Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 5

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት

ትራንስፖርት ቢሮ
የቀ/ተ/መ/ግ/ፕ
የክፍያ አፈጻጸም መመሪያ
አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ትራንስፖርት ቢሮ የቀ/ተ/መ/ግ/ፕሮግራም የክፍያ አፈጻጸም መመሪያ


ቁጥር-----/2005 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

6.1.3. የተቋራጭ የሥራ ክፍያ /interim payment certificate /


ተቋራጭ የሥራ ክፍያ ሲጠየቅ መሟላት የሚገባቸዉ ቅድመ ክፍያ ሁኔታዎች
6.1.3.1. የሥራ ክፍያ ሰነድ ሊይዛቸዉ የሚገባ ዝርዝር ጉዳዮች
ሀ. በስራ ዝርዝር / FINAL BOQ / ቅደም ተከተል መሠረት በየስቴሽኑ የተሰሩ ዝርዝር
ስራዎች ቴክ.ኦፍ.ሸት/ Take off sheet /
ለ. የማሽን እና ሌሎች ዕዳዎች ዝርዝር መግለጫ እና ያከፋፈሉ ሁኔታ
ሐ. ክፍያ የሚጠየቅባቸዉ ዝርዝር ሥራዎች / FINAL BOQ / ዉስጥ ብቻ ያሉት
መሆን ይገባዋል፡፡
መ. የኮንትራት ዉል ክፍያ መጠን እና የተጠየቀዉ ክፍያ በንጽጽር የቀረበበት
ሠንጠረዥ
ሠ. የሥራ ዝርዝር ማጠቃለያ ሠንጠረዥ
ረ. . የዞኑ ፣የአማካሪዉና የተቋራጩ ማህተም እና የተወካዮቻቸዉ ፊርማ በየገጹ
ያረፈበት
ሰ. የክፍያ መጠን በሚገለጽበት የክፍያ ሰነድ ገጽ ላይ የዞኑ እና የአማካሪዉ ማህተም
(ያዘጋጀዉ አማካሪዉ ሆኖ ስራ አስኪያጁ በፊርማዉ ያረጋግጣል፤ ያረጋገጠዉ የዞኑ
ባለሙያ እና የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ የስራ ህደት ባለቤት፣ያጸደቀዉ የዞኑ
መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ወይም የልዩ ወረዳዉ ጽ/ቤት ሃላፊ ይሆናል ፡፡
የመምሪያዉ ወይም የጽ/ቤት ሃላፊ ለረጅም ጊዜ በቢሮ የማይገኝ ከሆነ የስራ ሂደቱ
ባለቤት ሊያጸድቀዉ ይችላል ፡፡ ከዚህ ዉጪ ሌላ ዉክልና ተቀባይነት አይኖረዉም ፡፡
በተጨማሪም የሁሉም ፈራሚዎች የሥራ ሃላፊነታቸዉን የሚገልጽ የቲተር ማህተም
ሊያርፍበት ይገባል ፡፡
ሸ. በፕሮጀክት ቦታ ያለ የማቴሪያል ክፍያ የማይፈጸምበት በመሆኑ በክፍያ ሰነድ ዉስጥ
አይካተትም
ቀ. ያልተሰሩ ስራዎች ወይም ከተሰራዉ ዉጪ የተጋነኑ ስራዎች በክፍያ ሰነድ ዉስጥ
ቢካተቱ የጠየቀዉ ፣ ያዘጋጀዉ ፣ እንዲሁም ያጸደቀዉ አካል በኮንትራት አስተዳደር
ህግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
6.1.3.1. የሥራ ክፍያ ቅድመ ሁኔታዎች
ሀ. ክፍያዉን በተመለከተ አማካሪዉ ለዞኑ ሲጽፍ ለትራንስፖርት ቢሮ በግልባጭ
የተጻፈ ደብዳቤ ፣ዞኑ ክፍያዉ እንዲፈጸም ለትራንስፖርት ቢሮ የጻፈዉ
ደብዳቤ
ለ. በተጨማሪ ዞኑ በሚጽፈዉ ደብዳቤ አራቱም የተቋራጭ አባላት በሥራ ላይ
ስለመሆናቸዉ እንዲገለጽ ያስፈልጋል፡፡
ሐ. አራቱም የተቋራጭ አባላት ሙሉ ጊዜያቸዉን በስራዉ ላይ ስለማሳለፋቸዉ፣ ወጣ
ገባ ስለአለመኖሩ ፣ሌላ ተደራቢ ስራ አለመያዛቸዉ ፣ የዕለት ተዕለት የስራ
እንቅስቃሴ ማድረጋቸዉን ፣ ያልተሰራና የተጋነነ ስራ ክፍያ አለመጠየቃቸዉን
አራቱም አባላት መተማመኛ ከተጠያቅነት ጋር ይፈርሙና ለዞኑ/ልዩ ወረዳ
መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ /ጽ/ቤትና ለክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ያቀርባሉ፡፡
መ. ሶስቱም የአማካሪ አባላት ሙሉ ጊዜያቸዉን በስራዉ ላይ ስለማሳለፋቸዉ፣ ወጣ
ገባ ስለአለመኖሩ ፣ሌላ ተደራቢ ስራ አለመያዛቸዉ ፣ የዕለት ተዕለት የስራ
እንቅስቃሴ ክትትልና የማማከር አገልግሎት ማድረጋቸዉን ፣ ያልተሰራና የተጋነነ
ስራ ክፍያ አለመጠየቃቸዉን ሶስቱም አባላት መተማመኛ ከተጠያቅነት ጋር
ይፈርሙና ለዞኑ/ልዩ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ /ጽ/ቤትና ለክልሉ
ትራንስፖርት ቢሮ ያቀርባሉ፡፡
ሰ. የዞን ባለሙያ አማካሪዉ ያዘጋጀዉን የክፍያ ሰነድ መርምሮ ፣ያልተሰራና የተጋነነ
የስራ ክፍያ አለመኖሩን ፣ ፕሮጀክቱን በአካል ተገኝቶ በቂ መረጃ መዉሰዱን
ከተጠያቅነት ጋር መተማመኛ ይፈርምና ለዞኑ/ልዩ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት
መምሪያ /ጽ/ቤትና ለክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ያቀርባሉ፡፡
ረ. በፊደል ሐ ፣ መ እና ሰ የተጻፉ እና የተፈረሙ መተማመኛ ሰነድ ከክፍያ ሰነድ
ጋር አባሪ ተደርገዉ ይላካሉ፡፡

6.1.3.2 የስራ ክፍያ ቅደም ተከተል


ሀ. ተቋራጭ የሰራዉን ስራ ልኬት ከደጋፊ መረጃዎች ጋር አድርጎ ቴክ ኦፍ ሺት
በማዘጋጀት ለአማካሪ ያቀርባል ፡፡ ይህን የክፍያ ጥያቄ አራቱም አባላት
በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ ለአማካሪዉ ያቀርባሉ፤ አማካሪዉም ለዞኑ ያቀርባል፡፡

6.1.5. የአነስተኛ አማካሪዎች የዲዛይን እና የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ

6.1.5.1. የዲዛይን ሥራ ከፍያ

የዲዛይን ሥራ ክፍያ በቁርጥ ዋጋ ሰነድ ላይ በተቀመጠዉ መሠረት ክፍያዉ የሚጸመዉ በኪ.ሜ ነዉ ፡፡


ይህ ክፍያ የሚከናወነዉ በስምምነት ዉለታዉ መሠረት የሰዉ ሃይል ቅጥር ተከናዉኖ ፣ተገቢዉ
ቁሳቁሶች ተማልተዉ ሥራ ላይ መስማራታቸዉ ፣ የወጪ ሰነድ ተያይዞ ሲረጋገጥ እና ተቀባይነት ያገኙ
የዲዛይን ዶክመንቶች እና ሪፖርቶች ሲቀርቡ ነዉ ፡፡ የሚሰሩ ዲዛይኖች አባሪ የተደረገዉን ቼክ ሊስት
ያሟላ መሆን አለበት ፡፡
6.1.5.2 የሱፐርቪዥን ሥራ ክፍያ

የሱፐርቪዥንም ሥራ ክፍያ ቁርጥ ዋጋ ሰነድ ላይ በተቀመጠዉ መሠረት ክፍያዉ የሚፈጸም ሲሆን ለአማካሪዉ
ክፍያዉ የሚፈጸመዉ በየወሩ ሆኖ አማካሪዉ ስራዉን በተገቢ መልኩ እየፈጸመ ስለመሆኑ የሱፐርቪዥን ሥራ
ወራዊ ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅበታል ፡፡በዚህ ወራዊ ሪፖርት በተጨማሪ መካተት የሚገባቸዉ የደጋፊ
ሰራተኞች ቅጥር የተከናወነበት ፣ ደመወዝ የተከፈለበት ሰነድ፣ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ናቸዉ፡፡
ከላይ ከተጠቀሰዉ በተጨማሪ አማካሪዉ አባላቱ በሙሉ ሥራ ላይ ስለመሆናቸዉ በዉለታዉ መሰረት ተገቢዉን
የማማከር የክትትልና ድጋፍ አገልግሎት መስጠታቸዉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዞኑ ማምጣት ይጠበቅበታል ፡፡

የአማካሪዉ አባላት በሙሉ ወይም አንዱ ወይም ሁለቱ በወር ዉሰጥ በስራ ላይ ላልተገኙባቸዉ የስራ ቀናት
ከወራዊ ክፊያ ተቀናሽ ይሆናል፡፡

የኮንትራት ዉለታዉ ሊጠናቀቅ ሁለት ወር ሲቀረዉ አማካሪዉ በማጠቃለያ ሪፖርቱ በዓመቱ ዉስጥ
የሰራተኞች ቅጥር ያከናወነበት ፣ ደመወዝ የከፈለበት እና ቋሚ ንብረቶች የገዛበት ሰነድ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

በአጠቃላይ የአማካሪዉ የዲዛይን ሆነ የሱፐርቪዥን ስራ ክፍያ ሲፈጸም አማካሪዉ

ከቢሮዎ በብድር የወሰዳቸዉ ቅድመ-ክፍያዎችም ሆነ ሌሎች ዕዳዎች በክፍያ

ሴርትፍኬቱ ላይ በተገቢ መልኩ ተቀናንሰዉ የሚፈጸም ይሆናል ፡፡

You might also like