Constitutional Interpretation Directive No. 6 - 2014

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 17

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.

የፌዴሬሽን ምክር ቤት

የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታ አቀባበል፣ አያያዝና


ምላሽ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 6/2014

መጋቢት 2014 ዓ.ም

1
መግቢያ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 62፣ 83 እና የምክር ቤቱን


ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1261/2013 መሰረት ሕገ መንግስቱን
የመተርጎምና ሕገ መንግስታዊ ክርክር ሲነሳ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው በመሆኑ፣

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ መንግስቱን ከመተርጎምና ውሳኔውን ከማስፈጸም ሥልጣንና


ተግባር ጋር በተያያዘ በጊዜ ሒደት በአፈጻጸም የታዩ የአሰራር ክፍተቶችን መለየትና
በአዋጁ የተቀመጡትን ጥቅል ጉዳዮች ዘርዘር አድርጎ ማስቀመጡ አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፣

የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታ አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓትን
ግልፅ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ፍትሃዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በአዋጅ ቁጥር 1261/2013 አንቀጽ 83 መሰረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ

አንቀጽ 1

አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታ


አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 6/2014 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

አንቀጽ 2

ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1. “ሕገ መንግስት” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ


መንግስት ነው፡፡
2. “ምክር ቤት” ማለት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን
ምክር ቤት ነው፡፡

2
3. “አፈ-ጉባኤና ምክትል አፈ-ጉባኤ” ማለት እንደቅደም ተከተላቸው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ እና ምክትል አፈጉባኤ ናቸው፡፡
4. “አስተባባሪ ኮሚቴ” ማለት የምክር ቤቱ አፈጉባኤ፣ ምክትል አፈጉባኤ፣ የቋሚ ኮሚቴ
ሰብሳቢዎች እና በምክር ቤቱ በቋሚነት የሚሰሩ የቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊዎች እና
ያለድምጽ ቃለ ጉባኤ በመያዝ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሚሳተፉበት ኮሚቴ
ማለት ነው፡፡
5. “ቋሚ ኮሚቴ” ማለት የምክር ቤቱ የሕገ መንግስት ትርጉምና የውሳኔ አፈጻጸም
ክትትል ቋሚ ኮሚቴ ነው፡፡
6. “የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ” ማለት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 82(1)
መሰረት የተቋቋመው ነው፡፡
7. “ጽ/ቤት” ማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፅ/ቤት ነው፡፡
8. “ዳይሬክቶሬት” ማለት በጽ/ቤቱ ስር የተዋቀረው የሕገ መንግስት ትርጉምና የሕጎች
ሕገ መንግስታዊነት ክትትል ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
9. “ዳይሬክተር” ማለት የሕገ መንግስት ትርጉምና የሕጎች ሕገ መንግስታዊነት ክትትል
ዳይሬክቶሬትን በኃላፊነት የሚመራ ነው፡፡
10. “አቤቱታ” ማለት በማንኛውም ሰው ለምክር ቤቱ የሚቀርብ ይግባኝና ተያያዥ
አቤቱታ ነው፡፡
11. “አቤቱታ አቅራቢ” ማለት በራሱ ወይም በወከለው ሰው ስም ለምክር ቤቱ አቤቱታ
የሚያቀርብ ነው፡፡
12. “ይግባኝ ማለት“ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግስት ትርጉም
አያስፈልገውም በማለት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለምክር ቤቱ የሚቀርብ
አቤቱታ ነው፡፡
13. “የውሳኔ ሀሳብ ማለት“ በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ትርጉም ያስፈልገዋል
በማለት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለም/ቤት የሚቀርብ ነው፡፡
14. “ሬጅስትራር” ማለት በዳይሬክቶሬቱ ስር ተመድቦ ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ
አቤቱታዎችን አጣርቶ መዝገብ የሚከፍትና መረጃ የሚሰጥ ባለሙያ ነው፡፡
15. “ሰው ማለት“ የተፈጥሮ ወይም በሕግ የሰውነት አካል ያ ለው ነው፡፡

3
አንቀጽ 3

የፆታ አገላለፅ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ ያካትታል፡፡

አንቀጽ 4
በሕገ መንግሥት ትርጉም ተፈፃሚ ስለሚሆኑ መርሆዎች

1. ምክር ቤቱ የሚቀርቡለትን የሕገመንግሥት የትርጉም ጉዳዮች መርምሮ ለመወሰን


ጠቃሚ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን የሕገመንግሥት አተረጓጎም መርሆዎች
በመለየት ሥራ ላይ ያውላል፡፡
2. ምክር ቤቱ የሕገ መንግስት ትርጉም ጉዳዮችን መርምሮ ለመወሰን በሕገ መንግስቱ
የተደነገጉትን የሕገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎችን፣ የብሔራዊ ፖሊሲ
መርሆዎችን እና የሕገ መንግስቱን ዓላማዎች ስራ ላይ ያውላል
3. ለምክር ቤቱ የቀረበው ጥያቄ በሕገመንግሥቱ የሰፈሩትን መሠረታዊ መብቶችና
ነፃነቶች የሚመለከት ሲሆን ትርጉሙ ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም ዓቀፍ
የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት ስምምነቶችና የዓለም ዓቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር
በተጣጣመ መንገድ ይተረጎማል፡፡
አንቀጽ 5
የሥነምግባር መርሆዎች

የሕገ መንግስት ትርጉም በሚሰጥበት ጊዜ መከተል የሚገቡ የሥነ-ምግባር መርሆዎች


የሚከተሉትን ያካትታል፡-

ሀ. ቅንነት፣

ለ. ታማኝነት

ሐ. ገለልተኝነት፣

መ. የሕግ የበላይነትን ማክበር፣

ሠ. ሚስጢር ጠባቂነት፣

ረ. አለማዳላት፣

4
ሰ. ተጠያቂነት፣

ሸ. ግልጸኝነት፣

ቀ. ሐቀኝነትና ሌሎችንም ያካትታል፡፡

አንቀጽ 6

የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በምክር ቤቱ፣ በቋሚ ኮሚቴው፣ በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ፣
በፌደራል መንግስት፣ በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በዳይሬክቶሬቱ እና በአቤቱታ
አቅራቢዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት

ስለ አቤቱታ አቀራረብና ይዘት

አንቀጽ 7

የአቤቱታ አይነቶች
1. የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል የውሳኔ ሀሳብ የቀረበባቸው

አቤቱታዎች፤
2. የይግባኝ አቤቱታዎች፤

3. የውሳኔ አፈጻጸም አቤቱታዎች፣

4. እግድ፣ የውሳኔ ግልባጭ ይሰጠኝ እና ሌሎች አቤቱታዎች

አንቀጽ 8
ስለ ይግባኝ አቤቱታ
1. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም

በሚል በሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ሰው ለምክር ቤቱ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡


2. የይግባኝ አቤቱታ የሚከተሉትን ነጥቦች መያዝ አለበት፡፡

ሀ) አቤቱታው የተፃፈበት ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት፣


ለ) የምክር ቤቱን ሥም እና አድራሻ፣
ሐ) ምክር ቤቱ ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ያለውን ስልጣን፣
መ) የአቤቱታ አቅራቢው እና ተጠሪ ካለ ሙሉ ስምና አድራሻ፣

5
ሠ) የአቤቱታ አቅራቢው ፊርማ በየገጹ ያረፈበት፣
ረ) አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ አጭርና ግልፅ ሆኖ እንዲተረጎም የሚፈለገውን
የሕገ መንግስት ድንጋጌ፣ ከሕገ መንግስቱ ጋር ይቃረናል የተባለውን ሕግ
ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የሚያሳይ፤
ሰ) በማህተም የተረጋገጠ ሙሉ የመዝገብ ግልባጭ፤
ሸ) አቤቱታው በውክልና የሚቀርብ ከሆነ አቤቱታ አቅራቢው ሕጋዊ የሆነ
ውክልና ያለው መሆኑን የሚያሳይ፤
3. ለምክር ቤቱ የሚቀርብ ማንኛውም አቤቱታ በአማርኛ ቋንቋ ተፅፎ መቅረብ

አለበት፡፡ በተጨማሪም ከአቤቱታው ጋር ተያይዘው የቀረቡ ሰነዶች የተፃፉበት


ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ውጪ ከሆነ ሰነዶቹ ሕጋዊ በሆነ የትርጉም ድርጅት
በአማርኛ ቋንቋ ተተርጉመው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
አንቀጽ 9
የሕገ መንግስት ትርጉም ማቅረብ የሚችሉ ሰዎች
1. አቤቱታ በቀረበበት ጉዳይ ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው ማንኛውም ሰው በራሱ

ወይም በሕጋዊ ወኪሉ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡


2. ማንኛውም ፍርድ ቤት በያዘው ጉዳይ ላይ ሕገ መንግስታዊ ክርክር ሲነሳ የሕገ

መንግስት ትርጉም ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡


3. በአንድ አቤቱታ ውስጥ ከአንድ በላይ አቤቱታ አቅራቢዎች በሚኖሩበት ጊዜ

ከመካከላቸው አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ሕጋዊ ውክልና በማቅረብ አቤቱታ
ማቅረብና ጉዳዩን መከታተል ይችላሉ፡፡
አንቀፅ 10

የአቤቱታ ማቅረቢያ መንገዶች

ማንኛውም አቤቱታ አቅራቢ አቤቱታውን በአካል በመቅረብ ወይም በምክር ቤቱ ፋክስ፣


ኢሜይል አድራሻ ወይም መልዕክት ሳጥን ቁጥር በመላክ ማቅረብ ይችላል፡፡

6
አንቀጽ 11

ይግባኝ የማቅረቢያ የጊዜ ገደብ

1. በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው በተሰጠ

በ180 (በመቶ ሰማንያ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለምክር ቤቱ ማቅረብ


ይኖርበታል፡፡ የይግባኝ ባቅረቢያው የመጨረሻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ
የሥራ ቀን ይግባኙን ማቅረብ ይችላል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም ፡-

ሀ. በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 28 በስብዕና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተመለከተ


ማለትም ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች
የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው
የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት
እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢሰብአዊ የድብደባ
ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ እና፤

ለ. የብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ መብቶች ወይም የስልጣን ክፍፍል እና መሰል


ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ የይግባኝ አቤቱታዎች በይርጋ
አይታገዱም፡፡

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ ከአቅም

በላይ በሆነ ምክንያት ይግባኙን ማቅረብ ያልቻለ ሰው ከአቅም በላይ የሆነው


ምክንያት በተወገደ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለአፈ ጉባኤው በወቅቱ ያላቀረበበትን
ምክንያት አቅርቦ ከተፈቀደለት ይግባኙ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

አንቀጽ 12

በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች

1. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የቀረበለትን የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ

ከመረመረ በኋላ የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት የሚያቀርበው

7
የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለው ግልጽና
ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
2. ከሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ በሰነድና በሶፍት

ኮፒ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ መላክ አለበት፡፡


3. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የቀረበለትን የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ

መርምሮ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም በማለት የሚሰጠው ውሳኔ


በጉባኤው አባላት በፊርማ ተረጋግጦና ማህተም ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
4. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም

በማለት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለማቅረብ ለሚፈልግ ባለጉዳይ


ሙሉ የመዝገብ ግልባጭ በማህተም አረጋግጦ መስጠት አለበት፡፡

አንቀጽ 13

ስለ ክፍያ

1. ምክር ቤቱ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም እንደአስፈላጊነቱ ምክር ቤቱ

በሚያወጣው ሕግ መሰረት አቤቱታ አቅራቢው ክፍያ እንዲፈፅም ሊያደርግ


ይችላል፡፡

አንቀጽ 14

ቅድሚያ ስለመስጠት

1. ሀገራዊ ጉዳይን የሚመለከት አቤቱታ እንደሁኔታው እየታየ ቅድሚያ ተሰጥቶት

ሊታይ ይችላል፡፡
2. ለሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን አቤቱታ አቅራቢዎች እንደሁኔታው

እየታየ ቅድሚያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 15

8
ለቀረቡ አቤቱታዎች የሙያ አስተያየት የሚሰጥበት ጊዜ

1. እግድ፣ የውሳኔ ግልባጭ ይሰጠኝ እና ሌሎች መሰል አቤቱታዎች በአስር የስራ

ቀናት ውስጥ ምላሽ ይሰጣቸዋል፡፡


2. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል

በማለት የውሳኔ ሀሳብ ባቀረበባቸው መዝገቦች እና የሕገ መንግስት ትርጉም


የይግባኝ አቤቱታዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሕገ መንግስት ትርጉም
ባለሙያዎች የሙያ አስተያየት ተዘጋጅቶ ለቡድን መሪው መቅረብ አለበት፡፡
አንቀጽ 16
ስለ እግድ አቤቱታና ምላሽ አሰጣጥ
1. ለምክር ቤቱ የእግድ አቤቱታ ሲቀርብ ምክር ቤቱ የእግድ ትእዛዝ ሊሰጥ
የሚችለው፡-
ሀ) ለእግዱ ምክንያት የሆነው ዋናው ጉዳይ ለምክር ቤቱ የቀረበ ከሆነ፤
ለ) በውሳኔው መሰረት እንዲፈጸም መገደዱን የሚያሳይ ማስረጃ ከእግድ
አቤቱታው ጋር ተያይዞ የቀረበ ከሆነ፤
ሐ) ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ሊተካ የማይችል ጉዳት የሚደርስበት
ከሆነ፣
መ) ምክር ቤቱ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ንብረቱ በአለበት ሁኔታ ቢቆይ ሊበላሽ
የማይችል ከሆነ፣ እና
ሠ) ሁከትና ብጥብጥ ሊከሰት ይችላል ወይም ሌላ ከባድ አሳማኝ ምክንያት
መኖሩ ከታመነ ነው፡፡
2. ለምክር ቤቱ በቀረበ ጉዳይ ላይ የእግድ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጥያቄ ሲቀርብ አፈ

ጉባኤው አስተያየት እንዲሰጥበት ለቋሚ ኮሚቴው ሊመራ ይችላል፡፡


3. አፈ ጉባኤው የእግድ ትዕዛዝ ከመስጠቱ በፊት ሌላው ተከራካሪ ወገን አስተያየት

እንዲሰጥበት ሊያደርግ ይችላል፡፡


4. የቀረበው የእግድ አቤቱታ በአፈጉባኤው ተቀባይነት ካገኘ የእግድ ትእዛዙ
በአፈጉባኤው ተፈርሞ ለባለጉዳዩ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

9
5. አቤቱታው የእግድ ትእዛዝ የማያሰጥ መሆኑ በአፈ ጉባኤው ከታመነበት የእግድ

ይሰጥልኝ አቤቱታው ተቀባይነት አለማግኘቱን አቤቱታ አቅራቢው እንዲያውቀው


ይደረጋል፡፡
6. የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋል በሚል በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ በአጣሪ

ጉባኤው የተሰጠ የእግድ ትእዛዝ ምክር ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ


ጸንቶ ይቆያል፡፡
7. የተሰጠው የዕግድ ትእዛዝ መነሳት እንዳለበት በአፈ ጉባኤው ከታመነ ምክር ቤቱ

በቀረበው ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አፈ ጉባኤው የሰጠውን


የእግድ ትእዛዝ ሊያነሳው ይችላል፡፡

ክፍል ሶስት
የጉዳዮች ፍሰት፣ የመረጃ አያያዝና የአገልግሎት ተደራሽነት
አንቀጽ 17
የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታ የሚያልፍባቸው ሂደቶች
1. የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው የቀረበውን የውሳኔ

ሀሳብ እንደደረሰው ለቋሚ ኮሚቴው ይመራል፡፡


2. የውሳኔ ሀሳቡ የተመራለት ቋሚ ኮሚቴ መዝገብ እንዲከፈትለት ለሬጂስትራር

ይመራዋል፤
3. የውሳኔ ሀሳቦች እና በይግባኝ የቀረቡ አቤቱታዎች ለሬጂስትራር ቀርበው መዝገብ

ተከፍቶላቸው ለባለሙያዎች ይከፋፈላሉ፡፡


4. መዝገቦች በባለሙያዎች ተመርምረውና ተጠንተው የሙያ አስተያየት
ተዘጋጅቶላቸው ለቋሚ ኮሚቴው ይቀርባሉ፡፡
5. የቀረቡት የሙያ አስተያየቶች በቋሚ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎባቸው የውሳኔ ሃሳብ

ተዘጋጅቶላቸው ለምክር ቤቱ ይቀርባሉ፡፡


6. የቀረቡት የውሳኔ ሃሳቦች በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎባቸው ውሳኔ ይሰጥባቸዋል፡፡

7. የምክር ቤቱ ውሳኔ በአፈ ጉባኤው ተፈርሞ ለሚመለከታቸው አካላትና ለባለጉዳዮች

እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡

አንቀጽ 18

10
ስለ መረጃ አያያዝ

1. ምክር ቤቱ መረጃዎችን በሰነድ መልክና በመረጃ ቋት የመረጃ አያያዝ ዘዴ

አደራጅቶ ይይዛል፡፡
2. በሰነድ እና በመረጃ ቋት የመረጃ አያያዝ ዘዴ የተያዙ መረጃዎች ለሚመለከተው

አካል ተደራሽ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ 19

አገልግሎትን ተደራሽ ስለማድረግ

1. ምክር ቤቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ውሳኔዎች ለዜጎች እና ለተቋማት ተደራሽ

እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
2. የምክር ቤቱ ውሳኔዎችና መረጃዎች ተደራሽ የሚሆኑት በድረገጽ፣በህትመት፣

በመገናኛ ብዙሃን፣ በነጻ የስልክ መስመርና በሌሎች መሰል መንገዶች ነው፡፡

ክፍል አራት

የቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ፣ የዳይሬክተሩና ባለሙያዎች ተግባርና ኃላፊነት

አንቀጽ 20

የቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ ተግባርና ኃላፊነት

1. የቋሚ ኮሚቴው ጸሀፊ በምክር ቤቱ ውስጥ በቋሚነት ይሰራል፡፡

2. የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ አሰጣጥ


እንዲሁም የምክር ቤቱ ውሳኔ አፈጻጸም ዙሪያ የሚከናወኑ አጠቃላይ ሥራዎችን
ይመራል፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የቋሚ ኮሚቴ

ጸሀፊ ከምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የሚመሩለትን ጉዳዮች በመመርመር ምክረ ሀሳብ


ያቀርባል፡፡
4. የምክር ቤቱ የውሳኔ አፈጻጸምን በመከታተል ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ያቀርባል፡፡

5. ቋሚ ኮሚቴው የሚወያይበትን አጀንዳ እና አባሪ ሰነዶችን ከዳይሬክቶሬቱ ጋር

በመቀናጀት ለአባላቱ በቅድሚያ እንዲደርሱ ያደርጋል፡፡

11
6. ቋሚ ኮሚቴውን የሚመለከቱ ማናቸውንም ሰነዶች በአግባቡ አደራጅቶ ይይዛል፣

ሲጠየቅም መረጃ ይሰጣል፡፡

አንቀጽ 21

የዳይሬክተሩ ተግባርና ኃላፊነት

1. ዳይሬክተሩ የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ

አሰጣጥ ዙሪያ የሚከናወኑ አጠቃላይ ሥራዎችን ይመራል፡፡


2. በሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ አስፈላጊ ሙያዊ አስተያየቶች
ተዘጋጅተው ለቋሚ ኮሚቴ እንዲቀርቡ እና ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
አፈፃፀሙን ይከታተላል፡፡

አንቀጽ 22

የሕገ መንግስት ትርጉም ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት

ለምክር ቤቱ የቀረቡ አቤቱታዎች በዚህ መመሪያ ውስጥ በተቀመጠላቸው ጊዜ ሙያዊ


አስተያየት መዘጋጀቱን ይከታተላል፤ እንዲሁም ከባለሙያዎች የቀረበለትን ሙያዊ
አስተያየት አጠናቅሮ በሃርድና በሶፍት ኮፒ ለዳይሬክተሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤
አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
አንቀጽ 23
የሕገ መንግስት ትርጉም ባለሙያ ተግባርና ኃላፊነት
ባለሙያው የተመሩለትን የሕገ መንግስት ትርጉምና ሌሎች አቤቱታዎች በመመርመር
የሙያ አስተያየት በማዘጋጀት ለቡድን መሪው በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ ያስረክባል፤
እንዲሁም ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ 24
የሬጂስትራር ተግባርና ኃላፊነት
1. ለምክር ቤቱ የሚቀርቡ የሕገ መንግስት ትርጉም የይግባኝ አቤቱታዎች በዚህ

መመሪያ አንቀጽ 8 መሰረት መሟላታቸውን አረጋግጦ በመቀበል፣


እንደአቀራረባቸው ቅደም ተከተል መዝገብ ከፍቶ ለባለሙያዎች ያከፋፍላል፡፡
2. በዚህ መመሪያ መሰረት ተሟልቶ ያልቀረበ አቤቱታ ተስተካክሎ እንዲቀርብ

ለባለጉዳዩ ይመልሳል፡፡

12
3. የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ተብሎ ከሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ

ለምክር ቤቱ የሚቀርበውን የውሳኔ ሐሳብ ሲመራለት ተቀብሎ ከመዘገበ በኋላ


መዝገብ በመክፈት ለባለሙያ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
4. በምክር ቤቱ የተሰጡ ውሳኔዎች ግልባጭ ለጠየቀው ባለጉዳይ ይሰጣል፤ እንዲሁም

ጉዳዮች ያሉበትን ደረጃ በባለጉዳዮች መረጃ ሲጠየቅ ይሰጣል፡፡


5. ለምክር ቤቱ የቀረቡ አቤቱታዎች፣ መዝገቦች፣ የምክር ቤቱ ትዕዛዞች እና ውሳኔዎች

በስርዓትና በቁጥራቸው ቅደም ተከተል ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል፡፡


6. ከሌሎች ተቋማት እንዲቀርቡ ታዝዘው የቀረቡ መዝገቦችና ሰነዶች ጉዳዩ እልባት

ካገኘ በኋላ ወደመጡበት በወቅቱ እንዲመለሱ ያደርጋል፡፡


7. በመታየት ላይ ባሉ ጉዳዮች ለምርመራ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች በባለ ጉዳዩ

እንዲቀርቡ ሲታዘዝ ለባለጉዳዮች ያሳውቃል፤ ይከታተላል፡፡

አንቀጽ 25

የሕግ ሰነዶችና ዳታ ማኔጅመንት ኤክስፐርት


የምክር ቤቱ የሕገ መንግስት ትርጉም መዝገቦች፣ ቃለጉባኤዎችና መረጃዎች በአግባቡ
በሰነድና በመረጃ ቋት ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል ሲጠየቅም መረጃ ይሰጣል፡፡
ክፍል አምስት
የሕገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች ምላሽ አሰጣጥ ስርአት
አንቀጽ 26
የቡድን ውይይት ስለማድረግ
1. ባለሙያዎች በተመሩላቸው አቤቱታዎች ላይ በቂ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጉዳዮቹ

ላይ የሙያ አስተያየት አዘጋጅተው የቡድን ውይይት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች


ላይ ዳይሬክተሩ፣ ቡድን መሪ እና ባለሙያዎች በተገኙበት የቡድን ውይይት
ያደርጋሉ፡፡
2. ባለሙያዎች በቡድን ውይይቱ በተገኘው ግብአት መሰረት የሚስተካከሉ ሃሳቦች

ተስተካክለው ለቋሚ ኮሚቴው የሚቀርብ የሙያ አስተያየት ወይም የውሳኔ ሀሳብ


ያዘጋጃሉ፡፡
አንቀጽ 27
የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት

13
1. የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ፀሀፊ ከዳይሬክተሩ ጋር በመወያየት የቋሚ ኮሚቴን ስብሰባ

ጊዜና ቦታን ይወስናሉ፡፡


2. ዳይሬክተሩ የሙያ አስተያየት ወይም አስፈላጊ ሰነዶች ተደራጅተው ከቋሚ

ኮሚቴው የስብሰባ ጊዜ 15 ቀናት በፊት ለአባላት እንዲደርሱ ያደርጋል፤ የስብሰባ


ጥሪ እንዲተላለፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፡፡
3. በቋሚ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ መገኘት ያለባቸው ባለጉዳዮች ወይም አስረጂዎችና

ኤክስፐርቶች ካሉ ከስብሰባው ቢያንስ አምስት ቀናት በፊት ዝግጅት አድርገው


እንዲቀርቡ በዳይሬክተሩ በኩል የስብሰባው ቀንና ቦታ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡
4. የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይም ፀሀፊ ከዳይሬክተሩ ጋር በመሆን የስብሰባ
አጀንዳዎችን አዘጋጅተው ከስብሰባው ሦስት ቀናት በፊት ለሁሉም የቋሚ ኮሚቴ
አባላት እንዲደርስ ያደርጋሉ፡፡
አንቀጽ 28
የቋሚ ኮሚቴ ተግባር
1. ቋሚ ኮሚቴው ከዳይሬክቶሬቱ በቀረበለት የሙያ አስተያየት ውይይት ካደረገ በኋላ

የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ተቀብሎ ሊያጸድቀው ወይም ማስተካከያ እንዲደረግ ሊያዝ


ይችላል፡፡
2. ቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ እንዲሁም

የውጭ ባለሙያዎችን በአስረጂነት እንዲቀርቡና ማብራሪያ እንዲሰጡ ሊያደርግ


ይችላል፡፡
3. ቋሚ ኮሚቴው የጉዳዩን ዝርዝር መግለጫ እና የደረሰበትን መደምደሚያ በግልፅ

በሚያሳይ መልኩ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ያቀርባል፡፡


4. ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ማስተካከያ የሰጠ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው

በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ይፈፅማል፤ እንዲፈፀሙም ያደርጋል፡፡


5. ቋሚ ኮሚቴው በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ የውሳኔ ሃሳብ የሚሰጠው በምክር ቤቱ

የአሰራርና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ ቁጥር 3/2013 በተደነገገው መሰረት


ይሆናል፡፡
አንቀጽ 29
ለምክር ቤቱ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ማብራሪያ ስለመስጠት

14
ከሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ተብሎ
በቀረበ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ቋሚ ኮሚቴው ወይም ምክር ቤቱ ተጨማሪ ማብራሪያ
ሲያስፈልገው የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው አባላት ቀርበው ማብራሪያ
እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል፡፡
አንቀጽ 30
ስለምክር ቤቱ ውሳኔ
1. ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሣኔ የመጨረሻና አስገዳጅ
ይሆናል፡፡
2. የምክር ቤቱ የሕገመንግስት ትርጉም ውሣኔ የጉዳዩን ዝርዝር መግለጫ፣ የሕገ

መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋል ወይም አያስፈልግም ያለበትን ምክንያትና


የደረሰበትን መደምደሚያ በግልጽ የሚያሳይና ጥራቱን የጠበቀ መሆን
ይኖርበታል፡፡
3. የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ምክር ቤቱ

የሚሰጠው ውሳኔ የሚከተሉትን ነጥቦች አካቶ የያዘ ይሆናል፡-


ሀ) የምክር ቤቱ የስራ ዘመን፣ የስብሰባው አይነት፣
ለ) ስብሰባው የተካሄደበት ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት
ሐ) የመዝገብ ቁጥር፣ የተከራካሪዎች ስምና አድራሻ፣
መ) የቀረበው አቤቱታ በአጭሩ፣
ሠ) የጉዳዩ አመጣጥ፣
ረ) የአቤቱታው ጭብጥ፣
ሰ) በጭብጦቹ ላይ የተሰጠው ትንታኔ፣
ሸ) ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔና ትዕዛዝ፤
4. ምክር ቤቱ የሰጠው ውሳኔ በአፈ-ጉባኤው ፊርማ እና በምክር ቤቱ ማሕተም

መረጋገጥ አለበት፡፡
አንቀጽ 31
የምክር ቤቱ ውሳኔ በድጋሚ እንዲታይ ስለሚጠየቅበት ሁኔታ
1. የምክር ቤቱ ውሳኔ በድጋሚ እንዲታይ ወደ ምክር ቤቱ መቅረብ የሚችለው፡-

ሀ. ቀደም ሲል ምክር ቤቱ ውሳኔ ሲሰጥ የነበረው እንከን ታርሞ ወይም


ተሟልቶ እንደገና እንዲታይ የውሳኔውን ሃሳብ ባቀረበው አካል ሲጠየቅ፣

15
ለ. ቀደም ሲል ምክር ቤቱ ውሳኔ ሲሰጥ የሕገ መንግስት ትርጉም ስህተት
መፈፀሙና በዚህም ውሳኔ ምክንያት መሰረታዊ ጉዳት ደርሶብኛል የሚል
አቤቱታ አቅራቢ ሲቀርብ ነው፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ውሳኔው መሰረታዊ

የሕገ መንግሥት ትርጉም ስህተት እንዳለበት የሚመለከታቸው አካላትን በማማከር


አፈጉባኤው ካመነበት ጉዳዩ በድጋሚ ለምክር ቤቱ ለውይይት ሊቀርብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 32

ስለ ምክር ቤቱ ውሳኔ አፈጻጸም

1. ማንኛውም ሰው፣ የፌደራልና የክልል ፍርድ ቤቶች፣ የፌዴራልና የክልል


መንግሥታት፣ የመንግስት ባለሥልጣናት ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት
የምክር ቤቱን ውሣኔ የማክበር፣ የማስፈጸምና የመፈፀም ግዴታ ይኖርበታል፡፡
2. ቋሚ ኮሚቴውና ዳይሬክቶሬቱ የምክር ቤቱ ውሳኔ ግልጽና ለአፈጻጸም በሚያመች

ሁኔታ ተዘጋጅቶ ፈጻሚውንና የሚፈጸመውን ጉዳይ በግልጽና በጥራት የሚያብራራ


እንዲሆን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. በሕገ መንግሥት ትርጉም ላይ ምክር ቤቱ በሚሰጠው ውሣኔ በግልጽ ካልተመለከተ

በስተቀር ተፈፃሚ የሚሆነው ውሣኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡


4. አንድ ሕግ ወይም የአንድ ሕግ አካል ድንጋጌ ወይም የመንግስት አካል ወይም

የባለሥልጣን ውሳኔ ወይም ልማዳዊ አሰራር ተፈጻሚ እንዳይሆን በምክር ቤቱ


ሲወሰን ውሳኔው ከአስር ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለሚመለከተው አካል መድረስ
ይኖርበታል፡፡
5. አንድ ሕግ ሕገመንግሥታዊ አይደለም ተብሎ የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ

ሕጉን ላወጣው የፌዴራል ወይም የክልል የመንግሥት አካል በሶስት ወር ጊዜ


ውስጥ ሕጉን እንዲያሻሽል፣ እንዲለውጥ ወይም እንዲሰርዝ መገለጽ አለበት፡፡
6. ሕጉን እንዲያሻሽል፣ እንዲለውጥ ወይም እንዲሰርዝ የተገለጸለት የሚመለከተው

አካል ሕጉ ስለመሻሻሉ፣ ስለመለወጡ ወይም ስለመሰረዙ ለምክር ቤቱ በጽሁፍ


ማሳወቅ አለበት፡፡
7. ቋሚ ኮሚቴውና ዳይሬክቶሬቱ የምክር ቤቱ ሕገ መንግስታዊ ውሳኔ አፈጻጸም

ክትትል በማድረግ ስለአፈጻጸሙ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

16
ክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 33
የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው ወይም አካል የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ


የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
አንቀጽ 34
ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው መመሪያዎች
ይህን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም መመሪያና አሰራር በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ
ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡
አንቀጽ 35
መመሪያውን ስለማሻሻል
ይህ መመሪያ በማንኛውም ጊዜ በአስተባባሪ ኮሚቴው ሊሻሻል ይችላል፡፡
አንቀጽ 36
መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ፣
ይህ መመሪያ በአስተባባሪ ኮሚቴው ታይቶ ከፀደቀበት ከመጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም
ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አገኘሁ ተሻገር
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

17

You might also like