Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 4

የሰበር መ/ቁ 32269

ጥር 5 ቀን 2002 ዓ.ም

ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ

ሐጐስ ወልዱ

ሂሩት መለሰ

ታፈሰ ይርጋ

ዓልማው ወሌ

አመልካቾች፡- 1. ወ/ሮ ያለም ታፈረ ስብሐት

2. ወ/ሪት መነን ታፈረ ስብሐት

3. ተስፋዬ ታፈረ ስብሐት

4. ሰሎሞን ታፈረ ስብሐት ከጠበቃ መድህን

5. ወ/ሪት አፀደ ታፈረ ስብሐት መሐሪ ቀረበ

6. ወ/ሪት ንጉሣ ታፈረ ስብሐት

7. ወ/ሪት ሊሻን ታፈረ ስብሐት

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዓፈራ ሐዱሽ የሕይወት ታፈረ ወኪል

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ አባትነት ይረጋገጥልኝ በሚል

ክስ ላይ ተመስርቶ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው፡፡ ከመዝገቡ እንደሚታየው ክርክሩ

የተጀመረው በማህበራዊ ፍ/ቤት ሆኖ ልጅነት ይረጋገጥልኝ ክስ ያቀረበችው ተጠሪ ናት፡፡ ተጠሪ ህፃን

ሕይወት ታፈረ የተባለችውን ከአመልካቾች አባት መውለዷን በመግለጽ በሞግዚትነትዋ ነው ክሱን

1
ያቀረበችው የማህበራዊ ፍ/ቤቱ ህፃን ሕይወት የአቶ ታፈረ ስብሐት ልጅ ነች በማለት ሲወስን በዚህ

ላይ ይግባኝ የቀረበለት የወረዳ ፍ/ቤት ግን ህፃንዋ የአቶ ታፈረ ስብሐት ልጅ አይደለችም በማለት

ወስኖአል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ለከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረብዋ በዚህ ደረጃም ክርክሩ

ከተሰማ በኋላ የወረዳው ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ የማህበራዊ ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶአል፡፡ በመጨረሻም

በአመልካቾች በኩል ለትግራይ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበ ሲሆን ችሎቱ

የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብሎአል፡፡ የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሰበር አቤቱታው ከተመረመረ በኋላ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የተፈጸመ መሠረታዊ

የሕግ ስህተት የለም ተብሎ መዝገቡ ተዘግቶ የነበረ ሲሆን በድጋሚ ሊንቀሳቀስ የቻለው አመልካቾች

መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም በተጻፈ ቃለ መሃላ ዳኝነት እንደገና ይታይልን የሚል አቤቱታ

በማቅረባቸው ነው፡፡

እኛም የቀረበውን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን በግራ ቀኝ ወገኖች በኩል

ያለውን ሃሳብ ሰምተናል፡፡ ተጠሪ ዳኝነት በድጋሚ የሚታይበት ምክንያት የለም በማለት ስትከራከር

አመልካቾች ደግሞ የቀድሞ ውሳኔ የተሰጠው በሐሰት የተዘጋጁት ማስረጃዎች መሠረት በማድረግ

በመሆኑ ዳኝነቱ በድጋሚ ቢታይ ውሳኔው እንደሚሻር እርግጠኞች ነን የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡

እንደምንመለከተው በሰበር ችሎቱ እንዲወሰን የቀረበው ጭብጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 6

መሠረት ዳኝነት እንዲታይ የቀረበው ጥያቄ አግባብነት የሚመለከት ነው፡፡ አመልካቾች ጥያቄውን

ያቀረቡት ሕይወት ታፈረ የታፈረ ስብሐት ልጅ ነች የተባለችው እውነትም የታፈረ ስብሐት ልጅ ሆኖ

ሳይሆን በሐሰት የተዘጋጁ ማስረጃዎች በመቅረባቸው ምክንያት ነው፡፡ ማስረጃዎቹ በሐሰት የተዘጋጁ

መሆናቸውን ያረጋገጥነውም ጉዳዩ እስከ ሰበር ችሎት ድረስ ከሄደ በኋላ ነው የሚል ምክንያት

በመሰጠት ነው በእርግጥም አመልካቾች ጥያቄውን ያቀረቡት ቀደም ሲል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው

ውሳኔ ሊታረም ይገባል በሚል ለሰበር ችሎቱ አቤቱታ ከቀረበ በኋላ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም የዳኝነት

ይታይ አቤቱታ በዚህ ደረጃ ሊቀርብ ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ችሎቱ ተመልክቶታል፡፡ በሰበር

መ/ቁ 43821 በቀረበው ክርክር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.6 አተረጓጐም በሚመለከት ችሎቱ ተገቢ ነው

2
ያለውን ትርጉም ሰጥቶአል፡፡ በዚህም የቀድሞ ውሳኔ ይግባኝ ይባልበትም አይባልበት በሐሰተኛ ማስረጃ

እና ወንጀል ቀመስ በመሆኑ ተግባሮች ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ነው የሚል አቤቱታ እስከቀረበበት ድረስ

ዳኝነት እንዲታይ ጥያቄው ሊስተናገድ ይገባል ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሶአል፡፡ አቤቱታው

በቀጥታ መቅረብ ያለበት የመጀመሪያውን ውሳኔ ለሰጠው ፍ/ቤት እንደሆነም በውሳኔው ላይ

ተመልክቶአል፡፡ የሰበር ችሎቱ በዚህ ረገድ የሰጠው የሕግ ትርጉም ከዚህ በኋላ ገዢ (አስገዳጅ) በመሆኑ

ለያዝነው ጉደይም ተፈጻሚነት ያለው ነው፡፡ ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል፡፡

3
ውሳኔ

1. አልካቾች ያቀረቡት የዳኝነት እንደገና ይታይልን ጥያቄ ተቀብለን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.6

መሠረት ሊስተናገድ ይገባል ብለናል፡፡

2. የልጅነት ይረጋገጥልኝ አቤቱታ በመጀመሪያ ደረጃ አስተናግዶ ውሳኔ ይሰጠው የማህበራዊ

ፍ/ቤት በመሆኑ ይህ ማህበራዊ ፍ/ቤት አመልካቾች ሚያቀርቡትን የዳኝነት እንደገና

ይታይልን አቤቱታ በቀድሞው መዝገብ ተቀብሎ እንዲያስተናግድ በመቀጠልም የሁለቱ

ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳይ ይመለስለት ብለናል፡፡

3. በዚህ ሰበር ችሎት በተደረገው ክርክር ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሳራቸውን ይቻቻሉ፡፡

መዝገቡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ፀ/መ

You might also like