Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 3

አረፍተ ነገር

ባለቤት ና ማሰሪያ አንቀጽ ያለው የተሟላ ስሜትን የሚሰጥ የቃላት ህብረት ነው።አረፍተ ነገሮች የተለያዩ

እንደመሆናቸው

።ይህ ትርጉም ሁሉንም አረፍተ ነገሮች ያካትታቸዋል።ቃላት እርስ በርሳቸው እንደ ሰንሰለት ተያይዘው ገብተው

አንድ የተሟላ ስሜት ያለው ሃሳብ ሲገልጹ መደበኛ ሃረግ ወይም ዐረፍተ ነገር ይመሰርታሉ።

መደበኛ ሃረግን ከሌሎች ሃረጎች የለየው ማሰሪያ አንቀጽ እንደመሆኑ ዐረፍተ ነገርም ከሌሎች የሃሳብ

መግለጫዎች

ሁሉ የሚለየው የማሰሪያ አንቀጽ መኖር ነው።ይህም ይዘት መደበኛ ሃረግን ከዐረፍተ ነገር ጋር ያመሳስለዋል።

ዐረፍተ ነገር ማለት በቀጥተኛ ፍቺ ሲታይ የነገር ማረፊያ፣መግቻ፣መቋጫ ማለት ይሆናል።የሚገለጸው ነገር

ማረፊያ የሚያገኘው ደግሞ ሃሳቡን ሰብስቦ በሚገታው በማሰሪያ አንቀጹ ነው።(ዐ.ነገሩ ሃሳቡ ተንጠልጥሎ ያልቀረና

የተጠቃለለ

ንግግር ማለት ነው።)

የአረፍተ ነገር አይነቶች

 ነጠላ (ተራ) አረፍተ ነገር

 ውስብስብ አረፍተ ነገር

 ነጠላ ዐ.ነገር

ነጠላ(ተራ) አረፍተ ነገር ከአንድ ባለቤት ና ከአንድ ማሰሪያ አንቀጽ ብቻ የተመሰረተ የተሟላ ስሜትን

የሚሰጥ የቃላት ህብረት ነው።ይህ ዐረፍተ ነገር ከአንድ ባለቤትና ከአንድ ማሰሪያ አንቀጽ ብቻ ይመሰረታል

ስለተባለ

ግን ሁለት ቃላት ብቻ ይኖሩታል ማለት አይደለም ባለቤቱም ሆነ ማሰሪያ አንቀጹ የየራሳቸው ገላጭ እንዲኖ

ራቸው ሆነው ሊመሰረት ይችላል።በሌላም አገላለጽ ነጠላ ዐረፍተ ነገር መደበኛ ሃረግ ነው ሊባል ይችላል።

መደበኛ ሃረግ ና ነጠላ ዐረፍተ ነገር የስም ልዩነት እንጂ የይዘት ልዩነት የላቸውም ባለቤት ና ማሰሪያ

አንቀጽ የየራሳቸው ገላጭ እንደሚኖራቸው ንዑስ ሃረግ እንጂ ጥገኛ ሃረግ በውስጣቸው መያዝ እንደማይችሉ

መገንዘብ

ያስፈልጋል።

ለምሳሌ ፦ታታሪው ነጋዴ ብዙ ብር አተረፈ።


ቅጽል ወይም የስም ስም ወይም ተ.ግ(ገላጭ ቃል መሆንን/መኖርን
ገላጭ ተውላጠ ስም ወይም ገላጭ ንዑስ አመልካች(ድርጊት)
ወይም ንዑስ ሃረግ ሃረግ ወይም አመልካች ማሰሪያ
የሆነ ባለቤት ማሰሪያ አንቀጽ

ጎበዝ ተማሪ ትናንት ተሸለመ

ከሰአት በኋላ ትምህርት በዘጠኝ ሰአት ይጀመራል

ቀዩ ልጅ ወንድሜ ነው

በምሳሌው እንደምናየው ተጨምረው የገቡት የባለቤትና የማሰሪያ አንቀጽ ክፍሎች ለነጠላ ዐ.ነገሩ ተጨማሪ

ሃሳብ

ለመገንባት የገቡ እንጂ የዐ.ነገሩ ወሳኝ ክፍሎች እንዳልሆኑ በመዋቅሩ ውስጥ የቀረቡት ምሳሌዎችን ማየት ይቻላል።

እና የመዋቅሩ ቀመር ሲነበብ ቅጽል(የስም ገላጭ) ሲደመር ባለቤት፣ሲደመር ተውሳከ ግስ (የግስ ገላጭ) መሙያ

ሲደመር፣ማሰሪያ አንቀጽ ይሆናል።

ነጠላ ዐ.ነገር መዋቅር ውስጥ የሚገባው ማሰርያ አንቀጽ የድርጊት ከሆነ ተውሳከ ግስ (የግስ ገላጭ) ሊኖረው

ይችላል።ማሰሪያ አንቀጹ የመሆን ከሆነ ግን መሙያ ሊኖረው ይችላል።

 ውስብስብ ዐ.ነገር

አንድ ዐ.ነገር ተራ ካልሆነ ውስብስብ ነው።በውስጡም ሁለት ና ከዚያ በላይ ግሶችን የያዘ ነው።ዐ.ነገሩ

ከውስብስብ ሃረጎች የሚፈጠር ሰፊ መዋቅር ነው።

ሀ.ትእዛዝ እንደሰጠኸን ስራውን በአጥጋቢ ሁኔታ ሰርተነዋል።

ለ.አካባቢን መንከባከብ ስለቀረ በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ወረርሽኝ ገብቷል።

ሐ.ወደ ውጪ የሄደው መምህር ለዘመዱ ደብዳቤ ላከ።

ጥገኛ ሐረግ(መደበኛ ስም ባለቤት ተውሳከ ግስ(መሙያ) ማሰሪያ አንቀጽ


ሐረግ)
ትዕዛዝ እንደሰጠኸን እኛ (አንተ) ስራውን በአጥጋቢ ሁኔታ ሰርተነዋል

አካባቢን መንከባከብ በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ወረርሽኝ ገብቷል


ስለቀረ

ወደውጪ የሄደው መምህር ለዘመዶቹ ደብዳቤ ላከ

ዐ.ነገር የሐረጎችህ ሥርዓታዊ ግንኙነት የሚያስገኘው ክፍል መዋቅር ነው።የሚያስገኘው መሰረታዊ

ተዋቃሪዎች ረገድ ስምሙ ሆነው መገኘት ለዓረፍተ ነገሩ ሰዋሰዋዊ መሰረታዊ ናቸው።እነዚህ ሐረጎች በየውስጣቸው

የገቡት ሐረጎች ተራ ና ውስብስብ ያሰኛቸዋል።

ለምሳሌ፦

ሀ.ትንሿ ልጅ በፍጥነት ወደ ጨዋታዋ ሄደች ።

ለ.የዚህ ከተማ መሐንዲስ እርሱ ነው።

ሐ. አሰፋ አጭር ነው።

መ.የዛሬ ዐስራ አምስት ቀን የተከልከው ባህር ዛፍ ጠደቀ።

ሠ.መንግስቱን ትናንትና በዚህ በኩል ሲያልፍ አየሁት።

ረ.ብዙ ሰዎች አለምን ናቁ።

You might also like