Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 10

በቅድሥት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ

የልሳነ ግእዝ ክፍለ ትምህርት


ሴሚናር ክፍል-፭
Article on Tomare Tesbet /ጦማረ ትስብዕት/

በዘውዱ ግርማ

ለዶ/ር አንዱዓለም አስራት ፣ ለዶ/ር አብነት አስራት፣ ዶ/ር ቢኒያም ወልዱ


2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Contents
መግቢያ ................................................................................................................................. 2

ድርሳን ፩ ............................................................................................................................................... 3

ድርሳን ፪ ................................................................................................................................................. 3

ድርሳን-፫ ................................................................................................................................................. 4

ጦማረ ትስብዕት ከጥንካሬ እና ከድክመት አንጻር ሲፈተሸ ............................................................ 6

ማጠቃለያ ................................................................................................................................ 8

ማጣቀሻ .................................................................................................................................. 8

1
መግቢያ

አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሐፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ
ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት
በእስር ኖሩ በዚህም ወቅት ለብዙ መጸሐፍቶች መጻፍ መነሻ ምክንያት ሆኗል።በ1442 በሰንበት
ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤ/ክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን
ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳት በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል
። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቂቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት
ነው።እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ
ለድንግልማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ መናፍቃንን አጼ ዘርአ ያዕቆብ ተከራክረው
ረትተዋል ለጦማረ ትስብእት መጻፍ ምክንያት ሆኗል።

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20በላይ መጻህፍትንም


በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው

ከነዚህም መካከል፦

1. መጽሐፈ ብርሐን 12. ዜና አይሁድ

2. መጽሐፈ ሚላድ 13. ጊዮርጊስ ወልደአሚድ

3. መጽሐፈ ሥላሴ 14. ተአምረ ማርያም

4. መጽሐፈ ባሕርይ 15. ተአምረ ትስብኢት

5. ተዓቅቦ ምስጢር 16. ልፉፈ ጽድቅ

6. ጦማረ ትስብእት 17. ትርጓሜ መላእክት

7. ስብሐተ ፍቁር 18. ተአምረ ጊዮርጊስ

8. ክሂዶተ ሰይጣን 19. ትርጓሜ ወንጌላት

9. እግዚአብሔር ነግሠ 20. መልክዓ ማርያም

10. ድርሳነ መላእክት 21. መስተብቁዕ ዘመስቀል ይገኙበታል።

11. ተአምረ ማርያም

2
ከነእነዚህም መጽሐፎች መከከል አንዱ ጦማረ ትስብእት መሆኑና ድርስቱም የራሱ የዘርአ
ያዕቆብ መሆኑን ያስረዳንል፡፡ጦማረ ትስብእት አፄ ዘርዐ ያዕቆብ በዘመነ ንግሥናቸው በ1434 ዓ.ም

ጀምሮ ስለ በዓላት አከባበርና ስለ ሃይማኖታዊ ጉዳይ … በተመለከተ ከጻፏቸው ድርሳናት መካከል


አንደኛውና ዋነኛው ሲሆን ጦማሪው ጌታቸው ኃይሌ ፕሮፌሰር የጦማረ ትስብእት መዋቅር ሰዋስውንና
ይዘቱን በማብራራት ለኛም ሆነ ለሌሎች ኆኅተ ጥበብ ናቸው፡፡ ጦማረ ትስብእትመወ በውስጡ የያዛቸው
ዋና ዋናዎቹ፦
ድርሳን ፩ እምነ መስከረም ፩ እስከ ታኅሣሥ ፬
ድርሳን ፪ እምነ ጥር ፬ እስከ ሚያዚያ ፲፯
ድርሳን ፫ እምነ ግንቦት ፮ እስከ ሐምሌ ፪
ይህ መጽሐፍ በውስጡ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ… ይዘት ያለው ነው። በጦማረ
ትስብእት ውስጥ ሰዋስዋዊ መዋቅርና መልክአ ፊደላቱን ለማየት ችለናል፡፡
ድርሳን ፩
እምነ መስከረም ፩ እስከ ታኅሣሥ ፬
ድርሳን ዘይትነበብ አመ ፩ ለመስከረም በበዓለ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ፡፡ አመ ፲ወ፪ ለጥቅምት በበዓለ
ማቴዎስ ወንጌላዊ፡፡ ፳ወ፪ በዐለ ሉቃስ ወንጌላዊ አመ፲ወ፰ በበዐለ ፊሊጶስ ሐዋርያ አመ ፬ ለታኅሣሥ
በበዓለ እንድርያስ ሐዋርያ (ገጽ 1)
ድርሳን ፪
እምነ ጥር ፬ እስከ ሚያዚያ ፲፯
ኦ ፍቁራንየ ደቂቀ ወንጌል መፍትው ለነ ናዕርፍ በበዓሎሙ ለሐዋርያ አበዊነ ወመምህራኒነ፡፡ ወናክብር
ዕለተ ክለሌሆሙ በስመ ለክዑ ለሉሆሙ በሲኖዶስ… ወእመሰ ተአዘዝነ ከመዝ ናክብር ዕለተ ክለሌሆሙ
ለሐዋርያት ወለሰማዕታት ወጻድቃን እለ አብደሩ ክርስቶስሀ (ገጽ 1) ወፈድፋደኬ ይደልወነ ከመናክብር
ዕለተ በዓላቲሁ ለእገዝእትነ ማርያም (ማርቁም) ንግሥቶሙ፡፡ ሲመተ ሐዋርያትሂ ወክብረ ሰማዕታት
ወጻድቃን ይእቲ እግዝእትነ ማርያም፡፡ እስመ አልቦሙ ካልአ ፍኖተ ዘእንበሌሃ (ገጽ 1) እስመ ብእሲ
እንዘይቀትል ነፍስ አው ዘማዊ አው ሰራቂ አዊ ዘይገብር ኩሎ ኀጢአተ ሶበ ዐቀበ ተዝካረ ሰምማ
ለእግዝእትነ ማርያም በውሂበ ምጽዋት ወበ አክብሮ በዓላቲሃ ኢይሰርይ ኀጢአቱ ወኢይክደዲቀ (ገጽ 2)

3
ወይመላ ደብተራ ሞሎሕ ለክብረ ንግሣ ይደሉ ሰጊድ፡፡ ወለወልዳኒ እግዚብሔር ቃል ሰመዮ ጎግ ለስብሐተ
ስሙ ይደሉ ሰጊድ (ገጽ 3) ወገማልያልኒ ይቤ በእንተ መጻሕፈ ተአምሪሃ ለንግሥተ ሰማይ ወምድር
ማርያም…. ረከበ ለ1 ዲያቆን ዘስሙ ተጠምቀ መድኅን… ጸዊርየ ዘንተ ብራና ከመይጽሐፍ ቦቱ ተአምሪሃ
ለማርያም (ገጽ 3) በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ርእሱ ውስተ ኩርስ እምተገለፍኩ ሥጋ ለዐሠርቱ መዋዕለ
አውራኅጉአ በደም፡፡ (ገጽ 5) ወካዕበ ስምዑ መንክረ አኀው /ሐ/ ሀለውአ እለ ይቤሉ አንክሮ በዐላትሰ
በአዕርጎ ዕጣን ወበነሣአ መሥዋዕት ወኢኮነ ያጽርዑ ተግባረ እድ ሐሪሰ ወሐርጸ ወመቱረ ዕፀው ወሐዊረ
ፍኖት… እስመ ቀሪበ ኵርባን ይክልእ መንሱተ ወንሕነሰ ንገበር በዓለ ወላዲቱ ወጻድቃኒሁ (ገጽ5)፡፡
(እስመቀረበ ኵርባን- ቁርባን /ጸሐፊው አገው ይመስላል፡፡ድርሳን ፫ እምነ ግንቦት !፮ እስከ ሐምሌ ፪
ወንሕነሰ ክብር በዐለ በከመ ተአዘዘነ በሲኖዶስ ርሒቀነ እምጠንቋሊ ዘተሰምየ አይሁዳዊ ወመጣዐዌ
ወንብል ስብሐት ለእግዚአብሄር ኪያነ ለዘፈጠረ ከመናምልኮ (ገጽ ፮):: ናሁኬ መሀረ በርተሎሜዎስ
ለሕዝበ ክርስቲያን ስመ ኢያስትቱ ውሂበ ምጽዋት ለነዳያን (ገጽ ፮):: ወትገብር ፍልጠተ ማእከለ ብእሲ
ወብእሲቱ አድርዓከ… ወአንተሰ ጠንቋ ረሰይኩ ኵሎ ትጋህከ ለፈሊጠ ብእሲ እምብእሲቱ ለአብ
እምወልዱ ወለእም እምወለታ ወለመርዓት እምሐማታ ወኮንኩሙ ፀረ ለሕዝበ ክርስቲያን (ገጽ ፯):: ይቤ
ፊሊጶስ በሲኖዶስ ኦ ወልድየ ኢትኵን ፈታዌ እስመ ፍትወት ትስሕብ ኀበዝሙት ወእምድኅሬሁ ትሬስዮ
ለብእሲ ሰሐቀ ወሰለቀ ለኵሉ (ገጽ ፰)፡፡ ወመሀርከ ኅረየተ (ይተ) ዕለታት ወሰዓታት እስከተስመይከ
አይሁደ ወመጣዓዊያነ፡፡ ወካዕበ ይቤ እንድርያስ ኦ ወልድየ ዝያይ እምኩሉ እኩይ ወጽለእ ኩሎ እከየ (ገጽ
፱)
ድርሳን ፫
ድርሳን ዘይትነበብ አመ 1 ለግንቦት በበዓለ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ፡፡ አመ ፲ወ2 ለሀምሌ በበዓለ
ማቴዎስ ወንጌላዊ፡፡ ፳ወ2 በዐለ ሉቃስ ወንጌላዊ አመ፲ወ፰ በበዐለ ፊሊጶስ ሐዋርያ አመ 4
ለታኅሣሥ በበዓለ እንድርያስ ሐዋርያ (ገጽ 1)

ኦ ፍቁራንየ ደቂቀ ወንጌል መፍትው ለነ ናዕርፍ በበዓሎሙ ለሐዋርያ አበዊነ


ወመምህራኒነ….፡፡ ወናክብር ዕለተ ክለሌሆሙ በስመ ለክዑ ለሉሆሙ በሲኖዶስ… ወእመሰ
ተአዘዝነ ከመዝ ናክብር ዕለተ ክለሌሆሙ ለሐዋርያት ወለሰማዕታት ወጻድቃን እለ አብደሩ
ክርስቶስሀ (ገጽ 1)

4
ወፈድፋደኬ ይደልወነ ከመናክብር ዕለተ በዓላቲሁ ለእገዝእትነ ማርያም (ማርቁም)
ንግሥቶሙ፡፡ ሲመተ ሐዋርያትሂ ወክብረ ሰማዕታት ወጻድቃን ይእቲ እግዝእትነ ማርያም፡፡
እስመ አልቦሙ ካልአ ፍኖተ ዘእንበሌሃ (ገጽ 1)

እስመ ብእሲ እንዘይቀትል ነፍስ አው ዘማዊ አው ሰራቂ አዊ ዘይገብር ኩሎ ኀጢአተ ሶበ ዐቀበ


ተዝካረ ሰምማ ለእግዝእትነ ማርያም በውሂበ ምጽዋት ወበ አክብሮ በዓላቲሃ ኢይሰርይ ኀጢአቱ
ወኢይክደዲቀ (ገጽ 2)

ወይመላ ደብተራ ሞሎሕ ለክብረ ንግሣ ይደሉ ሰጊድ፡፡ ወለወልዳኒ እግዚብሔር ቃል ሰመዮ ጎግ
ለስብሐተ ስሙ ይደሉ ሰጊድ (ገጽ 3)

ወገማልያልኒ ይቤ በእንተ መጻሕፈ ተአምሪሃ ለንግሥተ ሰማይ ወምድር ማርያም…. ረከበ ለ1


ዲያቆን ዘስሙ ተጠምቀ መድኅን… ጸዊርየ ዘንተ ብራና ከመይጽሐፍ ቦቱ ተአምሪሃ ለማርያም
(ገጽ 3)

በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ርእሱ ውስተ ኩርስ እምተገለፍኩ ሥጋ ለዐሠርቱ መዋዕለ


አውራኅጉአ በደም፡፡ (ገጽ 5)

ወካዕበ ስምዑ መንክረ አኀው /ሐ/ ሀለውአ እለ ይቤሉ አንክሮ በዐላትሰ በአዕርጎ ዕጣን ወበነሣአ
መሥዋዕት ወኢኮነ ያጽርዑ ተግባረ እድ ሐሪሰ ወሐርጸ ወመቱረ ዕፀው ወሐዊረ ፍኖት…
እስመ ቀሪበ ኵርባን ይክልእ መንሱተ ወንሕነሰ ንገበር በዓለ ወላዲቱ ወጻድቃኒሁ (ገጽ 5)፡፡
(እስመቀረበ ኵርባን- ቁርባን /ጸሐፊው አገው ይመስላል፡፡

ወንሕነሰ ክብር በዐለ በከመ ተአዘዘነ በሲኖዶስ ርሒቀነ እምጠንቋሊ ዘተሰምየ አይሁዳዊ
ወመጣዐዌ ወንብል ስብሐት ለእግዚአብሄር ኪያነ ለዘፈጠረ ከመናምልኮ (ገጽ ፮)::

ናሁኬ መሀረ በርተሎሜዎስ ለሕዝበ ክርስቲያን ስመ ኢያስትቱ ውሂበ ምጽዋት ለነዳያን (ገጽ ፮)::

ወትገብር ፍልጠተ ማእከለ ብእሲ ወብእሲቱ አድርዓከ… ወአንተሰ ጠንቋ ረሰይኩ ኵሎ ትጋህከ
(ተ) ለፈሊጠ ብእሲ እምብእሲቱ ለአብ እምወልዱ ወለእም እምወለታ ወለመርዓት እምሐማታ
ወኮንኩሙ ፀረ ለሕዝበ ክርስቲያን (ገጽ ፯)::

ይቤ ፊሊጶስ በሲኖዶስ ኦ ወልድየ ኢትኵን ፈታዌ እስመ ፍትወት ትስሕብ ኀበዝሙት


ወእምድኅሬሁ ትሬስዮ ለብእሲ ሰሐቀ ወሰለቀ ለኵሉ (ገጽ ፰)፡፡

ወመሀርከ ኅረየተ (ይተ) ዕለታት ወሰዓታት እስከተስመይከ አይሁደ ወመጣዓዊያነ፡፡ ወካዕበ ይቤ


እንድርያስ ኦ ወልድየ ዝያይ እምኩሉ እኩይ ወጽለእ ኩሎ እከየ (ገጽ ፱)

5
፩. ጦማረ ትስብእት በጥንካሬ እና በድክመት ሲፈተሽ

፩.1 ከሥነ-ጽሑፍ አንጻር

ምንም እንኳን የዚያን ግዜ የአጻጻፍ ስልት እንደ አሁኑ ዘመነ ባይሆንም በወቅቱ በነበረው
የጽሕፈት ደረጃ ሲታይ ትልቅ አበርክቶ የነበረው ጽሑፍ እንደሆነ መረዳት ችለናል፡፡ ይኹን
እንጂ ከአሁን የአጻጻፍ ሥልትና ጽሕፈታዊ (ሰዋስዋዊ) መቅር አንፃር ሲታይ ግን ክፍተቶች
ይታዩበታል፡፡ ለምሳሌ እንደማሳያ፡-

ሀ. ከመልክዓ ፊደል አንጻር ሲታይ

በጦማረ ትስብእት ውስጥ ከመልክዓ ፊደል አጠቃቀም አንጻር ሲታይ እጅግ የተዋጣለት
ጽሑፍ መሆኑን ለማየት ችለናል ይኽም የጽሕፈቱን ጠንካራ ጎን አጉልቶ ያሳያል፡፡

ለ. ከስነጽሑፍ ጠቀሜታ አንጻር ሲታይ

ይህ ጽሑፍ በዘመኑ የነበሩ ጸሐፍት የቋንቋውን ሰዋስዋዊ ጠንቅቀው መጻፍ ባይችሉም


የግዕዝ ቋንቋን ሀሳባቸውን በመጽሐፍ ከመግለጽና መረጃን ዘግቦ ከመያዝ አኳያ ትልቅ
ፋይዳ እንዳለው ለማየት ሞክረናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጸሐፊው የተጠቀመው የአጻጻፍ
ስልት ንጽጽራዊ የአጻጻፍ ስልት በመሆኑ አንባቢዎች ከሌላ ጽሑፍ ተጨማሪ ማብራሪያ
እንዲፈልጉ ይጋብዛል፡፡

፩.፪ ከሃይማኖት አንጻር

ይህ ጽሑፍ አብዛኛውን ጊዜ ክብረ ቅዱሳንን ማለትም የቅድስት ድንግል ማርያምን፣


የነቢያትን፣ የሰማዕታትን፣ የሐዋርያትን እና የጻድቃንን ክብራቸውን አጉልቶ እና ከፍ
አድርጎ ዪያሳይ እና የበዓላታቸውን አከባበርም በስርዓት የሚዘክር በመሆኑ ከፍተኛ
ሃይማኖታዊ ፋይዳ አለው፡፡ ጽሑፉ አምልኮተ እግዚአብሔርን አጉልቶ፣ አምልኮተ
ጣዖታትን እንዲሁም ምንም ዓይነት ኃይል እንደሌላቸው የገለጸ ሲሆን ለሃይማኖት
ተከታይ ትልቅ አስተምህሮት አለው፡፡ ለዚህ ማሳያ

ጥንቁልናና ውጤቱ ገፅ 22 መስመር 28 እንዲህ ይላል ናሁኬ ጠንቋልያን ኢኮኑ


ፍሉጣነ እሞለ ይሠግዱ ለፀሐይ ልሎ ስለጠንቋይ ካወሳ በኋላ መጠንቆልና ማስጠንቆል

6
እንደሚያስቀጣ ‹‹ይቤ ሕዝቅኤል በአንተ ሥራኢሆሙ ለእለ ይሠግዱ ለፀሐይ ወይቤለኒ
እግዚአብሔር በእንተ ሥራኤሆሙ ለእለ ይሰግዱ ለፀሐይ ወአነሂ እትቤቀሎሙ›› ገፅ
23 መስመር 15 ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ጥንቁልና መንፈስ ቅዱስን እንደሚያሳጣ የሐዋርያን ትምህርትን በመጥቀስ


‹‹ወእለሂ ኮከበ ወያመልኩ ኃይለ ሰማይ ወይትአቀቡ ዕለተ ወሰዓታተ ኰነ መዝበረ
እምንፈስ ቅዱስ››በማለት ሲገልጽ ፍሬ አልባ እንደሚያደርግ ደግሞ ኢይትረከብ በኀበ
ጠንቋልያን ፍሬ ሠናይ ይቤ እግዚእነ ዝንቱ ወንጌል የሚለውን የጌታችንን ት/ት
በመጥቀስ ‹‹ወእኩይኒ ዕፅ ፍሬ እኩየ ….. ወዕፅኒ ሠናይ ፍሬ ይፈሪ ወኢይክል ዕፅ
ሠናይ ፍሬ እኩየ፡፡›› በማለት የጥንቆላን አስከፊነት ይገልጻል፡፡

፩.፫ ከፖለቲካ /ከአስተዳደራዊ/ ሂደት አንጻር

በዚህ ጽሑፍ በርካታ አስተዳደራዊ ጉዳዮች የተነሡ ሲሆን ንጉስ በዚያው የነበሩትን
ሥልጣን ፈላጊዎች እንዴት አድርጎ አሸማቆ ማስወገድ እንደሚችል የተለያዩ ሥልቶችን
በመጠቀም ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ እና ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ጠንቋይ እና መናፍቅ
የሚል ስም በመለጠፍ እና ስማቸውን በማጠልሸት …… እንደቻለ ከመጽሐፉ ዘመን ጋር
የፖለቲካ ሥርዐት ጋር የሚዛመድ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ለዚህም ጠንቋይ እና መናፍቅ
የሚለውን ማስወገጃ ስልት ተቀናቃይ አሸባሪ ወዘተ… በማለት ሲገልጽ ይስተዋላል፡፡

ይህንን አርቲክል ጠቅለል አድርገን ከትችት አንጻር ስንመለከተው ጠንካራና ደካማ ጎኖች
አሉት፡፡

ጠንካራ ጎን፡- ስልጣኔ ባልተስፋፋበት ዘመን ይህን ጽሑፍ ጽፈው ለአንባቢ ማብቃታቸው፣
ነገረ መለኮትን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ ነገረ ማርያምን፣ የባዕላትን አከባበር በሚገባ ለምእመናን
ማስተማር መቻሉ ጣዖታትንና ጠንቋልያንን በሕዝቡ ዘንድ እንዲጠሉ እንዲናቁ እንዲሁም ቦታ
እንዳይኖራቸው ማድረግ መቻሉ አምልኮተ እግዚአብሔር በሰፊው እንዲመለክ ማድረጉ እጅግ
በጣም የሚስደስት እና ነፍስን ጭምር የሚያለመልም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪም በእያንዳንዱ ክፍል ስመ እግዚአብሔርን እያስቀደመ ማለትም በስመ አብ


ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ብሎ መጀመሩ ከምንም በላይ ጽሑፉን ታለቅ እና
ብእሴ እግዚአብሔር የሆነ ሰው እንደጻፈው ያመላክታል፡፡

7
ክፍተቶች፡- ከክፍተት አንጻር ስንመለከተው ደግሞ እርእሱ እና የሚተላለፈው ሐሳብ
አለመጣጣሙ፣ የመልክአ ፊደል ችግር፣ የሰዋስው ግድፈት መኖሩ የጽሑፉ ዓላማ ግልጽ ሆኖ
መቅረብ አለመቻሉ፣ የቃላት፣ የሐረጋትና የዐረፍተ ነገር ድረታ /ድግግሞሽ/ እንዲሁም ቅደም
ተከተሉን የጠበቀ የሐሳብ ፍሰት አለመኖሩ ወዘተ… እንደ ክፍተት ይታያሉ፡፡

ማጠቃለያ

ጦማረ ትስብእት በውስጡ በርካታ ይዘቶችን ጠቅለል አድርጎ የያዘ አርቲክል ነው፡፡ ይሁን እንጂ
ይህ አርቲክል አርቲክል ለመባል ግን በርካታ በአርቲክል ውስጥ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች
ባለመካተታቸው ትክክለኛ አርቲክል ነው ለማለት እምብዛም አያስደፍርም፡፡ ምክንያቱም ከርዕሱ
ጀምሮ ስንመለከተው የተሰጠው ርዕስ እና በውስጡ የተገለጹት ይዘቶች ሆድና ጀርባ ናቸው፡፡
ማለትም ፈጽመው የማይገናኙ ናቸው፡፡

ከስነ ጽሑፍ እይታ አንጻር ስንመለከተው በግእዝ ቋንቋ የሚሰጠው ረብ /ፋይዳ/ ጎልቶ
ባለመታየቱ ለአንባብያን ምንም ቁም ነገር ይዞ እንዳልተነሳና ዓላማው ምንን ለማሳካት
እንደተጻፈ በግልጽ አይታወቅም ይሁን እንጂ ይህ አርቲክል ከተጻፈበት ዘመን አንጻር
ስንመለከተው ዘመናዊነትከላይ እንደገለጽነው ጦማረ ትስብእት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን
ይዳስሳል፡፡ ከእነዚህም ርዕሰ ጉዳዮች ወይም ይዘቶች መካከል ጥቂቶቹ ሃይማኖታዊ፣
ፖለቲካዊ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ሥነ ጽሑፋዊ ወዘተ ጉዳዮች ተካተዋል፡፡

ማጣቀሻ
www.wikiwaand.com ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ
 am.m.www.wekipidiya.org›wiki›
ጌታቸው ኃይሌ ‹‹ጦማረ ትስብእት›› አርቲክል

8
9

You might also like