Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Police University

ከ 1939 ጀመሮ
Since 1946

ቁጥር/Ref.No…………………………………
d}/Date…………………………………………
ለጋትሜትስ ኢንተርናሸናል ኃ.የተ.የግ.ማህበር

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- MV/LV Transformer ይመለከታል፡፡

ዩኒቨርሲቲያችን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን እና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የግንባታ ውል ስምምነት ፈጽሞ የፎረንሲክ
ኢንስቲትዩት ፕሮጀክት ግንባታን እያስነባ የሚገኝ ሲሆን ድርጅታችሁም የማማከር አገልግልት ስራውን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰው Transformer ዓይነትና ቮልቴጅ አቅሙ ተጠቅሶ በውል ሰነድ ላይ ግልጽ ዋጋ ተሞልቶለት የተቀመጠ
በመሆኑ ተቋራጭ ድርጅቱ በውሉ ላይ የተጠቀሰው 500 KVA ለሁሉም ፕሎኮች አገልግሎት ለመስጠት ስለማይችል G+4 አንዱ ፕሎክ
ጨለማ ስለሚሆን የሚያስፈልገው 630 KVA ነው በማለት ሳይት ላይ በነበረን የሶስትዮሽ ስብሰባ ላይ ሃሳቡ ተነስቶ ይበቃል ካለችሁ ኃላ
ተወቃሽ እንዳታደርጉን ስራውን ቀጥሉ በሉን በውላችን መሰረት ስራዉን እንቀጥል በዚህ ጉዳይ ለረጅም ጊዚያት መልስ ሊሠጥን አልቻለም
በማለት ቅሬታ በአማካሪው ድርጅት ላይ ማንሳታቸው ይታወቃል፡፡ እኛም በእናንተ በኩል ትክክለኛ ሙያዊ ምላሽ እንዲሰጥ
መስማማታችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ወገን በተገኘበት ግልጽ ሙያዊ ማብራሪያ ባለተሰጠበት ሁኔታ በቁጥር
ECWSWC/COUSlan/13613/2023 እ.ኢ.አ 04 OCT/2023 ለአቀረቡት ጥያቄ በተሰጠ መልስ በቁጥር /Re: ጋ/049/2016 በቀን
15/04/2016 ዓ.ም በግልባጭ እንዳሳወቃችሁን አሰሪው መስሪያ ቤት ከአሁኑ የትራንስፎርመር ግዥ ለመፈጸም ፕሮሰስ ይጀምር በማለት
መልስ መስጠታችሁን አሳዉቃችሁናል፡፡ ነገር ግን ይህን ለመፈጸም የተፃው ደብዳቤ በምን መነሻ እንደሆነ የማገልፅ ስለሆነ ከውለታ ውጪ
ስለሆነ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ በቂ ማብራሪያ አንድትሰጡን እንጠይቃለን፡፡

1. ትክክለኛ የሚበቃው የትራንስፎርም ቮልቴጅ አቅም ስንት ነው?

2. በበላቤት በኩል የሚገባ ከሆነ ለምን መጀመሪያ በተቋራጭ በኩል እንደሚገባ ውል ቀደም ሲል ተፈጸመ?
3. ውል ሲገባ በነበረው ዋጋ እና አሁን ላይ ዋጋ ለውጥ ያለ ስለሆነ ኪሳራውን ማነው ኃላፊነት የሚወስደው?
የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ በተሎ ምላሽ እንድትሰጡን ስንል እናሳውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ
 ለኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት መምሪያ
 ለኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለአስ/ልማ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
 ለኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለግዥና ፋይናነስ መምሪያ
 ለኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጅከት አስተዳደር ዋና ክፍል
 ለኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለዕቅድና በጀት ዋና ክፍል
ሠንዳፋ
 ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን እና ዲዛይን ሱፐርቢዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage; Serve with Compassion!
 +251-116860570/+251-116860857/+251-966006433  1503 óŸe/Fax +251-116860420
facebook.com/ethiopanpolice t.me/Epupage www.epu.edu.et Sendafa/Ethiopia
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Police University
ከ 1939 ጀመሮ
Since 1946

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቁጥር/Ref.No…………………………………

d}/Date…………………………………………
ለአስተዳደር ልማ/ም/ፕሬዝዳንት

ሠንዳፋ

የውስጥ የስራ ማስታዎሻ

ጉዳዩ፤- ከፌደራል ፖሊስ ምህንድስና መምሪያ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ስለሚዛወሩ ፕሮጀክቶች ይመለከታል፡፡

በቀን 14/05/2016 ዓ.ም በክቡር ምክትል ኮምሽነር ጄኔራል በተሠጠኝ ትዕዛዝ መሰረት በ 15/05/2016 ዓ.ም ረ/ኮምሸነር እሸቱ
ፊጣን በአካል በቢሮአቸው ተገኝቼ ለስራ እሳቸው ጋ መላኬን ገለጽኩላቸው፡፡ እርሳቸዉም ከማንደር አላዩን በመጥራት የፖሊስ
ሆስፒታል ማስፋፊያፕሮጀክት አካል የሆነውን የጤና ቢሮ ማሰፋፊያ G+8 ሕንፃ እና የአዋሸ አርባ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጥናት
በተመለከተ ተነጋግራቸሁ ወደ ዩኒቨርሲቲው ይዛወር በማለት ትዕዛዝ ከሰጡን በኋላ ምህንድስና ቢሮ ውስጥ ኮማንደር አላዩ
ኢንጅነር ወርቂቱ እና እኔ ሁነን በዝርዘር ስለጉዳዩ ስንወያይ

የጤና ቢሮ ማሰፋፊያ G+8 ሕንፃ የተወሰነ ዲዛይን መስተካከል የሚስፈልገው ነገር ስላለ አማካሪው ጋትሜትስ ዲዛይኑን
አስተካክሎ ለግንባታ ውል ሰምምነት በሚያመች መልኩ በሳምንት ውስጥ እንዲያቀርብ ተደርጎ ተጨማሪ ውይይት ከተደረገ
በኋላ በደብዳቤ ሰነዶችን እንድንካከብ የሚያሳዉቁን መሆኑን፡፡

ሲሆን ስለ ህንፃው በተመለከተ መከላክያ ኮንስትራክሽን ከአንድ አመት በፊት የግንባታ ዋጋ እንደሞላና ስምምነት ላይ
አለመደረሱን መረጃ የሰጡን ስለሆነ ለሌላ ተቋራጭ ለመስጠት የሚያግደን ነገር አለመኖሩን አረጋግጫለሁ፡፡

የአዋሽ አርባ ውሃ ጉድጓድን በተመለከተ ጥናቱን የያዘው የኦሮሚያ ውሃ ኮንስትራክሽን ሲሆን ዲዛይኑ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮን
ብቻ ሰለነበር የመስመር ዝርጋታ ዲዛይኑን ጨምሮ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚያቀርቡላቸው የተስማሙ መሆኑን እና ጥናቱና
ዲዛይኑ ሲያልቅ ሰነዱን ተረክበን ለተቋረጭ መስጠት እንደምንችል ነው የተጋገርነው፡፡ ሁለቱንም ፕሮጀክቶች የሚስተካከሉ
ነገሮች በእነርሱ በኩል እንደለቀ በደብዳቤ እንደሚያሳውቁን ተግባበተናል፡፡ እኔም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ቀጣይ ምን
እንደደረሰ ተከታትዬ ተጨማሪ ሂደቶችን የማሳውቅ መሆኔን በትህትና እገልጻለሁ፡፡ ከሠላምታ ጋር

ስንታየሁ ለገሰ

የፕሮጀክት አስተዳደር

ዋና ክፍል ኃላፊ

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage; Serve with Compassion!
 +251-116860570/+251-116860857/+251-966006433  1503 óŸe/Fax +251-116860420
facebook.com/ethiopanpolice t.me/Epupage www.epu.edu.et Sendafa/Ethiopia
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Police University
ከ 1939 ጀመሮ
Since 1946

ቁጥር/Ref.No…………………………………
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ
d}/Date…………………………………………
ለግዥና ፋይናንስ መምሪያ

ሠንዳፋ

የውስጥ የስራ ማስታዎሻ

ጉዳዩ፤- ከጋራ አካውንት ሂሳብ ወጪ ይመለከታል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በአደረገው የጋራ ስምምነት
መሰረት ለቅድመ ስራ ማስኬጃ የወሰዱት ገንዘብ ለሌላ ፕሮጀከት አገልግት ሳይውል ለራሱ ለፕሮጀከቱ ግንባታ
አንዲውል በጋራ አካውንት ሂሳብ መከፈቱ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተቋራጭ ድርጅቱ ለ 10,000 በበልክ ኩንታል ሲምንቶ ግዥ የሚውል 13,583,617.00 ( አስራ ሶስት
ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማኒያ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ አስራ ሰባት ብር) እና 5200 ኩንታል ሲሚንቶ በከረጢት
ብር 5692668.80 ( አምስት ሚሊዮን ስድሰት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስምንት ከ 80 ሳንቲም
በድምሩ 19276285.8(አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ሀለት መቶ ሰባስድሰት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር) ከጋራ
አካውንት ሂሳቡን በሚያንቀሳቅሱት ግለሰቦች ፊርማ ወጪ ሆኖ ግዥ እንዲከናወን በደብዳቤ ጠይቀወናል፡፡

ስለሆነም የጠየቁት ገንዘብ ለሲነር ማናጅመንት ፕሮጀክት ግንባታ የሚያገለግል ሲሚንቶ ግዥ መሆኑ ታውቆ ተገቢው
ትብብር በእናንተ በኩል ይፈጸምላቸው ዘንድ እገልጻለሁ፡፡

ከሠላምታ ጋር

ሥንታየሁ ለገሠ

ኮማንደር

ፕሮጀክት አስተዳደር ዋና ክፍል ኃላፊ

ግልባጭ

 በኢት/ፖ/ዩኒቨርሲቲ ለፕሮጀክት አስተዳደር ዋና ክፍል

ሠንዳፋ

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage; Serve with Compassion!
 +251-116860570/+251-116860857/+251-966006433  1503 óŸe/Fax +251-116860420
facebook.com/ethiopanpolice t.me/Epupage www.epu.edu.et Sendafa/Ethiopia
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Police University
ከ 1939 ጀመሮ
Since 1946

ለአስተዳደር ልማ /ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ቁጥር/Ref.No…………………………………

d}/Date…………………………………………
ሠንዳፋ

የውስጥ የስራ ማስታዎሻ

ጉዳዩ፤- ወርሃዊ የስራ ሪፖርት

በፕሮጀክት አስተደራደር ዋና ክፍል ከታህሳስ 20 እስከ ጥር 20 /2016 ዓ.ም የተሰሩ ዋና ዋና ተግባራት፤-

የፎረንሲክ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክት ክትተልና ቁጥጥር ስራ ተሰርቷል፡፡

ለፕሮጀከቱ የሶሰተኛ ዙር አድቫንስ ፔይመንት ክፍያ ደብደቤ ተጽፏል፡፡

የግንባታ ዋጋ መጨመር (Price Escaiation) በተመለከተ አማካሪ ድርጅቱ ባለቤት እና ተቋራጭ ድርጅቱ ሆነን በኢትዮጵያ
ኮንስትራክሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤት የመስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይቶችን አካሂድን ለቀጣይ ድርድር የሚሆኑ
አቅጣጫዎችን ለመገንዘብ ችለናል፡፡

በስሚንቶ ችግር ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው ግንባታ ተቋራጩ እንዲያስተካክል በማድረግ ግንባታው አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ
እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

የ G+8 ሕንፃ ግንባታ የስምንተኛ ወለል ኮንክሪት ሙሊት እየተካሄደ ነው፡፡

የሳይት ወርክ ስራ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ፎሌን ሜዳ ጥርጊያ ስራ ተጠናቆ ሴሌክት ማቴሪያል የማንጠፍና መጠቅጠቅ
ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ የመንገድ ዳር ግንብ ግንባታ በሳይት ውስጥ፡፡

የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ፎሌን ሜዳ መሰረት ንጣፍ (Foundation work) በመሰራት ላይ ነው፡፡

የግድግዳ ልስን ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

የመግቢያ በሮች ስራ ማጠናቀቅ እና የበር ገጠማ ስራ እየተከናወነ ነው፡፤

የጅበሰም ስራ

የሴፒቲ ታንከር ግንባታ

የኮንክሪት ዲች ስራ

የጥበቃ ማማ ግንባታ

የዙሪያ አጥር ግንባታ እና የብረት ግሪል ብየዳ

የፕሎኬት ማምረት ስራ እየተከናወነ ነው ፡፡

አጠቃላይ የፕሮጅክት አፈጻጸሙ 42.30% ደርሷል፡፡

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage; Serve with Compassion!
 +251-116860570/+251-116860857/+251-966006433  1503 óŸe/Fax +251-116860420
facebook.com/ethiopanpolice t.me/Epupage www.epu.edu.et Sendafa/Ethiopia
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Police University
ከ 1939 ጀመሮ
Since 1946

የሲኔር ማናጅመንት ፕሮጀክት በተመለከተ፡- ቁጥር/Ref.No…………………………………

d}/Date…………………………………………
ፕሮጀክቱ የስራ መቀዛቀዝ ችግር ስለተስተዋለበት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ግንባታው ያለበት ደረጃ በክቡር ምክትል
ኮምሽነር ሰብሳቢነት የሦስትዮሽ የስራ ክንውን ግምገማ ተደርጎ ስራው በተገቢው መንገድ የሚቀትልበት አቅጣጫ ላይ
መግባበት ተደርሷል፡፡

ሰሞኑን ለሁለተኛ ዙር አድቫንስ ፔይመንት የወሰዱት ገንዘብ በጥምር አካውንት ተከፍቶ ለፕሮጀክቱ ግንባታ ስራ ብቻ
እንዲውል መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል! Protect with Courage; Serve with Compassion!
 +251-116860570/+251-116860857/+251-966006433  1503 óŸe/Fax +251-116860420
facebook.com/ethiopanpolice t.me/Epupage www.epu.edu.et Sendafa/Ethiopia

You might also like