Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 5

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

የብሔራዊ ዓሣና የውኃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል

ስለተቀናጀ የዓሣ ግብርና፤ የዓሣ ምግብ፤ ጫጩት አረባብ የወንድ ቆረሶ ዓሣን ለይቶ
ስለማሳደግና መሠረታዊ የዓሣ ግብርናን አስመልክቶ የተዘጋጀ

የስልጠናና ሠርቶ ማሣያ ትግበራ ንድፈ ሐሳብ እቅድ

የግብርና ኤክስቴንሽንና ኮሚኒኬሽን የሥራ ሂደት


አዘጋጅ፡ ያሬድ መስፍን

የካቲት 24 ቀን‚ 2013 ዓ.ም


የብሔራዊ ዓሣ እና የውኃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል
ሰበታ

ርዕስ፡- የተቀናጀ ዓሣ ግብርና፤ የወንድ ቆረሶ ዓሣን ለይቶ ስለማሳደግ ፤ ስለ ዓሣ ምግብ ዓይነቶች እንዲሁም
መሠረታዊ የዓሣ ግብርናን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ሠርቶ ማሳያ

የስልጠናና ሠርቶ ማሳያው ቦታ፡ በብሔራዊ ዓሣ እና የውኃ ውስጥ ህይወት ምርምር ማዕከል፤ ሰበታ
ተሳታፊ ሰልጣኞች የሚመረጡባቸው ዞኖች፡-

ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን

የሰልጣኞች አይነት፡ ዓሣ የሚያረቡ አርሶ አደሮች፤ እንዲሁም የወረዳ ባለሙያዎች እና የቀበሌ ልማት ጣቢያ
ሠራተኞች

ከውጭ የተጋበዙ አጠቃላይ ተሳታፊዎች ብዛት፡ 13

ዓሣ አርቢ አርሶ አደሮች፡- 10

የወረዳ ባለሙያዎች እና የቀበሌ ልማት ጣቢያ ሠራተኞች፡- 2

ሾፌሮች፡- 1

በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ የማዕከሉ ሰራተኞች

አጠቃላይ ተሳታፊ የማዕከሉ ሠራተኞች ብዛት፡- 8

ተመራማሪዎች= 4

ሒሳብ ሠራተኛ=2

ሾሬር =1

መስተንግዶ =1

የስልጠናና ሠርቶ ማሣያው አስፈላጊነት

እንደሚታወቀው ማዕከላችን በዓሣ ግብርና ዙርያ አብረውን ለሚሠሩ እና እየሠሩም ላሉ የተለያዩ አካላት

ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ሥራ እየሠጠ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በፊት በማህበራዊ የምርምር ዘርፍ

በተደረገው የዳሠሣ ጥናት ውጤት እና በተከታታይነት ባገኘናቸው የአቅም ግንባታ ፍላጎቶች መሠረት አሁን

እየተገበሩ ላሉት የዓሣ ግብርና ሥራም ሆነ በቀጥይነት ላሰብናቸው በራስ (በአምራቹ) አቅም ለሚከወኑ

የማስፋፋት ሥራዎች ይረዳ ዘንድ ለዓሣ ግብርና እንደ ዋና ተግዳሮት ከሆኑት መካከል ከኩሬ አያያዝ በተጨማሪ
እንደ ዓሣ ምግብ፤ እና ጫጩት የመሣሠሉት ዋነኞቹ ሲሆኑ እነዚህን እና ሌሎቹንም በዘላቂነት ለመፍታት

ቅድሚያ የአቅም ግንባታ አስፈላጊ ስለሆነ ይህንንም በመረዳት እስከዛሬ ስንሰራባቸው ከነበሩ ዞኖች በአንዱ

ላይ ሥልጠናና ሠርቶ ማሣያን ማከናወን አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከስልጠናውና ሠርቶ ማሳያው ይገኛል ተብሎ የሚታሰበው እውቀትና ክህሎት

 የተሳታፊ አርሶ አደሮችን የሥራ ተነሳሽነት መጨመር

 በዓሣ ግብርና ላይ ተሳታፊ የሆኑ አርሶ አደሮች በራሳቸው የዓሣ ጫጩትን እንዲባዙ
የሚስችላቸውን እውቀት እና ክህሎት ማስጨበጥ

 አማራጭ የዓሣ ምግቦችን በአካባቢያቸው ከምን ሊያገኙ እንደሚችሉ ማሳወቅ እንዲሁም


የወንድ ቆረሶ አሶችን ብቻ መርጦ በማሳደግ ሁለቱንም ጾታዎች አንድ ኩሬ ውስጥ ከማሳደግ
ይልቅ የተሻለ እድገትን እንደሚያሳይ እና የዓሣ ግብርናን ከሌሎች የግብርና ሥራዎች (ሰብልና

እንስሳት) ጋር በማቀናጀት የተሸለ አጠቃላይ ምርት እንዲሁም ወጪ ቀናሽ አማራጮችን


ማሳወቅ ናቸው፡፡

ለስልጠናውና ሠርቶ ማሳያው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችና ፋሲሊቲዎች

 ለዓሣ ምግብነት ሊውሉ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶች (የኑግ ኬክ ወይም ፋጉሎ፤

የስንዴ ብጣሪ ወይም ፉሩሽካና የቢራ እህል ጭማቂ) ቢያንስ ከእያንዳንዱ አንድ አንድ ኪሎ

በጎድጓዳ ሳህን)
 ሁለት ወላድ አሶች እና አንድ ለማሳያነት የሚውል ኩሬ
 አንድ ጫጩት ዓሶችን የያዘ ኩሬ (ቢያንስ ለማሳያነት የሚሆኑ ሁለት ጫጮቶችን ማግኘት

የሚቻልበት)
 በሙከራ ላይ ያለ የተቀናጀ ዓሣ ግብርና ሰርቶ ማሣያ ቦታ (ለምሳሌ የተቀናጀ የዓሣ ግብርናው
ቦታ ወይም መንደር ዶሮን፤ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መስሪያ ቦታን፤ ደክ ዊድ እና አዞላ የውኃ
ውስጥ የዓሣ ምግቦችን፤ የአትክልት እና አልፋልፋ ሰብል ማሳን ሊያካትት ይችላል፡፡

ከውጭ የሚጋበዙ ተሳታፊዎች ዝርዝር

በብሔራዊ ዓሣና የውኃ ውስ ሕይወት ምርምር ማዕከል ቅጽር ግቢ ውስጥ ለሚካሔደው የሠርቶ ማሳያ መርኃ
ግብር የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ብዛት እና የሚመረጡባቸው ወረዳዎች

ተ.ቁ ተሳታፊዎች የሚመጡበት ቦታ ተሳታፊ ብዛት ወንድ ሴት

1 ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እና የማዕከሉ አርሶ አደሮች 10 8 2


ሠራተኞች የግብርና ባለሙያ 1 1 -
የልማት ጣቢያ ሠራተኛ 1 - 1
ተመራማሪዎች 4 4 -
ሾፌር 2 2 -
ሒሳብ ሠራተኛ 2 - 2
መስተንግዶ 1 - 1
ጠቅላላ የተሳታፊ ብዛት 21 15 6

የስልጠና በጀት

1.1. የስልጠና ውሎ አበል

ተ. ተሳታፊ የተሳታፊ የቀን አበል የሥልጠና አጠቃላይ


ቁ ብዛት ው ቀን ክፍያ
ብዛት
አርሶ አደሮች 10 250 4 10,000
የግብርና ባለሙያ 1 400 4 1,600
ከውጭ የመጣ ሾፌር 1 200 4 800
አሠልጣኝ 1 300 5 1,500
ተመራማሪዎች (አስተባባሪዎች) 3 300 4 3,600
ሒሳብ ክፍል (ሒሳብ ሠራተኛ) 1 301 4 1,204
ሒሳብ ክፍል (ገንዘብ ከፋይ) 1 259 4 1,036
አስተናጋጅ 1 259 4 1,036
የማዕከል ሾፌርና 1 301 4 1,204
ድምር 21 - - 21,980

1.2 የመስተንግዶ ወጪ
ተ.ቁ የተሳታፊ ብዛት የመስተንግዶ ወጪ በአንድ ሰው የሥልጠናው ቀን ብዛት አጠቃላይ ክፍያ
1 20 280 2 11,200

የስልጠናው አጠቃላይ ወጪ

ለ 21 የስልጠናው ተሳታፊዎች የአበል ክፍያ = 93,874

አጠቃላይ የመስተንግዶ ወጪ= 65,520

አጠቃላይ የመጓጓዣ ወጪ= 12,900


ድምር--------------------- 172,294 ብር

አጠቃላይ በጀት = 174,094

የስልጠናው ቀን፡- መጋቢት 15፣ 2013 ዓ.ም

You might also like