ለሚ ኩራ ህዋስ ማወያያ ሰነድ.docx

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 6

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ብልፅግና

ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት

የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ለብልፅግና ፓርቲ ህዋስ


አባላት ማወያያ የተዘጋጀ ሰነድ

ታህሳስ/2016 ዓ.ም
ለሚ ኩራ

1. መግቢያ
እንደሚታወቀው አገራችን የበርካታ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቶች ባለቤት ከመሆንዋ ጋር ተያይዞ በአለም

5
አቀፍ ቅርስነት ተመዝግበው አገራችንን በማስተዋወቅ ላይ የሚገኙ ቅርሶቻችን በርካታ ሲሆኑ ከነዚህ
ዉስጥ አንዱ የከተራ/ጥምቀት በአል አንዱ ነዉ፡፡
የከተራ/ጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በደማቅ ሥነ-
ስርዓት የሚበር ክብረ በዓል ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገበ ቅርስ በመሆን ቱሪዝምን በመሳብ
የአገራችን የገጽታ ግንባታ ከፍ የሚያድርግ ከመሆኑ በተጨማሪ ቱሪስቶችን በመሳብ የውጪ ምንዛሪን
እያስገኝ ይገኛል፡፡

የጥምቀት የአደባባይ በዓል በመሆኑ የሀገራችንና የአለም ሕዝብ በቀጥታ የሚከታተለው በዓል ነው፡፡
ስለሆነም በአወንታ የሚመለከቱት ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትን ያህል የጥፋት ኃይሎች ትውፊቱን
ለመጉዳት እና በገጽታው ላይ ጥላሸት ለመቀባት እንዲሁም የራሳቸውን አጀንዳና ሴራ በዚህ አጋጣሚ
ለማሳካት የሚችሉትን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ ይታወቃል፡፡

ይህም በተለያየ አካባቢ (ክልል)የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ቡድኖች የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የበአሉን ኩነት
የማበላሸትና ያልተገቡ መልዕክቶችን የመስተላለፍ ፍላጎት ያለዉ መሆኑን መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ ጽንፈኛው
ኃይል ቡድንም ፀጉረ ልውጦችን ወደ ከተማ በማስገባት የተለያዩ ብጥብጦችን እንዲነሱና የተለያዩ
ጥፋቶችን በመፈፀም የሕዝቡን ሰላም በማወክ መንግስት ሕግን ማስከበር አልቻለም የሚል መልዕክት
ለማስተላላፍ እየተዘጋጁ ይገኛል፡

በሌላ በኩል በዚህ ብቻ የሚቆም ሳይሆን ብጥብጡን የብሔርና የሃይማኖት መልክ በማስያዝ በሕዝቦች
መካከል ያለመተማመን እንዲፈጠርና ግጭት እንዲባባስ ለማድረግ ያለውን ኃይል ሁሉ ለመጠቀም ሰፊ
ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ስለሆነም መላው አመራራችንና አባላችን በዓላቱን እንደምቹ አጋጣሚ
በመጠቀም ጽንፈኛዉንና ጸረ-ሰላም ኃይሉ ተላላኪዎችን የማስረግና የማስማራት እቅድ ማክሸፍ
የሚያስችል ጠንካራ ዝግጅት በማድረግ በአሉን በአብሮነት እና በወንድማማችነት/እህትማማችነት መንፈስ
እንዲከበር አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በህዋስ ውይይታችንም በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግስታችን ለሰላም ያለውን


ቁርጠኝነት፣የሀይማኖት ተቋማትን ለመደገፍ እየሰራው ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በአላ በሰላማዊ መንገድ
እንዲከበር የአባላት ሚና ላይ ትኩረት በማድረግ ውይይት ማድረግና ጠንካራ አቋም ይዞ ለመውጣት
እንዲቻል ይህ የህዋስ ውይይት መነሻ ፅሁፍ ተዘጋጅቷል፡፡

2. የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ዳራ


የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት
የሚያስታውሰው ደማቅ ሀይማኖታዊ በዓል ነው።

1
በሀገራችን በየዓመቱ ጥር 10 ቀን በከተራ ዕለት ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ቦታ
በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው
በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ያሳልፋሉ።

ጥር 11 ቀን የጥምቀት ዕለት ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት
መሪነት ሁሉም ወደ ከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። የክርስትና ስማቸውንም የረሱ ወደ
ካህናቱ ይቀርቡና አዲስ የክርስትና ስም ይቀበላሉ። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤ ሰማያዊው
በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ» የሚለው የዕለቱ ቀለም በሊቃውንቱ አንደበት በያሬዳዊ ዜማ ጎልቶ ይሰማል።
ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬና ወንዱ በሆታ፤
ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው
ይመለሳሉ።ወጣቶች ከመንፈሳዊ ዝማሬው ጎን ለጎን የተለያዩ ባህላዊ ዘፈኖች፣ጭፈራዎችና ትርዒቶች
ጭምር የሚቀርብበት በመሆኑ በዓሉን ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው በዓል ነው፡፡

3. የጥምቀት በዓል ለሀገራችን ያለው ፋይዳ


የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግስታት ባህልና ሳይንስ በUNESCO በድንቃድንቅ መዝገብ የተመዘገበ
የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሀብት ነው፡፡በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት
በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን
ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩና የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳቡ በርካቶች በየአመቱ ወደ ሀገራችን
ይጎርፋሉ።ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ቢጫ ያለም ዘር በሙሉ በሁሉም ሥፍራዎች ደምቆ ይከበራል።
የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ
ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው።ይህ ሁነት ኢትዮጵያ በዓሉን
ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣አያሌ ቱሪስቶችን
ለመሳብ አስችሏታል።

4. የጥምቀት በዓል ለአዲስ አበባ ያለው ፋይዳ


አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መዲና፣የመላው ኢትዮጵያውያን የብሄር ብሄረሰቦች መኖርያ፣የአፍሪካ
መዲና፣የበርካታ ኢምባሲዎችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ የሆነች ከተማ ናት፡፡በመሆኑም የጥምቀት በዓል
በዕምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዕምነት ተከታዮች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩበት፣የህዝብ
ለህዝብ ግንኙነት የሚጎለብትበትና አንድነታችን የሚጠናከርበት፣ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገኝበት የንግድ
ግብይት የሚደራበት ትልቅ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ስለሆነም መንግስት ይህ የመላው ዓለም ሀብት የሆነ በዓል
ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እያደረገ ይገኛል፡፡ነገር
ግን አንዳንዶች መንግስት ኦርቶዶክስ ጠል እንደሆነ አድረጎ በማውራት የግል የፖለቲካ ፍላጎታቸውን
ለማሳካት የሚጥሩ፣ቤተክርስቲያንን የፖለቲካ መጠቀምያ በማድረግ ታቦት አስቁመው ግድያን የሚያውጁና
ከእምነቱ አስተምሮ ውጪ የሚንቀሳቀሱም ጭምር ታይተዋል፡፡ነገር ግን መንግስት ከለውጥ ወዲህ

2
በከተማችን ከ1200 ሄክታር በላይ የቤተ እምነት ቦታ በመስጠት፣በህገወጥ መንገድ የተያዙትን ወደ
ህጋዊነት የመቀየር፣ለጥምቀት ማክበርያ ቦታ ጭምር ካርታ በመስጠትና ምቹ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ
ለአብነት በክፍለ ከተማችን በወረዳ 14 በአባዶ ጂ7፣በወረዳ 8 ሰሚት ፔፕሲ ፊት ለፊት፣በወረዳ 13 መሪ
አካባቢ ያሉትን የታቦት ማደርያ ስፍራዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡የሀይማኖት አባቶችም ለከተማ አስተዳደሩ
ምስጋናና ዕውቅና መስጠቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

5. የበዓሉን ለማክበር ያሉ አስቻይ ሁኔታና ስጋቶች እንደመነሻ


5.1. አስቻይ ሁኔታዎች
 አብዛኛው የፓርቲያችን አባላቶች በሰላም ሰራዊት አመራርነት፣በብሎክ አመራርነት
የተለያዩ ማህበራዊ አደረጃጀቶችን በመምራት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ መሆኑና ይህም ለዚህ በዓል
የሚሰጠው የፀጥታ ስምሪት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ፡፡
 ማህበረሰቡ ለሰላም ያለው ቁርጠኝነት ለፀጥታ መዋቅሩ ድጋፍ በማደረግ ላይ መሆን
 የክ/ከተማችን ሰላም ለማስጠበቅ አኳያ የክ/ከተማችን ህዝብ ከግዜ ወደ ግዜ ከፍተኛ
እየሆነ መምጣቱ፣
 የተደራጀ ሕዝባዊ ሰራዊት በስራ ላይ ከመሆኑም በተጨማሪ የፀጥታ መዋቅሩ
በቁጥርም በተግባርም በተሻለ ቁመና ላይ መገኛቱ
 የአመራሩና የአባሉ አንድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱ እንዲሁም በርካታ
ተልዕኮዎችን በተመሳሳይ ግዜ ወስዶ በስኬት የማጠናቀቅ አቅም የፈጠረ መዋቅር ያለን መሆኑን፣
 ክ/ከተማችን ከሸገር ሲቲ ጋር በስፊው የሚዋሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከአጎራባች
ክ/ክከተሞች ጋር የቀናጀ የጸጥታ ስራ እተሰራ በመሆኑ የፀረ ሰላም ኃይሉ እኩይ ተግባራት እንዳይሳካ
የማድረግ አቅም ከግዜ ወደ ግዜ እየጎለበተ መምጣቱ፣
 በክፍለ ከተማችን በአደባባይ ተከብረው ያለፉ በዓላትን የመስቀሌ፣ ኢሬቻ፣ ኢድ፣
በሰሊም እንዲከበር ሁለም የወጣት ሊግ፣የሴት ሊግ፣የጥቃቅን፣የቢሮ፣የትምህርት ቤትና የመኖርያ የፓርቲ
አባሎቻችን ሰላማዊነቱን ሌት ተቀን በመስራት ከፀጥታ አካላችን ጋር በመሆን በጋራ በመጠበቅና የስጋት
ቦታዎችን በመለየትና እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መደረጉ፡፡

5.2. በስጋት ደረጃ ሊታዩ የሚችሉ ዋና ዋና ጉዳየዮች


 የጽንፍኛ ኃይል ትኩረቱን አዲስ አበባ ላይ በማድረግ የተለያዩ ፀጉረ ለውጦችን ሰርጎ
በማስገባት የተለያዩ የዝርፊያና ቅሚያ ድርጊቶች የሚስተዋሉ መሆኑ
 ጽንፈኛዉና ፀረሰላም ኃይል የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ወቅታዊ ሁኔታ
መነሻ በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎችን የመልቀቅ ዝንባሌዎች ይስተዋላሉ
 ጽንፈኛ ኃይሎች የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም የተዛባ መረጃ በመልቀቅ ህዝቡ
ዉስጥ ብዥታ የመፍጠር ሁኔታ የሚታይ መሆኑን፣
 ክፍለ ከተማችን ከሸገር ሲቲ ጋር የሚዋሰን መሆኑና ከተለያዩ ክልሎች ለሚመጡ

3
የጥፋት ሀይሎች መግቢያ በመሆኑ ለጸጉረ ልውጦች የተጋለጠ ስለሚሆን ሰፊ ስራ የሚጠብቅ ይሆናል፡፡

4
6. የአባላት ሚና
 በአሉን አሴቱና ሃይማታዊ ስነስርአቱን በጠበቀ አግባብ በሰላም እንዲከበርና ህዝቡ ያለምንም
የጸጥታ ችግር ማጠናቀቅ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር፣
 በአሉን በቅድመ በዓል፣ በበዓል ዕለት እና በድህረ በዓል ዕለታት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን
ቀድሞ በመተንበይ በመረጃና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ለመስራት፣
 በዓሉ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ በመሆኑ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ
መልኩ ተከብረው በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ፡፡
 በዓሉን በሰላም ለማክበር በተለይ የሰላም ጉዳይ ባለቤት እንዲሆን ማስጨበጥና ከፀጥታ
መዋቅሩ በተደራጀ መልኩ እንዲሳተፍ ማድረግ፤
 በዓላቱ ለየትኛውም የፖለቲካ ኃይሎች እንዳይውልና በኣሉ የሕዝብና የሕዝብ ብቻ እንደሆነ
በመረዳት መንግስት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለው ማህበረሰቡ በተደራጀ መልኩ
ከመንግስት ጎን በመሆን የክ/ከተማውን ሰላም መጠበቅ እንዳለበት በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ፤
 ከማንኛውም ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች ተቆጥበው በፍቅርና በጨዋነት መንፈስ እንዲከበር
የማስቻል ስራ መስራት፤
 በዓሉ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የማይፈልጉ ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያሰራጩትን
የማደናገርያ ወሬ ተከትሎ ህብረተሰቡ ውዥንብር ውስጥ እንዳይገባ አስፈላጊውን የግንዛቤ ማሰጨበጥ ስራ
መስራት ይጠበቅበታል፡፡

ማጠቃለያ
በክፍለ ከተማችን ከ70ሺ በላይ የብልፅግና አባላት የሚኙ ሲሆን እነዚህ አባላት በልማት፣በፀጥታ፣በበጎ
ፍቃድ፣በተለያዩ የፓርቲና የመንግስት የንቅናቄ ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡በዚህም
ክፍለ ከተማችን በሁሉም ተግባራት ወደ ፊት እንዲወጣ አይነተኛ ሚኛ ተጫውተዋል፡፡በርካታ የጥፋት ድግሶችም
በአባላችን ቆራጥ ተሳትፎና በሰላም ወዳዱ ህዝባችን ተጋልጠዋል፣በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉም ማድረግ
ተችሏል፡፡አሁንም መጪውን የጥምቀት በዓል ከመቼውም ጊዜ በላይ በደመቀ፣ሀይማኖታዊና እሴቱን በጠበቀና
ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር የግንባር ቀደም በመሆን ግዴታችንን መወጣት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል፡፡

You might also like