43327

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የሰበር መ/ቁ 43327

የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም


ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ
መንበረፀሐይ ታደሰ
ሂሩት መለሰ
ብርሃኑ አመነው
አልማው ወሌ
አመልካች፡- 1/ አቶ ታመነ ጌታቸው
ጠ/ፍቅሬ ሞያ ቀረቡ
2/ ወ/ሮ ብርሃኔ አበበ
ተጠሪዎች፡- 1/ሰንራይዝ የኢንዱስትሪ ሥራ ኮንስትራክሽንና የንግድ አገልግሎት በኢትዮጵያ
ሃ/የተ/የግ/ማ
2/ አቶ ዳዊት ወዳጆ ደባይ
መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡
ፍርድ
የሰበር አቤቱታ የቀረበው የአክሲዮን ማህበር እንዲፈርስ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ በመደረጉ
ነው፡፡ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው ክርክር መነሻ የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ
በአክሲዮን ባለመብቶች መካከል አለመግባባት ስለተፈጠረ ማህበሩ ሥራውን መቀጠል አልቻለም
በሚል ምክንያት ማህበሩ እንዲፈርስ እና ሂሣቡ እንዲጣራ እንዲወሰን የሚል ነበር፡፡ በሁለተኛ ተጠሪ
በኩል የቀረበው ክርክር የአመልካቾች ድርሻ 3% ሦስት በመቶ ብቻ መሆኑን እና የሌሎች አባላት ድርሻ
97% ዘጠና ሰባት በመቶ/ ስለሆነም አንደኛ አመልካች በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ከሥራ አስኪያጅነት
እንዲነሳ መደረጉን ጠቅሶ ማህበሩ ሊፈርስ የሚያስች በቂ ምክንያት የለም በማለት ክሱ ውድቅ
እንዲደረግ አመልክቷል፡፡
የፌ/የመ/ደዳ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ በንግድ ሕግ ቁ 542(1) መሠረት
ማህበሩን ለማፍረስ የሚያበቃ በቂ ምክንያት የለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡
ይግባኝ የቀረበለት ፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን ሰርዟል፡፡ የሰበር አቤተታ ያቀረቡት
አመልካቾች ጠበቃ በማህበሩ አባላት መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ የተፈጠረ መሆኑን በጥቀስ ማህበሩ
እንዲፈርስ የቀረበው የዳኝነት ጥያቄ ውድቅ መደረጉ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ነው ሲሉ የሥር
ፍ/ቤቶች ውምኔ እዲሻር አመልክተዋል፡፡
ይህ ሰበር ችሎትም የአክስዮን ማህበሩ አይፈርስም የተባለበትን አግባብ ለመመርመር
ተጠሪዎችን አስቀርቧል፡፡ በመልሳቸውም የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በሕግ ረገድ የተፈፀመ ስሕተት
እንደሌለው አጥብቀው ተከራክረዋል፡፡
እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ አገናዝበን መርምረናል፡፡ አመልካቾች ሥር ፍ/ቤት
ያቀረቡት አቤቱታ በማህበሩ አባላት መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ ተፈጥሯል በሚል ማህበሩ እንዲፈርስ
እንዲወሰን የንግድ ሕግ ቁጥር 542(1) ጠቅሰው ዳኝነት መጠየቃቸውን መዝገቡ ያስረዳል በዚህ ረገድ
አመልካቾች ባለማስረዳታቸው እና አለ የተባለው አለመግባባት የ 1 ኛ አመልካች ከሥራ አስኪያጅነት
መነሳት ጋር በተያዘ ሆኖ የቀረበው ምክንያት ግን እንደሕጉ ይዘት በቂ ምክንያት ሊባል የሚያስችል
ባመሆኑ የሥር ፍ/ቤት የአመልካቾችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ተረድተናል፡፡
የአመልካቾች ጠበቃ ለሰበር ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት በሥር ፍ/ቤት ያልቀረበ የፍሬ ነገር
ክርክር ያነሱ ቢሆንም ዋነኛው መነሻ በአመልካቾች እና በ 2 ኛ ተጠሪ መካከል ብርቱ ጭቅጭቅ
ስለመኖሩ አጠናክሮ የተከራከረበትን መሠረት በማድረግ እንደተመለከትነው በግራ ቀኙ መካከል ፍ/ቤቱ
ጭቅጭቅ ነበር ወይስ አልነበረም የሚለው የፍሬ ነገር ክርክር አስመልክቶ በሥር ፍ/ቤት ይህንን
አመልካቾች ያላረጋገጡ መሆኑን በፍርድ ተረጋግጧል፡፡
በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠን ፍሬ ነገር በመቀበል በሕግ ረገድ
የተሳሳተ ስለመሆኑ ለመመርመር ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ ይህንን ከሕጉ ይዘት ጋር ማየት አግባብ
ሆኖ አግኝተናል፡፡
የተጠቀሰው የንግድ ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 542(1) በግልጽ እንደተመለከተው ማህበሩ እንዲፈርስ
የሚጠይቀው ወገን በቂ ምክንያት መኖሩን ማስረዳት እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ በዚህ ረገድ
ከአመልካቾች በቂ ምክንያት ስለመኖሩ ያላስረዱ መሆኑን ከላይ በዝርዝር ተመልክተናል፡፡
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ በሕግ ረገድ ስሕተት አለው
ለማለት የሚያስችል መሠረታዊ ምክንያት አላገኘንም፡፡
ስለዚህ የቀረበውን የሰበር አቤቱታ ባለመቀበል በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የተፈፀመ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡
ውሳኔ
የፌ/የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 115486 የሰጠው ፍርድ እና የፌ/ከፍተኛ ፍ/ቤት
በመ/ቁ 70504 የሰጠው ፍርድ ፀንቷል፡፡ የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ
ብለናል፡፡ መዝገቡን ዘግተን መልሰናል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት


ፀ/መ

You might also like