Disk Audit Manual

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 3

የታክስ ኦዲት ሥራ አመራር ስትራቴጅ

1. የታክስ ኦዲት ትርጉም

ታክስ ኦዲት በታክስ ኦዲተሮች አማካኝነት የሚፈጸም ተግባር ሲሆን ታክስ ከፋዩ በአንድ የሂሳብ ጊዜ ወይም ግብር ዘመን ውስጥ
መክፈል የሚገባውን ትክክለኛ የታክስ ክፍያ ለመወሰን እንዲያስችል ታክስ ከፋዩ በታክስ ህጉ መሠረት ተገዥ ስለመሆኑ እና
እውነተኛ፣ ፍትሃዊ፣ አስተማማኝ እና ትክክለኛ የግብር ማስታወቂያና የሂሳብ መግለጫ ያቀረበ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲባል
የታክስ ከፋዩን የንግድ ድርጅት አሰራሮችና የሂሳብ ምዝገባዎችን የመመርመር ሂደት ነው፡፡

2. የታክስ ኦዲት ሥራ አመራር ስትራቴጅ አስፈላጊነት

 ለህግ ተገዥ የሆኑ ግብር ከፋዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የግብር ከፋዮችን አላስፈላጊ መጨናነቅ ለማስወገድ፣

 በሀገራችን እና በክልላችን የተጣጣመ የታክስ አስተዳደር ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ፣

 ከታክስ ኦዲት ስራ አመራር ጋር በተያያዘ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፣

 ለህግ ተገዥ የሆኑ ግብር ከፋዮችን በመለየት ለማስተማር፣ ለመደገፍ፣ ቀላልና ቀልጣፋ መስተንግዶ እና እውቅና ለመስጠት፣

 የታክስ ኦዲት ሽፋኑን (Coverage) እና ውጤታማነቱን (Productivity) ለማሻሻል፣

 በታክስ አስተዳደሩ የህግ ተገዥነትን ለማሳደግና ለማሻሻል፣

 የግብር ከፋዮችንና የመንግስትን ጊዜና ወጪ ለመቀነስ፣

 በክልላችን የሚተገበረው የታክስ ኦዲት ስራ አመራር ስትራቴጅ ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ ነው።

3. የኦዲት ዓይነቶች

ስጋትን መሠረት ያደረገ የሂሳብ መዝገብ ምርመራ (Risk Based Audit) ለታክስ ህግ ተገዥ ለሆኑ ወይም የታክስ ህጉን
ለሚያከብሩ ግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የማስተማር፣ የመደገፍ፣ ቀላልና ቀልጣፋ መስተንግዶ እና እውቅና
የመስጠት ሂደት ነው፡፡

ይህ የታክስ ኦዲት የምርመራ ዘዴ የታክስ አስተዳደሩን እና የግብር ከፋዮችን ወጪ ከመቀነስ ባሻገር ግብር ከፋዮች በታክስ ሥርዓቱ
ላይ አመኔታ እንዲያሳድሩ የሚያደርግ ነው፡፡

ስጋትን መሠረት በማድረግ የሚከናወኑ የኦዲት አይነቶች

 ዴሰክ ኦዲት፣

 ውስን ኦዲት፣
 አጠቃላይ ኦዲት እና

 ሌላ አይነት ኦዲት በመባል ይታወቃሉ፡፡

ሂሳብ መዝገቡን እንዳለ መቀበል

ግብር ከፋዩ ሂሳብ መዝገቡን በታማኝነትና በትትክል ሰርቶ ካቀረበ የስጋት ደረጃው በጣም ዝቅተኛ ስለሚሆን በሁሉም የስጋት
መስፈርቶች ተጠቃሎ በተገኘው ውጤት ከ 0% እስከ 10% ይመደባል። ስለሆነም የነዚህ ግብር ከፋዮች ሂሳብ መዝገብ እንዳለ
የሚወሰድ ይሆናል። የምንከተለውም አቅጣጫ ለነዚህ ግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የማስተማር፣ የመደገፍ፣ ቀላልና
ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሁም እውቅና መስጠት ይሆናል።

3.1 ዴስክ ኦዲት (Desk Audit)

ዴስክ ኦዲት በክልላችን ከአሁን በፊት ተግባራዊ ያልተደረገ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡ ይህ የኦዲት ዓይነት ግብር ከፋዩ ያቀረበውን
የታክስ ማስታወቂያ ከግብር ከፋዩ ሌላ ተጨማሪ ደጋፊ ሰነድ ሳያስፈልግ ኦዲተሩ ቢሮ ውስጥ ሆኖ በገቢ ተቋሙ የተገኙ
መረጃዎችን በመጠቀም የማረጋገጥ ሂደት ነው፡፡

ለምሳሌ:- በግብር ዘመኑ ግብር ከፋዩ ያቀረበውን የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ለማረጋገጥ በገቢ ተቋሙ አማካኝነት የተሰበሰቡ
የግብይት መረጃዎችን መጠቀም፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ማስታወቂያ ላይ በየወሩ የተገለፀውን ጠቅላላ አቅርቦት ሽያጭ
ድምር ውጤት በትርፍና ኪሳራ መግለጫ ላይ ከተገለፀው ዓመታዊ ገቢ ጋር ማነፃፀር፣ ግብር ከፋዩ በየወሩ የስራ ግብር
ለመክፈል ያቀረበውን ወርሃዊ የደመወዝ መክፈያ ሰንጠረዥ (ፔሮል) ላይ የተገለፀውን ድምር በትርፍና ኪሳራ መግለጫ ላይ
ከተገለፀው የደመወዝ ወጪ ጋር ማነፃፀር። በዚህ የኦዲት ዓይነት የሚመረመሩ ሂሳብ መዝገቦች በውስን ኦዲት ዓይነት
የማይሸፈኑ ግብር ከፋዮች ማለትም በሁሉም የስጋት መስፈርቶች ተጠቃሎ በተገኘው ውጤት ከ 10% በላይ እስከ 35%
በሚመደቡት ላይ ነው፡፡

3.2 ውስን ኦዲት (Single Issue Audit)

ውስን ኦዲት (Single Issue Audit) በክልላችን ከአሁን በፊት ተግባራዊ ያልተደረገ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡ ይህ የኦዲት ዓይነት
ግብር ከፋዩ ባቀረበው የታክስ ማስታወቂያ መሠረት የአንድን የግብር ዘመን በታክስ ዓይነት ወይም በአንድ ጉዳይ ላይ
በማተኮር የኦዲት ሥራ የመስራት ሂደት ነው፡፡

ለምሳሌ፡- ግብር ከፋዩ ከአቀረበው የታክስ ማስታወቂያ ውስጥ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቅድመ-ግብር ወይም በአንድ የሂሳብ
አርዕስት ላይ ትኩረት በማድረግ የሂሳብ ምርመራ ሥራን የመስራት ሂደት ነው፡፡ በዚህ የኦዲት ዓይነት የሚመረመሩት ሂሳብ
መዝገቦች በመካከለኛ ስጋት ደረጃ እና በአጠቃላይ ኦዲት ዓይነት የማይሸፈኑ ግብር ከፋዮች ማለትም በሁሉም የስጋት
መስፈርቶች ተጠቃሎ በተገኘው ውጤት ከ 35% በላይ እስከ 50% በሚመደቡት ላይ ነው፡፡
3.3 አጠቃላይ ኦዲት (Comprehensive Audit)

በአጠቃላይ ኦዲት (Compressive Audit) በክልላችን የሂሳብ መዝገብ በሚያቀርቡ በሁሉም ግብር ከፋዮች 100% ተግባራዊ
በመደረግ ላይ የሚገኝ የኦዲት ዓይነት ነው፡፡ ይህ የኦዲት ዓይነት ግብር ከፋዩ ያቀረበውን የሂሳብ መዝገብ ሙሉ በሙሉ
በዝርዝር የሚመረመርበት የኦዲት ዓይነት ነው፡፡ ይህ የሂሳብ መዝገብ ምርመራ ዓይነት ከፍተኛ ወጪና ጊዜ የሚጠይቅ
በመሆኑ የምርመራ ስራው ተግባራዊ የሚሆነው በሌላ ዓይነት ኦዲት ግብር ከፋዮች ማለትም በሁሉም የስጋት መስፈርቶች
ተጠቃሎ በተገኘው ውጤት ከ 50% በላይ እስከ 100% በሚመደቡት ላይ ነው፡፡

3.4 ሌላ ዓይነት ኦዲት (Other Special Type)

ልዩ የሂሳብ መዝገብ ምርመራ ዓይነት (Special Audit) በክልላችን አልፎ አልፎ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ትኩረት የሚያደርገው
ወንጀል ነክ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ የታክስ ስወራና ማጭበርበር ድርጊት በፈጸሙ ግብር ከፋዮች ላይ የሚደረግ የምርመራ
ሂደት ነው፡፡

4. የመምረጫ መስፈርቶች ዝርዝር አፈጻጸም

የሂሳብ መዝገቦችን በስጋት መምረጫ መስፈርቶች መሠረት ለመለየትና በታክስ ኦዲት ዓይነቶች ለመመደብ የተቀናጀ የመንግስት
ታክስ አስተዳደር ዘዴ (Standardized Integrated Government Tax Administration System) (SIGTAS)
“ሲግታስ” ፣ የግብር ከፋዮች የባህሪ ፍረጃ፣ የታክስ ኢንተለጀንስና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ኢንስፔክተሮች መርህ እና
የግብር ከፋዮችን ፋይል የመረጃ ምንጮች በመጠቀም የስጋት መለያ መስፈርት፣ ክብደት፣ የስጋት ደረጃ እና የመረጃ ምንጭ
መካተት ይኖርበታል፡፡

5. የኮሚቴ አደረጃጀት

የሂሳብ መዝገቦችን በመስፈርቶች መሠረት ለመለየትና በየኦዲት ዓይነቶች ለመመደብ የኮሚቴ አደረጃጀትና ተግባር በዝርዝር
ተለይቷል።

ከግብር ከፋዮች ለምርመራ የቀረቡና የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦችን በመምረጥ በመስፈርቶች መሠረት ለመለየት እና በየኦዲት
ዓይነቶች ለመመደብ የተለያዩ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም የሂሳብ መዝገብ አቅራቢ ግብር ከፋዮችን
በየኦዲት ዓይነቶች ለመመደብ የኮሚቴ አባላትና ተግባር በአሰራሩ በግልፅ ስለተለየ በዛ መሠረት የሚተገበር ይሆናል።

You might also like