Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 15

አብክመ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን

ባህር ዳር

ሚያዝያ 2016 ዓ.ም

0
ማውጫ

1. የፊት ገጽ (Cover Page)

2. ማውጫ (Table of Content)

3. አጭር መግለጫ (Executive Summary)

4. መግቢያ (Back Ground)

5. የፕሮጀክት ሪፖርት ዋና ክፍል

6. የወልድያ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

7. ጭልጋ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

8. ገንደውሃ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

9. የፕሮጀክቶች ዋና ዋና አፈጻጸምና ተግዳሮቶች


10. የወደፊት አቅጣጫዎች

1
አጭር መግለጫ
የአብክመ ማረ/ቤቶች ኮሚሽን በስሩ በሚያስተዳድራቸው 31 ማረ/ቤቶች ውስጥ ከ 16,000 በላይ የህግ
ታራሚዎችን የተለያዩ አገልግሎቶችን እያገኙ የርምት ጊዜያቸውን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡
በነዚህ 31 ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የአገልግሎት መስጫ መሰረተ-ልማቶች በእጅጉ ያረጁ እና
ቀድሞውኑ ለማረሚያ ቤት ተብለው የግንባታ ዲዛይኖችና እስታንዳርድ ስፔሲፊኬሽኖች ከግምት ውስጥ
በማስገባት የተዘጋጅ ባለመሆናቸው ባዋጅ የተሰጠውን ስልጣን እና ሃላፊነት ለመወጣት የተቸገረ መሆኑን
የክልላችን መንግስት በመረዳትና ለማረሚያ ቤቶች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ማረሚያ ቤቶች እንደ አዲስ
የመገንባት እና የማሻሻል ስራዎችን በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ኮሚሽኑ ለሶስት ነባር ካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት ተመድቦለት ወደስራ የገባና በተለየይም አብዛኛው
የፊዚካል ስራቸው በመከናወን ላይ የነበሩትንና በሆላም በጸጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጡትን የወልድያና
አይከል ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡
ግንባታው ያልተጀመረው የግንደ ውሃ ማረሚያ ፕሮጀክትም የካሳ ክፍያ ተጠቃሎ ያልተከፈለ በመሆኑ የግንባታ
ስራው አልተጀመረም በጥቅሉ ሪፖርቱ ከላይ የተገለጹ ጉዳዮችን በዝርዝር ይዳስሳል፡፡

መግቢያ

ማረሚያ ቤቶች በአዲስ እንዲሰሩ ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች ሶስት ሲሆኑ የመጀመርያው እና ዋናው በርካታ
ማረሚያ ቤቶች ለረጅም አመታት ያለበቂ እድሳት አገልግሎት እየሰጡ የቆዩ ከመሆናቸው በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ
የታራሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ማረሚያ ቤቶች ከአቅም በላይ የተጨናነቁ በመሆናቸውና
አሁን ካሉበት ነባራዊ ሀኔታ አንጻር ሲታዩ በርጅና ብዛት አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ደረጃ የደረሱ በመሆኑ ፣
ሁለተኛ ማረሚያ ቤት የሌላቸው አዲስ የተዋቀሩ ዞኖች እንዲከፈትላቸው ጠንካራ ጥያቄ በዞኑ አስተዳደርና

2
በህብረተሰብ ዘንድ እየቀረበ መሆኑ ሲሆን ሶስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ አሁን አሁን ማረሚያ ቤቶች የሚገኙበት ቦታ
ለተለያዩ የልማት ስራዎች የተፈለጉ ከመሆናቸው በላይ የነባር ማረሚያ ቤቶች ይዞታ በከተሞች መሀል መገኘት ከፍሳሽ
አወጋገድ ጋር ተያይዞ የመልካም አስተዳደር ጥይቄዎች እያስነሱ የሚገኝ ሲሆን፤ እንደ ሀይቅ ማረሚያ ቤት ያሉ ተቋማት
ደግሞ በተፈጥሮ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ በመሆናቸው እነዚህ ችግሮች እየተባባሱ የሄዱ በመሆኑ
ነው፡፡
በመሆኑም በበጀት አመቱ እቅዳችን የወልድያና ጭልጋ ፕሮጀክቶች 100 ፐርሰንት ለማጠናቀቅ አቅደን ወደስራ የገባን
ቢሆንም በክልላችን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት እና ውል የገቡ ስራ ተቆራጮች በውሉ መሰረት ለመቀጠል
ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የግንባታ ስራዎቹን ማጠናቀቅና ያልተቻለ ሲሆን ሌላው በጀት ተመድቦለት የነበረው የግንደ ውሃ
ማረሚያ ቤት ፕሮጀክትም በመሬት ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ የተጠናቀቀ እና ዞኑ ከሶስተኛ ወገን ነጻ አድርጎ ያስረከበን
ባመሆኑ የግንባታ ስራውን ማስጀመር አልተቻለም፡፡

የፕሮጀክት ሪፖርት ዋና ክፍል

በዚህ ክፍል በጀት ተመድቦላቸው እንዲገነቡ ፍቃድ ያገኙ ሶስት(3) ማረሚያ ቤቶች የግንባታ አፈጻጸምን የምንዳስስ
ሲሆን በተለይም ግንባታቸው በጥሩ አፈጻጸም ላይ የነበሩትን እና በሆላም በጸጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጡትን
የወልድያ እና ጭልጋ ማረ/ቤቶች ፕሮጀክት በስፋት የምንዳስስ ሲሆን እንዲሁም በሶስተኛ ወገን አለመጽዳት ምክንያት
የግንባታ ስራው ያልተጀመረውን የግንደውሃ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት እስኪቋረጡ ድረስ የተከናወኑ አፈጻጸሞች
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1.የወልድያ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

 ግንባታው የተጀመረበት ጊዜ ሀምሌ 2010 ዓ.ም. ሲሆን ግንባታውን ለማጠናቀቅም

158,818,052.20 ብር ተመድቦ የነበረ ቢሆንም በዲዛይን ለውጥ ምክንያት በተፈጠረ

ተጨማሪ ስራ 18,391,340.73 ብር ተጨማሪ በውሉ ተፈጽሞል፡፡በዚህም መሰረት ግንታው

3
በ 720 ቀናት ሊጠናቀቅ የነበረ ቢሆንም በታወቁ ምክንያቶች የግንባታ ማጠናቀቂያ ግዜው
ሚያዝያ 17 2014 ዓ.ም ድረስ ተራዝሞል ፡፡
 የግንባታው አፈጻጸም

የዋናው ውል አፈጻጸም

የግንባታውን ፊዚካል ስራ አፈጻጻም ስንመለከት በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 63.30 በመቶ


የሚሆነው የፊዚካል ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን ይሄውም አጠቃላይ የግንባታ ስራው ከተያዘለት
በጀት አንጻር በፋይናንሻል አፈጻጸሙ ሲታይ 50.53 (69,783,181.00) በመቶ የሚሆነው ስራ
ተከናውኗል ማለት ነው፡፡

የተጨማሪ ውል (variation) ግንባታ አፈጻጸም

የደጋፊ ግንብ (retanining wall) በውል ጊዜው መሰረት በመከናዎን ላይ የሚገኝ ሲሆን
እስካሁን 71.00 በመቶ የሚሆነው የፊዚካል ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ይህውም በፋይናንሻል
አፈጻጸም ሲገለጽ 62.17 (9,941,750.00) በመቶ የሚሆነው ስራ ተከናውኖል ማለት ነው፡፡

 ጠቅላላ የፕሮጀክቱ በጀት.


o በመጀመሪያው ውል መሰረት የፕሮጀክቱ በጀት፦158,818,052.20
o በመጀመሪያው ውል መሰረት የአማካሪ ጠቅላላ በጀት 1,664,556.00

o በተሻሻለ ውል መሰረት የአማካሪ በጀት…2,269,167.62

ጠቅላላ የተስተካከለ የፕሮጀክቱ በጀት 179,478,560.00

 ግንባታው እስኪቆረጥ ድረስ በስራ ላይ የዋለ በጀት

o የግንባታ/ኢንቨስትምንት/ በጀት …89,857,554.23


o የአማካሪ በጀት……2,269,167.62
o ጠቅላላ እስከ 2015 በጀት ዓመት ስራ ላይ የዋለ…92,161,400.00

 ለ 2016 በጀት ዓመት ለፕሮጀክቱ ተመድቦ የነበረ በጀት …17,720,939


o ለግንበታ /ኢንቨስምንት …16,888,761
o ለአማካሪና ቁጥጥር …832,178.00
o ድምር…17,720,939.

 በ 2015 በጀት ዓመት ስራ ላይ የዋለ

4
o .ለግንበታ /ኢንቨስምንት …የለም
o ለአማካሪና ቁጥጥር … 34‚678.23
ድምር…………… 34‚678.23
 በ 2016 በጀት ዓመት እስካሁን ስራ ላይ የዋለ
o .ለግንበታ /ኢንቨስምንት …የለም
o ለአማካሪና ቁጥጥር … የለም
ድምር…………… የለም

ቀሪ በጀት 140,636,460.31 (መንግስት ያደረገውን ያዋጋ ማስተካከያ የሚያካትት)

ማሳሰቢያ

በወልድያና አካባቢው በነበረው የጸጥታ ችግር የግንባታ ስራው ከተቋረጠ አንድ አመት ከ 7 ወራትን አስቆጥሮል፡፡

5
የበጀት ዕቅድ አፈጻጸም
የበጀት አፈጻፀም (በ የ 2016 በጀት ዓመት የበጀት አጠቃቀም አፈጻጻም የዘጠኝ
%) ለ 2016 በጀት ዓመት ወር
ለፕሮጀክቱ የተያዘ ለ 2016 በጀት
ተ የፕሮጀክቱ ስም የበጀት ከ 2016 የ 9 ወር በጀት
ጠቅላላ በጀት ዓመት የተያዘ ከጠቅ የተመደበ የ 1 ኛው የ 2 ኛው
. ምንጭ በጀት የተጠየቀ በጀት የ 3 ኛው አፈጻጻም
በብር በጀት በብር ላላ (የተፈቀደ) በጀት ሩብ ሩብ
ቁ ዓመት በብር ሩብ
በጀት በብር ዓመት ዓመት
በጀት ዓመት
ብር ሣ ብር ሣ ብር ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብ ሣ ብር ሣ ብር ብር ሣ

1 ወልድያ መንግስት 177,209,392. 9 17,720,939 50.53 0 140,636, 31 17,720,939 - 0 0 0 0 0
ማረ/ቤት 3 460.

የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም


የፊዚካል ስራዎች የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወር የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በፐርሰንት
ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ አፈጻጸም (በ%) (በ %)
ተ የፕሮጀክቱ ስም የሚገኝበት ቦታ የተጀመረበ የሚጠናቀቅበት ከጠቅላላ ከ 2016 የ 1 ኛው የ 2 ኛው የ 3 ኛው ሩብ
. ት ዘመን ዘመን (ዓ.ም) ግንባታ በጀት ሩብ ሩብ ዓመት ዕቅድ የ 9 ወር እቅድ
ቁ ዞን ወረዳ ቀበሌ (ዓ.ም) ዕቅድ ዓመት ዓመት ዓመት አፈጻጸም በ% አፈጻጸም በ%
ዕቅድ ዕቅድ ዕቅድ
አፈጻጸ አፈጻጸም
ም በ% በ%
1 ወልድያ ማረ/ቤት ሰ/ ወልድያ ጎንደር ሀምሌ ሚያዝያ 2014 63.30 0 0 0 0 0
ወሎ በር 2010 ዓ.ም ዓ.ም
2 ወልድያ ማረ/ቤት ሰ/ ወልድያ ጎንደር ሀምሌ 2014 71.00 0 0 0 0 0
ተጨማሪ ውል ወሎ በር ዓ.ም

6
1. ጭልጋ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

 የተቋራጩ ስም……አያሌው አዲሱ ህ/ስራ ተቋራጭ


 የአማካሪው ስም……ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን

ፕሮጄክቱ የተጀመረበት ዘመንና የደረሰበት አፈጻጸም፣

ግንባታው የተጀመረበት ጊዜ ሀምሌ 2010 ዓ.ም.ሲሆን ግንባታውን ለማጠናቀቅም 132,974,300.ብር ሲሆን ግንታው
በ 720 ቀናት ሊጠናቀቅ የነበረ ቢሆንም በታወቁ ምክንያቶች የግ ንባታ ማጠናቀቂያ ግዜው ሀምሌ 27 2014 ዓ.ም ድረስ
ተራዝሟል ፡፡

በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ የተከናወነው የፊዚካል ስራ በመቶኛ ሲገለጽ 45.76 በመቶ የሚሆነው የግንባታ ስራ የተጠናቀቀ
ሲሆን ይህም በፋይናንሻል አፈጻጸም ሲገለጽ 44.54 (59,223,103.73) በመቶ የሚሆነው ስራ ተጠናቆል፡፡

ፕሮጀክቱን ለማስቀጠል የተመደበ በጀት አፈጻጸም

 ጠቅላላ የፕሮጄክቱ በጀት.


o በውሉ መሰረት የፕሮጄክቱ በጀት፦132,974,300.

o በመጀመሪያው ውል መሰረት የአማካሪ ጠቅላላ በጀት 1,664,556.00


o ጠቅላላ የፕሮጄክቱ በጀት …134,638,856.00

 ግንባታው እስኪቆረጥ ድረስ በስራ ላይ የዋለ በጀት

o የግንባታ/ኢንቨስትምንት/ በጀት …58,663,971.91


o የአማካሪ በጀት……970,990.58
o ጠቅላላ እስከ 2015 በጀት ዓመት ስራ ላይ የዋለ…59,646,521.8

 በ 2016 በጀት ዓመት ለፕሮጄክቱ የተመደበ በጀት...13,297,430


o ለግንበታ /ኢንቨስምንት …12,465,152
o ለአማካሪና ቁጥጥር …832,278
o ድምር…13,297,430
 በ 2015 በጀት ዓመት ስራ ላይ የዋለ
o .ለግንበታ /ኢንቨስምንት …የለም

7
o ለአማካሪና ቁጥጥር … 11‚559.41

 በ 2016 በጀት ዓመት እስካሁን ስራ ላይ የዋለ


o .ለግንበታ /ኢንቨስምንት …የለም
o ለአማካሪና ቁጥጥር … የለም
ድምር…………… የለም

8
የበጀት ዕቅድ አፈጻጸም
ለፕሮጀክቱ የተያዘ ለ 2016 በጀት የበጀት አፈጻፀም (በ
የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወር አጠቃቀም አፈጻጻም
ጠቅላላ በጀት በብር ዓመት የተያዘ %) ለ 2016 በጀት ዓመት
ተ የፕሮጀክቱ የበጀት በጀት በብር ከጠቅ ከ 2016 የ 9 ወር በጀት
የተመደበ የ 2 ኛው
. ስም ምንጭ ላላ በጀት የተጠየቀ በጀት የ 1 ኛው ሩብ የ 3 ኛው አፈጻጻም
(የተፈቀደ) ሩብ
ቁ በጀት ዓመት በብር ዓመት ሩብ
በጀት በብር ዓመት
በጀት ዓመት
ብር ሣ ብር ሣ ብር ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ
1 ጭልጋ መንግስት 134,638 13,297,4 44.54 0 121,304,184 22 17,720,9 - 0 0 0 0 0 0
ማረ/ቤት ,856 30 39

የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም


የፊዚካል ስራዎች የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወር የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በፐርሰንት
ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ አፈጻጸም (በ%) (በ %)
ተ የፕሮጀክቱ ስም የሚገኝበት ቦታ የተጀመረበ የሚጠናቀቅ ከ 2016 የ 2 ኛው ሩብ
. ት ዘመን በት ዘመን ከጠቅላላ የ 1 ኛው ሩብ የ 3 ኛው ሩብ
በጀት ዓመት ዕቅድ የ 9 ወር እቅድ
ቁ (ዓ.ም) (ዓ.ም) ግንባታ ዓመት ዕቅድ ዓመት ዕቅድ
ዞን ወረዳ ቀበሌ ዓመት አፈጻጸም በ%
አፈጻጸም በ
አፈጻጸም በ%
አፈጻጸም በ%
ዕቅድ %
ዕቅድ
1 ጭልጋ ማረ/ቤት ማ/ ጭልጋ ሰራባ 201 ዓ.ም ሀምሌ 45.76 0 0 0 0 0
ጎንደር 2014

9
3.የግንደውሃ ማረሚያ ቤት ፕሮጀክት አፈጻጸም

 የተቋራጩ ስም……
 የአማካሪው ስም……
ይህ ፕሮጀክት በመንግስት ግንባታው እንዲከናዎን ፍቃድ ያገኘና በጀት የተመደበለት ሲሆን በኮሚሽናችን
በኩልም 20 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ስራ በመጀመርያው ስድስት ወራት ለማከናዎን እቅድ ይዞ ወደስራ
የገባ ቢሆንም አሁን ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እና ለመሬት ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ያልተከናዎነና
ከሶስተኛ ወገን ነጻ ያልተደረገልን በመሆኑ ዲዛይን አዳፕቴሽን እና ሌሎች ስራዎችን በማከናዎን የግንባታ
ስራውን ማስጀመር አልተቻለም፡፡
በ 2016 በጀት ዓመት ለፕሮጄክቱ የተመደበ በጀት...13,297,430
o ለግንበታ /ኢንቨስምንት …
o ለአማካሪና ቁጥጥር …
o ድምር…13,297,430

 በ 2016 በጀት ዓመት እስካሁን ስራ ላይ የዋለ


o .ለግንበታ /ኢንቨስምንት …የለም
o ለአማካሪና ቁጥጥር … የለም
ድምር…………… የለም

10
የበጀት ዕቅድ አፈጻጸም
ለፕሮጀክቱ ለ 2016 በጀት የበጀት አፈጻፀም (በ የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወር በጀት አጠቃቀም አፈጻጻም
የተያዘ ጠቅላላ ዓመት የተያዘ %) ለ 2016 በጀት ዓመት
ተ የፕሮጀክቱ ስም የበጀት በጀት በብር በጀት በብር ከጠቅ ከ 2016 የተጠየቀ በጀት የተመደበ የ 1 ኛው ሩብ የ 2 ኛው የ 3 ኛው የ 9 ወር
. ምንጭ ላላ በጀት ዓመት በብር (የተፈቀደ) ዓመት ሩብ ሩብ በጀት አፈጻጻም
ቁ በጀት በጀት በጀት በብር ዓመት ዓመት
ብር ሣ ብር ሣ ብር ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ ብር ሣ
1 ገንደውሃ መንግስት 13,297,43 0 13,297,43 0 0 0 125,000,0 13,297, - 0 0 0 0 0
ማረ/ቤት 0 0 00 430

የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም


የፊዚካል ስራዎች የ 2016 በጀት ዓመት የ 9 ወር የፊዚካል ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በፐርሰንት (በ
ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ ፕሮጀክቱ አፈጻጸም (በ%) %)
ተ የፕሮጀክቱ የሚገኝበት ቦታ የተጀመረበት የሚጠናቀቅበት ከጠቅላላ ከ 2016 የ 1 ኛው ሩብ የ 2 ኛው ሩብ የ 3 ኛው የ 9 ወር እቅድ
. ስም ዘመን (ዓ.ም) ዘመን (ዓ.ም) ግንባታ በጀት ዓመት ዕቅድ ዓመት ሩብ አፈጻጸም በ%
ቁ ዞን ወረዳ ቀበሌ ዕቅድ ዓመት አፈጻጸም በ% ዕቅድ አፈጻጸም በ ዓመት
ዕቅድ % ዕቅድ
አፈጻጸም
በ%
1 ገንደውሃ ም/ መተ ገንደው አልተጀመረም ሀምሌ 2018 0 0 0 0 0 0
ማረ/ቤት ጎንደር ማ ሃ

11
የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዋና ዋና ተግዳሮቶች

የወልድያ ፕሮጀክት በትህነግ ወረራ ምክንያት በ ሀምሌ ወር 2013 ዓ.ም የግንባታ ስራው የተቋረጠ ሲሆን
የአይከል ፕሮጀክት ደግሞ ባካባቢው በተፈየጠረ የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በሚያዝያ ወር 2013 ዓ.ም
የግንባታ ስራው መቋረጡ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ሁለቱም ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራው ከተቋረጠ ሁለት አመት እና ከዛ በላይ የሆናቸው ሲሆን ከዚህ
ጋር ተያይዞ በተፈጠረ የዋጋ ንረት ምክንያት የስራ ተቋራጮቹ በመንግስት የተደረገው (61.95) በመቶ የዋጋ
ንረት ማካካሻ በቂ አይደለም በሚል ምክንያት ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹ የግንባታ ስራ እዲቀጥሉ የተደረጉ ጥረቶች ባጭሩ

በወልድያና አካባቢው የነበረው የጸጥታ ችግር አንጻራዊ ሰላም መታየት ከጀመረበት የካቲት 15 ቀን 2014
ዓ.ም ጀምሮ የስራ ተቋራጩ ወደ ስራ እንዲገባ በደብዳቤ ቢገለጽለትም ፡-

1 ኛ. በጦርነቱ ለወደሙ ንብረቶች የካሳ ክፍያ ካልተከፈለን

2 ኛ. ከተፈጠረው የገበያ ዋጋ ንረት ጋር ተያይዞ የዋጋ ማሻሻያ ካልተደረገልን

3 ኛ. ለባከኑ የስራ ቀናቶች ተጨማሪ ጊዜ ካልተሰጠን ገብቶ ለመስራት እንቸገራለን

በሚል ምላሽ የሰጠ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት በጉዳዩ ላይ ከአማካሪ ድርጅቱ፣ ከፕላን ኮሚሽንና ከገንዘብ
ቢሮ ጋር በጉዳዩ ዙርያ ስንነጋገርና ስንጻጻፍ ቆይተን የክልሉ መንግስት ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የግንባታ
ስራዎችን ዋጋ ንረት በሚመለከት የዋጋ ንረት ማሻሻያ የተደረገ ለመሆኑ በደብዳቤ የገለጸልን ከመሆኑ ጋር
ተያይዞ ለስራ ተቋራጮቹ (30.95) የዋጋ ንረት ማስተካከያ ተደረገ በመሆኑ ወደ ግንባታ ስራቸው እንዲገቡ
በደብዳቤ ቢገለጽላቸውም ሀምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በዋጋ ማሻሻያ ዙሪያና በጸጥታ ችግር
ለወደሙና ለተበላሹ ንብረቶች ካሳ እንዲከፈለን ያቀረብነው ጥያቄ መልስ ካላገኘ ወደስራ ለመግባት
እንቸገራለን በሚል በድጋሜ መልስ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ኮሚሽናችን ሀምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ያቀረቡት ጥያቄ በኮሚሽኑ ብቻ
መልስ የሚሰጠው ባለመሆኑ የክልልሉ መንግስት መልስ አስከሚሰጥ ወደ ስራ ገብተው ግንባታውን እያከናወኑ
እንዲቆዩና የመንግስትን ምላሽ እንዲጠብቁ በሚል በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ከዚህ በኋላም ጉዳዩ በመጻጻፍ ብቻ መፍትሔ የማያገኝ በመሆኑ ኮሚሽናችን ጉዳዩን በውይይትና በምክክር
እልባት ለመስጠጥ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እያለ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ በ 19/04/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ
በግንባታ ስራዎች ላይ የዋጋ ንረት ማስተካከያ የተደረገ ለመሆኑ ያሳወቀን ሲሆን በድጋሚ በዚሁ መመርያ ላይ
ተጨማሪ ማብራርያ በ 2/5 2015 ዓ.ም የላከልን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለስራ ተቋራጮቹ በ 9/5 2015 ዓ.ም
በተጻፈ ደብዳቤ (61.95) የግንባታ ስራዎች ዋጋ ንረት ማስተካከያ የተደረገ ለመሆኑ ተገልጾላቸዋል፡፡

12
ይሁንና የስራ ተቋራጮቹ ለኮሚሽኑ በጻፍት ደብዳቤ ድርጅታችን ከዚህ በፊት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ
እንዲሰጠን እየጠየቅን እንዲሁም ከድርጅታችን ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት በተፈጠረው የዋጋ ንረትና
የጊዜ መጓተት በጋራ ቁጭ ብለን ተነጋግረን መፍትሄ ማስቀመጥ ካልቻልን ስራውን ለመስራት እንቸገራለን
የሚል ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጡ በመሆኑ ግንባታዎቹን ማሰጀመር ሳይቻል ቀርቶል፡፡

ሆኖም ኮሚሽናችን ግንባታዎቹ ተጠናቀው ላገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ እስከ በጀት
አመቱ መገባደጃ ድረስ የአማካሪ ድርጅታችንን ምክሮች በመቀበል እልህ አስጨራሽ ውይይት በማድረግ
ፕሮጀክቶቹ እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ጥረቶች እያደረገ የቆየ ቢሆንም የስራ ተቋራጮቹ ባሳዩት ግትር አቋም
የሚጠበቀው ውጤት አልተገኘም፡፡

ውልን መሰረት በማድረግ የተወሰድ እርምጃዎች

የወልድያ ፕሮጀክትን በተመለከተ የግንባታ ስራው በማከናወን ላይ እያለ ባሳዩት መዘግየት (deliance) ምክንያት
የመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቂያ በቁጥር መህዲግቁስድ/088/2011 በቀን 02/12/2011 ዓ.ም በፕሮጀክቱ ተጠሪ መሀንዲስ

በኩል የተሰጣቸው ሲሆን የግንባታ ስራው በጸጥታ ችግር ተቋርጧል አንጻራዊ ሰላም ከተፈጠረ በኋላ እና በቁጥር

ል/ዲ/ቁ/ኮ/84/2015 በቀን 25/07/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ደግሞ ፕሮጀክቱን የማማከር ስራ በማከናወን ላይ ያለው

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ወደ ስራ እንዲገቡ የ 2 ኛ ዙር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶቸዋል፡፡

ሆኖም የስራ ተቋራጩ በራሱ አነሳሽነት በቁጥር ቢአ/02140/15 በቀን 09/08/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የሀገር ውስጥ

ጦርነት በመከሰቱ እና ይሄውም ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ስለሆነ እና ከ 60 (ስልሳ) ቀናት በላይ ስለቆየ ከ 30 ቀን

በኋላ ማለትም ከቀን 10/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ በተቋራጩ አነሳሽነት የተቋረጠ መሆኑን አሳውቆል፡፡

የአይከል ፕሮጀክትን በተመለከተ በቁጥር መህዲግቁስድ/ጭማቤትግፕ/154/12 በቀን 17/11/12 ዓ.ም በውሉ መሰረት

ፕሮጀክቱ መድረስ ከሚገባው አፈጻጸም እጅግ ዝቅተኛ እና ከሚጠበቀው ባታች በመሆኑ ይህንን ደካማ የስራ

እንቅስቃሴ በማረም የባከኑ የስራ ጊዜያትን የሚያካክስ ስራ እንዲሰሩ የመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቅያ ተሰጥቶል፡፡

በተጨማሪም ስራ ተቋራጩ በመጀመርያ ዙር ማስጠንቀቂያው መሰረት ወደስራ መግባት ባለመቻሉ በቁጥር

ልዲኮቁ/2/332/15 በቀን 05/11/2015 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የግንባታ ስራውን ማከናወን እነዲጀምሩ የሁለተኛ ዙር

(2 ኛ) ማስጠንቀቂያ ባማካሪ ድርጅቱ ተሰጥቶቸዋል፡፡

13
የገንደውሃ ማረሚያ ቤት በተመለከተ ዞኑ የተጠየቀውን የካሳ ክፍያ እንዲከፍሉ እና ከሶስተኛ ወገን ነጻ አድርገው

እንዲያስረክቡን ጥረቶችን እያደረግን የምንገኛ ሲሆን የጸጥታ ሁኔታው ሲሻሻል በአካል ጭምር በመሄድ ጥረቶች

ይደረጋሉ፡፡

የወደፊት አቅጣጫዎች

ሁለቱ ገንባታቸው ተጀምረው የተቋረጡ ፕሮጀክቶችን በሚመለከት ከስራ ተቋራጮች ጋር ውይይት እያደረግን የቋየን

በመሆኑ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ የተራዘመ ግዜ እንዳይወስድ በግል ግል (arbitration) እንዲቋጭ በማድረግ ለ አዲስ

ስራ ተቋራጮች እንዲሰጥ እና ስራው እንዲጠናቀቅ ለማድረግ አቅጣጫ ተይዞል፡፡

14

You might also like