Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የመ/ቁጥር ፦ 13171

ቀን ፦ 27/062016.ዓ.ም

ለሀዋሳ ከተማ የመ/ደ/ፍ/ቤት

መሀልና ሐይቅ አካባቢ ምድብ ችሎት

ሀዋሳ

የአፈ/ከሳሽ ፦ የሐይቅ ዳር መረዳጃ እድር ፦ አድራሻ ሐይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱማሌ ቀበሌ

የአፈ/ተከሳሽ ፦ አቶ ካቻው ሙኤ ፦ አድራሻ ሐየሰቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱማሌ ቀበሌ

የአፈፃፀም ተከሳሽ ለቀረበበት የአፈፃፀም ክስ በቀን 21/06/2016.ዓ.ም ፅፎ ላቀረበው መቃወሚያ ከአፈ/ከሳሽ የተሰጠ
መልስ"፦

፦ በመሠረቱ በቅድሚያ ክሱ የአፈፃፀም ክስ መሆኑ እና በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 378 የአፈ/ክስ የሚጠይቃቸውን ፍሬ


ነገሮች አሟልቶ በግልፀና በተብራራ ሁኔታ የቀረበ ክስ በሆነበት እና ይህም በአፈፃፀም ተከሳሽ ታውቆ ባለበት
የአፈ/ተከሳሽ ሆን ብሎ ፍ/ቤቱን በማሳሳት እንደ መደበኛ ክስ ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና አማራጭ
መልስ ተገቢነት የሌለው ፣ የአፈ/ከሳሽም መልስ እንድሰጥ በችሎቱ መታዘዜ ፍፁም አግባብነት የሌለው በመሆኑ
በአፈፃፀም ክስ ላይ የተከበረው ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ሊያርመው እና ሊያስተካክለው እንደሚገባ ለተከበረው
ፍርድ ቤት በአክብሮት አመለክታለሁ።

1. ከአፈ/ከሳሽ የቀረበውን የአፈፃፀም ክስ " የአፈ/ተከሳሽን እንደማይመለከት ፣ የማህበራዊ ፍርድ ቤቱም ስልጣን
ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ " ነው በማለት የአፈ/ተከሳሽ ይቃወም እንጂ በማህበራዊ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ በግልፅ
እንደተብራራውና በክስ ክርክሩ የቀረቡት የሰገድ ማስአጃዎች እንዳረጋገጡት የአፈ/ከሳሽ እንዲለቀቅለት በጠየቀው ቤት
ላይ ከአከራየኝ የሐይቅ ዳር ክ/ከተማ የቤቶች ልማት ከገባሁት የተከራይነት ሀሰጋዊ ውል መሠረት ከውል የመነጨ መብት
ያለኝ የአሁን የአፈ/ተከሳሽ የማስለቀቅ ክስ ባቀረብኩበት የጥበቃ ቤት ውስጥ የገባው ከስራ ከመሰናበቱ በፊት የመረዳጃ
እድሩ ተቀጣሪ ጥበቃ በመሆኑ በስራ ላይ በነበረ ጊዜ ለማረፊያና ልብስ ለመቀየሪያ ተብሎ የሰጠነው ክፍል ቤት መሆኑ
ክርክር ሊቀርብበት የማይችልና የሚታመን በሆነበት የአፈ/ተከሳሽ የአፈ/ከሳሽን መብትና ጥቅም እንደሌኝ አድርጎ
የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 33(2) እና(2)ጠቅሶ ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት የሌለውና አስቀድሞ በማህበራዊ ፍ/ቤት
ያልቀረበ መቃወሚያ ውድቅ ሊደረግ የሚገባው ከመሆኑም በላይ ፍርዱን ከመፈፀም የማያድነው ነው ተብሎ ውድቅ
እንዲደረግልኝ፤ የአፈ/ከሳሽ ያቀረበው የሰነድ ማስረጃም የአፈ/ከሳሽ በውል በተከራየነው ቤት ላይ መብት የማይሰጠውና
የክ/ከተማው አስተዳደር ቤት እንዲያፈላልግለት የተሰጠ የትብብር ደብዳቤ በመሆኑ ለዚህ የአፈ/ክስ እንደመከላከያ
ሊቀርብ የማይችል ማስረጃ ነው ተብሎ ውድቅ እኔዲደረግልን።

2. የአፈ/ተከሳሽ የማህበራዊ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም ካለ በክስ ክርክሩ ወቅት ይህን መቃወምና በይግባኝ ማሻር እንጂ
አሁን በአፈፃፀም ክስ ጊዜ እንደ ፍርዱ ከመፈፀም ውጭ የማህበራዊ ፍ/ቤቱ ስልጣን አስመልክቶ ተቃውሞ የሚቀርብበት
ፈቃጅ የስነ ስረዓት አካሄድ ባለመኖሩ መቃወሚያው የህግ መሠረት የለውም ተብሎ ውድቅ እንዲደረግልኝ ።

በአጠቃላይ የአፈ/ተከሳሽ የቀረበበትን የአፈፃፀም ክስ እንደ ፍርዱ ላለመፈፀም የሚያቀርበው ያልተገባ መከራከሪያ ስነ
ስረዓታዊ አካሄድን ያልተከተለ በመሆኑ ውድቅ ሆኖ የአፈ/ተከሳሽ ፍርዱን ተገዶ እንዲፈፅምልን ለተከበረው ፍ/ቤት
እናመለክታለን።

የአፈ/መልሳችን በእውነት የቀረበ ነው


ስለ/የአፈ/ከሳሽ ፦

You might also like