Professional Documents
Culture Documents
Payment
Payment
ትራንስፖርት ቢሮ
የቀ/ተ/መ/ግ/ፕ
የክፍያ አፈጻጸም መመሪያ
አጭር ርዕስ
የሱፐርቪዥንም ሥራ ክፍያ ቁርጥ ዋጋ ሰነድ ላይ በተቀመጠዉ መሠረት ክፍያዉ የሚፈጸም ሲሆን ለአማካሪዉ
ክፍያዉ የሚፈጸመዉ በየወሩ ሆኖ አማካሪዉ ስራዉን በተገቢ መልኩ እየፈጸመ ስለመሆኑ የሱፐርቪዥን ሥራ
ወራዊ ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅበታል ፡፡በዚህ ወራዊ ሪፖርት በተጨማሪ መካተት የሚገባቸዉ የደጋፊ
ሰራተኞች ቅጥር የተከናወነበት ፣ ደመወዝ የተከፈለበት ሰነድ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ናቸዉ፡፡
ከላይ ከተጠቀሰዉ በተጨማሪ አማካሪዉ አባላቱ በሙሉ ሥራ ላይ ስለመሆናቸዉ በዉለታዉ መሰረት ተገቢዉን
የማማከር የክትትልና ድጋፍ አገልግሎት መስጠታቸዉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዞኑ ማምጣት ይጠበቅበታል ፡፡
የአማካሪዉ አባላት በሙሉ ወይም አንዱ ወይም ሁለቱ በወር ዉሰጥ በስራ ላይ ላልተገኙባቸዉ የስራ ቀናት
ከወራዊ ክፊያ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
የኮንትራት ዉለታዉ ሊጠናቀቅ ሁለት ወር ሲቀረዉ አማካሪዉ በማጠቃለያ ሪፖርቱ በዓመቱ ዉስጥ
የሰራተኞች ቅጥር ያከናወነበት ፣ ደመወዝ የከፈለበት እና ቋሚ ንብረቶች የገዛበት ሰነድ ሪፖርት ያደርጋል፡፡