........................ በገዳሙ ቋሚ ንብረት

15
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
........................ ባጠቃላይ ቤተክህነት የበጀት ድጎማ

ደረጃ በመስጠት የሚመለሱ ጥያቄዎችን በምናዘጋጅበት ጊዜ በዋናነት መታሰብ ያለበት ጉዳይ፡-


 ትዕዛዙ በትክክል መስፈሩንና መስፈርቶቹ በግልፅ መቅረባቻ ነው፡፡
 የሚዘረዘሩት ነጥቦች ከአስር(ከ 10) መብለጥ የለባቸውም ፡፡
 እነርሱም በአንድ ገፅ ላይ መስፈር አለባቸው፡፡
 ደረጃ የሚሰጣቸው ስንት እንዲሆኑ ወይም ሁሉም እንደ ሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
ኢንተርቫል
ለምሳሌ፡- እድሜዎ ከ 15 – 20 ከ 41 – 50
ከ 21 – 30 ከ 50 በላይ
ከ 31 – 40

3.3.1.6. የጥያቄዎች ቅደም ተከተል


ጥያቄዎቹን ወደመጨረሻው መጠየቅ ቅርጽ ለመለወጥ አጥኚው ስንት ጥያቄዎች በመጠየቁ መካተት እንዳለባቸውና
የጥያቄዎቹንም ቅደም ተከተል መወሰን አለበት፡፡ በዚህ ረገድ የሚከተሉት አጠቃላይ መመሪያ ተጠቁመዋል፡-

 ስሜትን የሚነኩና ክፍት ጥያቄዎችን በመጠይቁ መጨረሻ ማስፈር


ለምሳሌ፡- ከፆታ ጋር የተገናኙ፣ ገቢን የሚመለከቱ፣ ሃይማኖትን በሚመለከቱ፣ ወዘተና እንዲሁም ክፍት ጥያቄዎችም
ጊዜንና ማሰብን ስለሚጠይቁ መጨረሻ ቢሆኑ ይመርጣል፡፡
 በመጀመሪያ ለመመለስ ቀላል የሆኑትን ጥያቄዎች ማስፈር ቢቻል የመክፈቻ ጥያቄዎች አስደሳችና አጓጊ መሆን
አለባቸው፡፡
 ጥያቄዎችን በጊዜ ወይም በርዕስና በመሳሰሉት ቅደም ተከተል ማስቀመጥ
 በአንድ ዓይነት መንገድ የሚያሰጡ ዝንባዎችን የሚያመጡ የጥያቄ ሥልቶችን ማስወገድ፡፡

3.3.1.7. የጥያቄዎች አወቃቀር


የጥሩ መጠይቅ ይዘት ዋንኛ መለኪያው የጥያቄዎቹ በጥራትና በግልፅ መቅረብ ነው፡፡
ጥያቄው ግልፅ በማይሆንበትና ከባድ የሚሆንበት ጊዜ መልስ ሰጪዎች የጥያቄውን መንፈስ(ትርጉም) በመቀየር
ለመመለስ ይሞክራሉ፡፡ በሌላ አባባል መላሾች ጥያቄውን በተለያየ ደረጃ በመገንዘብ የተለያ መልስ ይሰጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ
ጥናቱን ውድቅ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ሆኖም የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም መላሾች ጥያቄውን እንዲረዱትና በአንድ ዓይነት ሁኔታ እንዲገነዘቡት ማድረግ
ይቻላል፡-
 ጥያቄዎችን አጭር ማድረግ
- አጭርና ቀጥተኛ ጥያቄዎችን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላሉ፡፡
- በተጨማሪም መጠየቁ በፍጥነት ተምልቶ እንዲመለስ ይረዳል፡፡
 አንድ ጥያቄ ብቻ መጠየቁን ማረጋገጥ
 ተነባቢ እንዲሆን ማድረግ
 እያንዳንዱን ቃል ማየትና በጣም ቀላል ቃል መጠቀም
 ሁሉንም ትርጓሜዎችን፣ ይሁንታዎችንና መግለጫዎችን በግልፅ ማስፈር
ለምሳሌ፡- የአንድን ግለሰብ ደመወዝ ለመጠየቅ ደመወዙ በዓመት፣ በወር፣ በሳምንት ወይንም በቀን
መሆኑን መግለፅ አለበት፡፡
 በጉልህ ማስታወስን የሚጠይቁ ጥያቄዎችን አለመጠየቅ፡፡ምሳሌ፡- ባለፈው ሣምንት ስንት ጊዜ ከተማ
ወጡ; ስንት ጊዜ ቤተመጽሃፍት ገቡ;
16
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 ትክክለኛ የሆነ መልስ ለማግኘት ምንጭን መጠቀም፡፡
 አመለካከትንና አስተሳሰብን የሚመለከቱ ስፊ እና አጠቃላይ የሆኑ ጥያቄዎችን አለመጠየቅ፡፡
ለምሳሌ፡- እርስዎ ራስዎን ጠንካራ ታታሪ ሠራተኛ ነኛ ብለው ይገምታሉ ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ
በቀን ስንት ሰዓት ይሰራሉ ብሎ መጠየቅ
 ጥያቄውን ቀላልና በፍጥነት የሚመለስ ማድረግ
 የሚያዳሉ፣ ጫና የሚፈጥሩ፣ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚመሩና ስሜትን የሚነኩ ጥያቄዎችን
ማስወገድ፡፡
3.3.1.8. የመግቢያ ጽሑፍ - ለጽሑፍ መጠይቅ

 የሚጠይቅ ጥያቄዎች ከተጻፉና በቅደም ተከተል ከተቀመጡ በኋላ ቀሪው ተግባር የመግቢያ ፅሁፍ ማዘጋጀት
ነው፡፡
 ይህም በመጠይቅ አዘገጃጀት ላይ ዋናው ክፍል ነው፡፡
 ምክንያቱም የጥናቱን ምንነት ስለሚገልፅ የመላሾቹንም ትብብር ስለሚጠይቅ ነው፡፡
 የመግቢያ ፅሁፍ አጠር ብሎ በጥሩ ሁኔታ መዘጋጀት አለበት፡፡
 የመግቢያ ፅሁፍ የሚፃፈው፡-
 አጥኚውን የሚደግፈው ድርጅት ሙሉ ስሙን በመፃፍ ይጀምራል
 የጥናቱን አላማና አስፈላጊነት
 መረጃዎችን ማን እንዲሰበስብ
 ጥናቱ ለምን እንዲካሄድ
 መረጃው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል
 ማን መረጃው ማየት እንደሚችል
 የመላሾች ምሥጢር የተጠበቀ መሆኑን
 ሥም መፃፍ የማያስፈልግ መሆኑን
 የመላሾችን ትብብር ማመስገን
 የመጠይቁ መመለሻ ጊዜው ቀኑን፣ ወሩንና ዓመተምረቱን ማስቀመጥ
 ካስፈለገ የአጥኚውን አዳራሽ መፃፍ ወዘተ.
3.3.1.9. የጽሑፍ መጠይቅ ቅድመ ሥርጭት
 መጠይቁ ወደ ተፈላጊ መላሾች ከመሰራጨቱ በፊት ጥያቄዎቹ በሚገባ መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ፡፡
 አሻሚ፣ አስፈላጊ ያልሆኑና ወዘተ ዓይነት ጥያቄዎችን በማየት የማስተካከል ሥራ መሥራትና ለሥርጭት
ማዘጋጀት፡፡
3.3.1.10. የጽሑፍ መጠየቅ ደካማ ጎን
 ያልተማሩና ልጆችን በመጠይቁ ልንጠቀምባቸው አንችልም፡፡
 ከተሰራጩት መጠይቆች መካከል የሚመለሰው መጠይቅ ከ 40 – 50 በመቶ ስለማይበልጥ የመረጃዉን ታማኝነት
ይቀንሰዋል፡፡
 አንዳንድ ጊዜ መልስ ሰጪዎች ምስጢራዊ ጥያቄዎችን በጽሑፍ መመለስ ላይወዱ ይችላሉ፡፡
 ያልተሟላ መልስ የሰጠን ወይም ገደብ የሌለው መልስ የሰጠን መላሽ ማረጋገጫ የለም፡፡
3.3.2. የመርሐግብር መጠይቅ
 መርሐግብር መጠይቅን መልስ ለማስሞላት ለዚህ ተግባር የተመረጡና እንዴት እንደሚሞላ በሰለጠኑ መላሾች
የሚከናወን ይሆናል፡፡
 የመጠይቁ አሠረጫጨትና አመላለስ ከሌሎች መጠይቆች የተለየ ነው፡፡
 ይህ መጠይቅ ከጽሑፍ መጠይቅ የሚለይበት ነጥቦች፡-

17
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 መጠይቁ አብዛኛውን ጊዜ ለመላሾች የሚላከው ፖስታ ነው፡፡
 በዚህ ዓይነት መጠይቅ መረጃ መሰብሰብ የበለጠ ውድ ነው፡፡
 በዚህ ዓይነት የመሰብሰቢያ ዘዴ መጠይቆች በብዛት ይመልሳሉ፡፡
 በመርሐግብር መጠይቅ የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ የመላሾች ማንነት ይታወቃል፡፡
 በመርሐግብር መጠይቅ መላሾች ቃል ከገቡበት ጊዜ የበለጠ ፈጥነውመልሱን ሞልተው ይመልሳሉ፡፡
(ስለዚህም መረጃን በፍጥነት መሰብሰብ ይቻላል)
 መጠይቅ ማስሞላት የሚቻለው መላሾች የተማሩና ተባባሪ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡
 የመርሐግብር መጠይቅ ዘዴ በብዛት ናሙና ማሠራጨት ከባድ ነው፡፡
 በመርሐግብር መጠይቅ አሞላል አጠቃላይ የተጠናቀቁና በትክክል የተሞሉ መጠይቆች ይመለሳሉ፡፡
 መርሐግብር መጠይቅ ማለት ለጥናቱ ተግባር በተመረጡና በሰለጠኑ መላሾች የሚሞላ ነው፡፡
 አሰረጫጨቱም ከጽሑር መጠይቅ የሚለይ ነው፡፡

3.3.3. ቃለ መጠይቅ
 ቃለ መጠይቅ የመግባት ወይም የግንኙነት ሂደት ሲሆን ቃለ መጠይቅ የሚያደርግለት ሰው ፊትለፊት በቃል
ወይም በስልክ መረጃ የሚሰጥበት ስልት ነው፡፡የነዚህን መረጃ የመስጫ ስልቶች ግለሰባዊ ቃለመጠይቅና የስልክ
ቃለመጠይቅ ተብለው ይታወቃሉ፡፡
 በግለሰባዊ ቃል መጠይቅ ስልት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ቃል ሰጪውን ፊትለፊት በማግኘት ይጠይቀዋል፡፡
 በታዳጊ ሀገሮች የስልክ ቃለ መጠይቅ ስልት ብዙ ጊዜ ተግባራዊ አይሆንም፡፡

3.3.3.1. የቃለ መጠይቅ ዓይነቶች


 የቃለ መጠይቅ ንድፎች (Designs) በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመድባሉ፡፡
ሀ/ መዋቅራዊ ቃለ መጠይቅ (Structured Interview)
ለ/ ኢመዋቅራዊ ቃለ መጠይቅ (Unstructured Intreview)

ሀ/ መዋቅራዊ ቃለ መጠይቅ (Structured Interview)


 ቃለ መጠይቅ ከመካሄዱ በፊት ደረጃውን የጠበቀ ቃለ መጠይቅ ይዘጋጃል፡፡
 በቅድሚያ የተዘጋጁ ጥያቄዎችንና በከፍተኛ ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀ ቀረፃን ያካትታል፡፡
 በሌላ አባባል በዚህ ዘዴ አንድ ዓይነት ጥያቄዎች ለሁሉም ተጠያቂዎች በአንድ ዓይነት ቅደም ተከተልይቀርባል፡፡
 ቃለ መጠይቅ አድራጊው ሰው ጥያቄዎችን ለመቀየር አይችልም፡፡
 ስለዚህም በመዋቅራዊ ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቁ ግትር የሆነ የጥያቄ አወቃቀር የሚከተልና ጥያቄዎችን አንድ
ዓይነት መልከና ቅደም ተከተል በመጠየቅ የሚዘጋጅ ነው፡፡

ለ/ ኢመዋቅራዊ ቃለ መጠይቅ (Unstructured Intreview)


 በዚህ ዘዴ አጠያየቁ እንደሁኔታው የሚቀያየር ነው፡፡
 ምንም እንኳን የጥያቄዎቹ ዝርዝርና ቅደም ተከተል በቅድሚያ የተወሰነ ቢሆንም ቃለ መጠይቅ አድራጊው ሰው
የጥያቄዎቹን መልክ የማደራጀትና ቅደም ተከተላቸውንም የማስተካከል ነፃነት አለው፡፡
 ጥያቄዎቹን ማሻሻልና አንዳንድ አዳዲስ ጥያቄዎችን ከመጠይቁ ዝርዝር መጨመር ይችላል፡፡

3.3.3.2. የቃለ መጠይቅ አደራረግ ዘዴ

ቃለ መጠይቅ አዘጋጆች
 የሚፈለገውን መረጃ ለማግኘት ይቻል ዘንድ መጠይቅ በጥንቃቄ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡
 ቃለ መጠይቅ አድራጊዎችንም በመመልመል ለሚሰበሰበው የመረጃ ዓይነትና በመረጃ አሰጣጡ አካሄዱላይ ማተኮር አለበት፡፡
18
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
 በቃለ መጠይቅ አድራጊውና በቃል ሰጪው መካከል ብዙ ክፍተት መኖር የለበትም፡፡
 ሁለቱም በተቻለ መጠን በአንድ እድሜ ክልልና ከአንድ ፆታና የኑሮ ደረጃ ቢሆኑ ይመርጣል፡፡
 የቃል ሰጪው ትኩረት በቃለ መጠይቅ አድራጊው አለባበስ ላይ እንዳይሆን የጠያቂዎች አለባበስ የተለመደ መሆን አለበት፡፡

የቃለ መጠይቅ አቀራረብ


 አንድ ቃለ መጠይቅ ሲቀርብ በቃለ መጠይቅ አድራጊውና ተጠያቂ መካከል ያለው መቀራረብ (ግንኙነት) ወሳኝ ነው፡፡
 ቃለ መጠይቅ አድራጊው ጥሩ ሪፖርት ይኖረው ዘንድ የሚከተሉትን ማስታወስ አለበት፡-
 ቃለ መጠይቅ አድራጊው በትህትና ማንነቱንና ምን እንደሚሰራ በተጨማሪም ጥናቱ ስለምን እንደሆነ
ለተጠያቂው መንገር ይጠበቅበታል፡፡
 ቃል ሰጪው እንዴት እንደተመረጠና በመጠየቁም ጉዳት የሌለው መሆኑን መናገር፡፡
 በመጀመሪያ አስጨናቂ ጥያቄዎችን አለመጠየቅ፡፡
 በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ መጠይቅ ካስፈለገም ጥያቄውን መድገም እንዲሆም መላሹ ጥያቄውን መረዳቱን
ማረጋገጥ፡፡
 ለመላሹ የመመለሻ በቂ ጊዜን መስጠት (ሆኖም በጣም እንዳያጓትተው ብዙ ዕድል አለመስጠት)
 ለጥያቄው መልስ ሐሳብ ለመስጠት አለመምከር፡፡
 የመደነቅ፣ የመናደድ ወይም የመደንገጥና ወዘተ ምዕልክት አለማሳየት፡፡
 ግልጽ የማይመስሉ መልሶች ላይ ማስታወሻ መያዝና ካስፈለገም ማብራራያ መጠየቅ፡፡
 ከመጀመሪያው ጥያቄ መልሱ ወጣ ካለ ወደ ርዕሰ ጉዳዩ ለመመለስ የተለያ ስልቶችን መጠቀም፡፡

ቃለ መጠይቅ አዘጋገብ
 ቀጠሮ ከመያዙ በፊት ከባለሥልጣናት በኩል ያሉ እንቅፋቶች መወገዳቸውን ማረጋገጥ፡፡ ደብዳቤም መያዝ ጥሩ ነው፡፡
 ለቃል ሰጪውም የሚመች ጊዜ መመረጥ አለበት፡፡

3.3.3.3. የቃለ መጠይቅ ጠንካራና ደካማ ጎን

ጠንካራ ጎን(ጥቅሙ)
 የበለጠና ጠለቅ ያለ መረጃ ሊገኝ ይችላል፡፡
 ቃለ መጠይቅ አድራጊዎች በራሳቸው ክህሎት ቃል ሰጪዎች መልስ ከመስጠት እንዳይቆጠቡ ያደርጋል፡፡
 ጥያቄን እንደገና የማጠናቀር ዕድል አለ፡፡
 በዚህ ዘዴ ግለሰባዊ መረጃዎች በቀላሉ ይገኛሉ፡፡
 የተጠያቂዎቹን የቋንቋ ችሎታ፣ መጠንና የትምህርት ደረጃ ከግምት ውስጥ ያስገባ በማድረግ የጥያቄው በሌላ በኩል
የመተርጎም ሁኔታን መቀነስ ይቻላል፡፡

ደካማ ጎን (ጉዳቱ)
 በቃለ መጠይቅ አድራጊዎችና በቃል ሰጪዎች መካከል አድሏዊነት ሊንፀባረቅ ይችላል፡፡
 አንዳንድ ግለሰቦችን በዚህ ዘዴ ለማግኘት አዳጋች ስለሚሆን መረጃ አሰባሰቡንበቂ እያደረገውም፡፡
 መላሾችቃ፤ መጠይቁን አስደሳች ለማድረግ የማይጨበጥ መረጃ እስከመስጠት ሊደርሱ ይችላሉ፡፡

3.3.4. ምልከታ (Observation)

3.3.4. ውስን የቡድን ውይይት (Focus Group Discussion)

19
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
3.4. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ መሰብሰቢያ
 ሁለተኛ ደረጃ የምንላቸው በሌላ ሰው ከዚህ በፊት የተሰበሰቡና የተተነተኑ መረጃዎች ሆነው ምንጮቹ የታተሙ
ወይም ያልታተሙ ጽሑፎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
 ጥቅሞቹ፡-
 ጊዜና ገንዘብን ይቆጥባል

 መረጃው ግላዊነትን ይቀንሳል


 የማወዳደር ትንታኔን ያቀላል
 ችግሮቹ፡-
 አጥኚው የሚፈልጋቸው አንዳንድ መረጃዎች ላይገኙ ይችላሉ
 የመጀመሪያው አጥኚ ያልተገነዘበው የመረጃ ስህተት ሎኖር ይችላል፡፡
 አጥኚው ማጥናት ለሚፈልገው ችግር መረጃው ተስማሚ ወይም በቂ ላይሆን ይችላል፡፡
 የሁለተኛ ደረጃን መረጃ ስንጠቀም የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ይገባል፡-
1/ የመረጃ አስተማማኝነት
ይህንንም ለማረጋገጥ፡-
 መረጃውን ማን ሰበሰበው
 የመረጃው ምንጮች ምን ምን ናቸው
 በትክክለኛ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ነው የተሰበሰበው
 መች በየትኛው ዘዴ ተሰበሰበ
 በሰብሳቢው ላይ አድልዎ ነበር ወይ
 የተፈለገው የጥራት ደረጃ ተገኝቶ ነበር ወይ
የሚባሉትን ጥያቄዎች ማጤን ያስፈልጋል፡፡
2/ የመረጃው ተስማሚነት
 መረጃው ለጥናቱ ተስማሚ ላይሆን ስለሚችል ይህንን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡
3/ የመረጃው በቂነት
 በአጥኚው የተሰበሰበው መረጃ ከሚያጠናው ጥናት ጋር አብሮ የማይሄድ ከሆነ መረጃው ብቃት
ስለሌለው መጠቀም የለበትም፡፡
 አንድ አጥኚ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዴን ለመመረጥ ሲያስብ የጥናቱ ሥፍትና ዓላማ፣ የገንዘብ
አቅም፣ የጊዜ ሁኔታና የሚፈለገው ጥራት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
3.5. የመረጃ ትንተና

3.5.1. መረጃ ማሰናዳትና መተንተን


 አንድን ጥናት በተጠናከረ መንገድ ለመፃፍ የተሰበሰቡት መረጃዎች በአግባቡ መተንተን ይኖርባቸዋል፡፡
 ከልዩ ልዩ ሰነዶች፣ በጽሑፍ መጠየቅ፣ በቃለ መጠይቅ፣ በምልክት ወይም በሌሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ጥናቱ
ከሚፃፍበት ዓላማ ወይም መላምት ጋር ተገናዝበው በቅደም ተከተል በጥንቃቄ መተንተን ይኖርባቸዋል፡፡
 አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚያደርገው
ትንታኔንና ትርጉምን እንጂ ጥሬ የሆነ መረጃን በማቅረብ ብቻ አይደለም፡፡
ስለሆነም የጥናትን ግኝቶችን በጥንቃቄ ለመተንተንና ለመተርጎም የሚከተሉትን ነጥቦች መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

20
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

 በተቻለ መጠን አስተያትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየትና አንዱን ከሌላ ጋር አለማጋጨት፡፡


 የምርምሩን ወሰን አለመዘንጋትና ከጥናቱ ወሰን ዘሎ ወደሚሄድ ትንታኔ ወይም ትርጉም ውስጥ አለመግባት፡፡
 የተሳሳተ ትንታኔ ወይም ትርጉም አለመስጠት፡፡
 ከአጥኚው ወይም ከዘመኑ አስተሳሰብ ጋር የሚቃረን ግኝት ካለ ያንን አለማስቀረት፤ ልዩ ለውጥ አለማድረግ፡፡
 ግኝቶችን መተንተን ለጥናት የማይሆኑ የስታትስቲክ ስልቶች አለመጠቀም፡፡ አግባብነት ያላቸውን አሀዛዊ መረጃዎች
በሰንጠረዥ፣ በግራፍና በሌሎችም መንገዶች በመጠቀም ከሙሉ ትንታኔ ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 በትንተና ወቅት የሚወዳደሩና ሊወዳደሩ የሚችሉትን ብቻ ማወዳደር፡፡
 በአጠቃላይ አሀዛዊ የጥናት ዘዴን በመጠቀም በአግባቡ መተንተንና ተገቢ ስልቶችንም መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

3.5.2. የምርምሩን ውጤት ግንዛቤ ማስቀመጥ


 በምርምሩ ስለተገኙት ግኝቶች አጠቃላይ ግንዛቤ ሲሰጥ፡-
 ስለግኝቶቹ የሚሰጠው አጠቃላይ ግንዛቤ በጥንቱ ዓላማና በሚገኘው መረጃ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡
 ስለግኝቶቹ አጠቃላይ ግንዛቤ በጠንካራ ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ እንጂ በትንሽ ፍንጭ ላይ የተመሠረተ መሆን
የለበትም፡፡
 በጥናቱ ውስጥ ባልነበሩት አዲስ ማስረጃዎች ላይ የተመሰረተ አጠቃላይ ግንዛቤ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 በስህተት ላይ በተመሠረተ ትንታኔና አተረጓጎም ላይ የተመሠረተ አጠቃላይ ግንዛቤ መሆን የለበትም፡፡

3.5.3. የምርምሩን (የጥናቱን) ፍሬ ነገር አሳጥሮ ማቅረብ


 ጥናቱን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አንባቦ ለመረዳት ጊዜ ስለማይኖርና አንባቢያን ባላቸው ጥቂት ጊዜ ውስጥ
የጥናቱን ፍሬ ነገር ለማወቅ መፈለጋቸው የጥናቱን ፍሬ ነገር አሳጥቶ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ስለሆነም
በተቻለ መጠን የጥናቱ ዓላማ በአጭሩ ማስቀመጥና እንዲሁም ዓበይት የሆኑትን ግኝቶች በአጭሩ ማስፈር ተገቢ
ይሆናል፡፡

3.5.4. የመፍትሔ ሀሳቦች መስጠት


 አንድ ጥናት የሚጠናው ለተወሰነ ችግር መፍትሔ ለማግኘት ነው፡፡
 አጥኚውም በአገኘው መረጃ ላይ መመርኮዝ የመፍትሔ ሃሳቦችን ማስቀመጥ አለበት፡፡
 መፍትሔው ከራሱ የሚመነጭ ሳይሆን መረጃ በተሰበሰበበት ወቅት ከሚገኘው ጥቆማ ነው፡፡
 የመፍትሔ ሀሳቦች በሚሰጡበት ጊዜ በሚገባ መገንዘብ የሚገባው የሚሰነዘሩት የመፍትሔ ሃሳቦች ባለው ተጨባጭ
ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን ነው፡፡

21
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

ክፍል አራት

1. የጥናታዊ ጽሑፍ አጠቃላይ ይዘት

4.1. የጥናታዊ ጽሑፍ ሽፋን ይዘት

1 ኛ. በገጹ አናት ላይ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


የሚል ይሰፍራል፣

2 ኛ. ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ሙሉ ሥም ጋር ጥናቱ የሚቀርብለት ክፍል ይጠቀሳል፣

3 ኛ. የጥናቱ ርዕስ ይከተላል፣

4 ኛ. የአጥኚው ሙሉ ሥም በስተግራ በኩል ጫፍ ላይ ይሠፍራል፡፡ አዘጋጅ ከላይ


ሙሉ ስም ከታች

5 ኛ. የአማካሪው ሙሉ ሥም በስተቀኝ በኩል ጥግ ላይ ይሆናል፡፡ አማካሪ ከላይ


ሙሉ ስም ከታች

6 ኛ. በመጨረሻም ጥናቱ አልቆ የተረከበበት ወርና ዓ.ም. በስተቀኝ በኩል ከታችኛው ገፅ ሥር


በጥግ ቦታ ላይ ይቀመጣል፡፡ (ምሳሌ፡- ነሐሴ 2010 ዓ.ም.)

4.2. የመጀመሪያ አባሪ መረጃዎች ይዘት

ምሥጋና፣ መክሰት አርዕስት (የአርዕስት ማውጫ)፣ የሠንጠረዥ ማውጫና ምህፃረ ቃላት እነዚህን በተመለከተ በክፍል ሁለት ላይ
በቀረበው መሠረት በቅደም ተከተላቸው በየገፅ በየገፃቸው ይሰፍራሉ፡፡ ገፃቸውም የሮማን ቁጥርን በመጠቀም ይገለፃሉ፡፡ እንጂ
ከዋናው ጽሑፍ ጋር ተጠቃሎ የገጽ ጽሑፍ አይሰጣቸውም፡፡

4.3. የምዕራፍ አንድ - የጥናቱ ዕቅድ ይዘት

 በመቀጠልም በክፍል ሁለት ትምህርታችን ውስጥ በንዑስ ክፍል 2.2.2. ላይ በሰፈረው መሠረት በቅደም ተከተላቸው በዝርዝር
ይገለፃሉ፣

 የመጀመሪያ አባሪ መረጃዎች ካጠናቀቁ በኋላ በአዲስ ገፅ ላይ ምዕራፍ አንድ በሚል ከሥሩ ዓበይት ርዕስ የሆነው የጥናቱ
ዕቅድ ይቀመጣል፡፡

 ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ ዋና ጽሑፍ ስለሆነ የገጽ ቁጥር መሠጠት ይጀምራል፡፡

22
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

4.4. የምዕራፍ ሁለት - የተዛማጅ ጽሑፍች ዳሰሳ ይዘት

- ምዕራፍ አንድ ሙሉ ለሙሉ ተብራርቶ ካለቀ በኋላ የሚቀጥለው ምዕራፍ ሁለት ነው፡፡ በአዲስ ገጽ ላይ ይጀምራል፡፡
- ስለዚህም ምዕራፍ ሁለት በሚል ከሥሩ ዓበይት ርዕስ የሆነው የተዛማጅ ጽሑፎች ዳሰሳ ይቀመጣል፡፡
- የራሱ የሆነ መግቢያ ይኖረዋል፡፡ /መጠኑም ቢበዛ ግማሽ ገፅ ሆኖ በአንድ አንቀጽ ይገለፃል፡፡/
- በዚህ ዓበይት ርዕስ ውስጥ ከርዕሱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ቀደምት ሥራዎች የሚዳሰሱበት ምዕራፍ ነው፡፡
- የተዛማጅ ጽሑፎች ዳሰሳ ሲዘጋጅ በትንሹ ከሥምንት/8/ ያላነሱ ከጥናቱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ጽሑፎችን መጠቀም
የግድ ይላል፡፡
- ይህንን ምዕራፍ ስናዘጋጅ ከተለያዩ ተዛማጅ ጽሑፎች የምናገኛቸውን ሀሳቦች ማለትም ከጥናታችን ጋር ተያያዥነት
ያላቸውን ማለት ነው እነዚህን ሀሳቦች ስናሰፍር በየአዲስ መስመሩ መጀመሪያም ይሁን ጨረሻ ላይ በቅንፍ ውስጥ የደራሲው
ሙሉ ስም፣ ፅሑፍ የተገኘበት ገፅ አና ደራሲው ያሳተመበት ዓ.ም. የግድ መሥፈር ይኖርበታል፡፡ /ምሳሌ፡- ዲ/ን ዳንኤል
ክብረት፣ ገፅ 20-21፣ 2006 ዓ.ም./

4.5. የምዕራፍ ሦስት - የመረጃ ትንታኔ ይዘት

- የምዕራፍ ሁለት አጠቃላይ ሀሳብ ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕራፍ ሦስት በሚል ከሥሩ ዓበይት ርዕስ የሆነው የመረጃ ትንታኔ
ይቀመጠጣል፡፡
- የዚህ ምዕራፍ ይዘትም፡-
1. 3.1. በሚል ንዑስ ርዕስ የመረጃ ምንጮች፣ የአሰባሰብ ሁኔታው እና የትንታኔው ዘዴ አጠቃላይ ምልከታ በሚል መግቢያ
ይኖረዋል፡፡
- በዚህ ንዑስ ርዕስ ውስጥም ከጥናቱ ርዕስ ጀምሮ ዓላማውን በመግለፅ እንዲሁም መረጃ ለመሰብሰብ
የተጠቀምንባቸውን የመረጃ ምንጮች እና በተጨማሪም ለተጠቃሚዎች የተበተነው የመጠይቅ ብዛት ተገልፆ
የአሰባሰብ ሁኔታውም በመቶኛ ይገለጣል፡፡ በመጨረሻም የመረጃ አተናተን ዘዴው እንዴት ሊሆን እንደሚችል
በአጭሩ የሚገለፅበት ንዑስ ክፍል ነው፡፡
2. 3.2. በሚለው ንዑስ ክፍል ውስጥም ከመጠይቅ የተገኙ የመረጃዎች ትንታኔ በሚል ርዕስ ተጠቅመን ሁለት ሌሎች
ርዕሶችን እንገልፅበታለን፡፡
- 3.2.1. በሚል ንዑስ ርዕስ የመላሾች የግል ማህደር መግለፅ ይኖርብናል፡፡
- 3.2.2. በሚል ንዑስ ርዕስ ውስጥም ተጠያቂዎች በጥናቱ ርዕስ ዙሪያ በመጠይቁ መሠረት የተሰጡ ምላሾች በሚል
ወደ ጥያቄዎች መልሶቻቸው እንገባለን፡፡
- ጥያቄዎቹንና መልሶቻቸውን መሠረት በማድረግ ሰንጠረዥን በመጠቀም በመቶኛ በመግለፅና በመተንተን
እያንዳንዱን ጥያቄ በዚህ መልክ እየሰራ እንሄዳለን፡፡

ምሳሌ፡-

23
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

የመላሾች የመልሱ ዓይነት


ተ.ቁ. ጥያቄ
ዓይነት ይጠቅማል አይጠቅምም መልሱ ያልሰጡ
80% 15% 5%
ተማሪ
100% - -
መምህር

4.6. የምዕራፍ አራት - የጥናቱ መደምደሚያ ይዘት

ይህ ምዕራፍ በውስጡ አራት/4/ ንዑሳን ክፍሎች ይኖሩበታል፡-


1. መግቢያ(Introduction)
2. ግኝቶች (Findings)
2.1. ጠንካራ ጐኖች(Strenth)
2.2. ደካማ ጐኖች(Weakness)
3. ማጠቃለያ(Conclusion)
4. የመፍትሔ ሀሳብ(Recommendation)

1. መግቢያ(Introduction)
- ምዕራፍ አራት 4.1. በሚል ንዑስ ርዕስ መግቢያ ይኖረዋል፡፡
- የመግቢያው ይዘትም፡-
- የምዕራፍ ይዘት መሠረት ያደረገው ምዕራፈ ሦስትን የመረጃ ትንታኔ መሠረት ያደረገ መሆኑን መግለፅ፣
- ከትንታኔው ውስጥ የተገኙትን መልሶች በጠንካራና ደካማ ጐናቸው በመለየት በግኝት ውስጥ ማስፈር፣ ከግኝቱም በመነሳት
የማጠቃለያና የመፍትሔ ሀሳብ እንደሚዘጋጅ ማስገንዘብ፡፡

2. ግኝቶች (Findings)
- ግኝቶች የሚባሉት ከመረጃ ትንታኔ ከመላሾች የተገኙ ጠንካራና ደካማ ጐኖችን(አስተያየቶችን) ማለት ነው፡፡
- እነዚህ ዓኝቶችም 4.2 በሚል ንዑስ ርዕስ ግኝቶች በማለት ይሰወራል፡፡
- የተገኙትንም ጠንካራና ደካማ ጐኖች፡-
 ጠንካሮቹን ጐኖች(አስተያየቶችን)ጠንካራ ጐኖች በሚል ርዕስ ውስጥ ማስፈር፣
 ደካማ ጐኖችን(አስተያየቶችን)ደካማ ጐኖች በሚል ርዕስ ውስጥ ማስፈር፡፡

3. ማጠቃለያ(Conclusion)
- አንድ ጥናት ያተኮረበት ችግር እንዴት ሊፈታ እንደሚችልና በምን ዓይነት መንገድ ሊጠቃለል እንደሚችል የሚገለፅበት ክፍል
ነው፡፡
- ማጠቃለያ የጥናታዊ ሥራ ግብ መግለጫ ስለሆነ ዝግጅቱ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡
- በግኝቶች ውስጥ የሰፈሩትን የጠንካራና የደካማ ጐኖችን ተጨባጭ መረጃዎችን መሠረት ባደረገ የማጠቃለያ ሥራ ይሠራል፡፡

4. የመፍትሔ ሀሳብ(Recommendation)

24
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

- በማጠቃለያው ላይ የተነሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ለወደፊቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚመከርበትን፣ ትኩረት እንዲደረግ
የሚጠቆምበትን እና እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቢያ የሚሰጥበትን ሀሳቦች በመጥቀስ የመፍትሔ ሀሳብ ማዘጋጀት
ይጠበቅብናል፡፡

- የመፍትሔ ሀሳብ ሲዘጋጅም የሚከተሉትን ነጥቦች መሠረት ማድረግ ተገቢ ነው፡-


1. በመፍትሔ ሀሳብነት የሚቀርበው ሀሳብ ተግባራዊ መሆን የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
2. መፍትሔ ሀሳቡ የተነባቢነት እንዲሆን እጥር ምጥት ብሎ መቅረብ አለበት፡፡
3. የመፍትሔ ሀሳቡ ለመጨረሻ ውሳኔ ሀሳብ መስሎ መቅረብ የለበትም፡፡ (የአጥኚው ቋንቋ ላላ ማለት ይኖርበታለ፡፡)

4.7. የዋቢ መጻሕፍት አጠቃቀም ይዘት

- ዋቢ መጽሐፍት የምንላቸው ጥናቱ በተካሄደበት ጊዜ ሃብ ለማስተካከልና ጥናታዊ ጽሁፉን ፈፃሜ ላይ ለማድረስ አገልግሎት
የሰጡ መጽሐፎች፣ መዛግብተ ቃላት፣ አውደ ጥናቶች፣ መጽሔቶች፣ ጋዞጦች፣ ሰነዶችና ማስታወሻዎች ወዘተ…
የመሳሰሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ እነዚህም በዝርዝር የአደራደር ሥርዓት ይዘው በጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ ይቀርባሉ፡፡
የአደራደሩን ሥርዓት በጥልቀት በምሳሌ ከማሳየታችን በፊት ስለአደራደሩ ሥርዓት አጠቃላይ መርህ በአጭሩ እንደሚከተለው
ይቀርባል፡፡

የዋቢ መጻሕፍት የአደራደር ሥርዓት አጠቃላይ መርህ

1. ዋቢ ጽሑፎች በፊደል ተራ ቅደመ ተከተል መደርደር ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ የደራሲው ሥም በተጠቀሰበት ሥራ ውስጥ የደራሲው
ሥም የመጀመሪያ ፊደል፤ የደራሲው ሥም ባልተገለፀበት ሁኔታ ደግሞ የርዕሱ የመጀመሪያ ፊደል ለአደራደሩ ተቀዳሚ ሆኖ ያገለግላል፡፡

2. ዋቢ ጽሑፎች በፊደል ተራ ቅደም ተከተል ሲደረደሩ በአንድ ደራሲ የተፃፉ ቁጥራቸው በርካታ መጽሐፍት ሲያጋጥሙ አሮጌውን ሥራ
በማስቀደም በኀትመት ዘመናቸው ወይም በርዕሳቸው ፊደል ቅደም ተከተል መደርደር ይገባል፡፡

3. በአደራደሩ ሂደት የአውሮፖዊ ስም ሲያጋጥም የመጨረሻው (የቤተሰብ ሥም) በቅድሚያ የወሰድና የሥሙ የመጀመሪያ ፊደል
ለአደራደሩ ቀዳሚ ይሆናል፡፡ ሆኖም በአህፅሮት ማስፈር አይፈቀድም፡፡

4. በሁለት አውሮፖዊያን ደራሲያን የተጻፈ ከሆነ የመጀመሪያው ደራሲ ሥም ከላይ በ3 በተቀመጠው ሥርዓት መሠረት ይቀርባል፡፡
የሁለተኛው ደራሲ ሥም ገን እንዳለ ይፃፋል (የቤተሰብ ሥም አይቀድምም)፡፡

5. ጽሑፉ በሶስትና ከዚያ በላይ ደራሲያን የተፃፈ ከሆነ የመጀመሪያው ደራሲ ሥም መውሰድና በ3 በተጠቀሰው መሠረት ማስቀመጥ
የሚለውን አፅርዎት ማስከተል፡፡ ደራሲያኑ ኢትዮጵያዊያን ከሆኑ ደግሞ እገሌና ሌሎች ብሎ ማመልከት ይቻላል፡፡

6. የመዘርዝሩም አፃፃፍ በስተግራ በኩል ካለው ህዳግ የተነሣው የመጀመሪያ መስመር በስተቀኝ ካለው ህዳግ መግቻ ላይ ያበቃል፡፡ ተከታታዩ
መስመር ግን የመጀመሪያው መስመር ከደመረበት አምስት ፊደል ቦታ ገባ ብሎ መጀመር አለበት፡፡

7. ዋቢ ጽሑፎች ሲደረደሩ በተዋረድ በድርብ ክፍተት(Double Space) መስፈር አለባቸው፡፡

8. በዋቢ ጽሑፎች አደራደር ሂደት የደራሲ ሥም፣ ዓመተ ምሕረት፣ ርዕስ ወዘተ… ቅደም ተከተለ አንድ ወጥ አይደለም ይህም የሆነበት
የተለያዩ የአደራደር ሥልቶች(ሥርዓቶች) ስላሉ ነው፡፡

25
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር
ምሳሌ፡- ኢትዮጵያዊ ደራሲ
1. የሀርቫርድ ሥርዓት
ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡(1980)የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

2. የAPA ሥርዓት
ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ (1980)የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

3. የMLA ሥርዓት
ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣(1980)

4. የThe Chicago Manual of Style ሥርዓት


ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ (1980)የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

ከዚህ ቀጥለው የሚቀርቡት ምሳሌዎች በተለይ በአንደኛው ደረጃ ላይ የተጠቀሰውነ የአሰፋፈር ሥልት መሠረት ያደርጋሉ፡፡

በአንድ ደራሲ የተጻፈ መጽሐፍ

ኢትዮጵያዊ ደራሲ፡-ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ

ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ (1980)የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

ደራሲ Bahiru Zewde


Bahiru Zewde (1991) A History of Modern Ethiopia Addis Ababa University Printing Press.

አውሮፖዊ ደራሲ፡- Helen Megrath

Megrath, H. (1998) All about Food. Great Britain: Oxford University Press.

ደራሲ፡- Jhon W-Best

Best, J.W. (1981) Research in Education.New Delhi; Printice Hall Ince.

26
ጥናትና ምርምር
ጥናትና ምርምር

በሁለት ደራሲያን የተጻፈ መጽሐፍ

ኢትዮጵያዊያን ደራሲያን

የደራሲዎች ሥም፡- ሥዮም ተፈራና አየለው ሺበሺ

ሥዩም ተፈሪና አየለው ሺበሺ (1982)አጭር የምርምር ዘዴ፡፡ አዲስ አበባ፣ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፡፡

አውሮፖዊያን ደራሲያን

ደራሲዎች፡- Frank Kerecks and Robley Winfrey Kereck,F, and Robley, W (1951) Report Preparation: The lwoa State
College Press.

በሦስትና ከሶስት በላይ ደራሲያን የተጻፉ መጽሐፍት

የደራሲዎች፡- መሥፍን ሀብተማርያም፣ አዳምረታ፣ አበራ ለማ፣ ገበየሁ አየለ፣ ሰለሞን ለማ፣
ሙሉነህ መንግሥቱ

መሥፍን ሀብተማርያምና ሌሎች (1977)አባደፋርና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች፡፡ አዲስ አበባ፣ ኩራዝ አሳታሚዎች
ድርጅት

በአንድ ደራሲ የተጻፉ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መጻሕፍት

ደራሲ፡- ሀዲስ ዓለማየሁ


ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ (1960)ፍቅር እስከ መቃብር፡፡ አዲስ አበባ፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

(1980)የልምዣት፡፡ አዲስ አበባ፣ ንግድ ማተሚያ ቤት፡፡

4.8. የመጨረሻ አባሪ መረጃዎች ይዘት

- ዋቢ መጽሐፍት፣ የጽሑፍ መጠይቅ፣ የቃለ መጠይቅ/ካለ/ እና የመረካከቢያ ሰነድ ሲሆኑ እነዚህም በቅደም ተከተላቸው
የሮማን አሀዝ በመጠቀም በተለያዩ ገፆች ላይ ይሰፍራሉ፡፡ እንጀ ከዋናው ጽሑፍ ጋር ተጠቃሎ የገፅ ጽሑፍ አይሰጣቸውም፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

27
ጥናትና ምርምር

You might also like