Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 15

ታኦማጎሲስ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ትዕይንት ፩

(መድረክ ሲከፈት ቤተክርስትያን ተቃጥሎ መድረኩ በሰማዕታት ደም ተጥለቀልቆ ይታያል፡፡ የተጎዱ እና


ሞተው የሚወጡ ሠዎች ይታያሉ። የሚያለቅሱ እና በቃጠሎው ደንግጠው የሚጮሁ ሠዎች... እ ሣቱን
ለማቃጠል ሲጣደፉ ይታያል።)

አባ ገ/ኪዳን፦ ጴጥሮስ መሰቀልህ ወዴት አለ? ጳ ውሎስ መሰየፍህ የታለ? እ ስጢፋኖስ መወገርህ
የታለ? …አቤት ስለብርሃን ስንቶቹ ጠፉ ንዋየ ቅድሳት ተቃጠሉ ሃብቶች ምስጢራቶች አመድ ሆኑ። አገልገይ
ካህናት እና ዲያቆናት የእሳት እራት ሆኑ . . . አ ለቁ ኧረ እንደው ይህች ቤተክርስቲያን ምንኛ መከራ በዛባት
በሲና በረሃ እነሙሴን የታደግህ አምላክ ወዴት አለህ? ም ነው ይሄን ግፍ እያየህ ዝም አልከን? እውን አለህ
ፈጣሪ? ጣ ር ስቃያችን መከራችን መቼ ያበቃለት ይሆን? ስ ለስምህ ስንሰቃይ ስንገደል ስለ ምን ዝም ትላለህ?
(ምዕመኑ በምሬት እያዘነ ይገባል ጫጫታ ላጭር ጊዜ ይቀጥላል)

ተላላኪ፦ መንገድ . . . ከ ፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እየመጡ ስለሆነ እባክችሁ መንገድ (ባለስልጣናቱ
በሁለት ጋርድ ታጅበው ይገባሉ።)

ባለስልጣን፦ (ከገቡ በኋላ አንገታቸውን እየነቀነቁ ያዝናሉ ወደ መነኩሴው ዙረው) አባቴ እስኪ ስለተፈጠረው
ነገር ያስረዱን?

አባ ገ/ኪዳን፦ በዓቴን ዘግቸ ፀሎት እያደረኩ በነበርኩበት ሰዓት ጩኸት ሰማሁ በበሩ ጭላንጭልም የብርሃን
ወገግታ ሲንቦገቦግ ተመለከትኩ፡፡ ምን ተዐምር ነው ብየ (ሳግ እየተናነቃቸው) ብ ወጣ ቤተክርስትያኗ
ታቃጥላ፤ ካህናት እንደበግ ታርደው እንደ እንጨት በእሣት ውስጥ ምዕመኑ እያቸሁ እሳቱን ለማጥፋት ቅጠል
ቆርጠው ውሃ ይዘው ሲሯሯጡ ደረስኩባቸው፡፡ ንዋየ ቅድሳት መፀሃፍቱን ተቃጥለው ሁሉም እንዳልነበር ሆኖ
አየሁ…

ሚኒስትር፦ (ነገሩን ከሰሙ በኋላ ወደ ጋዜጠኞቹ እየሄዱ) የተፈፀመው እኩይ ተግባር ልብን የሚነካ ለማየት
የሚዘገንን ነው፡፡ የማረጋግጥላችሁ ነገር ቢኖር ይህን እኩይ ተግባር የፈፀሙት ሃይሎች ከህግ እንደማያመልጡ
ነው፡፡ለዚህም መንግሰት ይሄን ጉዳይ ከግብ ለማደረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሌት ተቀን ይሰራል፡፡ በእውነቱ
ይህች ቤተክርስትያን ሃገር ማለት ናት፡፡ ይሄን ጉዳይ ከዳር እሰክናደርስ ማሃበረሰባችን ከጎናችን ሆኖ እነዚህን
እኩይ ሃይሎች ለመያዝ እንዲተባበረን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ጋዜጠኛ፦ (ድምፅ መቅረጫውን ወደመነኩሴው አዙሮ) አባቴ እስኪ ስለወደሙት ንብረቶች፣ ስለታረዱት
አገልጋዮች ያለዎትን መረጃ ይንገሩን?

አባ ገ/ኪዳን፦ ቤተክርስትያኗ እንደምትታየው ሙሉ በሙሉ ወድማለች፡፡ በውስጥ የነበሩት ቅርሶችም አመድ


ሁነዋል፡፡ ምሽቱን ከነበሩት አገልጋዮች ውስጥ ሁለት ካህናት እና አንድ ዲያቆን ታርደዋል ነገር ግን አንድ
ዲያቆን የደረሰበት አልታወቀም። እሳት ይብላው ይትረፍ አልታወቀም፡፡

ሚኒስትር፦ በሉ እግዚአበሔር ያፅናችሁ። በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከጎናችሁ ነን። ችግር በተፈጠረ ሰአት
any time በራችን ክፍት ነው። (እየተዋከበ ይወጣል አባ ገ/ኪዳን አብረዋት ይወጣሉ።)

አባ ሳሙኤል፦ ምነው ፈጣሪየ መከራችንን ጣር ሰቃያችንን አበዛኸው፡፡ ከቁጥር የበዛ ታንኳዎች እያሉ አንተ
ባለህበት ከቶ ለምን ይሆን ወጀቡ ማየሉ? እ ውን ወርቅ ለሰጠ ጠጠር ዳቦ ለሰጠ ድንጋይ ይገበዋልን? ፊ ደልን
ከነቁጥሩ፤ ነፃነትን ከነክብሩ፤ ሀገርን ከነድንበሩ ላቆየች ቤተክርሰትያን ይህ ይገባታል? የ ጎረሱበትን እጅ፤
የጠቡትን ጡት የሚቆርጡ የእፉኝት ልጆች ምንኛ በዙ? (ወደ አባ ገ/ኪዳን እየዞሩ) እ ኔ እምለው አባ እኔ
ምለው እንደው እኒህ የመንግስት አካላት እንዳሉት ወንጀለኞችን ይዘው ጥያቄያችንን ይመልሱልን ይሆን?

አባ ገ/ኪዳን፦ እንዴታ አባቴ በሚገባ ይመልሱታል . . . አ ልሰሙም እንዴ! ባ ለስልጣኗ የተናገሩትን ነገር
ለደረሰው የንብረት ኪሳራ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉልንም ቃል ገብተዋል እኮ

አባ ሳሙኤል፦ እንጃ!!! እ ኔስ ምኑም ደስ አላለኝም ነገሩ ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኖ ተዳፍኖ እንዳይቀር ነው


ስጋቴ።
አባ ገ/ኪዳን፦ አባቴ እንደው ከፈጣሪ ቀጥሎ መቼስ ከመንግስት አካላት ውጭ ለሌላ ለማን አቤት ይባላል
ብለው ነው ባይሆን በጸሎታችን እናግዛቸዋለን እንጂ . . .

አባ ሳሙኤል፦ እስኪ ይሁን . . . እንደው የተሰውትስ ሰማእታት ሆኑ የደም አክሊል ተቀዳጁ እንላለን . . . የዛ
የደግ አገልጋይ የዲያቆን መርእድ ነገር ነው እንጂ የሚያሳስበኝ. . . እንደው የበላውስ ጅብ ኣልጮኸም?

አባ ገ/ኪዳን፦ ኧረ እንደው አባቴ ጅብ ይብላው በሳት ውስጥ አመድ ሁኖ ይቅር ምንም የሚታወቅ ነገር
የለም። ብቻ የቃጠሎው ቀን ምሽት ለጠዋት የኪዳን ጸሎት ቤተ መቅደስ እያዘገጀ ነበር . . . እንደው እንደኔ
ስጋት አብሮ በእሳት ውስጥ ነዶ አመድ ሁኖ እንዳይሆን ነው ፍራቻዬ።

አባ ሳሙኤል፦ ኧረ አባ ደግደጉን እናስብ. . . ብቻ ፈጣሪ ያመጣውን ከመቀበል ውጭ ምን አማራጭ


አለን . . . እንደው ፍንጭ ሳናገኝ ከመፈረጃችን በፊት ግን የአካባቢ ፖሊሶች ስለ ልጁ ጉዳይ በደምብ
እንዲያጣሩ ብናሳስባቸው ጥሩ ነው።
አባ ገ/ኪዳን፦ እንዴ!!! የ ተፈጠረውን ነገር ሁሉ በደምንብ ነው የነገርኳቸው በተቻላቸው ሃቅም እልባት
እንደሚሰጡት እና ሁኔታውን አጣርተው እንደሚነግሩን ቃል ገብተውልናል።

አባ ሳሙኤል፦ ኧረ እንደው እነዚህን ልጆች ቀኑን ሙሉ ሲለፉ ዋሉ እስቲ እንደው ያሰናብቷቸው።


/ጸሎት ይደረጋል/

ትዕይንት ፪

(መጋረጃ ሲከፈት አራት ሰዎች ይታያሉ)

ሬዲዮ ጋዜጠኛ፦ /ከውስጥ ይነበባል/ ከሁለት ወር በፊት የእሣት አደጋ በደረሰበት ገዳም ጉዳይ በማጣራት ላይ
እንደሚገኝ የፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ኮሚሽነር አዱኛ ግርማ እንደገለጹት ከሆነ በገዳሙ ላይ የደረሠው
የእሣት አደጋ ወደአጎራባች አካባቢዎች እንዳይዳረስ ፖሊስ ባደረገው ርብርብ ከህብረተሠቡ ጋር በመሆን የከፋ
ጉዳት ሊያደርስ ይችል የነበረውን ቃጠሎ በጊዜ መቆጣጠር ተችሏል። የአደጋውን ምክንያት እና የደረሱትን
ጉዳቶች በተመለከት አሁንም የማጣራት ሂደቱ የቀጠለ ሲሆን ህብረተሠቡ ፖሊስ አጣርቶ ትክክለኛውን መረጃ
እስከሚያቀርብ ድረስ ያለምንም መደናገር በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል። በሌላ በኩል በገዳሙ ምእመናን
እና ካህናት ፍትህ ተጓድሏል ብለው ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ። ምዕመናኑ ጥፋት የፈጸሙ አካላት
ተጣርተው ባልተያዙበት እና በህግ ባልተጠየቁበት ሁኔታ የደህንነት ስጋት ውስጥ ነን ሲሉ አማረዋል። ብሩህ
ራዲዮ በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን ባለስልጣን አናግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል። ማጣራትና ፍትህ
ዘግይቷል ለሚሉ ባለስልጣኗ መልስ አላቸው።
ሚኒስቴር፦ ህዝቡ... እእእ... ፍትህ ዘግይቷል ማለቱን በተለያየ መልኩ ሲገልጽ ቆይቷል።እእእ... ኃሣቡ
እንደኃሣብ ጥሩ ነው እንደአካሄድ ግን ፖሊስም ሆነ ሌሎች የፍትህ አካላት የሚሠሩበት የራሱ የሆነ ስርዓት
አለ። እእእ... አሁን መረጃ በማሠባሠብ ሂደት ላይ ነን። መረጃዎችን አሰባስበን እንደጨረስን የሚጠየቁ አካላት
የሚኖሩ ከሆነ የምናቀርብ ይሆናል። እእእ... ሌላ ማለት የምፈልገው ነገር ግን ማህበረሰቡ ያለምንም መደናገር
የማጣራት ውጤቱን እንዲጠብቅ በትህትና እጠይቃለሁ። አመሠግናለሁ።
ማክዳ፦ ምነው እንደሸማኔ መወርወርያ ወዲያና ወዲህ ትወራጫለህ?
ዳጊ፦ አንች ምን አለብሽ አለ ሰውየው
ማክዳ፦ እኔ እንጃ ወንድሜ ፎንቃ ሳያሰቃይህ አልቀረም
መርዕድ፦ እንግዲህ ፎንቃ የሚለውን ቃል መንዝረን፤ አበጥረን አበጠርጥረን ስናየው ቃሉ የቻይንኛ ነው፡፡
ምክንያቱም ፎንቃ ልክ እንደ ቻይና እቃ ላይበላይ ስታየው ማንነትክን የሚገዛ ውብ እና ማራኪ ነው፡፡ነገር ግን
ውስጡ ስትገባ ፎንቃ እራሱ እንደቻይና እቃ መንፏቀቁ የማይቀር ነው። እኔ የምመክርህ ከፎንቃ ይልቅ ፍቅር
እነዲይዝህ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር መስራች በሞቱ አለምን የገዛው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ
የመሰረታቸው ነገሮች ደግሞ መሰረታቸው አለት ነው፡፡ አለቱም አይፈርስም አይናወፅም ስለዚህ የቻይና እቃ
ከመሰለው ፎንቃ ይልቅ ክርሰቶስ የመሰረተው ፍቅር እጅግ ይበልጣል፡፡
ዳጊ፦ ባክህ አንተ የኑሮ ውድነት እንጂ ፍቅር አላሳበደህም።
እናት፦ ኧረ እንዴው እናንተስ ወዲያ! እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ ስለከንፈር ወዳጅ ታወራላችሁ? ምናለ እኔን እንኳን
ብታፍሩኝ?... ይኸው ይህ ህመምተኛ ልጅ እንኳን ከእናንተ ተሽሎ ሲመክራችህ! አይይይ... እንዲህ በዋል
ፈሰስ ሆናችሁ ትቀሩ? ያ መርዕዴ ነበር እንጂ የሚያከብረኝ ... እናቴ እናቴ የሚለኝ አይ ልጄን! /እያለቀሰች/
ማክዳ፦ እማዬ ደሞ ለምንድን ነው በሆነ ባልሆነው ስሙን እያነሣሽ የምታለቅሽው?
እናት፦ አይ ያወለደ አንጀት! እሡን ስትወልዱ ይገባችኋል። (ተነስታ ወደጓዳ ትገባለች)
ዳጊ፦ እማዬን ተያት ባክሽ ... ይልቅ ማኪዬ ምን ልበላት? እ ምን ልበላት? እንዴው ሄጄ እወድሻለሁ ልበላት?
ማክዳ፦ አይ እንደርሱ አትበላት እጠላሻለው በላት
ዳጊ፦ ባክሽ ማክየ አትቀልጅብኝ
ማክዳ፦ ቆይ እኔ እምልህ ለመሆኑ ጠይቀሃታል
ዳጊ፦ ያልጠየኩበትን ቀን ጠይቂኝ ስንት ቀን እኮ እንደተመላለስኩማክዳ፦ እሽ ምን አልካት?
ዳጊ፦ ባለፈው ነጭ ሱፌን ታውቂዋለሽ… እሱን ገጭ አድርጌ ደሞ ነጩን ጫማዬን ተጫምቼ ሄድኩልሽ
ማክዳ፦ ሙሽራ መስለህ ነዋ የሄድከው
ዳጊ፦ ወይ እሷ እቴ…. ሙሽራ መምሰሌ መች ታያትና ከዛ አልኩሽ ሄድኩና ሃይ ቆንጆ እንዴት ነሽ
ስላት..."ምነው ደሞ ዛሬ የጠፋ ሻማ መስለህ መጣህ" አላለችኝም መሰለሽ፡፡
መርዕ፦ ቂቂቂ……እውነትዋን እኮ ነው ነጭ በነጭ ለብሰህ በዛ ላይ ይሄን ከሰል የመሰለህ ፊት ስትጨምርበት
እውነትም እኮ የጠፋ ሻማ ነው የምትመስለው፡፡ እኔ የምልህ ለምን የበራ ሻማ መስለህ ሄደህ አታስደምማትም?
ዳጊ፦ የበራ ሻማ… እንደዛ መምሰል እችላለሁ እንዴ?
መርዕድ፦ ታዲያስ
ዳጊ፦ እንዴት (በጁ ወደ እሱ እንዲመጣ ይጠቅሰዋል)
መርዕድ፦ ለምን ፊትህን ቀይ ቀለም ተቀብተህ አትሄድም….?
ዳጊ፦ ሂድ... እኔ ደግሞ አንተን ቁምነገር አለህ ብዬ መስማቴ
ማክዳ፦ ስማ ወንድሜ መጀመርያ ከቤትህ ሸክ ብለህ የፓሪስን ሽቶ ተቀብተህ ፓጃሮ መኪናህን እየነዳህ
ከቆመችበት ፊት ሂደህ ገጭ ትላለህ፡፡ ያኔ አይደለም ጋቤና ፓርቶመጋላ ላይ ጠፍረህ ብትወስዳት ባ…ባ...
አያለች እንደበግ ትከተልሃለች፡፡
ዳጊ፦ ማክየ አንች እኮ አትምከሪ እንጅ ስትመክሪ አንጀት አርስ ነሽ /ለመውጣት ይጀምረና ሲገባው/ አንች
ምንድን ነው ያልሽው? የፓሪስ ሽቶ?... ፓጃሮ?... አይደለም ፓጃሮ ጋሬስ የት ይመጣል?
መርዕድ፦ ይሄኔ ነው ማበድ
ማክዳ፦ ቆይ እሰኪ እንዲህ ክንፍ ያልክላትክን ልጅ ለምን አታሳየኝም?
ዳጊ፦ እንደውም ዛሬ ከነጋ አላየኋትም ንፍቅ ብላኛለች በኋላ አሳይሻለሁ።
መርዕድ፦ አላየኋትም? ጅራት የላትም እንጅ ጅራቷ በይው እንደው በሞቴ ጤዛ ለሆነው ለዘመኑ ፍቅር
እንዴት ሠው እንዲህ ይሆናል? ደግሞ ልጂቷ እኮ ብታያት የገነፈለች ጀበና ነው የምትመስለው ልብስዋ
የመኸር ድርቆሽ ፊቷ የሐምሌ ጭጋግ የመሰለ፡፡ ልጁ እኮ እነደነዱት የሚነዳ እንስሳ ነው የሆነው፡፡ እንግዲህ
አሳማ እንዳንለው ጅራት የለው ፈረስ አንለው መነሳንስ የለው፡፡ ወይ ፍቅር አለ ዘፋኙ!!
አባ ገ/ኪዳን፦ ቤቶች እንደምን ሠነበታችሁ?
ማክዳ፡- ውይ አባ መጡ... እንደምን አሉ? ይባርኩን (መርዕድ ሹልክ ብሎ ይወጣል)
አባ ገ/ኪዳን፦ ወለተማሪያምስ
ማክዳ፦ አለች ውስጥ ሆና ነው... እማዬ (ወደ ጓዳ ዞራትጣራለች) አባ መጥተዋል?
እናት፦ ውይ በሞትኩት ... መጡ እንዴ አባ? /ተጠግታ መስቀላቸውን ትሣለማለች/እንደው በሠላም ነው ግን
የመጡት አባቴ?
አባ ገ/ኪዳን፦ አዎ በሠላም ነው... እንደው በዚህ ሳልፍ እግረመንገዴን ሳልፍ ሠላም ልበላችሁ ብዬ ነው።
በዛውም ስለዲያቆን መርእድ የተሰማ ፍንጭ ካለ ለመጠየቅ ነበር።እናት፦ አይይይ አባቴ... እንዴው ደግ ልጄ
የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ እኔም ወይ እርሜን አላወጣሁ ሞተም ብዬ አላረፍሁ ከቀን ቀን ይመጣል ብዬ ደጅ ደጁን
ማየት ብቻ... /ያለቃቅሳሉ/
አባ ገ/ኪዳን፦ ይተው እንጂ ወለተማርያም ወደ እግዚአብሔር መጮህ ነው የሚበጀው። ፖሊሶችም
ክትትላቸውናላቋረጡም... የሆነ ነገር እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነኝ እኛም በጸሎት እንተጋለን። ... /ከአፍታ ጸጥታ
በኋላ/ እኔ የምልሽ ወለተማርያም ይህ አሁን የወጣው ልጅ ያለዛሬም አይቼው አላውቅ... ጤነኛም አይመስል...
ማን ነው?
እናት፦ ወዲህነው ነገሩ... መቼስ ይህ አባታቸው አያመጣብኝ ጉድ የለም ... ቅርብ ጊዜ ነው... ከሌላ የወለደው
ልጁ ነው ቤተሠብም ስለሌለውና የአዕምሮ መታወክ ስላለበት እንደው ከወንድምና ከእህቱ ጋር ሲሆን፤ የሠው
ፍቅር ሲያገኝ በሽታው መለስ ቢልለት ብለው ይኸው አምጥተው ጣሉብኝ... መቼስ ወላድ ነኝ በልጅ
የሚጨክን አንጀት የለኝ። እኔም ይሁን ብዬ ተቀበልኩት።
አባ ገ/ኪዳን፦ አይ ወለተ ማርያም መልካም ስራ ነው ያደረግሺው በሰማይ በትሽን እየሰራሽ ነው
እግዚአብሔር ይባርክሽ። በሉ እኔ ልሂድ።
እናት፦ የሆነ እህል ብጤ እንኳን አፍዎ ላይ ጣል ሳያደርጉ?
አባ ገ/ኪዳን፦ አይ እቸኩላለሁ... /እየወጡ/
ትዕይንት ፫

/መጋረጃ ሲከፈት ካቢኔ1ን ጨምሮ 5 ሰዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ይታያሉ/

አባ ሳሙኤል፦ እንዴት ህግ አለ በሚባልበት ሀገር አማኝ በሞላበት መንደር በሁለት ወር እንዴት ሶስት
ቤተ_ክርስቲያን ይቃጠላል?
ሚኒስተር፦ አባታችን እኛ ወንጀለኞችን ለመያዝ ሌተ ተቀን ያለመታከት እንቅልፍ አጥተን እየሰራን ነው፡፡
እናንተም ብትሆኑ በእናንተ መነፀር ብቻ ሳይሆን በኛም መነፀር ማየት ይገባችኋል፡፡
አባ ሳሙኤል፦የናንተ እንቅልፍ ማጣት ቅጥ አጣ /በንዴት/ እኛንስ ቢሆን በዚህ በእረጅና ዘመናችን ለምን
የመንግስትን ደጅ ታሰጠኑናላችሁ?
ካቢኔ1፦ ይሄን ያክልማ አያካበዱ ባንድ ቀን ውስጥ ስንት ቤት በሚቃጠልበት ሃገር የናንት ቤት መቃጠሉ ምን
ይደንቃል? የራሳችሁ አምላክ ያልጠበቀውን መቅደስ ማን ይጠብቃል? ቅርሱን ስጡን በሙዚየም እናስቀምጥ
አልን አሻፈረኝ አላችሁ፡፡
አባ ሳሙኤል፦ መቅደሱንማ ይጠብቃል ቢዘገይም እንኳን ትዕግስትን በቁጣ ምህረቱን በመኣት የለወጠ ዕለት
በፊቱ ማን ይቆማል? አይበጃቸውም ና ከእግዚአብሔር ጋር አይጋጩም ፡፡ ዝም ያለ አይምሰልህ የታቦተ
ጽዮንን ከእሰራኤል መማረክ አንድ ትምህርት ነው፡፡የእስራኤል በደል ቢበዛ በረከታቸውን ኃይላቸውን በጠላት
አሥማረከ። በኋላ ግን ከበደላቸው ሲመለሱ ኃይል በረከታቸውን መልሶ ሰቷቸዋል፡፡ እናም ይህ ትውልድ
አምላኩን ረስቷል። በአፍላ ትጀምሩታላችሁ በወራት ትተውታላችሁ። ያወቃችሁትን እረሳችሁት
ያላወቀችሁትን ለማወቅ ትጠራላችሁ የያዛችሁትን ትረገጣላቸሁ የረገጣችሁትን ትይዙታላችሁ። ምኞታችሁ
ብዙ ነው አምሮታችሁ ልክ የለውም። በዚህ የተነሳ ምስጢር ለመካፈል ውርስ ለመረከብ የሚያስችል ስብዕና
አልገነባችሁም፡፡ እኛ ገዳማውያን መገናኛውን ድልድይ ስላልገነባን እና ከናንተ ስለራቅን ሳይሆን ስለማታዩት
(ማየት ስለማትፈልጉ) አለበለዛም እንደልቦለድ ገፀባህርይ የራሳችሁን ያሸበርቀ አስረካቢ ፈጥራችሁ እውኑን
ሳይሆን ምናባችሁን መረከብ ፈለጋችሁ፡፡ እኛ ደግሞ እናንተ ታዩን ዘንድ አላሸበረቅንም ማሸብረቅም
አንፈልግም በዚህም ምክንያት ለናንተ ምስጢር ለመንገር ቅረስን ለማውረስ ከባድ ሁኗል፡፡እኛ አባቶቻችን
እናምናለን። በእነርሱም ደስ ይለናል የነገሩንን ተቀብለን ቃልኪዳናቸውን ጠብቀን እንኖራለን ጽላተ ጽዮን
አክሱም ጽዮን እንዳለች ሲነግሩን መጋረጃ ገልጠን ሳጥን ከፍተን እንይ አንልም፡፡ጌታ የተሰቀለበት ግማደ
መስቀል ክፋይ ግሸን ማርያም አለ ሲሉን ቆፍረን አውጥተን እንይ አላልንም ቅዱሱ ጽዋ መንዝ ውስጥ አለ
ሲሉን ዋሻ እናስስ አላልንም አባቶቻችን አምነን አገራችን የበረከት ምድረ መሆንዋን አምነን የጌታችንን የጽዋ
ስጦታ ተቀብለን በእምነት እንኖራልን። ምንም የለንም ሁሉም ግን የኛ ነው ድሆች ብንባልም ባለፀጎች ነን
የተራቆትን ብንመስልም የፀጋ ልብስ አልን፡፡ ሀዘንተኞች ብንመስልም ደስተኞች ነን። ስለ ሃገራችን መባረክ
ቅድስት ሃገር መሆን ቅዱሱ ቅርስ በእጃችን እንዳለ ዓለም እነዲያረጋግጥልን እንፈልጋልን፡፡ ስላከበራችሁን
እግዚአብሔር ይስጥልን። (አባ ሳሙኤል ይወጣሉ)
ሚኒስትር፦ እባክወትን አባቴ ይረጋጉ ቆይ አንዴ ያዳምጡኝ ፤ ምን ማለት ነው አንተ እንዴት አንዲህ
ትናገራቸዋለህ? እራሳችን በራሳችን ወጥመድ እንዴት ታጠምዳለህ?
አባ ገ/ ኪዳን፦ ይቅረታ አቋረጥኳችሁ እባከዎትን ክቡርነትዎ ይቅርታ
ምኒስትር፦ ቆይ አንተ ምን ማድረግህ ነው እንዴት እዚ ድረስ ትመጣለህ? ካልጠራሁህ በስተቀር በአካል እዚ
እንዳትመጣ አላልኩህም። ሰው ቢያይህስ? ሽማግሌው አይተውህስ ቢሆን? ቆይ ነገሮች ወዴት እየሄዱ ነው
እነዴት ነው አነደዚህ የተወሳሰቡት ምንድን ነው እያደረጋችሁ ያላችሁ?
አባ ገ/ ኪዳን፦ ይኸውልዎት ክቡርነትዎ እኛ ቤተ_ክርስቲያኗን ስናቃጥል እቅዳችን የነበረው ቅረሶችን ከዘረፍን
በኋላ ከቤተክርስቲያኗ ጋር አብሮ እንደወደመ ማስመሰል ነበር። ነገር ግን እኛ ቅርሶቹን ከማገኘታችን በፊት
ዲያቆኑ ቅርሶቹን ይዞ ተሰውሯል፡፡
ሚኒስትር፦ እሱንማ ደጋግማችሁ ነገራችሁኝ አሁን የኔ ጥያቄ ዲያቆኑ የት ነው ያለው? የሚለው ነው
(ጠረጴዛውን እየመታ)
አባ ገ/ ኪዳን ፦ አዎ ክቡርነተዎ እኛም ስናጣራ የቆየነው እርሱን ነው፡፡ እናም ባደረገነው ማጣራት መሰረት
ከዲያቆኑ ጋር ያገናኘዋል ብለን ባሰብንበት ቦታ ላይ መረባችን ዘርግተናል እንግዲህ አሳው መረቡ ውስጥ
እሰኪገባ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል ።
ሚኒስትር፦ ስማ የቅርቤ ሰው ያደረኩህ እኮ እንደዚ አይነት ተራ ወሬ እንድታወራልኝ አይደለም። ቅርሱ የት
እንደደረሰ እንድታውቅ መስሎኝ ከገዳሙ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖርህ ያደረኩት። ይሄን ማድረግ የማትችል
ከሆነ ምን ትሰራልኛለህ እንዳስወግድህ እገደዳለሁ። ስሙ ሁላችሁም ቢሆን የተሰጣችሁን ስራ ባግባቡ
ሰርታችሁ ቅርሱንም ባጭር ጊዜ እጄ ውስጥ እንዲገባ እፈልጋለሁ አሁን ጨርሻለሁ ሁላችሁም ውጡ፡፡
ትዕይንት ፬
/ማክዳ ከውጭ እየሮጠች ትመጣለች/
ማክዳ፦ ዳጊ... ዳግም...ወንድሜ /እየተጣራች ወደ መድረክ ትገባለች መድረኩም ይከፈታል/ ዳጊ መጣችልህ
ዳግም፦ ማናት ደግሞ የምትመጣው /አልጋው ላይ ጋደም ብሎ/
መርዕድ፦ ማን ትሆናለች ያቺ ዝልዝል ስጋ የመሰለች መንቃራ ናታ
ዳግም፦ አትይኝም... እውነትሽን ነው እንዴ ማኪዬ /ካልጋው ላይ እየተነሳ ቁጭ ብድግ ይላል/
ማክዳ፦ አዎ እራሷ ነች።
ዳግም፦ እና ምን ላድርግ ማኪዬ እ… /በባዶ እግሩ ይነጎራደዳል/
መርዕድ፦ ኧረ ሰውዬ ተረጋጋ ልትበር ነው እንዴ?
ማክዳ፦ ባክህ አትርበትበት መጀመርያ ተረጋጋ... ደሞስ እሷ መጣችብህ እንጅ አንተ አልሄድክባት... ደግሞ
ስማ አሁን እሷ ስትመጣ እንዳትቅለሰለስ እንዳትፈራ እሽ ኮስተር ቀብረር ነው እምትልባት...
ዳግም፦ ኧረ አልፈራም /ኮራ ጀነን ለማለት እየሞከረ/
ማክዳ፦ በል አሁን ጫማህን ልብስህንም አስተካክል /ጫማውን እና ልብሱን አስተካክሎ ይቆማል/
ሊዲያ፦ ቤቶች ዳጊ ዳግም /ወደመድረክ እየወጣች ዳግም አልጋው ስር ይደበቃል/ ...ሀይ እንዴት ናችሁ?
መርዕድ፦ ሀይ... ዛሬ ደግሞ ከቄራ የወጣ ውሻ መስለሻል ባክሽ።
ሊዲያ፦ ዳጊ የለም እንዴ /ማክዳ ዳጊ ካልጋው ስር እንዲወጣ ትጠቁመዋለች/
ዳግም፦ አቤት አለሁ ፈለግሺኝ /የለበሰውን ኮት እያስተካከለ/
ሊዲያ፦ እኔን ስታይ ነው እንዴ አልጋ ስር የተደበከው?
ዳግም ፦ ኧረ አይደለም ደግሞስ ለምን ብየ እደበቃለሁ? በዚህ ውስጥ እኮ አይጥ አይቸ እሷን ልገድል
እያባረረኩ ነበር።
ሊዲያ፦ እና አይጧን ጉድጓዷ ውስጥ ገብተህ ነው እንዴት እምትገድላት?
መርዕድ፦ በለው በለው ገባችለት ቂቂ…
ሊዲያ፦ ታድያ አይጧን ገደልካት ወይስ አመለጠችህ?
ዳግም፦ አይ አይጧን ልገድላት ሳባርራት ሳባርራት ከቆየሁ በኋላ መጨረሻ ላይ አይጧ ከሌሎች አይጦች ጋር
ተቀላቀለችብኝ
መርዕድ፦ ከዛ ከሌሎች አይጦች ጋር ስለተመሳሰለችብህ እና መለየት ስላቃተህ ትተሃት መጣህ ቂቂ…
/ሁሉም ይስቃሉ...ዳግም ይናደዳል/
ዳግም፦ ምነው ልታሰድቢኝ ነው እንዴ የመጣሸው
ሊዲያ፦ ኧረ እኔ ለቁም ነገር ነው የመጣሁት
ዳግም፦ ቁምነገር... ምንድን ነው /በጉጉት/
ሊዲያ፦ የፍቅር ጥያቄህን መቀበሌን ልነግርህ ነው የመጣሁት።
ዳግም፦ እ……እውነትሽን ነው?... (ደስታውን መቆጣጠር አልቻለም ማክዳን ሄዶ ያቅፋታል)መርዕድ፦ ቱ
ቱ…ቱ በሞትኩት አሁን እሱን ወንድ ብለሽ የፍቅር ጥያቄህን ተቀብዬሃለሁ አልሽው? እኔ እምልሽ ለምን ፆታ
አትቀያየሩም... ቂቂ
ዳግም ፦ ተይው ባክሽ ይኸ እብድ ነው። እና እኔ የምልሽ ሊሉዬ እና በቃ የፍቅር ጥያቄዬን ተቀበልሽ?
ሊዲያ ፦ አዎ ተቀብያለሁ /ይተቃቀፋሉ/
መርዕድ ፦ ግም ለግም አብረህ አዝግም አለ ያገሬ ሠው
ሊዲያ ፦ በናትህ ይሄን እብድ አስወጣልኝ ምንም ቀልቤ አልወደደውም ምን ይመስላል በጌታ ሲያስጠላ!
ዳጊ ፦ ና ውጣ /ወደ መርዕድ ለማስወጣት እየሄደ/
መርዕድ ፦ ሂድ /በእጁ እየቃጣው/… ወንድ አሰዳቢ … ሆ ሆ ይችማ እራሷ ደሊላ ናት። አንቺ ገና ከመግባትሽ
ከገዛ ቤቴ ያስወጣሽኝ ትንሽ ስትቆዪማ እንጃ ...
ዳጊ ፦ ባክሽ እንደውም እኛ እንውጣ እስኪ የመጀመርያ ቀን ፍቅራችንን በደስታ እናክብረው።
ማክዳ ፦ ምን ከቤቴ ውጭ እያልከኝ ነው?
ዳጊ፦ ኧረ አይደለም የኔ ቆንጆ ልጋብዝሽ ብዬ እኮ ነው።
ማክዳ ፦ እውነት?... ምን ትጋብዘኛለህ?
ዳጊ፦ ምን ልጋብዝሽ /እያሠበ/...እ... በቃ ሚሪንዳ እጋብዝሻለሁ።
ማክዳ ፦ ሚሪንዳ?... ስታየኝ በሽተኛ እመስላለሁ?
ዳጊ፦ በቃ ሻይ በዳቦ እጋብዝሻለሁ።
ማክዳ ፦ ጭራሽ?
ዳጊ፦ እና ምን ልጋብዝሽ... በቃ ደስ ያለሽን እጋብዝሻለሁ / ይወጣሉ/
ማክዳ ፦ ስማ ወንድሜ እራስህን ጠብቅ
መርዕድ፦ እኔ እኮ እንደው አወቅሁ አወቅሁ ሰለጠንኩ ሰለጠንኩ ተማርኩ ተማርኩ የምትሉ ሰዎች ግርም
ትሉኛላቹ።
ማክዳ፦ ሆ…. እቴ አንተ ደግሞ እብደትህ ሊጀምርህ ነው፡፡
መርዕድ ፦ እውነቴን እኮ ነው ምኞታችሁና አምሮታችሁ ልክ የለውም፡፡ ያማራችሁን ስታገኙ ወድያው
ይሰለቻቹሃል፡፡ ተው የተባላችሁትን ትሰራላችሁ የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ የተፈቀደላችሁን ችላ
ትላላችሁ፡፡ ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተ መቅደሱን በመስታዎት ሰርታችሁ መቅደስ
ባትገቡ እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ፡፡ ሁሉንም ማየት እና ማወቅ ትፈልጋላችሁ
በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም። ሁሉ አላችሁ ግን ባዶ እጃችሁን ናችሁ። ሐይማኖት እንጂ እምነት
የላችሁም፡፡
ማክዳ፦ ወይ አንተ ደግሞ ምነው መቅደስ ታሪክ እምነት እያልክ የምትቀባጥረው? እንደውም ስላልገባን እና
ስላልተረዳነው እንጂ ኋላ ለመቅረታችን እና ለመድከማችን ምክንያቱ ይሄ በአጉል ባህል የተተበተበ እምነት
ታሪክ ምናምን የምትሉት ነገር ነው፡፡ እኛ ታሪክ እናእምነት እያልን ስናላዝን አለም ቀድሞ ተወንጭፏል።
መርዕድ፦ አንቺም እንዲ አልሽ? ባለቤቱ የጣለውን ማን ያነሳዋል? እምነታችን እና ታሪካችን አዋደን ሀገራችንን
ከማሳደግ ይልቅ ከእጅ ገብቶ አንድ ቀን ለማያድር ገንዘብ መፅሀፍቶችንና ታሪካችንን እንሸጣለን፡፡ እናንተ
ዘመናዊ ነን የምትሉ ሰዎች ደግሞ ተምራቹ እውቀት ስታገኙ ሠርታችሁ ሀብት ስታፈሩ ከላይ የሆናችሁበትን
ሀገር ለቃችሁ ሰፋ ወዳለው እንሂድ ብላችሁ እንደገና ከታች ትጀምራላችሁ ትቀጥላላችሁ፡፡ በመጨረሻም
ከጀመራችሁበት ትገኛላችሁ፡፡ ቸኩላችሁ ትወስናላችሁ ወድያውኑ ትፀፀታላችሁ ከታሪክ ፍቅርና ልማትን
ሳይሆን ጥላቻ እናጥፋትን ለይታችሁ ትቆፍራላችሁ ከዚያም ቀጥላችሁ የከበረ ማዕድን እንዳወጣችሁ ሁሉ
በኩራት ደረታችሁን ነፍታችሁ ሳትመርጡ ሁሉን በአደባባይ ትዘሩታላችሁ። የአሸናፊነትን እና የተሸናፊነትን
ሀውልት በአንድ ላይ ታቆማላችሁ፡፡ ለግልፅነትና ለነፃነት እያላችሁ በምታደርጉት ሽኩቻ እርቃን ወደ መሆን
ወረዳችሁ፡፡ በዚህ አለም ጥድፍያ ታማችኋል ሀገራችሁን ትንቃላችሁ ጥላችሁ ለመሄድ ትፈልጋላችሁ
ከሄዳችሁ በኋላ ደግሞ አፍታ ሳትቆዩ ሀገሬ ናፈቀኝ ትላላች፡፡ በቁማችሁ የናቃችሁትን አፈር በሞታችሁ
ልትለብሱት ትመኛላችሁ፡፡ ለሀገሬ አፈር አብቃኝ ብላችሁ በድናችሁን ልካችሁ የወገናችሁን ልብ
ትሰብራላችሁ፡፡
ማክዳ፦ የሚሠማህ የለም እንጂ ትናገራለህ እኮ።
መርዕድ፦ ታዲያ በፈረንጅ አዝማሪ የተዛጋ ጆሮ እንዲህ አይነቱን ፍሬ ነገር መች ይሠማና።
ማክዳ ፦ አንተ ከሰሙህ ብዙ ታወራለህ በል እኔ አሁን የምሄድበት አለኝ።
መርዕድ ፦ /ለትንሽ ቆይታ ወድያ እና ወዲህ እየተሰላሰለ ይቆያል/ /በግባተ ድምፅ
ተቃጠለ ተቃጠለ… ደውል ይደወላል። /(ከመድረክ በስተጀርባ) አድኑኝ አድኑኝ አ… አ… አድንኝ ይቅር
በላቸው …. የማቃሰት ድምፅ ይሰማል/ መርዕድ ራሱን በእጁ ይዞ ትንሽ ይጨነቃል ወደ ተመልካች ዞሮ….
አንቺ መሬት የትኛው አይነት ነሽ? ኮረኮንች ወይስ ለም? ነጭ ነቀዝ ደግሞ ለውስጥሽ ፈልቋል ቢዘራብሽ ታፈሪ
ይሆን? የአባቴን ዘር ይዤ ነበር፡፡ ልዘራብሽ ፈለግሁ። ግን የአባቴ ዘር እንክርዳድ የማያበቅል መሬት ያሻል። …
ኡፍ ባላደራነት እንዴት ይከብዳል? እንዴት ያስጨንቃል ያውም የህይወት አደራ መጠበቅ ግን እኮ ይህ አደራ
ህይወትን የሚሰጥ አደራ ነው፡፡ ዓለም ፈጥና ታስውባለች ታከስማለች ታበቅላለች ታጠፋለች፡፡ ነገር ግን
የእውነት አደራ ለመጠበቅ ይህችን ዥንጉርጉር ዓለም ጥሎ መቅበዝበዝ ከድሎት ወደ ስቃይ መግባት የወደፉት
ብርሀንን እያዩ እና ተስፋ እያደረጉ ፍጥነትን ወደዚያ መጨመር እንዴት ያረካል (ደውል ይሰማል) አቤት
ይሰማኛል … የሰማዕታት ጥሪ ያስተጋባል ... አንቺ ጀምበር ንጋት ነሽ ስልሽ ልትጠፊብኝ ነው? ገና እኮ
አልጠገብኩሽም። ገና የማወርሰውን የአባቶቼን ዘር ማስቀመጫ ሳላዘጋጅ ተዋሕዶ በሰማዕታት ደም ፈንጥቃ
ሳታበቃ ሁሉም ሳይመገባት ልትጨልምብኝ ነው?
ትዕይንት ፭
/ትዕይንቱ ሲጀምር አባ ገ/ማርያም እና ሊዲያ በሕዝቡ በኩል ገብተው እየተጓዙ/
አባ ገ/ ኪዳን ፦ ስሚ ሊዲያ መቼም ወንድ ልጅን እንዴት አድርጎ ምስጢር እንደምታውጣጭው ላንቺ
መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው ፡፡
ሊዲያ ፦ እሱን ለኔ ተወው እናንተ ግን በመጀመርያ ክፍያዬን እንድትሰጡኝ እፈልጋለሁ
አባ ገ/ኪዳን ፦ /ቆም ብሎ እጇን ይዞ ያዞራትና/ ምን ነካሽ ሊዲያ ሴራሽን በስርዓት ሰርተሸ ስትጨርሽ ሙሉ
ገንዘቡንእንደምንሰጥሽ ከተነጋገርንና ለስራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ከወሰድሽ በኋላ በዚህ ሰዓት እንደዚህ
አይነት ነገር ማንሳት ተገቢ ነው?
ሊዲያ ፦ እንጃ ብቻ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም እንዳትክዱኝ ፈራሁ
አባ ገ/ኪዳን ፦ ምን ማለትሽ ነው… ብቻ አንች ስራውን አሳምረሽ ስሪ እንጂ ስለ ክፍያው አትጨነቂ
እንደውም ሰርፕራይዝ አለሽ … ታዲያ ሊዲያ ምን አልባት የተለየ ነገር ካስተዋልሽ ማንኛውንም ውሳኔ መወሰን
ይኖርብሻል።
ሊዲያ ፦ እሺ በቃ እኔ ልሂድ ምን አልባት ስቆይ እንዳይጠረጥር
አባ ገ/ኪዳን፦ አይዞሽ በርች እኔ ደግሞ እዚህ አካባቢ እጠብቅሻለሁ
ሊዲያ ፦ እሱን ለኔ ተወው ስንቱን ወንድ ነኝ ያለ ጀግና እንዳንበረከኩ አትርሳ /ይህን ከተናገረች በኋላ ወደ
መድረክ ትሄዳለች /
/ መጋረጃው ሲከፈት ደግሞ ወደ ተመልካች ዞሮ ይታያል /
ሊዲያ ፦ ሰርፕራይዝ /ከጀርባው መጥታ ወገቡ ላይ እየተጠመጠመች/
ዳግም፦ ምነው ሊዱ? ደጅ አስጠናሽኝ /ወገቡ ላይ የተጠመጠመውን እጇን እንዳትለቀው በመያዝ/ ሠባት
ሠዓት ቀጥረሽኝ ዘጠኝ ሠዓት ትመጫለሽ?
ሊዲያ ፦ ምን ታካብዳለህ ሁለት ሠዓት ነው የጠበከኝ ለፍቅር ሲባል ሁለት ሠዓት መጠበቅ ደግሞ ለፍቅር
ከሚከፈለው መስዋዕትነት ትንሹ ነው፡፡
ዳግም ፦ እሱማ አይደለም ሁለት ሠዓት እነዛን ሁሉ ጊዜያትን ጠብቄሽ አይደል?
ሊዲያ ፦ በል አሁን ና ቁጭ በልና የፍቅር ቀምበጣችንን እንቀንጥስ /የያዘችውን ወይን ከቦርሳዋ አውጥታ
እያስቀመጠች/ እስቲ ብርጭቆ ይዘህ ና /ወደ ውስጥ ገብቶ ብርጭቆ ይዞ ይመጣል... ወይኑን በሁለቱም
ብርጭቆዎች ቀድታ ትሰጠዋለች ደግሞ የሰጠችውን ወይን ተቀብሎ ሊጠጣ ሲል/
ሊዲያ ፦ ኧረ ፋራ አትሁን ችርስ…. /ከዛ ውስጥ ላይ ብርጭቋቸውን ያጋጩና ይጠጣሉ ዳጊ ትንሽ ከተጎነጨ
በኋላ ብርጭቆውን ሊመልሰው ሲል/ ይሄማ አይመለስም ጨርስ።
ዳጊ ፦ ምነው የኔ ቆንጆ ዛሬ እቅድሽ እኔን ማስከር ነው እንዴ ነው ወይስ አስክረሽ ልትደፍሪኝ ነው ?
ሊዲያ ፦ አንተ! እኔ እንኳን እንደዛ አላሰብኩም… ደሞስ ማድረግ ብፈልግ ማን ከልካይ አለብኝ
ዳግም ፦ እሱስ ልክ ነሽ ካሁን በኋላ ንብረቴም ሰውነቴም ያንችው ነው፡፡ሊዲያ ፦ ግን ቤት ውስጥ ማንም
የለም አይደል?
ዳጊ ፦ አዎ ማንም የለም እማ ሰው ለመጠየቅ ወጣ ብላለች። ማኪ ደግሞ አንቺ እንደምትመጭ ስነግራት
“ፍቅረኛሞች ሲገናኙ ብቻቸውን ሁነው ማውራት አለባቸው” ብላ እዚ ጎረቤት ቤት ሄዳለች... ሙድ የገባት
እኮ ናት።
ሊዲያ፦ እንደዛ ክሆነ ጥሩ እኔ እምልክ ዳጊዬ እጠይቅሃለው እያልኩ እኮ። እስኪ ስለ ቤተሰቦችህ አውራኝ።
ዳጊ፦ ሊዱ ደሞ ስለ ቤተሰቦቼ ሌላ ቀን እነግርሻለው አሁን ስለኔ እና አንቺ ብቻ እናውራ። ያለከልካይ
ፍቅራችንን እንኮምኩም።
ሊዲያ፦ እህ ዳጊ ደሞ የቤተሰቦችህ ጉዳይ ይኔ እና ያንተ ጉዳይ አይደል እንዴ? …እንዲያውም ማለት ነው
አዲስ ፍቅረኛሞች ሲገናኙ ስለ ምን እንደሚያወሩ ታቃለህ? ስለቤተሰቦቻቸው ነው እሺ። /በማኩረፍ እየዞረች/
ዳጊ፦ እሺ ቆይ ምን ልንገርሽ?
ሊዲያ፦ በቃ ስለቤተሰቦችህ ሁሉን ንገረኝ
ዳጊ፦ አባታችንና እናታችን የተለያዩት በልጅነታችን ነው። ያኔ እናቴ የገቢ ምንጭ ስላልነበራት እኛን ለማሳደግ
የጉልበት ስራዎችን ትሰራ ነበር። ነፍሱን ይማረውና ወንድሜ መርዕድም ከናታችን ከአቅሙ በላይ የሆኑ
ስራዎችን እየሰራ እኛን ለማሳደግ ብዙ መስዋዕትን ክፍሏል። እኔ የ15 ዓመት ልጅ እያለሁ አባታችን መሞቱን
ሰማን። አባቴ ከኛ ውጭ ልጅ ስላልነበረው የአባታችን ሀብት ለኛ ተፈርዶልን ሁሉን ወረስን።
ሊዲያ፦ የሞተው ወንድምህ መርዕድ ነው ያልከኝ?
ዳጊ፦ አዎ መርዕድ
ሊዲያ፦ ግን እንዴት ነው የሞተው?
ዳጊ፦ መርዕድ በአንድ ገዳም ውስጥ በዲቁና ያገለግል ነበር። አንድ ቀን ምሽት ገዳሙ በወንበዴዎች
ይቃጠላል። ታዲያ በዚያ ምሽት የነበሩ ካህናት፤ መነኮሳትና አገልጋዮች ታርደው ተቃጥለው ተገኙ ያኔ ነበር
መርዕድ የሞተው።
ሊዲያ፦ ወይኔ በጣም ነው እሚያሳዝነው… እኔ እምልህ ዳጊየ ይኸ እብዱ ልጅ ምናችሁ ነው ።
ዳጊ ፦ ማን…. መርዕድ /በመሣሣቱ እየደነገጠ/
ሊዲያ፦ መርዕድ???
ዳጊ ፦ /እየተርበተበተ ለመረጋጋት እየሞከረ/ አልኩ እንዴ እንደዛ …. አይ ስለሱ ስናወራ ስለቆየን እኮ ነው ….
እሱማ አባታችን ከሌላ የወለደው ወንድማችን ነው ። ዘመዶቹ በጠና ሲታመምባቸው እንደው ከወንድሞቹና
ከእህቱ ጋር ሲሆን ቢሻለው ብለው ከእኛ ጋር ይዘውት መጡ …. እኛም ለወንድማችን እንደ መርዕድ ነው
የምናየው። ደሞ እኮ መርዕድም እሱም አባታቸውን ነው የሚመስሉት
ሊዲያ፦ እህ... ቅድም አባታችን ከእኛ ውጭ ልጅ የለውም አላልከኝም?
ዳጊ ፦ ብያለሁ እንዴ …. ኧረ አላልሁም ምን አልባት በደንብ አልሰማሽኝ ይሆናል /እየተርበተበተ... ዞር ብሎ
በረጅሙ ይተነፍሣል/ …. ይልቅ እሱን ተይውና እንዴት ናፍቀሽኝ አንደነበር በናትሽ ሌላ ወሬ እያወራሽ
ሙዴን አትከንችው።
ሊዲያ፦ በቃ ባንተ ቤት ወሬ ኣስቀይሰህ ነው? እንዳውም ተጣልቸሀለሁ እሽ? ውይ ሊዱ ደሞ ማወቅ
እምትፈልጊውን ነገር ነገርኩሽ አደል እንዴ?
ሊዲያ፦ ምኑን ነገርከኝ እንዲ እየዋሸከኝ …. አንተ ገና እንዲ በመጀመሪያ ቀን የዋሸከኝ ትዳር ስንይዝማ እኔ
እንጃ….
ዳጊ፦ ተይ እንጂ እንዲህ አትሁኝ ሊዱየ /የእምቢታ ምልክት በትከሳዋ ታሳየዋለች / ስለፈራሁ እኮ ነው።
ሊዲያ ፦ ምኑን ነው ምትፈራው?
ዳጊ፦ ኡፍ!!! /በጭንቀት/… እንደዛ ከሆነ… ማለቴ እውነቱን እንድነግርሽ ከፈለግሽ ቃል አንድትገቢልኝ
አፈልጋለሁ
ሊዲያ፦ የምን ቃል?
ዳጊ፦ አሁን የምነግርሽን ነገር ለማንም አንደማትናገሪ።
ሊዲያ፦ /ለመስማት በመጓጓት/ አንተን ይንሳኝ …. ጌታን ደሞ እኮ በባል እና በሚስት መካከል ምንም ምስጢር
መኖር የለበትም …. ምስጢርህን ምስጢሬ አድርጌ ልጠብቅ ቃል እገባልሃለሁ
ዳጊ፦ በቃ እሺ ይኼ ወንድማችን ከኛ የደበቃቸው ብዙ ምስጢሮች አሉ። ከተቃጠለችው ገዳም ጋር እና
ከጠፉት ቅርሶች ጋርም ሳይገናኝ አይቀርም

ሊዲያ ፦ ምን… /በድንጋጤ ቆማ መልሳ ትቀመጣለች/ ማ …ለ…ቴ …. እንዴት? ማለቴ ቅርሶቹ የት እንዳሉ
ያውቃል?
ዳጊ፦ ይመስለኛል ብቻ እኔንጃ ባክሽ አንዳንዴ ሁላ ዝም ብዬ ሳየው መርዕድን ይመስለኛል። አንቺ ግን ምን
ይሰራልሻል ይሄን ማወቅ?
ሊዲያ፦ ኧረ ምንም ዝም ብዬ ነው /ወደ ጠረጴዛው ጠጋ ብላ ብርጭቆውን ትጥላለች/ ውይ ወይኔ
ብርጭቆው ወደቀ
ዳግም ፦ተይው ይሰበር ደግሞ ለብርጭቆ
ሊዲያ፦ እስኪ ብርጭቆውን ቀይረው
ዳግም ፦ ይቀየራል/ብርጭቆውን ይዞ ወደ ውሰጥ ይገባል/
/ደግሞ ወደ ውሰጥ እንደገባ ሊዲያ ስልኩን አውጥታ ትደውላለች/
ሊዲያ ፦ ሄሎ አለቃ... አሣው መረባችን ውስጥ ሳይገባ አይቀርም... የሆነ መረጃ አግኝቻለሁ አዎ እንዳሰብነው
መርዕድ በቃጠሎው ምክንያት ሞቷል ግን ቤት ውስጥ ያለው እብድ ልጅ ስለቅርሶቹ ሳያውቅ
አይቀርም...ብዙም ላስወራው አልቻልኩም ግን እብዱ ወንድማቸው ከመርዕድ ተብዬው ጋር የጠበቀ ግንኙነት
የነበራቸው ይመስላል... /ዳግም ጓዳ ከውስጥ ወጥቶ ከጀርባ ቆሞ ያዳምጣል/
/ወደ ጀርባዋ ስትዞር ታየዋለች/ በቃ ቻው በሗላ እደውላለሁ /ሊዲያ ስልኩን ዘግታ ወደ ጀርባ ስትዞር ዳግም
አሳት ጎርሶ ይጠበቃታል/
ዳግም፦ ምንድነው?
ሊዲያ፦ አይ ምንም አይደል ጓደኞቼ እኮ ደውለው እነሱን እያወራሁ ነው ምነው ቀናህ እንዴ? (ትጠጋዋለች)
ዳግም፦ በጣም እንጂ እንዴት ቀናሁ መሰለሽ ፤ ቆይ ማነሽ ለማን ነው ይሄን ምስጢር የተናገርሽው? (በጥፊ
ይመታታል
ወደኋላ ትሸሻለች)
ሊዲያ ፦ እባክህ ተረጋጋ ዳጊ... አንተ እንደምታስበው አይደለም።
ዳግም ፦ ዝም በይ አንች እስስት (አንገቷን ያንቃታል)
ሊዲያ ፦ አነቅኸኝ እኮ ዳጊ... ተው እሞትብሀለሁ... ስለፍቅራችን ብዬህ ተረጋጋ (ይለቃታል)ዳግም፦ ምን
መሆንሽ ነው ሊዱ... እንዴት እኔ አምኘሽ እንደዚህ ጉድ ታደርጊኛለሽ ሊዱ... ስንት መስዋዕትነት የተከፈለበትን
ምስጢር በአደባባይ ትዘሪዋለሽ?
(ከቦርሣዋ ውስጥ ሽጉጥ አውጥታ ትገድለዋለች። ከገደለችው በኋላ ደንግጣ ሽጉጡን ትጥለዋለች። ኩርምት
ብላ ትቀመጣለች)
ማክዳ፦ (እየሮጠች ትገባለች) ምንድን ነው...(ዳግምን ታየዋለች)... ዳጊዬ ... ዳግም... ወንድሜ (ታለቅሳለች...
በቁጣ ወደሊዲያ ትሄዳለች) ምንድን ነው ያደረግሽው አንቺ አረመኔ... ወንድሜን ገደልሽው (ሄዳ
ታንቃታለች)... አንቺ ነፍሠበላ አረመኔ (ሊዲያ እንደምንም ሽጉጡን ፈልጋ ትገድላታለች)
ሊዲያ፦ (ሽጉጡን እንደያዘች ትጮሀለች) ደንግጣ ወደግድግዳው ትሄዳለች። ጩኸቱን ሠምቶ አባ ገብረኪዳን
ይመጣል።
አባ ገ/ኪዳን ፦ (አካባቢውን ቃኝቶ ሽጉጡን እየተቀበላት) በጣም ጥሩ ስራ ነው የሠራሽው ሊዲያ። ለዚህ
ስራሽ ደግሞ ሽልማት ይገባሻል... አዝናለሁ ሊዲያ ምስጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም (ተኩሠው ይገድሏትና
ይወጣሉ)
እናት፦ ማክዳ... (ያይዋቸዋል)... ማክዳ... ማክዳ... ዳግም ልጄ... ልጆቼ (በምሬት እያለቀሠች) ኧረ የት ልግባ...
ኧረ ወዴት ልግባ... ኧረ የሠው ያለህ... ኧረ ምን ፍዳ ነው።
መርዕድ፦ ቤቶች ... (ልጆች ወድቀው እናት በምሬት እያለቀሱ ያያቸዋል። የያዘውን ኮተት ትቶ በፍጥነት
ወደነሡ ይሄዳል) ዳጊ... ዳጊዬ አትሙት... ማኪዬ... ማክዳ እባካችሁ ትታችሁኝ አትሂዱ። በለጋ እድሜዬ ድክ
ድክ ብዬ አሣድጌ ፍሬያችሁን ሳላይ ትታችሁኝ አትሂዱ... እናቴ ተነሡ በያቸው (እናቱን ያቅፋታል) እማ...
እናቴ በእኔ ጦስ ነው የሞቱት... ይቅር በይኝ እናቴ ...(እናት በድንጋጤ ትወድቃለች)
ትዕይንት ፮
(መጋረጃው ሲከፈት አባ ሳሙኤል ብቻቸውን በትካዜ ተቀምጠው ይታያሉ)
አባ ገ/ኪዳን፦ ምነው አባታችን በሠላም ነው እንዲህ ትክዝ ብለው የተቀመጡት?
አባ ሳሙኤል፦ አዎን በሠላም ነው... ዛሬ ማለዳ መልዕክት ደርሶኝ ነው እዚህ መቀመጤ።
አባ ገ/ኪዳን፦ የምን መልዕክት? ማን ነው የላከው?
አባ ሳሙኤል፦ ‘ገዳሙ ውስጥ እንዳገኝዎት’ ነው የሚለው ማን እንደሆነ ግን አልተገለጸም።
አባ ገ/ኪዳን፦ አብሬዎት ልቆይ ይሆን?
አባ ሳሙኤል፦ ግድ የለም... ግድ የለም እርስዎ ይሂዱ... እኔ ልጠብቃቸው። (አባ ገ/ኪዳን ይወጣሉ)
መርዕድ፦ (ከመድረክ ውጭ) አባቶች ጥሩኝ አባቶች ሞታችሁ ሞቴ ሊሆን ብርሃናችሁ ሊያበራልኝ
ይጠራኛል። ስለእውነት ስደታችሁን ልቀበል ጥሪያችሁ ይሰማኛል ፤ አባቶች የከሃዲዎች ሰይፍ በአንገቴ ቢዘረጋ
ቅርሴን ላላወጣ ከእውነት መንገድ ወደ ኋላ ላልል እናንተ የቀመሳችሁትን የሞት ፅዋ ልቀምስ … ቃል ለሰማይ
ቃል ለምድር …. ቅዱሳን አባቶች ለሰማዕትነት ተሹማችሁ በደማችሁ የህይወት ታሪክን ፃፋችሁ፡፡ የድል
አክሊልን አገኛችሁ፡፡ አባቶቼ እኔም እንደናንተ የአላውያንን የግፍ ስቃይ በመፍራት ከመንገዳችሁ ላልወጣ
ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር …. አባቶች ያሬድን አስታውስ አትርሳ... ስርዓትን እንዳትጥስ ማለታችሁን
አልዘነጋም። ግን እግዚአብሔር እንደጠበቃችሁ እንዲጠብቀኝ ድል ማድረግን እንዲሰጠኝ ለኔ ለደካማ ልጃችሁ
ለምኑልኝ፡፡ አባቶች አኩሪ ፍኖታችሁን ልከተል እናንተ ከሄዳችሁበት ከእውነት መንገድ ፈቀቅ ላልል ቃል
ለሰማይ ቃል ለምድር፡፡ (ንግግሩን ጨርሶ እየተንጎራደደ ሲሄድ ከአባ ሳሙኤል ጋር ይገናኛል)
መርዕድ ፦ አባታችን
አባ ሳሙኤል፦ አቤት የኔ ልጅ … ሠዓሊተ ምህረት ምንድን ነው የማየው? ዓይኔ ነው ወይስ መርእድ ነህ?
መርዕድ፦ …… መርዕድ ነኝ… መርእድ ነኝ አባቴ...
አባ ሳሙኤል፦ ምን መርዕድ …. እውን በህይወት አለህ? አቤት የእግዚአብሄር ስራው…. ረቂቅነቱ እስራኤልን
ከግብፅ አስወጥቶ ቀይ ባህርን ከፍሎ ያሻገረ አምላክ እውን አንትንም ከዚያ እቶን እሳት ውስጥ አትርፎ ለዚህ
አበቃህ ?
መርዕድ ፦ አዎ አባቴ አለሁ …. አዎ እግዚአብሄር አትርፎኛል ይባርኩኝ አባቴ (እግራቸው ስር ይደፋል )
አባ ሳሙኤል፦ ተነስ ልጄ ተነስ እግዚአብሄር ይባርክህ … እኔ እምልህ መርዕዴ እስካሁን የት ነበርክ እኛ እኮ
በሳት ተቃጥለህ አመድ ሆነሀል ብለን ተስፋ ቆርጠን ነበር …… ቆይ እንዴትስ ተረፍክ?
መርዕድ ፦ አለሁ አባቴ እኔማ በእግዚአብሄር ታምር ተረፍኩ …… የቃጠሎው ምሽት ወንበዴዎች ቃጠሎውን
ካቃጠሉ በኋላ ቅርሶቹን ሲፈልጉ አየኋቸው እናም ቅርሶቹን ማትረፍ እንዳለብኝ ገባኝ ቅርሶቹንም ይዤ
ከቦታው ተሰወርኩ ስል እራሴን ቀይሬ ተቀመትኩ ወንበዴዎቹ ግን አሁንም ከለቀቁኝም ያለሁበትን ቦታ
አነፍንፈው ደርሠው ቤቴ ድረስ መተው ወንድሜንና እህቴን ገደሉብኝ። አባቴ ፈተናዬ በዝቷል እኔ አቅቶኛል
ይህን አደራ ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም አባቴ አደራዬን ይቀበሉኝ (በጀርባው የተሸከመውን አኩፋዳ
እየሰጣቸው)
አባ ሳሙኤል፦ እውነት ቅርሶቹም እስካሁን አሉ? ተመስገን አምላኬ ላንተ ምን ይሳንሃል የዘገየህ ቢመስልም
እንኳን የሚቀድምህ የለም። ተመስገን (እያለቀሰ መሆኑን አይተው) ተው እንጂ ልጄ እንዲህ አትሁን
እግዚአብሄ ር እኮ ፈተናውን የሚያበዛብህ በወዳጆቹ ላይ ነው… አየህ መርዕድ ይህ ታሪክ ከዚህ አለማዊ
ነገሮች አሳጥቶህ ይሆናል ነገር ግን ሀገርህን ታሪክህን ሀይማኖትህን ጠብቀህበታል። ትውልድን አትርፈሀል
በዚህም ደግሞ ደስ ሊልህ ይገባል (ሁለት ፖሊሶች ወደ እነሱ ይመጣሉ)ፖሊስ 1፦ አቶ መርዕድ
በቤተክርስቲያን ማቃጠል ወንጀል እና በሰው ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል
መርዕድ፦ እባኮህ አባቴ አድኑኝ ይገሉኛል
አባ ሳሙኤል፦ ምንድነው የምታወሩት እሱ መልካም ሰው ነው፡፡ ምንም ደም እጁ ላይ የለበትም፡፡
ፖሊስ 2፦ እርሱን ለኛ ተውት በፖሊስ ስራ ውስጥ ጣልቃ አይግቡ (መርእድን እያዳፉ ይወስዱታል። አባ
ለመከተል ይሞክራሉ ይርቋቸዋል።)
መርዕድ፦ እባካችሁ ተውኝ ... እባካችሁ ልቀቁኝ ...
(ፖሊሶቹ ካለፉ በኋላ)
ጭምብል ለባሽ፦ እንዳይንቀሳቀሱ ባሉበት ይቁሙ…. (መነኩሴው ለማምለጥ ወደተዘጋው መጋረጃ እየሮጡ
ይገባሉ። ወንበዴዎቹም እያባረሩ ይከተሏቸዋል።መጋረጃ ውሰጥ የሩጫ እግር ኮቴ ይሰማል ያዛቸው ያዛቸው ….
በላቸው በላቸው የሚል ድምፅ ይሰማል)
ወንበዴ፦ ቅርሱን የት አስቀመጡት?
አባ ሳሙኤል፦ እባካችሁ ተውኝ አ…… አ…… አ…… ይላሉ……
ትዕይንት ፯
መጋረጃ ሲከፈት አባ ተ/ማርያም እና መርዕድ በሰንሰለት ታስረው ከፊታቸው ሁለት ጋርዶች ቆመው
ይታያሉ፡፡ ሚኒስቴሯ ከሁለት ሰዎች ጋር ትገባለች…. እጆቿን ወደኋላ አጣምራ ትንጎራደዳለች
ሚኒስቴር፦ እናንተ ግን ምን ጉዶች ናችሁ? ለምን ትግስታችንን ትፈታተናላችሁ… ኧረ ከሌላውስ የተለየ
ለታሪክና ለእምነት አጉል ተቆርቋሪ ያደረጋችሁ ማነው?
አባ ሳሙኤል፦ እኛማ በእውነት መሰረት ላይ የታነፀች ርትዕት የሆነች ተዋህዶን ያመንን የስላሴ የእጅ ስራዎች
ለመመረጥ የበቃን እድለኞች ነን፡፡
ጋርድ 1፦ ዝም በል! ደግሞ መልስ ይሰጣል ዘልዛላ
ሚኒስቴር፦ ተው ቆይ እስኪ ይልቅ የእብደት ተግባርህን ትተህ የሰወርካቸውን እቃዎች መፃህፍት ብትሰጠን
ይሻላል መጻህፍቶቹ ከናንተ ይልቅ ለኛ ያስፈልጋሉ… አያችሁ መጻህፍቶቹን እጁ ውስጥ ለማስገባት አለም
በጉጉት ይጠብቃል። ይሄ ኝ ለእኛ ሁለተኛ ጉዳያችን ነው።የእኛ ዓላማ ቤተክርስቲያኗ ከህንጻዎቿ ባሻገር
ደምቃ የታተመችባቸውን ታሪኳንና የደመቀ አሻራዋን ማጥፋት ነው። መጽሐፍቱ እጃችን ውስጥ ከገቡ ደግሞ
ጫራታውን ሞቅ አርገን በብዙ ሚሊዬን ዩሮዎች እንቸበችባቸዋልን
መርዕድ፦ የክርስቲያን ጦር ያሸንፋል ታሪክ አይጠፋም
ሚኒስቴር ፦ (ጯ ...በጥፊ ትመታዋለች) … ዝም በል! አውቆ አበድ …. ሽማግሌው አድምጠኝ ለምን ሞኝ
ትሆናላችሁ ዛሬ እናንተ አሳልፋችሁ ባትሰጡን ነገ ከነገ ወድያ መፅሀፍቶቹን እጃችን ውስጥ ማስገባታችን
የማይቀር ነገር ነው ስለዚህ ወይ የድግሱን ቅርጫ አልያም ምትን ትመርጣላችሁ፡፡
አባ ሳሙኤል፦ እሰየሁ በሀጥኣን እጅ በሰማዕትነት ማረፍ እሰየሁ ስለ ተስፋ ቃሉ በአላውያን እጅ በሰማዕትንት
ማረፍ። ምን ጊዜም እኮ ወርቅና አማኝ በእሳት ነው የሚፈተነው፡፡ ክቡርነትዎ በስሙ መሰቃየት ስለስሙ
መሞት እንዴት ያረካል መሰለሽ… ስለዚህ በሰማዕትነት መሞት ሞት ሳይሆን ክብር ነው አዎ፡፡
ሚኒስቴር፦ አንተኛውስ ምን ትላለህ?
መርዕድ፦ ሙት ውዳቂ ነው አንፈራም፡፡ እመኝኝ ክቡርነቶ መቼም ቢሆን መጽሐፍቱን አታገኟቸውም።
ሚኒስቴር ፦ አንድ እድል ብቻ አላቹ ምንአልባት በምታውቁት ሰው ስትጠየቁ ይሻል ይሆናል አስገቡት
/አባ ገ/ኪዳን በመነኩሴ ልብሳቸው ከአንድ ጋርድ ጋር ይገባሉ።/
አባ ሳሙኤል:- /በድንጋጤ/ አባ እርሶንም ያዙዎት። አይፍሩ የሁሉም ጌታ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው
አባ ገ/ኪዳን:- ማነው የተያዘው? እኔ የመጣሁት ከምትሞቱ ቅርሶቹ ያሉበትን በሰላም እንድትናገሩ
ላስጠነቅቃቹ ነው?
መርዕድ:- አልገባኝም አባ ምንድን ነው እየተካሄደ ያለው
አባ ገ/ኪዳን:- እስከዛሬ ከስራቹ ሰቀመጥ እንደናንተ ጅል አደረጋቹኝ እንዴ? ብለው ቆቡንና አስኬማውን
ያወልቁታል። ሁለቱም በድንጋጤ ያዩዋቸዋል
መርዕድ:- እንዴ እነዳጊ የተገደሉ ለት ከኛ ቤት ሲወጡ አይቾታለው እኮ እርሶ ኖት የዚ ሁሉ ጠንሳሽ
አባ ሳሙኤል:- ያኔ ከሚኒስትሯ ቢሮ ስወጣ በር ላይ ተጋጭተን ነበር። ያለነገር አልነበረም ጀርባዬን የከበደኝ።
ምን ያለው ሴጣን ቢጠጎት ነው ይሄን ሁሉ በቤተክርስቲያን ላይ
አባ ገ/ኪዳን:- ሀሀሀሀ ምን ይሉት ሴጣን? ገንዘብ የሚሉት መልአክ ነው እንጂ 1000 መፅሀፍት ይዛቹ
ቤሳቤስቲን የሌላቹ ችግረኞች፤ በዩሮ በዶላር መመንዘር የሚችል ሀብት ይዛቹ ፍርፋሪ የምትለምኑ ደሀዎች
ናቹ። አሁን ይሄን እድል ተጠቀሙበትና ይኼ ከላያቹ ላይ የማይወልቀውን ብጫቂ ቀይሩበት። ቅርሶቹ የት
ናቸው?
አባ ሳሙኤል:- አንዲት ቃል ከአፋችን ከምትወጣ ምላሳችን ተበጥሳ ትጣል።
መርዕድ:- አትልፉ ቅርሶቹን መቼም አታገኟቸውም ግደሉን ለኛ ክርስቲያኖች ሞት ክብራችን ነው::
ሚኒስቴር፦ በቃቹ ትዕግስቴን ነው የጨረሳችሁት ከዚህ በላይ ለእናንተ ጊዜ መስጠት ተገቢ አይደለም (ሽጉጥ
ከጋርዱ ላይ መንትፋ ታወጣለች መነኩሴው ላይ ትደቅናለች)
ካብኔ 2፦ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ በቁጥጥር ስር ኖት ኮማንደር ወደ ውስጥ ግባ (ሁለት
ፖሊሶች ይመጣሉ) አዩ አለቃዬ እናንተ በቤተክርስቲያን ላይ ወንበዴዎችን አስርጋችሁ እንደምታስገቡት ሁሉ
ቤተ ክርስቲያንም ስለ ደህንነቷ የሚቆረቆሩላት ልጆች አስተምራ ለዚህ አብቅታለች ምንም እንኳን በስልጣን
በልጣችሁ ብዙ ነገር ብታደርጉም እኛም ስለ ቤተክርስቲያናችን እስከ ሞት ድረስ እንታገላለን….
ኮማንደር፦ በቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቅ ደባን በመፈፀም በቅርስ ምዝበራ እንዲሁም በሰው መግደል ወንጀል
ስለተጠረጠራችሁ በቁጥጥር ስር ውላችኋል……

**************
**********
*****
*
ወስብሐት ለእግዚአብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!!

You might also like