ሞትና ዘላለማዊ ህይወት

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 15

2ኛ ትምህርት

ሞት በኃጢአት በተበከለች ዓለም

ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘፍ. 2፡16-17፣ ዘፍ.
3፡1-7፣ መዝሙር 115፡17፣ ዮሐንስ ወንጌል 5፡28-29፣ 2 ቆሮ. 5፡21።

የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ


ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት
ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” (ሮሜ 5፡12)

እግዚአብሔር ዓለማትን ሁሉና ይህችን ዓለም ወደ መኖር ያመጣው


በክርስቶስ በኩል ነው (ዮሐ. 1፡1-3፣10፣ ቆላ. 1፡16፣ ዕብ. 1፡2)። ነገር ግን
እግዚአብሔር አብ ክርስቶስን በማክበር ይህችን ዓለም አብረው
እንደሚፈጥሩ ሲናገር “ሉሲፈር በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ቀናበት” (Ellen G.
White, The Story of Redemption, p. 14) ከዚያም በርሱ ላይ ማሴር
ጀመረ።

ከሰማይ ሲባረር ሰይጣን በዚህች ምድር ላይ “የአዳምንና የሔዋንን ደስታ


ለመረበሽ” እና በሠማይ ሀዘንን ለማምጣት ወሰነ። በልቡ አዳምና ሔዋንን
እንዳይታዘዙ ማድረግ ብችል እግዚአብሔር ለነርሱ መንገድ አዘጋጅቶ ይቅር
ቢላቸው እርሱና ሌሎች የወደቁት መላዕክትም በዚያው መንገድ
የእግዚአብሔርን ምህረት እንካፈላለን ብሎ አሰበ። Ellen G. White, The
Story of Redemption, p. 27. የሰይጣንን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ
በመረዳት እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ራሳቸውን ለፈተና እንዳያጋልጡ
አስጠነቀቃቸው (ዘፍ. 2፡16-17)። ይህም ማለት ዓለም ፍፁምና ኃጢአት
አልባ በነበረችበት ወቅት የሰው ልጆች መታዘዝ የነበረባቸው ነገር ነበር
ማለት ነው።

በዚህ ሳምንት በአዳምና ሔዋን ውድቀት ዙሪያ እየተመለከትን እንዴት


ኃጢአትና ሞት ዓለማችንን እንደወረሰና ያኔ በኤድን እንዴት እግዚአብሔር
የተስፋን ዘር እንደተከለ እንወያያለን። መስከረም 28 ሰንበት ለመዘጋጀት
የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።

እሁድ:- መስከረም 22

በውጥረት ውስጥ የተነገሩ ቃላት

ዓለም ከጌታ እጅ ስትወጣ ፍፁም ነበረች (ዘፍ. 1፡31)። ሞት ለአዳምና


ለሔዋን እንግዳ ነገር ነበር። በዚያ አውድ እግዚአብሔር ወደ ኤድን ገነት
መጣና “ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን
ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” (ዘፍ.
2፡16-17) ዘፍጥረት 2፡16-17 ፍጹም በሆነው በኤድን ገነት የነፃ ምርጫን
እውነታ የሚያሳየው እንዴት ነው? ማለትም በራሳቸው ምርጫ መምረጥ
ባይችሉ ኖሮ እግዚአብሔር ማስጠንቀቅ ለምን አስፈለገው?
ከዚህ ማስጠንቀቅያ በኋላ በሆነ ጊዜ ሰይጣን የእባብን አካል ለብሶ ወደ
ኤድን ገነት ገባ። እባቡ የተከለከለውን ፍሬ በደስታ እየበላ አለመሞቱን ሔዋን
ተመለከተች። “የተከለከለውን ፍሬ ራሱ በልቶ” (ኤለን ኋይት፣ የሃይማኖት
አባቶችና ነብያት፣ ገፅ 54) ምንም አልሆነም ነበር።

ዘፍጥረት 3፡1-4ን ያንብቡ። ራስዎን በሔዋን ቦታ ያስቀምጡና እነዚያ ቃላት


አሳማኝ የሚመስሉት ለምንድነው?

ከሰው አስተሳሰብ አንፃር ከእግዚአብሔር ቃላት ይልቅ የእባቡ አመክንዮ


የበለጠ አሳማኝ ይመስሉ ነበር። በመጀመሪያ ደረጃ በዚያ ጊዜ በነበረው
ዓለም ስለኃጢአትና ሞት መኖር የሚገልፅ ማስረጃ አልነበረም። በሁለተኛ
ደረጃ እባቡ በእርግጥም የተከለከለውን ፍሬ እያጣጣመ እየበላ ነበር።
ስለዚህ ሔዋን እንደእርሱ ላለማድረግ ምን ይከለክላታል? የእግዚአብሔር
ትዕዛዝ እጅግ አፋኝና ትርጉም አልባ መስለው ታዩ።

እንዳለመታደል ሆኖ ሔዋን በነዚያ በሁለት የሚጋጩ ቃላት ጉዳይ ስትወስን


ሶስት መሠረታዊ መርሆችን ረስታ ነበር፤ (1) መንፈሳዊውን ነገር
ለመመርመር የሰው አስተሳሰብ ብቻ የሁልጊዜ የተሻለ መንገድ አይደለም፤
2) የእግዚአብሔር ቃል ምክንያታዊ ያልሆነና ትርጉም አልባ መስሎ ቢታየንም
ሁልጊዜ ትክክልና የሚታመን ነው፤ 3) በራሳቸው ክፉ ወይም ስህተት
ባይሆኑም እግዚአብሔር የመታዘዝ መፈተኛ እንዲሆኑ የሚመርጣቸው
ነገሮች አሉ። በኤድን ገነት የሔዋን ልምምድ የአንድ ጊዜ ጉዳይ አይደለም።
በየዕለቱና በየቅፅበቱ በእግዚአብሔር ቃል(በብዙዎች ጆሮ በማይሰጠው) እና
በዙሪያችን ባሉ አማላይ ጥሪዎች መካከል መምረጥ ይኖርብናል።
ምርጫዎቻችን ዘላለማዊ ውጤቶች ይኖሯቸዋል።

ግልፅ ከሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ጋር የሚጋጩ የዓለም


መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ሰኞ:- መስከረም 23

በእባብ መታለል

ዘፍጥረት 3፡1-7ን ያንብቡ። ሔዋን የእግዚአብሔርን ቃል ከመስማትና


የእባቡን ቃል ከመስማት ለመምረጥ የተጠቀመችው መለያ ምን ነበር?

ዘፍጥረት 3 የፈተና ይዘትን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።


እግዚአብሔር የተከለከለውን ፍሬ ከተመገቡ በእርግጥም እንደሚሞቱ
ለአዳምና ሔዋን አስጠንቅቋቸዋል(ዘፍ. 2፡16-17)። የእባብን አካል
በመልበስ ሔዋንን ወደ ኃጢአት ለመምራት ሰይጣን የተለያዩ ስልቶችን
ተጠቀመ። በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን መመሪያ ስለሁሉም ዛፎች አድርጎ
አቀረበ። “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን?” (ዘፍ.
3፡1) ብሎ ጠየቃት። ሔዋን ደግሞ ክልከላው ስለ አንዲቱ ዛፍ ብቻ
እንደሆነና ከሷ ከበሉ ወይም ከነኳት እንደሚሞቱ ነገረችው።

ከዚያ ሰይጣን ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ የሆነ ነገርን ተናገረ።


“ሞትን አትሞቱም” (ዘፍ. 3፡4) አላት።
በመጨረሻም እግዚአብሔር ሆን ብሎ አስፈላጊ እውቀትን ከርሷና ከባሏ
እንደከለከለ አድርጎ አቀረበላት። አታላዩ “ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ
እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ
እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።” (ዘፍጥረት 3፡5) ብሎ ተከራከረ።
የሔዋን አዲስ ነገርን ለማወቅ ያላት ጉጉት ወደ ሰይጣን ቀጠና እንድትገባ
አደረጋት። ከዚያ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ወይም የሰይጣንን ማባበያ
ለመቀበል አጣብቂኝ ውስጥ ገባች። ያየችውንና የራሷን ስሜት በማዳመጥ
የእግዚአብሔርን ቃል ተጠራጥራ ውሳኔዋን አደረገች።

በመጀመሪያ ከምግብነቱ አንፃር ዛፏ ለመብል መልካም እንደሆነች


ተመለከተች። በሁለተኛ ደረጃ ከውበት አንፃር “ለዓይኗ ደስታ” እንደሆነ
አሰበች። በሶስተኛ ደረጃ ከአሳማኝነት አንፃር “ለጥበብም መልካም ነበር”።
ስለዚህ በራሷ አስተሳሰብ የእባቡን ቃላት ለመስማትና ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ
ለመብላት በቂ ምክንያቶች ነበሯት።

አንዳንድ ሰዎች ሁሉም አይነት እውቀቶችን ብናውቃቸውና “መልካሙን


ብንይዝ” (1 ተሰ. 5፡21) ችግር የለውም ብለው ይሞግታሉ። አሳዛኝ የሆነው
የአዳምና የሔዋን የኤደን ገነቱ ልምምድ ግን ያ እውቀት በራሱ ችግር ውስጥ
የሚከት ሊሆን እንደሚችል ያሳያል። አንዳንድ ነገሮችን ባናውቃቸው
ይሻለናል።

ይህ ታሪክ ወደ ኃጢአት የሚመሩ ምርጫዎቻችንን ትክክል አድርጎ መከራከር


ምን ያክል ቀላል እንደሆነ የሚያስተምረን እንዴት ነው?
ማክሰኞ:- መስከረም 24

አትሞቱም

ዘፍጥረት 3፡4ን ያንብቡ። ይህ ውሸት በዘመናት የሚደገምባቸው የተለያዩ


መንገዶች የትኞቹ ናቸው? ሁሉ

የዚህ ውሸት አንዱ ኃይለኛ መገለጫ ነፍስ አትሞትም በሚለው እምነት


ውስጥ ይታያል። ይህ አስተሳሰብ ለብዙ ጥንታዊ ሃይማኖቶች እና
ፍልስፍናዎች መሠረት ነበር። በጥንቷ ግብፅ በፒራሚዶች ውስጥ
እንደሚታየው የሙታንን አስከሬን የማድረቅ ልምዶችን እና የቀብር ቦታ
በግንባታ ማስዋብን አነሳስቷል። ይህ ንድፈ ሐሳብ ከግሪክ ፍልስፍና ዋና
ምሰሶዎችም አንዱ ሆኗል። ለምሳሌ፣ በፕላቶ ሪፐብሊክ ውስጥ ሶቅራጥስ
ግላኮንን “ነፍሳችን እንደማትሞትና እንደማትጠፋ አታውቅምን?” ሲል
ጠየቀው። በፕላቶ ጽሁፍ ላይ፣ ሶቅራጥስ በተመሳሳይ ሁኔታ “ነፍስ
የማትሞት እና የማትጠፋ ናት፣ እናም ነፍሳችን በእውነት በሲኦል ውስጥ
ትኖራለች” በማለት ተከራክሯል። እነዚህ የፍልስፍና ፅንሰ-ሀሳቦች አብዛኛው
የምዕራባውያን ባህል እና ከሐዋሪያት በኋላ ያለውን የክርስትናን እምነት
ቀርፀዋል። ነገር ግን የመነጩት ቀደም ብሎ በኤደን ገነት ውስጥ ከራሱ
ከሰይጣን ነበር።

በኤደን የፈተና ማዕከል ላይ፣ ሰይጣን ለሔዋን “አትሞቱም!” በማለት


አረጋገጠላት። በዚህ አገላለፅ ሰይጣን የራሱን ቃል ከእግዚአብሔር ቃል
በላይ አስቀመጠ።

ነፍስ አትሞትም ከሚለው አስተምህሮ በተቃራኒ እነዚህ ጥቅሶች ምን


ያስተምራሉ? ይህን ውሸት ለመቋቋምስ እንዴት መጠቀም ይቻላል? ( መዝ.
115:17፣ ዮሐ. 5:28፣ 29፣ መዝ. 146:4፣ ማቴ. 10:28፣ 1 ቆሮ. 15:51-
58 )

በዘመናዊው ዓለም ውስጥ እንኳን ነፍስ አትሞትም የሚለው ሰይጣናዊ


ጽንሰሐሳብ ተንሰራፍቷል። መጽሃፎች፣ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች
ስንሞት በቀላሉ ወደ ሌላ ንቃተ-ህሊና እናልፋለን የሚለውን ሃሳብ
ማስተዋወቅ ቀጥለዋል። ይህ ስህተት በብዙ የክርስቲያን መድረኮች ላይ
መታወጁ እንዴት የሚያሳዝን ነገር ነው። ሳይንሱም ሳይቀር በዚህ ውስጥ
ገብቷል። በአሜሪካ ውስጥ የሞቱትን ነገር ግን እስካሁን በሕይወት አሉ
ብለው የሚያምኑትን በነርሱ አጠራር “ድህረ ቁስ አካላት” የተባሉትን ሙታንን
ለማግኘት የሚያስችለንን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር የሚሞክር ተቋም አለ። ይህ
ስህተት በጣም ከመስፋፋቱ አንፃር በሰው ልጅ ታሪክ የመጨረሻ ክስተቶች
ውስጥ ወሳኝ ሚና መጫወቱ ምንም አያስደንቅም።

በእርስዎ ባህል ውስጥ ይህ ውሸት በምን መንገዶች ይገለጻል? ስሜታችን


ከሚነግረን ነገር በላይ በእግዚአብሔር ቃል መታመን ያለብን ለምንድን ነው?

ረቡዕ:-መስከረም 25
የኃጢአት ውጤቶች

በዘፍጥረት 3፡7-19 እና በሮሜ 5፡12 መሠረት ዋናዎቹ የኃጢአት ውጤቶች


የትኞቹ ነበሩ?

ሔዋን በእባቡ አሳማኝ ንግግር ስለተማረከች የምትከተለው መንገድ


የሚያስከትለውን መዘዝ አላሰበችም። ከተከለከለው ፍሬ የመብላት ተግባር
በራሱ በትክክል የሚወክለውን ያህል ጉልህ አልነበረም። ሔዋን እንዲህ
ባለው የዓመፀኝነት ድርጊት ለእግዚአብሔር ያላትን ታማኝነት በማፍረስ
ለሰይጣን ታማኝነቷን ሰጠች።

ዘፍጥረት 3 የአዳምና የሔዋን ውድቀት እና አንዳንድ በጣም አሳዛኝ


ውጤቶችን ይገልጻል። ከሥነ-መለኮት አንፃር፣ ሁለቱም በቲዎፎቢያ
(እግዚአብሔርን በመፍራት) ተይዘው ራሳቸውን ከእርሱ ደበቁ (ዘፍ. 3፡8)።
ከስነልቦናዊና ማህበራዊ ግምገማ አንፃር በራሳቸው አፈሩ እና እርስ በርስ
መካሰስ ጀመሩ (ዘፍ. 3፡7፣ 9-13)። ከአካላዊ አተያይ ላብ የሚያልባቸው፣
ህመም የሚሰማቸው እና በመጨረሻ የሚሞቱ ሆኑ (ዘፍ. 3፡16-19)።
ከሥነ-ምድር አንጻር የተፈጥረችዋ ዓለም ተበላሸች (ዘፍ. 3፡17፣18)።

የኤደን ገነት እንደቀድሞው ውብ እና አስደሳች ቦታ መሆኑ ቀረ። “በአበባ እና


በሚረግፍ ቅጠል ላይ የመጀመሪያዎቹን የመበስበስ ምልክቶች ሲያዩ
አዳምና አጋሩ ሰዎች አሁን ስለሞቱት ሰዎች ከሚያዝኑት በላይ አዝነዋል።
የደካሞችና ለስላሳ አበባዎች መሞት በእርግጥም ለሐዘን መንስኤ ነበር።
ጥሩዎቹ ዛፎች ቅጠሎቻቸውን ሲጥሉ ግን ሞት የሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ
ድርሻ እንደሆነ አረጋገጠ።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት፣
ገጽ. 62።

አዳምና ሔዋን መኖራቸውን አቁመው ወዲያው አልሞቱም፤ ነገር ግን በዚያው


ቀን የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው። እግዚአብሔር ለአዳም፡- “ወደ ወጣህበት
መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ
አፈርም ትመለሳለህና።” (ዘፍ. 3፡19)። ውድቀቱ ለሰው ልጆች ሁሉ አሳዛኝ
ውጤቶችን አመጣ። ሐዋርያው ጳውሎስ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ
ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ
ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” በማለት ተናግሯል(ሮሜ 5:12)።

አሳዛኙ እውነታ የሰው ልጅ በሁሉም ዘመናት እንዳደረገው እኛም ዛሬ በኤደን


የተፈጸመውን መዘዝ እየተቀበልን መሆናችን ነው። ነገር ግን በኢየሱስ እና
በመስቀሉ ምክንያት ኃጢአት ዳግመኛ በማይነሳበት ዓለም ውስጥ የዘላለም
ሕይወት ተስፋ ስላለን ምንኛ አመስጋኞች ሆነን ይሆን? የሔዋንን አሳዛኝ
ሁኔታ ስናሰላስል የራሳችን ኃጢአቶች ስለሚያስከትሏቸው ውጤቶች ምን
ትምህርት እናገኛለን?

ሐሙስ:- መስከረም 26

የመጀመሪያው የወንጌል የተስፋ ቃል


ዘፍጥረት 3፡15-21ን ያንብቡ። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ለሰው ልጆች
ሁሉ ምን ተስፋ ማግኘት ይቻላል?

ዘፍጥረት 3 ከውድቀት በኋላ በአለማችን ለይ ስለሆነው አሳዛኝ ክስተት


ይገልፅልናል። ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር ተለወጠ፤ አዳምና ሔዋንም ዓለም
ከኃጢአት በፊትና በኋላ ምን እንደምትመስል ልዩነቱ ታያቸው። ግን በዚህ
መደናገጥና ተስፋመቁረጥ ውስጥ ሆነው ሳለ እግዚአብሔር ለአሁኑ
ማረጋገጫ ለወደፊቱ ደግሞ ተስፋን ሰጣቸው። በመጀመሪያ እባቡን በመሲሁ
መምጣት የተስፋ ቃል ረገመው። “በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ
መካከል፣ ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም
ተረከዙን ትቀጠቅጣለህ።”— (ዘፍጥረት 3፥15) ሲል አወጀ።

ጠላት (enmity) የምትለው ቃል ወይም በእብራይስጥ ‘eybah’ ሲሆን


በክፉና በመልካም መሀል እስከመጨረሻው የሚዘልቀውን ተጋድሎ ብቻ
የሚወክል ሳይሆን በእግዚአብሔር ጸጋ በሰዎች አዕምሮ ውስጥ
የተተከለውን የግል የሆነ ኃጢዓትን መጥላትንም ያካትታል። ከፍጥረታችን
ሁላችንም የወደቅን (ሙታን) (ኤፌ. 2፡1፣5)፤ “የኃጢዓትም ባሪያዎች” ነበርን
(ሮሜ 6፡20)። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነው ይህ ጸጋ ከሰይጣን ጋር
ጠላትነት እንዲኖረን አድርጓል። በኤድን ያገኘነውና የመለኮት ስጦታ የሆነው
ይህ ጠላትነት(enmity) የአዳኙን ጸጋ እንድንቀበል አስችሎናል። ይህን
የሚለውጥ ጸጋና አዲስ ኃይል ካልተቀበልን የሰው ዘር የሰይጣን ምርኮኛ
እንደሆነ ይቀጥላል፤ ሁሌም የእርሱን ጉትጎታ ለመቀበልና ለማድረግ ዝግጁ
እንሆናለን።
ጌታ በመቀጠል ይህን መሲሐዊ ተስፋን ለማስረዳት የእንስሳትን መሥዋዕት
ተጠቀመ (ዘፍ. 3፡21 ይመልከቱ) “አዳምም እግዚአብሔር በሰጠው
መመሪያ መሰረት ለኃጢዓት መስዋዕት ሲያቀርብ ለእርሱ በጣም
የሚያሠቃይ ሥነ ሥርዓት ነበር።። እግዚአብሔር ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን
ሕይወት ለመቅጠፍ እና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ለማቅረብ እጁ መነሳት
ነበረበት። ለመጀመሪያ ጊዜም ሞትን አየ። የሚደማውን እንስሳ፣ በሞትና
በህይወት ጣረሞት ውስጥ ሲንፈራፈር ሲያይ ለሰው ልጅ ሲል መስዋዕት
የሚሆነውን፣ በሟቹ እንስሳ የተመሰለውንና ወደፊት የሚመጣውን
የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን በእምነት ማየት ነበረበት።” ኤለን. ጂ.
ኋይት፣ The story of redemption, ገጽ 50

2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21ን እና ዕብራውያን 9፡28ን ያንብቡ። በኤድን መጀመሪያ


ላይ ስለተገለጠው ነገር እነኚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል?

ቀስ በቀስ እንደሚሞቱ በማወቅ (ዘፍ. 3፡19፣ 22-24) አዳምና ሔዋን


ከኤድን ገነት ጥለው ወጡ። ነገር ግን ዕራቁታቸውን ወይም ባገለደሙት
በበለስ ቅጠል አልወጡም (ዘፍ 3:7)። እግዚአብሔር እራሱ ከቆዳ ልብስ
አዘጋጀ ደግሞም እራሱ አለበሳቸው (ዘፍ. 3፡21)፤ ይህም የጽድቅ ልብስን
የመጎናጸፍ ምልክት ነው (ዘካ. 3:1-5፣ ሉቃ. 15፡22ን ይመልከቱ)። ስለዚህ፣
በዚያን ጊዜም ቢሆን፣ ገና ከመጀመሪያው፣ በኤደን፣ ወንጌል ለሰው ልጆች
ተገልጦ ነበር።

አርብ:-መስከረም 27
ተጨማሪ ሀሳብ

ከኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፎች “የሃይማኖት አባቶች እና ነቢያት” በሚለው


መጽሐፍ ውስጥ፣ ከገጽ 52-62 “ፈተናና እና ውድቀት” የሚለውንና “የቤዛነት
እቅድ” ገጽ 63-70 የሚለውን ክፍል እንዲሁም ስነ ትምህርት ከሚለው
መጽሐፍ ውስጥ “የመልካም እና ክፉ እውቀት” ከገጽ 2327 የሚል ርዕስ
ያለውን ክፍል ያንብቡ። በቅርብ ዓመታት ውስጥ የሞት ጫፍ ልምምዶች
(Near Death Experiences, NDEs) በሚባሉት ላይ ጥናቶች
ተካሂደዋል። የሚሆነው ሰዎቹ “ይሞታሉ”፤ ልባቸው መምታቱን ያቆማል፤ እና
መተንፈስ ያቆማሉ። ሆኖም፣ ከዚያ በኋላ ወደ ህይወት ይመለሳሉ፤ ነገር ግን
ወደ ሌላ የህልውና ግዛት ውስጥ ስለመንሳፈፋቸው እና ከብርሃናማ ፍጡር
ጋር ስለመገናኘታቸው አስደናቂ ታሪኮችን ይዘው ይመጣሉ።

አንዳንዶች ለረጅም ጊዜ የሞቱ ዘመዶቻቸውን ስለመገናኘታቸው ያወራሉ።


ስለ ሞት እውነቱን ያልተረዱ ብዙዎች ክርስቲያኖችንም ጨምሮ እነዚህ
ታሪኮች የነፍስ አለመሞትን የበለጠ የሚያረጋግጡ ናቸው ብለው ያምናሉ።
ነገር ግን፣ አብዛኞቹ እነዚህ ተሞክሮዎች ያጋጠሟቸው በሞቱበት ወቅት
ያገኟቸው መንፈሳዊ ፍጡራን አጽናኝ ቃላትን፣ ስለ ፍቅር፣ ሰላም እና ጥሩነት
ጥሩ መግለጫዎችን እንደሰጧቸው ይናገራሉ(እና ይህ የሆነ ነገር ችግር
እንዳለ የሚያሳይ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል)።

ነገር ግን በክርስቶስ ስለመዳን፣ ስለ ኃጢአት እና ስለ ፍርድ ምንም


አይሰሙም። ከሞት በኋላ ያለውን የክርስቲያን ሕይወት እየቀመሱ፣ ቢያንስ
ቢያንስ መሠረታዊ የሆኑትን የክርስትና ትምህርቶች ከእሱ ጋር ማዳበር
አልነበረባቸውም? ሆኖም፣ የተማሩት ነገር በአብዛኛው እንደ ኒው ኤጅ
አስተምህሮ ይመስላል፤ ይህም በብዙ አጋጣሚዎች ለምን “ከመሞታቸው”
በፊት ከነበሩበት ባነሰ ዝንባሌ ወደ ክርስትና እንደሚመጡ ሊያስረዳ
ይችላል። እንዲሁም፣ ከነዚያ ክርስትያኖች መካከል አንዳቸውም ሞተው
የተመለከቱት ነገር ክርስትያኖች እንደሚያስተምሩት አይነት ሰማይ ስለመሆኑ
ያላመኑትና ከኒው ኤጅ ስሜታዊ መግለጫዎች በተቃራኒ ሌላ የክርስትና
አስተምህሮ ያላገኙት ለምን ይሆን? መልሱ በኤደን ሔዋንን ባሳታት እባብ እና
በተመሳሳይ ውሸት ተታልለው ነው። (11ኛ ትምህርትን ይመልከቱ።)

የመወያያ ጥያቄዎች

1.የአዳምና የሔዋን ተሞክሮ አምላክ ይቅር ባይነት የኃጢአት መዘዝን ሙሉ


በሙሉ እንደማይሽር የሚያሳየው እንዴት ነው? ይህን ሁልጊዜ ማስታወስ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

2.መልካምና ክፉን የሚያስታውቀው ዛፍ ለአዳምና ለሔዋን የጠላት


“የእርግማን ምድር” ነበር። እኛው ራሳችን ለመግባት የምንፈተንባቸው
አንዳንድ “የእርግማን ምድሮች” የትኞቹ ናቸው?

3.ሰይጣን ለአምላክ ሕዝቦች “የክርስቶስ መሥፈርቶች ቀድሞ ከሚያምኑት


ባነሰ ደረጃ ጥብቅ እንደሆኑና ከዓለም ጋር ቢስማሙ ከዓለማውያን ሰዎች
ጋር ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ።”—Ellen G. White፣ Testimonies
to Ministers and Gospel Workers, p. 474. ሊያሳምናቸው
እየሞከረ ነው። በዚህ ረቂቅ ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ ምን ማድረግ
ይኖርብናል?

You might also like