Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 23

ሥነ ሐተታ ዐሠርቱ ቅኔያት ዘጽሑፋን

እመጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ኀይሉ


ወልደ ታሪክ
የቅኔያት ትንተና

ሠኔ ፳፻፲ወ፭ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ::


በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት ዘርፍ፤ የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ክፍል፡፡
ግብረ ቤት መረጃ

 የት/ት ዘመን: - 2015/2021/22


 መርሐ ግብር: - Regular Ge’ez M.Th. Degree 1th year 2nd semester
 ዘርፍ: - Ethiopian Church Studies
 ትምህርት ክፍል: - Ge’ez Language
 የትምህርቱ ርእስ: - Genres and Nature of Ge’ez Quine
 የትምህርቱ መምህር: - Dr. Zelalem Meseret
 አዘጋጆች: - ገብረ ሕይወት ፈንታኹን
በጋሻው ተክሌ
መስፍን ተከሥተ
 Place: - Addis Ababa Region / Arat Kilo

i
መክሥተ አርእስት

ግብረ ቤት መረጃ .............................................................................................................................................. i


መክሥተ አርእስት............................................................................................................................................ ii
መግቢያ ........................................................................................................................................................... ii
ክፍል ፩ዱ ....................................................................................................................................................... 1
፩. ቅኔያት ፩.................................................................................................................................................... 1
፩.፩. ጉባኤ ቃና ዘአለቃ ወልደ ያሬድ ............................................................................................................... 1
፩. እማሬያዊ የቅኔው ትርጕም፤ .................................................................................................................... 1
፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤ ................................................................................................................... 1
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ........................................................................................................................ 1
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤....................................................................................................................... 1
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት ......................................................................................................................... 1
፩.፪ ዋይዜማ ቅኔ .............................................................................................................................................. 2
፩. እማሬያዊ የቅኔው ትርጕም....................................................................................................................... 2
፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ) ..................................................................................................................... 2
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ........................................................................................................................ 2
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤....................................................................................................................... 2
፭. ዐቢይ የቅኔው መልእክት ......................................................................................................................... 3
፮. ተጨማሪ................................................................................................................................................. 3
፯. ርእይ...................................................................................................................................................... 3
፩.፫. ዋይዜማ ቅኔ ዘአለቃ ለማ ......................................................................................................................... 3
፩. እማሪያዊ የቅኔው ትርጕም፤ ..................................................................................................................... 3
፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤ ................................................................................................................... 3
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ........................................................................................................................ 4
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤....................................................................................................................... 4
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤....................................................................................................................... 4
፮. ተጨማሪ................................................................................................................................................. 4

ii
፯. ርእይ...................................................................................................................................................... 4
፩.፬ ዋይዜማ ቅኔ ዘአለቃ ለማ ........................................................................................................................... 5
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................... 5
፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤ ................................................................................................................................. 5
፫. የቅኔው ዐውድ (መቸት)፤ ........................................................................................................................ 5
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤....................................................................................................................... 5
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤....................................................................................................................... 5
፮. ተጨማሪ................................................................................................................................................. 6
፯. ርእይ...................................................................................................................................................... 6
፩.፭. ሣህልከ ቅኔ ............................................................................................................................................. 6
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................... 6
፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤ ................................................................................................................................. 6
፫. የቅኔው ዐውድ /መቼት/፤ ....................................................................................................................... 6
፫. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤ ....................................................................................................................... 7
፮ ተጨማሪ .................................................................................................................................................. 7
፯. ርእይ...................................................................................................................................................... 7
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................... 8
፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤ ................................................................................................................................. 8
፫. የቅኔው ዐውድ መቼት፤ ........................................................................................................................... 8
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤....................................................................................................................... 8
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤....................................................................................................................... 8
፮. ተጨማሪ................................................................................................................................................. 8
፯. ርእይ...................................................................................................................................................... 9
፪.፪. መወድስ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ - ወጽአ ይዝራዕ ........................................................................................ 9
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................... 9
፪. ቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤................................................................................................................... 10
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ...................................................................................................................... 10
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤..................................................................................................................... 10
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤..................................................................................................................... 10
፮. ርእይ .................................................................................................................................................... 10

iii
፪.፫ መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ- ትዕግሥተ ንባቡ ................................................................................... 11
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................. 11
፪. የቅኔው መፈጠሪያ /ምንጭ/፤ ................................................................................................................ 11
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ...................................................................................................................... 11
፬. የቅኔው መንገድ፤................................................................................................................................... 12
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤..................................................................................................................... 12
፮. ርእይ .................................................................................................................................................... 12
፪.፬. መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ለማ -ጻድቅ ይምሕር............................................................................................... 12
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................. 13
፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤ ............................................................................................................................... 13
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ...................................................................................................................... 13
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤..................................................................................................................... 13
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤..................................................................................................................... 13
፮. ርእይ .................................................................................................................................................... 13
፪.፭. አሠረ ንጉሥ ዘአለቃ ለማ - ምኒልክ ግበር .............................................................................................. 14
፩. የቅኔው ትርጕም፤ ................................................................................................................................. 14
፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤ ................................................................................................................. 14
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤ ...................................................................................................................... 14
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤..................................................................................................................... 14
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤..................................................................................................................... 14
፮. ተጨማሪ............................................................................................................................................... 15
፯. ርእይ.................................................................................................................................................... 15
ማጠቃለያ ...................................................................................................................................................... 16
ስምዐት/ወሃቢ/ዋቢ/ ....................................................................................................................................... 17

iv
መግቢያ
ቅኔ ማለት እንደመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬና እንደ ቅኔ ምሁራን ‹‹ቀነየ›› ገዛ ከሚለው ኀላፊ ግስ
የተገኘ ሲኾን ቃላዊና ምስጢራዊ ትርጉሙ ደግሞ በዋናነት ለፈጣሪ መገዛት፤ ለፈጣሪ የሚቀርብ አምኃ
ስብሐት፤መሥዋዕተ ስብሐት፤ የነገር ስልት (ጥበብ)፤ ግጥም ብቻ ያይደለ ምጣኔ፤ስያሜ ያለው፤ አንድ
ሰው በተረዳው መጠን ከሰው የማይበደረው (የማይኮርጀው)፤ ዐስቦና ቈጥሮ የሚነግረው፤ የሚዘረፍና
ከባለቅኔ የሚነጠቅ፤ የራስ የኅሊና ሀብት ብቻ የኾነ፤ ያልተማሩት የሚጠሉትና የሚመኙት፤ የተማሩት
ደግሞ ልሙትልህ ብለው የሚያፋቅሩት፤ ሐሳባቸውንና ቁጭታቸውን የሚገልጹበት እውነተኛ ትምህርተ
እግዚአብሔር ነው፡፡

ቅኔ ከሊቃውንቱ አንደበት ላይ ሊነጠቅ ይችላል፤ ነገር ግን አይመረመርም፤ የሰዎች ቅኔም ለፈተና ቀርቦ
ማንም ሊቅ (ሰው) በፈተናው እስካኹን ድረስ አልፎ አልተገኘም፤ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ቅኔ
(ሐሳብ) ይልቅ የግለሰብእ ሐሳብ (ቅኔ) ስለሚከብድ ነው፡፡
እንደማሳያም ይኽ መጽሐፍና የቅኔው ደራሲ ታላቁ ሊቅ አለቃ ለማ ኀይሉ ከረቂቁ ቅኔያቸው ጋራ
ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ስለኾነም በመጽሐፈ ትዝታ ዘለአቃ ለማ ወልደታሪክ በሚለው ውስጥ እንድንሠራና እንድንመራመር


በተሰጠን ትእዛዝ መሠረት በዐይነት የተሰጡን ቅኔዎች በቊጥር ዐሥር ሲኾኑ፤ ትእዛዛቱም፡-
1. የቅኔው መፈጠሪያ ምንጭ (ፈሊጥ፡ አባባል፡ ምሳሌ) ፤
2. የቅኔው ወቅታዊ ዐውድ (ታሪክ፡ ጦርነት፡ ወ.ዘ.ተ)
3. የቅኔው ማቀረቢያ መንገድ (ሠምና ወርቅ ….)
4. የቅኔውን በትክክል መተርጐም ከራስ ትረጓሜ ጋራ ማሳየት፤
5. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤ ላይ ሌላ ተጨማሪ ዕይታ ካለ ….. በሚል ርእሰ ጉዳይ ተመሥርተን
እንድንሠራ ያነሣሣን ፈጣሪ ይመስገን ፤ መምህራችንንም አምላክ እድሜና ጤና ይሰጥልን፡፡

ii
ክፍል ፩ዱ

፩. ቅኔያት ፩

፩.፩. ጉባኤ ቃና ዘአለቃ ወልደ ያሬድ


አኀውየ ንኅድግ ፍቅረ እንሰሳ ዓለም፤
በሰኑይ ዕለት እስመ ይቀስፈነ ጾም፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤201/249)

፩. እማሬያዊ የቅኔው ትርጕም፤


ወንድሞቼ ሆይ የዓለም እንሰሳ ፍቅርን እንተው፤ ጾም በሰኑይ ዕለት ይቀሰፈናልና፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤

= መጽሐፋዊ ነው፤

 ጥቅስ =
 ‹‹ወይሤርየነ ወያሐይወነ በሰኑይ መዋዕል፤›› (ሆሴዕ. ፮÷፫)
 ‹‹ወምንት/ተ/ ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ኀጉለ፡፡›› (ማቴ. ፲፮÷፳፮፤ ሉቃ. ፱÷፳፭)

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤

= የጾም ዋይዜማ ነው፤

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ሠምና ወርቅ = እንሰሳ ዓለም
ለ. ኅብር /የዘርፍ ኅብር/ = ፍቅር
ሐ. ሠም ገፊ = ጾም፤ ሰኑይ ዕለት ነው፡፡
፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት
በሠሙ ይኽን ዓለም በወዲያኛው ዓለም መለወጥ ሲኾን፥ የወርቅ መልእክት ደግሞ ከሰኞ ዠምሮ ከሥጋና
ከእንሰሳት ተዋጽኦ በመከልከል የሚጾም ዐዋጁን (ትምህርትን) የሚነገር ነው፡፡
፮. ተጨማሪ
ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት ከወቅቱ አንጻር ግዕዝ ሲኾን ዕዝል መኾንም ይችላል፡፡
ለ. የቤት መምቻው = ም
ሐ. ድምፀት = ምክር፤ ምናኔ፤ ዓለምን መተው፤

፯. ርእይ = ውስጠ ተሰሳቢውን እጅግ የጠበቀ ነው፡፡

1
፩.፪ ዋይዜማ ቅኔ
ኢይበቁዕ ክብረ አዝማድ
እስመ ወልደ ባዕል ወድቀ ውስተ እደረኀብ ኃያል፤
አግብርት እንዘጽጉባን ወይተርፍ እክል፤
ምሳሌዝኒ ነገር አጠየቀተነ ጎል፤
አምጣነ ወልዳ ኢድኅነ እምለቢሰቈጽል፤
እንዘወርቀ ትፈትል ድንግል፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤228/229)

፩. እማሬያዊ የቅኔው ትርጕም


የዘመድ ክብር (ብልጽግና) አይጠቅም፤ አይረባም፡፡ አገልጋዮች ጠግበው እኅል ሲተርፍ የባለጸጋ ልጅ
በርኃብ ወድቋል (አልቋል)ና፤ የዚኽንም ምሳሌ በረት አስረድታናለች፤ ድንግል የወርቅ ሐር ስትፈትል
ልጇ ቅጠል ከመልበስ አልዳነምና፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)

ሀ. የሠሙ ምንጭ = መጽሐፋዊ ጥቅስ ነው፡፡


፩. ‹‹ኢይትሜነን ነቢይ ዘእንበለ በሀገሩ ወበቤቱ፤›› (ማቴ. ፲ወ፫÷፳ወ፯) ፡፡
፪. ‹‹ወይቤሎሙ እግዚእ ኢኮነ ምኑነ ነቢይ ዘእንበለ በሀገሩ ወበቤቱ ወበኀበ አዝማዲሁ፤›› (ማር. ፮÷፭) ፡፡
‹‹ትረክቡ ሕፃነ እሱረ መንኰቢያቲሁ ወጥብሉለ በአጽርቅት ወስኩብ ውስተ ጎል፡፡›› (ሉቃ. ፪÷፲፪ ፤
ማቴ. ፩÷፩፤ ፪÷፩ ፤ ከደነቶ እሙ ቈጽለ በለሶን (ድጓ ገጽ ፻፹፮) ፡፡
፫. ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ፤ (ሉቃ. ፬÷፳ወ፬) ፡፡
፬. ‹‹ወለሊሁ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕተ ኮነ ከመ ኢይከብር ነቢይ በሀገሩ፤›› (ዮሐ. ፬÷፵ወ፬)
ለ. የወርቅ ምንጭ
‹‹በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ውስተ ማሕፀነ ድንግል ኀደረ›› (መጽሐፈ ዚቅ ገጽ ፻፰)

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤


የበዓለ ልደት ዋይዜማ ነው፡፡

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ኅብር= ክብረ አዝማድ፤ ወልደ ባዕል፤ አግብርት፤ እክል፤ ለቢሰቈጽል፤ ፈትለ ወርቅ
ለ. ሠም ረገፍ = ጎል፤ ወልደ ድንግል፤

2
፭. ዐቢይ የቅኔው መልእክት
ሀ. በሠም ሲገለጽ = አባባል፤ ዘመድ አይጠቅምም
ለ. የወርቅ ዐቢይ መልእክት እግዚአብሔር ወልድ ለድኅነተ ዓለም ከድንግል ማርያም በጎለ እንሰሳ
ተወልዶ ‹ከደነቶ እሙ ቈጽለ በለሶን› የሚለውን የሚሳይና በሥጋ መራቡን የሚያስተምር ነው፡፡

፮. ተጨማሪ
ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት - ዓራራይ
ለ. የቤቱ ግጥም (መምቻው) ‹‹ል›› ቤት
ሐ. ደምፀት = ረኀብ ፡ ችግር (መቸገር)፤

፯. ርእይ
ሀ. ቅኔው የቀረበበት የዐ.ነገር ስልት በሁለት ማሠሪያና በሁለት አሥረጅ በመኾኑ መልካም ነው፡፡
ለ. ከሙያ አንጻር = ባለቤት ቀድሞ ሳይነገር ዝርዝር መቅደሙ ከባል ቀድሞ ልጅ ይሰጥሽ የሚለውን
የቅኔ መምህራን የስሕተት አባባልን እውን ያደርገ ነው፤ ምሳሌ ወልዳ የሚለው ነው፡፡

፩.፫. ዋይዜማ ቅኔ ዘአለቃ ለማ


አነ ወዝናም
እንዘ ንጹሓን እምነውር ወእንዘበቀል አልብነ፤
አሮን እምበዊአቤቱ በከንቱ ከልአነ፤
እስመ እመ ዐረግነ ላዕለ ወእመታሕተ ወረድነ፤
ዘምስለአቡነ አሮን ያስተሳልመነ፤
አረጋዊ ኢተረክበ ለነ፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤248)

፩. እማሪያዊ የቅኔው ትርጕም፤


እኔና አሮን ከነውር የነጻን ስንኾን በቀልም ሳይኖረብን አሮን ወደቤቱ ከመግባት በከንቱ ከለከለን፤
ወደ ላይ ብንወጣ ወደታችም ብንወርድ፤
ከአባታችን አሮን ጋራ የሚያስታርቀን ሽማግሌ አልተገኘልንምና፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤

አባባል = ገድለ አሮን

3
፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤
የጻድቁ አቡነ አሮን ዘመቄት የበዓል ዋይዜማ ይመስላል፡፡

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. አንጻርና ሠም ረገፍ = አነ ወዝናም፤ አሮን

ለ. ወርቅ ረገፍ = በቀል ፤አረጋዊ

ሐ. ኅብር = ዐረግነ ላዕለ ወታሕተ ወረድነ

መ. ሠምና ወርቅ = አቡነ አሮን

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


ሀ. ለሠሙ፡-
በቤተሰብእ ጠብ ምክንያት አንተም ተው አንተም ተው የሚል አስተራቂ ሽማግሌ ሰው መታጣትን
የሚያሳይ መልእክትን ይዟል፡፡
ለ. የወርቅ መልእክት፡-
በዓመ ሓራ መቄት የሚገኘው የጻድቁ አቡነ አሮን የዋሻ /የፍልፍል/ ቤተ ክርስቲያን በአናቱ ላይ ፀሓይና
ሰማይ እየታየበት በተኣምራት ዝናብ የማይነጥበበት /ዝናብ የማያስገባ/ በመኾኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ባለ
ቅኔው የቤተሰብእ ጠብ በማስመሰል ‹አነ ወዝናም› ማለታቸው ምን አልባት ዋይዜማ ቅኔ እንዳያደርጉ
ወይም ከማሕሌት እንዳይገቡ የተከለከሉ ይመስላል፡፡

፮. ተጨማሪ

ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት = አራራይ


ለ. የቤት መምቻው = ‹‹ነ››

ሐ. ድምፀት = ጥላቻ/ጠብ

፯. ርእይ
ሀ. እጅግ የቅኔው አሰካክ/አወቃቀር/ ይበል ነው፡፡
ለ. ምን አልባት ‹‹እምበዊአ ቤቱ›› እም "በ" ከሚለው በስተቀር

4
፩.፬ ዋይዜማ ቅኔ ዘአለቃ ለማ
ዘካርያስ አበአሐዱ ወአበብዙኀን አብርሃም
እምወሊደ ውሉድ አቀብ ዘኖፃ በረስዓኖሙ ኢስእኑ፤
አብ እምነውሉድ ይቀድም አኮኑ፤
ለኢትዮጵያሰ እም ዕበያ ዘአይትርከብ መጠኑ፤
እስከጽንፈ ዓለም ከመንዜኑ፤
እምነኵሉ ትውልድ በበዘመኑ፤
አበዊሁ ዘወለደ መኑ፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤234)፡፡

፩. የቅኔው ትርጕም፤
ያንድ ልጅ አባት ዘካርያስ፤ የብዙዎች አባት አበርሃም
ልጆቹን ከመውለድ/የአሸዋ ዓቀበት በእርግናቸው ጊዜ አልተሣናቸውም (አልደከሙም) አባት ከልጁ
ይቀድማል፡፡ ልኩ መጠኑ የማይታወቅ የኢትዮጵያን ገናናነት ግን እስከ ዓለም ዳርቻ እንናገር ዘንድ፤
በየዘመኑ ከትውልድ ኹሉ አባቱን የወለደ ማን ነው?

፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤
አባባል፤ ‹ልጅ ካባት አይበልጥም›

፫. የቅኔው ዐውድ (መቸት)፤


ከመጽሐፉ መረዳት እንደቻልነው ሢመተ ጳጳሳትን ያመለክታል፡፡

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. አንጻር፤ ለ. መጠየቅ ‹አበዊሁ ዘወለደ መኑ› ሐ. ሠምና ወርቅ፤
መ. ተዛምዶ ሲኾኑ የቅኔው ዐውደ ታሪክ ባለመታወቁ (በባለቅኔው ኅሊና ስለቀረ) ይኽን ይመስላል
ለማለት አያስደፍርም፤ ዝም ብሎ መገመትም ደፈሬታ ነው፡፡ ምክንያቱም ቅኔ ማለት የግለሰብእ የኅሊና
ፍሬ ፅንስ ራእይና ሕልም ነውና፡፡

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


ከሠሙ አንጻር ብቻ ሲታይ ‹ተስአሎ ለአቡከ ወይነግረከ› የሚለውን ጥቅስ ይዞ የሚያስተምር ነው፡፡
ይኽም ‹ልጅ ቢሮጥ አባቱን አይቀድም› የሚል ይመስላል፡፡ በተጨማሪም አብርሃምና ዘካርያስ
በስተእርግና መውለዳቸውን ይጠቅሳል/ያመለክታል፡፡

5
፮. ተጨማሪ
ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት = ዕዝል /ሕዙል/
ለ. የቅኔው ግጥም /ቤት = "ኑ"
ሐ. ድምፀት = የአባትና የልጅ መቅደምና መከተል ነው፡፡
መ. ቅኔው የቀረበበት የዐረፍተ ነገር ስልት ባንድ የግስ ማሠሪያና አስረጅ፤ በአንድ የመኾን ግስ ነው፡፡

፯. ርእይ
የቅኔው ምስጢር ለባለቅኔው ብቻ የቀረ ነው፡፡

፩.፭. ሣህልከ ቅኔ
ማእዜ ለመደት ገዳመ ዕዝራ
አስካለ ማርያም ዘወጽአት እምድካመ አንስት ብሔራ፤
ለዘይሬእያ ኀይለጸላዒ
እስመ ብእሲተ ኢኮነት በግብራ፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤234/35) ፡፡

፩. የቅኔው ትርጕም፤
የዕዝራን ገዳም መቼ ለመደችው?
ከሴቶች ድካም/አገሯ የወጣች አስካለ ማርያም
ለሚያያት የጠላት ኃይል በሥራዋ ሴት አልኾነችምና፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤
መጽሐፋዊ ነው፤ የአስካለ ማርያም የሥራ ኹኔታ
‹‹ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት ወሶበ ርእያ ኢኮነ ብእሲተ አላ ሀገር ቅድስት››
(ዝማሬ ገጽ ፵፫፤ ዚቅ ገጽ ፸፪-፸፫፤ ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ 353 ዕዝራ፲)፡፡

፫. የቅኔው ዐውድ /መቼት/፤


በአርባዕት መወድስ ቁመት ጊዜና የአስካለ ማርያም መገኘት
፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ
ሀ. ወርቅ ረገፍ/ ከፊል ጠቃሽ/ - ገዳመ ዕዝራ፤ኀይለ ጸላዒ፤ ብእሲተ
ለ. ሠም ረገፍ = አስካለ ማርያም
ሐ. ሠምና ወርቅ = ድካመ አንስት ሀገራ

6
፫. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤
ሀ. ሠም = ወሶበ ርእያ ዕዝራ ኢኮነት ብእሲተ
ለ. ወርቅ = የአስካለ ማርያም ሴት ስትኾን ሀገር ናት ማለት ሀገር ኹሉን ቻይ መኾኑን ያሳያል፡፡

፮ ተጨማሪ
ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት ግእዝ
ለ. የቅኔው ግጥም /ቤት/= ራ
ሐ. ድምፀት = ሙገሳ
መ. የቅኔው ግጥም ብዛት ሁለትና ማንደርደሪያ ያለው መደብ በሰረገላ ነው፡፡

፯. ርእይ
ለሰሙ የተጠቀሰው ጥቅስ ግልጽ ሲኾን
በወርቁ በኩል ግን የቅኔው ምስጢር ለባለቅኔው ብቻ ነው ግልጽነቱ፤
ምክንያቱም አስካለ ማርያም ማናት? የትኛዪቱስ ንግሥት?

ክፍል ሁለት
፪. ቅኔያት ፪
፪.፩ መወድስ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ - ሰይፈ ምኒልክ
ሰይፈ ምኒልክ ክርስቶስ ዘኢይሠአር
ላእከ ኮነ ለግዝረተ ክሳድ በየዋሃቱ፤
ወእንተ ኢዘርዑ ሰብአ እምኢትዮጵያ ገራህቱ፤
የአርሩ እንበለ ጊዜሁ አስይፍት መገብቱ፤
ወኢተዘከረ ምኒልክ፤
ለመሥዋዕት በግዐ አምጣነ ሮማዊ መሥዋዕቱ፤
ለዓለም
አሕጸረሂ ኑኀ ምልክና በመጠነ ፀሓይ መስፈርቱ፤
አምጣነ ረሰየ አድማስ ወሰነ ለመንግሥቱ፤
ወእንዘ ይእኅዝ ምድረ ለባሕቲቱ፤
ሰማየ ለሥላሴ ኀደገ በኂሩቱ፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤150/219)፡፡

7
፩. የቅኔው ትርጕም፤
የማይሻር ክርስቶስ/የምኒልክ ሰይፍ፤
አንገትን ለመግዘር መልእክተኛ አገልጋይ ኾነ፤
ያልዘሩትን ሰው ከርሻው/ኢትዮጵያ ያለ ጊዜው ያጭዳሉ ሹማምንቱ/አስይፍት፡፡
ምኒልክ ለመሥዋዕት በግ አላሰበም፤ መሥዋዕቱ ሮማዊ ነውና (ኢጣሊያ)፤
ያገዛዙን ቁመት ወርድ በመስፈሪያው/ፀሓይ ልክ አሳጠረ፤
ለመንግሥቱ ዳርቻ አድማስን አድርጓልና፡፡
ምድርን ለብቻው ይዞ፤ በቸርነቱ ሰማይን ለሥላሴ ተወላቸው፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤
መጽሐፋዊ ነው፤ ‹እብል እንከ ክርስቶስ ላእክ ኮነ ለግዝረት› (ሮሜ. ፲፭ ÷፰)
‹‹ማእረሩሰ ኅልቀተ ዓለም እሙንቱ ወዐጸዱኒ እሙንቱ መላእክት›› (ጾመ ድጓ ዘደብረ ዘይት ገጽ ፻፬)

፫. የቅኔው ዐውድ መቼት፤


በአድዋ በዓል ጊዜ ይመስላል፤ ምክንያቱም በአደራሽ እንደተደረሰ መጽሐፉ ገጽ 218 ላይ ይገልጻልና፡፡

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ሠም እና ወርቅ - ሰይፈ ምኒልክ ክርስቶስ
- ኢትዮጵያ ገራህቱ
- አስይፍት መገብቱ
ለ. ለዋጭ - ላእከ ኮነ ፤ በግዕ
ሐ. አንጻር
መ. ኩሸት / ግነት/ - ወእንዘ ይእኅዝ ምድረ ለባሕቲቱ ፤ ሰማየ ለሥላሴ ኀደገ በኂሩቱ

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤

- በጦርነት ስለሞቱት ጣሊያኖች ፍርድ ለሥላሴ መስጠት ነው፡፡

- ምኒልክ ጣሊያንን ድል ነስቶ የኢትዮጵያን ወሰነ ግዛት ማስከበርና መከበር ነው፡፡

፮. ተጨማሪ

ሀ. የቅኔው ዜማ = ማእከለ ግእዝ ወዓራራይ ምድቡም ግእዝ ነው፡፡

ለ. የቅኔው ግጥም = ቱ ፤ ቊጥሩ ስምንት

ሐ. ድምፀት = ወርኀ ማእረርና ምስፍና

8
፯. ርእይ

- ገጸ ንባቡ እጅግ ይበል የሚያሰኝ ነው፤ ቅኔው ንባብም ምስጢርም አለው፤ ነገር ግን በውስጠ ተሳቢ
በቅኔ ሞያ ሲታይ የሳቢና የተሳቢ ቅደም ተከተልን የሳተ ይመስላል፡፡
ምሳሌ፡- ‹ወእንተ ኢዘርኡ ሰብአ እምኢትዮጵያ ገራህቱ፤
የአርሩ እንበለ ጊዜሁ አስይፍት መገብቱ፤›ን የመሰለ ነው፡፡

፪.፪. መወድስ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ - ወጽአ ይዝራዕ


ወጽአ ይዝራዕ ደመ አጻብእ
ዘራዒ እግርኪ በርደተ ዝናም በቀል፤
ወለአስዋከ ግብጽ ቦሙ መከየድኪ ምጽላል፤
አምጣነ ረኀብ ወድካም፤
ገብሩ በዓለ ተሐውሶ በከርስኪ ሐቅል፤
ወእምድምፀ አእባን ዘይኬልሑ፤
መርፈቀ ሶኮና ኆኅት አኀዘ ይትለዐል፤
ለዓለም
ይጼልሉሂ በተባርዮ ዲበ ገጽኪ ምስሓል፤
አዕይቲሆሙ ብዙኀት ተውላጣተ መልክእ ኪሩቤል፡፡
ብዝኀ መባልዕት አእማት ዘኢያትለውኪ ድንግል፤
እግዚአብሔር እንዘምስሌኪ እስመ አንብዐ ገጽ እያሴስል፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤223/24) ፡፡

፩. የቅኔው ትርጕም፤
ገበሬ/እግርሽ በዝናብ/በቀል (ቂም ጠብ) መውረድ
የጣቶችን ደም ሊዘራ ወጣ
ለግብፅ እሾኾችም መጠጊያ እግርሽ አላቸው፤ ረኃብና ድካም በኾድሽ በረሀ መመለስ/በዓልን አድርገዋልና፡፡
ከሚጮኹት ደንጋዮች ድምፅ የተነሣ የደጃፍ/እግር መድረክ ከፍ ከፍ ማለት ዠመረ፤
በፊትሽ ምስሓል (የመቅደሱ መለመኛ) ዐይናቸው ብዙ የኾነ የመልክእ መለዋወጥ/ ኪሩቤል በመፈራራቅ
ይገርዳሉ፤ የመብል/ባርያ ብዛትን ያላስከተልሽ ድንግል፤
እግዚአብሔር ካንቺ ጋራ እያለ የፊት እንባን አያርቅምና፡፡

9
፪. ቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤
መጽሐፋዊና ተሰዶተ ድንግል ነው ፡፡
‹‹ናሁ ወጽአ ዘራዒ ከመይዝራዕ ወእንዘ ይዘርዕ ቦ ዘወድቀ ውስተ ፍኖት … ወቦ ዘወድቀ ውስተ ሦክ››
(ማቴ. ፲፫÷፫-፰) ፡፡
‹‹ወኮኑ ኪሩቤል ይረብቡ ክነፊሆሙ እመልዕልት እንዘ ይጼልሉ ክነፊሆሙ መልዕልተ ተድባብ ወገጾሙ
ይትናጸር በበይናቲሆሙ በዲበ ተድባብ›› (ዘፀ. ፴፯÷፰)፡፡
‹‹እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል ዘትነብር ዲበ ኪሩቤል›› (ኢሳ. ፴፯÷፲፯) ፡፡

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤


ወርኀ ጽጌ ይመስላል፡፡ የእመቤታችን ስደት (ቦታውም አዳራሻ ይመስላል) ፡፡

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ሠምና ወርቅ = ዘራዒ እግርኪ
ርደተ ዝናም በቀል
መከየድኪ ምጽላል
ከርስኪ ሐቅል … የመሰለ ነው፡፡
ለ. ሠም ረገፍ = ደመ አጻብእ
ሐ. ኅብር = እግዚአብሔር እንዘ ምስሌኪ እስመ አንብዐ ገጽ ኢያሴስል፡፡

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


ቅድስት ድንግል ማርያም በስደቷ የተቀበለችውን ጸዋትወ መከራ ኹሉን ያመለክታል፡፡

፮. ርእይ

- ቅኔው ከመጽሐፍ ጋራ የተዛመደ ነው፡፡

- ባለቅኔው ከቅኔ ጋራ ዐብረው የተሠሩ ይመስላሉ፡፡

- የወርቅ ዝርዝር በቅኔ ውስጥ በብዛት ይታይበታል፤

10
፪.፫ መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ- ትዕግሥተ ንባቡ
ትዕግሥተ ንባቡ ለኢዮብ እምኀበ ኢሰምዐ
ባሕታዌ ልደት ኤልያስ ለሀገረ ልማድ ዘየኀይሣ፤
ዕራቆ ኢወጽአ ለወላዲቱ እምከርሣ፤
ወለእንተ ዝናም ይውኅዛ
ጠፈረ ሰማይ በቃሉ ፈወሳ፤
አምጣነ አልቦ እንተያርኁ
ወዘየዐፁ ሰማየ ዘእንበሌሁ ጊዜኀሠሣ፤
ለዓለም
አንስትሂ ዘሰማርያ ለእምረኀበ ፀንሣ፥
ለልደተ ቅብዕ ኢያስተብቊዓ ዘፈረ ከመይግሥሣ፤
ወለሠገራት ዘወጽኡ ለኀሢሠ በቀል አንበሳ፤
ኀበ ማዕዱ ነደ እሳት አርፈቆሙ በበኀምሳ፤ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤229/30)፡፡

፩. የቅኔው ትርጕም፤
የኢዮብን ትዕግሥት ነገር ካልሰማ ዘንድ
ልማድ አገርን የሚነቅፍ የልደት ብቸኛ (በልደቱ ልዩ የኾነ) ኤልያስ
ከናቱ ኾድ ራቁቱን አልወጣም፤ ዝናም የሚፈሳት ሰማይንም በቃሉ አዳናት፤
ያለሱ በቀር በፈለገ ጊዜ ሰማይን የሚዘጋና የሚከፍት የለምና፤
የሰማርያ ሴቶች ረኃብ ቢፀንሱ ቅቤ ዘይትን ለመውለድ የልብሱን ዘርፍ ሲዳስሱ አልለመኑትም፤
ቂም በቀል አንበሳን ለመፈለግ የመጡ ወታደሮችን ኸማዕዱ ነደ እሳት ዐምሳ ዐምሳ አድርጎ አስቀመጣቸው፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ /ምንጭ/፤


መጽሐፋዊ፤አባባልም ጭምር አለው፤
‹‹ወይቤ ዕራቅየ ወጻዕኩ እምከርሠ እምየ ወዕራቅየ እገብእ ውስተ መሬት›› (ኢዮ. ፳÷፳፩)፡፡
‹‹ወመጽአት ብእሲት እንተደም ይውኀዛ እምዐሠርቱ ወክልኤቱ›› ማር ፭÷፳፭፤ ሉቃ ፰÷፵፫)

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤


ልደተ ኤልያስ ነቢይ /አርባዕት መወድስ ቁመት/

11
፬. የቅኔው መንገድ፤
ሀ. አንጻር፤ ነቃፊ ጥቅስ፡- ትዕግሥተ ንባቡ ለኢዮብ
ለ. ሠምና ወርቅ፡- ባሕታዊ ኤልያስ
ሐ. ወርቅ ረገፍ፡- ሠም ረገፍ፤

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


የኤልያስን ልደት ከኢዮብ ልደት ጋራ በማወዳደር - ‹ዕራቅየ ወጻዕኩ እምከርሠ እምየ፤ ዘጥብሉለ እሳት›
የሚለውን ተፈጥሯዊ ልደትና ተኣምራዊ ልደተ ኤልያስ ነው፡፡

፮. ርእይ
ሀ. ከዚኽ ቅኔ አንዱን ካንዱ አሰናስሎ መቀኘት የሊቅነት ሞያ እንደኾነ መረዳት ችለናል፡፡
ለ. ከሞያ አንጻር = ለወላዲቱ እምከርሳ = ለ ና እም ወለሠገራት
ሐ. ከዜማ ልክ አንጻር = ዘፈረ ከመ ይግሥሣ
መ. ከግጥም (ከስንኝ) አንጻር = አንበሳ ፈወሳ እምከርሣ፤ ኀሠሣ፤ ቤቱ መፋለሱን ያሳያል፡፡

፪.፬. መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ለማ -ጻድቅ ይምሕር


ጻድቅ ይምሕር ነፍሰ እንሰሳሁ
ለዝሰ ሕግ ያዕቆብ ተሀየዮ፤
አመደመ በግዕ በግፍዕ በልብሰ ዮሴፍ ሴረዮ፤
ኀዲጎ በግዐ እንተ ተገፍዐ
ያዕቆብ አምጣነ ለወልዱ ብዙኀ በከዮ፤
ወእንበለ ጌጋይ የሐምዮ፤
ለአርዌ ንጹሕ እንዘ ይነግር እከዮ፡፡
ለዓለም
አብሰ ግፍዐበግዕ ወዘያዕቆብ ርእዮ፤
ለወልዱ ኢተራሕርሐ እንዘ ቤዛ በግዕ ይሬስዮ፤
ወከመ ጸላኢ ኢይበል ከመያዕቆብ ኢርእዮ፤
ምሳሌሁ ቅድመ ዓለም ወድኀረ ዓለም ኢተሌለዮ፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤236/37)፡፡

12
፩. የቅኔው ትርጕም፤
ለከብቱ አካል ያዝናል ይራራል ደግ ሰው፡፡
ይኽንን ሕግ ግን ያዕቆብ ቸል አለው፡፡
የበግ ደም በግፍ የዮሴፍን ልብስ በለወጠው (ቀለም ባገባው) ጊዜ
የተበደለ በግን ትቶ ያዕቆብ ለልጁ አልቅሷልና
ንጹሕ አርዌን ያለበደል ያማዋል ክፋቱን እየነገረ፡፡
አብ ግን የበግን መበደል የያዕቆብን መበደል ዐይቶ፤
የበግ ቤዛ (ዋጋ ለውጥ) ሲያደርገው ለልጁ አላዘነም አልራራም፡፡
ጠላት ‹እንደ ያዕቆብ እንጂ ልጁን ባያየው ነው! › እንዳይል፤
ቅድመ ዓለም ድኅረ ዓለም አልተለየውም፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ፤
መጽሐፋዊ አባባል ነው፤
‹‹ወነሥኡ ክዳኖ ዘዐስቅ ወሐረዱ ላዕሌሁ ማሕስዐ ጠሊ ወመልእዎ ደመ ለክዳኑ›› (ዘፍ. ፴፯÷፴፩)፡፡
‹‹ይሜጡ ነፍሶ ቤዛ አባግዒሁ›› (ዮሐ. ፲÷፲፩-፲፮)
‹‹ወልዶ ጥቀ ኢምህከ እምኔነ አላ መጠወ በእንተ ኵልነ›› (ሮሜ. ፲÷፴፪)፡፡

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤


- ስብከት በሌሊተ እሑድ አርባዕት መወድስ ቁመት

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ነቃፊ፤ ለ. አንጻር፤ ሐ. ወርቅ ረገፍ፤ መ. ኅብር፤

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


ትንቢተ ነቢያትን አመልካች ነው፡፡

፮. ርእይ

- ቅኔው በዝርው ውስጠ ወይራና በኅብር ያሸበረቀ ወደር የሌለው ቅኔ ነው፡፡

- ለዝሰ ሕግ የሚለው ንባብ አከራካሪ ነው፡፡

- ‹ኀዲጎ በግዐ እንተ ተገፍዐ› = እንደዚኽ ያለውን ሙጫ ነው ይላሉ፡፡

- ቅኔውም ኵልክሙ መወድስ መኾንም ይችላል፡፡

13
፪.፭. አሠረ ንጉሥ ዘአለቃ ለማ - ምኒልክ ግበር
ምኒልክ ግበር ላዕለሮምያ መጠነ እዴከ ትክል፤
አምጣነ ለአጺድ በጽሐ ማእረራ ወመዋዕሊሃ ለኀጉል፤
ዓዲ ተዘከር ወስተ ወንጌል፤
ላዕለሮምያ በለስ ኢሀሎ አስካል፤
ከመይቤ ወልደ ያሬድ ቃል፡፡ (መንግሥቱ ለማ፤ 2003፤141/215/16)፡፡

፩. የቅኔው ትርጕም፤
ምኒልክ በሮምያ ላይ እጅኽ እንደ ቻለ መጠን አድርግ፤
መከሯ ለመታጨድ፡ ቀኗም ለጥፋት ቀርቧልና፡፡
ዳግመኛ በወንጌል ያለውን ዐስብ፤ በሮምያ/በለስ ላይ ፍሬ የለም እንዳለ ወልደ ያሬድ/ቃል (ወልድ)፡፡

፪. የቅኔው መፈጠሪያ (ምንጭ)፤

- ምጽአተ ጣሊያንና መጽሐፋዊ ነው፡፡

- ‹‹ኢይኩን ፍሬ እምውስቴትኪ ለዓለም›› (ማቴ ፳፩÷፲፱)

- ‹‹ኅድግዎ ይልሀቁ ኅቡረ እስከ ጊዜ ማእረር ወሶበ ፈጸመ ፈርዮተ ሶቤሃ ይፌኑ ማዕጸደ›› (ማቴ.
፲፫÷፴ ፤ማር. ፬÷፳፱ ፤ ዮሐ. ፬÷፳፭)፡፡

- ‹‹አልቦ ፍሬ ዘይበልዕ እምኔኪ ለዓለም›› (ማር› ፲፩፤ ሉቃ ፲፫÷፯)፡፡

፫. የቅኔው ዐውድ (መቼት)፤


ድኅረ ቊርባን፤ ድኅረ ክብር ይእቲና ድኅረ ዝማሬ ቅድመ ነጋሢ (ንጉሥ)

፬. ቅኔው የቀረበበት መንገድ፤


ሀ. ትንቢተ ቅኔ፤ ትእዛዝ፤ ሰሚ፤ ድልዋኒክሙ
ለ. ሠምና ወርቅ = ሮምያ በለስ፤ ሐ. አነጻጻሪ /አንጻር/

፭. የቅኔው ዐቢይ መልእክት፤


- ከምንጩ እንደተረዳነው ጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት የተደረሰ ትንቢተ ቅኔ ነው፡፡
ስለዚኽ ‹ድልዋኒክሙ ንበሩ› - ተዘጋጅቶ መጠበቅን ያመለክታል፡፡
ባለ ቅኔው እንደነቢያት - ነቢይ እንደኾነ አስመስሏቸዋል፤ ቅኔያቸውም እንደ ትንቢተ ነቢያት = ትንቢት
እንደኾነ የሚያሳይና የቅኔን ምንነትና ጠቀሜታን ለዘለዓለም የሚያስረዳ ኹኖ አግኝተነዋል፡፡

14
፮. ተጨማሪ
ሀ. የቅኔው የዜማ ስልት ዕዝል
ስሙ የዕዝል ዕጣነ ሞገር አሠረ ንጉሥ/ ነጋሢ
ለ. የቤት መምቻው ፤ ል፤ የቤቱ ቊጥር = ፭ ቤት ነው፤
ሐ. ድምፀት = ምጽአተ ጣሊያን ወኅልቀታ/ ይኽም የባለ ቅኔውን መንፈሳዊነት ያሳያል፡፡

፯. ርእይ

- የባለ ቅኔው እንደ ነቢያት = ነቢይ


ቅኔያቸውም እንደ ትንቢተ ነቢያት ትንቢት እንደሆነ የሚያሳይና የቅኔን ጠቀሜታ ለዘለዓለም የሚያስረዳ
መኾኑን ተረድተናል፡፡

15
ማጠቃለያ
በመጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ወልደ ታሪክ በሚለው ጽሑፍ ውስጥ በቊጥር ዐሥር ከኾኑ ቅኔዎች
በመነሣት የእያንዳንዱን ቅኔ መነገሪያ (መፈጠሪያ)፤ ዐውድ (መቼት)፤ ቅኔው የቀረበበት መንገድና ዐቢይ
መልእክት ምን እንደኾነ መመርመርና መረዳት እንድንችል አድርጎናል፤ በዚያ ዘመን የአለቃ ለማ የቅኔ
ብስለትንም ካኹኑ ዘመን ቅኔና የቅኔ መምህራን ጋራ ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ርቀት ያኽል እንደኾነ
ተመልክተናል፤ ዐቅማችንንም ዐውቀንበታል፡፡
ይኽም ማለት ምንም እንኳን የሊቃውንቱን ቅኔ ሙሉ በሙሉ መተርጐምና ማመስጠር፤ ሞያዊ
ኺደቱንም ጭምር እንደዚኽ ነው፤ ይኽንንም ይመስላል፤ ባይባልም መገመት ግን እንደሚቻል
ተረድተንበታል ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ቅኔ በኹኔታው /በጠባይዑ ያለ ደራሲው/ ያለ ባለቤቱ/
በደንብ አይተረጐምም፤ አመስጥሮም የለውም፡፡
ለዚኽም ነው ‹‹እሳት ያለ ባለቤቱ አይነድም›› እንደሚባለው በየጊዜው የተነሡ የቅኔ መምህራን ኹሉ
የቅኔያቸውን አመስጥሮ ቀርቶ ተራ የቅኔያቸውን ትርጕም ‹ይኽን ብትፈታ አንገቴን ለስለት እሰጣለኹ! ›
የሚሉት፡፡
ስለኾነም በመምህራችን ዶ/ር ዘለዓለም መሠረት ትምህርታዊ ትእዛዝ ምክንያት የተሰጠንን የቤት ሥራ
በመጽሐፈ ትዝታ ውስጥ ከቅኔው ትርጕምና የምስጢር ፍንጭ በመነሣት /በመታገዝ/ መሥራት ስላስቻለን
ቸሩ መድኀኔዓለም የተመሰገነ ይኹን፡፡

16
ስምዐት/ወሃቢ/ዋቢ/
፩. መምህር ሔኖክ ወልደሚካኤል፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፤፲፱፻፺፩ ዓ.ም ፡፡
፪. መጽሐፈ ዚቅ ወመዝሙር፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፤፲፱፻፹፮ ዓ.ም ፡፡
፫. መንግሥቱ ለማ፤ መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ፤
፪ሺሕ፫ ዓ.ም፡፡
፬. መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፤መጽሐፈ ቅኔ /ዝክረ ሊቃውንት/፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት
፳፻፲ወ፪ ዓ.ም፡፡
፭. ምዕራፍ ዘቅዱስ ያሬድ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፤፲፱፻፹፯ ዓ.ም፡፡
፮. ቡሩክ ጌታቸው (መጋቤ ምስጢር)፤ ጾመድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ፳፻፲፭ ዓ.ም፡፡
፯. ብሉይ ኪዳን ስምንቱ ብሔረ ኦሪት፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ፲፱፻፺፬ ዓ.ም ፡፡
፰. ትንቢተ ኢሳያስ ፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ፳፻ወ፩ ዓ.ም ፡፡
፱. አርባዕቱ መጻሕፍተ ብሉያት፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም ፡፡
፲. ወንጌል ቅዱስ ዘእግዚእነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ካርስቶስ፤ተስፋ ገብረ ሥላሴ ፲፱፻፹፰ ዓ.ም፡፡
፲፩. ዝማሬ መዋሥዕት፤ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ፲፱፻፹ ዓ.ም፡፡
፲፪. የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ንባቡና ትርጓሜው ትንሣኤ ዘጉባኤ ማሳተሚያ ፲፱፻፹፰ ዓ.ም፡፡

17

You might also like