Professional Documents
Culture Documents
All Document Reader 1710961360104
All Document Reader 1710961360104
All Document Reader 1710961360104
ፎቅ ከተባሉ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት እንዳለው የእንጨት ደረባ ቤት ዓይነት ካልሆነ በስተቀር
እንደ ዛሬው ተመልካችን በውበታቸው የሚያነሆልሉ ሰማይ ጠቀስ ቤቶችን አዲስ አበባ ገና አልተዋወቀችም
ነበር።
ከእኒያ ጕስቁል የአዲስ አበባ ሰፈሮች መካከልም ጠመንጃ ያዥ በመባል የምትታወቀው አንዷ ሠፈር
ነበረች:: ጠመንጃ ያዥ እንደ ሌሎቹ የሀገራችን ቦታዎች በተወላጆቿ የምትለማ፣ ሕጻናት እንደ ልብ
የሚቦርቁባት፣ ኮረዶች ፍቅርን በነፃነት የሚሸምቱባት፣ ወጣቶች እንዳሻቸው የሚፈነጩባት አልነበረችም፡፡
በአንጻሩም ጣሊያኖችና ባንዳዎች በአስነዋሪ ድርጊታቸው የሚጠየቁባት ሰዓት መቅረቧን አውቀው እንደ ባሕር
ምንም እንኳ ዘመኑ እንደ_ ወትሮው በነፃነት መቦረቅ የተከለከለበት ቢሆንም፣ መስከረም የጸደይ ወራት
መግቢያ በመሆኑ ጋራው ሸንተረሩ፣ በተፈጥሮ ጌጥ መንቈጥቈጥ ጀምሯል፡፡
በአጭር አነጋገር እኔ ተወለድሁና ወላጆቼ በደስታ ወይን ስከሩ፡፡ ይሁን እንጂ በማላውቀው ምክንያት የወላጆቼን
/
እያልሁ የምጠራቸው አያቴ ወ ሮ ነገኤ ዲንሳ ወሊሶ ይኖሩ
ነበርና በስድስተኛ ወሬ ወደዚያው ወሰዱኝ፡ አባቴ አቶ ገሠሠ ወልደ ኪዳን አገሩ ቡልጋ ሲሆን፤ የአባቴ እናት
( ) /
አያቴ ወ ሮ ሐበሻ ሁሴን አሊ ሰዲቅ ደግሞ የወሎ ተወላጅ ናቸው ::
እናቴ ወ ሮ ጌጤነሽ ጉርሙ /
ግን ከወሊሶ አለፍ ብሎ ከሚገኘውና ‹‹ጐሮ›› እየተባለ በሚጠራው ወረዳ ውስጥ ነው የተወለደችው፡፡ እናቴ
ሙስሊም ነበሩ :: /
የአባቴ አባት አያቴ አቶ ወልደ ኪዳን የኋላዬ ወ ሮ ሐበሻን ያገቡት በስገሌ ዘመቻ
ላይ ተገናኝተው ነው ::
ከጋብቻቸው በኋላም ክርስትና አስነሥተዋቸው ወ ሮ ሐበሻ ግዛው ተብለው /
ተጠሩ። እኔም አልተጠመቅሁም ነበር፡፡ እናቴንና ሴት አያቴን ክርስትና ያስነሥዋቸው አያቴ አቶ ወልደ ኪዳን
ኮልፌ አካባቢ ነው :: ኮልፌ የሄድኩበት ምክንያት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አባቴ ከጠመንጃ ያዥ ሠፈር ወደ
ኮልፌ በመዛወሩ ምክንያት ነው፡፡
አባቴና ዘመዶቼ ሲናፍቁኝ ከወሊሶ እመጣና ለተወሰነ ጊዜ እርሱ ዘንድ እቆይ ነበር፡፡
የወሊሶው ሠፈራችን በተለምዶ ‹‹አረብ ተራ›› ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ ዛሬ ቀበሌ ዜሮ ሦስት በሚል ስያሜ
የትምህርት ቤታችን ስም ግዮን›› ይባል ነበር። በኋላ ስሙ ተለውጦ ‹ራስ ጐበና አባ ዳጨው፡ ተብሏል ::
በአሁኑ ወቅት የትምህርት ቤቱ ስም ወሊሶ ሊበን , ተብሎ ተሠይሟል :: ትምህርት ቤት ከገባሁ በኋላ
( ጥበቡ በቀለ፣ ከበደ ዓለማየሁ፤ ሰናይ፣ ሽፈራው ጥላሁን፤ ..." የሚባሉ ጓደኞችንም ማግኘት
/
ያስተምሩን እንደ ነበር አስታውሳለሁ፡፡ የት ቤቱ ዲሬክተር
ዛፍ ላይ ወጥተን ያንን ቆላዲ እየተሻማን ስንለቅም የዛፉ ቅርንጫፍ ይገነጠልና ከሥር ካለው ባሕር ውስጥ
እንገባለን፡፡ ከሁላችንም ለአደጋ የተጋለጠው ዘሪሁን ጆቴ ነበር፡፡ እሱን ለማውጣት ስንረባረብ ለካስ አካባቢው
የሽፍቶች መናኸሪያ ኖሯል፤ ድንገት ጥይት ይተኵላል። በዚህ ጊዜ የት እንግባ ?አትምህርት ቤት ጠፍተን
ነው የመጣነው፡ ወላጆቻችን የት እንዳለን አያውቁም። የሚገርመው ነገር የጥይት ድምፅ ለመጀመሪያ ጊዜ