የሽያጭ ውል

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ሚያዚያ

ቡና ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ፤ ለመሸጥ፤እና ለመግዛት የተፈረመ የመግባቢያ ሰነድ


ሻጭ

አድራሻ

ገዢ

አድራሻ

1.የውል አላማ

1.1 ይህ ውል ሻጭ ወደ ውጭ ሀገር የሚላክ እና ደረጃውን የጠበቀ የቡና ምርት ያላቸው እና ይህንኑ ለመሸጥ
ፍላጎት ያላቸው በመሆኑ፤ ገዢ ደግሞ በ ሀገር ላላቸውየቡና ገበያ ስራ ደረጃውን የጠበቀ
የቡና ምርት ለመግዛት የሚፈልጉ በመሆኑ ሻጭ እና ገዢ ከዚህ በታች በተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች መሰረት
የተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ ነው፡፡

1.2 ይህ የመግባቢያ ሰነድ በቀጣይ ለሚፈረመው የሽያጭ ውል እንደ ግብዐት የሚያገለግል ሲሆን በውስጥ
የተቀመጡት ድንጋጌዎች በቀጣይ ከሚፈረመው የሽያጭ ውል ድንጋጌዎች ጋር ተስማምተው ይተረጎማሉ፡፡

2. ውል ስላረፈበት የቡና ምርት እና የውሉ ጠቅላላ ድንጋጌዎች

2.1 በዚህ መግባቢያ ሰነድ መሰረት የሚሸጠው ቡና በ ክልላዊ መንግስት ዞን ወ


የሚመረት እና ብዛት ቶን/ኪሎግራም/የሆነው ቡና ሲሆን ይህም ቡና በገበያ ስሙ የ
ቡና በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

2.2 ሻጭ ይህ ቡና ምርት ለውጭ ሀገር ገበያ ተገቢ የሆነው ደረጃ ያሙአላ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ይሰጣሉ፡፡

2.3 ሻጭ በዚህ ስምምነት መሰረት የሚሸጡትን ቡና ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን
ማረራረጫ የመስጠት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህንንም በተመለከተ ከኢትዮጲያ ምርት ገበያ፤ ከቡናና ሻይ
ባለስልጣን እና ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ መንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር ተገቢውን ክሊራንስ አቅርበው ከገዢ ጋር
በሚደረግ የቡና ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ ያለምንም መቆራረጥ የመላክ ግዴታ አለባቸው፡፡

2.4 ሻጭ ደረጃውን የጠበቀውን ቡና ተገቢ የሆነውን ክፍያ በመፈፀም እስከ ጅቡቲ ድረስ በማድረስ መርከብ
ላይ መጫኑን ማረጋገጥ የሚገባቸው ሲሆን ቡና ከሚጫንበት መጋዘን እስከ ጅቡቲ ድረስ ያለው ጉዞ ተገቢ
የሆነውን የመድፍ ሽፋን የተሙላለት መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

ሻጭ የሚላከው ቡና ደረጃውን የጠበቀ ለመሆኑ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ብቃት ማረጋገጫ የማቅረብ


ግዴታ ያለባችው ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ ገዢ በብቃት ማረጋገጫ ሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

3.ስምምነቱ ያረፈበት የገንዘብ መጠን፤ የሚላከው ቡና መጠን እና የአከፋፈል ሁኔታ

3.1.ሻጭ ለገዢ በሚያደርጉት ሽያጭ በሽያጭ ወቅት የሚኖረው ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ በስምምነት


ሊያወጡ የሚችሉ ሲሆን ይህም የገንዘብ መጠን ግን ግራ ቀኙ ወገኖች ከሚያወጡት የዋጋ ገደብ ውጭ
ሊወጣ አይችልም፡፡
ሚያዚያ

3.2.በዚህም መሰረት ሻጭ እና ገዢ በየአመቱ የዋጋ ገደብ የሚያወጡ ሲሆን ይህ የዋጋ ገደብ ዝቅተኛውን እና
ከፍተኛውን የሽያጭ ዋጋ መጠን የሚወስን ሬንጅ ያለበት መሆን አለበት፡፡

3.3.ሻጭ ለሚሸጡት ቡና ገዢ ቡናው መርከብ ላይ ከመውጣቱ በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ መፈፀም
አለባቸው/ቡናውን ከተረከቡ በኃላ ይከፍላሉ/ቅድሚያ የተወሰነ መጠን በመክፈል ቀሪውን ከሽያጭ በኃላ
ይፈጽማሉ፡፡

4.የግራ ቀኙ ወገኖች ግዴታዎች

1.ሻጭ ደረጃውን የጠበቀ ቡና ገዢ የግዢ ትዕዛዝ ከሰጡበት እለት አንስቶ ባሉት ቀናት ውስጥ
ወደ ጅቡቲ ወደብ በማድረስ ወደ መርከብ የመጫን ግዴታ አለባቸው፡፡

2.ሻጭ የሚላከው ቡና እስከ መርከቡ ድረስ ያለውን የትራንስፖርት፤ የመድን እና ከጉዞው ጋር ያለውን ተያያዥ
ወጪዎች መሸፈን አለባቸው፡፡

3.ከገዢ ትዕዛዝ ከደረሳቸው ቀናት አንስቶ ስምምነት በተደረሰበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ቡናውን መላክ ባይችሉ
ለሚደርሰው ኪሳራ ከገዢ ጋር በመስማማት ይከፍላሉ፡፡

4.ገዢ በውሉ መሰረት የሻጭ ክፍያ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡

5.የውል ጊዜ

ይህ ውል ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ለ 5(አምስት) ዓመታት የጸና ሲሆን እንደተዋዋይ ወገኖች ስምምነት የውሉ
ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

6.የውል መፍረስ

6.1 ይህ ውል ተዋዋይ ወገኖች ሲስማሙ ሊፈርስ ይችላል፡፡

6.2 ይህ ውል የውሉ አላማ ሲሳካ ሊፈርስ ይችላል፡፡

6.3 ይህ ውል ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው ወገን ግዴታውን ባይወጣ ግዴታውን በተወጣው ወገን
ላልተወጣው ወገን የ ወራት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሰጠት አለበት፡፡

7.አለመግባባት

7.1 በግራ ቀኙ ወገኖች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ተዋዋይ ወገኖች ልዩነታቸውን በስምምነት ለመጨረስ
ተገቢውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፤

7.2 ይህ ሳይሳካ ቀርቶ ጉዳዩ ወደ ክርክር የሚያስገባ ቢሆን ግራቀኙ በሚመርጣቸው የሽምግልና ዳኞች
አማካኝነት ጉዳዩ በሽምግልና ደኝነት ጉባኤ የሚታይ ሲሆን ሰብሳቢ ዳኛ ደግሞ ግራ ቀኙ ወገኖች
በሚመርጣቸው የሽምግልና ዳኞች ምርጫ የሚመረጥ ይሆናል፡፡

7.3 የሽምግልና ዳኞችን ወጪ በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የሶስቱን ዳኞች አበል በእኩል የመክፈል ግዴታ
ያለባቸው መሆኑን ተስማምተዋል፡፡
ሚያዚያ

ወይም

ግራ ቀኙ ወገኖች በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በስምምነት መፍታት ካልቻሉ ስልጣን ባለው የፌደራል
ፍ/ቤት የሚታይ ይሆናል፡፡

8. ውሉ የሚመራበት ህግ

ይህ ውል በኢትዮጲያ ህግና ስርዐት የሚመራ ይሆናል፡፡

ይህ የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ሚያዝያ ቀን 2016 ዓ.ም ተዋዋይ ወገኖችና ምስክሮቻቸው


በተገኙበት ተፈረመ፡፡

ስለ ገዢ ስለ ሻጭ

ስም
ስም

ፊርማ ፊርማ

ምስክሮች

ስም ፊርማ

ስም ፊርማ

You might also like