Road Regulation Handout-A4

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 38

ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

ምዕራፍ አንድ

1. የትራፊክ ህግና ደንቦች


1.1. የትራፊክ ምንነትና ትርጉም
 ትራፊክ ማለት፡- ተንቀሳቃሽ ወይም ተላላፊ ማለት ሲሆን በአየር፣ በባህርና በየብስ ያለውን እንቅስቃሴ ሁሉ
ትራፊክ ብለን እንጠራዋለን፡፡
 የትራፊክ ደህንነት ሲባልም ለምሳሌ፡- በየብስ ላይ በትራፊክ ተሳታፊዎች፣ ማለትም አሽከርካሪዎች፣
መንገደኞች፣ በእንሰሳት፣ በተሽከርካሪዎችና በማንኛውም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በሚያስገኝ
ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ አካል ላይ ጉዳት ሳይደርስ ጤናማ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ማከናወን ማለት
ነው፡፡
 የትራፊክ ፖሊስ ማለት የትራፊክ ደንብን ለማስከበር የተመደበ የፖሊስ ሃይል ባልደረባ ነው፡፡
 መንገድ ማለት፡- ለተላላፊ ክፍት የሆነ በተለምዶ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙበት ጎዳና፣ የከተማ መንገድ፣
አውራ ጎዳና፣ የገጠር መንገድ ወይም መተላለፊያ ነው፡፡
1.2. ዓለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች
 የመንገድ ዳር ምልክቶች ስለትራንስፖርት ህግና ደንብ፣ አደገኛ ስለሆኑ ስፍራዎች፣አገልግሎት መስጫ
ተቋሟት በምን ያህል ርቀት ላይ እንደሚገኙና መንገዶች ወዴት እንደሚዘልቁ ለመንገድ ተጠቃሚዎች
በመጠቆም አሽከርካሪዎች በማንኛውም መንገድ ላይ ከመንገዱ ጋር ተግባብተው እንዲያሽከረክሩና
የትራፊኩ እንቅስቃሴ የተቀላጠፈ እንዲሆን የሚረዱ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ዓለም አቀፍ
የመንገድ ዳር ምልክቶች በሚሰጡት ትርጉም ወይም በሚያስተላልፉት መልዕክት (ትዕዛዝ) ልዩነት የተነሳ
በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የሚከፈሉ ሲሆን የሚሰሩበት ቀለምና ቅርፃቸው ምን መልዕክት እንደሚያስተላልፍ
ይጠቁማል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
1. የሚያስጠነቅቁ
2. የሚቆጣጠሩ (የሚወስኑ)
3. መረጃ ሰጪ ናቸው
1) የሚያስጠነቅቁ፡- እነኝህ የመንገድ ዳር ምልክቶች አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት መንገድ ላይ
ስለሚያጋጥማቸው አደገኛ ሁኔታ አስቀድመው እንዲያውቁና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚረዱ ምልክቶች ሲሆኑ
ቅርፃቸው አብዛኛውን ጊዜ ባለ ሶስት ማዕዘን ሲሆን ክፈፋቸው በቀይ ቀለም የተቀባ ሆኖ መደባቸው ነጭ
የሚያስተላልፉት መልዕክት አብዛኛው በጥቁር ቀለም በፅሁፍ፣ በምስል፣ በቁጥር፣ ወይም በቀስት ነው፡
በመንገድ ላይ ስለሚተላለፉ ሰዎች እንሰሶችና ተሽከርካሪዎች፣ ስለ መንገዱ ሁኔታ፣ ማለትም የመንገዱን ገፅ
ከመልከዓ ምድራዊ አቀማመጡ አንፃር ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ሜዳ፣ ጠመዝማዛ ወዘተ… በማለት ያመለክታሉ፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 1
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

የሚያስተላልፉት መልዕክት በጥቁር ሲሆን በስዕል፣ በክብደት፣ በቁጥር፣ በቀስት ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡

1. በሰዓት ከ 20 ኪ/ሜ በላይ ማሽከርከር ክልክል ነው

2. በሰዓት ከ 60 ኪ/ሜ በላይ ማሽከርከር ክልክል ነው

3. ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ በእጅ የሚገፉትም ጭምር እንዳያልፉበት የተዘጋ መንገድ


ነው፡፡

4. ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 2
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

5. ጠቅላላ ርዝመቱ በምልክቱ ላይ ከተገለፀው በላይ ማለፍ ክልክል ነው

6. የተበላሸ ተሽከርካሪ እየጎተቱ መጓዝ ክልክል ነው

7. ምልክቱ ባለበት አቅጣጫ እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው

8. ቀስቱ በሚያመለክተው አንፃር ወደ ቀኝ መታጠፍ ክልክል ነው

9. ቀስቱ በሚያመለክተው አንፃር ወደ ግራ መታጠፍ ክልክል ነው

10. ከሁለት እግር በላይ ያላቸውን አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ምልክቱ ከተተከለበት ስፍራ
ጀምሮ መጨረሻ የሚል ሌላ ምልክት እስክሚታለፍ ድረስ መቅደም ክልክል ነው

11. ከሁለት እግር በላይ ያላቸው ሞተር ተሽከርካሪዎች በዚህ በኩል ማለፍ የተከለከለ ነው

12. ሞተር ብስክሌት እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው

13. በሞተር ሃይል የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ እንዳያልፍ የተከለከለ


መንገድ ነው

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 3
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

14. ጠቅላላ ክብደቱ በቶን በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ማንኛውም ተሽከርካሪ
ማለፍ ክልክል ነው

15. ቀስቱ እንደሚያመለክተው በስተግራ ወደ ኋላ ዞሮ መመለስ ክልክል ነው

16.

17. ለማንኛውም እንሰሳትና በእንሰሳት ለሚሳቡ ተሽከርካሪዎች ማለፍ ክልክል ነው

18. በሰው ሃይል የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪዎችን በዚህ ማለፍ ክልክል ነው

19. ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ላይ እግረኞች ማለፍ ክልክል ነው

20. የአክስሉ ጭነት በምልክቱ ላይ ከተመለከተው ክብደት በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል
ነው

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 4
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

21. ጠቅላላ ስፋቱ በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው

22. ጠቅላላ ከፍታው በምልክቱ ላይ ከተመለከተው በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው

23. የከተማ ክልል ምልክት ስለሆነ የከተማ ውስጥ ህጎችን ሳያከብሩ ማሽከርከር ክልክል ነው

24. የከተማ ክልል ወሰን መጨረሻ ስለሆነ እንደ መንገዱ ደረጃና ሁኔታ ለመንገዱ በሚፈቅደው
የፍጥነት ወስን አሽከርክር

25. ማንኛውንም ዓይነት የማስጠንቀቂያና የጥሩንባ ድምፅ ማሰማት ክልክል ነው

26. ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፡-


ሀ/ መገናኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ

ለ/ በውስጡ መጨረሻ የሚል ፅሁፍ ያለበት የዚህ ዓይነት ምልክት እስክታልፍ ድረስ
ተሽከርካሪ ማቆም ክልክል ነው
27. ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፡-
ሀ/ መገናኛ / መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ

ለ/ በውስጡ መጨረሻ የሚል ፅሁፍ ያለበት የዚህ ዓይነት ምልክት እስክታልፍ ድረስ
ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ በፍፁም ማቆም ክልክል ነው

28. ማቆም የሚከለክለው ምልክት ትዕዛዝ መጨረሻ ነው

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 5
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

29. ይህ ምልክት ከተተከለበት ስፍራ ጀምሮ፡-


ሀ/ የሚቀጥለውን መገናኛ ወይም መስቀለኛ መንገድ እስክታልፍ ድረስ ወይም
ለ/ መጨረሻ የሚል ፅሁፍ የተፃፈበት የዚህ ዓይነት ሌላ ምልክት እስክታልፍ ድረስ
ተሽከርካሪን በማዘግየት ማቆም የተከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን አሽከርካሪው ከተሽከርካሪው
ሳይወጣ ሰዎችን ለማሳፈር፣ ዕቃ ለመጫንና ለማውረድ ብቻ ለጥቂት ጊዜ ይቻላል

30. ይህ ምልክት ባለበት መንገድ ላይ ከፊት ለፊት ለሚመጣ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ሳይሰጡ
ማሽከርከር ክልክል ነው

31. ቁም ! የጉምሩክ መ/ቤት / ፍተሻ ቦታ ነው


 ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ሁሉ ማንኛውም አሽከርካሪ ተሽከርካሪውን አቁሞ በጉምሩክ
ተቆጣጣሪዎች ሳያስፈትሽ ማለፍ ክልክል ነው

32. በምልክቱ ላይ ከሚታየው በአነሰ ርቀት ተጠግቶ ማሽከርከር ክልክል ነው

33. አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነት ለጫነ ተሽከርካሪ ማለፍ ክልክል ነው

34. ፊት ለፊት እያሽከረከሩ ማለፍ ክልክል ነው

35. በሰዓት ከ 80 ኪ/ሜ በላይ ማሽከርከር ክልክል ነው

36. ጠቅላላ ክብደቱ በምልክቱ ላይ ከተገለፀው በላይ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማለፍ ክልክል
ነው

37. ስልክ / ሞባይል እያነጋገሩ ማሽከርከር ክልክል ነው

2.2. ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 6
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ቅድሚያ የሚያሰጡ የመንገድ ዳር ምልክቶች የሚያስተላልፉት ትዕዛዝ እንደስያሜያቸው ቅድሚያ የሚያሰጡ


ሲሆኑ በቅርፃቸው፣ በመደባቸውና በቀለማቸው የተለያዩ ናቸው፡፡

38. ቁም ! ይህ ምልክት ባለበት ማንኛውም የሚመጣ ተሽከርካሪ መስቀለኛ መንገድ ከመግባቱ


በፊት አቁሞ ግራና ቀኝ ሳይመለከትና የመንገዱን ሁኔታ አጣርቶ ቅድሚያ ሳይሰጥ ማለፍ
የተከለከለ ነው
39. ቁም ! ይህ ምልክት ባለበት ማንኛውም የሚመጣ ተሽከርካሪ መስቀለኛ መንገድ ከመግባቱ
በፊት አቁሞ ግራና ቀኝ ሳይመለከትና የመንገዱን ሁኔታ አጣርቶ ቅድሚያ ሳይሰጥ ማለፍ
የተከለከለ ነው

40. ከፊት ለፊት ለሚመጣ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ስጥ

41. በመገናኛ መንገድ ላይ ለተላላፊ ቅድሚያ ስጥ

42. ይህ ምልክት ባለበት ቅድሚያ አለህ

43. ቅድሚያ አለህ የሚለው ምልክት መጨረሻ

44. ይህ ምልክት ባለበት ከፊት ለፊት ደሴት ላይ ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቀህ አሽከርክር

45. በጠመዝማዛ መንገድ ላይ ቅድሚያ በመስጠት ተጠንቅቀህ አሽከርክር

46. ይህ ምልክት ባለበት ቦታ ላይ ወደ ትራፊክ ክብ ደሴት አስቀድሞ ለገባ ተሽከርካሪ ቅድሚያ


ስጥ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 7
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

2.3. የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች፡- የሚያስገድዱ የመንገድ ዳር ምልክቶች የሚሰጡት ትዕዛዝ አስገዳጅ
ነው፡፡ አብዛኛው ቅርፃቸው ክብና አራት ማዕዘን፣ መደባቸው ሰማያዊ የሚያስተላልፉት መልዕክት በነጭ
ሲሆን በስዕል፣ በቀስት፣ በቁጥር ይገለፃሉ፡፡

47. ለአንድ ረድፍ ከተቀመጠው አነስተኛ ፍጥነት በላይ ማሽከርከር የሚያስገድድ

48. በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን የተቀመጠ የፍጥነት ወሰን

49. በተለያየ ረድፍ ውስጥ ተፈፃሚ እንዲሆን የተቀመጠ አነስተኛ የፍጥነት ወሰን

50. ቀስቱ በሚያመለክተው አቅጣጫ በኩል ባለው መንገድ ላይ ብቻ አሽከርክር

51. የቀስቱ ምልክት እንደሚያመለክተው በስተቀኝ በኩል ብቻ ዕለፍ

52. የቀስቱ ምልክት እንደሚያመለክተው በስተግራ በኩል ብቻ ዕለፍ

53. ቀስቱ እንደሚያመለክተው አደባባዩን ዙር

54. ቀስቱ እንደሚያመለክተው ከምልክቱ በግራና በቀኝ ብቻ ዕለፍ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 8
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

55. ይህ ምልክት ባለበት አካባቢ ለተሽከርካሪዎች ማቆሚያ የተዘጋጀ ወይም የተወሰነ ስፍራ
አለ

56. ቀስቱ በሚያመለክተው ፊት ለፊት ብቻ አሽከርክር

57. ፊት ለፊትና ወደ ግራ ብቻ አሽከርክር

58. ፊት ለፊትና ወደ ቀኝ ብቻ አሽከርክር

59. ለፈረሰኛ ብቻ የተፈቀደ መንገድ

60. ለሳይክል ብቻ የተፈቀደ መንገድ

61. አደገኛ ፍንዳታ የሚያስከትል ጭነት ለጫነ ተሽከርካሪ የተፈቀደ መንገድ

62. ለከባድ ተሽከርካሪዎች ለማሽከርከር የተፈቀደ መንገድ

63. የደሴቱን ግራ በመያዝ አሽከርክር

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 9
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

64. የደሴቱን ቀኝ በመያዝ አሽከርክር

65. አነስተኛ የፍጥነት ወሰን

66. የአነስተኛ ፍጥነት መጨረሻ

2) መረጃ ሰጪ የመንገድ ዳር ምልክቶች


 መረጃ ሰጪ ምልክቶች በሁለት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላሉ፡-
1) ራሱ መረጃ ሰጪ፡- ቅርፃቸው አራት ማዕዘን ሆኖ በአብዛኛው መደባቸው ውሃ ሰማያዊና ነጭ ነው፡፡
በአንዳንድ አገሮች አረንጓዴ የሚጠቀሙ አሉ፡፡

67. ለተበላሹ ተሽከርካሪዎች የጥገና አገልግሎት መስጫ

68. የቴሌፎን አገልግሎት መስጫ

69. የነዳጅ መቅጃ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 10
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

70. ሆቴል ወይም ሞቴል

71. የተሽከርካሪ ማቆሚያ / ፓርኪንግ

72. ምግብ ቤት ያለበት አካባቢ

73. መዝናኛ ወይም ቡና ቤት

74. ተጎታች ቤቶች ማረፊያ ድንኳኖች ያሉበት አካባቢ

75. የወጣቶች መኖሪያ / መዝናኛ

76. የእግር ጉዞ አካባቢ

77. የአውቶቡስ ማቆሚያ

78. የአይሮፕላን ማረፊያ

79. የቀይ መስቀል ዕርዳታ መስጫ

2) አቅጣጫ አመልካች፦ የመንገዶችን ዘላቂ መሆን ወይም አለመሆን የሚገልፁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ናቸው፡፡

80. አዲስ አበባ ከተማ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 11
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

81. የአዲስ አበባ ከተማ መጨረሻ

82. ጅማ ከተማ

83. የጅማ ከተማ መጨረሻ

84. ወደ ጅማና ደብረዘይት መሄጃ

85. ቦሌ አካባቢ

86. ወደተለያዩ አቅጣጫዎች የሚያስኬድ መንገድ

1.3. በመንገድ ላይ የሚቀቡና የሚሰመሩ መስመሮች


 በመንገድ ላይ የሚቀቡና የሚሰመሩ መስመሮች አገልግሎት

 የት ቦታ ላይ ወደ ሌላ አቅጣጫ ገብተን መቅደም እንደምንችል ወይም እንደማንችል ይጠቁማሉ፣


 ለመታጠፍና ዞሮ ለመመለሰ የምንጠቀምበትን ረድፍ ያመለክታሉ፣
 በትራፊክ መብራት አካባቢ የምንቆምበትን ስፍራ ያመለክታሉ፣
 የመንገድ መሃልና ጠርዝን ያመለክታሉ፣
 ለእግረኞች መተላለፊያ የተከለሉ ስፍራዎችን ያመለክታሉ፣
 አንድን መንገድ በሁለት ነጠላ መንገዶች ይከፍላሉ፣
 አንድ አቅጣጫ መንገድን በረድፍ ይከፋፍላሉ፣
 የመንገድ ዳር ምልክቶችን መትከል አስቸጋሪ በሆነበት መንገድ ላይ ምልክቶችን ተክተው ይሰራሉ፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 12
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 በመንገድ ላይ የሚሰመሩ መስመሮች በሁለት ይከፈላሉ


1) በመንገድ አግድመት የሚሰመሩ መስመሮች

 በአጭር ርቀት ውስጥ እግረኞች መንገድ ማቋረጥ እንዲችሉ የሚሰመር መስመር ነው፡፡

 አሽከርካሪዎች በዚህ መስመር ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ላሉ እግረኞች ምን ጊዜም ቅድሚያ መስጠት

አለባቸው፡፡

2) በመንገድ አቅጣጫ የሚሰመሩ መስመሮች፡- አንድን መንገድ ለሁለት የሚከፍል መስመር ሲሆን አሽከርካሪዎች

የየራሳቸውን አቅጣጫ ተከትለው እንዲያሽከረክሩ የተሰመሩ ናቸው፡፡

2.1. አንድ መንገድ በተቆራረጠ መስመር ለሁለት ሲከፈል

 ይህ መስመር የትራፊክ መጨናነቅ በማይበዛባቸው ወይም ለዕይታ አስቸጋሪ ባልሆኑ መንገዶች ላይ በመሰመር

ለአሽከርካሪዎች ግልፅ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

 መታጠፍ፣ ዞሮ መመለስና ወደ ሌላ አቅጣጫ ገብቶ መቅደም የፈለገ አሽከርካሪ እንደመንገዱና እንደትራፊኩ

ሁኔታ በጥንቃቄ የተቆራረጠውን መስመር አልፎ መሄድ ይቻላል፡፡


2.2. አንድ መንገድ ባልተቆራረጠ /ድፍን/ ለሁለት ሲከፈል
 ይህ መስመር የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው ወይም ለዕይታ አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶች ላይ በመሰመር

ለአሽከርካሪዎች ግልፅ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

 ማንኛውም አሽከርካሪ ያልተቆራረጠውን መስመር አልፎ ዞሮ መመለስ፣ መቅደምና ታጥፎ መሄድ አይችልም፡፡
ነገር ግን እንደመንገዱና እንደትራፊኩ ሁኔታ መስመሮቹን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ ላይ የግራ ረድፉን ይዞ
መቅደም ይችላል፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 13
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

2.3. አንድ መንገድ በተቆራረጠና ባልተቆራረጠ መስመር ለሁለት ሲከፈል


– በተቆራረጠው መስመር በኩል ያለው አሽከርካሪ ሁለቱንም መስመሮች አልፎ መቅደም፣ ዞሮ መመለስና ታጥፎ
መሄድ ይችላል፡፡
– ባልተቆራረጠው መስመር በኩል ያለ አሽከርካሪ መስመሮቹን አልፎ መቅደም፣ ዞሮ መመለስና መታጠፍ
አይፈቀድለትም፡፡ ነገር ግን እንደመንገዱና እንደትራፊኩ ሁኔታ መስመሮቹን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ ላይ
የግራ ረድፉን ይዞ መቅደም ይችላል፡፡

2.4. አንድ መንገድ የትራፊክ ደሴት ለሁለት ሲከፈል


ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደሴትን ረግጦ መቅደም፣ ዞሮ መመለስና መታጠፍ አይፈቀድለትም፡፡
ዞሮ መመለስና መታጠፍ የፈለገ አሽከርካሪ እንደመንገዱና እንደትራፊኩ ሁኔታ በጥንቃቄ በደሴቱ መቋረጫ
ለመታጠፍና ለመዞር በተዘጋጀው ስፍራ ላይ ወደ ቀኝ አስፍቶ ዞሮ መመለስና መታጠፍ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም

ቀድሞ በተገለፀው ሁኔታ ደሴቱን ሳይረግጥ በራሱ ነጠላ መንገድ የግራ ረድፉን ይዞ መቅደም ይችላል፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 14
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

2.5. ባለ አንድ አቅጣጫ መንገድ በተቆራረጠ ነጭ መስመር በረድፍ ሲከፋፈል


 ማንኛውም አሽከርካሪ በራሱ ረድፍ ውስጥ በማሽከርከር ፍጥነት ለመጨመር፣ ለመቀነስ ወይም ለመታጠፍ
ይችላል፡፡
 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ረድፍ መቀየር ይችላል፡፡
 ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ መታጠፍ ይችላል፡፡
 የተቆራረጠውን መስመር አልፎ ማሽከርከር ይችላል፡፡
 መንገዱ ባለ አንድ አቅጣጫ በመሆኑ ዞሮ መመለስ አይቻልም፡፡

 በመገናኛ /አደባባይ/ መንገዶች መድረሻ ላይ የሚሰመር መስመርና አቅጣጫ አመልካች ቀስት


 ማንኛውም አሽከርካሪ የተቆራረጠውን መስመር ጨርሶ ድፍን መስመር ውስጥ ከመግባቱ በፊት ወይም
ከመገናኛው መንገድ በ 5 ዐ ሜትር ርቀት በመንገድ ላይ ባለው የቀስት ምልክት መሰረት የሚሄድበትን አቅጣጫ
በመምረጥ መቅደም ይችላል፡፡
 የተቆራረጠውን መስመር ጨርሶ ድፍን መስመር ውስጥ ከገባ በኋላ ከመገናኛው መንገድ በ 3 ዐ ሜትር ክልል
ውስጥ አቅጣጫ እንዲቀይርና እንዲቀድም አይፈቀድለትም፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 15
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ሌሎች በመንገድ ላይ የሚቀቡ ቅቦች

 የመቆሚያ ስፍራ ቅብ፡- አሽከርካሪዎች በምልክቱ ውስጥ ለማቆሚያ በተዘጋጀው ስፍራ ላይ ብቻ መቆም

አለባቸው፡፡

 የማስተላለፊያ ምልክት ቅብ፡- አሽከርካሪዎች ምልክቱ በሚያሳየው አቅጣጫ ብቻ ማለፍ አለባቸው፡፡

 ቅድሚያ ስጥ የሚል ምልክት ቅብ፦ ምልክቱ / ቅቡ ቅድሚያ ለተላላፊ በመስጠት በጥንቃቄ ማሽከርከር

እንዳለብህ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

 በመታጠፊያ መንገዶች ላይ ተተክለው የሚገኙ ልዩ ልዩ አንፀባራቂ ምልክቶች

1. ወደ ግራ የሚታጠፍ አደገኛ ኩርባ መንገድ ላይ የሚተከል


የማስጠንቀቂያ ምልክት

2. ፊት ለፊት የሚቀጥል መንገድ አለመኖሩን የሚያስጠነቅቅ


የቀስቱንና የትክል ድንጋይ አንፀባራቂ ምልክት

3. ወደ ቀኝ የሚታጠፍ አደገኛ መጠምዘዣ መንገድ ላይ የሚተከል


የማስጠንቀቂያ አንፀባራቂ ምልክት

1.4. አለም ዓቀፍ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች


 የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ማለት፡- በመገናኛ ስፍራዎች ከተለያየ አቅጣጫ በመምጣት ላይ የሚገኙ
አሽከርካሪዎችና እግረኞች ስርዓትን በያዘ መንገድ በየተራ መተላለፍ እንዲችሉ በተለያዩ ቀለማት ባላቸው
መብራቶች መልዕክት የሚያስተላልፉ የትራፊክ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡
 የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራት ተግባር
1) የትራፊክ ፖሊስን ተክቶ የማስተላለፍ ተግባር ያከናውናል፣

2) የማስተላለፍ ተግባር ብቻ ያከናውናል፣

3) ከተተከለበት ውጭ አያገለግልም፣
4) በሌላ አቅጣጫ ተሽከርካሪ ቢኖርም ባይኖርም በኤሌክትሪክና በኤሌክትሮኒክስ እገዛ ኡደቱን ጠብቆ
ያስተላልፋል፣
መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 16
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች በሚሰጡት አገልግሎት በሁለት ይከፈላሉ


1. የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት
2. የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት
1) የእግረኞች ማስተላለፊያ መብራት
 እግረኞችም ሆኑ ተሽከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት መንገድ እንዳያቋርጡ እንዲሁም ተሽከርካሪዎች
በሚቆሙበት ጊዜ መንገድ ማቋረጥ እንዲችሉ የተለያየ ቀለም ባላቸው መብራቶች መልዕክት የሚያስተላልፍ
የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ሲሆን በውስጡም ከተሽከርካሪ መተላለፊያ መብራት መለየት እንዲቻል የእግረኞች
ስዕል ይኖራቸዋል፡፡
 የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራቶች በቀለማቸው ቀይና አረንጓዴ ናቸው
 የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራቶች በአበራር ቅደም ተከተላቸው ቀይ፣ አረንጓዴ ነው

1. ቀይ የእግረኛ ምስል ያለበት መብራት ሲበራ እግረኞች መንገድ እንዲያቋርጡ


አይፈቀድላቸውም

2. አረንጓዴ የእግረኛ ምስል ያለበት ሲበራ እግረኞች ለመተላለፊያ በተሰመረ


መስመር ውስጥ ብቻ እንዲያቋርጡ ይፈቀድላቸዋል

2) የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች፡- ከተለያየ አቅጣጫ ወደ መገናኛው መንገድ በመምጣት ላይ ያሉ


አሽከርካሪዎች በየተራ እንዲተላለፉ የሚያደርግ መብራት ሲሆን ከእግረኞች ማስተላለፊያ ጋር በቅንጅት
ተሽከርካሪና እግረኞች በየተራ እንዲተላለፉ በማድረግ አደጋ እንዳይፈጠርና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ
የሚረዱ የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡

 የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች በቀለማቸው ከላይ ወደ ታች፡-


 ቀይ
 ቢጫ
 አረንጓዴ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 17
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች በአበራር ቅደም ተከተላቸው፡-


 ቀይ
 ቀይና ቢጫ
 አረንጓዴ
 ቢጫ

1. ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ፡-


 በሚበራበት አቅጣጫ ያሉ ተሽከርካሪዎች ለእግረኛ መተላለፊያ
የተሰመረውን መስመር ሳያልፉ መቆም አለባቸው
 ቀይ መብራት እየበራ አልፎ መሄድ በህግ ከማስጠየቁም በተጨማሪ ለአደጋ
ያጋልጣል

2. ቀይና ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራቶች በአንድነት ሲበሩ፡-


 በቀይ መብራት ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ለመሄድ ይዘጋጃሉ
 ወደ መገናኛ መንገድ በመድረስ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ከእግረኛ መተላለፊያ
መስመር ሳያልፉ በመቆም ለመሄድ ይዘጋጃሉ

3. አረንጓዴ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ፡-


 አሽከርካሪዎች ቀድመው ወደመረጡት አቅጣጫ ማለፍ አለባቸው
 በዚህም ወቅት ዘግይተው በእግረኛ መተላለፊያ ውስጥ በማለፍ ላይ ላሉ
እግረኞች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው

4. ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ብቻውን ሲበራ፡-


 ወደ መገናኛው መንገድ በመምጣት ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ለእግረኛ
መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፉ ይቆማሉ
 ወደ መገናኛው መንገድ ቀድመው የገቡ አሽከርካሪዎች በፍጥነት መንገዱን
ለቀው መውጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 ብልጭ ድርግም የሚል ቢጫ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ፡-


 አሽከርካሪው በመንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ፍጥነቱን
በመቀነስ ለተላላፊዎች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ ማለፍ ይችላል
 ይህ መብራት በአብዛኛው የትራፊክ መጨናነቅ በማይበዛበት ወቅት ለምሳሌ፡-
በምሽት አሽከርካሪዎች ሌሎች ተላላፊዎች ሳይኖሩ ለረጅም ሰዓት
እንዳይቆሙ እንደሁኔታው በጥንቃቄ መተላለፍ እንዲችሉ ሊያገለግል ይችላል

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 18
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ብልጭ ድርግም የሚል ቀይ የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት ሲበራ፦


 ማንኛውም አሽከርካሪ በመንገዱ ላይ አደገኛ ሁኔታ እንዳለ ተገንዝቦ ለእግረኛ
መተላለፊያ የተሰመረውን መስመር ሳያልፍ በመቆም አደጋ የማያስከትል
መሆኑን ሳያረጋግጥ እንዲያልፍ አይፈቀድም፡፡ ይህ መብራት በባቡር ሃዲድ
ማቋረጫ፣ ባቡር በሚያልፍ ጊዜና በመገናኛ ስፍራዎች ላይ የአደጋ አገልግሎት
ተሽከርካሪዎች ሲንሳቀሱ ወይም ሌላ አደገኛ ሁኔታ ሲኖር የሚበራ ነው

 መብራቶች ጎን ለጎን በጥንድ ሆነው ከተዘጋጁ የሚያስተላልፉት መልዕክትም ጥንድ ይሆናል

 ቀይ መብራት በበራበት በኩል ቀስቱ እንደሚያመለክተው ወደ ግራ የሚታጠፉት


አሽከርካሪዎች ይቆማሉ
 አረንጓዴ መብራት በበራበት በኩል ቀስቱ እንደሚያመለክተው ቀጥታ ፊት ለፊትና
ወደ ቀኝ ስለተፈቀደላቸው መሄድ አለባቸው

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 19
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 አረንጓዴ በበራበት በኩል ቀስቱ እንደሚያመለክተው ወደ ግራ ለሚታጠፉ


አሽከርካሪዎች እንዲጓዙ ተፈቅዶላቸዋል
 በቀዩ መብራት በኩል ከአናቱ ፊት ለፊት ወይም ወደ ቀኝ ታጥፈው የሚጓዙ
አሽከርካሪዎች እንዲቆሙ ይገደዳሉ

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከፊት ለፊት የሚመጡትን አሽከርካሪዎች


ያስቆማል

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከኋላ የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ያስቆማል

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከፊት ለፊትና ከኋላ ወደ መስቀለኛ መንገድ


የሚመጡትን ተሽከርካሪዎች ያስቆማል

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 20
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ፊት ለፊት ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ወደ


ፊትና ወደ ቀኝ እንዲጓዙ ይፈቅዳል፡፡

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከቀኝ ወደ ግራ ቀጥታ፣ ወደ ቀኝና ወደ ግራ


ታጥፈው የሚሄዱ አሽከርካሪዎች እንዲያልፉ ይፈቅዳል

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከኋላ ቆመው የነበሩ አሽከርካሪዎች ቀጥታ


ወደ ፊትና ወደ ቀኝ ታጥፈው እንዲጓዙ ይፈቅዳል

 ይህ የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክት ከግራ ወደ ቀኝ ቀጥታ፣ ወደ ቀኝና ወደ ግራ


ታጥፈው የሚሄዱ አሽከርካሪዎች እንዲያልፉ ይፈቅዳል

1.5. የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች

1.6. የትራንስፖርት ህግና ደንቦች


 የፍጥነት ወሰን

የተፈቀደው የፍጥነት ወሰን


ከከተማ ክልል ውጭ
የተሽከርካሪው ጠ/ክብደት በከተማ ክልል
በ 2 ኛ ደረጃ በ 3 ኛ ደረጃ ውስጥ
በ 1 ኛ ደረጃ መንገድ
መንገድ መንገድ
ጠ/ክብደቱ እስከ 3,500
100 ኪ/ሜ በሰዓት 70 ኪ/ሜ በሰዓት 60 ኪ/ሜ በሰዓት 60 ኪ/ሜ በሰዓት
ኪ /ግ
ጠ/ክብደቱ ከ 3,500 ኪ/ግ
80 ኪ/ሜ በሰዓት 60 ኪ/ሜ በሰዓት 50 ኪ/ሜ በሰዓት 40 ኪ/ሜ በሰዓት
እስከ 7,500 ኪ/ግ
ጠ/ክብደቱ ከ 7,500 ኪ/ግ 30 ኪ/ሜ
70 ኪ/ሜ በሰዓት 50 ኪ/ሜ በሰዓት 40 ኪ/ሜ በሰዓት
በላይ በሰዓት

 ማቆም የሚከለከልባቸው ቦታዎች


1. ተርፎ በሚወጣ ጭነት ላይ ከፊትና ከኋላ 30 ሳ/ሜ ካሬ ቀይ ጨርቅ ማንጠልጠል አለብን፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 21
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

2. በተሽከርካሪ ላይ የሚጫን ጭነት መትረፍ የሚችለው ከፊት 1 ሜትር ሲሆን ከኋላ 2 ሜትር ነው፣

3. ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ከባድ ተሽከርካሪዎችን በከተማ አውራ ጎዳና ላይ ከ 2 ሰዓት በላይ ማቆም የተከለከለ

ነው፣

4. አንድ ተሽከርካሪ በሌላ ተሽከርካሪ ሲጎተት በመሃል ያለው ርቀት ከ 3 ሜትር መብለጥ የለበትም፣

5. አንድ አሽከርካሪ ያለ ማቋረጥ /ያለ ዕረፍት/ ከ 4 ሰዓት በላይ ማሽከርከር የለበትም፣

6. ከጎርፍ ማስተላለፊያ ፉካ በ 5 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም የተከለከለ ነው፣

7. ከባቡር ሃዲድ ማቋረጫ በ 6 ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መለዋወጥ የተከለከለ ነው፣

8. አንድ አሽከርካሪ ከፊት ካለው ተሽከርካሪ ጋር 6 ሜትር ርቀት መኖር አለበት፣

9. ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት በከተማ ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ ማቆም የሚፈቀደው ለ 6 ሰዓት ብቻ

ነው፣

10. ማንኛውም ዓለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች በተተከሉበት ቦታ በ 12 ሜትር ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ

መሄድ የተከለከለ ነው፣

11. የመንገዱ ስፋት ከ 12 ሜትር ካልበለጠ በስተቀር በቆመ ተሽከርካሪ ትይዩ አንፃር ማቆም የተከለከለ ነው፣
12. "ቁም" የሚል የመንገድ ዳር ምልክት ባለበት ስፍራ በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ማቆም የተከለከለ ነው፣
13. በሆስፒታል የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጫና ከእሳት አደጋ መከላከያ መግቢያ በሮች በ 12 ሜትር ባነሰ ርቀት
ውስጥ ተሽከርካሪ ማቆም ክልክል ነው፣
14. በመስቀለኛ መንገድ ውስጥ ወይም ከመስቀለኛ መንገድ በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ ማቆም ክልክል
ነው፣
15. በነዳጅ መቅጃ (ማደያ) መግቢያና መውጫ በ 12 ሜትር ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ክልክል ነው፡፡
16. የአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራ አካባቢ ከፊትና ከኋላ በ 15 ሜትር ባነሰ ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ ማቆም ክልክል
ነው፣
17. በባቡር ሃዲድ ማቋረጫ አካባቢ ከ 20 ሜትር ባነሰ ርቀት ውስጥ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ ነው፣
18. በመስቀለኛና በባቡር ሃዲድ ማቋረጫ መስመር በ 30 ሜትር ክልል ውስጥ መቅደምና አቅጣጫ መቀየር
የተከለከለ ነው፡፡
19. ተሽከርካሪ መንገድ ዳር በምናቆምበት ወቅት ከመንገድ ዳር ጠርዝ 40 ሳ/ሜ መሆን አለበት፣
20. የተበላሸን ተሽከርካሪ ከከተማ ክልል ውጪ በአውራ ጎዳና ላይ ከ 48 ሰዓት በላይ ማቆም የተከለከለ ነው፣
21. ተሽከርካሪ በብልሽት ምክንያት መንገድ ላይ ቢቆም ባለሶስት ማዕዘን አንፀባራቂ ምልክት ከፊትና ከኋላ በ 50
ሜትር ላይ መቀመጥ አለበት፣
22. ከፊት ለፊትህ የሚመጣን ተሽከርካሪ በ 50 ሜትር ርቀት ማየት የማይቻልበት ማንኛውም መታጠፊያ ቦታ
ላይ መቅደም የተከለከለ ነው፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 22
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

23. ረጅሙን የግንባር መብራት በከተማ ውስጥ፣ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ቦታዎችና ከፊት የሚመጣ
ተሽከርካሪ በ 50 ሜትር ክልል ውስጥ ከሆነ ማብራት ክልክል ነው፣
24. ፍሬቻ መታጠፊያ /መዞሪያ/ ቦታ ከመድረሳችን 50 ሜትር ሲቀር ማብራት አለብን
25. የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ዳር ምልክቶች ድርጊት ከሚፈፀምበት 50 ሜትር ላይ ይተከላሉ፣
26. አንድን ከፊት ያለ ተሽከርካሪ ከቀደምን በኋላ ወደ ቀኝ ረድፍ ለመግባት ከቀደምነው ተሽከርካሪ 50 ሜትር
መራቅ አለብን፣
27. የአደጋ አገልግሎት ዕርዳታ መስጫ ተሽከርካሪዎችን ከ 100 ሜትር ባነሰ ርቀት ተከታትሎ ማሽከርከር
የተከለከለ ነው፣

 በተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ መሳሪያዎች


1) የተሽከርካሪ የመገናኛ መሳሪያዎች፡- እነዚህ መሳሪያዎች አሽከርካሪው ከሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ጋር
ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጡባቸው መሳሪያዎች ናቸው፡፡
 ክላክስ / ጡሩምባ
 የማስጠንቀቂያ መብራቶች
 ፍሬቻዎች
 የኋላ መብራቶች
 የማቆሚያ መብራቶች
 የጎን መብራቶች
 የሰሌዳ መብራት
2) የተሽከርካሪ የመከላከያ መሳሪያዎች
 የፊት / የግንባር መስታወት
 የአየር ከረጢት በመኪናው
 አካል ላይ የተለጠፈ የብረት ዘንግ
 የሚተጣጠፍ / የሚሰምጥ መሪ
 ባምፐር / ፓራውልት
 0 የደህንነት ቀበቶና የራስ ድጋፍ
3) ለአነዳድ ምቾት የሚሰጡ መሳሪያዎች
ወንበር ማስተካከያ
ጭጋግ / በረዶ ማቅለጫ
አየር ማቀዝቀዥና ማሞቂያ
የፍጥነት መቆጣጠሪያ / መግቻና አየር ማስገቢያ የሚባሉት መሳሪያዎች

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 23
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

4) የፍጥነትና አቅጣጫ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፡- እነዚህ መሳሪያዎች የተሽከርካሪን ፍጥነትም ይሁን አቅጣጫ
መቆጣጠር የሚያስችሉ ናቸው፡፡ እነሱም፡- መሪ፣ የእግር ፍሬን፣ የእጅ ፍሬን፣ የነዳጅ መስጫ ፔዳል፣ ማርሽ
መለዋወጫ ዘንግ ናቸው፡፡
5) የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፡- የግንባር /የፊት መስታወትና መብራቶች፣ የጎንና የኋላ ትዕይንት
መቆጣጠሪያ መስታወቶች፣ የፀሃይ ጨረር መከላከያዎች፣ የበረዶ ወይም ጭጋግ ማቅለጫ ሙቀት ሰጪ
መሳሪያና የውስጥና የውጪ መብራቶች ናቸው፡፡
6) የስርቆሽ መከላከያ መሳሪያዎች፡- ተሽከርካሪያችንን ካቆምንበትና በቂ ጥበቃ ከሌለበት ስፍራ በሌቦች
እንዳይሰረቅ የሚከላከሉ መሳሪያዎች ናቸው እነሱም፡- የማስነሻ ቁልፍ /ደውል/፣ የመሪ ዘንግ ቁልፍና የበር
ቁልፍ ናቸው፡፡

 ሌሎች የመንገድ ትራንስፖርት ህጎች

1. ርቀትን ጠብቆ ማሽከርከር፡- አሽከርካሪዎች ወደ ፊትም ይሁን ወደ ኋላ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ርቀትን ከፊት፣


ከኋላ፣ ከቀኝና ከግራ በኩል ያሉትን ተሽከርካሪዎች ጠብቆ ማሽከርከር ይኖርባቸዋል፡፡

ፍጥነት በኪ/ሜ በተሽከርካሪዎች መሃል ሊኖር የሚገባው ርቀት


በሰዓት 4 ዐ-5 ዐ 2 ዐ ሜትር ርቀት መኖር አለበት
በሰዓት 5 ዐ-6 ዐ 25 ሜትር ርቀት መኖር አለበት
በሰዓት 7 ዐ-8 ዐ 30 ሜትር ርቀት መኖር አለበት
በሰዓት 9 ዐ-1 ዐዐ 36 ሜትር ርቀት መኖር አለበት
በሰዓት 100-110 43 ሜትር ርቀት መኖር አለበት
በሰዓት 110-120 48 ሜትር ርቀት መኖር አለበት

2. የኋላና የጎን መመልከቻ መስታወት አጠቃቀም


 አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ከቀኝ፣ ከግራና ከኋላ ያሉትን ተሽከርካሪዎች ርቀትን በመስታወት
በመመልከት መቆጣጠር ይኖርባቸዋል፡፡
 አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ከፍተኛ ጥንቃቄ ከፊታቸው ያለውንም ማገናዘብና ማስተዋል
ይመከራል፡፡
 የሚመለከቱትም በአይን ብቻ ቢሆን ይመከራል፡፡
3. የፍሬቻ አጠቃቀም፡- ለሌሎች አሽከርካሪዎች መሄድ የሚፈልግበትን አቅጣጫ በማሳወቅ /ፍሬቻ በማብራት/
አቅጣጫ ወዳሳየበት እርምጃ ለመውሰድ አስፈላጊውን ክንውን መጀመርና ማከናወን አለበት፡፡

የፍሬቻ አገልግሎት
የግራ ፍሬቻ የቀኝ ፍሬቻ
ከቆምንበት ለመነሳት ለመቆም
ለመቅደም ለማስቀደም

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 24
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

ወደ ግራ ለመታጠፍ /ዞሮ ለመመለስ/ ወደ ቀኝ ለመታጠፍ


ከቀኝ ወደ ግራ ረድፍ ለመለወጥ ከግራ ወደ ቀኝ ረድፍ ለመለወጥ

4. ረድፍ ለመያዝና ተከታትሎ ለማሽከርከር ማድረግ ያለብን፡- አሽከርካሪዎች ማሽከርከር በሚፈልጉበት አቅጣጫ
ለማሽከርከር የመንገድ መሃል መስመር ህግና ደንብን በማክበር ረድፋቸውን በመያዝ ማሽከርከር ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ተከታትሎ ለማሽከርከር፡- ማንኛውም አሽከርካሪ ከሌላ ተሽከርካሪ ተከትሎ በሚያሽከረክርበት ወቅት
በማንኛውም ጊዜ ያለአንዳች አደጋ ማቆም እንዲችል ራሱንና ከፊት የሚያሽከረክረውን ተሽከርካሪ ፍጥነት፣
የመንገዱን ግልፅነት፣ የትራፊክ እንቅስቃሴን ብዛትና ሁኔታ በማመዛዘን በሚያሽከረክረው ተሽከርካሪና ከፊቱ
ባለው ተሽከርካሪ መሃል በቂ ርቀት ጠብቆ ማሽከርከር አለበት፡፡
6. ለመቅደም፡- አሽከርካሪዎች ሌሎች ተሽከርካሪዎችን መቅደም በሚፈልጉበት ጊዜ ሊያደርጓቸው የሚገባቸው፡-
 መቅደም የሚቻለው በግራ በኩል ብቻ መሆኑን መገንዘብ፣
 የተወሰነ ርቀት ከተጓዝን በኋላ አደጋ በማያስከትል ሁኔታ ረድፍ ለመያዝ በቀኝና በመሃል ስፖኪዮ
የቀደምነውን ተሽከርካሪ ፍጥነትና ርቀትን መመልከትና የቀኝ ፍሬቻ በማሳየት የመሪ እርምጃ በመውሰድ
ረድፍ መያዝ፣
 የቀደምነው ተሽከርካሪ በኋላ መመልከቻ መስታወት ውስጥ እስኪታይ ድረስ አቅጣጫ ሳይለውጡ ቀጥታ
ማሽከርከር፣
 ሶስተኛ ተደራቢ ሆኖ መቅደም ክልክል ነው፣
 መቅደም ከመጀመራችን በፊት ከሌላ አቅጣጫ የሚመጣ ተሽከርካሪ ሳይደርስ ከቀደምን በኋላ ወደ ቀኝ ረድፍ
ለመመለስ የሚያስችል በቂ ርቀት እንዳለ መገመት ያስፈልጋል፣
7. ለማስቀደም፡- ምልክት የሰጠን ተሽከርካሪና በፍጥነት በመጓዝ እየመጣ ያለን ተሽከርካሪ በኋላ መመልከቻ ስፖኪዮ
መመልከት፡፡
 በቀኝ ጎን መመልከቻ ስፖኪዮ ሌሎች ተሽከርካሪዎች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ፣
 ፍቃደኛ መሆናችንን የሚገልፅ የቀኝ ፍሬቻ ማሳየት፣
 ወደ ቀኝ የመሪ እርምጃ መውሰድና ረድፍ መያዝ፣
 የቀደመን ተሽከርካሪ ትክክለኛ ረድፍ እስኪይዝ የተሽከርካሪ ፍጥነት መቀነስ አለብን፣
8. ከፊት ለፊት የሚመጣን ተሽከርካሪ ለመተላለፍ
 ከፊት ለፊት የሚመጣውን ተሽከርካሪ ለመተላለፍ ከቀኝ በኩል ካለው የመንገዱ ዳር ተጠግተህ በመንዳት በቂ
የመተላለፊያ ቦታ በግራ በኩል መተው ያስፈልጋል፡፡
 ተራራማና ዳገት በሆኑ ቦታዎች ላይ አሽከርካሪዎች መተላለፍ ቢያስፈልግ ቁልቁለት የሚወርደው አሽከርካሪ
ወደ ዳገት ለሚወጣው አሽከርካሪ እንደአስፈላጊነቱ ፍጥነቱን በመቀነስ ወይም በማቆም የማሳለፍ /ቅድሚያ
የመስጠት/ ግዴታ አለበት፡፡
 የህዝብ ማመላለሻ የያዘ አሽከርካሪ በሁለቱም አቅጣጫ ቢሆን ቅድሚያ አለው፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 25
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

9. አቅጣጫ አለዋወጥ፡- አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪን በሚያሽከረክሩበት ጊዜ፣ አቅጣጫ በሚለውጡበት ጊዜ፣


ለሌሎች አሽከርካሪዎች በሚገባ ማመልከትን ሊተገብሯቸው የሚገቡ ነጥቦች፡-
 አሽከርካሪዎች ከአንድ ረድፍ ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ከመምረጣቸው በፊት አጠቃላይ የትራፊክ እንቅስቃሴ
በስፖኪዮ በመጠቀም መመልከት፣
 ፍሬቻ ማሳየት፣
 ፍጥነት መቀነስ፣
 በድጋሚ ስፖኪዮ መመልከትና መንገዱ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የመሪ እርምጃ መውሰድና ረድፍ መያዝ፣
10. የተሽከርካሪን ፍጥነት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች
 መንገዱ የተሰራበትን አካባቢ /የቦታው የጂኦግራፊ አቀማመጥ/ ሁኔታ
 የመንገዱን አሰራር
 የተሽከርካሪው የጭነት ልክ /የሞተሩ ጉልበትና አስተማማኝነት
 የአካባቢው አየር ሁኔታ /አቧራማ፣ ጭጋግ፣ ጉም፣ ብርሃን፣ ጨለማ ወዘተ…
11. በዳገትና በቁልቁለት ላይ ለማሽከርከር፡- አሽከርካሪዎች በዳገት ወይም በቁልቁለት መንገዶች ላይ
በሚያሽከረክሩበት ጊዜ በተለይ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ምክንያቱም በቀላሉ ለአደጋ የመጋለጥ ዕድሉ
ከፍተኛ ስለሆነ፡፡
 ዳገት ለሚወጣው ተሽከርካሪ ቅድሚያ መሰጠት አለበት፣
 ህዝብ የጫነ ተሽከርካሪ ከየትኛውም አቅጣጫ ሲመጣ ቅድሚያ አለው፣
12. ተሽከርካሪን ለማቆም፡- በጉዞ ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ከተለያየ አቅጣጫ ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ
አይተው እርምጃ መውሰድ ያለባቸው ሲሆን እግራቸው ከነዳጅ መስጫው ፔዳል እስከ ፍሬን መያዣው ፔዳል
ለማድረስ በአማካይ ዐ.75 ሰከንድ ያህል ጊዜ ይፈጅባቸዋል፡፡

ምዕራፍ ሁለት

2. ሥነ-ባህሪ
2.1. የሥነ-ባህሪ ምንነት
 ይህ ምዕራፍ ከማሽከርከር ስነ-ባህሪ ጋር የሚገናኙ ጉዳዮችን ያብራራል፣
 እንዲሁም የአሽከርካሪ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ይተነትናል በመጨረሻም የአሽከርካሪን ሃላፊነትና ተግባር ይገልፃል፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 26
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

– ባህሪ፡- የሰው አስተሳሰብ፣ አመለካከትና ድርጊት ውጤት ነው፡፡ በቀጥታ ሊቃኝ፣ ሊመዘገብና ሊለካ የሚችል
ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሊታወቅ የሚችል ሊሆን ይችላል፡፡
 የተለያዩ የስነ-ባህሪይ ባለሙያዎች ለስነ-ባህሪይ የተለያየ ትርጓሜ ሰጥተዋል፡፡ ከነዚህ ትርጓሜዎች ውስጥ ሁለቱ
እንደሚከተለው ተገልፀዋል፡፡
 ሥነ-ባህሪ፡- የሰዎችንና የእንስሳስትን ባህሪይ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዲስፕሊን ነው፡፡
 ሥነ-ባህሪ፡- ባህሪንና የአዕምሮ አስተሳሰብ ሂደትን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዲስፕሊን ነው፡
 የስነ-ባህሪ ግቦች
 ባህሪን መግለፅ
 የተለያዩ ባህሪያትን መንስኤ ማብራራት
 ወቅታዊ የባህሪን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የወደፊቱን መተንበይ
 ባህሪን ማሻሻል ማለትም የሰው ልጅ መልካምና መጥፎ ባህሪያትን እንዲያዳብር
 መልካም ያልሆነውን ባህሪይ በተለያዩ የስነ-ባህሪይ ዘዴዎች መለወጥ ሌላኛው የስነ-ባህሪ ግብ ነው
2.2. የማሽከርከር ስነ-ባህሪ
 አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የሚያሳዩትን ባህሪ የሚያጠና የስነ-ባህሪይ ዘርፍ ነው፡፡
 የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ዓላማ፡- አላስፈላጊ የማሽከርካር ባህሪን በማስተካከል በተሽከርካሪ የሚደርስ አደጋን
መቀነስ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በአሽከርካሪዎች የሚደርስ አደጋን ለመቀነስ የተለያዩ ጥረቶች
የተደረጉ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ይህን አደጋ ለመቀነስ ከሚደረጉት ጥረቶች መካከል የአሽከርካሪዎችን መልካም ባህሪ በማዳበር ወይም
በማጠናከር ነው፡፡
ይህም የሚከናወነው በግንኙነት ክፍሎቶች ላይ የሚከተሉትን ጉዳዮች እንዲያበረታ አደርጎ በማስተማር
ነው፡፡

 የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ጠቃሚ ሃሳቦች


 ትህትና፡- ለመንገደኞች ትሁት መሆንን፣
 ርህራሄ፡- የሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎችን ስሜት መጠበቅ፣
 ቤተሰባዊ ዕይታ፡- ለተሳፋሪዎች መልካም መሆንን፣
 እንደ ዜጋ ህግና ደንብን አክባሪ መሆን፣ ለመንገድ ወይም ለእንቅስቃሴ ህግጋት ተገዢ መሆንን፣
 ከሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ጋር መንፈሳዊ ትስስር መፍጠር
 ስነ-ምግባራዊና ምክንያታዊ መሆን፣
 የፈጠራ አነዳድ ልምምዶችንና የዘመኑን የሳይንስ ግኝቶች ማዳበር፣
 የሌላን መንገድ ተጠቃሚ ስሜት መጋራት፣
 የማሽከርከር ስነ-ባህሪያዊ ጉዳዮች
1) ዝግጁነት፡- የብስለት፣ የችሎታ፣ የትምህርትና የመነሳሳት የጋራ ውጤት ነው፡፡
 የዝግጁነት መገለጫ የሆኑትና ከማሽከርከር በፊት ሊጤኑ የሚገባቸው ጉዳዮች እንደሚከተለው ይገለፃል፡-

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 27
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ለማሽከርከር ጤነኛ መሆንህን አረጋግጥ፣


 የህመም ስሜት የሚሰማህ ከሆነ አደጋን ተከላክሎ ለማሽከርከር ብቁ ላትሆን ትችላለህ፡፡ ምክንያቱም
ህመም የማስተዋል፣ የመወሰን ችሎታንና አካላዊ ቅልጥፍናን ሊቀንስ ይችላል፡፡
 መፈተሽ ያለብህን ነገር መፈተሽና መስተካከል የሚገባውንም ነገር ማስተካከል የዝግጅት መገለጫ
ነው፡፡
 የመንገድ፣ የአየርና የትራፊክ ሁኔታ በአነዳድ ወይም በማሽከርከር ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ችግር
መገመት ሌላው የዝግጁነት መገለጫ ነው፡፡
2) መነቃቃት፡- በሰዎች ውስጥ ያለ ሁኔታ ባህሪን ወደ ግብ የሚያንቀሳቅስ ሂደት ነው፡፡
 መነቃቃት ባህሪን ለመምራትና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችላል ለስራ ውጤት መነሳሳት ከፍተኛ ፍላጎት
ያለው ሰው የሚገጥሙትን ችግሮች እንደ ፈተና በመቁጠር ለውጤቱ የበለጠ ይሰራል፡፡
 ተነሳሽነት ያለው አሽከርካሪ በማንኛውም የትራፊክ ሁኔታ ውስጥ የሚወስደው ውሳኔና እርምጃ ፈጣን
መሆን እንዳለበት ይረዳል፡፡
 ተነሳሽነት ያለው አሽከርካሪ በትራፊክ ፍሰት ውስጥ ምን ምርጫ እንዳለው ለመወሰን ይረዳል፡

3) መረጃን የመሰብሰብና የመተርጎም ሂደት

ሀ/ መገንዘብ (Sensetion)

 መረጃን ከአካባቢያችን በስሜት ህዋሳቶቻችን የመቀበል፣ የመለወጥና ወደ አዕምሯችን የመላክ ሂደት ነው፡፡
 የመስማት ሂደት ተግባሩን የሚያከናውነው በስሜት ህዋሳቶቻችን አማካኝነት ማለትም በማየት፣ በመስማት፣
በማሽተት፣ በመቅመስና በመዳሰስ ነው፡፡
 አይን አካባቢን ለማወቅ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት የስሜት ህዋስ ነው፡
 በብዙ ጥናቶች እንደተረጋገጠው በአብዛኛው ከ 80% እስከ 90% አካባቢን ለማወቅና ስለአከባቢ መረጃ
ለመሰብሰብ የሚያስችለው በማየት ነው፡፡

ለ/ ትኩረት /Attention/

 ትኩረት በስሜት ህዋሳቶቻችን አማካኝነት ከሚደርሱን መረጃዎች መካከል ዋናውንና ተፈላጊውን የመምረጥ
ሂደት ነው፡፡
 በመሆኑም አሽከርካሪዎች ለማሽከርከር የሚረዳቸው መረጃ ላይ ትኩረት ማድረግን ሊያዳብሩት የሚገባ ጉዳይ
መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡

ሐ/ ማስተዋል /Perception/

 በስሜት ህዋሳቶቻችን አማካኝነት የመጣን መረጃ የመምረጥ፣ የማቀናበርና ትርጉም የመስጠት ሂደት ነው፡
 አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት አዕምሯቸው በመስራት ላይ እንዳለ ኮምፒዩተር ነው ማለት ይቻላል፡፡
2.3. የባህሪ መለዋወጥ መንስኤዎች

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 28
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

1) ከተፈጥሮ የሚወረስ /ከቤተሰብ የወረስናቸው/ ባህሪያት፡- ያለን አመለካከት፣ አስተሳሰብና ተግባራዊ እንቅስቃሴ
ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ በዘር / በውርስ ያገኘኸውን ባህሪ ማወቅ የአኗኗር ስልትህን ከሁኔታዎች ጋር
ለማለማመድና በተወሰኑት ባህሪያት ላይ ትኩረት ለመስጠትና በሌሎች ላይ ጊዜን ላለማጥፋት ይረዳል፡፡
2) የምንኖርበት አካባቢ፡- ከአካባቢያዊ ነገሮችና ሁኔታዎች ጋር በምናደርገው መስተጋብር ባህሪያችን ላይ ተፅዕኖ
የሚኖረው ሲሆን እየተቀረፀና እያደገ ይመጣል፡፡ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ድምፅ በሚበዛበት፣ በጣም ሞቃት
በሆነ አካባቢና የትራፊክ መጨናነቅ ባለበት ቦታ በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የተለመደውን ዓይነት ባህሪ
እንደሚያንፀባርቁ ይገለፃሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በሚደክመንና የህመም ስሜት በሚሰማን ወቅት የባህሪ ለውጥ ልናሳይ
እንችላለን፡፡
3) አካላዊ ሁኔታ፡- የአካላችን ሁኔታ ማለትም የሰውነት ጥናካሬና ክብደት እንዲሁም የዕድሜ ሁኔታ በባህሪ ላይ
ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡
4) ሃይለ-ስሜታዊ /ውጥረት/፡- ውስጣዊ ፍላጎትን፣ ፍቅርን፣ ጥላቻን፣ ሃዘንን፣ ብስጭትን ወዘተ… የመግለፅ ሂደትን
ያመላክታል፡፡
 ለሰዎች ወይም ለነገሮች ያሉን ስሜቶች ከሚፈለገው በላይ በሚሆንበት ወቅት ወደ ሃይለ-ስሜት ውጥረት
ውስጥ ይከተናል፡ ይህም ለባህሪ መለዋወጥ ምክንያት ይሆናል ማለት ነው፡፡
 አሽከርካሪዎች ለሃይለ-ስሜት ውጥረት መንስኤ የሆኑትን ምክንያቶች ለይቶ በማወቅ ሁኔታዎችን ከግምት
ያስገባ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያስችላቸዋል፡፡
5) ስልጠና፡- የተመረጠ አመራርና ዕቅድ ባለው መንገድ የሚከናወን ድርጊት ሲሆን የሰውን ልጅ በሚፈለገው
አኳኋን ለማስተማር ያስችላል፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ በሰለጠነበት ዘርፍ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ ያስችለዋል፡፡
 በአሽከርካሪዎች ከሚደረገው አደጋ የተወሰነው ከአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ የሚከሰት መሆኑን የዘርፉ
ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
 ስለሆነም ከአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ ችግር የሚፈጠርን አደጋ ደረጃውን በጠበቀ የአሽከርካሪዎች
ስልጠና ሊወገድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ስልጠና የባህሪ ለውጥ ማምጫ መንገድ በመሆኑ ነው፡፡
2.4. የአሽከርካሪዎች ሙያዊ ሥነ-ምግባር
 ሙያ፡- በህብረተሰቡ ውስጥ የተከበረና የተወደደ የስራ መስክ ሆኖ በተወሰነ የዕውቀት መስክ በትምህርትና
ስልጠና የሚገኝ ነው፡፡
 ስነ-ምግባር፡- መልካሙንና መጥፎውን ለመለየት የሚያስችልና መጥፎውን በመተው መልካሙን
እንድንከተል የሚያበረታ እሴት ነው፡፡
 ስነ-ምግባር ለማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር አብሮ ለመስራትና ለመኖር አስፈላጊ ነው፡፡
 የሙያ ስነ-ምግባር፡- ማለት ባለሙያው በተሰማራበት ሙያ የሚሰራውን ስራ ውጤታማ እንዲሆን
እንደተሰማራበት የሙያ ዓይነት አባላቱ በጥብቅ መከተል የሚገባቸውን መርሆዎችና ስነ-ስርዓቶች ያመላክታል፡፡
 በተለይም ማሽከርከር የአዕምሮና የአካል እንቅስቃሴን ቅንጅት የሚጠብቅ ሙያ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው
ይገባል፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 29
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ሙያዊ ስነ-ምግባራቸውን አክብረው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች የሚከተሉትን መልካም ተግባራት


ያከናውናሉ
 ከነዱ አይጠጡም ከጠጡም አይነዱም፣
 በህክምና ባለሙያ የታዘዙና በስራቸው ላይ ችግር እንደማያደርስ ካልተገለፀላቸው በስተቀር መድሃኒት
ወስደው አያሽከረክሩም፣
 ያለምንም ዕረፍት ከአራት ሰዓት በላይ አያሽከረክሩም፣
 የእንቅልፍ ስሜት በተሰማቸው ጊዜ ሙሉ እረፍት ይወስዳሉ፣
 ስለጉዟቸው ዕቅድ ያወጣሉ፣ ጊዜ ይቆጥባሉ፣ የችግር መንስኤ እንዳይሆኑ ይዘጋጃሉ፣
 የተሳፋሪው ደህንነት የአሽከርካሪው ሃላፊነት መሆኑን ይገነዘባሉ፣
 ለማሽከርከር አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ላይ መኪናቸውን አያሽከረክሩም፣
 የመኪናቸውን ጠቅላላ አካል ይጠብቃሉ፣
 የመኪናቸውን የተለያዩ ክፍሎች በአግባቡ መስራታቸውን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ያረጋግጣሉ፣
 በመታጠፊያ መንገዶች ላይ ብርቱ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፣
 ረጅም መብራት አስፈላጊ ባልሆነበት ቦታ አያበሩም ወይም አይጠቀሙም፣
 በከፍተኛ ጥንቃቄ ማሽከርከር የሚገባቸው ቦታ በጥንቃቄ ያሽከረክራሉ፣
 ለእግረኞች ቅድሚያ ይሰጣሉ፣
 በእነርሱ የሃላፊነት ጉድለት ህይወት ያለው ነገር እንዲጠፋ አይፈልጉም፣
 የማሽከርከር ሙያ ብቃታቸውን ከፍ ለማድረግ ይጥራሉ፣
 የፍጥነት ወሰን ገደብን ያከብራሉ፣
 የመንገድ ስነ-ስርዓት ምልክቶችንና ትዕዛዞችን ያከብራሉ፣
 ለትራፊክ መብራት ትዕዛዝ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣሉ፣
 የትራፊክ ፖሊስ ትዕዛዝንና የሌሎችን የትራንስፖርት ባለስልጣናት መመሪያዎች ያከብራሉ፣
 በእንቅስቃሴና በማቆም ሂደት ተገቢውን ምልክት በተገቢው ቦታና ጊዜ ይጠቀማሉ፣
 በአጠቃላይ የአሽከርካሪዎችን መልካም ስነ-ምግባራት አሟልተውና ጠብቀው የሚያሽከረክሩ
አሽከርካሪዎች በራሳቸው፣ በቤተሰባቸው፣ በህብረተሰቡና በመንግስት ሃብትና ንብረት ላይ አደጋን
ከማድረስ ይቆጠባሉ፡፡

 የአሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪያት


 የአሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪያት የምንላቸው፡-

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 30
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ሞገደኝነት
 ከሚፈለገው በላይ ራስ ወዳድነት
 ሃይለ-ስሜታዊ አለመረጋጋት
 ቸልተኝነት
 ትኩረት ለመሳብ መሞከር (ልታይ ልታይ ባይነት)
 ሃላፊነት መዘንጋት
 ሱሰኝነት ወዘተ…
 የሌ 0 ላውን መንገድ የሚዘጉና ካለ እነርሱ በስተቀር ሌላ የመንገዱ ተስተናጋጅ እንደሌለ የሚቆጥሩ፣
 ቅጣት ከሌለ በስተቀር ህግን በራሳቸው ተነሳሽነት የማያከብሩ፣
 መግጨትና መጋጨትን በቀላሉ የሚመለከቱ፣
 ማቆም በማይገባቸው ቦታ ላይ መኪናቸውን የሚያቆሙና ለአጠቃላይ እንቅስቃሴ እንቅፋት የሚሆኑ፣
 ካልጠጡ የማይነዱ፣
 ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተቀምጠው ከነዱ ጠቅላላ ህጉችን በመሻር በማን አለብኝነትና በእብጠት በመወጠር
በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር ልታይ ልታይ ባይነት የሚያጠቃቸው፣
 ጫት መቃምና ማጨስ በሚያሽከረክሩበት ወቅት የሚያዘወትሩ ናቸው፡፡
2.5. የአልኮል መጠጥና የትራፊክ አደጋ
 የትራፊክ አደጋ እንዲፈጠር ምክንያት ከሚሆኑት ነገሮች ውስጥ የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከር አንዱ
ነው፣
 የአልኮል መጠጥ የአሽከርካሪውን የማሽከርከር ሁለንተናዊ ብቃት በመቀነስ የትራፊክ አደጋ እንዲፈጠር
ምክንያት በመሆኑ ብዙዎች አካለ ጎደሎ እንዲሆኑ፣ ህይወታቸው እንዲያልፍ፣ቤተሰቦቻቸው እንዲበተኑና
ንብረት እንዲወድም ስለሚዳርጉ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች አረጋግጠዋል፣
 በአንድ ጥናት እንደተመለከተው በአሜሪካ ከአደገኛ የመንገድ የትራፊክ አደጋዎች ውስጥ 44% የሚደርሰው
የአልኮል መጠጥ ጠጥተው በሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ነው፣
 ስለዚህ "ከጠጡ አይንዱ ከነዱ አይጠጡ" የሚለውን የትራንስፖርት ደንብ ማክበር በዘርፉ ለሚደርሰው አደጋ
መቀነስ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፣
 በማሽከርከር ችሎታ ላይ የአልኮል መጠጥ ተፅዕኖ
 የአልኮል መጠጥ በማዕከላዊው ስርዓተ-ነርቭ ላይ የመደበት /Derpressant/ ተፅዕኖ ያደርሳል፡፡
 የአልኮል መጠጥ በደማችን ውስጥ በፍጥነት በመሰራጨት የአዕምሯችንን መደበኛ የሆነ ተግባር የሚቀንስ
ሲሆን ውሳኔ የመስጠት ብቃት፣ ስሜትና ባህሪይ ላይም ተፅዕኖ ያደርሳል፡፡
 ተሽከርካሪን ማሽከርከር አብዛኛውን መሰረታዊ ክፍሎች የሚጠብቅ ድርጊት ነው፡፡ ይኸውም መገንዘብን፣
ማተኮርን፣ ውሳኔ መስጠትን፣ አካላዊ ቅልጥፍናንና እነኝህን ክህሎቶች የማቀናጀት ችሎታ የሚጠይቅ
ድርጊት ነው፡፡ በመሆኑም የአልኮል መጠጥ የአሽከርካሪውን የማየት፣ የማተኮር፣ የማገናዘብ፣ ውሳኔ
የመስጠት ችሎታውንና ቅልጥፍናውን በመቀነስ የትራፊክ አደጋ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡
 የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ ባሪያት

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 31
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 በራሱ ረድፍ ውስጥ ያለመቆየት፣


 በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር፣
 በጣም ዝግ ባለ ፍጥነት ማሽከርከር፣
 ሰፋ ያለ ቦታ ወስዶ ተሽከርካሪን ማዞር
 ፍጥነት መቀነስና በማይታመን ሁኔታ ፍጥነት መጨመር፣
 ከጎንና ከፊት ለፊት ያለን ተሽከርካሪ በጣም ተጠግቶ ማሽከርከር
 በግዴለሽነትና ምልክት ሳያሳዩ መቅደም፣
 የመኪናውን የፊት መብራት በአግባቡ ሳያበሩ ማሽከርከር፣
 ለትራፊክ ምልክት ተገዥ ያለመሆንና የመሳሰሉት የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ የሚያሽከረክር ግለሰብ ባህሪያት
ናቸው፡፡
– ስለዚህ "ከጠጡ አይንዱ ከነዱ አይጠጡ" የሚለውን የትራንስፖርት ደንብ ማክበር በዘርፉ ለሚደርሰው አደጋ
መቀነስ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
 የአልኮል መጠጥ በጠጡ ወቅት ማድረግ ያለብን
 መጠጥ ሊጠጡ ካሰቡ አማራጭ የትራንስፖርት መንገዶችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
 የህዝብ ትራንስፖርት ወይም ታክሲ መጠቀም፣
 ሌላ አሽከርካሪ ማለትም አልኮል መጠጥ ያልወሰደ ተሽከርካሪውን እንዲያሽከረክርልን ማድረግ፣፣
 ሌላ አሽከርካሪ እንዲያደርስዎት ስልክ ደውለው መጥራት፣
 የአልኮል መጠጥ መጠጣት አስፈላጊ መስሎ ከታየዎት ከቤተሰብዎና ከጓደኞችዎ ጋር በመኖሪያ
ቤት መጠጣት የራስን ህይወት ከአደጋ ማዳንና መኪናዎን ተቆጣጥሮ የማሽከርከር ብቃት ከፍ
ያደርጋል፡፡
2.6. የሞገደኛና ክልፍልፍ አሽከርካሪዎች አነዳድ
 ሞገደኛ አነዳድ የምንለው በማሽከርከር ሂደት አሽከርካሪው በሌሎች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ
ለመቀነስ የሚረዳው ባህሪ በተረበሸ ስሜት ተፅዕኖ ስር በወደቀበት ሁኔታ የሚያሽከረክርበት ሂደት ነው፡
 ይህን የማሽከርከር ሂደት በሞገደኝነት የተሟላ የሚያሰኘው ሌሎች አሽከርካሪዎች ተመሳሳይ የሆነን
የአደጋ ተጋላጭነት ደረጃ በተሻለ ሁኔታ ሊያሳልፉት ይችላሉ ተብሎ ስለሚታመንና በሞገደኝነት
የተሞላው የማሽከርከር ሂደት ግን አሽከርካሪው በሌሎች ላይ የሚያደርሰውን የአደጋ መጠን
ስለሚጨምር ነው፡፡
 ሞገደኛ አነዳድ በተደጋጋሚ በመጥፎ ስሜት ውስጥ የማሽከርከር ውጤት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡
የዚህም በመጥፎ ስሜት ውስጥ የማሽከርከር ምንጭ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በቂ ያልሆነ
ስልጠና እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
 ከሞገደኛ የማሽከርከር ሂደት ጋር የተያያዙ የተለያዩ ችግሮች ወይም ግድፈቶች አሉ ከእነርሱም መካከል
በዋናነት የሚከተሉት ናቸው፡-

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 32
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 አልኮል፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ ከባድ መድሃኒት ወስዶ በእንቅልፍ፣ በድብርት ወይም በከባድ ህመም ውስጥ
ሆኖ ማሽከርከር ነው፡፡
 ተናደው፣ ተቆጥተው ወይም እነኝህን መሰል ስሜት ውስጥ ሆነው ማሽከርከር
 በፍርሃት ውስጥ ሆነው ማሽከርከር፣ በጭንቀት ውስጥ ሆነው ማሽከርከር፣
 በማሽከርከር ላይ እያሉ አትኩሮትን በሌላ ነገር መውሰድ፣
 በፍጥነት ማሽከርከር ሱስ ተይዞ ማሽከርከር፣
 የትራፊክ ህጎችን ያለማክበር፣ የተሳሰተ ግምትና ማጠቃለያ መስጠት
 የትራፊክ ህጎች ግንዛቤ አለመኖርና የራስን የአነዳድ ስህተቶች አለመቀበል፡፡
 የሞገደኛ አነዳድ ፈርጆች
1) ትዕግስት ማጣትና ትኩረት አለመስጠት
 የትራፊክ መብራትን አለማክበር (ቀይ መብራት መጣስ)
 የትራፊክ ቢጫ መብራት ሲበራ ፍጥነት ያለመቀነስ
 ያለአግባቡ ረድፍን መቀየር ወይም መሽሎክሎክ
 ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር
 ከፊት ለፊት ያለን ተሽከርካሪ በጣም ተጠግቶ ማሽከርከር
 አስፈላጊውን የትራፊክ ምልክት ለሌሎች አሽከርካሪዎች አለማሳየት
 ፍጥነት በመጨመርና በመቀነስ መወላወል
 የማቋረጫ መንገዶችን መዝጋት
2) ተፅዕኖ የማድረግ ትግል
 ተሽከርካሪን ላለማሳለፍ መንገድ መዝጋት
 በተሽከርካሪዎች መካከል ሊኖር የሚገባው ክፍተት ሌላ ተሽከርካሪ እንዳይገባ የመኪና ጥሩንባ
በተደጋጋሚ በማስጮህ፣ በምልክትና በመጮህ መሳደብና ማስፈራራት
 ለማስፈራራት ወይም ለማስገደድ ሲባል ከፊት ለፊት ያለን መኪና ከኋላ ተጠግቶ ማሽከርከር
 ለመበቀል ተሽከርካሪን በድንገት ማቋረጥ
 በበቀል ስሜት በድንገት ፍሬን መያዝ
3) ግዴልሽነትና የመንገድ ላይ ፀብ
 በአልኮል መጠጥ ተመርዞ ማሽከርከር
 መሳሪያ መደቀን ወይም መተኮስ
 በጣም ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት ማሽከርከር
 መንገድ ዳር ተሽከርካሪ በማቆም ማስፈራራት ወይም መደባደብ
 ሞገደኛ አሽከርካሪ ላለመሆን መደረግ የሚገባቸው ክንዋኔዎች
 ወደሚፈልጉብት ቦታ በሰዓቱ ለመድረስ በቂ ጊዜ መመደብ፣ (የሚያሽከረክሩት በከተማ ውስጥ ከሆነ)
 ከተቻለ የጉዞን ፕሮግራም በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓቶች ላይ አለማድረግ፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 33
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 ሊያዘገይዎት የሚችል ጉዳይ መኖሩን በቅድሚያ በስልክ መግለፅ፣


 አዝናኝና ለስላሳ ሙዚቃዎችን በተሽከርካሪው ውስጥ ድምፁን ዝቅ አድርገው በመክፈት ማድመጥና
ብስጭትዎን ማብረድ፣
 በሚያሽከረክሩበት ወቅት ዘና ማለት፣ በወንበር ላይ ተስተካክለው መቀመጥና መሪውን በአግባቡ
መያዝ፣
 በመኪናው ውስጥ ያለን ምቾት ማሻሻል፣
 ስሜትን መቆጣጠር፣ ሞገደኛ አሽከርካሪ ሲያጋጥም ከመበቀል መቆጠበ፣
 ለሌሎች ቅድሚያ መስጠት፣ ጨዋ መሆን፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትና ይቅር ባይ መሆን፣
 ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ በትዕግስትና በቂ ጥንቃቄ በማድረግ ማሽከርከር፣
 ሞገደኛ አሽከርካሪ ሲያጋጥም ማድረግ ያለብን
ረድፍዎን ላለመልቀቅ ሲሉ ፉክክር ውስጥ አለመግባት
አፀያፊ ስድቦችንና ምልክቶችን ችላ ማለት
የአይን ለአይን ግንኙነትን ማስወገድ
ሳይበሳጩ ዘና ብለው ሁኔታዎችን መከታተል
ችግሩን ሳያባብሱ በሰላም ለመጨረስ ጥረት ማድረግ
ሁኔታውን ለትራፊክ ፖሊስና ለህግ አስከባሪዎች ማሳወቅ
ዕይታዎን የሚያሽከረክሩበት መንገድ ላይ ማድረግ
 ሶስቱ የማሽከርከር ባህሪያት ዘርፎች
1) የስሜት ባህሪ፡- ፍላጎትን፣ አመለካከትን፣ እሴትን፣ መነሳሳትንና ማንኛውንም ግብ ያለመ የሰዎች
ድርጊት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ረድፍን ከመቀየር በፊት ምልክት ማሳየት በስሜታዊ የማሽከርከር ባህሪይ ገፅ ውስጥ ያለ
ነው፡፡
2) የመገንዘብ ባህሪ፡- መረዳትን፣ ማሰብን፣ ምክንያት፣ ማናቸውንም ውሳኔ መስጠትንና የሰዎችን ድርጊት
ማጤንን ያካትታል፡፡
ለምሳሌ፡- ረድፍን ከመቀየር በፊት ምልክት ማሳየት በስሜታዊ ባህሪይ ገፅ ውስጥ ብቻ የሚገለፅ
አይደለም፣ በማገናዘብ ሁኔታ ውስጥም ይገኛል፡፡ ይህም ሲባል አሽከርካሪው በተለምዷዊ ስሌት መረጃን
ያጠናክራል በሁል ግዜ የማሽከርከር ተግባር ትክክለኛ ውሳኔ ማድረግን መማር አስፈላጊ የሚሆነው
በማገናዘብ የማሽከርከር ክህሎት ነው፡፡
3) የክህሎት ባህሪ፡- በአዕምሮ አዛዥነትና በአካል እንቅስቃሴ የሚፈፀሙ ማናቸውንም የክህሎት ባህሪያት
ያከተተ ነው እነኝህ ባህሪያት የአዕምሮና የእንቅስቃሴ ቅንጅትን የሚጠይቁ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- ረድፍ ከመቀየር በፊት ምልክት ማሳየት ጥልቅ እንቅስቃሴን የሚጠይቅ ድርጊት ሲሆን
የአይናችንና የእጃችን ቅንጅት፣ የአካል ዝግጁነትን (ምናልባት ፍሬን መያዝ ካስፈለገ) ወደ ኋላ ለማየት
የአንገት እንቅስቃሴን፣ የአተነፋፈስ ለውጥ ሂደትንና የመሳሰሉትን በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ መፈፀምን
የሚጠይቅ ነው፡፡
መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 34
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 የማሽከርከር ባህሪ ስነ-ባህሪያዊ ዘርፎች

ሃላፊነት ጥንቃቄ /ደህንነት/ ብቃት


ስሜታዊ ሃላፊነት ስሜታዊ ደህንነት ስሜታዊ ብቃት (Affective Profiency)
አዕምሯዊ ሃላፊነት አዕምሯዊ ደህንነት ክህሎታዊ ብቃት
ክህሎታዊ ሃላፊነት ክህሎታዊ ደህንነት

2.7. የመልካም አሽከርካሪ ባህሪያትን የማዳበር ስልት


 መልካም ያልሆነ ስሜትን መቆጣጠር
 ጥቃቅን የማሽከርከር ስህተቶችን ልምድ ያለማድረግ
 ራስን በራስ የመለወጥ ደረጃዎች
1) አሽከርካሪው እኔ ይህ አሉታዊ ልማድ አለብኝ ብሎ መጠንቀቅ፣
2) አሽከርካሪው አሉታዊውን ልማድ ሲፈፅም በራሱ ላይ መመስከር፣
3) ይህን አሉታዊ ልማድ መቀየር ናቸው፣
 ስለዚህ አሽከርካሪው ድክመቶቹን ለይቶ በመጥቀስ ስተቶች ሲፈፅም በመገንዘብ ራስን የማሻሻል ወይም
የመለወጥ ሂደትን ማዳበር ይገባል፡፡
 ውጤታማ የመግባባት ክህሎትን ማዳበር
 መቻቻል፡- የማንወደውን ወይም የማንስማማበትን አመለካከት፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ እምነት ወዘተ…
ለመፍቀድ ዝግጁ መሆን፡፡
 ማካፈል፡- አንዳንድ ነገር በጋራ ለማከናወን ከሌሎች ጋር መሳተፍ፡ በሌላ አነጋገር ያለህን ነገር ሌላው
እንዲጠቀምበት ፈቃደኛ መሆን፡፡
 አዛኝ መሆን፡- ሌሎች ሰዎች ችግር ሲያጋጥማቸው ችግሩን እንደራስ በማየትና በመገንዘብ የሚቃለልበትን
መንገድ መፈለግ፡፡
 መደራደር፡- ስሜትን የሚጎዱና ራስን ከአደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎችን የመቋቋም ችሎታ ነው፡፡ ይህ
ማለት ሁለት ወገኖች አንዳንድ ጉዳዮችን በመተው የነበረባቸውን ያለመግባባት ሁኔታ ማስወገጃ ስልት
ነው፡፡

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 35
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

2.8. አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር


 የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች
1) የአሽከርካሪ ባህሪይ /ሁኔታ/፡- የሚባለው የአደጋው ምክንያት አሽከርካሪው መሆኑ በትራፊክ ፖሊስ
ሲረጋገጥ ነው፡፡
 የአሽከርካሪ ብቃት ማነስ
 መጠጥና አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ማሽከርከር
 የመ/ሥ/ሥ/ት አለማክበር
 የጥንቃቄ ቀበቶ አለማሰር
 ሞባይል እያናገሩ ማሽከርከር
 እያሽከረከሩ ሌላ ጉዳይ ማሰብ
 ከሚገባው ፍጥነት በላይ ወይንም በታች ማሽከርከር
 በቂ እንቅልፍ ያለመተኛት
2) የተሽከርካሪ ሁኔታ፡- ተሽከርካሪዎች በወቅቱ ጥገና ያለማግኘትና ብዙ ጊዜ ከማገልገል የተነሳ በእርጅና
የቴ/ክ አቋማቸው ሊጓደል ይችላል የቴ/ክ አቋሙ ያልተሟላ ተሽከርካሪ ሁልጊዜ ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ
የምናሽከረክረው ተሽከርካሪ በወቅቱ በጥገና ሙያተኛ ማስፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ ምሳሌ፡-
 በደንብ ያልተጠገነ ፍሬን
 የተበላሸና በደንብ የማይታዘዝ መሪ
 ጥርሳቸው የተበላና የተነፈሱ ጐማዎች
 የማይሰሩ የዝናብ መጥረጊያዎች
 በተፈለገ አቅጣጫ የማይስተካከሉ የጐንና የኋላ መመልከቻ መስታወቶች
 የውጭውን ሁኔታ በሚገባ የማያሳዩ ወይንም የወላለቁ መስታወቶች
 በንቅናቄ የሚከፈቱ በሮች
 በደንብ ያልተጠገነ የተሽከርካሪ መቀመጫ

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 36
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 የማይሰሩ ጠቋሚ አመልካች መብራቶች


 ያረጀና ልዩ ልዩ ብልሽቶች ያሉበት ሞተር
 የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
 የመገናኛ መሳሪያዎች ብልሽት
 የዳሽ ቦርድ ላይ ጠቋሚ መሳሪያዎች ብልሽት
 የትዕይንት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ብልሽት
 የተሽከርካሪ ቴክኒክ አቋም
3) የአካባቢ ባህሪይ፡- የሚባለው በድልድይ መሰበር፤ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በአደገኛ ናዳ ወይም
በሚንሸራተት መንገድ፣ በተፈጥሮ ጉዳዮች ለአደጋ መጋለጥ ናቸው፡፡
2.9. በአነዳድ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ የአካባቢ ባህሪያት
1) በምሽት ጊዜ ማሽከርከር፡- የምሽት አነዳድ ከቀን አነዳድ ሶስት ጊዜ የበለጠ አደገኛ መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል፡፡
ምክንያቱም የዕይታ ውስንነት ስላለ ለሚያጋጥም አደጋ ሁኔታ ተረድቶ ቶሎ ምላሽ ለመስጠት አሽከርካሪው
ይዘገያል፡፡ በምሽት አነዳድ ወቅት የመንገዱ ሁኔታ ራሱ በአነዳድ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡
2) በዝናባማና ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ስለማሽከርከር
 በጭጋግማ የአየር ሁኔታ ተሽከርካሪን ያለማሽከርከር ይመረጣል፡፡ ማሽከርከር ካለብን ግን፡-
ሀ/ አጭሩን የግንባር መብራት መጠቀም
ለ/ የጭጋግ መብራት /ፎግ ላይት/ መጠቀም
ሐ/ ወደ ጭጋግ ቦታ ፍጥነት ቀንሶ መግባት
መ/ ሁሉንም የጐን መብራቶች ማብራት
ሠ/ አደጋ ቢደርስ ተሽከርካሪ ለማቆም ዝግጁ መሆን
ረ/ የውጭ መስታወት በጉም ከተሸፈነ የዝናብ መጥረጊያ መጠቀም
ሰ/ የውስጠኛው የመስታወት አካል በጉም ከተሸፈነ የውስጥ ማሞቂያ መጠቀም ካልሆነ ፎጣ ተጠቅሞ
ማፅዳት
3) በፀሃያማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ማሽከርከር
 በየሁለት ሰዓቱ ጉዞ /ከ 150 ኪ.ሜ/ በኋላ የጐማ ሙቀት መጨመሩን ማየትና አቁሞ ማቀዝቀዝ፣
 የዘይትና የውሃ ሙቀት መቆጣጠር፣
 ራዲያተር ክዳን ለመክፈት መጠንቀቅ፣
 ሙቀት ያለበትን አካባቢ በዝቅተኛ ሙቀት ጊዜ ለማለፍ መሞከር፣
4) በተራራ ላይ ስናሽከረክር፡- የመሬት ስበት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ወደ ላይ ስንወጣ ስበቱ ፍጥነታችንን
ይቀንሰዋል፡፡ ወደ ታች ስንወርድ የመሬት ስበት ፍጥነታችንን ይጨምረዋል፡፡
5) በአቧራማ መንገድ ላይ ስለማሽከርከር
 አቧራ ዕይታን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ በምሽት ሰዓት የሚደረገውን ጥንቃቄ ለአቧራማ
መንገዶችም ተጠቀም፣
 ተሽከርካሪን በቅርብ ርቀት ተከትለህ አታሽከርከር፣
 አቧራ ወደ ተሽከርካሪ እንዳይገባ በርና መስኮቶች መዘጋታቸውን አረጋግጥ፣

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 37
ወታ/አሽ/ሥ/ዲ/መንት

 አመቺ ሁኔታ ካልተፈጠረና ፍቃደኝነት እስካላገኘህ ጊዜ ድረስ አትቅደም፣


 የተሽከርካሪህ ጐማ መሬት ላይቆነጥጥ ስለሚችል በዝግታና በጥንቃቄ አሽከርክር፣
2.10. በተሽከርካሪ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ የተፈጥሮ ህጐች
1. የመሬት ስበት (Gravity)
2. የኢነርሺያ ህግ (Inertia) 0.0
3. ፖቴንሻል ሃይል (Potential Energy)
4. ካይኔቲክ ሃይል (Kinetic Energy)
5. ሞመንተም (Momentum
6. ሰበቃ (Friction)
7. የሴንትሪፔታል ሃይል (Centripetal Force)
8. የሴንትሪፊዩጋል ሃይል (Centrifugal Force)

ምንግዜም ቢሆን ራሳችንና ሌሎችን ከትራፊክ


አደጋ እንጠብቅ!!!

መንገድ ሥነ-ሥርዓት ገፅ 38

You might also like