'81

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የ'81 ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት ዝርዝርና አቆጣጠር…ክፍል 1

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በዚህኛው ጽሑፌ ትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ዝርዝርና አቆጣጠር፤

የመጻሕፍቱን ጸሐፍያን፣ የተጻፉበትን ዓመታት፣ የተጻፉበትን ቦታ፤ ሌሎች ቤተ

እምነቶች ከማይቀበሏቸው መጻሕፍት መታየት ያለባቸውን ቁም ነገሮችና ተዛማጅ

ጉዳዮች ለመዳሰስ እሞክራለሁ። መልካም ንባብ:~~~

ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት የተለያየ አቆጣጠር ቢኖርም እንደ

ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አቆጣጠርና በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ ተዘርዝሮ እንደተቀመጠው

የ’81 ዱ መጻሕፍት ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል።

( የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነት ሥርዓት አምልኮትና የውጭ ግንኙነት ገጽ 42-45)

46 ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት፦

÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷

1/ኦሪት ዘፍጥረጥ

2/ኦሪት ዘፀአት

3/ኦሪት ዘሌዋውያን

4/ኦሪት ዘኁልቁ

5/ኦሪት ዘዳግም

6/መጽሐፈ ኢያሱ

7/መጽሐፈ መሣፍንት

8/መጽሐፈ ሩት

9/1 ኛ እና 2 ኛ ሳሙኤል

10/1 ኛ እና 2 ኛ ነገሥት

11/1 ኛ ዜና መዋእል

12/2 ኛ ዜና መዋእል

13/መጽሐፈ ኩፋሌ

14/መጽሐፈ ሄኖክ
15/መጽሐፈ እዝራና መጽሐፈ ነህምያ

16/መጽሐፈ እዝራ ካልዕና እዝራ ሱቱኤል

17/መጽሐፈ ጦቢት

18/መጽሐፈ ዮዲት

19/መጽሐፈ አስቴር

20/መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ

21/መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ እና ሣልሳዊ

22/መጽሐፈ ኢዮብ

23/መዝሙረ ዳዊት

24/መጽሐፈ ምሣሌ

25/መጽሐፈ ተግሳጽ

26/መጽሐፈ ጥበብ

27/መጽሐፈ መክብብ

28/መኃልየ መኃልይ

29/መጽሐፈ ሲራክ

30/ትንቢተ ኢሳይያስ

31/ትንቢተ ኤርምያስ

32/ትንቢተ ሕዝቅኤል

33/ትንቢተ ዳንኤል

34/ትንቢተ ሆሴዕ

35/ትንቢተ አሞጽ

36/ትንቢተ ሚክያስ

37/ትንቢተ ኢዩኤል

38/ትንቢተ አብድዩ

39/ትንቢተ ዮናስ
40/ትንቢተ ናሆም

41/ትንቢተ ዕንባቆም

42/ትንቢተ ሶፎንያስ

43/ትንቢተ ሀጌ

44/ትንቢተ ዘካርያስ

45/ትንቢተ ሚልክያስ

46/ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባው ነገር ቢኖር፦

----1 ኛ እና 2 ኛ ሳሙኤል

----1 ኛ እና 2 ኛ ነገሥት

----መጽሐፈ ዕዝራና ነህምያ

----ዕዝራ ካልዕ እና ዕዝራ ሱቱኤል

----2 ኛ እና 3 ኛ መቃብያን

ሁለት ሁለቱ እንደ አንድ እንደሚቆጠሩ:

~~~1 ኛ ዜና መዋእል እና

~~~2 ኛ ዜና መዋእል ደግሞ

በአንዳንድ መጻሕፍት ላይ ሕጹጻን ወይም ትሩፋን እንደሚባሉ እንዲሁም

+++ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

በሌላ አጠራር 4 ኛ መቃብያን እየተባለ እንደሚጠራ ልናውቅ ይገባል።

(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 2-3 & መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 24)

You might also like