Article 1

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 4

ወታደሮች ፣ አሸባሪዎችና ወንጀለኞች ከሚገድሉት ሰው በላይ ራሱን የሚገድለው ይበዛል!

በዲያቆን ኤርምያስ ክንዴ

ጥር 3/2015

- ከላይ በርእስነት ያስቀመጥሁት ዐሳብ ከ Yuval noah hararri መጽሐፍ የተገኘ ነው። ሙሉ ገጸ ንባቡ እንዲህ
ይላል። "For the first time in history, more people die today from eating too much than
from eating too little;more people die from old age than from infectious diseases; and
more people commit suicide than are killed by soldiers, terrorists and criminals combined.
In the early twenty-first century, the average human is far more likely to die from
bingeing at McDonald’s than from drought, Ebola or an al-Qaeda attack." [Homo deus,
A brief history of tomorrow, Yuval noah hararri] ከዚህ ገጸ ንባብ ውስጥ በርእስነት የመረጥሁት ጉዳይ
ይህ መጣጥፍ ስለምን ሊያወራ እንደሚችል ጥቁምታ ሳይሰጥ አይቀርም። ከሰሞኑ ብዙ ራስ የማጥፋት ዜናዎች
በርከት ብለው ሲሰሙ ሰንብተዋል። ድርጊቱ ከሚፈጸምበት ዘግናኝ አኳኋን ባሻገር መንስኤውና ምንጩ የማኅበረሰብ
ውይይት (Social discourse) አካል የመሆን እድሉ በጣም አናሳ ይመስለኛል። ዩቫል ኖኅ ኀራሪ በተናገረው መጠን
(ተገድሎ ከሚሞተው በላይ አብዛኛው ራሱን አጥፍቶ የመሞቱ ነገር) ሃገራችን ችግር ውስጥ የገባች አይመስለኝም።
ግን አለም እየተከተለችው ያለችው መስመር ከዚህ ውጭ መዳረሻ ያለው አይመስልም። በሃገራችን በዜና አውታሮች
ከሚነገሩት ጀምሮ የሚዲያ ሽፋን ሳይሰጣቸው በየሰፈሮቻችን እስከምንሰማቸው የራስን መግደል ዜናዎች በምዕራቡ
ዓለም እየነፈሰ ያለው የትርጉም አልባነት ንፋስ በእኛም ዘንድ እየነፈሰ ስለመሆኑ ይነግረናል።

- መቼም ሰው በአንድ ጀምበር ራሱን ለመግደል ሊቆርጥ አይችልም። መነሻው የተለያየ ሊሆን ቢችልም መዳረሻውን
ትርጉም አልባነት (Meaninglessness) ያደረገ ቀቢጸ ተስፋ ለብዙ ጊዜያት በብርቱ ሲፈትነው ከሰነበተ በኋላ
ከዚህ ፈተናና ስቃይ "ለመገላገል" ሲል የሚወስደው የመጨረሻ እርምጃ ነው። ስለዚህ ማተኮር ያለብን ወደዚህ
ውሳኔ ወዳደረሰው ትርጉም አልባነት ላይ እንጂ ድርጊቱ ላይ ብቻ መሆን ያለበት አይመስለኝም።

- የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ሲኖር መሠረታዊ ፍላጎት ከሚባሉት ከምግብ ፣ ከልብስና ከመጠለያ ይልቅ ጥልቅ የሆነ
የሕይወት ትርጉም (Profound sense of meaning) የሚያስፈልገው መሆኑ ተደጋግሞ አይነገርም። ነገር ግን
የሰው ልጅ አንዳች የሚኖርለት ጥልቅ የሆነ የሕይወት ትርጉም የግድ ያስፈልገዋል። ሁልጊዜ ይሕንን ትርጉም
ለማግኘት መቃተቱም አይቀርም። መሠረታዊው ነገር ይህ ትርጉም እንዴት ይገኛል የሚለው ነጥብ ነው። በአለም
ዙርያም ሆነ በሃገራችን ዘንድ ባሉ ወጣቶች ዘንድ ቀላል የማይባል ተሰሚነት ያለው ካናዳዊው ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
ጆርዳን ፒተርሰን ትርጉምን ከኃላፊነት ጋር ያቆራኘዋል። ይህ ዐሳብ በከፊል ትክክለኛነትን ያዘለ ሊሆን ይችላል። ነገር
ግን ኃላፊነት በምልዓት ትርጉምን ይሰጣል ብሎ መደምደም አሳሳች ድምዳሜ ይመስለኛል። አንድ ሰው ጥሩ ሞያ
ስላለው ፣ ቤተሰብ ስለመሠረተ ፣ ሃገራዊ ኃላፊነት ስለተወጣ....ወ.ዘ.ተ ትርጉምን በምልዓት ያገኛል ብሎ ማሰብ
እጅግ አዳጋች ነው። የሊዮ ቶልስቶይን ኑዛዜ (Confessions) ያነበበ ሰው ይህንን በጥልቀት የሚያሰላስለው
ይመስለኛል። (ላላነበባችሁት አጥብቄ Recommend አደርጋለሁ።) ቶልስቶይ ገና በሃያዎቹ መጀመርያ በሩሲያ
ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ገናና ሰው መሆን የበቃ ኃያል ጸሐፊ ነበር። የጻፋቸው መጻሕፍት እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ነበሩ ፣
ዝናው ታላቅ ነበር ፣ ቤተሰብ መሥርቶ ልጆች የሚያሳድግ አባ ወራም ነበር። ነገር ግን ቶልስቶይ በሃምሳ አመቱ ራሱን
የማጥፋት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ከላይ የዘረዘርኋቸው ነገሮች ሁሉ በዚህ ዓለም ላይ ለመኖር በቂ ምክንያት ሆነው
እንዳላገኛቸው በመጽሐፉ ይተርካል። በሃገራችንም ራሳቸውን ስለማጥፋታቸው ከሚነገርላቸው ሰዎች መካከል
የቤተሰብ መሪ ፣ የድርጅት መሪ ፣ መምህራን...ወ.ዘ.ተ ይገኙበታል። የዚህ Implication ኃላፊነት ብቻውን የመኖር
ትርጉምን እንደማይሰጥ የሚናገር ነው። በተለይ ሰዎች ሊጋፈጡት የሚቸግራቸው ከባድ ፈተና በመጣባቸው ጊዜ
ከዚህ ፈተና ለመውጣት ኃላፊነታቸው የሚጠቅማቸው መሆኑ ያጠራጥራል።

- ስለዚህ የሰው ልጅ ከዚህም የጠለቀ የትርጉም መሻት ውስጥ ይገባል። ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ ከሆኑ የተፈጥሮ
አደጋዎች ጀምሮ እለት እለት እስከሚያጋጥሙት ፈተናዎች ድረስ ሕልውናው ይፈተናል። ስለዚህም በዚህ ጥልቅ
የትርጉም መሻት ውስጥ ይቃትታል። በዚህ የተነሳ ነው ሰው ያለ እግዚአብሔር መኖር አይችልም የሚባለው። እርሱ
እግዚአብሔር ብሎ የሰየመው አካል ይለያይ ይሆናል እንጂ አንድ ሰው ያለ አምላክ መኖር አይችልም። ምሥራቃዊው
ቄስ ቶማስ ሆፕኮ አንድ ሰው መጥቶ በእግዚአብሔር መኖር አላምንም ቢልዎት ምን ይመልሱለታል ሲባሉ
"ስለማታምንበት እግዚአብሔር ንገረኝ እኔም ላላምንበት እችላለሁና" የሚል ግሩም መልስ ሰጥተዋል። ሌላም ከዚህ
ጋር የተያያዘ ገጸ ንባብ "Man can not live with out religion every man has the highest purpose
of life. The difference between believers and unbelievers is not about whether God exists
or not. But it's about what they believe to be God" [A Voice for our time, Alexander
schememann radio talks] ግሪካዊው ሊቅ ክሪስቶስ ያናራስም "Man sees his existence threatened
by powers or factors that he cannot control. His own natural powers do not suffice to
avert illness, pain, and death. He therefore resorts to imaginary powers that can offer
hope o f protection, a reassurance that comes from autosuggestion" ይሕ Reassured የመሆን
ፍላጎቱም ወደተሳሳተ ትርጉም ሊመራው ይችላል።" [Against religion, page 1]
- በክርስትና ውስጥ ግን እውነተኛ የሕይወት ትርጉም የሚገኘው ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ዝምድና መሠረት ነው።
ሰው እግዚአብሔርን ከሕይወቱ ማስወገድ አይችልም። በሌላ ነገር ሊተካው ግን ይቻለዋል። ይህንን የተካውንም ነገር
አምላክ አድርጎ እንደተቀበለው አያስተውልም። ከእግዚአብሔር የተለየ ስለሆነ ለሕይወቱ የተሳሳተ ትርጉም ይሰጣል
፣ በዚያም መሠረት ዓለምንም ሆነ ሕልውናን ይበይናል። ይህንን የሚያጠናክር አንድ ገጸ ንባብ እንጥቀስ "It's not
coincidence that such dissimilar idiologists of consistent materialism and determinism as
marx and freud agree on one thing, they conduct all these searches not from above but
from below, and they refute all attempts to present these absolute values as an
autonomous reality independent of any higher entity. With Freud this is expressed and
reduced not only love but also all types of human creativity, religion everything else in
the world into sexual energy : and with marx in reducing all the diversity of life in to
economic relations" [A Voice for our time, Volume 1, page 78, Alexander Schmemann]
ማርክሲዝም ዓለምን በመደብ መነጽርነት ሲመለከት ፍሮይድ ደግሞ ሁሉንም ነገር "ለሩካቤ" ያስገዛል። የማርክስ
የሕይወት ትርጉም መደብ ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሲሆን ለፍሮይድ ደግሞ የሁሉም ነገር ትርጉም
ውል "ሩካቤ" ነው።

እንዳረዘምሁት ቢገባኝም እንደ መጠቅለያ ሽራፊ ታሪክ በመጣጥፌ ላይ ላክልበት

- ዶክተር ዴቪድ ቤንትሌ ኸርት የተባለው የምሥራቅ ኦርቶዶክስ እውቅ ጸሐፊ በአንድ መድረክ ላይ የተናገረውን
አስገራሚ ታሪክ ለአሰላስሎት ይረዳን ዘንድ ላስፍረው። "ቨርጂኒያ በማስተምርበት ጊዜ አንድ ብሩሕ አእምሮ ያለው
Undergraduate ተማሪ ነበር። ይሕ ተማሪ የሚኖረው እዚያው ዩንቨርቲው ውስጥ በተሰራ የአንድ እውቅ ሰው
መታሰቢያ ሕንጻ ላይ ነበር። ይህ ልጅ ድንገት ራሱን አንቆ የመግደሉ ወሬ ተሰማ። ለምን እንደሆነ ለማወቅ የቻለ
አልነበረም። ከዚያ ጓደኛዬ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ አስደንጋጭ ነገር አወቀ። ይህ ልጅ ራሱን የማጥፋት አዝማሚያ
እንደነበረው ባልንጀሮቹ ያውቁ ነበር። ሊታደጉት ግን ምንም ጥረት አላደረጉም። ለምን እንደሆነ ሲጠየቁ ራሱን
የማጥፋት "መብቱን" እና "ነጻነቱን"መጋፋት ስላልፈጉ እንደሆነ ተናገሩ።" አሁን እየተገነባ ያለው ድኅረ ዘመናዊነት
መር ስልጣኔ ከቁሳቁስ ወገን ሁሉንም አሟልቶ ዋናውን የመኖር Faculty ትርጉምንና እሴትን ፈጽሞ የሚያጠፋ ነው
ብዬ ልደምድም።
አምላካችን እግዚአብሔር በትርጉም አልባነት ውስጥ የሚሰቃዩ ወገኖቻችንን ሁሉ ወደ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን
ያመጣልን ዘንድ እንለምናለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

You might also like