Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

ቁጥር፡-

ቀን፡-

የማጓጓዣ ውል
አንቀጽ አንድ

ተዋዋይ ወገኖች
ይህ ውል የተደረገው ከዚህ በኋላ አጓጓዥ ተብሎ በሚጠራው
___________________________________________ አድራሻው ክ/ከተማ
_______________ወረዳ ____የቤ/ቁ. ስልክ ፋክስ
በሆነው
እና

ከዚህ በኋላ አስጫኝ ተብሎ በሚጠራው________________________________


አድራሻው___________________ክ/ከተማ ________ወረዳ__________የቤ/ቁ ___________ስልክ
በሆነው መካከል ነው፡፡

አንቀጽ ሁለት
የውሉ ዓለማ
ይህ ውል የተደረገው አስጫኙ መጠኑ፤ መዳረሻው እና የማጓጓዣ ዋጋው ከታች በተ/ቁ. 3 ላይ የተገለፀውን
ጭነት አጓጓዥ እንዲያጓጉዝለት በመፈለጉና አጓጓዡም ጭነቱን ከታች በዝርዝር በተመለከተው መሰረት
ለማጓጓዝ በመስማማቱ ነው፡፡

አንቀጽ ሶስት
የጭነቱ መጠን፣ መዳረሻና ዋጋ
3.1. አጓጓዥ የመጫን አቅማቸው 400 (አራት መቶ) ኩንታል የሆኑ የጭነት መኪኖችን የሚያቀርብ ሲሆን
ጭነቱም የሚጓጓዘው ከታች በሠንጠረዡ እንደተገለጸው ይሆናል፡፡

ተ.ቁ የጭነቱ አይነት የጭነቱ መነሻ የጭነቱ የማጓጓዣው የክፍያው ሁኔታ


መድረሻ ታሪፍ
1

3.2. አስጫኝ ጭነቱን ሲያስጭን የተጫነው ጭነት ከ 400 (አራት መቶ) ኩንታል የሚበልጥ ሆኖ ከተገኘ
በተጫነው ኩንታል ልክ ለአጓጓዥ ለመክፈል የተስማማ ሲሆን የጭነቱ ልክ ግን ከ 400 (አራት መቶ)
ኩንታል ያነሰ ሆኖ ከተገኘ በመኪናው የመጫን አቅም ልክ ማለትም በ 400 (አራት መቶ) ኩንታል ታስቦ
የማጓጓዣን ዋጋ ለአጓጓዥ ይከፍላል፡፡ በተጨማሪም የተጫነው ክብደት በመሬት ሚዛን ሲመዘን በሰነዱ
ላይ ካለው በልጦ ከተገኘ ክፍያው የሚታሰበው በሚዛኑ ክብደት መሰረት ይሆናል፡፡

አንቀጽ አራት

የአጓጓዥ መብትና ግዴታ

4.1. አጓጓዥ ጭነቱ ከተጀመረ ጀምሮ በ --- ቀናቶች ተሽከርካሪዎችን በመመደብ ጭነቱን ለማጓጓዝ ግዴታ
ገብቷል፡፡

4.2. አጓጓዥ ጭነቱን በተረከበበት ዓይነትና ሁኔታ መልሶ ማስረከብ አለበት፡፡

4.3. አጓጓዥ በተረከበው ጭነት ላይ ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ለሚደርስ ጉድለት ወይም መበላሸት ኃላፊ
በመሆን ለተበላሸው ወይም ለጎደለው ጭነት በወቅቱ የገበያ ዋጋ መሰረት ለአስጫኝ ይከፍላል፡፡

4.4. ተሽከርካሪው በጉዞ ላይ እያለ በሚደርስበት አደጋና አቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ጭነቱ ጉዳት ቢደርስበት
በአካባቢው በሚገኝ ፖሊስ ጽ/ቤት ወይም መስተዳደር በሚቀርበ ማረጋገጫ መሰረት ካሳ ለአስጫኝ
እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

4.5. አጓጓዥ ጭነቱን ያስጫነው ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ብልሽት ወይም እክል ቢያጋጥመው ብልሽቱ ወይም
እክሉ ባጋጠመው በአምስት ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪው እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ወይም ምትክ
ተሽከርካሪ መመደብ አለበት፡፡

4.6. አጓጓዥ ተሽከርካሪውን ለጭነት ዝግጁ አድርጎ ካቀረበ በኋላ ሳይጭን ለሚባክነው ጊዜም ሆነ ጭነቱን
ለማራገፍ ዝግጁ ሆኖ ጭነቱ ሳይራገፍለት ለሚባክነው ጊዜ በዲመሬጅ አዋጅ 811/2006 መሰረት
አስጫኝ ኪሳራ ይከፍላል፡፡

አንቀጽ አምስት

የአስጫኝ መብትና ግዴታ

5.1. አስጫኝ እንዲጓጓዝለት የጠየቀውን የጭነት መጠን ከተሟላ የጭነት ሰነድ ጋር ዝግጁ አድርጎ ያቀርባል፡፡

5.2. አስጫኝ ያስጫነውን ጭነት ባስረከበበት ዓይነትና ሁኔታ የመረከብ መብት አለው፡፡

5.3. አስጫኝ ጭነቱን ለመጫንና ለማራገፍ የሚወጡትን ወጪዎች በሙሉ ይሸፍናል፡፡

5.4. አስጫኝ የአጓጓዡ ተሽከርካሪ ጭነቱን ለመጫንም ሆነ ለማራገፍ የሚደርስበትን ቀንና ሰዓት በጭነት
ማዘዣው ላይ መፃፍና በፊርማ ማረጋገጥ አለበት ፡፡

5.5. ለጭነት የተላከ የአጓጓዥ መኪና በአስጫኝ ችግር ምክንያት በባዶ ቢመለስ ተሽከርካሪው ቢጭን ኖሮ
የሚከፈለውን ክፍያ አስጫኝ ይከፍላል፡፡
አንቀጽ ስድስት

የክፍያ ሁኔታ

6.1. አስጫኙ አጓጓዡ ጭነቱን ያስረከበበትን ሰነድ እንዳስረከበው በ 10/አስር/ ቀናቶች ውስጥ የማጓጓዣ
ክፍያውን ለመፈፀም ግዴታ ገብቷል፡፡

አንቀጽ ሰባት
አለመግባባቶችን ስለመፍታት
7.1. በአስጫኝና በአጓጓዥ መካከል ውሉንና አፈፃፀሙን አስመልክቶ የሚነሱ አለመግባባቶችን በመነጋገርና
በስምምነት ለመፍታት ይሞከራል፡፡

7.2. አለመግባባቶች በስምምነት ካልተፈቱ ተዋዋይ ወገኖች ጉዳያቸውን ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ
ይችላሉ፡፡

አንቀጽ ስምንት
ውሉ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ውል በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን አንስቶ የፀና ይሆናል

ስለ አስጫኝ ስለአጓጓዥ
ስም ስም
ፊርማ ፊርማ
ቀን ቀን

ምስክሮች
1. ስም ፊርማ ቀን
2. ስም ፊርማ ቀን

You might also like