አዕማደ ምስጢር ዮሲ

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 18

አዕማደ ምስጢር ፩ እና 2

አላማው ፡-በዚህ የማስተማሪያ መጽሐፍ ወስጥ አምስቱን አዓማደ ምስጢራት ቤተ ክርስቲያን


እንማራለን፡፡
 ስለ አምስቱ አዕማደ ምስጢር የምንማርበት
 ስለ እያንዳንዱ ምስጢር ትርጉሙን መሰረተ መጽሐፍ ቅዱስን በማድረግ እንማራለን፡፡
 በየወቅቱ ለሚነሱ የመናፍቃን ጥያቄዎችን መልስ በመስጠት ለሚይቁ ጥያቄዎች መልስ
በመስጠት
 የተለያዩ መጽሐፍትን በማንበብ እውቀትን ማክበር ወዘተ
መግቢያ፡- ትምህርተ ሃይማኖት ወደ እግዚአብሔር የምታደርሰን ፍኖተ እግዚአብሔር የምናው
ቅበትና ዘላለማዊ ሕይወቱንም የምንጎናፀፍበት ‹‹ርትዕት ሃይማኖት›› የምነገነዘብበት ነው፡፡
 ትምህርተ ሃይማኖትን ሊቃውንት ዶግማና ቀኖና ብለው በሁለት ይከፍሉታል ፡፡ደግማ
ማለት መሠረተ እምነት ማለት ነው፡፡
 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የሀይማኖት መሰረት እንደ ሆኑ የምታምነው የምታስተምረው
አምስቱን አዕማደ ምስጢራት ነው፡፡
 የሀይማኖር መሰረት የሚባሉት አምስቱ አዕማደ ምስጢራት የሚከተሉት ናቸው፡፡
-1 ምሥጢረ ስላሴ 4- ምስጢረ ቁርባን
2- ምስጢረ ስጋዌ 5- ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ናቸው፡፡
ለምን ምስጢር ተባሉ?
 ለአማንያን እንጂ ለኢ-አማንያን ሰለማይነግሩ
 በማናየው ነገር ለእኛ ረድኤትን ስለሚያሠጡን
 በእምነት ስለምንረዳቸው
 በአጠቃላይ በአይነ ሥጋ ለማይታየው በእጅ ስለማይዳሰሰው አምላክ አንድነትና ሶስትነት ስለ ስጋ
መልበሱ ሰለዳግም ምጽአቱ ሰለሚናገሩ ነው፡፡
ለምን አዕማድ ተባሉ?
 አምስቱ አዕማድ ምስጢራት ‹‹አዕማድ›› መባላቸው ለክርስትና እምነት ምሶሶ በመሆናቸው
ነው፡፡ ዐምድ የሚለው የግዕዝ ቃል በነጠላ ትርጉሙ ምሶሶ ዋና ቋሚ ማለት ሲሆን በብዙ
ደግሞ አዕማድ ይባላሉ፡፡
ለምን አምስት ሆኑ?
 ለአምስቱ አዕማድ ምስጢራት ስያሜ መሰረቱ (318 ቱ) ሊቃውንት በኒቂያ ጉባኤ
ከአስታወቁት ከሀይማኖት ቀኖና (ፀሎተ ሀይማኖት) የተገኘ ነው፡፡

1
 አምስቱ አዕማድ ምስጢራት የእምነት ምሶሶዎች መሆናቸው በሚከተሉት ቃላት መመልከት
ይቻላል፡፡
 ማቴ 28፥19 ‹‹ ሒዱና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ
እያስተማራችሁ ደቀ መዝሙሮቼ አድርጓቸው፡፡
 ምስጢረ ስላሴን
 ዮሐ 1፥14 ‹‹ቃልም ስጋ ሆነ ››- ምስጢረ ሥጋዌ
 ማር 16፥16 ‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡
ምስጢረ ጥምቀት
 ሥጋዩን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ፡ዮሐ 6፥54
ምስጢረ ቁርባን
 ዮሐ 11፥25 ‹‹ ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው
ይሆናል፡፡
ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን
በአጠቃላይ ፡- አንድ ሰው በዚህ አለም ውስጥ ሲኖር አምስቱን አዕማደ ምስጢራት በሚገባ ማወቅ
ይጠበቅበታል፡፡ አንድ ክርስቲያን ወደ ክርስትናው አለም ከመቀላቀሉም በፊትም ሆነ በኋላ እነዚህን
አምስቱን አዕማደ ምስጢር ጠንቅቆ ማውቅ ይጠበቅበታል፡፡ በእለት ወደ እለት የዳበረ የትምህርተ
ሀይማኖት ዕውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ ምክንያቱም መሰረተ እምነት ሀሊዎተ እግዚአብሔር ፣ነገረ
ሥጋዌ ፣ምስጢረ ጥምቀት፣ምስጢረ ቁርባንና ምስጢረ ትንሳኤ ሙታንን በሰፊው የሚዳሰስበት በመሆኑ
ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ቅድሰት ቤተክርስቲያን ሰው ከእግዚአብሔር እንዳይርቅና ከእግዚአብሔር ጋር
በእምነት እንዲፀና እነዚህን ምሰሶዎችን ታስተምረዋለች፡፡ በእነዚህ ምሶሶዎች የተደገፈ ጠላታችን
አጋንንትንና መናፍቃንን ድል ያደርጋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል እያንዳንዱ አዕማደ ምስጢራት እንመለከታለን፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፤አሜን፡፡
2 ምስጢረ ሥላሴ
 ሥላሴ የሚለው ቃል መሰረታዊ አመጣጡ ግዕዝ ሲሆን ‹‹ሠለሰ›› ሶስት አደረገ ከሚለው ግስ
የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም ሶስትነት ሶስት መሆን ማለት ነው፡፡
 ይህ ምስጢር የስላሴን አንድነት ሶስትነት የምንማርበት ትምህርት ነው፡፡
 ሥላሴ በስም፣በአካል፣በግብር ሶስት ሲሆን በቀረው ሁሉ አንድ ናቸው፡፡
 ቅድስት ቤተክርስቲያን በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በመጠቀም ስላሴን አሙልታና አጉልታ
ታስተምራለች እነሱም

2
 ሥላሴ ዋህድ፡- ቃሉ የሚያሳየው በአንድ እግዚአብሔርነት ከሚገኝ ከሶስቱ አካላት በቀር
መንትያ ወይም ተመሳሳይ የሌለውና ብቻውን የነገረ ያለና የሚኖር ሶስትነትን
የሚያመለክት መጠሪያ ነው፡፡

 ሥላሴ ዘለዓለም፡- ጊዜ ቀደሞት ከጊዜ በኋላ የመጣ ጊዜ አልቆበት ከጊዜ በኋላ የማያልፍ
ስለመሆኑ ለማስገንዘብ መጠሪያ ነው፡፡
 ቅዱስ ስሉስ (ልዩ ሶስትነት) በሶስትነት አንድነት በአንድነት ሶስትነት ያለበት በመሆኑ ልዩ
ሶስትነት በማለት ይገለፃል፡፡
ለምን ልዩ ተባለ?መልስ እንድነትን የማይነጣጥል ሶስትነት፤ሶስትነትን የማይጠቀልል
አንድነት ያለበት ስለሆነ ነው፡፡
 ቅድስት ስላሴ አምፃኤ አለማት ወላዴ ዓለማት እንትነቱን ለመገለጽ ቅድስት ስላሴ በማለት
ይነገራል፡፡
 ማን ፈጠረን? ስላሴ
 ስላሴ ስንት ናቸው?አንድም ሶስትም ናቸው
 አንድነታቸው እንዴት ነው ?በባህርይ በመለኮት በአገዛዝ በስልጣን አለምን በመፍጠር
እንዲሁም በማሳለፍ
 ሶስትነታቸው እንዴት ነው?በስም በአካል በግብር
 የስም ሶስትነታቸው?በስም ፣በአካል፣በግብር
 የስም ሶስትነታቸው?አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
 አብ ማለት ምን ማለት ነው?አባት የማን?የወልድ
 ወልድ ማለትስ?ልጅ የማን ልጅ?የአብ የባሕርይ ልጅ
 መንፈስ ቅዱስ ማለትስ?ሠራፂ ከማን የሠረፀ?አብን አክሎ ወልድን መስሎ ከአብ የሠረፀ
ወይም የተገኘ፤
 የአካል ሶስትነታቸው??- አብ ፍፁም አካል፡ፍፁም ገጽ፡ፍፁም መልክ አለው
- ወልድ ፡ፍፁም አካል፡ፍፁም ገጽ፡ፍፁም መልክ አለው
- መንፈስ ቅዱስ ፡ፍፁም አካል፡ፍፁም ገጽ፡ፍፁም መልክ አለው
 የግብር ሶስትነታቸውስ? አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ፡፡
የስላሴን አንድነት
ስላሴ በስም በአካል በግብር ሶስት ናቸው፡፡
 የስም ሶስትነት ፡-አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ

3
 ስላሴ የስም ተፋለስ የለባቸውም፡፡
 የስላሴን የስም ቅደም ተከተል ማፋለስ የለብንም፡፡
 አብም አብ ነው፡-ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይደለም
 ወልድም ወልድ ነው፡- አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም
 መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው፡- አብ ወልድ አይደለም
(ሀይማኖት አበው ቅዱስ አግናጢዎስ)
በስም ሶስትነት፡-
 አብ አባት ይባላል እንጂ ልጅ መንፈስ ቅዱስ አይባልም
 ወልድም ልጅ ይባላል እንጂ አባት መንፈስ ቅዱስ አይባልም
 መንፈስ ቅዱስም ሠራፂ ይባላል እንጂ አባት ልጅ አይባልም፡፡
የአካል ሶስትነት፡-
 ሁሉም እኔ ባይ አካል አላቸው፡፡
 ሶስቱም እያንዳንዳቸው የራሳቸው ፍፁም መልክ ገጽ አላቸው
 ለአብ ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገጽ አለው
 ለወልድም ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገጽ አለው
 ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም አካል ፍፁም መልክ ፍፁም ገጽ አለው
N.B . አካል፡- ማለት ሙሉ ሰውነትን ከራስ ፀጉር እግር ጥፍር
መልክ፡-ማለት የሰውነትችን ክፍሎች የሚወክል ነው፡፡
ገጽ፡- ማለት ከአንገት በላይ ያለውን ይወክላል፡፡
የግብር ሶስትነት፡- ግብር ማለት ስራ ማለት ነው፡፡ በአንዱ ግብር አንዱ ሊሳተፍበት የማይችል ልዩ
የግብር ሶስትነት ነው፡፡
 የአብ ግብሩ ፡ መወለድ ፣ማስረፅ ነው፡፤
 የወልድ ግብሩ ፡መወለድ
 የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ ፡መስረፅ (መገኘት) ነው፡፡
የስላሴን አንድነትና ሶስትነት በመጽሐፍ ቅዱስ
1. ምስጢረ ስላሴ በብሉይ ኪዳን
 በዘመነ ብሉይ የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት በግልጽ አይታውቅም ነበር፡፡
ምክንያቱም፡
 የሰው ልጅ ጥንተ ተአብሶ ስለነበረበት
 የሰው ልጅ ከአእምሮ ጥበት አንጻር ሊረዳው ስለማይችል፡፡

4
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድነቱን ሶስትነቱን ሊገለፅ ሰለፈለገ
 ጌታችን ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት በአዲስ ኪዳን አንድነቱን ሶስትነቱ
እግዚአብሔር በግልጽ ለመግለፅ ስለፈለገ ነወ፡፡
 ነገር ግን ለሰው ልጅ በተረዳ መጠን የስላሴ አንድነትና ሶስትነት እግዚአብሔር
እንደገባላቸው ይረዱ ነበር፡፡
 ዘፍ 3፥22 ‹‹እነሆ አዳም ክፍውንና ደጉን ይለይ ዘንድ ከእኛ እንደአንዱ ሆነ››
 ዘፍ 11፥7 ‹‹ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እንዳይሰማ ቋንቋቸውን እንደባልቅባቸው››
 ት.ኢሳ 6፥1 ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ ምድር ሁሉ በክብሩ
ተሞልታለች››
ወዘተ…………
2. ምስጢረ ስላሴ በሀዲስ ኪዳን
 ምስጢረ ስላሴ በሀዲስ ኪዳን ግልፅ የሆነበት ነው፡፡
 ማቴ 3፥17 ‹‹ጌታችን በዮርዲያኖስ ሲጠመቅ ሶስትነት ተረጋግጧል››
 ሉቃ 1፥35 ‹‹ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑል ኃይልም
ይፀልልብሻል፡፡ ከአንቺ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡
 2ኛ ቆሮ 13፥12 ‹‹የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሔር ቸርነት
የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን››
ምስጢረ ስላሴን የሚያስረዱ ተፈጥሮአዊ ምሳሌዎች
ለምስጢረ ስላሴ ምሳሌ መስጠት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ለስላሴ ምሳሌ ማግኘት
ስለማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን የሰውን ልጅ ይረዳው ዘንድ በስነ-ፍጥረት ማስረዳት
ይቻላል፡፡ምሳሌ ስንሰጥ ግን በተቃራኒው ነው፡፡ ምክንያቱም ትክክለኛ ምሳሌ ስለማይገኝነው፡፡
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተለያየ ስነ-ፍጥረት ሶስትነት አስተምረዋል፡፡
ሀ/ በፀሐይ=በፀሐይ የስላሴን አንድነትና ሶስትነት አስተምረዋል፡፡
 ፀሐይ በአካሏ አንድነታቸውን
 ፀሐይ በግብሯ ደግሞ የስላሴን ሶስትነት ታስተምራለች፡፡
የፀሐይ ግብር ክበብ በአብ
ብርሃኗ በወልድ እንመስላለን፡፡
በሙቀቷ መንፈስ ቅዱስ
ለ/ የሰው ተፈጥሮ
 ሰው በውስጡ ሦስት ነገር ስላለው የምስጢረ ስላሴ አሰረጅ መሆኗ ይቀርባል፡፡

5
 የነፍስ አካሏ አንድ ነው ግብሯ ግን ሦስት ነው፡፡

-በልብነቷ አብ
- በቃልነቷ ወልድ ይመሰላል፡፡
- በእስትንፋስነቷ መንፈስ ቅዱስ
 ነገር ግን አንድ ነፍስ ትባላለች እንጂ ሦስት ነፍስ አትባልም፡፡አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም
አንድ አምላክ ይባላሉ አንጅ ሦስት አምላክ አይባሉም፡፡
ሐ/በዓለም መፈጠር ይመስላል
 አለምን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ መፍጠር የአብን ወላዲነት ያስረዳል፡፡
 በዕለተ ስሉስ (ማክሰኞ) ገበሬ ያልደከመበት መሬት እፅዋት አብቅላ መገኘቷ ለመንፈስ ቅዱስ
መስረፅ ማስረጃ ነው፡፡
2 ምስጢረ ሥጋዌ
 በዚህ ትምህርተ ሃይማኖት ክፍል የምንማረው የአምላክ ሰው የሰው አምላክ መሆኑና ድኅነተ
አለም ነው፡፡
 ሥጋዌ ‹‹ሠገወ›› ሥጋ ሆነ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ሥጋነት፣ሥጋ መሆን
ሥጋ መባል ማለት ነው፡፡
 ምስጢረ ስጋዌ ማለት ሰው የመሆን ሰው የመባል ስጋ የመልበስ ምሥጢር ማለት ነው
 ምስጢር በአጠቃላይ ሰው የመሆን ምስጢር ማለት ነው፡፡
 ሰው የመሆን ስጋ የመልበስ ምስጢር የምንለው ከሶስቱም አካላት ስላሴ ግብራት ሥላሴ
አስማተ ስላሴ አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ በተለየ ሰው ከአመቤታችን
ከቅድስት ድንግል ማርያም ቀድሞ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተወለደ ድህረ ዓለምም ከእሷ
ያለ አባት ከሥጋዊ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑና ሥጋ መልካም ለማምልክት ነው፡፡
አምላክ ለምን ሠው ሆነ ?
 እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ፤ በተወላዲነት ግብሩና በልጅነት ስሙ ከአብ ዕሪና
ሳይለይ ከዙፋኑ ሳይርቅ ከዘመናት በኋላ ረቁቅ ምሉዕና ልዑል አካሉን ሳይለቅ በሰው
በህርይ /ግዙፍ፣ውሱንና፣ትሑት/ ሰው ሆኖ በስጋ ተገለጠ፡፡ ሰውም ከሰውነት ባህርይ
ሳይለይ ከሃማሚነቱ ሳይርቅ ግዙፍ ውስንና ትሑት አካሉን ይዞ በአምላክ ባሑርይ
/ረቂቅ/፣፣ምሉዕና ልዑል) ከዘመናቱ የነበረ አምላክ ሆነ፡፡
 አምላክ ሰው የሆነበት ዋናው ምክንያቱም፡-
የሰዎችን የዘር ሀጢያት ለማጥፋት

6
መርገመ ነፍስና መርገመ ስጋን ለመደምሰስ
በገነት መካከል ለአዳም የተናገረው ቃል ኪዳን ለመፈፀም
የሰው ልጆች መጥፋት (የአዳም ትዕዛዝ መተላለፍ)
የሰይጣንን ጦር (ስውር ሴራ) በቀላሉ ለመሰባበር
የእርቁን የፍቅሩን ለመግለፅ
አዳም ሲበደል ተጣልተው የነበሩትን ሰማይና ምድር ሰወና መላእክት ሰውና
እግአብሔር ሕዝብና አህዛብ ለማስታረቅ………..
የተዋህዶ ምስጢር
 ተዋህዶ ማለት ከሁከት አንድ አካል ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ
የመሆን ምድጢር ነው፡፡
 የአምላክ ሰው መሆን የሰው አምላክ መሆን የሚነገርበት ምስጢር ነው፡፡
 በምስጢረ ቀዋህዶ የማይታየው የመለኮት በስጋ ታየ፣ተጨበጠ ተዳሰሰ የሚታየው የሚዳሰሰው
ስጋ ደግሞ በመለኮት ረቂቅ ማለት ነው፡፡
 ሁለት አካል የሚባለው መለኮታዊ አካልና ስጋዊ (ሰብአዊ)አካል ነው፡፡
 መለኮታዊ አካል፡- ረቂቅ ምሉዕ ሰፊና ልዑል ነው፡፡
 ሥጋዊ አካል፡- ግዙፍ ውሱንና ትሁት ነው፡፡
 ሁለት ባህርይ የሚባለውን መለኮታዊ ባህርይና ሰብአዊ ባህርይ ነው፡፡
 መለኮታዊ ባህርይ፡- መራብ መጠማት መታመምና መሞት የማይስማማው የፍጡራን
ዕውቀት መርምሮ የማይደረስበት የህይወት መሰረትና ምንጭ ነው፡፡
 ሰብአዊ በህርይ፡- ከእራቱ ባህርያት ስጋና ከአምስተኛው ባህርይ ነፍስ የተገኘ ሲሆን
መራብ መጠማት መታመምና መሞት የሚስማማው ነው፡፡
የወልደ እግዚአብሔር ልደታት
 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማንያን የጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ሁለት ልደታት እንዳለው ያስተምራሉ እነዚህም ፡-
1/ ቀዳማዊ ልደት 1/ ዳኀራዊ ልደት
1/ቀዳማዊ ልደት
 ቀዳማዊ ልደት የምንለው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ
ከእግዚአብሔር አብ የሰው ህሊና በማይመረምረው ምስጢር የተወለደው ልደት ነው፡፡
ልደቱም እንደ ሰው ልደት ሳይሆን ከአብ ሲወለድ አብን አክሎ አብን መስሎ አካሉ
አካሉን ባህሪው ባህርይውን መስሎ ባለማነስ ባለመብለጥ ባለመለየት ባለመለወጥ ነው፡፡

7
2/ ዳኀራዊ ልደት
 ይህ ልደት አለም ከተፈጠረ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ከተፈፀመ በኃላ እግዚአብሔር
ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ሁለተኛው ልደት ነው፡፡ ይህ ልደቱም ጌታችን
መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት ቀኑና ሰዓቱ ሲደርስ
የተወለደው ልደት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
 ገላ 4፥4 "ጊዜው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከው ከሴትም ተወለደ"
 ት.ኢሳ 7፥14"እነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ሰሙንም
አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ተወለደ፡፡
የምስጢረ ስጋዌ ምሳሌዎች
 ለምስጠረ ስጋዌ ትክክለኛ ምሳሌ መስጠት አይቻልም ነገር ግን የሰው አእምሮ በተረዳው
መጠን በምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ሀ/ የሰው ነፍስና ስጋ
 የሰው ልጅ ከእናቱ ማህፀን ስጋና ነፍስን ነስቶ ፅንስ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ስጋ
ነው፡፡ይህ ነፍስ ነው ብሎ መለየት መከፋፈል አይቻልም፡፡ በዚህም መሰረት ስጋ
ከመለኮት ጋር ከተዋህደ በኋላ ይህ ስጋ ነው ይህ መለኮት ነው ብሎ መክፈል
አይቻልም፡፡
ለ/ የጋለ ብረት
 አንድ ብረት ከእሳት ካስገቡት ጊዜ ብረትነቱን ሳይለቅ በብረቱ ቅርጽ መጠን እሳት
ይሆናል፡፡ ስጋም መለኮት በተዋህዶ ጊዜ በስጋው ባህርይውን ሳይለቅ በተአቅቦ እሳታዊ
መለኮትን ገንዘብ አደረገ፡፡
 ተአቅቦ በተዋህዶ ማለት የመለኮትና የስጋ ተዋህዶ ያለምንም መለያየት መነጣጠል
ማለት ነው፡፡
 ይህ ምሳሌ ግን የማይወክልበት ምክንያት አለ፡፡ ብረቱ ከእሳት ከወጡት በኋላ
እሳትነቱን ለቆ ወደ ጥንታዊ በረትነቱ ይመለሳል፡፡የነገረውን ተዋህዶም ይቀይረዋል፡፡
በመካከለኛው መለያየት ይፈጠራል፡፡ ነገር ግን መለኮትና ስጋ ከተዋሀዱ በኋላ
የተለያዩበት ጊዜና ሰዓት የለም፡፡
፫ ምስጢረ ጥምቀት
 የጥምቀት ትርጉም -ጥምቀት የሚለው ቃል"አጥምቀ"/ጠመቀ/ ፣ነከረ፣ዘፈቀ ካለው የግዕዝ ግስ
የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መነከር መዘፈቅ መጠመቅ በተገብሮ መነከር መላ አካልን በውሃ

8
ወስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡
 በምስጢረ ጥምቀት ስንጠመቅ መላ አካላችንን ውሃ ውስጥ መሰጠም አለበት፡፡
 ካህኑ ተጠማቂውን ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ማድረጉ ምሳሌ አለው፡፡
 መጥለቅ ወደ መቃብር የመውረድ መውጣት (ብቅ) ማለት ደግሞ የትንሳኤ ምሳሌ ነው፡
 ሶስት ጊዜ መፈፀሙ የስላሴን ሶስትነት ሲያመለክት ግብሩ ደግሞ አንድ አይነት መሆኑ
አንድነቱን ያመለክታል፡፡ ይህም ተጠማቂው በስላሴ አምኖ መጠመቁን ያመለክታል፡፡
 ጌታ በከርሠ መቃብር ሶስት መዓልትና ሦስት ለሊት አድሮ የመነሳቱ ምሳሌ ነው፡፡
የጥምቀት አስፈላጊነት
 በልጅነት አጀማመር ጥምቀት የመጀመሪያ ነወ፡፡ ጥምቀት የምስጢራት ሁሉ በር ከፋች
ነው፡፡
ጥምቀት ለምን የመጀመሪያ ተባለ?
 የምስጢራት ሁሉ መክፈቻ ምስጢር /በር/ነው፡፡
 ጥምቀት መርሆ ምስጢራት ይባላል፡፡ ምክንያቱም
 የምንወለድበት ምስጢር ነው፡፡ዮሐ 3፥6
 ከክርስቶስ ጋር የምንተባበርበት ምስጢር ነው
 ክርስቶስን ለብሰን ለሰልፉ የምንዘጋጅበት ነው፡፡ ገላ 3፥27
 በህይወት መዝገብ (የስላሴን ልጅነት/ የምናገኝበት ነው፡፡
 በአጠቃላይ የጥምቀት አስፈላጊነት
ሀ/ከድህነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማር 16፥16
ለ/ ሁለተኛ ያልተወለደ መወለድ ያልቻለ መንግስተ ሰማያትን ማየት፣ማግኘትና መውረስ
አይችልም ፡፡ ዮሐ 3፥3-12
ከውሃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም ልደት ማድረግ አለበት፡፡
ሐ/ ስርየተ ኃጥአት ይገኛል፡፡
 በተለያየ ሀጢያት የነበሩ ሰዎች በአህዛብነት በነበሩበት ጊዜ የፈፀሙዋቸውን
የርኩሰት ስራዎች የሀጢያት ሰንኮፍ ቆርጦ በሚጥል ጥምቀት ከሀጢያት ነጻ
መውጣት ይችላል፡፡
 የሐ.ሥራ 22፥16
 የሐዋ ሥራ 9፥15-17
 የሐዋ ሥራ 2፥36
መ/ በጥምቀት ጌታችን እንመስለዋለን፡፡ሮሜ 6፥ 8

9
ሠ/ አዲስ ህይወትን መለጎናፀፍ፡፡ ሮሜ 6፥4
ረ/ የክርስቶስ አካል የቤተክርስቲያን አካል ለመሆን፡፡ ገላ 3፥27
ለጥምቀት የሚያስፈልጉ ነገሮች(መደበኛው የውሃ ጥምቀት)
1. ለጥምቀት የሚያስፈልጉ ቦታዎችን ማዘጋጀት
 ፈሳሽ ወንዝ ካለ
 የተጠማቂውን አካል ማጥለቅ የሚችል እቃ ጉድጓን ማዘጋጀትማ መሙላት
 አነዚህ ከላይ የተገለፁት ከሌሉ የተጠማቂውን አካል ሊያርስ የሚችል ውሃ ቀድቶ በላዩ
ላይ መጨመር/መድፋት/
2. የሚያጠምቅ ካህን የሚያስጠምቅ ምዕመን
3. ተጠማቂው/አስጠማቂው/ የሚያስገልጉ ነገሮችን ማዘጋጀት
4. ወደ ጥምቀት ሲገቡ ምንም ይዞ መግባት እንደማይቻል መንገር
5. ዋስ አዘጋጅ ያስፈልጋል፡፡ ይህም የክርስትና አባት/እናት/ ዋና አላማውም ክርስትና እምነት
እንዲያስተምሩዋቸው፡፡
የጥምቀት አይነቶች
 የጥምቀት ባህርይዋ አላማዋ አንድ ሲሆን ሶስት አይነት የአጠማመቅ ስርዓት አላት፡፡ እነሱም
ሀ) የውሀ ጥምቀት
ለ) የእንባ ጥምቀት
ሐ) የደም ጥምቀት
ሀ). የውሀ ጥምቀት
 በቤተ ክርስቲያናችን መደበኛው ጥምቀት ነው፡፡
 ወንድ በተወለደ በ40 ቀን ሴት በተወለደች በ80 ቀን ይጠመቃሉ፡፡ ምክንያቱም የአዳምና
የሔዋንን ልደት መሰረተረ በማድረግ ነው፡፡ እንዲሁም አዳምና ሔዋን አግኝተውት
የነበረውን የልጅነት ፀጋ አስወስደው ስለነበር በጥምቀት ደግሞ ልደት እንዲያገኙ ለመጠየቅ
ነው፡፡
ለ) የእንባ ጥምቀት፡- የጸጸት እንባ ማለትነው፡፡
 ይህም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ሀገር በፈታ ቤተክርስቲያንና ካህን ቢታጣ ምዕመናን
ሃይማኖቱን አውቀው ባህሉን ተረድተው ነገር ግን ሰላም በመጥፋቱ ካህን በመታጣቱ አዝነው
በዚህ የበቃነው በሀጥያታችን ብዛት በሰውነታችን ክፋትና በልባችን ትዕቢት ነው በማለት
ተጸጸተው የሚያለቅሱት ለቅሶ ነው፡፡ ይህም ለቅሶ እንደ ጥምቀት ይቆጠራል፡፡
ሐ) የደም ጥምቀት /ደመ ሰማዕት/

10
 የሰማዕት ደም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በዘመነ ሰማዕታት ማለትም፡- አላውያን ነገስታትና
መናፍቃን መኳንንት በበዙበት የሃይማኖት ነፃነት በሌለበት ሀገር ጊዜና ሁኔታ ያተኮረ
ጥምቀት ነው፡፡
 እውነተኞች የክርሰቶስ ተከታዮች በክርስትናቸው ፀንተው ስለክርስቶስ በመመሰከራቸው
በሠይፍ ሲቀሉ በእሳት ሲቃጠሉ በሚደረገው ገቢረ ታምር አማካይነት ሰማዕቱ/ቷ ካለፈ በኋላ
በሰማዕቱ/ቷ አምላክ እናምናለን በማለት መስክረው በሠይፍ ቢሞቱ ደማቸው እንደ ጥምቀት
ይቆጠርላቸዋል፡፡
የወልደ እግዚአብሔር ጥምቀት
 ለምን ተጠመቀ?ትህትናን ለማስተማር ማቴ 3፥15 አርአያ ለመሆን
 የእዳ ደበዳቤ ለመደምሰስ፡፡ ቆላ 2፥13-15
 አንድነቱን ሶስትነቱን ለመግለጽ ፡፡ ማር 3፥16
 ለምን ዮርዲያኖስ ወንዝ ተጠመቀ?-ትንቢቱ ለመፈፀም መዝ 113፥3-6
ምሳሌውን አማናዊ ለማድረግ
የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡፡
 ጥምቀቱን ለምን በውሃ አደረገ?
 ውሃ ለጥፋት ብቻ ሳይሆን ለድህነትም እንዲሆን ለመግለፅ፡፡(የኖህ ዘመን)
 ውሃ በሁሉም ቦታ ለሁሉም ቤት ስለሚገኝ
 ከሀጢያት እድፍ ትጠራላችሁ ሲል፡፡
 ውሃ መልክን ያሳያል እኛም በጥምቀት የስላሴን ልጅነት እናያለን፡፡
 ውሃ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳል ጥምቀትም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ነው፡፡
የጥምቀት ምሳሌዎች፡-
 ለጥምቀት ተምሳሌት የሚሆኑ በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም የተጠቀሱ ብዙ ምሳሌዎች
አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶችን እንመለከታለን፡፡ አነሱም
ሀ) የኖኅ ውኃ 1ኛ ጴጥ 3፥20-21
 ኖኅና ቤተሰቡ ከጥፋት ውኃ የዳኑበት መርከብ የቤተክርስቲያን ውኃው ደግሞ የጥምቀት
ምሳሌ ነው፡፡
ለ) የእስራኤል በኤርትራ ባህር መካከል ማለፍ
 1ኛ ቆሮ 10፥1-2
ሐ) በዕዝረት የንዕማንና የኢዮብ በዮርድያኖስ ወንዝ ተጠምቆ መዳን
 ዘፍ 17፥14

11
 ቆላ 2፥10-12
መ) የጥፋት ውኃ ዘፍ 6፥7
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማን ስም ተጠመቀ?
"እንዲ መልከ ጼድቅ ስርዓት የአለምን ካህን ብርሃንን የምትገልፅ የአብ የባህርይ ልጅ ሆይ
ይቅር በለን"
 ጌታችን የተጠመቀው -- በ30 ዘመኑ /በዘመነ ሉቃስ/
 መቼ ተጠመቀ -- ጥር 10 ቀን ለ11 አጥቢያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት
 ለምን በ10 ሰዓት ተጠመቀ?
 እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ሲል ነው፡፡
 ከጨለማ ወደ በርሃን ማውጣቱን በመግፅ፡፡
 ከጥፋት ወደ ድንነት አመጣኋችሁ ሲል ነው፡፡
 ለምን ጥምቀቱን በሌሊት አደረገ?
 መንፈስ ቅዱስ ሲያርፍበት እርግብ ናት እንዳይሉ
 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከወጣ በኋላ ለምን መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አምሳል
ወረደ?
 ለዮሐንስ ወረደ እንዳይሉ
 መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለውሃ ነው እንጅ ለጌታ አይደለምና
 ሠዎች ማረፊያ ያጣች እርግብ በባህር ስትበር በጌታ ላይ አረፈች እንዳይሉ
 መንፈስ ቅዱስ ለምን በእርግብ አምሳል ወረደ?
 የኃጢያት ባህር ጎደል ሲል እንደ ኖህ ዘመን
 እርግብ የዋህ በመሆኗ ቤቷን አትለቅም መንፈስ ቅዱስም ሁሉን ይጠብቃልና፡፡
 በሲኦል ውስጥ ያሉ ነፍሳት መቼ ተጠመቁ?
 ጌታችን ወደ ሲኦል ሔዶ ለነፍሳን እጆቹን ባሳያቸው ጊዜ ጥምቀት ሆኖ
ተቆጠረላቸው፡፡ 1ኛ ጴጥ 1፥11, 3፥19

4 ምስጢረ ቁርባን
 ምስጢረ ቁርባን ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ ነው፡፡
 ቁርባን ቃሉ የሱርስትና የግሪክ ሲሆን ትርጉሙ በቁሙ መንፈሳዊ አምኃ (ስጦታን፣
መስዋዕት መባዕ ለአምላክ የሚቀርብ የሚሰጥ ገንዘብ ማለት ነው፡፡

12
 ቁርባን በአጠቃላይ በእየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም ነው፡፡
 የምስጢረ ቤተክርስቲያን ሁሉ የበላያቸው መሰብሰቢያቸው መፈፀሚያቸው የሆነው
ቅዱስ ቁርባን በጌታ ትዕዛዝ ፀሎተ ሀሙስ ማታ መስርቶታል፡፡
 ምስጢረ ቁርባን ከሁሉ ምስጢር በላይ የሆነበት ዋናው ምክንያት ጌታ የሰውን ልጆች
ለማዳን በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ካሳ
የከፈለበትን የማዳን ስራ የፈፀበትን ሁኔታ የሚያረጋግጥና የሚመሰክር ነው፡፡እንዲሁም
አማኞች ከሥጋውና ከደሙ ተካፋይ በመሆን የህይወትን ፀጋ እንዲቀበሉ ሰለሚያደርግ
ነው፡፡
 ይህም ምስጢር የፀጋ ሁሉ ምንጭ ስለሆነ ሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ በስጋ
ወደሙ ምስጢር አማካይነት የፈፀማሉ፡፡
 ቅዱስ ቁርባን ለሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አክሊል ነው፡፡ እንዲያውም
የምስጠራት ሁሉ ምስጢር ይባላል፡፡ ምክንያቱም
አንድ ተጠማቂ ተጠምቆ እንደወጣ ቅዱስ ቁርባን መቀበል አለበት፡፡
አንድ ተነሳሒ ቀኖናውን ሲጨርስ በካህኑ ፍቃድ ቀኖናውን ጨርሶ በቅዱስ ቁርባን
ያትመዋል፡፡
በቅዱስ ጋብቻ ለመኖር የወሰኑ ተጋቢዎች ከስርዓተ ተክሊል በኋላ አስቀድሰው
ቅዱስ ቁርባን ይቀበላሉ፡፡
የምስጢረ ቁርባን አጀማመር
 ምስጢረ ቁርባንን የመሠረተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ማቴ 26፥26
 ይህንም ምስጢረ ቁርባን የመሠረተው በስቅለቱ ዋዜማ ማለትም በዕለተ ሐሙስ ምሽት
ታላቁን ስጦታውን ለሠው ልጆች ሰጥቷል፡፡
 መስዋዕተ ኦሪት አልፎ መስዋዕተ ሀዲስ በመተካት ምስጢረ ቁርባንን በምሴተ ሐሙስ
በጌታችን አማካኝነት ተመሠረተ፡፡
ለመቁረብ የሚደረጉ ነገሮች
1. ማመን =ማለት ንሰሃ ገብቼ ስጋወንና ደሙን ብቀበል ፈውስ አገኛለሁ፡፡ ስጋውንና ደሙን
በኃጢያት ብቀበል ግን አቀሰፋለሁ ብሎ ማመን
2. ንሰሃ መግባት =ከመቁረብ በቅድሚያ ያስፈልጋል፡፡
ንሰሃ ለመግባት ሀ/ ከልብ ጋር መማከር

13
ለ/ ውስን ኃጢያትን መጥላት
ሐ/ ወደ መምህረ ንሰሃ መሄድ
መ/ ኃጢያትን ከተናገሩ በኋላ የተሠጠውን ቅኖና መጨረስ
3. 18 ሰዓታት ወይም አፍን ምሬት እስኪሰማው ድረስ የጌታን መከራ ሀሞተ በጠጣቱን እያሰቡ
መፆም ነው፡፡
4. በትዳር የሚኖሩ ከሆነ ከሩካቤ ግንኙነት መከልከል፡፡
ከቁርባን በኋላ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች
 ከልብስ አለመራቆት፡- በቁርባን የሚገኘው ፀጋ ዘለዓለማዊ መሆኑን ማሰብ
 ስግደትን ጨምሮ አድካሚ ስራዎችን መስራት አይገባም
 ከክፍ ነገር ሁሉ መከልከል፡፡
 ከቁርባን በቃለ ማየቁርር (ፀበል) እንዲሁም መክፈልት መቅመስ
በቅዱስ ቁርባን የሚገኝ ፀጋ
ሀ/ የዘለዓለም ህይወት ዮሐ 6፥56
ለ/ ስርዓተ ኃጢያት ያስገኛል ማቴ 26፥26
ሐ/ የኃጢያት ልጓም ሆኖ ያገለግላል፡፡ ዮሐ 6፥35, 6፥54

ስርዓተ ቁርባን
 ቅዱስ ቁርባን ካህናት ህፃናት ደናግል ህዝባውያን ምዕመናን ቤተክርስቲያን የሰራችላቸውን
ቅደም ተከተል ጠብቀው ይቆማሉ፡፡
 የአቀራረብ ቅደም ተከተላቸውም
፩ በቅድሚያ መቅደስ ውስጥ የሚቀርቡ
 ሊቃነ ጳጳሳት --ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት-- ቆሞሳት-- ቀሳውስት--ዲያቆናት
2 ከንፍቀ ዲያቆናት ጀምሮ ሁሉም በየማዕረጉ በቅድስት ውስጥ ይቆርባሉ፡፡
 በመጨረሻም ማየ መቁሪር/የቅዳሴ ጠበል/ ቅዱስ ቁርባን ለተቀበሉ ወዲያውኑ ይሰጣቸዋል፡፡

5 ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን


ትርጉም፡-
 የተለያዩ ሥጋና ነፍስ በመጨረሻቸው ዘመን እንደገና ኀብረት እንዲኖራቸው ዳግመኛ
በማይፈርስና በማይበሰብስ ስጋ እንደሚነሱ የሚገልፅ የቤተ-ክርስቲያን እምነትና ትምህርት
ለትንሳኤ ሙታን ይባላል፡፡

14
 ይህም ትምህርት ለሠው አስተሳሰብ ደቂቅ ምስጢር በመሆኑ ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን
ይባላል፡፡
 የማንኛውም ሰው ሥጋና ነፍስ ከሞተ በኋላ ተለያይተው ይኖራሉ፡፡
በመጨረሻው የፍርድ ቀን ግን ነፍስና ስጋ ተዋህደው ይነሳሉ፡፡
 መ.መክብብ 3፥20 "ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሔዳል ሁሉም ከአፈር ነው ወደ አፈር
ይመለሳል"፡፡
 ሞት ሲባ ለሰው ልጅ የስጋና የነፍስ መለያየት መሆኑን መገንዘብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ
ነው፡፡
 ቅዱሰት መጻሕፍት ሞት ማለት የስጋና የነፍስ መለያየት መሆኑን ያስተምራል፡፡ለምሳሌ
 የዕ 2፥26 "ከነፍስ የተለየ ስጋ የሞተ ነው"
 ማቴ 10፥28 "ሥጋንም የሚገድላትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ"
 መዝ 30(31)፥5 "በእጅህ ነፍሴን እሰጣለሁ"
 ሉቃ 23፥46"… አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ አሰጣለሁ"
ይህም ማለት በሞት ጊዜ ከሥጋ ተለይታ የሚትሔድ ነግስ እንደለች ያስረዳናል፡፡
 ሞት ለሰው ልጅ የህይወት ፍፃሜ አይደለም፡፡
 የአንድ ሰው ነፍስ ከስጋው በምትለይበት ጊዜ ወደ አጸደ ነፍስ ትጓዛለች፡፡
 አፀደ ነፍስ የሚባሉትም ገነትና ሲኦል ናቸው፡፡
 ገነት የጻድቃን ጊዜያዊ ማረፊያ ስትሆን
 ሲኦል ደግሞ የኃጥአን ጊዜያዊ ማረፊያ ነው፡፡
 ከምጽአተ ክርስቶስ በኋላ በገነት ያሉ ወደ መንግስተ ሰማያት በሲኦል ያሉ ደግሞ ወደ ገሃነመ
እሳት ይሄዳሉ፡፡
 እስከ ምጽአት ድረስ ግን ገነትና ሲኦል የነፍሳት ጊዜያዊ ስፍራ ሆነው ይቆያሉ፡፡

ትንሳኤ ክርስቶስ
 ትንሳኤ ክርስቶስ የክርስቶስን ከሙታን መካከል ተለይቶ በሶስተኛው ቀን መነሳትን የሚያስረዳ
ነው፡፡
 ትንሳኤ አምላካችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለሰው ልጆች ከዋለላቸው ውለታዎች መካከል
የመጨራሻውና ደገኛው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በስጋ አለም አናውቀውምና፡፡
 በህያው መድሐኒትነቱ ወይም በዳግማዊ አዳምነቱ ሞትን በመሻር ሕይወትን በመስጠት
ትንሳኤውን ገለጠ፡፡

15
 የጌታችን የኢያሱስ ክርስቶስ ትንሳኤው የደስታችን መጨረሻ የሃዘናችን መዝጊያ፣
የክርስትናችን መሠረት ነወ፡፡
ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ የተመሰሉ ምሳሌያት
 የኖህ ሶስት ቀን ሙሉ በስካር መቆየትና በሶስተኛው ቀን መንቃት
 የይስሐቅ በአብርሃም ህሊና መስዋዕትና በሶስተኛው ቀን መዳን ወይም አለመሰዋት
 የዮናስ ሶስት መዓልትና ሶስት ለሊት በዓሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ አድሮ መውጣት ወዘተ… ዮና
2፥1-2
ስለክርስቶስ ሶስት ቀንና ሶስት ለሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብር አጥፍቶ መነሳቱ
ምሳሌ ናቸው፡፡ ዘፍ,9፥20-24
ዘፍ 22፥1-14
የክርስቶስ ትንሳኤ አላማ
 ክርሰቶስ መቀበሩ ሙስና መቃብርን ሞትን ለማጥፋት ሲሆን መነሳቱ ደግሞ መሠረታዊ አላማ
ነበረው፡፡ እነሱም፡-
ትንሳኤ ሕይወት መሆኑን ለማረጋገጥ
 ዮሐ 5፥26, 14፥6, 11፥25
 1ኛ ቆሮ 15፥45
ለሰው ሁሉ ትንሳኤን ለማብሰር
 መዝ 15፥9-11
 ዮሐ 11፥24
 ኢሳ 26፥19
 ዳን 12፥2-3
ከሞት በኋላ ስለአለው ትንሳኤ ለማሳወቅ ነው፡፡
 ማቴ 22፥23
 1ኛ ቆሮ 15፥20-24
ሁለት አይነት ትንሳኤ ሙታን አለ፡፡
ሀ) ትንሳኤ ዘለክብር/ የክብር ትንሳኤ
ለ) ትንሳኤ ዘለሃሳር/የሀሳር ትንሳኤ/
ሀ) ትንሳኤ ዘለክብር፡-
 በዚህች ምድር ላይ ሳለ በተቀደሰችው ሃይማኖት ጸንተው መልካም ምግባር የሰሩ ሁሉ የክብር
ትንሳኤ ይነሳሉ፡፡

16
 በዚህች ትንሳኤ ወንድ 30 ዓመት ጎልማሳ ሴት ደግሞ 15 ዓመት ቆንጆ ሆነው ከፀሐይ
ከጨረቃ ደምቀው ይነሳሉ፡፡
 ፈጣሪያቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን መሰለው በክብር ይነሳሉ፡፡
 በመንግስተ ሰማያት እንደ ከዋክብት ደምቀው በዘለዓለማዊ ደስታ ይኖሩ ዘንድ ይነሳሉ፡፡ ማቴ
25፥34
ከትንሳኤ በኋላ የሚንኖረው ሕይወት
 እርጅና የሌለው ኑሮ ወንድ የ30 ዓመት ሴት የ15 ዓመት
 አንድ መልክ ያለን እንሆናልን የመልክ ልዮነት የለም፡፡
 እንደ መላዕክት እግዚአብሔትን በማመስገን እንኖራለን፡፡
 ከክርስቶስ ጋር ፍፁም ተዋህደን እንኖራለን፡፡
ለ) ትንሳኤ ዘለአሳር፡-
 የሀዘን ትንሳኤ የሀጢያን ትንሳኤ
 ሀጢያን አፈር ትቢያ የነበረ ስጋቸውን ከነፍሳቸው ጋር ተዋህዶ ይነሳል፡፡
 አበጋዛቸው ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡
 ተስፈቸው ጨልሞ በገሃነም እሳት ሲሰቃዩ ለዘለአለም ይኖራሉ፡፡
የትንሳኤ ሙታን ምሳሌዎች፡-
 ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን ትንሳኤ ሙታንን በተለያየ መልኩ ይመስላሉ፡፡
1) በዘር መስለውታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፥36
 ዘር ሞታ ትበሰብሳለች አገዳ አውጥታ ትበሰብሳለች፡፡ ዘርም ታፈራለች እኛም
ምግባር እምነት ከሰራን ብንሞትም ብንበሰብስም በኋላ እንነሳለን፡፡
2) በሰው መነሳትና መተኛት መስለውታል፡፡
 የሰው መተኛት =ሞቱን
 የሰው ልጅ ተኝቶ መነሳት=ትንሳኤውን……ወዘተ
የፃድቃንና የኃጢአን ምሳሌዎች፡-
 ፃድቃን በበግ ይመሰላሉ፡፡ ምክንያቱም
ሀ/ በጎች ደጋ እንጂ ቆላ አይስማማቸውም፡፡ ፃድቃን በመከራ ስጋ እንጂ በተድላ በደስታ ለመኖር
ሀይማኖታቸውን አይክዱም፡፡
ለ) በጎች እረኛቸው ባሰማራቸው ቦታ ይኖራሉ፡፡ፃድቃንም ክርስቶስ ባሰማራቸው በአንዲት ሀይማ
ኖት ፀንተው ይኖራሉ፡፡
ሐ) በጎች ጥቂት ሳር ካገኙ በፍቅር ይመገባሉ፡፡ ፃድቃንም ያገኙትን በአንድነት ይጠቀማሉ፡፡
መ) በጎች ላታቸው የወደቀ ሐፍረተ ስጋቸው የተሸፈነ ነው፡፡ ፃድቃንም ሀጢያታቸው በሰው ዘንድ
ገለጠ አይደለም፡፡

17
ሠ) በጎች አቆልቁለው እንጂ አሸቅበው አያዩም፡፡ ፃድቃንም ሁል ግዜ በትህትና ይኖራሉ፡፡
 ፃድቃን በቀኝ ይመሰላሉ፡፡ ምክንያቱም
 ቀኝ ቀና ነው፡፡ፃድቃንም ሃይማኖት ምግባር ለመስራት ቀና ናቸው፡፡
 ቀኝ ፈጣን ነው፡፡ ፃድቃንም ሃይማኖት ምግባር ለመስራት ፈጣን ናቸው፡፡
 ቀኝ ብርቱ ነው፡፡ ፃድቃንም ሃይማኖት ምግባር ለመስራት ብርቱ ነው፡፡
 ሀጢያን በፍየል ይመሰላሉ ምክንያቱም፡-
ሀ) ፍየሎች በቆላ እንጂ በደጋ አይኖሩም፡፡ ሀጢያን ለተድላ ለደስታ ሲሉ ሃይማኖ
ታቸውን ይክዳሉ፡፡
ለ) ፍየሎች እረኛቸው ባሰማራቸው አይፀኑም፡፡
ሐ) ፍየሎች የሚመገቡት ቅጠል ሞልቶ በፍቅር አይመገቡም፡፡ ሀጢያንም እንዲሁ
ሀጢያታቸው በአደባባይ የታወቀ ነው፡፡
መ) ፍየሎች ሁልግዜ አሸቅበው ይመለከታሉ፡፡ ሀጢያንም ምንም ደግ ስራ ሳይሰሩ
እዩን እዩን ማለት ያበዛሉ፡፡
 ሀጢያን በግራ ይመሰላሉ፡፡ ምክንያቱም
 ግራ ጠማማ ነው፡፡ ሀጢያንም ሃይማኖት ምግባር ለመስራት ጠማማ ናቸው፡፡
 ግራ ዳተኛ ነው፡፡ ሀጢያንም ሃይማኖት ምግባር ለመስራት ዳተኞች ናቸው፡፡
 ግራ ሰነፍ ነው፡፡ ሀጢያንም በምግባር በሃይማኖት በኩል ሰነፎች ናቸው፡፡
ወስበሐት ለእግዚአብሔር የቆየን፡፡

18

You might also like