Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 51

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

Educational Assessment and Examinations Services

የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና አስፈፃሚዎች


ተግባርና ኃላፊነት፣ ምልመላ፣ መረጣ፣ ምደባ እና የተለያዩ ክፍያዎች አፈፃፀም ማንዋል

ይህ ማኑዋል ለፈተና አስተዳደር ሥራ ያግዝ ዘንድ የተለያዩ የግብረ


ኃይል አደረጃጀቶችን፣ የተፈታኞችና የፈተና አስፈጻሚዎች መብት፣
ግዴታ፣ የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች ጭምር የያዘ ነው፡፡

ነሐሴ / 2014 ዓ.ም


አዲስ አበባ
መውጫ ገጽ
መግቢያ ..................................................................................................................................... - 3 -
1. የአውጪው ስልጣን ............................................................................................................. - 4 -
2. አጭር ርዕስ......................................................................................................................... - 4 -
3. ትርጓሜ .............................................................................................................................. - 4 -
4. ምህፃረ ቃል ........................................................................................................................ - 5 -
5. ዓላማ................................................................................................................................... - 6 -
5.1. ዋና ዓላማ.......................................................................................................................................- 6 -
5.2. ዝርዝር ዓላማ.................................................................................................................................- 6 -
6.የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት እና አስፈጻሚዎች (አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት እና
የምልመላ መስፈርት) ................................................................................................................. - 7 -
6.1. የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት....................................- 7 -
6.2. የፈተና ማዕከል ግብረ ኃይል (በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሚመራ የፈተና ግብረ ኃይል)....- 8 -
6.3. የተፈታኞች አገልግሎት ግብረ ኃይል (በአስተ/ርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት የሚመራ) .........- 9 -
6.4. የፈተና አሰጣጥ ማዕከል ግብረ ኃይል (በአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚመራ)...........- 11 -
6.5. የፈተና ማስፈጸሚያ ግብአት አቅርቦትና አስፈጻሚዎች ክፍያ አገልግሎት ግብረ ኃይል Error!
Bookmark not defined.
7. በክልሎችና በከ/አስተዳደሮች የሚቋቋሙ ግብረ ኃይሎች፣ አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት... - 12 -
7.1. የክልል /ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ግብረ ኃይል .......................................................- 12 -
7.2. በዞን ትምህርት መምሪያ የሚመራ ዞናዊ የፈተና ግብረ ኃይል ............................................- 13 -
7.3. በወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሚመራ በወረዳ የፈተና ግብረ ኃይል (01) ............................- 13 -
8. የፌደራል ፖሊስ የፈተና ማዕከላት ግብረ ኃይል (እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ)....................... - 14 -
9. የፈተና አስፈጻሚዎች (Exam administrators) አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት .................. - 16 -
9.1. የፈተና ማዕከል ኃላፊ .................................................................................................................- 16 -
9.2. የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ .....................................................................................................- 17 -
9.3. የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ...................................................................................................................- 18 -
9.4. ሱፐርቫይዘር................................................................................................................................- 21 -
9.5. ፈታኝ ...........................................................................................................................................- 23 -
9.6. የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ...................................................................................................- 26 -
9.7. የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ...............................................................................................................- 28 -
10. የፈተና አስፈፃሚዎች መመልመያ መስፈርት ................................................................. - 29 -
11. የፈተና አስፈጻሚዎችና ተፈታኞች መብትና ግዴታ (በፈተና አስተዳደር የተፈቀዱና
የተከለከሉ ጉዳዮች) .................................................................................................................. - 31 -
11.1. የፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ ....................................................................................- 31 -
11.2. የተፈታኞች መብትና ግዴታ.....................................................................................................- 32 -
12. የፈተና አስፈጻሚዎች ክፍያ አይነት፣ ተመን እና አፈጻጸም ............................................ - 35 -
12.1. የውሎ አበል ክፍያ......................................................................................................................- 35 -
12.2. የአገልግሎት ክፍያ /session payment/ ..................................................................................- 35 -
12.3. የትራንስፖርት ወጪ ክፍያ .......................................................................................................- 36 -
12.4. የመረጃ ልውውጥ ሞባይል ካርድ ወጪ ክፍያ .........................................................................- 36 -
12.5. የተፈታኞች የምግብ አገልግሎት ክፍያ ...................................................................................- 36 -
12.6. የተለያዩ ወጪዎች ክፍያ ...........................................................................................................- 36 -

-1-
13. የክፍያ አፈፃፀም፣ ሂሳብ ሰነድ መረጃዎች እና ሂሳብን ማወራረድ አፈፃፀም ሁኔታ ........... - 37 -
9. ማጠቃለያ ......................................................................................................................... - 37 -
አባሪ 1፡- የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ ዝርዝር መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ ................................ - 39 -
አባሪ 2፡- የፈተና አስፈጻሚዎች ምደባ ማጠቃለያ ቅጽ ............................................................. - 40 -
አባሪ 3፡- የፈተና እስፈጻሚዎች ክፍያ አፈጻጸም ማጣቃለያ ስንጠረዥ ...................................... - 41 -
አባሪ 4፡- የመንግስት ሠራተኞች ውሎ አበል ክፍያ ማወራረጃ - ቅፅ - 2 .................................... - 0 -
አባሪ 5፡- የፈተና አስፈፃሚዎች የውሎ አበል እና የትራንስፖርት ክፍያ መፈፀሚያ ቅጽ ............ Error!
Bookmark not defined.
አባሪ 6፡- የፈተና አስፈፃሚዎች የአገልግሎት (ሴሽን) ማስፈረሚያ ቅጽ ....................................... - 2 -
አባሪ 7፡- የፈተና አስፈፃሚዎች የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ መፈፀሚያ ቅጽ ............................... - 3 -
አባሪ 8፡- ደረሰኝ ለማይገኝላቸው ወጪዎች የሚከፈል ክፍያ መመዝገቢያ እና ማስተላለፊያ ቅፅ . - 4 -

-2-
መግቢያ
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መካከል የኢትዮጵያ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከማዘጋጀት እስከ ውጤት መግለጫ ሰርተፊኬት መስጠት ድረስ
ያሉ የፈተና አስተዳደር ተግባራት ይገኙበታል። አገልግሎቱ ለ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና መስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ
ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ላይ ይገኛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፈተና አስተዳደር አስፈፃሚዎች
ምልመላ፣ ምደባና የተለያዩ የፋይናንስ ክፍያዎች አፈፃፀም ማንዋል ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም በፈተና
አስተዳደር አስፈፃሚነት ለሚሳተፉ የፈተና አስፈፃሚዎች ከስራው ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቆይታ
መሰረት በማድረግ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የቀን የውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት
የውሎ አበል ክፍያ እንዲሁም ፈተናውን በማስተዳደር ሂደት የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት መሰረት
የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ የሚከፍል ይሆናል።

አገልግሎቱ ከላይ በተገለፀው አግባብ የፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላና ምደባ፣ ተግባርና ኃላፊነትን
እንዲሁም የቀን ውሎ አበል፣ የአገልግሎት፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ክፍያዎችን መሰረት
በማድረግ የገንዘብ አጠቃቀም ሰንጠረዥ (Breakdown) በማዘጋጀት አስፈላጊውን ክፍያ በገንዘብ
ሚኒስቴር በኩል ለፈተና ማዕከላት (ዩኒቨርስቲዎች) ገንዘቡ እንዲደርስ በማድረግ የፈተና አስተዳደር
ሂደቱ ተፈፃሚ ለማድረግ የአፈጻጸም ማንዋል አዘጋጅቷል። ይህ የአፈጻጸም ማንዋልም በጥቅሉ አራት
ክፍሎች ያሉት ሲሆን እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል፡፡

-3-
ክፍል አንድ

አጠቃላይ

1. የአውጪው ስልጣን
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀጽ
9 (2) በተሰጠው ሥልጣን እንዲሁም በ“ሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012” ላይ
ባሉ ድንጋጌዎች መሠረት ይህን የአሰራር ማኑዋል አውጥቷል፡፡

2. አጭር ርዕስ
ይህ የአፈጻጸም ማንዋል “የፈተና አሰጣጥ እና አፈፃፀም ማንዋል 01/2014” ተብሎ ይጠቀሳል።

3. ትርጓሜ
የቃሉ ወይም የሀረጉ ፍቺ ሌላ ራሱን የቻለ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ሰነድ
ለሚገለጹ ይዘቶች እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት በሚሳተፉ ፈተና አስፈፃሚዎች መካከል ለሚኖር የጋራ
መግባባት ከታች የተቀመጡ ቃላት ወይም ሀረጋት የሚከተለው ትርጓሜ ይኖራቸዋል።
3.1. አገልግሎት፡- አገልግሎት ማለት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋም ነው፡፡
3.2. የፈተና ማዕከል፡- ፈተናውን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመስጠት የተመረጠ ዋና የፈተና ማእከል ሲሆን
የፌደራል የመንግስት ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች ናቸው። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት
(Universities) በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ስር የሚገኝ የትምህርት
አገልግሎት የሚሰጥ መንግስተዊ ተቋም ማለት ነው፣
3.3. የፈተና ጉድኝት ማዕከል፡- የፈተና ጉድኝት ማዕከል (Exam Cluster Center) ማለት በፈተና
ማዕከል ውስጥ የሚገኝ ከአንድ በላይ የሆኑ የፈተና ጣቢያዎችን በአንድ አካባቢ የያዘ የፈተና
አሰጣጥ አደረጃጀት ነው፡፡
3.4. ንዑስ የፈተና ማዕከል፡- ንዑስ የፈተና ማዕከል ማለት ከዋናው የፈተና ማዕከል ስር ሆኖ
በካምፓሶች/ኮሌጆች (University Campus)) ደረጃ የተደራጀና ፈተና የሚሰጥበት ተቋም ሲሆን
ከአንድ በላይ የጉድኝት ማዕከላት ሊይዝ የሚችል ነው፡፡
3.5. የፈተና ጣቢያ፡- የፈተና ጣቢያ ማለት በጉድኝት ማዕከል ሥር የሚገኝ አንድ እና ከአንድ በላይ
የሆኑ ትምህርት ቤቶች (የግልና የመንግስት) ተፈታኞችን የያዘ ሲሆን በአገልግሎቱ የተሰጠ
የራሱ መለያ ቁጥር (Group Number) ያለው አደረጃጀት ነው፣
3.6. መፈተኛ ክፍል፡-መፈተኛ ክፍል ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ እስከ 36 (ሰላሳ ስድስት)
ተፈታኞችን የሚይዝ ለፈተና አሰጣጥ ምቹ የሆነ አንድ መፈተኛ ክፍል ማለት ነው፣ ሆኖም ግን
በአንድ የፈተና ጣቢያ የፈተና ክፍሉ አዳራሽ ከሆነ እና ከሰላሳ ስድስት በላይ ተፈታኞችን

-4-
የሚይዝ ከሆነ በፈተና አደራሽ ውስጥ ሰላሳ ስድስት ተፈታኞችን የያዘ ስብስብ እንደ አንድ
መፈተኛ ክፍል ይቆጠራል፣
3.7. የፈተና አስፈጻሚዎች፡- የፈተና አስፈጻሚዎች ማለት በፈተና አሰጣጥ ሂደት በማዕከል ኃላፊነት፣
በጉድኝት ማዕከል አስተባባሪነት፣ በጣቢያ ኃላፊነት፣ በሱፐርቫይዘርነት፣ በፈታኝነት፣ በአንባቢነት፣
በመልስ ወረቀት ቆጣሪነት፣ በፈተና ኮረጆ ተረካቢና አስረካቢነት ወዘተ በመሰል ሥራዎች
የሚሳተፉ ሰዎች ማለት ነው፤
3.8. የፈተና ማዕከል ኃላፊ፡- የማዕከል ኃላፊ ማለት በዋና ወይም በንዑስ የፈተና ማዕከል የፈተና
አሰጣጥ ሂደቱን የሚመራ የፈተና አስፈጻሚ ነው፡፡
3.9. የፈተና ጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፡- የፈተና ጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ማለት ከስሩ የተለያዩ
የፈተና ጣቢያዎችን የሚያስተባብር የፈተና አስፈጻሚ ነው፡፡
3.10. የፈተና ጣቢያ ኃላፊ፡- የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ አንድ ወይም ከአንድ
በላይ የሆኑ የመፈተኛ ክፍሎችን እና ፈተና አስፈፃሚዎችን የሚመራ፣ ተጠሪነቱ ለፈተና ጉድኝት
ማዕከል አስተባባሪ የሆነ የፈተና አስፈጻሚ ነው፣
3.11. ሱፐርቫይዘር፡- ሱፐርቫይዘር ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ የአራት መፈተኛ ክፍሎች የፈተና
አሰጣጥ ሂደት የሚመራ እና ተጠሪነቱ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊ የሆነ የፈተና አስፈፃሚ ማለት ነው፣
3.12. ፈታኝ፡- ፈታኝ ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ በአንድ መፈተኛ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ብዛታቸው
እስከ 36 (ሰላሳ ስድስት) ድረስ የሆነ እና ዓይነ ስውር ተፈታኝ ያልሆኑ ተፈታኞችን የፈተና
አሰጣጥ ሂደት የሚመራና የሚቆጣጠር ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር የሆነ ሰው ማለት ነው፣
3.13. አንባቢ / ረዳት ጸሐፊ፡- አንባቢ / ረዳት ጸሐፊ ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ ለሚገኝ የዓይነ
ስውር ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎችን የማንበብ እና የመልስ ወረቀት መረጃዎችን የመፃፍ / የእጅ
እንቅስቃሴ ችግር ላለበት ተፈታኝ የመልስ ወረቀት መረጃዎችን የመፃፍ አገልግሎት የሚሰጥና
ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር የሆነ የፈተና አስፈፃሚ ሰው ማለት ነው፣
3.14. የመልስ ወረቀት ቆጣሪ፡- የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ማለት በአንድ የፈተና ጣቢያ የመልስ ወረቀት
የመቁጠር እና የመልስ ወረቀቶቹን የማደራጀት አገልግሎት የሚሰጥ የፈተና አስፈፃሚ ነው፣
3.15. ሴሽን (Session)፡- ሴሽን ማለት አንድ የትምህርት ዓይነት ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ቆይታ
ነው፡፡
3.16. የሴሽን ክፍያ፡- አንድ የፈተና አስፈጻሚ በፈተና አስፈፃሚነት ስራ ሲሳሰተፍ የሚከፈል የሙያ
አገልግሎት ክፍያ ነው፣

4. ምህፃረ ቃል
1.1. ኢፌዲሪ ት/ሚ - ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር
1.2. ትምፈአ - ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
1.3. ት/ቢሮ - ትምህርት ቢሮ

-5-
5. ዓላማ
5.1. ዋና ዓላማ
የተፈታኞችና የፈተና አስተዳደር አስፈፃሚዎች ምልመላ፣ መረጣ፣ ምደባ፣ ስምሪት እንዲሁም
የተፈታኞችና የአስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እና የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮችና የተለያዩ
ክፍያዎች አፈፃፀም የሚመራበትን ወጥ የሆነ አሠራር በማዘጋጀት የፈተና አስተዳደር ስራን
ውጤታማ ማድረግ ነው።

5.2. ዝርዝር ዓላማ


የዚህ ማንዋል ዝርዝር ዓላማዎች፡-
5.2.1. የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ምደባ በአፈፃፀም ማንዋሉን መሰረት በፍትኃዊነትና
በጥራት እንዲፈጸም ያስችላል፣
5.2.2. በፈተና አስፈፃሚዎች ምልመላና ምደባ አፈፃፀም ላይ የሚቀርቡ የአፈፃፀም ቅሬታዎችን
ለመቀነስ ያግዛል፣
5.2.3. ለፈተና አስፈፃሚዎች የሚከፈሉ ክፍያዎችን በአግባቡ ተፈፀሚ ለማድረግ ያስችላል፣
5.2.4. መንግስት በፈተና አስተዳደር አፈፃፀም ሂደት የሚጠቀመውን የሰው ኃይል እና የገንዘብ
ሀብት ፍትሀዊ እና በውጤታማነት ላይ የተመሰረተ ማድረግ ያስችላል፣
5.2.5. ጉዳዩን በሚያስፈጽሙ አካላት በተደጋጋሚ የሚቀርቡ የአፈፃፀም ግልፀኝነት ጥያቄዎች
እንዲሁም የፋይናንስ አሰራር መመሪያ ከማስጠበቅ አንፃር መፍትሄ መስጠት ያስችላል።

-6-
ክፍል ሁለት

የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት እና አስፈጻሚዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት እና


የምልመላ መስፈርት
6. የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት
የፈተና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ማለት ከፈተና አሰጣጡ ጋር ተዘዋዋሪ ግንኙነት ያላቸው የፈተና
ሥራ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚመለከት ሲሆን በፌዴራል፣ በክልል እና በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን
አስተዳደራዊ አደረጃጀት መሰረት በማድረግ በፈተና ስራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ የምልመላ እና ምደባ
ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡ መዋቅራዊ የሥራ ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በሚኒስትር የሚመራ
ብሔራዊ የፈተና ግብረ ኃይል

በክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ትምፈአ በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሚመራ


ክልላዊ የፈተና ግብረ ኃይል የፈተና ግብረ ኃይል

በዞን ትምህርት መምሪያ የሚመራ


ዞናዊ የፈተና ግብረ ኃይል በአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት በአካደሚክ ም/ ፕሬዚዳንት የሚመራ
የሚመራ የፈተና ግብረ ኃይል
የፈተና ግብረ ኃይል

በወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሚመራ


በወረዳ የፈተና ግብረ ኃይል

ማሳሳቢያ፡-
ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና በዩኒቨርሲቲዎች ስር የሚተዳደሩ ከምፓሶች ወይም
ኮሌጆች ያላቸውን አስተዳደራዊ መዋቅር መሠረት በማድረግ የፈተና አስተዳደር ሥራን የበለጠ
ውጤታማ ሊያደርጉ ይችላሉ ብለው ያመኑአቸውን ተጨማሪ አደረጃጀቶችንና ግብረ ኃይሎችን
ማቋቋም ይችላሉ፡፡ ማንኛውንም ያቋቋሙትን አደረጃጀት ወይም ግብረ ኃይል ተግባሩና ኃላፊነቱ በዚህ
ማኑዋል ከተጠቀሱት የአሠራር ስርዓት ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው፡፡

-7-
6.1. የፈተና ማዕከል ግብረኃይል (በዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሚመራ)
የፈተና ማዕከል ግብረ ኃይል ፈተና በሚሰጥበት የፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ አስተዳደራዊ
ሥራዎችን በበላይነት ለመምራት የሚያስችል አደረጃጀት ነው፡፡ ይህ ግብረ ኃይል ከስሩ ከሚቋቋሙት
የተለያዩ ግብረ ኃይሎች የተውጣጡ ከ 5-11 የሚደርሱ አባላት ይኖሩታል፡፡ አደረጃጀቱ
በዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት የሚመራ ሲሆን ከዋና ግቢ ተነጥሎ የሚገኝ ካምፓስ ወይም ኮሌጅ ደረጃ
ሲኖር በከምፓሱ አስተዳደር ዲን የሚመራ ይሆናል፡፡ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ወይም
በትምህርት ሚኒስቴር ለሚወከል አካል ይሆናል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 የፈተና ማዕከሉን (የዩኒቨርሲቲውን/ከምፓሱን/ኮሌጁን) የፈተና ስርዓት የሚመራ የተለያየ
ግብረ ኃይል ያቋቁማል፣ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣
 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር የተማሪዎችን ትራንስፖርት
(የማድረስና የመመለስ) ስራ እና ምደባን በሚመከት በቅርበትና በቅንጅት ይሠራል፤
ይተባበራል፡፡
 እንደአስፈላጊነቱ ከክልል ወይም ከከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ አመራር፣
የክልል/የከተማ አስተዳደር የፍትህ አካላት (ፍርድ ቤቶችና የጸጥታ አስተዳደር አካላት)
እንዲሁም የአከባቢው የመንግስትና የጸጥታ አስተዳደር ጋር ጥምር ግብረ ኃይል ሊያቋቁም፣
ለትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ ተግባርና ኃላፊነት ሊሰጥ ይችላል፡፡
 ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኞች አንባቢ እና የመልስ ወረቀት አደራጅ ይመለምላል
ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያሳውቃል፡፡
 በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ኃይል ስራውን በተመለከተ መረጃ
ይለዋወጣል፤ የፈተናው ሂደት ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ በየቀኑ አፈፃጸሙን
ይገመግማል፣ ይከታተላል፣
 በፈተናው ሂደት ውስጥ የሚገጥሙ ችግሮችን ፈጣን የሆነ ምላሽ በመስጠት ይፈታል፣
 የፈተናውን አፈፃጸም ከግብረ ኃይሉ ጋር በየዕለቱ በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን
እንዲሟሉ ያደርጋል፣
 ለፈተና ጉዳይ የተመደበውን በጀት ከፋይናስ ኃላፊዎችና ባለሙያ ጋር ለሚፈለገውና
ለተፈቀደለት የሰው ኃይል እንዲውል አቅጣጫ ይሰጣል፤ያስተባብራል ይመራል፤
 የፈተና አስተዳደር አፈፃፀሙ ሰላማዊ እና ከፈተና ደንብ መተላለፍ የፀዳ እንዲሆን
ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል.፤ ችግር ሲፈጠር በተዋረድ ሪፖርት ያደርጋል፣ አስፈሊጊውን
እርምጃ በመውሰድ የፈተናው ስራ እንዲቀጥል ያደርጋል፤

-8-
 የፈተና አስተዳደር ማስፈፀሚያ በጀት መነሻ በማድረግ የፈተና አስፈፃሚዎች የክፍያ ሰነድ
በማዘጋጀት ክፍያ ይፈፅማል፣ ሂደቱን በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ሂሳቡን
በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያወራርዳል፤
 ከፈተና አሰጣጥ ስራ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከአገልግሎቱ ይረከባል፣ ምስጥራዊነቱና
ደህንነቱን ባስጠበቀ መልኩ ልዩ ጥበቃ ያስደርጋል፣ ስራው ሲጠናቀቅ ተመላሽ በማድረግ
ለአገልግሎቱ እንዲደርስ ያደርጋል፤
 በቅደመ ፈተና እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ከስራው ጋር በተያያዘ የመፈተኛ ጣቢያዎች
የፈተና አስተዳደር እና ለተፈታኞች ዝግጁ መሆናቸውን በተዋረድ ሱፐርቪዢን በማድረግ
ያረጋግጣል፣ አስፈሊጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ከፈተና ደንብ መተላለፍ ነፃ ሆኖ በሰላማዊ እና በተረጋጋ ሁኔታ
እንዲካሄድ አስፈሊጊውን ሁሉ ያደርጋል፣ ያልተጠበቁ ችግሮች ሲከሰቱ አፊጣኝ ምላሽ
በመስጠት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡

6.2. የተፈታኞች አገልግሎት ግብረ ኃይል (በአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት የሚመራ)


በፈተና ማዕከሉ ደረጃ ተመድበው የመጡ ተፈታኞችንና የአይነ ስውራን ተማሪዎች አጋዦችን
በጾታቸው መሰረት የዶርም፣ የምግብ፣ የጽዳት፣ የጤናና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ
የሚያደርግ ግብረ ኃይል ነው፡፡ ግብረ ኃይሉ በዩንቨርስቲው/በካምፓሱ የአስተዳደርና ልማት
ዘርፍ ምክትል ፕሬዘንዳት የሚመራ ይሆናል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-

 ተፈታኝ ተማሪዎች ግቢ ከመግባታቸው በፊት የመኝታ ክፍሎች፣ አልጋ፣ ፍራሽ፣ ትራስና


የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆናቸውን
ያረጋግጣል፡፡
 ተፈታኞች የህክምና አግልግሎት እንዲያገኙ ያደረጋል፣ አገልግሎቶ በሚጠበቀው ደረጃ
መኖሩን ያረጋግጣል፡፡
 በግቢ ውስጥ የመብራት፣ የሱቆች፣ ሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ ጸጉር ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎች
ኖረው ተፈታኞች እንዲጠቀሙ ያደርጋል፡፡
 ያልተሟሉና ከአቅም በላይ ለሆኑ ችግሮች ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በወቅቱ ሪፖርት
ያቀርባል፣
 በሚሰጠው የተማሪዎች ቁጥር ልክ ለወንድና ለሴት ተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታ
አገልግሎት እንዲያገኙ ድልደላ ያካሂዳል፣
 ተማሪዎች በተመደቡበት የመኝታ ክፍል መገኘታቸውን በየዕለቱ ይቆጣጠራል፣

-9-
 የመኝታ፣ የሻውርና የመጸዳጃ ክፍሎችን የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት ግንዛቤ
ይሰጣል፣ አፋፃጸሙን ይቆጣጠራል፣
 የሰዓት ዕላፊ ገደብ ህግ በማውጣት ያሳውቃል፣ ይከታተላል፣
 ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆነ የማደሪያና መፀዳጃ ቦታዎችን ለይቶ ያዘጋጃል፣
እንደአስፈላጊነቱ ድጋፍ የሚሰጡ ሰዎችን ይመድባል፡፡
 በየኮሌጁ/በየካምፓሱ/ የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየሰዓቱ የቁርስ፣
የምሳና እና የእራት አገልግሎት የተሟላ እንዲሆን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
 የመመገቢያ አደራሾችንና የመመገቢያ ዕቃዎችን ንጽህና እንዲጠበቅ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
 በምግብ አገልግሎት ዙሪያ ሚገጥሙ ችግሮችን ለፕሬዚዳንት ሪፖርት ያቀርባል፣
 በየዕለቱ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች፣ የምግብ ቤት አደራሾችን ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፣
 የሻውር ቤቶችንና መጸዳጃ ክፍሎችን ጽዳት ይከታተላል ይቆጣጠራል፣
 ተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ ድንገተኛ በሽተዎች ለአገልግሎት የሚውሉ መድሀኒቶች
በቅድመ ዝግጅት ወቅት እንዲሟሉ ያደርጋል፣
 የተማሪዎችን ቁጥር የሚመጥን የድንገተኛ ህክምና ክፍሎችን ያዘጋጃል፣
 ለ24 ሰዓት ለሙሉ አገልግሎት አንቡላንሶችን እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
 በተማሪዎች /ክሊኒክ/ጤና ጣቢያ/ ባለሙያዎችን በመመደብ ለ24 ሰዓት የህክምና
አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፤
 መሰረታዊ የሆኑ የውሃና የመብራት አገልግሎቶች በቅድመ ዝግጅት ውስጥ እንዲሟሉ
ያደርጋል፤
 አገልግሎት እንዳይቋረጥ ጀነሬተሮችን፣ የውሃ ታንከሮች ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
 የአገልግሎት መቋረጥ ሲገጥም ፈጣን የሆነ ጥገና በማካሄድ አገልግሎቱን እንዲቀጥል
ያደርጋል፤
 ለተፈታኞች አገልግሎት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በወቅቱ በመለየት እንዲቀርቡ
ያደርጋል፣
 ለፈተና አስጣጡ የሚያስፈልጉ የጽህፈት መሳሪያዎችንና የተለያዩ ግብአቶችን በወቅቱ
እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
 የፈተና አስፈጻሚዎችን ክፍያ በተዘጋጀው መመሪያ የክፍያ ማስፈጸሚያ ተመን
(breakdown) መሰረት አዘጋጅቶ ክፍያ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡ ይከታተላል፣
ይደግፋል፡፡
 የክፍያ ጉዳዮችን ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር በመነጋገር
ያስፈጽማል፣ አቅጣጫ ይሰጣል፣ የሂሳብ ማወራረድ ሂደትን ያስፈጽማል፣

- 10 -
 ከአገልግሎቱ በተላከው የክፍያ ማስፈጸሚያ ተመን ልክ እና መመሪያ መሰረት የመክፈያ
ሰነድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በፈተና ስርዓቱ ሂደት ውስጥ ለተሳተፉ አካላት እና ክፍያ
ለሚመለከታቸው ክፍሎች ክፍያ ይፈጽማል፤
 ክፍያ የተፈጸመበትን የክፍያ ሰነድ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያቀርባል፤

6.3. የፈተና አሰጣጥ ማዕከል ግብረ ኃይል (በአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት የሚመራ)
የፈተና አሰጣጥ ማዕከል ግብረ ኃይል በስሩ የሚገኙ ኮሌጆችንና የትምህርት ክፍሎችን በመጠቀም
ከአንድ በላይ ለሆኑ የፈተና ጣቢያዎች አስተዳደራዊ የሆኑ ድጋፎችን የሚሰጥና የሚያስተባብር
ሲሆን በበላይነት በአካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንት የሚመራ ይሆናል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 በየካምፓሱ ለፈተና ደህንነት ጥበቃ ምቹ የሆኑ የፈተና መከዘኛዎችን ያዘጋጃል፤
 በተመደቡለት የተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ልክ መፈተኛ ክፍሎችን ያዘጋጃል፣ በቂና
ለፈተና ምቹ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 ለፈተና የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮችን፣ ፈታኝ መምህራንና የአይነ ስውራን አንባቢዎችን
በየፈተና ክፍሉ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር በመሆን ይደለድላል፣ ለስራው ውጤታማነት
ይተባበራል፤
 የፈተና ደህንነቱን ለመጠበቅ ከተደራጀው የጸጥታ ሀይል ጋር በመተባበር ይሰራል፣
የፈተና ደንብ ጥሰትን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ይከላከላል፤
 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል በአግባቡ ተፈትሸው እንዲገቡ ያደርጋል፤
 የመልስ ወረቀቶችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን በትምህርት ቤት እና በተፈታኝ
አይነት በተፈታኞች መለያ ቁጥር (Reg. No) ቅደም ተከተል እንዲሰበሰብ፣ ተቆጥሮ
እንዲታሸግና ርክክብ እንዲደረግ ይተባበራል፣
 እንደተማሪዎች ቁጥር መጠን የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችን እንዳስፈላጊነቱ
በአስተባባሪነት እንዲሳተፉ ያደርጋል፣
 የዚህ ግብረ ኃይል አመራርና አባላት በፈተና ወቅት ወደ መፈተኛ ክፍል ከ50 ሜትር
ርቀት ውስጥ መግባትና ወደ ክፍል ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
 የየዕለቱን የፈተና ሂደት የአፈፃጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለፕሬዚዳንት
እንደአስፈላጊነቱም ለአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪፖርት ያቀርባል፣

- 11 -
7. በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የሚቋቋሙ ግብረ ኃይሎች፣ አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት
7.1. የክልል /ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ግብረ ኃይል
በቢሮ ኃላፊ የሚመራ ሆኖ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትሩ ለሚወክለው አካል
ይሆናል፡፡ በዋናነት ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ ክልሉ የፈተና ዘርፍ ዳይሬክተር፣ የክልል
ጸጥታ አካላት፣ የክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ፣ እና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የሚሳተፉ
ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ አባላትንና ከስር በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ የሚቋቋሙ
ንዑስ ግብረ ኃይሎችን የክልሉ ቢሮ ኃላፊ ሊያቋቁም ይችላል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 የክልሉ ተፈታኞች ወደዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉትን ጉዞ ትራንስፖርት ከክልሉ መንግስትና
ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ ያመቻቻል፡፡
 የክልሉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በሚደረገው ምደባ ከትምፈአ እና በክልሉ
ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅርበት ይሠራል፣ ያመቻቻል፣ ይተባበራል፡፡
 የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘር ይመለምላል፣ ለምደባ
ከተሟላ መረጃ ጋር ያስተላልፋል፣ ምደባቸው ሲታወቅም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ
እንዲሄ ጥሪ ያስተላልፋል፣ መሄዳቸውን ይከታተላል፣ ተመድበው ያልሄዱ ሲገኙም
እንደአስፈላጊነቱ እርምጃ ይወስዳል፣ ያስወስዳል፡፡
 የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘር ምልመላ ተገቢውን
አግባብነትና ጥራት ያሟላ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
 ከባለድርሻ አካላት ጋር በፈተና ደህንነት መረጋገጥና ደንብ ጥሰት መከላከል ላይ
ውይይት ያደርጋል፣ ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡
 ጸረ ኩረጃ ንቅናቄ ያደርጋል
 ለተፈታኞችና ለቤተሰቦቻቸው ተገቢውን ገለጻ (Orientation) ይሰጣል፤
 ተፈታኞችን ስለ ፈተና አሰጣጥ፣ ስለተፈቀዱና ስለተከለከሉ ጉዳዮች እንዲሁም
ስለመብትና ግዴታቸው በፈተና ጣቢያቸው በማወያየት ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡና
የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን እና ግብአቶችን አሟልተው እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣
 ተፈታኞችን ወደ ተመደቡበት መፈተኛ ዩኒቨርስቲ ለማድረስ የሚያስችሉ የትርንስፖርት
አማራጮችን እና የተለያዩ ግብአቶችን እንዲሟሉ ያደርጋል፣
 በተወሰነውና በቀረበው የትርንስፖርት አማራጭ መሰረት ተፈታኞችን ወደ መፈተኛ
ዩኒቨርስቲ ከፈተናው ሁለት ቀን በፊት ያደርሳል ፈተናውን ሲጨርሱም ወደ ቤታቸው
እንዲመለሱ ያደርጋል፣
 የፈተና አሰጣጡን ለማሳለጥ በአገልግሎቱና በየኒቨርስቲ ደረጃ ከተቋቋሙ ልዩ ልዩ ግብረ
ኃይሎች ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ይሰጣል፣ይቀበላል፡፡

- 12 -
7.2. በዞን ትምህርት መምሪያ የሚመራ ዞናዊ የፈተና ግብረ ኃይል
በዞን መምሪያ ኃላፊ የሚመራ በዋናነት ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር ተናቦ የሚሰራ ይሆናል፡፡
ተጠሪነቱም ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ነው፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ከክልሉ ጋር በመሆን የጉድኝነት ማዕከል ኃላፊ፣ ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘር ምልመላ አብሮ
ይሰራል፡፡ ምልመላው አግባብነትና ጥራት ያለው እንዲሆን ይሠራል፡፡
 የተፈታኞችን ጉዞ እና መመለሻ ትራንስፖርት ጉዳይን ከክልሉ ጋር ሆኖ ይሰራል፡፡
 ተፈታኞች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲሄዱ ሁኔታዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን
ያመቻቻል
 ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመሄዳቸው በፊት ተገቢውን ኦሬንቴሽን መውሰዳቸውን
ያረጋግጣል፤ እንዲወስዱም ያደርጋል፡፡
 ከክልል ትምህርት ቢሮና ከትምፈአ ጋር አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል፤ ይቀበላል፡፡

7.3. በወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ የሚመራ በወረዳ የፈተና ግብረ ኃይል
በወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሚመራ ሆኖ በዋናነት ከዞኑ ትምህርት መምሪያ ጋር ተናቦ የሚሰራ
ይሆናል፡፡ ተጠሪነቱም ለዞኑ ትምህርት መምሪያ ይሆናል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ከዞኑ ትምህርት መምሪያ ጋር በመሆን የጉድኝነት ማዕከል ኃላፊ፣ ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘር
ምልመላ አብሮ ይሰራል፡፡
 የወረዳውን ተማሪዎች አስተባብሮ ወደፈተና ማዕከል የሚወስድና የሚመልስ አንድ ኃላፊ
ይመድባል፤ መረጃውንም በተዋረድ ያሳውቃል፡፡
 የተፈታኞችን ጉዞ እና መመለሻ ትራንስፖርት ጉዳይን ከክልሉና ከዞኑ ትምህርት መምሪያ
ጋር ሆኖ ይሰራል፡፡
 ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንዲሄዱ ሁኔታዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን
ያመቻቻል፤
 ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመሄዳቸው በፊት ተገቢውን ኦሬንቴሽን መውሰዳቸውን
ያረጋግጣል። እንዲወስዱም ያደርጋል፡፡
 ለአካል ጉዳተኛና ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ተፈታኞች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
ለዚህም ከሚመለከታቸው ጋር አብሮ ይሰራል፤ ለዩኒቨርሲቲ ሲያሰረክብም ለይቶ በአግባቡ
ያሰረክባል፡፡
 ከትምህርት ቢሮና ከዞን ትምህርት መምሪያ ጋር አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣል፣ ይቀበላል፡፡

- 13 -
8. የፌደራል ፖሊስ የፈተና ማዕከላት ግብረ ኃይል (እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ)
ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡትን የፖሊስ አባላትን እንዲያዝ በተመደበ ኃላፊ የሚመራ ይሆናል፡፡
ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊሲ ሆኖ በየፈተና ማዕከላቱ ራሱን በቻለ በአንድ የአመራር ሰንሰለት
የሚኖረው ይሆናል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ መረጃዎችን ለትምህርት ሚኒስቴርም የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ይህ
አደረጃጀት በአንድ የፈተና ጣቢያ ደረጃ ዝቅተኛው ቁጥር 02 ፖሊሲ ሲሆን ከፍተኛው 20 እንዲሆን
ተደርጎ አንድ ፖሊስ ለ150 ተፈታኞች እንዲፈትሽ ተደርጎ የተመደበ ነው፡፡ በአንድ የፈተና ማዕከል
ስር የተፈታኞችን ቁጥር መሰረት በማድረግ ከስድስት እስከ 212 የፌደራል ፖሊስ የተመደበ ቢሆንም
የፀጥታ አካሉ በራሱ ግምገማ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ በልዩ ሁኔታ
እንዲመደብ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለአገልግሎቱ በማሳወቅ ሊመድብ ወይም ያለውንም አሸጋሽጎ
ሊመድብ ይችላል፡፡

በፈተና ስርጭት፣ በፈተና አሰጣጥ እና የመልስ ወረቀት አመላለስ ወቅት የደህንነት ጥበቃ እና እጀባ
የሚያደርግ ኃይል እንደ ጉዞ መስመሩና ተፈታኝ ብዛት የሚመደብ ሆኖ የተለየ የጸጥታ ሥጋት
ያለባቸው ቀጠናዎች ተጨማሪ ኃይልና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የመከላከያ ድጋፍ እንዲያገኙ ይደረጋል።
ለፍተሻ ከማዕከል ከተመደቡት ፌደራል ፖሊሶች በተጨማሪ በዩኒቨርስቲ የሚገኙትንም በአንድ
የአመራር ሰንሰለት ስር ሆነው እንዲሰሩ ያደረጋል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ በዩኒቨርሲቲ በር አካባቢ
የዩኒቨርሲቲ ፖሊሲን ሊጠቀም ይችላል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ማንኛውም ተፈታኝና ፈተና አስፈጻሚ ወደ ፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል ይዞ እንዳይገባና
እንዳይጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን አለመያዙንና አለመጠቀሙን ያረጋግጣል። አስፈላጊውን
እርምጃ ይወስዳል፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝና የፈተና አስፈጻሚ መብቱ እንዲከበርና ግዴታዉን እንዲወጣ
ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር ይሰራል፣ መፈጸማቸውንም ይከታተላል፣ አስፈላጊውን እርምጃ
ወስዳል፣ እንዲወሰድም ያደርጋል።
 ፈተና እና መልስ መስጫ ወረቀቶች የተቀመጡበትን አዳራሽ የ24 ሰዓት ሙሉ ጥበቃ
ያደርጋል፡፡
 የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፡፡
 የፖሊስ አባላት ተገቢውን ዲስፕሊን ጠብቀው እየሠሩ መሆናቸውን ይከታተላል፣
እንደአስፈላጊነቱ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡፡
 ከሌሎች የፈተና አስተዳደር ግብረ ኃይል ጋር መረጃ ይሰጣል፣ ይቀበላል።

- 14 -
 ከማእከል የተመደቡ የፌደራል ፖሊስ አባላት ፈተናውን ከማዕከል ወደ ፈተና መስጫ
ማዕከላት ጊዜያዊ ማከማቻ አዳራሽ ቦታ በማጀብ የማድረስ፣ የመልስ ወረቀቶችን በእጀባ
የመመለስ እና በፈተናው የጥያቄ ወረቀቶችና የመልስ ወረቀቶች ላይ የስርቆት ወይም ጉዳት
የማድረስ ወንጀል እንዳይፈጸም የመከላከል እና የመጠበቅ ግዴታ ይወጣል፣
 በፈተና ማዕከል ደረጃ ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ እና ወደ መፈተኛ ክፍል ሲገቡ
በእጅና በመፈተሻ መሳሪያ (Metallic Detector) በአግባቡ ይፈትሻል፡፡ ስልክን ጨምሮ
ማንኛውን ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው እንዳይገቡ ያደረጋል፣
 ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ለፈተና ጥያቄ ወረቀቶችና በየቀኑ በተፈታኞች
መልስ ለተሰጠባቸው የመልስ መስጫ ወረቀቶች ማስቀመጫ የሚሆን ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ
ክፍል ያዘጋጃል፤ ለክፍሉም የ24 ሰዓት ጥበቃ ያደርጋል፤
 የፈተና ማስቀመጫው ክፍል በሚከፈትበትና በሚዘጋበት ወቅት ሁሉ የፈተና አሰጣጡን ሥራ
ከሚመሩት አካላት ጋር በመሆን የፈተናውን ደህንነት ይቆጣጠራል፤
 የፈተና ጥያቄ ወረቀቶች ወደ መፈተኛ ጣቢያ ሲጓጓዙና ተፈታኞች መልስ የሰጡባቸው
የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ሲጓጓዙ አስፈላጊውን እጀባ ያደርጋል፣
 በፈተና ጣቢያ በመገኘት ከመፈተኛ ክፍል ውጭ /በፈተና ጣቢያ ግቢና በዙሪያው/ ያለውን
ለፈተና አሰጣጡ ሂደት አዋኪ የሆነ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ
ከሆነም ተገቢውን ርምጃ ይወስዳል፤
 ከፈተና ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘሮች የሚቀርቡለትን የደንብ ማስከበር ጥያቄዎች ተቀብሎ
አስፈላጊ ከሆነም የጣቢያ ኃላፊው ጥያቄ ሲያቀርብ ብቻ ወደ መፈተኛ ክፍል በመግባት
ሥርዓት አልበኞችን ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ተገቢውን
እርምጃም ይወስዳል፤ለፈተና ጣቢያ ኃላፊና በፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ለሚሳተፉ የትምህርት
ባለሙያዎች የፈተና አሰጣጡ ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ በፈተና ጣቢያው ግቢም ሆነ ውጭ
አስፈላጊውን ክትትልና የደህንነት ጥበቃ ያደርጋል፤
 የፈተና ጣቢያ ኃላፊው በወሰነው ቦታ በመሆን ተገቢውን ስነ ስርዓት የማስከበር ተግባር
ያከናውናል፡፡ ለልዩ እርዳታ ካልተፈለገ በቀር ወደ መፈተኛ ክፍሎች መግባትና መጠጋት
አጥብቆ የተከለከለ ነው፡፡

- 15 -
9. የፈተና አስፈጻሚዎች (Exam administrators) አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት
የፈተና አስፈጻሚዎች ማለት በቀጥታ ከፈተና አሰጣጡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው የፈተና ሥራ
አመራሮችና ባለሙያዎች የሚመለከት ሲሆን የተፈታኞችን ብዛት መሰረት በማድረግ የሚወሰን
መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አደረጃጀቱ፣ ዓይነቱ፣ ብዛቱ እና ተግባርና ኃላፊነታቸው ተጨባጭ
ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ተፈፃሚ ይሆናል። በዚህ መሰረት እንደሚከተለው ተፈፃሚ ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የፈተና ማዕከል ኃላፊ

የፈተና የጉድኝነት ማዕከል አስተባባሪ

የፈተና ጣቢያ ኃላፊ

ሱፐርቫይዘር

ፈታኝ

9.1. የፈተና ማዕከል ኃላፊ


የፈተና ማዕከል ኃላፊ ተጠሪነቱ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው፡፡ በዋናው የፈተና
ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና ንዑስ ማዕከላት (ካምፓስ ወይም ኮሌጅ) አንድ የፈተና ማዕከል ኃላፊ ከት/ት
ሚኒስቴር፣ ከትምፈአ እና እንደአስፈላጊነቱ ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት የትምህርት የሚመለመልና
በአገልግሎቱ የሚመደብ ሲሆን ከስሩ የተመደቡትን የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችን በሃላፊነት
የሚመራ ሰው ነው፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ለተመደበበት የፈተና ማዕከል ለተደለደሉ ተፈታኞች የሚበቃ ያክል ብዛት ያለው የጥያቄ
ቡክሌት ከነመጠባበቂያው የያዘ፣ በአግባቡ ታሽጎ የተቆለፈ፣ በሸራው ላይ ለመለያነት የተጻፈ

- 16 -
ጽሑፍ ትክክልና ግልጽ ሆኖ የተጻፈ፣ ያልተቆረጠ፣ ያልተበሳ፣ እርጥበት ያልነካውና ያልበሰበሰ
ሸራ (ኮሮጆ) መሆኑን አረጋግጦ ከአገልግሎቱ ይረከባል፡፡
 የተረከባቸውን ፈተና እና የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን ዝርዝሩ ቀድሞ በተሰጠው የጸጥታ
አካላት በማሳጀብና ተገቢው የደህንነት ጥበቃ መደረጉን በማረጋገጥ ወደ ተመደበበት ፈተና
መስጫ ማዕከል በኃላፊነት ያጓጉዛል፣
 ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲደርስም ደህንነቱ ቀድሞ ተፈትሾ በተረጋገጠና የጦር መሳሪያ የታጠቀ በቂ
የሰው ኃይል በቀን የ24 ሰዓት ጥበቃ ለማድረግ በተመደበበት አዳራሽ ውስጥ ፈተናውን
ያስቀምጣል፣ አዳራሹን በራሱ ቆልፎ ቁልፉን ይይዛል፣ ከጥበቃዎቹ ጋር ይፈራረማል፣
 ፈተናው በሚሰጥበት ዕለት የዕለቱን ፈተና እና የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን ለጉድኝት
ማዕከል አስተባባሪዎችና ለጣቢያ ኃላፊዎች ያሰረክባል፡፡
 እንደአስፈላጊነቱ በማዕከሉ የተመደቡ ተፈታኞችንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ታሳቢ በማድረግ
ረዳት በአገልግሎቱ ሊመደብለት ይችላል፡፡
 የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪዎችን ያሰለጥናል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
 በተመደበበት ማዕከል የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ይመራል፡፡
 በፈተና አስተዳደር ዙሪያ ከአገልግሎቱ የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣
ይተገብራል፣ ፈተና አፈጻጸሙን በተመለከተ ለአገልግሎቱ ሪፖርት ያቀርባል፤
 ተፈታኞች በፈተና ማዕከል ቆይታቸው ተገቢውን የምግብ፣ የመኝታ፣ የጤናና መሰል
አገልግሎቶች በትክክክል ስለማግኘታቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
 የፈተና አስፈጻሚዎች በፈተና አሰጣጥ ቆይታቸው ስለሰጡት አገልግሎት የቆይታ እና የሙያ
አገልግሎት ክፍያ በመመሪያው መሰረት እንዲከፈላቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
በቅንጅት ይሰራል፡፡
 የመልስ ወረቀት አሰባስቦ እና በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦ ለአገልግሎቱ ያሰረክባል፣
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ በጽሑፍ ከአገልግሎቱ ይወስዳል፡፡

9.2. የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ


የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ተጠሪነቱ ለፈተና ማዕከል ኃላፊ ነው፡፡ በዋናው የፈተና ማዕከል
(ዩኒቨርሲቲ) እና/ወይም የፈተና ንዑስ ማዕከላት (ካምፓስ/ኮሌጅ) አንድ የፈተና ጉድኝት አስተባባሪ
የሚመደብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የፈተና ማዕከሉ 31 እና በላይ የፈተና ጣቢያዎችን የያዘ ከሆነ
ተጨማሪ በየ31 የፈተና ጠቢያዎች አንድ ተጨማሪ የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ይመለመላል፣
ይመደባል፡፡

- 17 -
ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት በማዕከል ለሚያስተባብራቸው የፈተና ጣቢያዎች የሚያስፈልገውን
ፈተና የያዙ ፖስታዎችና ተዛማጅ ቁሳቁሶች በአግባቡ ከማዕከል ሃላፊው ተረክቦና ደህንነቱ
በተጠበቀ ሁኔታ በየእለቱ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች እንዲሰራጭ ያደርጋል፣
 ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከማዕከል ኃላፊው ጋር ውል ይዋዋላል፣ የፈተና
ሥራን በተመደበበት የጉድኝት ማዕከል (ቦታ) በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
 ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣
 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ፈተናው የተፈታኞችን የመልስ ወረቀት እና ሌሎች ለፈተና
ስራ አገልግሎት የተሰጡ ቁሳቁሶችን ከፈተና ጣቢያዎች በመሰብሰብ ከ ትምፈአ ለተመደበው
የማዕከል ሃላፊ ያስረክባል፣
 ለተመደበበት የጉድኝት ማዕከል ለተደለደሉ ተፈታኞች የሚበቃ ያክል ብቻ ብዛት ያለው
የጥያቄ ቡክሌት የያዘ፣ በአግባቡ የታሸገና የተቆለፈ፣ በሸራው (ኮሮጆ) ላይ ለመለያነት የተጻፈ
ጽሑፍ ትክክል የሆነ ሸራ እንዲሁም ኮሮጆው ያልተቆረጠ፣ ያልተበሳ፣ እርጥበት ያልነካውና
ያልበሰበሰ ሸራ (ኮሮጆ) መሆኑን አረጋግጦ ከማዕከል ኃላፊው ጋር ያደራጃል፡፡
 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች የዕለቱን ፈተና ቡኩሌቶችን የያዘ ሸራና
የመልስ ወረቀት የያዙ ሸራዎችን የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
 ለጣቢያ ኃላፊዎች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ በስሩ ያሉ ጣቢያ ኃላፊዎችን
ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፡፡
 የጣቢያ ኃላፊዎች የመልስ ወረቀት በአግባቡ አደራጅተውና እና አሰባስበው ለማዕከል ኃላፊ
ያሰረከቡ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
 ከማዕከል ኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከማዕከል ኃላፊው በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

9.3. የፈተና ጣቢያ ኃላፊ


የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ተጠሪነቱ ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ነው፡፡ ይህ አደረጃጀት የመፈተኛ
ጣቢያን መሰረት በማድረግ የሚሠራ ሲሆን በአንድ የፈተና ጣቢያ የተመዘገቡ ተፈታኞች በአንድ
የፈተና ጣቢያ የሚፈተኑ ከሆነ አንድ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ እንዲሁም ተፈታኞቹ ብዛታቸው ከፍተኛ
በመሆኑ ወይም የመፈተኛ ጣቢያው የመፈተኛ ክፍሎች አነስተኛ በመሆናቸው ምክንያት ተጨማሪ
የመፈተኛ ጣቢያ በአገልግሎቱ ውሳኔ ሲፈቀድ ጣቢያውን በፈተና ጣቢያ ኃላፊነት የሚመራ ተጨማሪ
አንድ የፈተና ጣቢያ ኃላፊ በድምሩ ሁለት የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ይመለመላል፣ ይመደባል፡፡
የፈተና ጣቢያው የተፈታኝ ብዛት ሰላሳ ስድስት እና ከዚህ በታች ከሆነ የጣቢያ ኃላፊው
የሱፐርቫይዘር እና የፈታኝነት ኃላፊነትን ደርቦ ፈተናውን ያስተዳድራል፡፡

- 18 -
ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ጋር ውል
ይዋዋላል፤ የፈተና ሥራን በተመደበበት የፈተና ጣቢያ በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
 የፈተና አስፈጻሚዎችና የፈተና ጣቢያው ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 ለሱፐርቫይዘሮች፣ ፈታኞች፣ አንባቢዎች፣ መልስ ወረቀት ቆጣሪዎችና ተፈታኞች በፈተና
ጣቢያ ደረጃ አስፈላጊውን የፈተና አሰጣጥ ገለፃ ይሰጣል፣
 በተለያዩ ምክንያቶች አድሚሽን ካርድ ይዘው ባለመምጣታቸው ወደ ፈተና አዳራሽ
እንዳይገቡ ለሚከለከሉ መደበኛ ተፈታኞች ከአገልግሎቱ ከተላከው ዝርዝር ማረጋገጫ
(Master List & Photo Album) ተማሪዎች ስለመሆናቸው ተገቢውን ማረጋገጫ እንዲሰጥ
በማድረግ ወደ ፈተና ክፍል እንዲገቡ ያደርጋል፣
 በጣቢያው ውስጥ ያሉ ተፈታኞችን፣ ፈታኞችን ሱፐርቫይዘሮችንና ፖሊሶችን ያስተባብራል፣
ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ በወቅቱ መፍትሔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ ውሣኔ ይሰጣል፡፡
ከአቅም በላይ ከሆነም ከማዕከል አስተባባሪው ጋር በመነጋገር ወይም ባለው የመገናኛ ዘዴ
በመጠቀም ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ለተከሰተው ችግር አፋጣኝ መፍትሄ
በመስጠት ስለአፈፃፀሙ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የጽሑፍ ሪፖርት
ያቀርባል፤
 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል እንዳይገባ
ያደርጋል፡፡ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል እንዳይወጣ ይቆጣጠራል፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ተፈታኝ ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ የተሰጠውን
የጥያቄ ወረቀት ይዞ እንዲወጣ የማይፈቀድለት ስለሆነ ይህ ተግባራዊ መደረጉን ይቆጣጠራል፤
 የፈተና ወረቀት የሚያሰራጭበትና ሥራውን የሚያከናውንበት አስተማማኝና አመቺ የሆነ
ጊዜያዊ ቢሮ ከፈተና መስጫ ማዕከል ተረክቦ የሚሰራጩና የሚሰባሰቡ የፈተናና የመልስ
መስጫ ወረቀቶች ደህንነትና ምስጢራዊነት እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ በዚህ ረገድ በራሱ
የጥንቃቄ ጉድለት ለሚከሰት ማንኛውም ችግር ኃላፊነት አለበት፡፡ በፈተና ወቅት በአካባቢው
በመንቀሳቀስ እገዛ ለሚሹ ሱፐርቫይዘሮችና ፈታኞች ድጋፍ ይሰጣል፤
 ማናቸውንም ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተጓዳኝነት የሚሞሉ ቅፃቅጾችን በአግባቡ በማስሞላትና
በመሙላት ለማዕከል አስተባባሪው ከመልስ ወረቀት ጋር ያስረክባል፤
 በፈተና አሰጣጥና በልዩ ልዩ የፈተና የሥነ ሥርዓት ጉድለት ከፈተና ስለሚታገዱ ተማሪዎች
በፈታኝና በሱፐርቫይዘር በግልና በቡድን የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግሮች ሪፖርት
ማቅረቢያ ቅጾች ላይ ተሞልተው በሚቀርቡለት ሪፖርቶች መሠረት ውሣኔ ያስተላልፋል፤
 የመልስ ወረቀት ተረካቢዎች የርክክብ ስራውን በአግባቡ መስራታቸውን ይከታተላል፤
በታሸገው ፖስታ ላይም ይፈርማል፤ የታሸጉት ፖስታዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ
እንዲከማቹ ያደርጋል፤

- 19 -
 የኮሌጅ ዲን/ትምህርት ክፍል ኃላፊ ወይም ተወካይ በፈተና አሰጣጥና በመልስ ወረቀት
ርክክብ ወቅት የማህተም፣ የቢሮና የጠቅላላ አገልግሎት ሥራ በመሥራት ለፈተናው ሥራ
መሳካት አስተዋፅኦ እያዲያበረክቱ ያደርጋል፤
 ማየት ለተሳናቸው ተፈታኞች በደንብ ማንበብና መልስ ማጥቆር የሚችሉ ፈታኞችን ወይም
የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ተፈታኞች የተመደቡ ረዳት ጸሐፊዎችን ትክክለኛነታቸውን
አረጋግጦ ይመድባል፡፡ እነዚህ ፈታኞች ጥያቄ በሚያነቡበት ጊዜ ተዘዋውሮ በመመልከት
በትክክል የማያነቡና የማያጠቁሩ ካጋጠመው ወዲያውኑ እንዲለወጡ በማድረግ ሁለተኛ
እንዳይመደቡም ያደርጋል፤
 በፈተና አሰጣጥ ወቅት በቀጥታ በፈተና አሰጣጡ ሂደት ከሚሳተፉ ሰዎች በስተቀር ወደ ፈተና
ጣቢያው ቅጥር ግቢ ወይም መፈተኛ አካባቢ ማንም ሰው እንዳይገባ ያደርጋል፤
 እያንዳንዱን ፈተና በመጀመሪያ ሰዓቱ ያስጀምራል፤ ሰዓቱ ሲያበቃም ተፈታኞች መስራት
እንዲያቆሙ ያስደርጋል፤
 በፈተና ጣቢያ የመልስ ወረቀት ከተቆጠረ፣ ከቀሪ መቆጣጠሪያ ጋር ተገናዝቦ የርክክብ ቅፅ
ከተሞላ በኋላ የመልስ ወረቀቶቹና የስም መቆጣጠሪያው ቅፅ በአንድ ላይ በመልስ ወረቀት
ማሸጊያ ፖስታ ውስጥ ተከተው እንዲታሸጉ ያደርጋል፤ በታሸገው ፖስታ ላይም የየኒቨርሲቲው
ወይም የከምፓሱ ማህተም እንዲያርፍበት ያደርጋል፤
 በፈተና ጣቢያው ውስጥ የተሰራባቸው የመልስ ወረቀቶች በጉዞ ወቅት እንዳይበላሹ ሆነው
መታሸጋቸውን ይቆጣጠራል፤
 የመልስ ወረቀት የያዙ ፖስታዎች የታሸጉበትን ሸራ እና የሸራው ቁልፍ የታሸገበትን ፖስታ
እንዲሁም ባዶ ሸራዎችንና የተረከባቸውን ቁልፎች በሙሉ ለማዕከል አስተባባሪው ወይም
በአግልግሎቱ ለተመደበው የኮማንድ ፖስት ተጠሪ ወይም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች
አግልግሎት መተማመኛ አስፈርሞ ያስረክባል፡፡
 በፈተና መስጫ ግቢ እና ክፍል ውስጥ በፈተና አሰጣጥ ወቅት በተፈታኞች እና በፈተና
አስፈፃሚዎች በግልም ሆነ በቡድን የሚፈጸሙ የፈተና ደንብ መተላለፍ መረጃዎችን በደንብ
መተላለፍ ቅጽ ላይ በማስሞላት ከፈታኝና ሱፐርቫይዘር ጋር ተፈራርሞ ለማዕከል አስተባባሪ
ያሰረክባል።
 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞችን ለፈተና ስራ አገልግሎት የተሰጡ ቁሳቁሶችን
ለማዕከል አስተባባሪ ያስረክባል፣
 በአንድ የፈተና ጣቢያ የተፈታኞች ቁጥር 36 እና በታች ሲሆን ፈታኝና ሱፐርቫይዘር
ሳያስፈልገው ራሱ ይፈትናል፡፡
 በፈተና ጣቢያው የፈተና አስፈጻሚዎችን አሰራር ሂደት ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ
ተፈታኞችን በአግባቡ እንዲፈተኑ ያደርጋል፣ በፈተና አስተዳደር ዙረያ ከማዕከል አስተባባሪው

- 20 -
የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና አፈጻጸሙንም
በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል።
 የጣቢያው ውስጥና ዙሪያው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑን ያረጋግጣል
 ማንኛውም የተከለከሉ ቁሳቁሶች/ዕቃዎች በጣቢያው የሌሉ ወይም ተፈትሸው የተወገዱ መሆኑን
ያረጋግጣል
 ተፈታኞች ወደ ፈተና ጣቢያው ሲገቡ በአግባቡ መፈተሻቸውን ይከታተላል፣ ጉድልት ሲኖር
ለእንዲስተካከል ከሚመለከታቸው ጋር ይሠራል
 ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞች፣ ለአይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢዎች እና መልስ ወረቀት
አደራጆች ስልጠና ይሰጣል፣ ወደ ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
 የመልስ ወረቀት በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦና አሳባስቦ ለጉድኝት ማዕከል ኃላፊ
ያሰረክባል፡፡
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ በጽሑፍ
ይወስዳል፡፡

9.4. ሱፐርቫይዘር
ሱፐርቫይዘር ተጠሪነቱ ለጣቢያ ኃላፊ ነው፡፡ በአንድ የፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍሎችን መሰረት
በማድረግ የሚመደብ ሲሆን አራት የመፈተኛ ክፍሎችን (ፈታኞችን) የሚመራ አንድ ሱፐርቫይዘር
ይመለመላል፣ ይመደባል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ ፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍሎች ከአራት
በታች ከሆኑ ሱፐርቫይዘር መመደብ ሳያስፈልግ በጣቢያ ኃላፊ የሚመሩ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሠረት
የመፈተኛ ክፍሎች ከ4 - 7 ሲሆኑ አንድ ሱፐርቫይዘር፣ የመፈተኛ ክፍሎች ከ8 - 11 ሲሆኑ ሁለት
ሱፐርቫይዘር፣ የመፈተኛ ክፍሎች ከ12 - 15 ሲሆኑ ሶስት ሱፐርቫይዘር በሚል አሰራር ተጨማሪ
ሱፐርቫይዘር እንደአስፈላጊነቱ ይመለመላል፣ ይመደባል።

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ስለ ፈተና አስተዳደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር ውል ይዋዋላል፣ የመፈተኛ
ክፍል ፈታኞች እና አንባቢዎች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 ከጣቢያ ኃላፊው ጋር በመተባበር ፈተናው በሥነ ሥርዓት እንዲከናወን የማድረግ ኃላፊነት
አለበት፤
 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን የፈተና አሰጣጥ መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋል፤
 አንድ ሱፐርቫይዘር በአማካይ 144 ተፈታኞችን ወይም ከአራት ያላነሱ የመፈተኛ ክፍሎች
የመቆጣጠርና የመከታተል ግዴታ አለበት፡፡ ሆኖም እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታና
እንደመፈተኛ ክፍሎችና አዳራሾች የመያዝ አቅምና የመቀራረብ ሁኔታ በአማካይ ከተገለፀው
የተለየ ምደባ ቢካሄድ ምደባውን ይተገብራል፤

- 21 -
 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል እንዳይገባ
ያደርጋል፡፡ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ካልሞላ ተፈታኙ ፈተናውን ሰርቶ ቢያጠናቅቅም
እንዳይወጣ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም ተፈታኝ ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ
ሳይጠናቀቅ የተሰጠውን የጥያቄ ወቀት ይዞ እንዳይወጣ ይቆጣጠራል፤
 ተፈታኞች በሚቀመጡባቸው ዴስኮች መካከል በተቻለ መጠን በቂ ርቀት መኖሩን
ያረጋግጣል፤
 ተፈታኞች ጎን ለጎን ተመሳሳይ የቡኩሌት ኮድ አለመያዛቸውን ያረጋግጣል፡፡
 በፕሮግራሙ መሠረት የተመደበ ሱፐርቫይዘር በተመደበበት ጣቢያ ፈተናው ከመጀመሩ
አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ በመገኘት ሥራውን ያከናውናል፡፡በተጨማሪም የጣቢያ ኃላፊው
ሁሉንም የመልስ ወረቀቶች ተረክቦና አደራጅቶ እስኪጨርስ ድረስ የጣቢያ ኃላፊውን
በመርዳት በጣቢያው መቆየት ይኖርበታል፡፡ በፈተና ሥራ ላይ ያረፈደ ወይም የጣቢያ
ኃላፊው እስኪያሰናብተው በጣቢያው ያልቆየ እንደሆነ በቅርብ ኃላፊ በኩል ለመለመለው
ክፍል የፈፀመው ግድፈት ተገልጾ ተፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድበት ሊያውቅ
ይገባል፡፡
 አንድ ሱፐርቫይዘር ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የተመደበባቸውን ክፍሎች
በማስተባበር ፈታኞችና ተፈታኞች ተግባርና ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣታቸውን በቅርበት
ይቆጣጠራል፤
 በእያንዳንዱ መፈተኛ ክፍል የትምህርቱ የሥም መቆጣጠሪያ በአግባቡ መወሰዱን፣
ተፈታኞችም በሚፈተኑት የት/ዓይነት ቡክሌት ኮድ መሠረት በስም መቆጣጠሪያ ቅፅ ላይ
መፈረማቸውን በማረጋገጥ፣የመልስ ወረቀቶችን ከተፈታኞቹ የምዝገባ ቁጥር አንፃር በትክክል
በማገናዘብና በቅደም ተከተል በማስተካከል፣ ተጓዳኝ ቅፃቅጾች በአግባቡ መሞላታቸውን
በማረጋገጥና ከፈታኞች በመረከብ ለጣቢያ ኃላፊው ያስረክባል፤
 ፈታኝ በተጓደለበት ሁኔታ በፈታኝነት ተመድቦ የሚሰራ ሲሆን ክፍያው ግን በሱፐርቫይዘር
ስሌት ይፈፀምለታል፤
 በተመደበባቸው ክፍሎች በመዘዋወር በተፈታኞች መልስ ወረቀት አናት ላይ ፈታኙ
የመዘገበው የቡክሌት ኮድ ቁጥር ተፈታኙ ከተሰጠው የፈተና ቡክሌት ኮድ ጋር አንድ ዓይነት
መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለበት ፈታኙን በመጠየቅና በማረጋገጥ
ትክክለኛ ሆኖ ሲያገኘው ፈታኙ በመልስ ወረቀቱና በስም መቆጣጠሪያ ቅፁ ላይ በፃፋቸው
ቡክሌት ኮዶች ጐን በፊርማ እንዲያረጋግጥ ያደርጋል፤
 የመፈተን ተግባርና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ፈታኞች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ
ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፤

- 22 -
 የፈተና ሥነ ሥርዓት ጉድለት የፈፀሙ ተፈታኞች ሲያጋጥሙ እንደአስፈላጊነቱ የግል ወይም
የቡድን የተፈታኞች የፈተና ደንብ መተላለፍ ሪፖረት ማቅረቢያ ቅጾችን ከፈታኙ ጋር
በመሙላትና በመፈረም ወዲያውኑ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
 በፈተና አሰጣጥ ሂደት ወቅት ከተፈታኞች በፈታኞች አማካይነት የሚቀርቡለትን ችግሮች
ማስታወሻ ይዞ ለጣቢያ ኃላፊው ያቀርባል፤
 ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በሱፐርቫይዘርነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ስልክ /ሞባይል/
ይዞ ወደ ፈተና ክፍሎች ውስጥ መግባትም ሆነ በአካባቢው መዘዋወር በጥብቅ የተከለከለ
መሆኑን በመገንዘብ ሞባይሉን ሌላ ቦታ አስቀምጦ የመግባት ኃላፊነት አለበት፤
 የሱፐርቫይዘርነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣
ለቆየበት የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ
በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
 የጣቢያ ኃላፈው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡በፈተና አሰተዲደር ዙሪያ
ከጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ማናቸውም የአሰራር ስርዓት ይቀበላል፣ ይተገብራል፣ ፈተና
አፈፃፀሙንም በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባል፤
 መፈተኛ ክፍሎችና ዙሪያቸው ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገላቸው መሆኑን ያረጋግጣል፣
እንዲሆኑም ይሠራል፣
 የተከለከሉ ቁሳቁሶችና መሣሪያዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥና ዙሪያ እንዳይኖሩ
ከሚመለከታቸው ጋር ይሰራል፣ ይከላከላል።
 የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ሲከሰቱም ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ይሰራል፣
ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል።
 ፈተና በሚሰጥበት ዕለት ከጣቢያ ኃላፊ የተረከባቸውን የታሸጉ የዕለቱን ፈተናና የመልስ
ወረቀት የያዙ ፖስታዎችን ለፈታኞች ያሰረክባል፣ ይከታተላል፡፡
 ፈታኞችን፣ አይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢን እና መልስ ወረቀት አደራጆችን ያስተባብራል፣ ወደ
ስራ ያስገባል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
 የመልስ ወረቀት በአግባቡ መደራጀታቸውን አረጋግጦና አሳባስቦ ለመልስ ወረቀት ቆጣሪ
ያሰረክባል፡፡
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

9.5. ፈታኝ
ፈታኝ ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር ነው፡፡ በአንድ የፈተና ጣቢያ ከተመዘገቡ ተፈታኞች ውስጥ ማየት
የሚችሉ (ዓይነ ስውር ተፈታኝ ያልሆኑ) በቁጥር ሰላሳ ስድስት ተፈታኞችን መሰረት በማድረግ
አንድን መፈተኛ ክፍል በፈታኝነት የሚመራ ፈታኝ ይመለመላል፣ ይመደባል፣ ከዚህ በአንፃሩ በአንድ

- 23 -
የፈተና ጣቢያ የተፈታኝ ብዛት 36 እና በታች ሲሆን ለፈተና ጣቢያው ፈታኝ እና ሱፐርቫይዘር
ሳያስፈልገው በፈተና ጣቢያ ኃላፊው ብቻ ፈተናው ይሰጣል፡፡

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ስለፈተና አስተዳደደር ሂደት አጠቃላይ ሁኔታ ከጣቢያ ኃላፊ ጋር ውል ይዋዋላል፣ የፈተና
ሥራን በተመደበበት የፈተና ጣቢያ የመፈተኛ ክፍል በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣
የመፈተኛ ክፍል እና ተፈታኞች ለፈተና ስራ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
 ፈታኙ በሚፈትንባቸው ቀናት ሁሉ ፈተናው ከመጀመሩ አንድ ሰዓት በፊት ለፈተና ጣቢያ
ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፡፡ በሰዓቱ ተገኝቶ ሪፖርት ካላደረገ በቅርብ ኃላፊ በኩል
በሚቀርበው ሪፖርት መሰረት በሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድ ይደረጋል፤
 አንድ ፈታኝ በአማካይ 36 ተፈታኞችን የመቆጣጠርና የመፈተን ግዴታ አለበት፡፡ሆኖም
እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታና እንደ መፈተኛ ክፍሎችና አዳራሾች የመያዝ አቅም
ከአማካኙ የተፈታኝ ቁጥር በላይ ሊፈትን ይችላል፤
 ተፈታኞችን በሚፈተኑበት ክፍል/አዳራሽ በር ላይ በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም ተከተል
በማሰለፍ እና የምዝገባ መታወቂያ /Admission Card/ በማየት መቀመጫ ያስይዛል፡፡
በተጨማሪም መፈተኛ ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ የተፈታኞችን ማንነትና የምዝገባ ቁጥር
ያረጋግጣል፤
 ተፈታኞች በምዝገባ ቁጥራቸው ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጫቸውን ከያዙ በኋላ የመልስ
ወረቀቶችን ያድላል፣ በመልስ ወረቀት ላይ ያሉትን መረጃዎች በትክክል መፃፍና
ማጥቆራቸውን እየተዘዋወረ ይቆጣጠራል፣ በአግባቡ ያልሞሉና ያላጠቆሩ ተፈታኞች ካሉ
እንዲሞሉና እንዲያጠቁሩ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
 ተፈታኞች ከእርሳስ፣ ከላጲስ፣ ከእርሳስ መቅረጫና ከማስመሪያ በስተቀር ሌሎች የተከለከሉ
ነገሮችን ማለትም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ሞባይልና ካልኩሌተር/ የመሳሰሉትን ወደ ፈተና
ክፍል ይዘው እንዳይገቡ ይቆጣጠራል፤
 በመልስ ወረቀቶች ላይ ያለው መረጃ በጥንቃቄ መሞላቱን ካረጋገጠ በኋላ የጥያቄ ወረቀት
የያዙ ፖስታዎችን በተፈታኞች ፊት በመክፈትና የቡክሌት ኮዶችን መሠረት በማድረግ
ወረቀቶችን ለተፈታኞች እንደ አቀማመጣቸው ያድላል፤በትርፍነት የቀሩ የጥያቄ ወረቀቶችን
ወዲያውኑ ሰብስቦ ለሱፐርቫይዘሩ ይሰጣል፤
 የጥያቄ ወረቀት በሚታደልበት ጊዜ ጐን ለጐን እንዲሁም ፊትና ኋላ የተቀመጡ ተፈታኞች
አንድ አይነት ቡክሌት ኮድ እንዳይደርሳቸው ጥንቃቄና ጥብቅ ክትትል ያደርጋል፡፡በመልስ
ወረቀት አናት ላይ በተሰጠው ቦታ ለተፈታኙ የተሰጠውን የፈተና ቡክሌት ኮድ በእስክሪፕቶ
ይጽፋል፤

- 24 -
 የፈተናውን የጥያቄ ቅርጽና ይዘት አስመልክቶ ከተፈታኞች የሚቀርብ ማንኛውንም ጥያቄ
ማስታወሻ ይዞ በሱፐርቫይዘሩ አማካይነት ለጣቢያ ኃላፊ ከማቅረብ ባለፈ ለተፈታኞች
የመሰለውን ማስተካከያ መስጠት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፤
 ማንኛውንም ዓይነት የፈተና ደንብ የተላለፈ ተፈታኝ ሲገጥመው ከሱፐርቫይዘሩ የግል የፈተና
ደንብ መተላለፍ ችግሮች ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፅ በመውሰድ ሞልቶና ፈርሞ ለሱፐርቫይዘሩ
ያቀርባል፡፡ በቡድን የተፈፀመ የፈተና ደንብ መተላለፍ ችግር ሲገጥመው ለዚህ ተብሎ
የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላትና በመፈረም ለሱፐርቫይዘሩ ያቀርባል፤
 የየፈተናውን መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ሰዓት ያስከብራል፤
 እያንዳንዱ ተፈታኝ የተመዘገበበትን የት/ዓይነት ለመፈተኑ በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ቅፅ
(Attendance Sheet) ላይ የጻፈው የምዝገባ ቁጥርና የፈተናው ወረቀት /ቡክሌት/ ኮድ
ትክክለኛነት በተፈታኙ ስምና ፊርማ እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
 በፈተና ወቅት ተፈታኞችን ከመቆጣጠርና የፈተና አሰጣጥ ደንብ ከማስከበር ውጭ በፈተና
ክፍል ወይም አዳራሽ ውስጥ ፈተና ማንበብ ወይም ሌላ ሥራ መሥራት በፍፁም
አይፈቀድም፤
 ተፈታኞች የሚያጋጥማቸው ችግር ሲኖር ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በቅርብ ላለው
ሱፐርቫይዘር ወይም ለጣቢያ ኃላፊው ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል፤
 ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ዘግይተው የሚመጡ ተፈታኞች ወደ ፈተና አዳራሽ
አንዳይገቡ ይከለክላል፡፡ እንዲሁም ፈተናው ከተጀመረ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ተፈታኞች
እንዲወጡ አይፈቅድም፡፡ የመጨረሻው ደወል ከመደወሉ በፈት የሚወጡ ተፈታኞች ካሉ
የፈተና ወረቀቱን ይዘው እንዳይወጡ ያደርጋል፡፡ ለፈተናው ከተፈቀደው ጊዜ በመጨረሻው
15 ደቂቃ ውስጥ መውጣት ስለማይፈቀድ የፈተና ወረቀቶች በሙሉ እስከሚሰበሰቡ ድረስ
ተፈታኞች መልስ መስጫ ወረቀታቸውን ገልብጠው በማስቀመጥ በቦታቸው በፀጥታ
ተቀምጠው እንዲጠብቁ ያደርጋል፤
 ተፈታኞች በፈተና ክፍል ውስጥ ሲጋራ ማጨስና፣ ማስቲካ ማኘክ፣ ቆብ ማድረግ፣ ልብስ
መከናነብ፣ ዕቃ መዋዋስና የመሳሰሉትን ተግባራት እንዳይፈጽሙ ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፤
 በጣቢያ ኃላፊው በታወቀ ምክንያት የጊዜ ገደብ ለውጥ ካልተገለጸ በስተቀር በጥያቄ ወረቀት
የሽፋን ገጽ ላይ ለእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት በተፈቀደው ጊዜ መሠረት ፈተናው
እንዲካሄድ ያደርጋል፤
 ፈተናው ተጀምሮ አስኪጠናቀቅ ድረስ ተፈታኞች የቀራቸውን ጊዜ በየ30 ደቂቃው
ያስታውሳል፤
 ሕጋዊ ምዝገባ አካሂደው ፈተናው ሲሰጥ ያልተገኙ ተፈታኞችን በትክክል በማረጋገጥ የምዝገባ
ቁጥራቸውን በተፈታኞች መቆጣጠሪያ ቅጽ (Attendance Sheet) ግርጌ በተዘጋጀው ቦታ ላይ
ያሰፍራል፤ ፊርማውንም ያኖራል፤

- 25 -
 ፈተናው እንደተጠናቀቀ የመልስ ወረቀቶችን በእያንዳንዱ ቡክሌት ኮድ በመለየትና በምዝገባ
ቁጥር ቅደም ተከተል በማስተካከል፤ በተፈታኞች መቆጣጠሪያ ቅፅ (Attendance Sheet) እና
በስተግርጌ ከተፃፈው የቀሪዎች የምዝገባ ቁጥር ጋር በማገናዘብ ለሱፐርቫይዘሩ ወዲያውኑ
ያስረክባል፤
 ማንኛውም በፈተና ስራ ላይ በፈታኝነት የተሰማራ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ስልክ /ሞባይል/ይዞ
ፈተና ክፍል ውስጥ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ሞባይሉን ሌላ ቦታ
አስቀምጦ የመግባት ኃላፊነት አለበት፤
 የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ሲጠናቀቅ የተፈታኞችን እና ሌሎች ለፈተና ስራ አገልግሎት የተሰጡ
ቁሳቁሶችን ከተፈታኞች በመሰብሰብ ለሱፐርቫይዘር ያስረክባል፣
 የፈታኝነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ ለቆየበት
የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
 መፈተኛ ክፍሉ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑንና ፈተና ለማስፈተን ዕውቅና
የተሰጠው መሆኑኑ አረጋግጦ ይረከባል።
 በህግ ከተፈቀደለት ተፈታኝና ቁሳቁሶች ውጭ ማንኛውም በፈተና ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶች
ወይም መሣሪያዎች ቀድመው በክፍሉ ውስጥ በማንኛውም ቦታ አለመቀመጣቸውን እና
ተፈታኞችም አለመያዛቸውን ያረጋግጣል፣
 መፈተኛ ክፍል የገቡ ተፈታኞች ሁላቸውም አቴንዳንስ መፈረማቸውን እና የፈረሙት
እያንዳንዳቸው የመልስ ወረቀት መመለሳቸውን ያረጋግጣል።
 የመልስ ወረቀት በአግባቡ አደራጅቶ ለሱፐርቫይዘር ያሰረክባል፡፡
 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

9.6. የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ


የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ ተጠሪነቱ ለሱፐርቫይዘር ነው፡፡ በአንድ የፈተና ጣቢያ ለአንድ ዓይነ
ስውር ተፈታኝ አንድ አንባቢ መምህር ይመለመላል፣ ይመደባል፣ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአንድ
የፈተና ጣቢያ የዓይነ ስውር ተፈታኞችን ብዛት መሰረት በማድረግ ለእያንዳንዱ ዓይነ ሰውር ተፈታኝ
አንድ አንድ አንባቢ ይመለመላል፤ ይመደባል፡፡

ከዚህ ውጪ አንድ ተፈታኝ ዓይነ ስውር ሳይሆን የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ያለበት መሆኑ በክልሉ
በኩል በሚቀርብ ደብዳቤ ጥያቄ መሰረት አንድ ረዳት የመልስ ወረቀት ማጥቆር የሚሰራ ፈታኝ
ይመለመላል፣ ይመደባል፣ በዚህ ኃላፊነት የሚመደብ ፈተና አስፈጻሚ እንደማንኛውም ፈታኝ ፈተና
አስፈጻሚ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ርቆ ሊመደብ ይችላል።

- 26 -
ተግባርና ኃላፊነት፡-
 ለአንባቢነት የሚመለመው መምህር ወይም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያ የተፈታኞችን
የግል መረጃዎች (personal information) በከፍተኛ ጥንቃቄ መሙላት ይኖርበታል፤
 አንባቢው የፈተና ጥያቄዎችን ብዛትና የተመደበውን ሰዓት ለፈታኞች ማሳወቅ አለበት፤
 አንባቢው ተፈታኝ ተማሪው ተደግሞ እንዲንበብለት በጠየቀ ጊዜ የተመደበውን ሰዓትና
ቀጣዩን ፈተና ግምት ውስጥ በማስገባት ደጋግሞ ማንበብ ይኖርበታል፤
 አንባቢው አሻሚ የእንግሊዝኛ ድምጽ ያላቸው ቃላት ሲገጥሙ የትርጉም ልዩነት ሊፈጥሩ
ስለሚችሉ የእንዳንዱን ፊደል (spelling) ስም በመጥራት ለተፈታኞች ማንበብ አለበት፤
o ምሣሌ፣
 Rich – Reach
 Beach__ Bitch
 An – Un
 Know–now እና የመሳሰሉትን
 አንባቢው አገልግሎት የሚሰጣው ዓይነ ስውር ተማሪ ተገቢ ባልሆኑ የመፈተኛ ሥፍራ (በረንዳ፣
መተላለፊያ ኮሪደር ወዘተ) ላይ ሆኖ መፈተን እንደሌለበት ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል፤
 በፈተና ስራው የተመደቡበት ኃላፊነት የዓይነ ስውራን ተፈታኞች አንባቢ ከሆነ ተፈታኙ
በሚረዳው አግባብ በእርጋታ እና በትዕግስት ያነባል፣ ከተፈታኙ የተሰጠውን መልስ በመልስ
መስጫ ወረቀት ላይ ያጠቁራል፤
 አንባቢው ተፈታኙ ለእያንዳንዱ የፈተና ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ በከፍተኛ ጥንቃቄ በፈተና
ጥያቄዎቹ ላይ ምልክት እያደረገ ወደ መልስ መስጫ ወረቀቱ መገልበጥ የሚጠበቅበት ሲሆን
ፈተናው እንደተጠናቀቀ በትክክል መልሶቹ መገልበጣቸውን ያረጋግጣል፡፡
 የአንባቢነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ ለቆየበት
የውሎ አበል መፈረሚያ ቅጽ በእስክሪብቶ በትክክል መቀመጡን በማረጋገጥ በተዘጋጀው
መቆጣጠሪያ ላይ የባንክ አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይፈርማል፡፡
 የዓይነ ስውር ተፈታኝ ተማሪ መፈተኛ ቦታ ተገቢው የደህንነት ፍተሻ የተደረገለት መሆኑንና
ፈተና ለማስፈተን ዕውቅና የተሰጠው መሆኑኑ አረጋግጦ ይረከባል።
 የዓይነ ስውር ተፈታኝ በተሰጠው የስም ዝርዝር እና የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ መሠረት
ያስቀምጣል፣
 በህግ ከተፈቀደለት ተፈታኝና ቁሳቁሶች ውጭ ማንኛውም በፈተና ቦታ የተከለከሉ ቁሳቁሶች
ወይም መሣሪያዎች ቀድመው አለመቀመጣቸውን እና ተፈታኙም አለመያዙን ያረጋግጣል፣
 የፈተና መጀመሪያና ማቆሚያ ሰዓትን ይቆጣጠራል።

- 27 -
 በመፈተኛ ቦታ የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ ተከስቶ ሲገኝም በአግባቡ
መዝግቦ ይዞ በተሰጠው ቅጽ መሠረት ሞልቶና ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 ተፈታኙ አቴንዳንስ መፈረሙን እና የመልስ ወረቀት መመለሱን ያረጋግጣል
 መልስ ወረቀቱን ለሱፐርቫይዘር ያሰረክባል፡፡
 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ያከናውናል፡፡
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

9.7. የመልስ ወረቀት ቆጣሪ


የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ተጠሪነቱ ለጣቢ ኃላፊ ነው፡፡ በአንድ የመፈተኛ ጣቢያ በቁጥር እስከ 500
ተፈታኞች ብቻ ካሉ የመልስ ወረቀት ቆጣሪ አይመደብም፣ ሆኖም የተፈታኝ ብዛት ከ 501 - 1000
ሲሆን አንድ ፣ ከ 1001 - 2000 ሲሆን ሁለት፣ ከ 2001 - 3000 ሲሆን ሶስት እያለ በዚህ ስሌት
ይመደባል፣

ተግባርና ኃላፊነት፡-
 በየፈተና ወቅቱ መጨረሻ የመልስ ወረቀቶችን ከሱፐርቫይዘሮች ቆጥሮ ይረከባል፤
 ከፈተና ጣቢያ ኃላፊው፣ ከኮሌጅ ወይም ትምህርት ክፍሉ ተወካይ ጋር በመሆን የመልስ
ወረቀቶችን በየፈተናዎቹ አይነት፣ ኮድና በተፈታኞች የምዝገባ ቁጥር ቅደም ተከተል
በማደራጀት በፖስታ ያሽጋል፤
 በታሸጉት ፖስታዎች ላይ ይፈርማል፣ ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እንዲቀመጡ በማድረግ
ለጣቢያ ኃላፊው እገዛ ያደርጋል፤
 በታሸገው ፖስታ ላይ በተፃፈው ቁጥርና በፖስታው ውስጥ ባለው የመልስ ወረቀት ብዛት
መካከል ልዩነት ከተፈጠረ ተጠያቂ ይሆናል፤
 አንድ መልስ ወረቀት ቆጣሪ እስከ 1000 የመልስ ወረቀቶች በሴሽን ቆጥሮ የመረከብ
ኃላፊነት አለበት፤
 በፈተና ጣቢያው ውስጥ የተሰራባቸውን የመልስ ወረቀቶች የያዙትን ፖስታዎች ውሃ
እንዳያበላሻቸው በላስቲክ ጠቅልሎ በጥንቃቄ በሸራ ከረጢት ውስጥ በመክተት የሸራውን አፍ
በካቦ አስሮ ይቆልፋል፡፡ የተቆለፈበትን ቁልፍም በወረቀት ጠቅልሎ ያሽጋል፤
 የሸራው/ዎቹ ቁልፍ/ቁልፎች በአንድ ፖሰታ ውስጥ ተከተው ፖስታው ይታሸጋል፡፡ ፖስታው
ሊከፈትባቸው በሚችልባቸው ቦታዎች ላይ የት/ቤቱ ማሕተም እንዲመታበት ያደርጋል፤
 የተረካቢነት አገልግሎቱን ለሠራበት ሴሽን በተዘጋጀው መቆጣጠሪያ ላይ ይፈርማል፣ የባንክ
አካውንቱን ትክክለኛነት አረጋግጦ ይሰጣል፡፡
 የጣቢያ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተጨማሪ ስራዎች ያከናውናል፡፡

- 28 -
 የመልስ ወረቀቶችን ተፈታኞች ከፈረሙት የአቴንዳንስ ፊርማ ጋር ያመሳክራል፣ እኩል
መሆናቸውን ቆጥሮ ያረጋግጣል።
 የዓይነ ስውር ተፈታኝ ተማሪ መልስ ወረቀት ይሰበስባል። ያደራጃል።
 የመልስ ወረቀቶች ያልተቀደዱ፣ ያልተቦጨቁ፣ ያልተቆረጡ፣ ያልተበሱ እና እርጥበት
ያልነካቸው መሆናቸውን ያረጋግጣል። እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲከሰትም ለፈታኝ ሪፖርት
ያደርጋል፡፡
 የመልስ ወረቀቶችን ያደራጃል፣ ለፈታኝ ያሰረክባል
 በመፈተኛ ቦታ የፈተና ደንብ ጥሰትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ ተከስቶ ሲገኝም በአግባቡ
መዝግቦ ይዞ በተሰጠው ቅጽ መሠረት ሞልቶና ፈርሞ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 የአግባቡ የተደራጀውንና የተቆጠረውን የመልስ ወረቀትን ለጣቢ ኃላፊ ያሰረክባል
 ሥራውን አጠናቆ ሪፖርት ሲያቀርብ ክሊራንስ ከጣቢያ ኃላፊ በጽሑፍ ይወስዳል፡፡

9.8. የፈተና አስፈፃሚዎች መመልመያ መስፈርት


9.8.1. የመጀመሪያ ድግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው፣ በመምህርነት ወይም
በትምህርት ባለሙያነት ያገለገለ ሆኖ ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪነት 10 ዓመት፣
ለጣቢያ ኃላፊነት 7 ዓመት፣ ለሱፐርቫይዘር 5 ዓመት፣ ለፈታኝነት 01 ዓመት እና
ከዚያ በላይ አገልግሎት ያለው፤
9.8.2. የስራው ባህርይ በሚፈለገው አግባብ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የአካል ብቃት
ያለው፤ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የፈተና ቁሳቁስ ተረክቦ ማስረከብ የሚችል፤
9.8.3. ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ ፤
9.8.4. ቀደም ሲል በፈተና አስፈፃሚነት ሰርቶ የሚያውቅ ከሆነ ምንም ዓይነት የስነ ስርዓት
ደንብ መተላለፍ (ጥፋተኝነት) መረጃ ያልተያዘበት መሆን ይገባዋል ወይም
ማስረጃ/ሪከርድ/ ተይዞበት ከሆነ እንደጥፋቱ ሁኔታ የውሳኔ ወይም የይቅርታ ጊዜ ገደቡ
የተጠናቀቀ መሆን አለበት፤
9.8.5. የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመድበው በየትኛውም የፌዴራል
መንግስት ክልል በሚገኙ የፈተና መስጫ ማዕከል፣ ጣቢያ ወይም መፈተኛ ክፍል
ኃላፊነቱን ተቀብሎ በቦታው በሰዓቱ በመገኘት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፤
9.8.6. በስራው አጋጣሚ የሚያገኛቸውን ምስጥሮች የመጠበቅ እንዲሁም የፈተና ደንብ
መተላለፍ ከመፈፀሙ በፊት ሁኔታውን የሚከላከል፣ ተፈጽሞ ከተገኘም ሁኔታውን
በተዋረድ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ የሚችል፣ ለዚህም በቅርብ ኃሊፊው ወይም
በስራ ባልደረቦቹ ምስክርነት የተሰጠው፤

- 29 -
9.8.7. በስሩ ያለ የፈተና አስፈፃሚዎችን ሰርቶ የማሰራት እና የመምራት ብቃት ያለው
ስለመሆኑ ቅርብ ኃላፊው እና በስራ ባልደረቦቹ ምስክርነት የተሰጠው፣
9.8.8. ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የመልስ መስጫ ወረቀቶችን እንዲሁም የፈተና ቁሳቁስ
ከፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ተረክቦ ለቅርብ ተጠሪው ማስረከብ የሚችልና ፈቃደኛ የሆነ፡፡
9.8.9. ለዓይነ -ስውራን ተፈታኞች በአንባቢነት መምረጫ መስፈርት ከፈታኞች ጋር ተመሳሳይ
ሆኖ ጥሩ የማንበብ ልምድ ያለው፣ ታጋሽ የሆነ፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ቢሆን
ይመረጣል፤
9.8.10. ለዓይነ-ስውራን አንባቢነት ለመመደብ አመልካች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን የተከታተለ
ወይም መሰረታዊ የልዩ ፍላጎት ዕወቀትና ክህሎት ስልጠና የተከታተለ ከሆነ ቅድሚያ
የማግኘት መብት አለው፡፡

- 30 -
ክፍል ሶስት
የፈተና አስፈጻሚዎችና ተፈታኞች መብትና ግዴታ
10. የፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ፤ የተፈቀዱና የተከለከሉ ነገሮች
10.1. የፈተና አስፈጻሚዎች መብት
 ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ ከፈተና አስተዳደር ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ጠይቆ
የመረዳት መብት አለው፡፡
 በህጉ የተፈቀደለትን የውሎ አበልና ሴሽን ክፍያዎችን በወቅቱ የማግኘት መብት
አለው፡፡

10.2. የፈተና አስፈጻሚዎች ግዴታ


 በተመደደበት የፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እንዲገኝ በተወሰነው ሰዓት፣ ቀንና ቦታ
የመገኘትና የተሰጠውን የፈተና አስፈጻሚነት ተግባር የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡
 የፈተና ደንብ ጥሰትን የመከላከል እና ተከስቶም ሲገኝ ፈርሞ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ
አለበት፡፡
 የተፈታኞችን መብት የማክበር
 በፈተና አስፈጻሚነት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ አለበት፡፡
 በተዋረድ የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶችን የመረከብና በአግባቡ አደራጅቶ
የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
 ለፍትህ አካላት በተለይም ለፌዴራል ፖሊስ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
 ተፈታኞች በአግባቡ መፈተሻቸውን፣ የተከለከሉ ነገሮችን አለመያዛቸውንና
አለመጠቀማቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
 ክሊራንስ የመውሰድ ግዴታ አለበት፡፡

10.3. ለፈተና አስፈጻሚዎች የተፈቀዱ ነገሮች


 የማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝንት ማዕከል አስተባባሪ እና ጣቢያ ኃላፊ ፡-
o ስልክ ከመፈተኛ ክፍል ውጪ እንዲይዙና እንዲጠቀሙ
o ቀድሞ ምንም ያልተጻፈበትን ማስተወሻ ደብተር እና አስክርብቶ እንዲጠቀሙ
የተፈቀደ ነው፡፡
 ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ በሐኪም የተፈቀደለትን መነጽር ሊጠቀም ይችላል፡፡

10.4. ለፈተና አስፈጻሚዎች የተከለከሉ ነገሮች


 ማንኛውም ማዕከል ኃላፊ፣ የጉድኝንት ማዕከል ኃላፊ፣ ጣቢያ ኃላፊ፣ ሱፐርቫይዘር፣
ፈታኝ፣ የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ፣ የመልስ ወረቀት ቆጣሪ መፈተኛ እና ሌሎች

- 31 -
የፈተና ግብረ ኃይል አባላት በሙሉ ወደ መፈተኛ ክፍል እና አካባቢ ስልክ፣ ስማርት
ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል
እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን ይዞ መግባት ክልክል ነው፡፡
 ማንኛውም ፈታኝና ሱፐርቫይዘርና የመልስ ወረቀት አደራጅ ማንኛውንም ዓይነት
መጽሐፍ፣ መጽሔት፣ ጋዜጣ፣ በመፈተኛ ክፍል ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ
ነው፡፡
 ማንኛውም ፈታኝና ሱፐርቫይዘርና የመልስ ወረቀት አደራጅ የጆሮ ጌጥ፣ የጸጉር ጌጥ፣
የአንገት ሐብል ወይም ጌጥ፣ የእጅ አምባር፣ የጣት ቀለበት ይዞ መገኘትም ሆነ ማድረግ
የተከለከለ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የጋብቻ ቀለበት የተፈቀደ ነው፡፡
 ማንኛውም ፖሊስ በልዩ ሁኔታ በጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ወይም በጣቢያ ኃላፊ ህግ
ለማስከበር ተጠይቆ ካልሆነ በስተቀረ መፈተኛ ክፍል መግባት የተከለከለ ነው፡፡
 ከፖሊስ በስተቀረ ማንኛውም የፈተና አስፈጻሚ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ፣
ስለት ያለው ወይም ሹል ብረት/ፕላስትክ በፈተና ማዕከል ይዞ መገኘትም ሆነ መጠቀም
የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ፖሊስ (የጸጥታ አካል) በህግ የተፈቀደውን ዓይነት ዩኒፎርም በአግባቡ
ሳይለብስ በፈተና አስፈጻሚነት በፈተና ማዕከል መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ማስቲካ ማኘክ የተከለከለ ነው፡፡

11. የተፈታኞች መብትና ግዴታ


11.1. የተፈታኞች መብት
የተፈታኞች መብቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አለው፡፡
 በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ
የማግኘት መብት አለው፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣
የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ
አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
 የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
 በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ
የማግኘት መብት አለው፡፡
 ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አለው፡፡

- 32 -
11.2. የተፈታኞች ግዴታ
ተፈታኞች የሚከተሉት ግዴታዎች አለባቸው፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት
ግዴታ አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ
ይዞ መገኘት አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ
አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን
መያዝ የለበትም፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት፤
 ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች
የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን
ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት
ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
 ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ
ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

11.3. ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች


ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እና ግቢ ውስጥ እንዲጠቀሙ የተፈቀዱ ነገሮች
የሚከተሉት ናቸው፡፡
 አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበረ ማስተወሻ ደብተር፣
የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
 ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንባች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
 ገንዘብ (ብር)፣
 የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
 የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ
ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

- 33 -
11.4. ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
በፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ
መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ
መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ
/ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ
ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ
የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ
መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣
ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ
ነው፡፡
 ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም
ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣
አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
 ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45
ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት
ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት
የተከለከለ ነው፡፡

- 34 -
ክፍል አራት

የፈተና አስፈጻሚዎች ክፍያ አይነት፣ ተመን እና አፈጻጸም


በክፍል ሁለት በቀረበው የፈተና አስተዳደር አስፈፃሚዎች የኃላፊነት ዓይነት መሰረት የተለያዩ
ክፍያዎች በተለያየ ተመን እና ብዛት ተፈፃሚ የሚሆን ይሆናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክፍያ
ዓይነቶች፣ ተመን እና ብዛት እንደሚከተለው ቀርቧል።

12. የውሎ አበል ክፍያ


አንድ ፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራው ጋር በተያያዘ ከሚኖርበት አካባቢ ርቆ በመሄድ
ስራውን የሚያከናውን ሆኖ ሲገኝ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የቀን ውሎ አበል አከፋፈል መመሪያ
መሰረት የቆይታ ጊዜ፣ የቆይታ ቦታ፣ የደመወዝ መጠን እንዲሁም የበረሃ አበል ተመንን መነሻ
በማድረግ የሙሉ ቀን ወይም / እና የቁርስ እና ምሳ አበል ተሰልቶ የጉዞ ቀናትን ጨምሮ ክፍያ
ይከፈላል፣

13. የአገልግሎት ክፍያ /session payment/


13.1. አንድ የፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራው ጋር በተያያዘ በሚሰጠው ኃላፊነት እና
ስራው ላይ ባለው የተሳትፎ ጊዜ መሰረት በተለያየ ተመን ሴሽን ሂሳብ ተሰልቶ ክፍያ
ይከፈላል፣
13.2. የፈተና ስራው በአንድ ማዕከል ሁሉም ተፈታኞች ተሰባስበው የሚሰጡ በመሆኑ በፈተና
አስፈጻሚዎችና በፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳደር በመሆኑ በቅድመ
ፈተና እና በድህረ ፈተና የሚከናወኑ ተግባራት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት
በአንድ ፈተና አይነት አንድ የነበረው ሴሽን ወደ ሁለት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡
13.3. በቅደመ ፈተና በማዕከል ያለው የፈተና የክዘና ማዕከል አንድ በመሆና ከፍተኛ ቁጥር
ያለው ተፈታኝና ፈተና አስፈጻሚ ስለሚሰመራ አስቀድሞ ገብቶ የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን
መፈጸም ያስፈልጋል፣ በዚህም አንድ የቅደመ ፈተና ሴሽን እንዲያዝለት ይደረጋል፡፡
13.4. የከሰአቱ ፈተና 9፡00 ተጀምሮ የሚጠናቀቀው 12፡00 ላይ በመሆኑ የድህረ ፈተና የመልስ
ወረቀት ቆጠራና ርክክብ ሥራዎችም እስከምሽቱ የሚዘልቁ በመሆናቸው ይህንን ታሳቢ
ያደረገ የሴሽን ክፍያ ስርአት መከተል የግድ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በቅደመ ፈተና፣
ጠዋት፣ ከሰአትና በድህረ ፈተና አራት ሴሽኖች ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ይኖሩታል፣
13.5. የሴሽን ብዛቱም ለዓይነ ስውር ተፈታኞች በአንባቢነት የሚመደብ ፈተና አስፈፃሚ
በአራቱም ቀናት በስራው ላይ ተሳታፊ ከሆነ አስር ሴሽን ተሳቢ የሚደረግለት ሲሆን
ለተፈጥሮ ሳይንስ አስራ አራት እና ለማህበራዊ ሳይንስ ፈተና አስፈጻሚዎች አስራ ሁለት
ሴሽን በሁለቱም ለተሳተፈ ሀያ ስድስት ሴሽን ታሳቢ ተደርጎ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል።

- 35 -
13.6. የክፍያ ተመኑም ባለፉት አመታት ለኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናው ጥቅም
ላይ ሲውል የነበረውን የ250 ብር (ፖሊስ፣ ሹፌር፣ የመልስ ወረቀት ቆጣሪ)፣ 300ብር
(ለፈታኝ፣ ለሱፐርቫይዘርና የፋይናንስ ባለሙያ)፣ 360 ብር(ጣቢያ ኃላፊ፣ የፋይናንስ ኃላፊ)፣
450ብር (የጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ፣ የማዕከል ኃላፊና የዩንቨርስቲ ግብረ ኃይል) እና
460 (የአይነ ሥውር አንባቢ) ብር ክፍያ እንደ ኃላፊነታቸው በተዋረድ የሚከፈል
ይሆናል፡፡

14. የትራንስፖርት ወጪ ክፍያ


አንድ ፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራ ጋር በተያያዘ ከሚኖርበት አካባቢ ርቆ በመሄድ
ስራውን የሚያከናውን ከሆነ በመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ታሪፍ መሰረት ሂሳቡ ተሰልቶ የየብስ
ትራንስፖርት ወጪ ክፍያ ይከፈላል። ለዚህም ፈተና አስፈጻሚው ህጋዊ ደረሰኝ የሚያቀርብ
ይሆናል፡፡

15. የመረጃ ልውውጥ ሞባይል ካርድ ወጪ ክፍያ


አንድ ፈተና አስፈፃሚ ከፈተና አስተዳደር ስራ ጋር በተያያዘ ከሚሰጠው ኃላፊነት አንፃር አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝ ለመረጃ ልውውጥ በተለያየ ተመን የሞባይል ካርድ ወጪ በጀት ይያዝለታል።

16. የተፈታኞች የምግብ አገልግሎት ክፍያ


በተፈታኝ ቁጥር መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ ተፈታኝ በዩኒቨርስቲ ቆይታው ለምግብ አገልግሎት
የሚያስፈልገው ውጪ በእያንዳንዱ ተፈታኝ ቁጥር መሰረት 30 ብር (ሰላሳ ብር) በሚቆይበት ቀን
ተሰልቶ የሚያዝ ይሆናል፡፡

17. የተለያዩ ወጪዎች ክፍያ


ለተፈታኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት (ለሰራተኞች የትርፍ ሰአት ክፍያ) እና ለፈተና
ጣቢያዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብአቶችን ለማሟላት (የጽህፈት መሳሪያ) በፈተና ጣቢያ ደረጃ
በተፈታኝነት የተመዘገቡ ተፈታኞች ብዛት ለአንድ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ በተፈታኝ 50 ብር (ሃምሳ
ብር) ስሌት ተሰልቶ በጀት ይያዝለታል። ዩኒቨርስቲዎች መመሪያውና ህጉ በሚፈቅደው መሰረት
ተጠቅመው የሚያወራርዱ ከሆነ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ ከልተጠቀሙ የሚመልሱ ይሆናል፡፡

ከላይ በዝርዝር የቀረበው የሰው ኃይል ዓይነት እና ብዛት አፈፃፀም እንዲሁም የክፍያዎች ዓይነት እና
ተመን በዚህ ማብራሪያ የመጨረሻ ገጽ በአባሪነት በሰንጠረዥ ቀርቧል።

- 36 -
18. የክፍያ አፈፃፀም፣ ሂሳብ ሰነድ መረጃዎች እና ሂሳብን ማወራረድ አፈፃፀም ሁኔታ
የክፍያ አፈፃፀም ሁኔታ እንደክፍያ ፈፃሚ መስሪያ ቤቱ የውስጥ አሰራር ተፈፃሚ መሆኑ እንደተጠበቀ
ሆኖ የሂሳብ ህጋዊ ሰነዶችን መሰረት በማድረግ ሂሳቡን ያንቀሳቀሰው አካል ክፍያ የፈፀመላቸውን
የፈተና አስፈፃሚዎች የፈተና አስተዳደር ስራው በተጠናቀቀ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሂሳቡን
በማወራረድ ተጠሪ ለሆነበት መስሪያ ቤት ሪፖርት ያቀርባል።

በዚህ መሰረት አገልግሎቱ በማንኛውም ደረጃ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የፈተና አስተዳደር ወጪዎችን
በጥቅል ሂሳብ በማስላት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ሂሳቡን ያስተላልፋል፣ የሚመለከታቸው ተቋማት
ከላይ በተገለፀው አግበብ የተላለፈላቸውን ሂሳብ ከአገልግሎቱ በሚደርሳቸው የአጠቃቀም ሰንጠረዥ
መሰረት በመጠቀም እና ሪፖርት በተቋማቱ ፋይናንስ አስተዳደር በኩል ለገንዘብ ሚኒስቴር በሪፖርት
ያሳውቃሉ። አገልግሎቱ በቀጥታ ክፊያ የሚፈጽምላቸው የፈተና አስፈፃሚዎች ሲኖሩ አገልግሎቱ
ክፍያቸውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በማስተላለፍ ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል፡፡ ሂሳባቸውም
በአገልግሎቱ በኩል የሚወራረድ ይሆናል።

የሂሳብ ሰነዶች ከላይ በተገለፀው አግባብ ክፍያ ለሚከፈልባቸው የክፍያ ርዕሶች ማረጋገጫነት
የሚቀርቡ ህጋዊ ሰነዶች ሲሆኑ በፈተና አስፈፃሚው ሰነድ አቅራቢነት እና በሂሳብ ባለሙያው ሰነድ
ማጣራትና ማረጋገጥ ሂደት ሂሳቡ የሚወራረድ ይሆናል።

19. ማጠቃለያ
ይህ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈታኝና አስፈጻሚ መብትና ግዴታዎችን፣
የተፈቀዱና የተከለከሉ ጉዳዮችን እንዲሁም የሰው ኃይል ዓይነትና ብዛት ለመወሰን እና የክፍያ
አፈፃፀም ተግባራዊ ለማድረግ የሚያገለግል ማንዋል አስፈላጊውን ሂደት አልፎ ተግባራዊ ለማድረግ
የቀረበ ሰነድ በመሆኑ እንደአስፈላጊነቱ ወደፊት ማሻሻያ ሊደረግበት ይችላል። ይህም ማስተካከያ
በደብዳቤ እስካልተገለፀ ድረስ ማንዋሉ ህጋዊ ሰነድ ሆኖ በስራ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ለማስፈጸም ከዚህ በፊት የነበሩ
ማኑዋሎችና ልማዳዊ አሠራሮች በዚህ ሰነድ ላይ በተጠቀሱ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

- 37 -
አባሪ 1፡- ደንብ መተላለፍ ስለመፈፀሙ ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፅ
የተፈታኙ ስም ________________________ መለያ ቁጥር ________________ቀን / / 2015ዓ.ም
የትም/ዓይነት________________ የክ/ደረጃ - 12ኛ የጥፋቱ ዓይነት- በግል_____ በቡድን______
የፈተና ጣቢያ ስም ___________________________ ክልል _____________ ዞን _____________

መለያ በተፈታኞች የሚተገበሩ የጥፋት ዓይነቶች መግለጫ ተ.ቁ ምልክት


1ሀ በስሙና በተሰጠው የምዝገባ ቁጥር ሌላ ሰው ያስፈተነ፣ 1
1ለ በሌላ ሰው ስምና ምዝገባ ቁጥር የተፈተነ፣ 2
1ሐ ከራሱ ፈተና ውጭ ለሌላ ተፈታኝ መልስ የሰራ፣ 3
1መ ፈታኝን የሰደበ፣ የዛተና ለመደብደብ የሞከረ፣ (ፈታኝ ማለት ፈተና ስራ አስፈፃሚዎች ማለት ነው፡፡) 4
1ሠ የሌላን ተፈታኝ የፈተና ወረቀት ወይም የመልስ ወረቀት የቀማ ወይም ለመቀማት የሞከረ፣ 5
በፈተና ክፍል ውስጥ ሌላውን ተፈታኝ ተረጋግቶ ፈተናውን እንዳይሰራ ያወከና ማናቸውንም ዓይነት የኃይል ወይም
1ረ 6
የጉልበት ተግባር በሌላ ተፈታኝ ላይ የፈፀመ፣

1ሰ የፈተና ጥያቄ ወረቀቱን በፈተና ሂደት ወቅት ከፈተና ክፍል ውጭ እንዲወጣ ለማድረግ የሞከረ ወይም ያወጣ፣ 7
ሌሎች ተፈታኞችን በማሳደም የፈተና ክፍሉንም ሆነ የፈተና ጣቢያውን ሰላም በማወክ የፈተናውን ሂደት
1ሸ 8
ለማስተጓጎል የሞከረ፣

1ቀ በፈተና ክፍል ውስጥ ሞባይል ይዞ የተገኘ፣ 9


የመሰናዶ ተፈታኝ ሆኖ ለ 10ኛ ክፍል ሲፈተን የተያዘ ተማሪ የተፈተነው ፈተና ውጤት ከመሰረዙም በተጨማሪ
1በ 10
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እንዲፈተን አይፈቀድለትም፣

1ተ በፈታኙ የሚሰጠውን ምክርና ተግሳፅ ባለመቀበል በአንድ የፈተና ክፍለ ጊዜ ተደጋጋሚ ጥፋቶች የፈፀመ፣ 11
1ቸ ከላይ ከተዘረዘሩት ጥፋቶች እኩል ወይም አቻ የሚሆኑ ሌሎች ጥፋቶችን የፈፀመ፣ (ጥፋቱ በፅሑፍ ይገለፅ) 12
2ሀ መኮራረጅ / ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሆነው ፈተናውን በጋራ መስራት፣ 13
ሆነ ብሎ የፈተና መልስ ሲያስቀዳ / ሲነግር ወይም በብጣሽ ወረቀት ፅፎ ለሌላ ተፈታኝ ሲያስተላልፍ የተገኘ ወይም
2ለ 14
የሰራበትን የፈተና ቡክሌት ለሌላ ሰው ሲሰጥ / ሲቀይር የተገኘ፣

የፈተና መልስ ከሌላ ተፈታኝ ሲቀዳ የተገኘ ወይም መልስ የተፃፈበት ብጣሽ ወረቀት በእጁ የተገኘ ወይም ከሌላ
2ሐ 15
ተፈታኝ መልስ የተሰራበት የፈተና ቡክሌት ሲቀበል የተገኘ፣

ፈታኙ በመልስ ወረቀቱ አናት ላይ የፃፈውን የቡክሌት ኮድ የለወጠ ወይም በአቴንዳንስ ላይ ከተፃፈው ቡክሌት ኮድ
2መ 16
ጋር ሲመሳከር ልዩነት ካሳየ፣
አጫጭር ፎርሙላዎችንና ማስታወሻዎችን በብጥስጣሽ ወረቀቶች ወይም በሌላ መልክ ይዞ በፈተና አዳራሽ ውስጥ
2ሠ 17
የተገኘ፣
2ረ ከውጭ ተሰርቶ የገባ መልስ ተጠቅሞ ፈተናውን የሰራ፣ 18
2ሰ በአንድ የትምህርት ዓይነት ፈተና ሁለት የመልስ ወረቀቶች በአንድ ተፈታኝ ስምና የምዝገባ ቁጥር ተሰርተው ቢገኙ፣ 19
2ሸ የፈተና መልስ መስጫ ወረቀቱን ሆነ ብሎ ያበላሸ፣ የቀደደ፣ 20
2ቀ ተፈታኞች ወደ ፈተና አዳራሽ ይዘው መግባት ከተፈቀዳላቸው መሳሪያዎች ውጭ ይዞ መግባት፣ 21
ስካርቭ፣ ባርኔጣ/ቆብ፣ ሻሽና የመሳሰሉትን አድርጎ/ለብሶ ወደ ፈተና አዳራሽ መግባት በፍፁም የተከለከለ ነው፡፡ይሁንና
2በ 22
በኃይማኖታዊና በባህላዊ ህጎች አስገዳጅነት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሙሉ የፊት ገፅታንና ጆሮዎች ያልሸፈነ
2ተ ከላይ ከተዘረዘሩት ጥፋቶች አቻ ወይም እኩል የሆኑ ሌሎች ጥፋቶችን የፈፀመ፣ (ጥፋቱ በፅሑፍ ይገለፅ) 23
ለሌላ ሰው ሲፈተን የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በህግ አግባብ የሚጠየቅ ከመሆኑ በተጨማሪ በማንኛውም ደረጃ
2ቸ 24
በመማር ላይ ያለ ከሆነ ለአንድ ዓመት ከትምህርቱ ይታገዳል፡፡

ፈታኝ ___________________ ሱፐርቫይዘር _________________ ጣቢያ ኃላፊ __________________

- 38 -
አባሪ 2፡- የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ ዝርዝር መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ
የ---------------------------ዩንቨርስቲ/ክልል ፈተና አስፈጻሚዎች መመልመያ ቅጽ

ለፈተና
የአስፈጻሚዎች የአስፈጻሚዎች ሙሉ አስፈጻሚነት የሚሰሩበት የትውልድ አድራሻ ሰልክ የንግድ ባንክ ኢሜል
ተቁ ምርምራ
ሙሉ ስም በአማርኛ ስም በእንግሊዝኛ የተመደቡበት ተቋም ቁጥር ሂሳብ ቁጥር አድራሻ
ኃላፊነት
ክልል ዞን ወረዳ

ማስታወሻ :- ሁሉም መረጃዎች በExcel ተሰርተው በሶፍት ኮፒ መላክ አለባቸው፡፡

- 39 -
አባሪ 3፡- የፈተና አስፈጻሚዎች ምደባ ማጠቃለያ ቅጽ

የ_________________________________ ዩኒቨርስቲ / ክልል ፈተና አስፈጻሚዎች የምደባ ቅጽ

የአስፈጻሚዎች የአስፈጻሚዎ የምደባ አድራሻ


ሙሉ ስም ች ሙሉ ስም የተመደቡበት የተመደቡበት የንግድ ባንክ ሂሳብ ኢሜል
ተቁ በአማርኛ በእንግሊዝኛ ዩኒቨርስቲ ክልል ዞን ወረዳ ሃላፊነት ቦታ ሰልክ ቁጥር ቁጥር አድራሻ ምርምራ

ማስታወሻ :- ሁሉም መረጃዎች በExcel ተሰርተው በሶፍት ኮፒ መላክ አለባቸው፡፡

- 40 -
አባሪ 4፡- የፈተና እስፈጻሚዎች ክፍያ አፈጻጸም ማጣቃለያ ስንጠረዥ
የፈተና አስፈፃሚዎች አጠቃላይ መረጃ የውሎ አበል ክፍያ ተመን እና ቆይታ ጊዜ የሴሽን ክፍያ

የሰው ኃይል ቆይታ ቆይታ


ተ.ቁ ሴሽን ብዛት
ግብዓት የፈተና አስፈፃሚ ምደባ እና ተመን - ለማህበራዊ ሳይንስ ለተፈጥሮ ሳይንስ
የፈተና አስፈፃሚ ኃላፊነት
ምንጭ ብዛት በሲቪል ሰርቪስ ተመን
(መጠሪያ ስያሜ) ማህበራዊ ተፈጥሮ
(አቅራቢ (ልዩ መግለጫ) መመሪያ መስክ ከተማ መስክ ከተማ
ሳይንስ ሳይንስ
ተቋም)
በአንድ መፈተኛ ክፍል
የተፈታኝ ቁጥር 36 ከሆነ
ፈታኝ - ዓይነ ስውራን ላልሆኑ አንድ ፈታኝ፣ ከ 36 ካለፈ
1 ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ 11.35 11*0.35 12.35 12*0.35 300.00 12 14
ተፈታኞች የሚያገለግል የተፈታኞች ብዛት እኩል
እየተከፈለ አንድ አንድ
ፈታኝ ይመደባል፣
ለአንድ ዓይነ ስውር
ተፈታኝ አንድ አንባቢ እና
የዓይነ ስውር ተፈታኝ አንባቢ
ለአንድ የእጅ እንቅስቃሴ
2 እና የእጅ እንቅስቃሴ ችግር ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ 11.35 11*0.35 12.35 12*0.35 460.00 10 የለውም
ችግር ያለበት ተፈታኝ
ያለበት ተፈታኝ ረዳት ፀሐፊ
አንድ ረዳት ፀሐፊ
ይመደባል፣

የመፈተኛ ክፍል ከ 2 - 5
ከክልል 2ኛ
ከሆነ 1 ፣ ከ 6 - 10 ከሆነ 2
3 ሱፐርቫይዘር ደረጃ ት/ቤት በከፍተኛ 12.35 12*0.35 13.35 13*0.35 300.00 12 14
፣ ከ 11 - 14 ከሆነ 3 በሚል
መምህራን
አሰራር ይመደባል፣

የተፈታኝ ብዛት 1000 ከሆነ


ከክልል 2ኛ አንድ፣ ከ 1001 - 2000
4 ፈተና ጣቢያ ኃላፊ ደረጃ ት/ቤት ከሆነ ሁለት፣ ከ 2001 - በከፍተኛ 13.35 13*0.35 14.35 14*0.35 360.00 12 14
መምህራን 3000 ድረስ ከሆነ ሶስት
በሚል አሰራር ይመደባል፣

- 41 -
የፈተና አስፈፃሚዎች አጠቃላይ መረጃ የውሎ አበል ክፍያ ተመን እና ቆይታ ጊዜ የሴሽን ክፍያ

የሰው ኃይል ቆይታ ቆይታ


ተ.ቁ ሴሽን ብዛት
ግብዓት የፈተና አስፈፃሚ ምደባ እና ተመን - ለማህበራዊ ሳይንስ ለተፈጥሮ ሳይንስ
የፈተና አስፈፃሚ ኃላፊነት
ምንጭ ብዛት በሲቪል ሰርቪስ ተመን
(መጠሪያ ስያሜ) ማህበራዊ ተፈጥሮ
(አቅራቢ (ልዩ መግለጫ) መመሪያ መስክ ከተማ መስክ ከተማ
ሳይንስ ሳይንስ
ተቋም)
የተፈታኝ ብዛት 1000 ከሆነ
አንድ፣ ከ 1001 - 2000
5 የመልስ ወረቀት ቆጣሪ ከዩኒቨርሲቲ ከሆነ ሁለት፣ ከ 2001 - በመካከለኛ የለውም የለውም የለውም የለውም 250.00 12 14
3000 ድረስ ከሆነ ሶስት
በሚል አሰራር ይመደባል፣
ከፌደራል
ፖሊስ
የፈተና ኮሮጆ ስርጭት አጃቢ፣ በጉዞ መስመር ደረጃ አራት
6 ኮሚሽን በመካከለኛ 13.35 13*0.35 13.35 13*0.35 250.00 12 14
ጥበቃና ፈታሽ ፖሊስ ይመደባል፣
(መነሻ አዲስ
አበባ የሆነ)
በማዕክል ደረጃ አንድ ሆኖ፣
ከትምፈአ
የፈተና ጣቢያው ሲበዛ ንዑስ
እና
7 የፈተና ማዕከል ኃላፊ የፈተና ማዕከል በማደራጀት በከፍተኛ 18.35 18*0.35 18.35 18*0.35 450.00 12 14
ከትምህርት
አንድ ማዕከል አስተባባሪ
ሚኒስቴር
ይመደባል፣

ከክልል 2ኛ
የፈተና ጉድኝት ማዕከል በ31 የፈተና ጣቢያ አንድ
8 ደረጃ ት/ቤት በመካከለኛ 13.35 13*0.35 18.35 18*0.35 450.00 12 14
አስተባባሪ ይመደባል
መምህራን

በዩኒቨርሲቲ/ከምፓስ ደረጃ
12 የፈተና ማዕከል ግብረ ኃይል ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ የለውም የለውም የለውም የለውም 450.00 12 14
አንድ ይመደባል፣

- 42 -
የፈተና አስፈፃሚዎች አጠቃላይ መረጃ የውሎ አበል ክፍያ ተመን እና ቆይታ ጊዜ የሴሽን ክፍያ

የሰው ኃይል ቆይታ ቆይታ


ተ.ቁ ሴሽን ብዛት
ግብዓት የፈተና አስፈፃሚ ምደባ እና ተመን - ለማህበራዊ ሳይንስ ለተፈጥሮ ሳይንስ
የፈተና አስፈፃሚ ኃላፊነት
ምንጭ ብዛት በሲቪል ሰርቪስ ተመን
(መጠሪያ ስያሜ) ማህበራዊ ተፈጥሮ
(አቅራቢ (ልዩ መግለጫ) መመሪያ መስክ ከተማ መስክ ከተማ
ሳይንስ ሳይንስ
ተቋም)
በክልልና በዞን ፈተና ክፍል
ኃላፊነት ተመደበው
13 የክልል/ዞን ፈተና ጉዳይ ፈጻሚ ክልል/ዞን ከአገልግሎቱ ጋር በመስራት የለውም 450 6 7
ላይ የሚገኙ አንድ አንድ
ባለሙያዎች
በወረዳ ደረጃ አንድ የፈተና
ጉዳይ ተመድቦ ተፈታኞችን
14 የወረዳ ፈተና ጉዳይ ፈጻሚዎች ወረዳ ወደ ተመደቡበት ዩንቨርስቲ ከፍተኛ 11.35 11*0.35 12.35 12*0.35 360 6 7
በማድረስና በመመለስ
የሚሳተፍ

በዩኒቨርስቲ/ካምፓስ ደረጃ
15 የፋይናንስ ኃላፊ ዩኒቨርስቲ አንድ የፋይናንስ ኃላፊ የለውም 360 12 14
ይመደባል

በዩንቨርሰረቲ/ካምፓስ ደረጃ
የፈተና አስፈጻሚዎችን
16 አካውንታት ዩኒቨርስቲ ብዛት መሰረት በማድረግ የለውም 300 12 14
ከ3-7 የሚደርሱ የፋይናንስ
ባለሙያዎች ይመደባሉ

- 43 -
የፈተና አስፈፃሚዎች አጠቃላይ መረጃ የውሎ አበል ክፍያ ተመን እና ቆይታ ጊዜ የሴሽን ክፍያ

የሰው ኃይል ቆይታ ቆይታ


ተ.ቁ ሴሽን ብዛት
ግብዓት የፈተና አስፈፃሚ ምደባ እና ተመን - ለማህበራዊ ሳይንስ ለተፈጥሮ ሳይንስ
የፈተና አስፈፃሚ ኃላፊነት
ምንጭ ብዛት በሲቪል ሰርቪስ ተመን
(መጠሪያ ስያሜ) ማህበራዊ ተፈጥሮ
(አቅራቢ (ልዩ መግለጫ) መመሪያ መስክ ከተማ መስክ ከተማ
ሳይንስ ሳይንስ
ተቋም)

1. የሞባይል ካርድ ወጪ - ለፈተና ጣቢያ ኃላፊ ብር 200.00 ፣ ለጉድኝት ማዕከል አስተባባሪ ብር 300.00 ብር ለማዕክል ኃላፊ 500 ብር
ይከፈላል።

2. የፈተና ሽራ ጫኝና አውራጅ ሰራተኛ _ በካምፓስ ደረጃ ፈተናው ተጭኖ ሲሄድ ከመኪና የማውረድ፣ ወደ ክዝና ቦታ የማስገባት፣ በፈተና
ማስታወሻ
15 አስጣጥ ቅደመ ተከተሉ መሰረት የመደርደር፣ ፈተና በሚሰጥበት ዕለት በየፈተና ጣቢያው በትኖ የማዘጋጀት እና ወደ መፈተኛ ክፍል
ልዩ ልዩ ወጪዎች
የማድረስ/የመጫን ተግባራትን ጨምሮ የሚሰራ ሲሆን ለጫኝና አውራጅ ከተያዘው በጀት የሚከፈል ይሆናል፡፡

3. የትርፍ ሰዓት አገልግሎት ክፍያ፣ ለጽህፍት መሳሪያ፣ የነዳጅ እና ለመሳሰሉት ወጪዎች በተፈታኝ 50 ብር ለአንድ ጊዜ ከተያዘው በጀት
በ12.6 መሠረት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለሚያጋጥሙ ወጪዎች አግባብነት ያለው ሰነድ እየቀረበ እና እየተፈቀደ ክፍያ ተፈጻሚ ይሆናል።

- 44 -
አባሪ 5፡- የመንግስት ሠራተኞች ውሎ አበል ክፍያ ማወራረጃ - ቅፅ - 2

1/ የመስሪያ ቤቱ ስም - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

2/ ፕሮግራም / የስራ ሂደት - የ 2014ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና


የሠራተኛ ስም - 4/ ደመወዝ መጠን
3/ _______________________ _______ 5/ የመጓጓዣ ዓይነት _________

6/ የውሎ አበል አከፋፈል ስሌት መግለጫ ሠንጠረዥ

ሀ/ ሠራተኛው በጉዞ ላይ የቆየበት ቦታዎች ( ለቁርስ ፣ ለምሳ ፣ ለእራት ) መግለጫ ሠንጠረዥ


የደረሰበት ቦታ
መነሻ ( የክልል፣ የዞን / የወረዳ ከተማ በፋይናንስ ብቻ የሚሞላ
ስም)
ተ.ቁ
ውሎ
የቀን የአየር ፀባይ
ቦታ ቀን ሰዓት ቁርስ ምሳ እራት አበል ድምር
ብዛት አበል
መጠን

ለ/ ሠራተኛው ለስራ የቆየባቸው ቦታዎች መግለጫ ሠንጠረዥ

ለስራ የታደረበት ቦታ በፋይናንስ ብቻ የሚሞላ


ተ.ቁ ቀን ( የክልል፣ የዞን ወይም የወረዳ)
የቀን የውሎ
ከተማ ስም የበረሃ አበል ድምር
ብዛት አበል

ሐ/ አጠቃላይ የውሎ አበል እና የነዳጅ ክፍያ ማጠቃለያ ሠንጠረዥ


ቅድሚያ የተከፈለ የገንዘብ ተመላሽ ድምር /
ተ.ቁ የክፍያ ዓይነት ተጨማሪ ክፍያ
መጠን የሚደረግ ልዩነት

1 የውሎ አበል

2 የነዳጅ

3 የጉልበት ሰራተኛ

4 ሌላ

ጠቅላላ ወጪ

የሠራተኛው ስም _________________________ ሂሳቡን ያዘጋጀው ሠራተኛ ስም ____________________

ፊርማ _____ ቀን / / 2015ዓ.ም ፊርማ ______ ቀን / / 2015ዓ.ም

ያረጋገጠው ኃላፊ ስም ___________________ ሂሳቡን ያረጋገጠው ኃላፊ ስም ____________________

ፊርማ _________ቀን / / 2015ዓ.ም


ፊርማ ______ ቀን / / 2015 ዓ.ም
አባሪ 6፡-የፈተና አስፈፃሚዎች የውሎ አበል እና የትራንስፖርት ክፍያ መፈፀሚያ ቅጽ

ማስታወሻ 1. ለአንድ ተከፋይ የሚፈፀም ማንኛውም ክፍያ በዚህ ገፅ ላይ ዓምድ ካለው በአንድ መስመር ላይ ማለቅ አለበት፣

ማስታወሻ 2. በውሎ አበል መቆጣጠሪያ ላይ ባለው ቀን ልክ የሚከፈለው ክፍያ በዚህ ቅጽ ላይ መፈረም አለበት፡፡

የተመለሰበ ተቀባ
የተነሳበት ተከፋይ ገንዘብ
ት የቆየበት ይ
ተ. የተሳታ የሚሰራበት መስሪያ የቀን
ቀን ፊርማ
ቁ ፊ ስም ቤት ስም አበል ቀ ሰዓ ቀ አበ ትራንስፖር ድም
ሰዓት ብዛት እና
ን ት ን ል ት ር
ስም

የከፋይ ስም ፊርማ ቀን / / 2015 ዓ.ም

-1-
አባሪ 7፡- የፈተና አስፈፃሚዎች የአገልግሎት (ሴሽን) ማስፈረሚያ ቅጽ

የፈተና ጣቢያ ስም ፡- __________________________________

ተ.ቁ የፈተና አስፈጻሚ ሙሉ ሥም ለፈተና ሥራ የፈተና ወቅት የፈተና ቀናት ሴሽን


የተሰጠው ኃላፊነት ብዛት
ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና
ቅድመ ፈተና
ጠዋት
ከሰአት
ድህረ ፈተና

የጣቢያ ኃላፊ ስም _______________________ፊርማ ቀን / /2015 ዓ.ም

-2-
አባሪ 8፡- የፈተና አስፈፃሚዎች የአገልግሎት (ሴሽን) ክፍያ መፈፀሚያ ቅጽ
የሴሽን ክፍያ ክፍያ ተቀባይ
የተሳታፊ የሚሰራበት መስሪያ ለፈተና ሥራ የሠራበት
ተ.ቁ ያልተጣራ ግብር የተጣራ ተሳታፊ ፊርማ እና
ስም ቤት ስም የተሰጠው ኃላፊነት የሴሽን ብዛት በነጠላ
ክፍያ ተቆራጭ ክፍያ ስም

TOTAL

የከፋይ ስም ----------------------------------------------ፊርማ ቀን / /2015 ዓ.ም

-3-
አባሪ 9፡- ደረሰኝ ለማይገኝላቸው ወጪዎች የሚከፈል ክፍያ መመዝገቢያ እና ማስተላለፊያ ቅፅ
ተ.ቁ ክፍያ የተፈፀመበት የተከፈለ ገንዘብ ክፍያ የተፈፀመለት ሰው
ቀን ቦታ ምክንያት ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

ብር ሣ ብር ሣ ስም ፊርማ
1

2
3

ጠቅላላ ድምር

የሠራተኛው ስም _______________ ፊርማ _________ ቀን / / 2015 ዓ.ም

-4-

You might also like