8 Module

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 4

መግቢያ

ሱር ታክስ ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ የመንግሥት የፋይናንስ ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች ሲከሰቱ በተወሰኑ ሸቀጦች

ወይም የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ በጊዜያዊነት የሚጣል ታክስ ዓይነት ነው፡፡ መንግሥት ሱር ታክስን ለመጣል

ከሚገደድባቸው ሁኔታዎች መካከል የሀገር ሉአላዊነት አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች

ሲከሰቱ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል የመንግሥትን ቀጥተኛ ድጎማ የሚፈልግበት ሁኔታ

ሲከሰት እና ለመሳሰሉት ወጪ መሸፈኛ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብና በሀገር የሚመረቱ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ

የበለጠ ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለመፍጠር እና የመሳሰሉት ይገኙበታል ፡፡

ሱር ታክስ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን ችሎ ለብቻው የተደነገገው በድርቅ ለተጎዱ ቀበሌዎች መርጃና

ማቋቋሚያ እንዲሁም ለተፈጥሮ አደጋና ለመከላከያ የሚውል ገንዘብ እንዲገኝ በገቢ ላይ ጊዜያዊ ተጨማሪ (ሱር)

ታክስ ለመወሰን መጋቢት 2/1967 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁ. 24/1967 ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሠረት ሱር ታክሱ

ከመቀጠር የሚገኝ የአንድ ወር ደመወዝና በዚያው ወር ውስጥ የተገኘ የመኪናና የሌላም አላዋንስ፣

የዳይሬክተሮች ቦርድ አበልና የማናቸውንም ሌላ አበል፣ ገቢ የሚያገኝ ማናቸውም ሰው የአንድ ወር ጠቅላላ

ገቢውን እንዲከፍል ያዛል፡፡ ክፍያው በ12 (አሥራ ሁለት) ወራት ተከፍሎ የሚያልቅ ሲሆን የአንድ ወር ደመወዙና

ሌሎች አበሎች ተደምረው ከብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ) በታች ገቢ ያለው ሰው ታክሱ እንደማይመለከተው

በአዋጁ ላይ ተመልክቷል፡፡

በሀገራችን ሱር ታክስ ከጥር ወር 1993 ዓ.ም. እንዲሁም በመቀጠል ከውጭ ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ /ቡና የነበረው

የቡና ቀረጥና ታክስ በዓለም የቡና ገበያ መውደቅ ምክንያት ከ1994 በጀት ዓመት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተነስቶ

ነበር ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታክሱ በአሁኑ ጊዜ ግን ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ስለተጣለ ተጨማሪ ቀረጥ የወጣ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 133/1999 ዓ.ም በተደነገገው መሠረት ታክሱ እየተሰበሰበ የሚገኝ ሲሆን

ስለዚህ ታክስ አስተዳደር ሥርዓት የታክስ ከፋይም ሆኑ ሌሎች የማህበረሰብ አባላት ግንዘቤ ለማስያዝ ይቻል

ዘንድ ይህ ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል ፡፡

1
ክፍል አንድ
አጠቃላይ

1.1 ዓላማ
 ዋና ዓሇማ

የተጨማሪ ቀረጥ ወይም ሱር ታክስ ደንብ ቁጥር 133/1999 ዓ.ም የአሠራር ሥርዓት

ላይ አገልግሎት ሰጪውም ሆነ ተቀባዩ ስለ የሱር ታክስን ምንነት እና ስለታክሱ

አስተዳደር ሥርዓት ላይ የጋራ ዕውቀትና መግባባት በመያዝ ታክሱ እንደሚከፈል

እንዲያውቁት ነው ፡፡

 ዝርዝር ዓላማዎቹ
 ሠልጣኞች ፡
 የሱር ታክስ ቀረጥ ጽንሰ ሃሳብን ይረዳለ ፡፡
 የሱር ታክስ የሚከፈልባቸውን እና ከታክሱ ነጻ የሆኑትን የገቢ ዕቃዎች በመሇየት
ግዴታቸውን ይወጣለ ፡፡
 የሱር ታክስ የሥሌት መሰረትና መጣኔውን ይረዳለ ፡፡
1.2. ውጤት
ተገልጋዮች የሱር ታክስ የህግ ድንጋጌዎችን ላይ ግንዘቤ ፈጥሮ ታክሱን አስልቶ ይከፍላለ፡፡

1.3.ወሰን
1.3.1. ሽፋን
ስሇሱር ታክስ / ተጨማሪ ቀረጥ ሇማስከፈል የወጣ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ዯንብ ቁጥር
133/ 1999 እና በተዋሀዶ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳዯብ ሥርዓት ዓሇም አቀፍ ኮንቬሽን
ማፅደቂያ አዋጅ ቁጥር 67/1985 አንቀጽ 4 እና የፌዴራል ታክስ አስተዳዯር
አዋጅ ቁ.983/2008ን ይሸፍናል ፡፡

1.3.2.የስልጠናው ተሳታፊዎች
ታክስ ከፋዮች ፤ የንግድ ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባሇሙያዎች እና ሌሎች ተገልጋዮች
ይሆናለ ፡፡

1.3.3. ስልጠናው የሚወስዯው ጊዜ.፡ ግማሽ ሰዓት ይሆናል ፡፡

2
2. ወዯ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ሱር ታክስ ስሇማስከፈል

2.1. ሱር ታክስ ማስከፈያ ልክ ( መጣኔ )

ሱር ታክስ ከተጨማሪው ቀረጥ ነጻ የሆኑት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ በደንብ ቁ.

133/1999 በተደነገገው መሠረት 10 % (አስር በመቶ) ተጨማሪ ቀረጥ እየተጣለ ይሰበሰባል፡፡

2.2. የታክሱ ስሌት መሠረት

ለሚከፈለው ሱር ታክስ ( ተጨማሪ ቀረጥ) የስሌት መሰረት የገቢ ዕቃው ዋጋ፣ የመድን አረቦን እና

የማስጫኛ ወጪ (Cost , Insurance and Transport) እንዲሁም በዕቃው ላይ ሊከፈል የሚገባው የጉምሩክ

ቀረጥ የኤክሣይዝ ታክስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ድምር ውጤት ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የገቢው ዕቃ

የጉምሩክ ዋጋ ሲደመር የዕቃው የጉምሩክ ቀረጥ ሲደመር የዕቃው ኤክሳይሰዝ ታክስ ሲደመር የተጨማሪ

እሴት ታክስ ጠቅላላ ድምር ሲበዛ 10 % (አስር በመቶ) ይሆናል በእቃው ላይ የሚከፈል ሱር ታክስ ይሆናል

ማለት ነው ፡፡

የሙከራ ጥያቄዎች ፤

1. የሱር ታክስ ( ተጨማሪ ቀረጥ ) በምን ዓይነት ግብይቶች ላይ ይፈጸማል ?


2. የሱር ታክስ ስሌት መሠረት በምሳሌ አሰረዳ ፤

3. ከሱር ታክስ ነጻ ስለመሆን

በሕግ ያ ወይም መንግሥት ባደረገው ስምምነት ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ የተደረጉ ሰዎች እና ድርጅቶች

የሚያስመጧቸው ዕቃዎች ሲሆኑ የሚከተሉትን ይጨምራል፤

 የመሬት ማዳበሪያዎች፣

 ነዳጅ፣ የብረታ ብረት ቅባቶች፣

 የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች እና ለተለየ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች፣

 አውሮፕላኖች፣ የአየር መንኮራኩሮች፣ የጠፈር መንኮራኩሮች እና የነዚሁ ክፍሎች፣

 የካፒታል (የኢንቨስትመንት) ዕቃዎች ሲሆን የገንዘብ ሚኒስቴር በደንቡ ከተጨማሪ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ

አገር እንዲገቡ የተፈቀደውን ዕቃዎች ዝርዝር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ እንዲሁም ለዚህ ደንብ አፈጻፀም

የሚያግዙ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል

3
የሙከራ ጥያቄ

ከሱር ታክስ ነጻ የሆኑትን ዘርፎች ሶስቱን ጥቀስ

ማጣቀሻ ፡

ወደ ሀገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ስለተጣለ ተጨማሪ ቀረጥ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር

133/1999 ዓ.ም እና ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮች

You might also like