Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 7

የቢዝነስ እቅድ

የ ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ

የንግድ ድርጅቱ ስም: ሔርሜላ ጀነራል ትሬዲንግ

አድራሻ: ሀዋሳ ታቦር መካነ እየሱስ


ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ገነት የገበያ አዳራሽ

ስልክ: 0935592614

አጭር መግለጫ
ይህ የቢዝነስ እቅድ የተዘጋጀው በሀዋሳ ከተማ ታቦር መካነ እየሱስ ፊትለፊት ገነት የገበያ
አዳራሽ ለሚገኘው ሔርሜላ ጀነራል ትሬዲንግ የማስፋፊያ ዕቅድነው .

ድርጅታችን ሔርሜላ ትሬዲንግ በ 10/11//2015 የተቋቋመ ሲሆን በኤልክትሮኒክ ሽያጭ


ገበያ ለይ ያለውን ክፍተት በመመልከት እና ስራው አዋጭ መሆኑን በመገንዘብ ለስራ አመቺ እና
ጥሩ የሚባል የገበያ እንቅስቃሴ ባለበት በሀዋሳ ከተማ ታቦር መካነ እየሱስ ፊትለፊት ገነት የገበያ
አዳራሽ የተለያዩ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማምጣት ለገበያ በማቅረብ ለይ እንገኛለን

በ ብር 1,000,000 የመነሻ ካፒታል የተጀመረ ቢዝነስ ሲሆን ለቴሌቪዥን እና


ለማቀዝቀዣ(ፍሪጅ)ብቻ 500,000 ብር እንዲሁም ለሌሎች በርከት ላሉ የኤሌክትሮኒክስ
እቃዎች ማለትም ለተለያዩ የፍራፍሬ መጭመቂያዎች,የቡና የቅመም እና የሽንኩርት
መፍጫዎች, በጥራት እና በውበት የተመረቱ የግድግዳ ለይ ሰዓቶች,self clean ያላቸው
ዘመናዊ የልብስ ካውያዎች, ከትልቅ እስከ ትንሽ የማብሰያ እና የመጋገሪያ ኦቨን እንዲሁም
ሌሎች የተለያዩ አይነቶች በተጨማሪም 200,000 ብር የተለያዩ የቤት እና የኩሽና
መገልገያዎችን በመያዝ የተመሰረተ ድርጅት ነው

ድርጅታችን ለመሸጫ ቦታ ማሳደሻ እና ለመደርደሪያ ፈርኒቸር ብቻ 195,000 ብር ተጨማሪ


በመበጀት የተቋቋመ ነው

በአሁን ለይ ደግሞ በሳምንት እስከ 20,000 ብር ሳምንታዊ ገቢ ያለን ሲሆን ከዚህም ገቢያችን
ለይ 40% ትርፍ እናገኛለን

በተጨማሪም በሶሻል ሚድያ ሽያጭ እስከ 10,000 ብር ሳምንታዊ ገቢ ያለን ሲሆን ይህንንም
ዘመናዊ የመሸጫ ዘዴ በመጠቀም እስከ አዲስ አበበ ድረስ የዴሊቨሪ ስራም እንሰራለን

በወር ውስጥ ከአንድ እስከ ሁለት ግዜም እቃ እናስገባለን

ድርጅታችን በስሩ አንድ ሰራተኛን በ 2000 ብር ቀጥሮ የሚሰራ ነው

በአጠቃለይ በወር እስከ 110,000 ብር ድረስ ገቢ እናስገባለን

ከጠቅላላ ገቢያችን ለይ የቦታ ኪራይ 12,000 በወር

የስራ ማስኬጃ 40,000

የሰራተኛ ደሞዝ 2000


እንዲሁም ለዴሊቨሪ አገልግሎት እና ለጫኝ አውራጅ 8000 ብር እናወጣለን እነዚህ ቋሚ
ወጪዎቻችን ሲሆኑ ለተለያዩ የደንበኛ አገልግሎቶች በወር እስከ 2000 ድረስ እናወጣለን

በአጠቃላይም ድርጅታችን በወር 44,000 ያህል ከወጪ ቀሪ ያገኛል

በዚህም ሂደታችን እስከ 200,000 ብር ተቀማጭ ያለን ሲሆን አሁን ደግሞ የማስፋፊያ እቅድ
ይዘናል

ይሄም የማስፋፊያ እቅድ ወደ ከፍታ እንደሚወስደን እናምናለን


የአገልግሎቱ መግለጫ
ጥራት ያላቸው ኤሌክትሮኒክስ እና የቤት ውስጥ እቃዎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው መሆኑ ይታወቃል
ስለዚህም የተለያዩ ሀገራት ምርቶችን ይዘን ቀርበናል።

ለምንሸጣቸው እያንዳንዱ እቃ ሀላፊነት የምንወስድ መሆኑ ደግሞ በደንበኞች ተመራጭ ያደርገናል።

የገበያ ፉክክር
እንደሚታወቀው ላለፈው አንድ አመት እቃዎችን በማምጣት ለተጠቃሚ እያቀረብን እንገኛለን

በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶችም ቢሆን የተሻለ ሽያጭ እያስመዘገብን ነው ከዎጋ ረገድም
ተመጣጣኝ በመሆኑ የደንበኞት ምርጫ ለመሆን ችለናል ለዚህም በአካል እና በሶሻል ሚድያ የሚገዙን ሰዎች
የሚሰጡን ምላሽ ምስክር ሊሆን ይችላል

የገበያ ስልት
የኤሌክትሮኒክስ እና የቤት ውስጥ እቃዎች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ይታወቃል ይህንንም በሁለት አይነት
መንገድ ለማሟላት እየሰራን እንገኛለን

የመጀመሪያው በአካል መጥቶ ለሚገዛ ደንበኛ ሲሆን

ሁለተኛው በሶሻል ሚድያ ማርኬቲንግ ነው

ሁለቱንም ዘመናዊ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንሰጣለን

እንዲሁም የተለያዩ የሽያጭ ጥቅል(package)በማዘጋጀት ፍላጎቱን እናሟላለን

የማስፋፊያ እቅድ ለምን አስፈለገ


በተመሳሳይ ስራ ለይ ከሚገኙ ሱቆች አንፃር በጣም የተሻለ እንቅስቃሴ እያሳየ የሚገኘው ድርጅታችን ካለው
የገበያ ፍላጎት አንፃር እንደሚፈለገው እቃዎችን እያመጣ ለማቅረብ የቦታ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ማነቆ
ሆኖበታል ስለዚህም የየክምችት ክፍል እና ተጨማሪ የመሸጫ ቦታ እንደሚያስፈልገው ተገንዝበናል

ስለዚህም በተለያዩ ቁልፍ የገበያ አከባቢዎች ለይ ቅርንጫፍ በመክፈት ጥራት ያላቸውን እቃዎች ለመሸጥ
እንዲሁም አሁን ባለንበት ሱቅ ለይ የሚታየውን የቦታ እጥረት ተጨማሪ ቦታ ለመከራየት ወስነናል
የማስፋፊያ እቅድ ምን ምን ያካትታል እና ምን ያህል ገንዘብ ያስፈልገዋል
የወጪ ዝርዝር የአገልግሎት ግዜ ዋጋ ምርመራ

ለተጨማሪ ቦታ ዘላቂ 8000*12= የሚያስፈልግ


ማስፋፊያ ኪራይ
96,000
(እስቶር)

የሽያጭ እቃዎች 400,000 የሚያስፈልግ


ማምጫ

የስራ ማስኬጃ 150,000 የሚያስፈልግ

የማስታወቂያ 10,000 የሚያስፈልግ


ሌሎች ወጪዎች 50,000 የሚያስፈልግ

ጠቅላላ ድምር 706,000

ይህንን የማስፋፊያ ስራ ለመስራት በተቀማጭ ሂሳባችን ለይ ያለው ገንዘብ በቂ ካለመሆኑ አኳያ ከ ከፍታ ማይሮ
ፋይናንስ ብድር መውሰድ አማራጭ አድረገን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ተቋማችሁ ይህንን የስራ ተነሳሽነት እና
ራዕይ ተመልክቶ ከጎናችን እንዲሆን እንጠይቃለን

ከሰላምታ ጋር

ሔርሜላ ጀነራል ትሬዲንግ

You might also like