Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 12

የመንግስት_አወቃቀር (የአሃዳዊ መንግስት እና

የፌደራሊዝም መንግስት አወቃቀር)

ተጻፈ በዳንኤል ተፈራ

ተሰነደ በባደገ ወንድሙ

መንግስት ሁለት አይነት አወቃቀሮች አሉት አንደኛው አሃዳዊ የመንግስት አወቃቀር ሲሆን ሁለተኛው ፌደራል መንግስት
አወቃቀር ነው፡፡ በአለማችን ላይ

የየትኛውም አገር መንገግስት አወቃቀር ብንመለከት ከእነዚህ ሁለት አወቃቀሮች ውጪ የሆነ የመንግስት አወቃቀር
የለም፡፡ አንድንድ አገሮች ውስጥ መንግስት የአሃዳዊና የፌደራል ቅይጥ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም እንደሱም ቢሆን አንድ
መንግስት ወይ አሃዳዊ ነው ወይ ፌደራላዊ ይሆናል እንጂ ከሁለቱ ውጭ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የሚያሳየን አሃዳዊም ሆነ
ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀሮች በየራሳቸው ሲታዩ በውስጣቸው በጥቃቅን ነገሮች የሚለያዩ ብዙ የተለያ አወቃቀሮች
እንዳሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያና አሜሪካ ሁለቱም ፌደራላዊ የመንግስት አወቃቀር ያላቸው አገሮች ናቸው ነገር ግን
በሁለቱ ፌደራል ስርአቶች መካከል ከፍተኛ የአወቃቀር ልዩነት አለ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፈረንሳይና ኡጋንዳ ሁለቱም
የአሃዳዊ የመንግስት መዋቅር ያላቸው አገሮች ናቸው፡፡ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ግን ከፍተኛ ውስጥዊ የአስተዳደርና
የስልጣን ክፍፍል ልዩነት አለ፡፡

1 አሃዳዊ_መንግስት

አሃዳዊ መንግስት ማለት ሁለትና ከሁለት በላይ አስተዳደራዊ ክፍፍሎች ባሉበት ሉአላዊ ሀገር ውስጥ የፖለቲካና
አስተዳደር ስልጣን (ህግ ማስፈጸም፤ህግ ማውጣትና ህግ መተርጎም ) በማእከላዊው መንግስት ቁጥጥር ስር የሆነበት
መንግስት ማለት ነው እንደዚህ አይነት የመንግስት መዋቅር ባላቸው ሃገሮች ውስጥ ክፍለ ሀገሮች፡ አውራጃዎች ወይም
ግዛቶች የሚኖራቸው የአስተዳደር ስልጣን ማዕከላዊ መንግስት በውክልና የሰጣቸው ስልጣን ብቻ ነው እንጂ
ከማእከላዊው መንግስት ቁጥጥር ውጭ የራሳቸው የሆነ ህገ መንግስታዊ ስልጣን የላቸውም፡፡ እንዲያውም በአሃዳዊ
መንግስት ውስጥ ማዕከላዊ መንግስት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደር ክልሎች ለአሰራር አያመቹኝም ብሎ ካመነ
አደረጃጀታቸውን ቀይሮ እንደገና በአዲስ መልክ ማደራጀት ይችላል፡፡

ለምሳሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዘመንና በደርግ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመን በ 14 ክፍለ ሃገሮች
የተከፈለች ነበረች፡፡ በደርግ የመጨረሻዎቹ አመታት ላይ ግን እነዚህ 14 ክፍለ ሃገሮች ወደ 25 አስተዳደራዊ ክልሎች
አድገዋል፡፡ በአሃዳዊ መንግስት ውስጥ የጎንዮሽ የስልጣን ክፍፍል ከላይ ወደታች (vertical) ማለትም በማእከላዊው
መንግስትና በአካባቢ አስተዳደሮች መካከል አይኖርም፡፡ አንድ ጥግ ላይ ቆመን ካየነው አሃዳዊ መንግስት ማለት የፌደራል
መንግስት በግልብጡ (converse) ሲታይ ማለት ነው አባባሉ ብዙም ከእውነት የራቀ አይደለም ግን በአሃዳዊ መንግስት

0
በማእከል ሆኖ ስልጣን ይቆጣጠራል ማለት ሁሉም አሃዳዊ መንግስታት ተመሳሳይ ናቸው ማለትም አይደለም፡፡ የፖለቲካ
ስልጣን ማእከላዊው መንግስት እጅ ውስጥ ተከማችቶ የሚገኝባቸው ወይም የተማከሉ አሃዳዊ መንግስታት እንዳሉ ሁሉ
ስልጣን ያልተከማቸባቸውና በመጠኑ የተማከሉ አሃዳዊ መንግስታትም አሉ፡፡

አሃዳዊ መንግስት ከዚህ የሚከተሉት ባህሪት ይንፀባረቅበታል-

 ቀልጣፋና_ቀላል_መንግስት --በአሃዳዊ መንግስት ውስጥ የፖለቲካ ስልጣን ተጠራቅሞ የሚገኘው በማእከላዊው


መንግስት ደረጃ ስለሆነ አካባቢያዊ ወይም ክፍለ ሃገራዊ ፓርላማ ወይም ምክር ቤት የሚባል ነገር የለም፡፡ ይህ
ማለት ተጠራቅሞ አሃዳዊ መንግስት ፌደራል መንግስት ጋር ሲተያይ አሰራሩ ቀላልና በአነስተኛ ወጪ ያለው
መንግስት ነው ማለት ነው፡፡ ከላይ ወደታች የሚወርድ አስተዳደራዊ የዕዝ ሰንሰለት በተመለከተ አሃዳዊ
መንግስት ስለሆነ ለስራ ቅልጥፍናና ለፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ የተመቸ የመንግስት አይነት ነው
 ተመሳሳይነት(uniformity)--በአሃዳዊ መንግስት ውስጥ ህግና ደንብ የሚወጣው በማእከላዊው መንግስት ደረጃ
ብቻ ስለሆነ ህግና ደንብ በየትኛውም የአሃዳዊው መንግስት ግዛት ውስጥ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ የህግና ደንብ
ተመሳሳይነት የዳኝነት ስራን፤ የህግ ማስፈፀም ስራን ቀላል ያደርገዋል፤ ዜጎችም የትም ኑሩ የት የህግ መደነጋገር
አይኖርባቸውም፡፡
 የስልጣን ክፍፍል አለመኖር-- በፌደራል ስርአት ውስጥ በማእከላዊው መንግስትና በግዛቶች መካከል የስልጣን
ክፍፍል አለ፡፡ እንዲህ አይነቱ የስልጣን ክፍፍል በአሃዳዊ መንግስት ውስጥ የለም፤ አሃዳዊ መንግስት ለክልሎች
ስልጣን በውክልና ይሰጣል ክልሎች እራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ አይተዋቸውም፡፡ በአሃዳዊ
መንግስት ውስጥ የስልጣን ከክፍፍል መንግስት ሙሉ ለሙሉ ትኩረቱን ወደ ልማትና ዕድገት እንዲያደርግ
ይረዳዋል።
 ተለማጭ ህገ-መንግስት (flexible constitution)- በፌደራል ስርአት ውስጥ በማዕከላዊ መንግስትና በክልሎች
መካከል ጠንካራና ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር ሲባል የፌደራል ህገ መንግስት ጠበቅ ያለና ለመቀየር ወይም
ለማሻሻል ብዙ ውጣ ውረድ የሚያስፈልገው ህገ መንግስት ነው፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ህገ መንግስቱን
ለማሻሻል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን የጋራ ጉባኤ ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ድጋፍና እንዲሁም
የሁለት ሶስተኛው ክልሎች ምክር ቤት ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡ የአሃዳዊ መንግስት ግን ሁኔታዎች በተለዋወጡ ቁጥር
ያለብዙ ውጣ ውረድ መሻሻል ወይም መለወጥ የሚችል ህገ መንግስት ነው፡፡

የአምባገነንነት አዝማሚያ- ከፌደራል መንግስት ጋር ሲነፃፀር አሃዳዊ መንግስት ወደ አምባገነንነት የመለወጥ


አዝማሚያው ከፍተኛ ነው፡፡ በአሃዳዊ መንግስት ውስጥ የፖለቲካ ስልጣን በማዕከል አንድ ሰው እጅ ላይ የመጠራቀም
ባህሪ ስላለውና እንደ ፌደራል ስርአት በክልልና በማዕከል የስልጣን ክፍፍል ስለሌለበት ይህ ሰው ታማኝነቱና አገር ወዳድነቱ
በቀነሰ ቁጥር በቀላሉ ወደ አምባ ገነንነት የመለወጥ አደጋው ከፍተኛ ነው፡፡ እንደዚህ ሲባል አሃዳዊ መንግስት የቱንም ያክል
ዴሞክራሲያዊ ቢሆን ወደ አምባ ገነንነት ስርአት በቀላሉ ይለወጣል ማለት አይደለም ከፌደራል ስርአት ጋር ሲነፃፀር ግን
ፌደራሊዝም ለአምባገነንነት እንዳይፈጠር የሚከላከለውን ያክል አሃዳዊ ስርአት አይከላከልም ለማለት ነው፡፡

1
ፌደራሊዝም_እራስን_በራስ ማስተዳደርና የጋራ
አመራር (self-rule and shared rule )
1. ፌደራሊዝም በአለማችን ውስጥ ካሉ ሁለት ዋና ዋና የመንግስት አወቃቀሮች ውስጥ አንዱ ነው
2. አገራችን ኢትየጵያ ፌዴራል ስራዓትን ከሚከተሉ አገሮች ውስጥ አንዷ ናት
3. አገራችን ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከሚጠብቋት ትልልቅ ምርጫዎች ውስጥ አንድ
የመንግስት መዋቃር ምርጫ ነው

ዛሬ በአለማችን ውስጥ ያለውን የመንግስት አወቃቀር አሃዳዊ እና ፌደራላዊ ብሎ በሁለት ግዙፍ ክፍሎች ከፍሎ
መመልከት ይቻላል፡፡ አሃዳዊ መንግስት ማለት የፖለቲካ ስልጣን በማእከላዊው መንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኝበት ወይም
ስልጣን በማእከል ተከማችቶ የሚገኝበት መንግስት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ዴንማርክና ሞሮኮ አሃዳዊ የመንግስት መዋቅር
ያላቸው አገሮች ናቸው፡፡

ፌደራሊዝም ማለት ደግሞ የፖለቲካ ስልጣን ከማእከል ተቆርሶ ለየአስተዳደር ክልሉ የሚሰጥበትና የአስተዳደር
አካባቢዎች የየራሳቸው መንግስት ያላቸው ስርአት ነው፡፡ የመንግስት መዋቀር አሃዳዊ እና ፌደራል ተብሎ ለሁለት ይከፈል
እንጂ አሃዳዊ ስርአቶም ሆኑ ሁሉም ፌደራላዊ ስርአቶች ተመሳሳይ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ አሜሪካ ህንድና ኢትዮጵያ
ፌደራላዊ የመንግስት መዋቅር ያለባቸው አገሮች ናቸው ነገር ግን ሶስቱም አገሮች ፌደራላዊ የመንግስት መዋቅር
ይኑራቸው እንጂ ሶስቱ አገሮች ውስጥ ፌደራሊዝም የተዋቀረበት መንገድ ይለያያል፡፡ የአሜሪካ ፌደራሊዝም ለሁሉም
የፌደራል ክልሎች እኩል ስልጣን የሚሰጥ ( symmetric federalism ) ሲሆን ህንድ ውስጥ ግን የፌደደራል ክልሎቹ
የተለያየ ስልጣን ደረጃ ነው ያላቸው (asymmetric federalism ) ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ እስከ ዛሬ እንደታየው ክልሎች
የራሳቸው የሆነ የፖለቲካ ስልጣን አላቸው ለማለት አይቻልም፡፡ የአሜሪካንና የህንድ ፌደራል ስርአት አወቃቀር
እንደሚለያይ ሁሉ ዴንማርክና ሞሮኮ ውስጥም ያለው አሃዳዊ መንግስት የተዋቀረበት መንገድም ይለያያል፡፡

ፌደራሊዝም ምንድነው?

በላቲን ቋንቋ ‹‹ፎደስ›› (foedus) ማለት ስምምነት፤ውል ወይም ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ በእርግጥም ፎደስ የሚለው
የላቲን ቃል በትክክል እንደሚናገረው ፌደራሊዝም ማለት የተለያዩ ህዝቦች በመካከላቸው ያለውን ድንበር አፍርሰው
አንድ ላይ ለመኖር እርስ በእርስ የሚገቡት ቃል ኪዳን ነው፡፡ በጣም ቀለል በሆነ አማርኛ ፌደራሊዝም ማለት የአንድ ሀገር
ሉአላዊነት በክልልና በማዕከል በመክፈል ህዝብ በክልል እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት በማዕከል ደግሞ የፖለቲካ
ስልጣንን ከሌሎች ክልሎች ጋር ተጋርቶ ሀገሩን በጋራ ማስተዳደርጨየሚችልበት መንግስታዊ መዋቅር ነው፡፡ ፌደራል

2
የመንግስት መዋቅር ባለባቸው አገሮች ውስጥ ዜጎች በሁለት እርከን ለተቀመጡ መንግስታት ግዴታ አለባቸው ፡፡
አንደኛው ግዴታ ለማእከላዊው መንግስት ወይም ብዙ ጊዜ ፌደራል መንግስት እየተባለ ለሚጠራው መንግስት ሲሆን
ሁለተኛው ግዴታ ደግሞ በክልል ደረጃ ለተቋቋሙ የክልል መንግስት ነው። በ 16 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮሃንስ
አልቶሽየስና በተከታዮቹ ተጀምሮ ቅርፅና ይዘቱን እያዳበረ ዛሬ ድረስ የዘለቀው የፌደራሊዝም ጽንሰ ሃሳብ በ 500
አመታት ታሪኩ ውስጥ ብዙ አዳዲስ ሃሳቦች ቢካተቱበትም ዋናውና መሰረታዊ ሃሳቡ ግን ዛሬም አልተለወጠም፡፡
የፌደራሊዝም ጽንሰ ሃሳብ ገና ሲጠነሰስ ጀምሮ መሰረታዊ ሃሳቡ እራስን በራስ ከማስተዳደር ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ዛሬም ቢሆን እጅግ በጣም መሰረታዊ የሆነው በአካባቢ እራስን በራስ ማስተዳደር (self- rule) እና በማእከል የፖለቲካ
ስልጣን መጋራት(shared rule) የሚለው የፌደራሊዝም መርህ አልተለወጠም ፡፡ እንደውም ፌደራሊዝም አድማሱን
እያሰፋ በዘር በሃይማኖት በቋንቋ በተከፋፈሉ ማህበረሰቦች ውስጥ በተለይ የማንነትና የመገንጠል ጥያቄ በተነሳባቸው
ሃገሮች ውስጥ ፍቱን መዳኒት መሆኑን ማስመስከር የቻለ የመንግስት መዋቅር ነው፡፡ በክልል ወይንም በአካባቢ እራስን
በራስ የማስተዳደር መብት በፌደራሊዝም ውስጥ ብቻ የሚገኝ መብት አይደለም፡፡ አሃዳዊ መንግስት ባለባቸው ሃገሮችም
ውስጥ ህዝብ በአካባቢው እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባቸው ብዙ ሃገሮች አሉ፡፡ በፌደራሊዝምና በሌሎቹ ያልተማከሉ
የአስተዳደር አይነቶች መካከል አንድ ትልቅ ልዩነት አለ፤ እርሱም በፌደራሊዝም ውስጥ ከማእከል ተቆርሶ ለክልሎች
የሚሰጠው ሉአላዊነት (sovereignty) ነው፤ በሌሎች ፌደራላዊ ባልሆኑ ነገር ግን ያልተማከለ አስተዳደር ባለባቸው
አገሮች ውስጥ ግን ከማእከል ተቆርሶ ለክልሎች የሚሰጠው የአስተዳደር ስልጣን ነው፤ እሱም ቢሆን የአካባቢ
አስተዳዳሪዎች የማእከሉ ተወካዮች ናቸው እንጂ በአካባቢው ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፤ ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ
እስከ ደርግ ዘመን ድረስ የነበረው መንግስት አሃዳዊ መንግስት ነበር የጠ/ግዛት ወይም የክፍለሃገር አስተዳዳሪዎች ከማዕከለ
እየተሸሙ ነበር የሚሄዱት፡፡ አገሮች ፌደራል መንግስት መዋቅርን የሚመርጡት በተለያዩ ምክንያቶች ነው፡፡ ብዙዎቹን
ምክንያቶች አንድ ላይ አስቀምጠን ስንመለከት ምክንያቶቹን በሁለት ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ ፌደራሊዝም ፍቱን
መድሃኒት ነው ተብሎ ከሚፈለግባቸው ምክንያቶች አንዱ አገርን ከመገነጣጠል አደጋ ያድናል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡
እራስን በራስ ማስተዳደር ጥያቄና የመገንጠል ጥያቄ የተያያዙ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ የመገንጠል ጥያቄ የተነሳባቸውን
አገሮች ታሪክ ስንመረምር አንድ ህዝብ የመገንጠል ጥያቄ የሚያነሳው እራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን ሲነፈግ
ወይም አንድ ህዝብ በብሄር በቋንቋ ወይም በሃይማኖት ማንነቱ የተነሳ ልዩነት ሲደረግበት ወይም መከራ ሲደርስበት ነው፡፡
የአገራችን የኢትዮጰያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ስንመለከት ኤርትራ ውስጥ የመገንጠል ጠያቄ የተነሳው በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ
መንግስት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስተዳድረውን ፌዴሬሽን አፍርሶ እራሷን በራሷ ታስተዳድር የነበረችውን
ኤርትራን 14 ኛው የኢትዮጵያን ጠ/ግዛት በማድረጉ ነው፡፡ በዘር በቋንቋ እና በሃይማኖት በተከፋፈሉ አገሮች ውስጥ
ፌዴራል የመንግስት መዋቅር ተመራጭ የሆነባቸው ሁለት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው ‹ፌደራሊዝም› ህዝብ
በአካባቢው እራሱን በራሱ ማስተዳደር እንዲችል ሙሉ መብትና ስልጣን የሚሰጥ መዋቅር መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው
ደግሞ ፌዴራሊዝም ከአሃዳዊ የመንግስት በተሸለ መንገድ ብዝሃዊነትን ማስተናገድ የሚችል መንግስታዊ መዋቅር መሆኑ
ነው፡፡ አሃዳዊ መንግስት ባለባቸው አገሮች ውስጥ የሉአላዊነት ብቸኛ ማደሪያ አሃዳዊው መንግስት ነው፤ ወይም ክልሎች
ሙሉ በሙሉ በማእከላዊው መንግስት ስር የሚተዳደሩ የአስተዳደር ክፍልፋዮች ናቸው እንጂ የራሳቸው የሆነ ሉአላዊነት
የላቸውም፡፡ ፌደራል የመንግስት መዋቅር ባለባቸው አገሮች ውስጥ ግን ክልሎች ከማእከል ተቆርሶ የተሰጠ ሉዓላዊነት

3
አላቸው፡፡ የአለማችን 40% የሚሆነው ህዝብ የሚኖረው ፌዴራል የመንግስት መዋቅርን በሚከተሉ 28 አገሮች ውስጥ
ነው፡፡ እነዚህ ሀገሮች ፌዴራሊዚምን የመረጡት በተለያየ ምክንያት ቢሆንም ብዙዎቹ ምክንያቶች ተመሳሳይ ናቸው፡፡
በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ፌዴራሊዝም የሚፈጠረው የተለያዩ ሉዓላዊ አገሮች ተወያይተው በሚያደርጉት ስምምነት
መሰረት ሲሆን በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ደግሞ ፌዴራሊዝም አንድን ሉዓላዊ አገር ከመበታተን አደጋ ለማዳን በህዝብ
ውሳኔ ወይንም በፓርላማ ስምምነት የሚፈጠር ስርአት ነው፡፡ የፌደራሊዝም አቀንቃኝ አገሮች ፌዴራል የመንግስት
መዋቅርን የሚመርጡት በሚከተሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ሉአላዊ
አገሮች በፌዴራል መዋቅር ሲተሳሰሩ አንደኛ የጋራ የሆነ ትልቅ የአገር ውስጥ ገበያ ይኖራቸዋል፤ - በጋራ የመልማትና
የማደግ ችሎታቸው ከእጥፍ በላይ ይጨምራል፡፡ እነዚህ የፌደራሊዝም ጠንካራ ጎኖች እንዳሉ ሆነው ፌደራሊዝም እንደ
ኢትዮጵያ ባሉ ዘውገ-ብዙና ሃይማኖተ-ብዙ አገሮች ውስጥ በአንድ በኩል የመገንጠል ጥያቄ ላቀረበ በአካባቢው እራሱን
በራሱ ማስተዳደር የሚችልበትን ዕድል ይፈጥራል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙሃኑ አናሳውን እንዳሰኘው የማይዘውርበት
ዲሞክራያዊ ስርአት ይፈጠራል፡፡ አገሮች ወደ ፌደራሊዝም የሚያመሩት በሶስት ዋናዋና መንገዶች ነው፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ መንገዶች ከብዙ አገሮች ልምድ የተገኙ ናቸው፡፡ ዛሬ በፌደራል የመንግስት መዋቅር የሚተዳደሩ
አገሮች የፌዴራል ስርአታቸውን የፈጠሩት ከሁለቱ መንገዶች በአንዱ ነው፡፡ ሶስተኛው መንገድ ግን ከቀድሞዎቹ ሶቭየት
ህብረት፤ ዩጎዝላቪያና ከዛሬዋ ኢትዮጵያ የተገኘ ልምድ ነው፡፡ በቀድሞዎቹ ሶቭየት ህብረትና ዩጎዝላቭያ ውስጥ የነበረው
ፌዴራል ስርአት ህዝቦች ወድደውና ተፈላልገው የፈጠሩት ስርአት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያም ውስጥ ከሃያ አምስት አመት
በላይ ያስቆጠረው ፌዴራል ስርአት የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድሉ ተሰጥቶትና ተሰጥቶትና ተወያይቶበት የፈጠረው የፌዴራል
ስርአት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፌዴራል ስርአት የሕወሓት መሪዎች ለነሱ በሚስማማ መልኩ ሸንሽነው
የፈጠሩት ‹‹ፌዴራሊዚም መሰል ››ስርአት ነው፡፡ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ 1922 አም እና በ 1945 አም በጉልበት
የፈጠረው የሶቭዬት ህብረትና ዩጎዝላቪያ ፌዴራል ስርአት ፈራርሶ ለብዙ ሉኣላዊ መንግስታት መፈጠር ምክንያት ከሆነ
ከሀያ አመታት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው ፌዴራል ስርአትም አሁን ያልውን መልክ ለውጦ ህዝብ
በአካባቢው እራሱን በራሱ ማስተዳደር ካልቻለና በማአከልም የፖለቲካ ስልጣንን እኩል ካልተጋራ ይዋል ይደር እንጂ
ተንኮታኩቶ መውደቁ የማይቀር ነው፡፡

ፌዴራሊዚም_የሚፈጠርባቸውን_ሦስት መንገዶች-

1-አብረን እንኑር ፌዴራሊዚም (Coming together federalism)- ‹‹አብረን እንኑር ›› ፌዴራሊዚም ሁለትና ከሁለት
በላይ የሆኑ ሉአላዊ አገሮች ፍጹም በሆነ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርተው በአንድ የፌዴራል መንግሰት መዋቀር ስር
ለመተዳደር ሲስማሙ የሚፈጠር ፌዴራሊዚም ነው፡፡ አገሮች እንደዚህ አይነት ስምምነት ላይ የሚደርሱት ቀልጣፋ
ውጤታማና ብቃት ያለው መንግስት ለመመስረት ትልቅና ነጻ የኢኮኖሚ ማህበረስብ ለመፍጠር ጠንካራ የመከላከያ
ተቋም ለመገንባትና በመካከላቸው ሊነሱ የሚችል ጦርንትና የጦርነት ስጋትን ለማስወገድ ነው፡፡ አሜሪካና ስዊዘርላንድ
በ‹‹አብረን እንኑር››ፌዴራሊዚም የተፈጠሩ አገሮች ናቸው፡፡ በአለም ውሰጥ የ‹‹አብረን እንኑር ›› ፌዴራሊዚም አይነተኛ
ምሳሌ የሆነችው አገር አሜሪካ ናት፡፡ የዛሬዋን አሜሪካ የፈጠሩ በአትላቲክ ውቅያኖስ በኩል የሚገኙት (East

4
Coast )የመጀመሪያዎቹ አስራ ሶስቱ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ናቸው፡፡ የተቀሩት ሰላሳ ሰባቱ ግዛቶች የህብረቱ (Union)
አባል የሆኑት በተለያዩ ጊዜያት ነው፡፡

2- አገር እናድን ፌዴራሊዚም (Holding Together Federalim )- ከላይ የተመለከትነው ‹‹አብረን እንኑር
››ፌዴራሊዚም ሉአላዊ መንግስታት ተሰባስበው አንድ ትልቅ አገር ሲፈጥሩ የሚፈጠር መዋቅር ነው፡፡‹‹አገር እናድን››
ፌዴራሊዚም ግን ስሙ እንደሚያመለክተው አገርን ከመበታተን አደጋ ለማዳን ሲባል በፖለቲካ ልህቃኑ ስምምነት ወይም
በፓርላማ ውሳኔ የሚፈጠር ፌዴራሊዚም ነው፡፡‹‹አገር እናድን ፌዴራሊዚም አንድ ሉአላዊ መንግስት በፓርላም ውይም
በህዝበ ውሳኔ ሉአላዊነትን ከማእከል ቆርሶ ለክልሎች ሲሰጥና እያንዳንዱ ክልል የራሱ ግዛት ፤ ህገ መንግስት ኖሮት እራሱን
በራሱ ማስተዳደር ሲጀምር የሚፈጠር ፌዴራሊዚም ነው፡፡ ብዙውን ግዜ‹‹አገር እናድን››ፌዴራሊዚም የሚፈጠረው
አዐዳዊ የመንግስት መዋቅር ባለባቸውና የመገንጠል ጥያቄ በተነሳባቸው ወይም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች‹‹እራሳችንን
በራሳችን እናስተዳድር‹‹የሚል ጥያቄ በሚያነሱባቸው አገሮች ውስጥ ነው፡፡ ‹‹አብረን እንኑር ››እና አገር እናድን››ሁለቱም
አገሮች ወደ ፌዴራሊዚም የሚመጡባቸው መንገዶች ናቸው፤ በሁለቱ መካከል ያለው አንድ ትልቅ ልዩነት በ‹‹አብረን
እንኑር››መንገድ ተጉዘው ፌዴራሊዚምን የሚፈጥሩ አገሮች በፌዴራል መዋቅር ከመተሳሰራቸው በፊት ሉአላዊ የነበሩ
አገሮች ናቸው፡ ፡በ‹‹አገር እናድን ››የሚፈጠረው ፌዴራሊዚም አንድ ሉአላዊ አገር ወደ ተለያዩ ክልሎች በመከፋፈል
የሚፈጠር ፌዴራሊዚም ነው፡፡ ህንድ ኢራቅና ቤልጂየም የ‹‹አገር እናድን››ፌዴራሊዚም ምሳሌዎች ናቸው ፡፡

3 -ጨፍልቀህ ግዛ ፌዴራሊዚም ( Putting together federalism)-‹‹ጨ ፍለረቀህ ግዛ ›› ፌዴራሊዚም


ከ‹‹አብረን እንኑር ፌዴራሊዚም እና ከ‹‹አገር እናድን ››ፌዴራሊዚም በሶስት ዋናዋና መንገዶች ይለያል ፡፡
አንደኛው‹‹ጨፍጭፈህ ግዛ››ፌዴራሊዚም ሲፈጠር በህዝብ መልካም ፈቃድ ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በጉልበትና በሀይል
የሚመሰረት ፌዴራሊዚም ነው፡፡ ሁለተኛው የፌዴራል ክልሎቹ ሉአላዊነት የተረጋገጠ አይደለም፤ ወይም የአገራችን
የኢትዮጵያ ልምድ በግልጽ አንደሚያሳየው ህዝብ በክልል እራሱን በራሱ በማእከል ደግሞ የፖለቲካ ስልጣን ተጋርቶ አገሩን
በጋራ አያስተዳደድርም፡፡ ሶስተኛው‹‹ጨፍልቀህ ግዛ ፌዴራሊዚም ከዲሞክራሲ ጋር የማይተዋወቅ ወይም ዲሞክራሲ
አልባ ፌዴራሊዚም ነው፡፡ ፌዴራሊዚም ደግሞ ያለ ዲሞክራሲ በፍጹም የማይታስብ የመንግስት መዋቅር ነው፡፡
የ‹‹ጨፍልቀህ ግዛ ፌዴራሊዚም አይነተኛ ምሳሌዎች የሆኑት ሶቭየት ህብረትና ዩጎዝላቪያ ውስጥ የፌዴራሉ ስርአት
መፈራረሱ ብቻ ሳይሆን ሰርብያ ከሮሺያ ኮሶቮና ቦስኒያ ሲለያዩ የብዙ ሰዎች ደም ፈስሷል ፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል
ተፈጽሟል፤ በብዙ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ውሰጥ በህወሃት የበላይ
ተቆጣጣሪነት የተፈጠርው ፌዴራሊዚም በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረትና ዩጎዝላቪያ ውሰጥ ከተፈጠረው ፌዴራሊዚም ብዙ
አይለይም፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው ፌዴራሊዚም የተፈጠረው በህዝብ በተመረጠ ፓርላም ውሳኔ ወይም
በህዝብ ውሳኔ ሳይሆን በህወሃት የበላነት በተመራው የሽግግር መንግስት ነው፡፡ የፌዴራል ህገ መንግስቱን የጻፋው፤ ዘጠኙን
የፌዴራል ክልሎች እንዳሰኘው ሸንሽኖ የከለለውና ባጠቃላይ ፌዴራሊዚም መልካም ስርአት ቢሆንም ይህንን ስርአት
በራሱ ውሳኔ ኢትዮጵያ ላይ የጫነው ሕወሃት በክልልም በማእከልም ብቸኛ ፈላጭና ቆራጭ ሀይል ነበር፡፡

የፌዴራሊዚም_አይነቶች

5
ዛሬ በአለም ላይ ፌዴራል የመንግስት ስርአትን የሚከተሉ ብዙ አገሮች አሉ ፡፡ አገሮች ፌዴራሊዚምን የመረጡበት
የየራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ ፌዴራሊዚም አንዳንድ አገሮች ውስጥ ‹‹ራስን በራስ የማስተዳደር ››ጥያቄ መልስ
ነው አንዳንድ አገሮች ውስጥ ትልቅ የጋራ ገበያና ጠንካራ ኤኮኖሚ የመፍጠር ፍላጎት ውጤት ነው፡፡ አንዳንድ አገሮች
ውሰጥ ደግሞ ፌዴራሊዚም በተለያዩ ቡድኖች መካከል ለሚነሱ ግጭቶችና አለመግባባቶች እልባት ለመስጠት የሚወሰን
ውሳኔ ውጤት ነው፡፡ አገሮች ፌዴራል የመንግስት አወቃቀርን የመረጡበት ምክንያት እንደሚለያይ ሁሉ የሚከተሉት
የፌዴራል ስርአት አወቃቀርም ያንኑ ያክል ይለያያል፡፡ ለምሳሌ አውሮፓ ውስጥ ያለው ፌዴራሊዚምና ሰሜን አሜሪካ
ውስጥ ያለው ፌዴራሊዚም የሚመሳሰሉበትም የሚለያዩበትም መንገድ አለ፡፡ እዚያው ሰሜን አሜሪካ ውስጥም ቢሆን
አሜሪካና ካናዳ ውስጥ ያለው ፌደራልዝም አወቃቀሩ ይለያያል፡፡ አሜሪካ ውስጥ ሁሉም የፌደራሉ አካላት ማለትም
የፌደራል ግዛቶች ተመሳሳይ ወይም እኩል የሆነ ስልጣን ነው ያላቸው/symmetric federalism/፡፡ ካናዳ ውስጥ ግን
አንዳንዱ የፌደራል ግዛት ከሌላው የፌደራል ግዛት የተለየ የስልጣን አለው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ የህዝብ ብዛቷ ከአንድ
ሚሊዮን በታች የሆነችው ዋዮሚንግ ግዛትና ከሰላሳ አምስት ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ካሊፎርኒያ በፌደራል
ስርአቱ ውስጥ ያላቸው ስልጣን እኩል ነው፡፡ በአነንጻሩ የካናዳ ህግ መንግስት ለአንዳንድ የፌደራሉ ክልሎች (quabac)
ከሌሎች ክልሎች የተለያየና ከፍያለ ስልጣን ይሰጣል (asymmetric federalisem )፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፌደራላዊ
የመንግስት መዋቀርን የሚከተሉ የተለያዩ ሃገሮች ውስጥ ሉአላዊነት ከመአከል ተቆርሶ ወደ ክልሎች የሚወርዱበት
መንገድ ይለያያል፡፡ በመሰረቱ ፌደራሊዝም ያልተማከለ አስተዳደር ስልት ነው፤ ያልተማከለ ሲባል ግን የአለማማከል
ደረጃውን ከአገር ወደ አገር ይለያያል፡፡ በአንድንድ ፌደራል ስርአቶች ውስጥ ክልሎች ትልቅ ስልጣን አላቸው፤ ለምሳሌ
አሜሪካ ውስጥ እያንዳንዱ ግዛት የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ ሳይገባበት የራሱን የግብር፤ የልማት፤ የትምህርትና የጤና
ፖሊሲ ማውጣት ሙሉ ስልጣን አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዱ ግዛት የአካባቢ ሚሊሺያና የፖሊስ ሃይል አለው፡፡
ህንድ ውስጥ እያንዳንዱ ግዛት የራሱ ህገመንግስት የለውም፤ ይህ ማለት ደግሞ ህንድ ውስጥ በማዕከላዊ መንግስትና
ክልሎች መካከል ያለው የስልጣን ግንኙነት እንደ አሜሪካ የላላ አይደለም፤ ወይም የህንድ ፌደራሊዝም ከአሜሪካ
ፌደራሊዝም በበለጠ መልኩ የተማከለ ፌደራሊዝም ነው ማለት ነው፡፡ ፌደራሊዚምን የመንግስት መዋቅራቸው
አድርገው የተቀበሉ ሃገሮች ሁሉም የሚመሳሰሉባቸው ሶስት ዋና ዋና ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ፌደራል ስርአት
ባለባቸው አገሮች ሁሉ ‹‹ራስን በራስ ማስተዳደር ›› እና ‹‹ የጋራ አገዛዝ ››(senf rule and shared rule )አለ፡፡ ሁለተኛ
ፌደራሊዝም ውስጥ የዜጎች ግዴታ የሁለት የተለያዩ አካላት ነው (ለክልል መንግስትና ለማእከላዊ መንግስት ) ሶስተኛ
ፌደራል ስርአት ባለባቸው ሃገሮች ውስጥ ብሄራዊ ድህንነት፤ አገር መከላከያና የውጭ ግንኙነት ስራዎች ለማእከላዊው
መንግስት የተተው ስራዎች ናቸው፡፡ በሁሉም ሃገሮች ውስጥ በፌደራሉ መንግስትና በክልል መንግስቶች መካከል ያለው
ግንኙነት በህገ መንግስቱ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ ያንዳንድ ሃገሮች ህገ መንግስት ለምሳሌ ጀርመንና አሜሪካ ውስጥ ህገ
መንግስቱ በግልጽ ለፌደራሉ መንግስት ያልሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት የክልሎች ስልጣንና ሃላፊነት እንደሆነ ህገመንግስቱ
ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ ካናዳና ህንድ ውስጥ ደግሞ ህገመንግስቱ በግልጽ በክልሎች ያልሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት የፌደራሉ
መንግስት ስልጣንና ሃላፊነት እንደሆነ ህገ መንግስቱ ውስጥ ተደንግጓል፡፡ እንዲህም ሁኖ አንዳንዴ ፌደራልና የክልል ህገ
መንግስቶች ሊጋጩ ይችላሉ፤ ይህ በሚሆንበት ጊዜ የፌደራሉ ህገ መንግስት የፀና ይሆናል፡፡ እስካሁን ድረስ
የተመለከትነው ሀገሮች ፌደራል ስርአት የሚፈጥሩበትን ሶስት መንገዶችና የተለያዩ የፌደራሊዝም ንድፈ ሃሳቦች መካከል

6
ያለውን ልዩነት ነው፡፡ ትክክለኛና የህዝብን እኩልነትን እራስን በራስ የማስተዳረር ጥያቄዎች የሚመልስ ፌደራል ስርአት
የሚፈጥረው በተራ ቁጥር አንድና ሁለት ላይ በተጠቀሱት መንገዶች ነው፡፡ በዚህ እርስ ውስጥ‹‹ጨፍልቀህ ግዛ››
ፌደራሊዝም ሶስተኛው መንገድ ሆኖ የቀረበው ሃገራችን ኢትዮጵያ ፌደራሊዚምን ለመፍጠር የተጓዘችበትን የተሳሳተ
መንገድ ለማሳየትና ይህንን መንገድ ማየቱ የወደፊቱን መንገዳችንን የመቀየስ ይጠቅማል በሚል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
ምስራቅ አውሮፓ ውስጥ በ‹‹ ጨፍልቀህ ግዛ›› ፌደራሊዝም መንገድ ተጉዘው የፌደራል ስርአት የፈጠሩ ሃገሮች
ለመለያየትና የየራሳቸውን ሉአላዊ ሃገር ለመመስረት

ያደረጉትን በደም የተጨማለቀ ጉዞ መለስ ብለን እንድንመለከትና ሃገራችን ኢትዮጵያ የህዝቦቿ ሃገር ስትሆንና የህዝቦቿ
ምርጫ ፌደራሊዝም ከሆነ ይህንን የህዝብ ምርጫ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባን ካሁኑ ማየት እንድንችል ነው፡፡
‹‹አብረን እንኑር›› ፌደራሊዝምና ‹‹ሃገር እናድን››ፌደራሊዝም ትልቁ ልዩነታቸው የመጀመሪያው ማለትም ‹‹አብረን
እንኑር›› ፌደራሊዝም ሉአላዊ ሃገሮች በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው ተማክረው አንድ ላይ ብንኖር ይበጀናል ብለው
የሚፈጥሩት ፌደራሊዝም ነው፡፡ ‹‹ሃገር እናድን›› ፌደራሊዝም ግን በአንድ ሉአላዊ ሃገር ውስጥ ህዝብ እራሱን በራሱ
የማስተዳደደር ጥያቄ ሲያቀርብ ወይም የመገንጠል ጥያቄ ሲነሳ ሃገርን ከመበታተን ለማዳን በፓርላማ ውሳኔ ወይም
በህዝብ ውሳኔ የሚፈጠር ፌደራሊዝም ነው፡፡ ‹‹አብረን እንኑር›› ፌደራሊዝም ሲፈጠር የፌደራል ስርአቱን በክልል ደረጃ
ለማዋቀር መሬት ላይ የሚሰራ ብዙ ስራ የለም፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ክልል የግዛት መጠኑና ድንበሩ ታውቆ ነው
የፌደራል ስርአቱን የሚቀላቀለው፡፡ ‹‹ሃገር እናድን›› ፌደራሊዝም ሲፈጠር ግን ወደ ተለያዩ ክልሎች የሚከፈለው አንድ
ሉአላዊ ሀገር ስለሆነ ክልሎቹ በምን መመዘኛ መካከል አለባቸው የሚለው ጥያቄ እጅግ በጣም አወዛጋቢ ጥያቄ ነው፡፡
ይህንን ጥያቄ የተለያ አገሮች በተለያየ መንገድ መልሰውታል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ፌደራል የመንግስት መዋቅር ሲመሰረት ዘጠኝ ክልሎች አብረው ተመስርተዋል፡፡ የህወሃት አገዛዝ
እነዚህን ክልሎች ለመከለል የተጠቀመው መመዘኛ አንድ ብቻ ነው፤ እሱም ጎሳ ወይም ቋንቋ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር
ቋንቋ የፌደራል ክልሎችን ለማካለል መመዘኛ ሆኖ በመቅረቡ ላይ ችግር የለም ችግሩ ቋንቋ ዋነኛው ወይም ብቸኛው
መመዘኛ ሆኖ መቅረቡ ነው፡፡ ቋንቋ የፌደራል ክልሎችን ለመከለል ብቸኛ መመዘኛ ሆኖ ሲቀርብ የሚከተሉት ችግሮች ይዞ
ይመጣል

1. አብረው በጉርብትና የኖሩ ህዝቦች መካከል የልዩነት አጥር ይሰራል


2. እራሳቸውን ችለው ክልል መሆን የማይችሉ የቋንቋ ስብስቦች ክልል እየሆኑ የፌደራሉ መንግስት ጥገኛ ሆነው
ይቀራሉ፤ ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ክልል መሆን የማይገባቸው ትናንሽ አካባቢዎች ከ 90 በመቶ በላይ አመታዊ
በጀታቸውን ከፌደራል መንግስት የሚያገኙ ክልሎች አሉ፡፡ እነዚህ የፌደራል መንግስቱ ተቀፅላዎች እንጂ
እራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ተብለው ሊጠሩ አይችሉም
3. በክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የሃብት ክፍፍል እና የኢኮኖሚ እድገት ልዩነት ይፈጠራል
4. በኩታ ገጠም ክልሎች መካከል የድንበር ግጭቶች እንዲፈጠሩ ምክንያ ይሆናል ፡፡ ባለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያ
ከእንደዚህ አይነት ግጭቶች ተገላግ አታውቅም፡፡ በተለይ በ 2009 መጨረሻና በ 2010 መጀመሪያ በሶማሌ እና

7
በኦሮሚያ ክልል መካከል በተደረገው ተከታታይ የተኩስ ልውውጥና የሰው ሕይዎት መጥፋት ዋነኛው ምክንያት
በቋንቋ ላይ የተመሰረተው የጎሳ ፌደራሊዝም ነው፡፡
5. ከፍተኛ መጠን ያለው የሃገር ሃብትና ጊዜ በክልሎች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማብረድና ሃገር ለማረጋጋት
የሚደረገው ጥረት ይባክናል
6. አንዳንድ ክልሎች ካላቸው የተፈጥሮ ሃብት፤ የሰው ሃይል ብዛትና ቆዳ ስፋት አንፃር ሲታዩ የመልማት
አቅማቸው ውስን ነው
7. የክልሎች በዘርና በቋንቋ ላይ መመስረት የሃገሪቱ ፖለቲካ በብሄር መሰረት ላይ እንዲዋቀር መንገድ ይከፍትና
ብሄራዊ እድገትና ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ለመፍጠር የሚደረገውን ሂደት ያዳክማል። ኢትዮጵያ ውስጥ
በቋንቋ ላይ የተመሰረተው ፌደራሊዝም አቀንቃኞች የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም መልካምነትና አዋጭነት ሲናገሩ
ደጋግመው እንደምሳሌ የሚያነሱት የስዊዘርላንድ ፌደራሊዝም ነው፡፡ ለዚህ አባባላቸው እንደማረጃ
የሚያቀርቡት ደግሞ የስዊዘርላንድ ፌደራል ስርአት የተዋቀረው ልክ እንደ ኢትዮጵያ ዘርና ቋንቋን መሰረት
አድርጎ ነው የሚለውን እውነትነት የሌለው አባባል ነው፡፡

ፌዴራሊዝምና_የወደፊቷ_ኢትዮጵያ

የወደፊቷ ኢትዮጵያ የፖለቲክ ሰርኣት ምን መምሰል አለበት የሚለው ጥያቄ ኢትዮጵያን በተለያ መልክ ቢመልሱት
ጠቅለል ባለ መልክ ሲታይ ሁለት በጣም የተለያ መስመሮች አሉ፡፡ አንደኛው መስመር ኢትጵያ ውስጥ በዜግነት ላይ
የተመሰረተ የፖለቲካ ስርአት መመስረት አለበት የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው
ፌዴራሊዝም በትክክል በስራ ላይ አለመዋሉ ነው እንጂ ችግሩ በማንነት ላይ የተመሰረተው የኢትጵያ ፖለቲካ በራሱ
ችግር የለውም የሚል ነው፡፡ የአንድ አገር ፖለቲካ ስርአት በብሄር ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ለአገር ግንባታ
ሊጠቅም ቀርቶ ከሁለት ተፎካሪ ብሄሮች የመጡ ግለቦችን አቀራርቦ ሃሳብ ለሃሳብ እንዲለዋወጡ ማድረግ እንደማይችል
የራሳችን አገር ተሞክሮ በግልጽ ይናገራል፡፡ አፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ ሰውና ተፈጥሮ ሀብት ካላቸው አገሮች ውስጥ አንዷ
ናይጄሪያ ናት። ናይጄሪያ 1960 ዓም ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጥታ ሉዓላዊ አገር ስትሆን የአገሪቱ ፖለቲካ የተመሰረተው በብሄር
ማንነት ላይ ነበር፡፡ ይህ በማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ አዲሲቷን አገር ናይጀርያን ገና በህፃንነቷ ነበር መበጥበጥ
ጀመረው ፖለቲካ ስልጣን ጥማት የሰከራው የናይጀሪያ ልሂቃን ናይጄሪያ የነጻነትን ጣዕም አጣጥማ ሳትጨርስ ነበር
የመጀመሪያው የጎሳ ግጭት የጀመሩት ይህ የጎሳ ግጭት ናይጀሪያ አፍሪካ አይታው ወደማታውቅ የእርስ በእርስ ጦርነት
ውስጥ ይዟት ከመግባቱ ባሻገር ለሚቀጥሉት ሰላሳ አመታት ናይጀሪያ የወታደራዊ አምባገነኖች መፈንጪያ አንድትሆን
አድርጓል፡፡ ናጄሪያ ነፃነቷን ካገነች ከ 57 አመታት በኋላ ዛሬ ከጎሳ ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ ስላልተቀላቀለች ሰላምና
መረጋጋት የጎደላትና ሙስና የነገሰባት ሃገር ናት፡፡ የማንነት ፖለቲካ ችግር አፍሪካ ውስጥ ብቻ አይደደለም ያለው፤ ቦስኒያ
ውስጥ Even birds don’t fly to the ther part “ የተባለ የሚነገርላት ከተማ አለች፡፡ እቺ በአንድ በኩል የቦስኒያ ዝሪያ
ያቸው በሌላ በኩል ደግሞ የክሮሺያ ዝሪያ ያላቸው ነዋሪዎች የሚኖሩበት ሞስታር የምትባል ለሁለት የተከፈለች ከተማ
ከዘርና ከሀይማት ግጭት ተላቃ አታውቅም፡፡ በዚች የአንድ አገር ዜግነት ያለቸው ህዝቦች በሚኖርባት የተከፋፈለች
ከተማ ውስጥ የአንደኛው ክልል ነዋሪ በምሽት ተሳስቶ ወደሌላኛው ከተማ ክልል ከሄደ መመለሱ አጣራጣሪ የሚሆንበት

8
ጊዜ አለ፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ የኢትጵያ ህዝብ በተለይ ወደፊቷን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመንባቱ ሂደት ውስጥ
ከፍተኛ ሚና ለሚጫወተው ምሩርና ወጣቱ ትውልድ ፊት ለፊት ላይ የሚጠብቁት ህገ መንግስታዊ ምርጫዎች ምን
ያህል ውስብስብና አስቸጋሪ ምርጫዎች እደሆኑ ከወዲሁ ለማሳሰብ ነው፡፡ ፊት ለፊታችን ላይ የሚጠብቁን የተለያዩ ህገ
መንግስታዊ ምርጫዎች ከባድ ውስብስብ የሚያደርገው የምርጫዎቹ መብዛት ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ምን አይትነ
ምርጫ ስርአት፣ ምን አይነት የመንስት ቅርፅና ምን አይነት የመንግስት መዋቅር ያስፈልጋታል የሚለውን ጥያቄ ከባድና
ውስብስብ የሚያደርገው አንደኛ-

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የፖለቲካ ባለጉዳች (Political Interest of the Stakeholders) የተለያና አንዳዴም የሚቃረን
ነው፣ ሶስተኛ ምርጫዎቹ እርስ በእርስ የተያያዙና ከሶስቱ ምርጫዎች አንዱን ስንመርጥ ምርጫው በተቀሩት ሁለቱ
ምርጫዎች ላይ ተፅዕኖ ስለሚያደርግ ነው፡፡ የወደፊቷን ኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫ ቅርፅና ይዘት ከሚሰጡት ህገ
መንግስታዊ ምርጫዎች ውስጥ አንዱ የመንግስት መዋቅር ምርጫ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚበጀኝ ፌዴራዝም ነው
ብሎ ፌደራል የመንግስት መዋቅርን ከመረጠ በፌደራል ስርአቱ ውስጥ ክልሎችን ለመከለል የምንጠቀመው መመዘኛ
በፖለቲካ ስርአቱ ምስረታ ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ለምሳሴ ክልሎች የሚከለሉት እንዳሁኑ ቋንቋን ወይም ዘርን
መሰረት በማድረግ ከሆነ ይህን ተከትሎ የሚመሰረተው የፖለቲካ ስርአትም ከዘርና ከማንነት የራቀ ሊሆን አይችልም፡፡
ኢትዮጵያን እንደገና ወደ ብሄር ተኮር ፖለቲካ ከወሰድናት ደግሞ አገራችንን አይናችን እያየ ናጄሪያን ከግማሽ ምዕተ
አመት በላይ ላሰቃያት በሽታ ዳረግናት ማለት ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ብሄር ተኮር ፖለቲካ ለኢትዮጵያ አያዋጣም
የሚል ጠንካራ ሃሳብ የቀረበው ናጄሪያ ላይ የደረሰው አደጋ ኢትዮጵያ ላይም ሊደርስ ይችላል በሚል ፍራቻ ብቻ
አይደለም፡፡ ብሄር ተኮር ፖለቲካ አንደኛ በተፈጥሮው ማህበረሰቦች የሚለያ ፖለቲካ በመሆኑ፣ ሁለተኛ ጠንካራ የአገር
አንድት ለመገንባተ የማይመች ስለሆነና ሶስተኛ ሰላምና መረጋጋትን የሚያደፈርስ ፖለቲካ ስለሆነ ነው፡፡ በፍልስፍና ደረጃ
ሲታይ አንድ ሰው የፖለቲካ አቅጣጫውን እሱ እራሱ ይመርጣል እንጂ ፖለቲካው ሰውን አይመርውም፡፡ የብሄር ፖለቲካ
ረጋ ብለን ካሰብንበት ሌሎች መርጠውልን በስሜታዊነት የምንቀላቀለው እንጂ እኛ ራሳችን በአመክንዮ ላይ ተመስርተን
መርጠን የምንቀላቀለው ፖለቲካ አይደለም፡፡ ይብዛም ይነስም የኢትዮጵያ ህዝብ ከፌዴራዝም ጋር ተዋውቋል፡፡ ዛሬ
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፌዴራል ስርአት ከዲሞክራሲ ጋር የማይተዋወቅና ጥቂቶች እንዳሰኛቸው የሚዘወሩት ፌዴራል
ስርአት ቢሆንም ፌዴራሊዝም ከዲሞክራሲ ጋር በአንድ ላይ ሲቀርብ ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ አገሮች ፍቱን መዲሃኒት
መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ እንዲህም ሆኖ ፌዴራሊዝም በተለይ በአገር አድን መንገድ የሚመሰረተው
ፌዴራሊዝም በአገሮች ውስጥ ተግባራዊ ሲሆን የፌዴራል ክልሎቹ የሚሰረቱበት መንገድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ
ያስፈልገዋል፡፡ ዛሬ ኢትያዮጵያ ውስጥ ያለው ፌዴራል ስርአት የተመሰረተው ዘር ቋንቋን እንደ ብቸኛ መመዘኛ
በመውሰድ ነው፡፡

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ስትመሰረት የህዝቦቿ ምርጫ ፌዴራል የመንግስት መዋቅር ከሆነ የፌዴራል ክልሎችን ለመከለል

 የህዝብ ብዛትን፣
 የቆዳ ስፋትን፣

9
 የመልማት አቅምን፣
 የተፈጥሮ ሀብት ስርጭትን፣
 ቋንቋን የአስተዳደር አመቺነትን፣
 የአብሮ የመኖር ታሪክን፣
 የታሪክ ትስስርን እና
 ኩታ ገጠም አስፋፈር

እንደ መመዘኛ መጠቀም ጠንካራ የፌዴራል ስርአት ለመፍጠር ከማስቻል ባሻገር ለዘላቂ ሰላምና ለእድገት አመቺ
ሁኔታዎችን ይፈጥራል፡፡ ፌዴራሊዚም ፍጹም የሆነ የመንግስተ መዋቅር አይደለም፣ እንደማንኛውም ፖለቲካዊና
ማህበራዊ ክስተት የራሱ የሆነ ጠንራና ደካማ ጎኖች አሉት፡፡ አንዳድ አገሮች ውስጥ ከአሃዳዊ የመንግስት መዋቅር ይልቅ
ፌዴራል መንግስት መዋቅር ቢኖር የሚመረጥበት ጊዜ አለ፡፡ ለምሳሌ ህንድን ያክል ትልቅና በዘር በሀይማትና በቋንቋ
የተከፋፈለ አገር በተማከለ አሃዳዊ የመንግስት መዋቅር ማስተዳደር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ አገሮች ፌዴራል
የመንግስት መዋቅርን የሚመርጡት የፌደራልዝም ጠንካራ ጎኖች ደካማ ጎኖቹን ስለሚፈትሹበት ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ
የፌደራልዝምን ጠንካራና ደካማ ጎኖቹ በቅደም ተከተል እንመለከታለን፡፡

የፌደራልዝም_ጠንካራ_ጎኖች

1.የፌደራልዝም አንዱና ትልቁ ጥቅም በአንድ በኩል ፖለቲካ ስልጣንን በክልልና በማእከል በመክፈል በሌላ በኩል ደግሞ
አንዱ የመንግስት ተቋም ሌላውን መቆጣጠር የሚችልበትን የመንግስት ስርአት በመገንባት የአምባገነንነት
አዝማሚያወችን የሚዋጋ ስርአት መሆኑ ነው ፡፡

2. በዘር:- በሃይማኖትና በቋንቋ በተከፋፈሉ ማህበርሰቦች ውስጥ ፌደራሊዝም ብዝኃዊነት {diversity} የተከበረበት
አገራዊ እድገት እንዲፈጠር ይረዳል

3. ፌደራል ስርዓት ባለባቸው ሀገሮች ውስጥ ማእከላዊው መንግስት ክልሎችን በማበርታታት ፤በማነቃቃትና እርስበርስ
እንዲወዳደሩ የተለያዩ ማበረታቻወችን በመስጠት የአስተዳደር ውጤታማነትና ቅልጥፍና እዲፈጠር ይረዳል።

4.አሃዳዊ መንግስት በክልል፡-በአውራጃ፡-በወረዳና በአጥቢያወች የሚኖረውንህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ተረድቶ


በየአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄወች የሚመልስ እቅድ ማውጣት ይቸግረዋል ፡፡በፌደራል ስርአት ውስጥ ግን
ከክልሎችና የአካባቢ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩት ህዝብ ቅርብ ስለሆኑ የህዝብን ጥያቄ በቅርብ ተገኝተው መመለስ
ይችላሉ

5.በፌደራልዚም ውስጥ በሁለት ደርጃ የተዋቀሩ መንግስታት (ማእከልና ክልል) ስላሉ አንዱ የአንዱን ስራ እቅስቃሴ
ይቆጣጠራል ፤ይህ የሁለትዮሽ ቁጥጥር በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ በህዝብ ላይ አሉታዊ ተጽኖ የሚደርጉ
ውሳኖወችም ለመቆጣጠር ያሰችላል።

10
6. ፌደራልዝም ህዝብን በሚኖርበት አካባቢ ጉዳዮች ላይ የሚያሳትፉ ትናንሽ የአስተዳደር አካላትን ስለሚፈጥር ህዝብ
በአካባቢውና የሀገሩን ጉዳዮች የማወቅና የመወሰን ብቃትና ችሎታ እዲኖረው ሁኔታወችን ያመቻቻል፡፡

7. ፌደራልዚም በዘር፡-በሃይማኖትና በቋንቋ በተከፋፈሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በማሰወገድ


የአብሮ መኖር ባህልን ይፈጥራል።

8.ፌደራልዚም የተለያዩ ህዝቦችን አሰባስቦ አንድ ትልቅ ሃገር በመፍጠር ጠንካራ የመከላከያ ተቋም፡-ከፍተኛ የልማት
ችሎታና ሰፊ ገበያ ያለው ግዙፍ ኢኮኖሚ ይፈጥራል

የፌደራልዚም_ደካማ_ጎኖች

1. በፌደራሊዝም ውስጥ አንዳንድ ጊዜ በማእከላዊ መንግስት በክልል መንግስታት መካከል የስልጣን ፉክክር ይታያል
እነዚህ ሁለት መንግስታት ለመደመጥ በሚያደርጉት የእርስ በርስ ፍትጊያ የመንግስት ውጤታማነትና ቅልጥፍና ይቀንሳል
(conflict of Authority)

2. በፌደራል ስርአት ውስጥ በተለይ ብሄረ ብሄር ፌደራልዚም ባለባቸው አገሮች ውስጥ በተቀናቃኝ ብሄሮች መንግስታት
ጎን ለጎን መኖር የብሄር ማንነት እዲጎላ ያደርጋል ፡፡ የብሄር ማንነት በጎላ ቁጥር ደግሞ የህዝብ ሀገር ወዳድነትና አርበኝነት
ጎልቶ የሚታየው በክልል ደረጃ ይሆንና ብሄራዊ የሀገር ወዳድነትና አርበኝነትን ያሳንሰዋል (Rejionalism over
Patriotism}

3. ፌደራልዚም ባለባቸው ሀገሮች ውስጥ መንግስት በሁለት ደርጃ (ክልልና ማእከል )እንዳለ ሁሉ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን
ያለው በእነዚሁ ሁለት ደረጃወች ነው፡፡አንዳንዴ ችግሮች ሲፈጠሩ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ ሁለቱ መንግስታት ጣት
እየጠቋቆሙ የተፈጠረው ችግር ትክክለኛው ተጠያቂ ማን እንደሆነ ለማቀቅ ያሰቸግራል (Lack of Accountability)

4. የክልል መንግስትና ማእከላዊ መንግስተ ሀገራዊና የክልል ውሳኔወች ለመወሰን የሚያደርጉት ድርድር አድካሚና ብዙ
ጊዜ የሚወስድ ነው ፡፡እንዲህ አይነቱ አድካሚና ብዙ ጊዜ የሚወስድ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ፈጣን ውሳኔ የሚፈልጉ
አንገብጋቢ ጉዳዮች ተጠልጥለው እንዲዘገዩ በማድረግ አስፈላጊ ችግር ይፈጥራል በፌደራል የመንግስት መዋቅር ውስጥ
ክልሎች ሉአላዊ ግዛቶች ናቸው፡-እንዲህ ማለት ደግሞ ክልሎች ማእከላዊ መንግስት ጣልቃ የማይገባበት የራሳቸው የሆነ
የስልጣን ክልል አላቸው ማለት ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ የክልሎች ስልጣን በጨመረ ቁጥር እንዳንድ ከልሎች በብሄራዊ ደረጃ
የሚቀየሱ ፖሊሲወችን የማይሰሙ ከሆነ ፖሊሶቹ በእነሱ ግዛቶች ውስጥ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ብዙ ጋሬጣወችን
ይፈጥራሉ፡፡ ፌደራል ስርአት በሚከተሉ ሀገሮች ውስጥ በክልሎች እና በማእከላዊ መንግስት መካከል የሚነሱ
አለመግባባቶች አንዳንዴ ተራ የፓርቲ ፖለቲካ ችግር የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ በፖርቲወች መካከል በሚነሱ ተራ የፖለቲካ
ሹክታወች የተነሳ በሚሰረዙ ወይም ተግባራዊ ባልሆኑ ፖሊሲወች የሚጎዳው ግን ፓርቲወቹ ሳይሆኑ ህዝብ ነው

ይህ ጽሑፍ የተወሰደዉ ከ Daniel Tefera fac3book ገጽ ነዉ።

11

You might also like