Professional Documents
Culture Documents
GMAN
GMAN
የማለት መብት
በዚህ አጭር ጽሁፍ የይዞታ ትርጉም ምን እንደሆነ፣
ይዞታን መሰረት ያደረገ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በምን
አግባብ ሊቀርብ እንደሚችልና ይህ ክስ ከባለቤትነት
ክርክር ጋር ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ፣ ሁከት
ይወገድልኝ የሚል ክስ ሲቀርብ ፍርድ ቤቶች የሚይዙት
ጭብጥ በተመለከተ ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት
ትርጓሜው ምን እንደሆነና ቀዳሚ የመግዛት መብት
ካለው መሀከል ባልና ሚስትን፣ ወራሾችን በተመለከተ
በህጉ ሊስተናገዱ የሚችሉበት አግባብ ለማየት
ተሞክሯል፡፡ በስተመጨረሻም የቅድሚያ ግዥ መብት
ያለው ሰው በሚገዛበት ጊዜ ስላለው የሽያጭ ስነ-ስርዓት፣
ግድግዳና ጣራቸው በአንድ በኩል የተያያዙ ቤቶችን
በተመለከተ በቅድሚያ ግዥ መብት ሊስተናገዱ
የሚችሉበት የህግ አግባብና የዘመዶች በቅድሚያ
የመግዛት መብትን እስመልክቶ በጽሁፍ በወፍ በረር
ቅኝት ተደርጎበታል፡፡
1/ የይዞታ ትርጉም፡-
በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1140 ላይ እንደተጠቀሰው
ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ
በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ከዚህ ድንጋጌ
መገንዘብ እንደሚቻለው ይዞታ ማለት አንድ
የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት አሻሚ ወይም
ድብቅ ባልሆነ ሁኔታ በቁጥጥር ስር በማድረግ ሊያዝበት
የሚቻል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ንብረቱን በቁጥጥር ስር
ማድረግ ብቻ ሳይሆን መጠቀምና መገልገልን የሚጨምር
መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ንብረቱን በእጁ አድርጎ
በእውነት የሚያዝበት ሊሆን ይገባል ማለት ንብረቱን
በእጁ አድርጎ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ንብረት ላይ
በእውነት ማዘዝ እንዲችል የንብረቱ አያያዝ
ያልተጭበረበረና በማንኛውም መንገድ ህገ ወጥ በሆነ
ሁኔታ ያልተገኘ መሆን እንደሚገባው ነው፡፡ በዚህ
መልኩ ንብረቱን ይዞ የሚገለገል ሰው በይዞታው ላይ
የመንጠቅ ሆነ የሁከት ተግባር ተፈጽሞበት እንደሆነ
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1149(1) መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ
ለማቅረብ መብት ይኖረዋል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ መሟላት ያለባቸው
ፍሬ ጉዳዮች
1) ሁከት የተፈጠረበትን ንብረት ባለይዞታው በእጁ
አድርጎ በእውነት የሚያዝበት መሆኑን፡፡
2) የይዞታ ክስ የሚቀርበውም ለክርክሩ መነሻ የሆነውን
ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም አይነት መብት በሌለው
ሰው ላይ ስለመሆኑ፡፡
3) ሁከት ፈጻሚው በሀይል ተግባር ወይም በሚስጥር
ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን የሚያረጋግጡ ፍሬ ጉዳዮች
ናቸው፡፡ በአንድ በፍርድ ቤት በነበረ ክርክር ገዥው
ንብረቱን የገዙበት የሽያጭ ውል ተገቢውን የአጻጻፍ ስነ-
ስርዓት ያልተከተለ ሆኖ ሳለ ገዥ በዚህ ሽያጭ ውል
የገዙት ቤት ላይ ሻጭ የሁከት ተግባር እየፈጸመ
ስያስቸገራቸው ሁከቱ እንዲወገድ ክስ መስርተዋል፡፡
ሻጭም ገዥ ይዞታውን የያዙበት ውል ተገቢውን
የአጻጻፍ ስነ-ስርዓት የተከተለ ስላልሆነ ይዞታውን
በእውነት የሚያዝበት አይደለም በማለት የሁከት
ይወገድልኝ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ሲል ተከራክሯል፡፡
ይህ ክርክር የህግ ትርጓሜ ያስፈልገዋል በሚል
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበ
ሲሆን ችሎቱም በቅጽ 9 በሰ/መ/ቁ 36645 በአብላጫ
ድምጽ በሰጠው ውሳኔ “ይዞታው የተላለፈበት ውል
የአጻጻፍ ጉድለት አለበት ከተባለ በንብረቱ መብት አለን
የሚሉ ሰዎች ውሉ ፈራሽ ነው እንዲባል የክስ ምክንያት
ከሚሆናቸው በስተቀረ ሁከት ይወገድ ተብሎ በሚቀርብ
ክስ ላይ ሊስተናገድ የሚያስችል አይደለም” በማለት
ገዥው ንብረቱን ከሻጭ ጋር ባደረጉት ውል መሰረት
ይዘው እያለ ሻጭ ሁከት እየፈጠረብኝ ነው በማለት
የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ተቀባይነት
ከውሉ አፈጻጸም ጉድለት ተለይቶ ሊስተናገድ ይገባዋል
በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡ በልዩነት የቀረበው
ሀሳብ ላይ “በውሉ መሰረት ንብረቱን በገዥ ስም
እስካላዞረ ድረስ ሻጭ ባለንብረት ተደርጎ ስለሚወሰድ
የንብረቱ ባለይዞታ የሆነው ገዥ ሰፊ የሆነውን
የባለቤትነት መብት ያለውን ሰው ሁከት ፈጥሮብኛል
ብሎ ሊከስ አይገባም፡፡ የይዞታ መብት ለማስከበር
የሚቀርብ ክስ የንብረቱ ባለቤት ሳይሆኑ በይዞታ ጣልቃ
የሚገቡ ሌሎች ሰዎችን ለማስቆምና ለመከላከል
የሚቀርብ የክስ አይነት ነው በማለት በልዩነት ወስኗል፡፡
እንደዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ሚዛን የሚደፋው ክርክር
በአብላጫ ድምጽ የተወሰነው ውሳኔ ነው የሚል አቋም
አለኝ፡፡ ምክንያቱም ባለይዞታው ምንም እንኳ ይዞታውን
የያዘው የአጻጻፍ ስነ- ስርዓቱን ባልተከተለ ውል ቢሆንም
በዚህ መልኩ ይዞታውን በመያዙ በእውነት አያዝበትም
ለማለት አያስችልም፡፡ ይህ ውል ተገቢው የውል ክርክር
ቀርቦበት እስካልፈረሰ ድረስ ባለ ይዞታው ይዞታውን
በተገቢው መንገድ ይዟል ከማለት በስተቀረ ውል
ባልፈረሰበት ሁኔታ ባለይዞታው በይዞታው ላይ
ለሚፈጠው የሁከት ተግባር ክስ ሊያቀርብ አይችልም
ሊባል አይገባም፡፡ ሻጭ የሆነ ወገን ይዞታውን በማይጸና
ውል ነው ለገዥ የሸጥኩት ካለም መብቱን
የሚያስከብረው የሁከት ተግባር በመፍጠር ሳይሆን
ተገቢውን የውል ክርክር በማቅረብ ነው፡፡ ተገቢ የሆነ
የውል ክርክር አቅርቦ በመካከላቸው ያለው ውል
እንደዲፈርስ ባላተደረገበት ሁኔታ በሻጭ የሚፈጸሙ
ተግባሮች በጸና ውል ከእርሱ የተሻለ መብት ባለው ሰው
ላይ እየተፈጠረ ያለ የሁከት ተግባር በመሆኑ በገዥ
የቀረበው ክስ ተገቢ ነው የሚል አቋም አለኝ፡፡
የይዞታና የባለቤትነት ክርክሮች
መደምደሚያ
ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ
በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ከዚህ መገንዘብ
እንደሚቻለው ይዞታ ማለት አንድ የሚንቀሳቀስም ሆነ
የማይንቀሳቀስ ንብረት አሻሚ ወይም ድብቅ ባልሆነ
ሁኔታ በቁጥጥር ስር በማድረግ ሊያዝበት የሚቻል
ማለት ነው፡፡ የይዞታና ባለቤትነትን የሚመለከቱ ጉዳዮች
የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የሚሸፈኑት በተለያዩ
የሕግ ድንጋጌዎች ነው፡፡ ለአብነት ያህል አንድ ሰው
ባደረገው የኪራይ ውል ሰበብ ቤቱን በሀይል ይዞ
ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ኪራዩን ከፍሎ ቤቱን
እንዲለቅቅ በሚል የሚያቀርበው አቤቱታ ባለሀብት
የሆኑትን ቤት ለማስለቀቅ የቀረበ የመፋለም ክስ እንጂ
የይዞታ ክርክር አይደለም፡፡ በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል
የማለት መብት ማለት ዋጋን በመክፈል የአንድ ንብረት
ሀብትነት ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባይነትን በአንዳንድ
ምክንያቶች የሚገዛውን ሦስተኛ ወገን ለማስለቀቅ ለአንዱ
ሰው የተሰጠ መብት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
Source: - MULUKEN SEID HASSEN (LAWYER)
EDITED G-MAN