Professional Documents
Culture Documents
Training Proposal On Monosex Tilapia Fish Feed and IAA at NFALRC Final Version
Training Proposal On Monosex Tilapia Fish Feed and IAA at NFALRC Final Version
ስለተቀናጀ የዓሣ ግብርና፤ የዓሣ ምግብ፤ ጫጩት አረባብ እና የወንድ ቆረሶ ዓሣን ለይቶ
ስለማሳደግ
ርዕስ፡- የተቀናጀ ዓሣ ግብርና፤ የወንድ ቆረሶ ዓሣን ለይቶ የማሳደግ እና ስለ ዓሣ ምግብ ዓይነቶች ግንዛቤ
ማስጨበጫ ስልጠናና ሠርቶ ማሳያ
የስልጠናና ሠርቶ ማሳያው ቦታ፡ በብሔራዊ ዓሣ እና የውኃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል፤ ሰበታ
ከምስራቅ ሸዋ (ቢሾፍቱ)፤ ከምዕራብ ሸዋ (ኤጀርሳ፤ ቶኬ፤ ጅባት፤ ቀርጫ ቡሌሆራ) እንዲሁም ከደቡብ
ምዕራብ ሸዋ ወንጪ ወረዳ
የሰልጣኞች አይነት፡ ዓሣ የሚያረቡ አርሶ አደሮች፤ እንዲሁም የወረዳ ባለሙያዎች እና የቀበሌ ልማት ጣቢያ
ሠራተኞች
አሠልጣኞች፡- 2
የጽዳት ሠራተኞች፡- 2
አስተናጋጅ፡- 1
ሾፌር፡- 1
ማዕከል ዳይሬክተር፡- 1
አይሲቲ፡- 1
እንደሚታወቀው ማዕከላችን በዓሣ ግብርና ዙርያ አብረውን ለሚሠሩ እና እየሠሩም ላሉ የተለያዩ አካላት
ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ሥራ እየሠጠ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በፊት በማሕበራዊ የምርምር ዘርፍ
በተደረገው የዳሠሣ ጥናት ውጤት መሠረት እና በተከታታይነት ባገኘናቸው የአቅም ግንባታ ፍላጎቶች
መሠረት አሁን እየተገበሩ ላሉት የዓሣ ግብርና ሥራም ሆነ በቀጥይነት ላሰብናቸው በራስ (በአምራቹ) አቅም
ለሚከወኑ የማስፋፋት ሥራዎች ይረዳ ዘንድ ለዓሣ ግብርና እንደ ዋና ተግዳሮት ከሆኑት መካከል ከኩሬ አያያዝ
በተጨማሪ እንደ ዓሣ ምግብ፤ እና ጫጩት የመሣሠሉት ዋነኞቹ ሲሆኑ እነዚህን እና ሌሎቹንም በዘላቂነት
ለመፍታት ቅድሚያ የአቅም ግንባታ አስፈላጊ ስለሆነ ይህንንም በመረዳት እስከዛሬ ስንሰራባቸው ከነበሩ ዞኖች
እና በተጨማሪነት በእቅድ ከተያዙ ወረዳዎች መካከል ከዞን ምስራቅ፤ ምዕራብን እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞንን
እንዲሁም በወረዳ ደረጃ ከምዕራብ ሸዋ ኤጀርሳ፤ ቶኬ፤ ጅባት፤ ቀርጫና ቡሌሆራ፤ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን
ደግሞ ወንጪ ወረዳን የሚያሳትፍ የሥልጠናና ሠርቶ ማሳያ መርሐ ግብር ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የሥልጠናና የሠርቶ ማሳያው መርኃ ግብር በአጠቃላይ የታቀደው ለ 6 ቀናት ሲሆን አጠቃላይ ተሳታፊውም ለ
ወረዳ ይጋበዛሉ፡፡ በአጠቃላይ ሁለቱም ዙሮች እያንዳናዳቸው አጠቃላይ የጉዞ ቀናትን ጨምሮ 3 ቀናትን
ይወስዳሉ፡፡ የስልጠና በመርኃ ግብሩም የመጀመሪያው ቀን ከላይ በተለዩት አርዕስት ሥልጠና በመስጠት
በተከታዮቹም ሁለት ቀናት በአሠልጣኝ የተደገፈ እና በሠልጣኞችም የሚብራራ የሠርቶ ማሣያ ተግባራት
በአጠቃላይ የዚህ ሥልጠናና ሠርቶ ማሣያ ዓላማም በመስክ ዳሰሳ ጥናት እና የግምገማ ጉብኝት ወቅት በዓሣ
አምራቹ ዘንድ ከዚህ በፊት በተለዩ የአቅም ውስንነቶች ላይ ተመርኩዘን ለምሳሌ በተቀናጀ የዓሣ ግብርና ዘዴ
ሠርተን ለማሳየት እንዲሁም ከሠልጣኞች የሚመጠትን እና ምርምሩን አቅጣጫ ለማስያዝ የሚረዱ ግብረ
መልሶችን ለመሰብሰብ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ጋር ዘላቂ ትስስርን ለመፍጠርም
በዓሣ ግብርና ላይ ተሳታፊ የሆኑ አርሶ አደሮች በራሳቸው የዓሣ ጫጩትን እንዲባዙ
የሚስችላቸውን እውቀት እና ክህሎት ማስጨበጥ
ለዓሣ ምግብነት ሊውሉ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች (የኑግ ኬክ ወይም ፋጉሎ፤
የስንዴ ብጣሪ ወይም ፉሩሽካና የቢራ እህል ጭማቂ) ቢያንስ ከእያንዳንዱ አንድ አንድ ኪሎ
በጎድጓዳ ሳህን)
ሁለት ወላድ አሶች እና አንድ ለማሳያነት የሚውል ኩሬ
አንድ ጫጩት ዓሶችን የያዘ ኩሬ (ቢያንስ ለማሳያነት የሚሆኑ ሁለት ጫጮቶችን ማግኘት
የሚቻልበት)
በሙከራ ላይ ያለ የተቀናጀ ዓሣ ግብርና ሰርቶ ማሣያ ቦታ (ለምሳሌ የተቀናጀ የዓሣ ግብርናው
ቦታ ወይም መንደር ዶሮን፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መስሪያ ቦታን፤ ደክ ዊድ እና አዞላ የውኃ
ውስጥ የዓሣ ምግቦችን፤ የአትክልት እና አልፋልፋ ሰብል ማሳን ሊያካትት ይችላል፡፡
በብሔራዊ ዓሣና የውኃ ውስ ሕይወት ምርምር ማዕከል ቅጽር ግቢ ውስጥ ለሚካሔደው የሠርቶ ማሳያ መርኃ
ግብር የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ብዛት እና የሚመረጡባቸው ወረዳዎች
ከእያንዳንዱ ወረዳ አንድ አንድ ሾፌር ቢመጣ ተብሎ ታስቦ አጠቃላይ ከ 5 ሾፌር ጋር 49 ተሳታፊዎች
ይጋበዛሉ፡፡
በብሔራዊ ዓሣና የውኃ ውስ ሕይወት ምርምር ማዕከል ቅጽር ግቢ ውስጥ ለሚካሔደው የሠርቶ ማሳያ መርኃ
ግብር የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ብዛት
1.2 የመስተንግዶ ወጪ
ተ.ቁ የተሳታፊ ብዛት የመስተንግዶ ወጪ በአንድ ሰው የሥልጠናው ቀን ብዛት አጠቃላይ ክፍያ
1 42 280 3 35,280
1.4 የመጓጓዣ ወጪ
ተ.ቁ የተሳታፊ ብዛት ደርሶ መልስ የመጓጓዣ ወጪ በአንድ ሰው የጉዞ ብዛት አጠቃላይ ክፍያ
1 27 200 ደርሶ መልስ 5,400
2.2 የመስተንግዶ ወጪ
ተ.ቁ የተሳታፊ ብዛት የመስተንግዶ ወጪ በአንድ ሰው የሥልጠናው ቀን ብዛት አጠቃላይ ክፍያ
1 53 280 3 44,520
2.4 የመጓጓዣ ወጪ
ተ.ቁ የተሳታፊ ብዛት ደርሶ መልስ የመጓጓዣ ወጪ በአንድ ሰው የጉዞ ብዛት አጠቃላይ ክፍያ
1 37 200 ደርሶ መልስ 7,400