5 6 7

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

567

5 6 7 ስሙኝ እናንተ ሙታን ልንገራችሁ የማይነገር ለህያውያን


ከወዳኛው አለም ሴጣንን አይታችሁታል
አላያችሁትም
እዚህ ትታችሁት ሄዳችሁ እዛ እንዴት ታጋኙታላችሁ
እዚህ ነው ከኛጋ ይኖል
567
ሴጣን ማለት ጎተራ ነው ስልቻ ነው የማይሞላ ጉድ ነው
ሴጣን ማለት ሆድ ነው
567
5 ልጅ ሁለት እናት እና አባት
ሴጣን ከ እባብ ተዋሃደ ሂዋንን አሳሳተ አሳተ
ከ እጸበለስ ተዋሃደ ሂዋን ሆድ ገባ
ከሆድዋ ተዋሃደ ለልጆቿ ተረፈ
ሴጣን ሲኦል ወረደ ማለት ወደሆድ ወረደ ማለት ነው
ከዚያስ?...
ከዚያማ ጭለማውስጥ ቁጭ ብሎ ይገዛን ያሰግድደን ጀመር
567
ቀኑን ሙሉ ስንለፋ፣ ስንሰራ፣ ስናስመስል ስንዋሽ
ለምን?
ለእንጀራ......
ለማን ?
ለሴጣን ሆድ......
ሆድ ይሄ ሆድ.... ይሄ ጎተር.... ይሄ ጭለማ የሴጣን ቤት መኖሪያ
ሰው ከተወለደበት እስኪሞት ተራራ ያህል እህል ይበላል
አይሞላ ታዲያ ይሄ ሆድ ሁሉ አይሞላ ሴጣን ነው
ሆድ.. ሆድ........
567
5 ልጅ 6 እናት 7 አባት
እንግዲ ሰሞኑን ስለክርስቶስ ስቅለት ተሰማላችሁ
ግን ማነው ሰው ሆኖ ያልተሰቀለ በልጁ ለቅሶ ያልተቸነከረ
ማነው በሚስቱ ሞት ያልተቀበረ
ደጋግሞ ሊነሳ ድጋግሞ ያልተቀበረ ማነው
567
እሳት ገሃነም ትገባላችሁ ብለው ያስፈራሩናል የት ነው ያለነው እና........
ገሃነውም አይደለምን? ......... እረ ወዲያ........
ሰላም ላንተ ህማማት ነውና የይሁዳን ታሪክ ልንገርህ
567
ሰማዩን አንጋጠው ቢያዩት ደመና አቶ ራቁቱን ቀረና
በጸሎት ሲጨምቁት ጠብ አልል አለና
ምንድ ጉዋጉታ ተነቃቅታ ደርቃ ቀረችና
የይሁዳም በሬዎቹ አንድ በአንድ ከዱትና
ታማኙ አልሞት ባዩ ሲሳ ብቻ ቀረ
ቀንበር ሊሸከም ሞፈር ሊጎትት አብሮት ሊሰራ እስከመጨረሻው
567
ይሁዳ ግ ን ሰው ነውና....... ከሃዲ ነውና...... በሪውን ሊሸጠው ተነሳ
ገዢ ታጣ......
እንግዲያው ና ሲሳይ የመጨረሻ ወዳጄ ዘመዴ ና ጉዋሮ እንሂድ ልንገርህ ለብቻህ አለና ወሰደው
567
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አለና የመጨረሻይቱን ሚስጢር በስለት ነገረው
እርድ
በሬው ከማዘኑ የተነሳ ምንም አላለም በዝምታ እጁን ሰጠ
ጸሃይ ይህንን አይታ በሃፍረት ፊቷን ልትሸሽግ ዞር ብትል ዳመና አጣች
ደም አለቀሰች
አረድኩት፣ ገፈፍኩት፣ ብልቱን አወጣሁት........
ጠብሰን ቀቅለብ በላነው ሲሳይን በሬየን ሲሳይን
የመጨረሻ ወዳጃችንን
ወጥ እንዳይሆን እንጀራ የለን ቋንጣ እንዳይሆን ቶሎ ጨረስነው
በላሁት ሲሳይ ዘመዴን ለሆድ ለሴጣን ሰዋሁት
ታዲያ ይሁዳ ከዳተኛ ነው ይላሉ
የኔን ታሪክ ያላወቁ
ይሁዳ እንኩዋን ተጸጸተ ተሰቀለ
እኔ ግን
ወየው ወየው ወይነ ዘመደ የይኔ ሲሳይን ወይነ ወዳጄን
(ድንጋይ አንስቶ)
ማረኛአንተ የዳዊት ልጅ ይቅር በሉኝ አባ
(ይቅር ይበልህ)
አልፈልግም የሱን ይቅርታ አልፈልግም
(በንዴት ድንጋሁን ወረወረው )
የተበደለ ምን ይቅርታ ያስፈልገዋል
ሰው በመሆኖት ይቅርታ ለመንኩ እንጂ
ፍርጣሪን ይቅርታ እለምናለው
እሱማ ሲከሰስ ይገባዋል(እጁን ዘርግቶ ለሙታን መናገር ጀመረ)
567
ንገሩልኝ ታገኙት እንደሆን
አበላቸው እህል ከልክለህ 5 ልጆች የሰጠሀኝ ምነው ብሎሃል በሉት
5 ልጆች ተሰብስቦ አብሮ ሲውል አንዲት ሳቅ ብቅ ሳትል ቀኑ መምሸቱ ምነው ብሎሃል በሉት
ልጆቼ አንድ ቀን እንኩዋን አኩኩሉ ሳይጫወቱ ማለቃቸው ምነው ብሎሃል በሉት
ልጆቼንም ሚስቴንም በአንድ ቀን ስቀብር ዝም ብለህ ማየትህ ምነው ብሆሃል በሉት
የፍርድ ቀን ሲመጣ የሚፈረድበት ማነው ብሎሃል በሉት
5 6 7 የፍርድቀን ሲመጣ........
ምነው አለቀሱ አባ

ምን ሆኑ አባ.......

ለኔ ነው ያለቀሱልኝ .........
(ቁጭ ብሎ አንገቱን ደፋ )

You might also like