Professional Documents
Culture Documents
8 Module
8 Module
ሱር ታክስ ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ የመንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች ሲከሰቱ በተወሰኑ ሸቀጦች
ወይም የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ በጊዜያዊነት የሚጣል ታክስ ዓይነት ነው፡፡ መንግሥት ሱር ታክስን ለመጣል
ከሚገደድባቸው ሁኔታዎች መካከል የሀገር ሉአላዊነት አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች
ሲከሰቱ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል የመንግሥትን ቀጥተኛ ድጎማ የሚፈልግበት ሁኔታ
ሲከሰት እና ለመሳሰሉት ወጪ መሸፈኛ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብና በሀገር የሚመረቱ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ
ሱር ታክስ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ ለብቻው የተደነገገው በድርቅ ለተጎዱ ቀበሌዎች መርጃና
ማቋቋሚያ እንዲሁም ለተፈጥሮ አደጋና ለመከላከያ የሚውል ገንዘብ እንዲገኝ በገቢ ላይ ጊዜያዊ ተጨማሪ (ሱር)
ታክስ ለመወሰን መጋቢት 2/1967 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁ. 24/1967 ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ሱር ታክሱ
ከመቀጠር የሚገኝ የአንድ ወር ደመወዝና በዚያው ወር ውስጥ የተገኘ የመኪናና የሌላም አላዋንስ፣
ገቢውን እንዲከፍል ያዛል፡፡ ክፍያው በ12 (አሥራ ሁለት) ወራት ተከፍሎ የሚያልቅ ሲሆን የአንድ ወር ደመወዙና
ሌሎች አበሎች ተደምረው ከብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ) በታች ገቢ ያለው ሰው ታክሱ እንደማይመለከተው
በአዋጁ ላይ ተመልክቷል፡፡
በሀገራችን ሱር ታክስ ከጥር ወር 1993 ዓ.ም. እንዲሁም በመቀጠል ከውጭ ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ /ቡና የነበረው
የቡና ቀረጥና ታክስ በዓለም የቡና ገበያ መውደቅ ምክንያት ከ1994 በጀት ዓመት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተነስቶ
ነበር ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታክሱ በአሁኑ ጊዜ ግን ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ስለተጣለ ተጨማሪ ቀረጥ የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 133/1999 ዓ.ም በተደነገገው መሠረት ታክሱ እየተሰበሰበ የሚገኝ ሲሆን
ስለዚህ ታክስ አስተዳደር ሥርዓት የታክስ ከፋይም ሆኑ ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ግንዘቤ ለማስያዝ ይቻል
1
ክፍል አንድ
አጠቃላይ
1.1 ዓላማ
ዋና ዓሇማ
የተጨማሪ ቀረጥ ወይም ሱር ታክስ ደንብ ቁጥር 133/1999 ዓ.ም የአሠራር ሥርዓት
እንዲያውቁት ነው ፡፡
ዝርዝር ዓላማዎቹ
ሠልጣኞች ፡
የሱር ታክስ ቀረጥ ጽንሰ ሃሳብን ይረዳለ ፡፡
የሱር ታክስ የሚከፈልባቸውን እና ከታክሱ ነጻ የሆኑትን የገቢ ዕቃዎች በመሇየት
ግዴታቸውን ይወጣለ ፡፡
የሱር ታክስ የሥሌት መሰረትና መጣኔውን ይረዳለ ፡፡
1.2. ውጤት
ተገልጋዮች የሱር ታክስ የህግ ድንጋጌዎችን ላይ ግንዘቤ ፈጥሮ ታክሱን አስልቶ ይከፍላለ፡፡
1.3.ወሰን
1.3.1. ሽፋን
ስሇሱር ታክስ / ተጨማሪ ቀረጥ ሇማስከፈል የወጣ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ዯንብ ቁጥር
133/ 1999 እና በተዋሀዶ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳዯብ ሥርዓት ዓሇም አቀፍ ኮንቬሽን
ማፅደቂያ አዋጅ ቁጥር 67/1985 አንቀጽ 4 እና የፌዴራል ታክስ አስተዳዯር
አዋጅ ቁ.983/2008ን ይሸፍናል ፡፡
1.3.2.የስልጠናው ተሳታፊዎች
ታክስ ከፋዮች ፤ የንግድ ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባሇሙያዎች እና ሌሎች ተገልጋዮች
ይሆናለ ፡፡
2
2. ወዯ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ሱር ታክስ ስሇማስከፈል
ለሚከፈለው ሱር ታክስ ( ተጨማሪ ቀረጥ) የስሌት መሰረት የገቢ ዕቃው ዋጋ፣ የመድን አረቦን እና
የማስጫኛ ወጪ (Cost , Insurance and Transport) እንዲሁም በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባው የጉምሩክ
ቀረጥ የኤክሣይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ድምር ውጤት ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የገቢው ዕቃ
የጉምሩክ ዋጋ ሲደመር የዕቃው የጉምሩክ ቀረጥ ሲደመር የዕቃው ኤክሳይሰዝ ታክስ ሲደመር የተጨማሪ
እሴት ታክስ ጠቅላላ ድምር ሲበዛ 10 % (አስር በመቶ) ይሆናል በእቃው ላይ የሚከፈል ሱር ታክስ ይሆናል
ማለት ነው ፡፡
የሙከራ ጥያቄዎች ፤
በሕግ ያ ወይም መንግሥት ባደረገው ስምምነት ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ የተደረጉ ሰዎች እና ድርጅቶች
የመሬት ማዳበሪያዎች፣
የካፒታል (የኢንቨስትመንት) ዕቃዎች ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር በደንቡ ከተጨማሪ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ
አገር እንዲገቡ የተፈቀደውን ዕቃዎች ዝርዝር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ እንዲሁም ለዚህ ደንብ አፈጻፀም
3
የሙከራ ጥያቄ
ማጣቀሻ ፡
ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ስለተጣለ ተጨማሪ ቀረጥ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር