Professional Documents
Culture Documents
4
4
4
መግቢያ
ዛሬ በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት ርእሰ-ነገሮች መካከል፣ ነገር ግን በሕይወት ውስጥ ደግሞ እጅጉን
አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ስለሆነው ስለ ይቅርታ እንነጋገራለን፡፡
ለምንድን ነው ይቅርታ አስቸጋሪ የሚኾነው? አስቸጋሪ የሚሆንበት ምክንያት ሰብኣዊ ባሕርያችን
ከይቅርታ ይልቅ በቀልን ፈላጊ በመኾኑ ነው፡፡ አንድ ሰው ሲጎዳን በተፈጥሮኣችን እኛም በጎዳን ሰው
ላይ በአጸፋው እንደዚያው እንድናደርግበት ይነግረናል፤ ማለትም ዋጋውን ወይም ዋጋዋን ማግኘት
አለበት/አለባት ብሎ በውስጥ ሹክ ይለናል፡፡
ኢየሱስ ያደረገው ግን እንደዚህ አልነበረም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ እንድናደርግ አያዘንም፡፡
ይቅርታ ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነ? አስፈላጊ የሆነበት ዋናው ምክንያት ነፃ ስለሚያወጣን ነው፡፡
እኛን ብቻ አይደለም የጎዱንንም ሰዎች ጭምር ነፃ ስለሚያደርጋቸው ነው እንጂ፡፡
የይቅርታን ኀይልን ስናገኝ፣ ሕይወታችንን፣ ቤተሰቦቻችንንና፣ ማኅበረሰባችንን ይለውጣል!
የእግዚአብሔር ጸጋ
3) በዚህ ምድር ስንኖር ንጹሕ፣ ቅዱስና፣ ፍሬ የሚያፈራን ሕይወት እንዲኖረን ኀይልን ያስታጥቀናል፡፡
ይቅርታ እና እርቅ
ይሁን እንጂ አንድ ሰው ይቅርታ እንዲደረግለት የማይፈልግ ከሆነስ? እሱ ወይም እሷ ይቅር ለማለት
ፈቃደኛ ካልሆኑስ?
በይቅርታ እና እርቅ መካከል ልዩነት አለ? እርቅ— ማለት በሁለት ወገኖች መካከል " ግንኑነትን
ማደስ" ሲሆን፣ ይቅርታ ግን ከአንድ ወገን የሚመጣ ነው፡፡
በሌላ አባባል ይቅር መባል የማይፈልጉትን እንኳ ይቅር ማለት ትችላላችሁ ማለት ነው፡፡. ይቅር
ማለት የእናንተ ምርጫ ሲሆን ፣ መቀበል ደግሞ የእነርሱ ምርጫ ነው፡፡
ኢየሱስ ይቅር እንዲላቸሁ እስክትጠይቁት ድረስ ዝም ብሎ ይቅር ሳይላችሁ ቢቆይ ኖሮ፣ ከዛሬ
2,000 ዓመታት በፊት ስለ ኀጢአታችሁ ባልሞተም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሳትጠይቁትም ቢሆን
አድርጎታል፡፡
የኢየሱስን አብነት ተከተሉ
የእዳ ስረዛ
ይቅርታ ማለት እዳን መሰረዝ ማለት ነው፤ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማራቸው ጸሎት ውስጥ
ስላለው አንድ ሐረግ አስባችሁ ታውቃላችሁን? እንዲህ ይላል፡- "እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር
እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤" (ማቴ 6፡12)፡፡
ለምድን ነው ኀጢአታችንን ይቅርበል ማለትን ትቶ በደላችንን ይቅር በል ያለው?
አንድን ሰው ስንበድል፣ ከዛ ሰው ላይ አንድን ነገር እየሰረቅንበት ሊሆን ይችላል፤ ምናልባት
ደስታውን፣ መልካም ስሙን፣ ቅንነቱን፣ ወይም የወደፊት እድል ፈንታ ጽዋ ተርታውን፡፡
ይቅር ትሏቸው ዘንድ ሰዎች በድለው የሰረቁባችሁ ምን ነገሮች አሉ? ሰዎችስ ምን ይዳዳሉ?
ሰዎች ነጻ እንዲሆኑ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሰረዝ የምትፈልጉት የበደል'ዳ ምን አለ?
የይቅርታ አስገራሚው ነገር— ሌሎችን ይቅር ስትሉ፣ እንዲሁም የመበቀል መብታችሁን ትታችሁ
ዕዳ-በደላቸውን በመሰረዛችሁ ምክንያት ራሳችሁን ነጻ ማውጣታችሁ ነው!
ይቅር ያለማለት የልብ ባርነት ይፈጥርብናል፣ ይልቁንም ደግሞ መራርነትና ጮካነት-ጥርጥር
በውስጣችሁ እንዲወለድ ያደርጋል፡፡
ይቅር ስትሉ ግን አንቀው የያዟችሁ ምሬትና ጮካነት (ክፉ አሳቢነት፣ ጥርጥር) ይለቋችሁና ልባችሁ
ነጻ ይወጣል፡፡
ይህ ሲባል ግን ሁሉም ጠባሳዎች ይወገዳሉ፣ እንዲሁም ሕመሙ በሙሉ ይጠፋል ማለት
አይደለም፡፡ ይቅር ማለት መርሳት አይደለምና፡፡
ይሁን እንጂ ለመኖር፣ ለመተንፈስ፣ በንጹሕ ልቡናና ኅሊና ሌላውን ለመውደድ ነጻ ናችሁ ማለት
ነው፡፡
አጋዥ ዘዴ
የበደሏችሁንና የጎዷችሁን ሰዎች ይቅር ማለት ውስጣችሁ የሚታገላችሁ ከሆነ ሊያግዛችሁ የሚችል
ዘዴ እንሆ፡-
አንድ ወረቀት አውጡና ይቅር ማለት ያቃታችሁን ሰው የሰረቀባችሁን ነገሮችን በሙሉ ጻፉ፤
ደስታችሁን፣ ክብራችሁን፣ በራስ መተማመናችሁን፣ ጓደኞቻችሁ፣ ቤተሰቦቻችሁ፣ ... በተቻለ
መጠን ለይታችሁ ለመናገር/ለመጻፍ ሞክሩ፡፡
ከዚያም ወረቀቱን እየተመለከታችሁ፡- "አዎን በደል ተፈጽሞብኛል፣ አዎን ይህ ሰው ብዙ ነገር
አድርጎኛል፡፡ የመናደዱ መብትም አለኝ፤ ነገር ግን ሰይጣን ልቤን በሰንሰለት ጠፍሮ እንዲይዘው
አልፈቅድለትም፡፡ ይቅር ማለትን መርጫለሁ፤ የዚህን ሰው በደል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሰርዤ
ይህን ሰው ነጻ ለማውጣት መርጫለሁ!" ትላላችሁ፡፡
ከዚያም ወረቀቱን ጨባብጡትና በእሳት አቃጥሉት— እጅግ ነጻ የመውጣት ተመክሮ(ልምምድ)
ይሆንላችኋዋል!
አንዴ እዳ-በደሎችን ከሰረዛችሁ በኋላ ከእንግዲህ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ሰውየው የበደለኝነት ስሜት
እንዲሰማው መልሳችሁ መላልሳችሁ ነገሮቹን እየጎተታችሁ አታመጧቸውም ማለት ነው፤ ያን
የምታደርጉ ከሆነ ግን ይቅርታ ያለማድረጋችሁ ማሳያ ነው ማለት ነው፡፡
ሰውዬው ይቅርታችሁን ተቀበለ አልተቀበለ፣ ምንም የሚለወጥ ነገር የለም፣ ምክንያቱ ከዚያ በኋላ
ነገሩ በእርሱና በእግዚአብሔር ዘንድ የተያዘ ይሆናል፡፡
አንድ ቀን እግዚአብሔር ፍጹም የሆነ ፍትህን ያመጣል፡፡ እያንዳንዱ ሰው በጻድቁና በእውነተኛው
ዳኛ ፊት መቆሙ ብሎም ለድርጊታቸው እና ለሐሳባቸው በሙሉ ተጠያቂዎች መሆናቸው አይቀሬ
ነው፡፡
ይቅርታ ማድረግ ማለት በቀልን መተውና የሰው ልጆችን ሁሉ በጽድቅና በርትእ ሊፈርድ ባለው
በእግዚአብሔር እጅ ሁሉንም ነገር ማኖር ማለት ነው፡፡
የይቅርታ የሕይወት ዘይቤ
ይቅር ባይነት ማለት አስከፊ ባሕሪዎቻቸውን ፊት ለፊት መጋፈጥ የለባችሁም ማለት አይደለም፡፡
ይህም ሲባል ደግሞ ዘለፋዊ ግንኙነት ውስጥ መቆየት ወይም ትክክለኛ ያልሆኑ ተግባሮች
እንዲቀጥሉ መፍቀድ አለባችሁ ማለትም አይደለም፡፡
የበዳያችሁን የበደል እዳ መሰረዝና የእሱን/የሷን መጻኢ እድል ፈንታም ደግሞ ሁሉን ለሚችልና
ለሚያውቅ አምላክ እጆች አሳልፎ መስጠት ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
እኔና እናንተስ?