Who Are The Amhar

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 23

ለመሆኑ አማራ ማነው – ከታሪክ መዝገብ [ኀይሌ ላሬቦ]

Published on: http://www.satenaw.com/amharic/archives/19236

AUGUST 13, 2016


fShare 476 Like 178 Share 488

488

ዐማራ ኅብረተ-ሰብ

ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብ ላይ ብዙ ግፍና


ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት
ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-
ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ
ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአተካራ ግብግብ ከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው
አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትና የፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን
አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩን ራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካችም ሆነ
ሰሚ፣ መንግሥት ነን ባዮቹ የወያኔ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያን ምድር ከታዩት ከናዚና
ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን ይለያሉ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል።

Page 1 of 23
በበኩሌ ጥላቻው ከየት መጣ ብዬ አውጥቼ አውርጄ ማሰላሰል ከጀመርሁ ዓመታት
ቈጥሬአለሁ። ዕድል ቀንቶኝ ከብዙ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጋር ኑሬአለሁ፤ አድጌአለሁም።
ስለዚህ ፍንጭ ይሰጠኝ ይሆናል ስል ወደልጅነት ሕይወቴ ወደኋላ ተመልሼ በዐይነ-መነጽሬ
ሳይና ሳሰላስል፡ ሁሌዬ ተመላልሰው እፊቴ የሚደቀኑብኝ ሁለት ገጠመኞች ናቸው። አንደኛው
በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከምትባል ከተማ በሠላሳ ኪሎሜትር ያህል ርቀት የሚገኝ መንዲዳ
የተባለ መንደር አለ። ባንድ የኢጣሊያን መሐንዲስ ለሕንፃ ሥራ ተቀጥረው ከሰሜን የመጡ
ሠራተኞች ባካባቢው ዘመናዊ ምግብ ቤት ስለሌለ፣ ሁሌዬ የሚበሉት ከተማሪዎቹ ጋር አብረው
ነበር። የቀረውን ምግብ ሁሉ በልተው፣ ጠላዉን ብቻ መተው ልማዳቸው ሁኖ ስለነበር፣
አስተናጋጁ ገርሞት አንድ ቀን ምክንያቱን ሲጠይቃቸው አላንዳች ማፈር “ዐማሮች ናችሁ
አሉን፤ ዐማራ ቂጥኝ አለውና እንዳይተላለፍባችሁ ምንም ዐይነት መጠጥ ቢሰጣችሁ
እንዳትጠጡ ተብለን ስለተመከርን ፈርተን ነው” ብለው በጨዋነት መልስ ሰጡ። ሌላው
በአሥመራ ከተማ በአንዳንድ አስተማሪዎች አነሣሽነት፣ ተማሪዎቹ እነዚህን ዐማሮች
አታናግሯቸው ተብለው ስለተመከሩ፣ ከደቡብ የመጣነው በመጀመርያው ዓመት ምንም
ብንጥር ጓደኛ ማፍራት ከባድ ሆነብን። እምብዛም ባይሆን ጥቂት ከምንቀርባቸው ጋር ችግሩ
ምን እንደሆነ ለማወቅ ተሰባሰብን። መልሱ እውነትም ‘ዐማሮች’ ስለሆነን እንደነበር ለማወቅ
ብዙም አልፈጀንም። ከሁሉም የከፋብን ግን ዐማሮች አይደለንም ስንል፣ ቀጥሎ የመጣው
ልውውጥ ነበር። “ዐማሮች ካልሆናችሁ፣ ታዲያ ጋላ ናችሁ እንዴ!” ተባልን። ለዚህም በአሉታ
ስንመልስ፣ “ታዲያ ከጋላ በታች ሰው አለ እንዴ!” ሲሉን ክው አልን። እንግዴህ እነዚህ
የልባቸውን የሚናገሩ ላቅመ አዳም እንኳን ያልደረሱ ልጆች ናቸው፤ በጭንቅላታቸው ውስጥ
የሚያንሸራሽሩት አሳቦች ግን የአካባቢውን ስሜት የሚያንፀባርቁ ሊሆኑ አይችሉም ብዬ
መከራከሩ የሚያዋጣ ስለማይመስለኝ አልፈዋለሁ። ሁኖም የገጠመኙ ወቅት የወያኔ መሪዎች
ልክ ወደጫካ ያመሩበት ጊዜ ስለነበር፣ የዛሬውን ሥራቸውን እያየሁ የለም እነሱ በዚህ ዐይነት
አስተሳሰብ የተበረዙ ሰዎች አልነበሩም ብዬ ማሰቡ ያዳግተኛል። በአፍሪቃ ቅኝ ገዢዎችና
በፋሽስቶች እጅ ባካባቢዎቻቸው ይካሄድ የነበረው ኀይለኛ ስብከት፣ በዐማራ ላይ ጥላቻ፣
በተቀረው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ንቀት እንዳሳደረባቸው አይጠረጠርም
ብል በሐሰት የምወነጀል መስሎ አይታየኝም።
በሁለተኛ ደረጃ መታወቅ ያለበት ወያኔዎች የቀዝቃዛ ጦርነት ፍጻሜው ውጤት መሆናቸው
ነው። በዚህ ጦርነት መጨረሻ፣ በሕይወቱ ወቅት እንደመዥገርት የሕዝባቸውን ደም
እየመጠጡ የደነደሱ መንግሥታት እምብዛም ሳይቈዩ ወዲያው ፈረጡ:: የሁለተኛው ዓለም
መሪዎች ተራ በተራ ከሥልጣናቸው ሲወድቁ፣ ያልታደሉት ታረዱ፤ በለስ የቀናቸው ደግሞ
ለፍርድ ቀርበው ሰለባቸው ከነበሩት ጋር ተፋጠጡ። በሦስተኛው ዓለም የሁለቱ ኀያላን
ባላንጣዎች መንግሥታት፣ ማለትም የአሜሪቃና የሶቭየት ኅብረት፣ ቱኪዎቻቸው የነበሩት
ገዚዎች ግን፣ እንደሁለተኛው ዓለሙ መሪዎች በየአመዳቸው አልቀሩም። እንደኢትዮጵያው
መንግሥቱ ኀይለማርያም፣ የሱማሌው ሲያድ ባሬና፣ የድሮዋ ዛይር የዛሬዋ ኮንጎ ሞቡቶ ሴሴኮ
የመሳሰሉት፣ ያን ሁሉ የድሎታቸውና ያምባገነንታቸው ወቅት ድንፋታና ጉራ ረስተው ይሰብኩ
ለነበሩት ለናት አገር ፍቅር እንደመቆም፣ ሁላቸውም ነፍሴ አውጭኝ እያሉ በደንገለላ ሳይሆን

Page 2 of 23
በሽምጥ ፈረጠጡ። በጦርነቱ ድልና የበላይነት ያገኘችው አሜሪቃም በኢትዮጵያ ውስጥ
መንግሥቱ ኀይለማርያምና ጀሌዎቹ በጣር ላይ መሆናቸውን ስታይ፣ ዕድሉ ሳያመልጣት በራሷ
ተላላኪዎች ልትተካቸው እንደተሟሟተች፣ ከደርግ መንግሥት ፍጻሜ ዋዜማ በተደረገው
በአስችኳይ ስብሰባ ላይ ጥርት ብሎ ይታያል። በስብሰባው፣ አሜሪቃ ሥልጣን ቋማጩቹን
ገለልተኛ አገላጋይ መስላ ብታደራደራቸውም፣ ኳሱንም ሜዳውንም ሙሉ በሙሉ በወያኔ እጅ
እንደተወች ለመረዳት አብዛኛውን ተመልካች አያዳግትም ነበር ቢባል ሐቅ ይመስለኛል።
ባሜሪቃና በዐረቦች ትብብር፣ የኅበረተሰባዊነትና የመደብ ጦርነት አንጋቢው ደርግ በመስኮት
ሲሸመጥጥ፣ የጐጥና የጐሣ አንጋቾቹ ወያኔዎች በበር አድርገው ብቅ አሉ። በአንድ አስተዋይ
ጓደኛዬ አባባል፣ ጅሎቹ የሩሲያን አምባገነን ቡችሎች፣ ባሜሪቃ አፋኝ አደንዝዝ ማጅራት
መቺዎች ተበሉ።

በጫካ ኑሮ ዘመናቸው ወያኔዎች የተራማጅነት ጨንበል እንዳጠለቀ ወረተኛ ሁሉ፣


በኅብረተሰብአዊነት የተኰተኰቱ፣ የቻይናው ማኦ ቲሰቱንግ ታማኝ ደቀመዛሙርት፣
የአልባኒያው ኤንቨር ሆሻ አድናቂዎችና አጨብጫቢዎች ሲሆኑ፣ አሜሪቃ ግን ለነሱ የበዝባዦች
ቊንጮና ደመኛቸው ነበረች። ሁኖም በደማስቆ መንገድ ክርስቲያኖችን ድምጥማቸውን
ሊያጠፋ ሲጓዝ እንደነበረው ሐዋርያዊው ጳውሎስ፣ እነሱም ባንዴ ከአሜሪቃን ጥልቅ
ጥላቻ ወደጥብቅ ፍቅር ተለወጡ። ሥልጣን ላይ እንደወጡ የተገበሩትም ልክ የአሜሪቃ
መንግሥት ዋና ጸሓፊ የነበረው ክሲንጀር ጥቂት ቀደም ሲል ስለኢትዮጵያ አረቀቀ የተባለውን
ነው ማለት ይቻላል። በቀዝቃዛ ጦርነትና በዐረብ-እስራኤል ግጭት ሰበብ ከ፲፱፻፷ዎቹ መጨረሻ
ላይ ጀምሮ፣ አሜሪቃ ስለኢትዮጵያ የነበራት መምርያ ከድሮው ከቅኝ ገዢዎቹ ከአውሮጳውያን
መርህ ብዙም የማይለይና የማይራራቅ ነበር ማለት ይቻላል። የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች ኢትዮጵያ
ካልተበታተነች የአፍሪቃን ክፍለ አገር በዘለቄታ ከሥልጣናቸው ሥር ለመያዝ አስተማማኝ
ዋስትና አይኖረንም ይሉ እንደነበር ሁሉ፣ አሜሪቃም በቀይ ባሕር አካባቢ ያላትን ጥቅሟን
እስከሚቻል ጊዜ ድረስ ለማስከበር፣ ኢትዮጵያ እንደ ዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ
ካልጠፋች በስተቀር አይሳካም ወደሚል አቋም የደረሰች ይመስላል። ቅኝ ገዢዋ ኢጣልያ
ኢትዮጵያን ለመቈጣጠር “የዐማራን አከርካሪ በማያዳግም ሁናቴ መስበር አለብን” ትል
የነበረውን አባባል፣ የወያኔም ባለሥልጣኖች በየጊዜው አስተጋብተውታል[1]። ስለዚህም
የወያኔና የአውሮጳውያን ቅኝ ገዢዎች ሕልም አንድ ነው ማለት ይቻላል። እንግዴህ አሜሪቃ
የ“ትግራይን ረፓብሊክ” መፍጠር ዋና ግቡ ያደረገውን ወያኔን ለሥውር ዓላማዋ ብትመርጥ
ምንም የሚገርም አይመስለኝም። አሜሪቃም እንደአውሮጳውያኖች ቅኝ ገዢዎች ዐማራ ቢጠፋ
ደንታቢስ ብትሆን ምን ይገርማል።

እንደተለመደው የወያኔ መንግሥት ሥራ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጽሑፎቼ እንዳነሣሁ፣ በጥላቻና


በድንቁርና ላይ የተመሠረተ ሁኖ ነው እንጂ እነሱና እነሱን የመሳሰሉ የጐጥና የጐሣ ምሁራንና
ልሂቃን የሚነበንቡት ዐማራ በሕይወት ኑሮም አያውቅም ማለት ይቻላል[2]። ዐማራ [በግእዝ
ቋንቋ አምሐራ] ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስሙ የሚነሣው፣ በተለያየ ስም
“ድግናጃን፣” “ደጋዛን”ና “ግዳዣን” በመባል በሚታወቀው በአክሱም ንጉሥ የሐዋርያዊነት

Page 3 of 23
ሥራ በተያያዘ ጉዳይ ነው። ንጉሡ ከመናገሻ ከተማው ወደመቶ ዐምሳ ሰባኪዎችን “ደብተራ”
ብሎ ከሠየማቸው በኋላ፣ ሕዝቡን እንዲያከረስትኑ ወደ “ዐማራ” ምድር እንደላካቸው ሰነዱ
ይገልጣል። እንግዴህ በዚህ ሰነድ መሠረት “ዐማራ” የሚያመለክተው፣ የተወሰነ የመሬት ክልል
መሆኑ አይካድም። የተለያዩና በየጊዜው የመጡት የውጭ አገርና ያገር ቤት ጸሓፊዎች አላንዳች
ማዛባት እንደሚናገሩ፣ ክልሉ በምዕራብ በኩል በአባይና እሱን በሚመግበው የበሽሎ ወንዝ፣
በሰሜን በአንጎትና ላስታ፣ በደቡብ በወንጭት ወንዝ፣ በምሥራቅ ደግሞ ወደደንከል በረሃ
በሚደርሰው ሰፋፊ ገደላገደል የተከበበውን ምድር ይዋሰናል። ይኸ ዝርዝር እንደማስረጃ
ካገለገለን እንግዴህ፣ ዛሬ የወያኔ መንግሥት ዐማራ ብሎ የሚጠራቸውን እንደነጐጃም፣
በጌምድር፣ ሸዋ እንዲሁም የወሎን ከፊሉን አያካትትም።

የዚህ ክልል ነዋሪዎች አፈታሪክ የሚነግረን፣ “ዐማሮች” ምንጫቸው በቀጥታ ከአክሱም ሲሆን፣
“ዐማራ” የሚለው ቃል ትርጒሙ “ነፃ ሕዝብ[3]” ማለት እንደሆነ ነው። ሁኖም ዐማራ
በሰፊውና በገነነ መልኩ በመቈራኘት የሚታየው ከገዢው መደብ ጋር በመያያዙ ይመስለኛል።
የአክሱማውያን መንግሥት ከብዙ የጨለማና የድብልቅልቅ ዘመን በኋላ የተተካው፣ በታሪክ
ዛጐ በመባል በሚታወቀው ሥርወመንግሥት ሲሆን፣ ከሱም ቀጥሎ የመጣው “ሰለሞናዊ’”
እያልን የምንጠራው ነው። የዛጐ መንግሥት በአገዎች እንደተቋቋመ ሁሉ፣ በታሪክ መሠረት
የሰለሞኖች ሥርወ መንግሥት ቈርቋሪ ደግሞ ግእዙ “ንጉሠ አምሐራ[4]” በሚለው በአፄ
ይኩኖአምላክ እንደሆነ ይታወቃል። እዚህ በጣም መጠንቀቅ የሚገባን ነገር አለ። “ንጉሠ
አምሐራ” የሚል ስያሜ ይኑራቸው እንጂ፣ ጐንደር የነገሥታቱ ቋሚ መናገሻ ከተማ ሁና
እስከተቈረቈረችበት ማለትም እንደአውሮጳ አቈጣጠር [አ.አ.] እስከ ፲፮፻፴፪ ዓ. ም. ጊዜ ድረስ፣
ምናልባትም ከመጀመርያው “ንጉሠ አምሐራ” ውጭ፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ሌላ ንጉሥ
ነበር ማለት ያዳግታል። ግዛታቸው ሰፊ፣ ተራራማና ገደላገደል የሞላበት ስለነበር፣ ለቊጥጥር
እንዲያመቻቸው ሲሉ፣ ነገሥታቱ የሚኖሩት በየጊዜው ሰፈር እየቀያየሩ “በዟሪ” ወይንም
“በተሽከርካሪ ከተማ፡” ነበር። ሥልጣናቸውን በየጊዜው በመፈታተን እከፍተኛ አደጋ ላይ
የሚጥሉት ሁናቴዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠሩት በአገራቸው ደቡብና ምሥራቅ ባሉት
የእስላሞች ባላባቶች በኩል ስለነበር፣ ይኸንን በመገንዘብ የዟሪ ከተማቸው ዋና ዋናዎቹ ግዛቶች
በደቡብ እንደነይፋትና ሸዋ፣ ደዋሮና ፈጠጋር የመሳሰሉት አገሮች ነበሩ። ከዘመነ-መሳፍንት
በኋላም ቢሆን፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ንጉሥ እንደሌለ ስለምናውቅ ወደዝርዝሩ መሄድ
አስፈላጊ ሁኖ አይታየኝም።

ዐማራ የተባለው ክልል የ”ዐማራ” የነገሥታት መቀመጫ ሁኖ እንደማያውቅ ግልጽ ከሆነ፣


አገሩን የሚገዙት ነገሥታቱስ ከዐማራ ቤተሰብ ወይንም ክልል የተወለዱ ነበሩ ወይ ብሎ
መጠየቁ ተገቢ መስሎ ይታየኛል። አፄ ይኩኖ አምላክ “ንጉሠ አምሐራ” ቢባሉም፣ በመከታተል
አልጋቸውን የወረሱት ነገሥታት ግን፣ ምናልባትም ከመጀመርያዎቹ ጥቂቶቹ በስተቀር፣
የአብዛኞቹን የቅርብ ወላጆቻቸውን [ማለትም አባትና እናት] ብንመለከት፣ ሙሉ በሙሉም
ሆኑ፣ በከፊል ከዐማራ ዘር ወይንም ምድር መሆናቸው እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው ማለት

Page 4 of 23
ይቻላል። ለማንኛዉም እስኪ ወደጥልቅ ሳንገባ ለማስረጃ ያህል የሚከተሉትን እንያቸው።
በ፲፮ኛ ዘመን የነገሡት ነገሥታት፣ ካፄ ልብነድንግል ባለቤት ከጐጃሜዋ[5] ከእቴጌ
ሰብለወንጌል በስተቀር፣ የሁሉም ሚስቶቻቸው የትግራይ ወይንም የሐዲያ ተወላጆች ነበሩ
ማለት ይቻላል። የቄንጠኛዋ የጐንደር ከተማ መንግሥት ነገሥታት፣ የአፄ ሱስንዮስ ዝርያ
ናቸው። እርሳቸው ደግሞ በእናታቸው ከቤተእስራኤል ሲሆኑ፣ ወልድ ሠዓላ ይባሉ የነበሩት
ሚስታቸው እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ በበኩላቸው ከኦሮሞ ብሔረሰብ መሆናቸው ይነገራል።
እናታቸውም እስላም ነበሩ ይባላል። ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር፣ ጐንደርን ከቈረቈረው
ከልጇ ፋሲለደስ ጀምሮ እስከ ዘመነ-መሳፍንት ድረስ በኢትዮጵያ ዙፋን ይቀመጡ የነበሩት
የኦሮሞ፣ የቤተእስራኤል ደም ካላቸው ብሔረሰብሶች የተወላለዱ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ
ማለት ነው።

የዘመነመሳፍንቱ ነገሥታት በደምገንቧቸው የነበረው ደም በግልጥ የቋራና የኦሮሞ ድብልቅ


ነው። የገዛራሳቸውን “ርእስ መስፍን ዘኢትዮጲያ[6]” በሚል የማዕርግ ስም ሠይመው፣
ነገሥታቱን በዘፈቀደ እንደጉልቻ እየቀያየሯቸው በበላይነት የሚመሩት ፈላጭቈራጮቹ
መሪዎች ደግሞ ከመላ ጐደል የየጁ ኦሮሞች[7] ነበሩ። ዘመኑም የሚታወቀው
በሥርወመንግሥታቸው የ“ወረሼኮች[8]” በመባል ነው። ዘመነ መሳፍንት ማለት እንግዴህ
የኦሮሞ ዝርያ ናቸው የተባሉት የየጁ መኳንንት ላንድ መቶ ዓመት ያህል የጐንደርን መንግሥት
ሙሉ በሙሉ የተቈጣጠሩበት የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን ነው ማለቱ እውነትትን ያንፀባርቃል
ብዬ አምናለሁ።

ከዘመነመሳፍንት ባሻገር፣ ወደዛሬዋ ወደዘመናዊት ኢትዮጵያ ብንመጣ ሁናቴው ብዙም


አይቀየርም። ሦስቱ አጼዎች (ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ[9]ና ምኒልክ) ከገዛ ራሳቸውም ሆኑ
ከሚስቶቻቸው መካከል አንድም ጭንጩ ዐማራ በርግጥ የለም ማለት ይቻላል። አፄ
ቴዎድሮስ[10] ከቋራ፣ አፄ ዮሐንስ ከትግራይ፣ አፄ ምኒልክ ከተለያየ ብሔረሰብ ናቸው። ልጅ
ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ[11] ደግሞ ያማራ ደም አለባቸው ቢባልና ቢለካ በርግጥ ካሥር
የአንድ ግማሽ እጅ እንኳን ላይሞላ ይችላል ብል ሐሰት አይደለም።
ከነገሥታቱ ወረድ ብለን በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙትን ባለሥልጣናት ብናይ፣ ደረጃው ሁሉንም
አካባቢና ብሔረሰብ ያካተተ ሁኖ እናገኘዋለን። ሁኖም በገዢዎች ትውልድ አካባቢ
ለሚመራመር ግለሰብ ታላቁ ችግር፣ ታሪክ ጸሓፊው በግልጥ ካልተናገረ በስተቀር በስም ብቻ
ተመሥርቶ ባለሥልጣኑ ከየትኛው ብሔረሰብ ወይንም አካባቢ እንደመጣ መንገር በጣም
ያዳግታል። ምክንያቱም በኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ውስጥ አንድ ግልጥ ሁኖ የሚታይ ጉዳይ
ቢኖር፣ ሥልጣንና ሹመት የግለ-ሰቡ የአገልግሎት ብቃትና ትጋት ፍሬ ውጤት እንጂ
በትውልዱ ዘርና አካባቢ የተገደበ አይደለም ማለት ይቻላል። ሿሚው በመጀመርያ ደረጃ
እንደመስፈርት የሚጠቀማቸው የተሿሚውን ችሎታና ታማኝነት እንጂ ከየትኛው ቤተሰብና
ብሔረሰብ ወይንም ቀዬ መምጣቱን አይደለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ አንድ በጥብቅ መታወቅ
ያለበት ነገር ቢኖር፣ ብዙ ጊዜ በተሳሳተ የአውሮጳውያን ታሪክ በመመሥረት ስለኢትዮጵያ

Page 5 of 23
የጉልተኛ ባላባት[12] ሥርዐት የሚናገሩ በርካታ ጸሓፊዎች ቢኖሩም፣ ሐቁ ግን እውነትን
ለማዛባትና ለማወናበድ ካልሆነ በስተቀር ሥርዐቱ ባገራችን በግልጥ የታየበት ጊዜ ከቶ የለም።
መደብ፣ ወገንና አካባቢ ጠቃሚነታቸው በሁለተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል። ግን
እንደችሎታና ታማኝነት ወሳኝ መስፈርቶች አይደሉም። ስለዚህም ነው እንግዴህ ከላይ
እንደተባለው ስለባለሥልጣኖቹ ማንነትና አካባቢ ብዙም የማናውቀው። ሁኖም አንዳንዴ
ካንድ ጉዳይ ጋር በማማያያዝ፣ የጥቂቶች ማንነታቸው ሲጠቀስ ይታያል። እስኪ ከነዚህ መካከል
ለወጉ ያህል ጥቂቶቹን እንመልከት። በአፄ ሱስንዮስ ዘመን ከሁሉም ታላቅ ሹመት ሁኖ
የሚገመተውን የጐጃምን ግዛት፣ “ጐጃም ነጋሽ” የሚለውን ያገሩን ገዢ ማዕርግ ተከናንቦ ለብዙ
ዓመታት ያስተዳደረው የጉራጌው ተወላጅ “ጐጃም ነጋሽ ክፍሎ” ነበር። ያፄ ሠርፀድንግልን
ሁለት ልጆች አግብቶ፣ መላ ኢትዮጵያን በበላይነት ያስተዳድር የነበረው በጊዜው የመንግሥት
ፈላጭ-ቈራጩ መኰንን፣ የወለጋው ተወላጅ ራስ ዘሥላሴ[13] ነበር። በ “ዳሞት
ጸሓፊላምነት” ማዕርግ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፣ ወሰንና ድንበር ለማስጠበቅ ሲል ብዙ
ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት፣ ንጉሠነገሥቱን እንደአ.አ. ከ፲፮፻፲፯ እስከ ፲፮፻፳፯ ዓ.ም.
በታማኝነት አገልግሎ፣ በመጨረሻም የዳሞት ግዛቱን ከኦሮሞ ወረራ ሊከላከል ሲል በጦር ሜዳ
ላይ ሕይወቱን የሠዋው ደጃዝማች ቡኮ፣ ከመጀመርያዎቹ የኦሮሞች ታላላቅ ገዢዎች አንዱ
ነበር። እንዲሁም ንጉሠነገሥቱ “እንደልቤ ታማኝ” ይሉት የነበሩት፣ ዋናው አማካሪያቸውና፣
ከቁመታቸው ዕጥረት የተነሣ በኦሮሞኛ ቃል “ጢኖ” በመባል የሚታወቁት፣ ጸሓፈ ትእዛዙ
አዛዥ ተክለሥላሴ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ነበሩ። ጽሑፋቸው እንደሚያመለክተው፣ አዛዥ ጢኖ
ከኦሮሞ ቋንቋና ባህል በተጨማሪ፣ ዐማርኛና ግእዝ አሳምረው የሚያውቁ፣ ቅኔ የሚቀኙ፣
አንደበታቸው የተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ናቸው። እነዚህ ለእንደዚህ ዐይነት ወግና ማዕርግ
ሊበቁ፣ ዕውቀትንም ሊገበዩ የቻሉት፣ “ጋላ” በኢትዮጵያ ፈጸመ የተባለው ወረራ ግማሽ ዘመን
ማለት ዐምሳ ዓመት እንኳን በማይሞላው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ እስከኛ ጊዜ ድረስ ባሉት ዐራት
መቶ ዓመታት ውስጥማ ምን ያኽል መቀራረብና መዋሐድ እንደተካሄደ መገንዘብ የሚያዳግት
አይሆንም።
ከላይ ስለልጅ ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ አንሥቻለሁ። ከነዚህ ሁለቱ ጋር በተያያዘ፣ በቅርብ ጊዜ
ባነበብሁት ባንድ ሊቅ ሕዝቅኤል ኢብሳ በተባሉ ያንድ ዩኒቬርሲቲ መምህር ተደርሶ በበርካታ
የኢትዮጵያ ድረ-ገጾች በወጣ ጽሑፍ ላይ አንዳንድ ኂሶች መሰንዘሩ ተገቢ መስሎ ይታየኛል።
ሊቁ “ኢትዮጵያ፤ የኦሮሞ እውከት፤ ስለብሔራዊ ጥያቄና ወደሕዝበመንግሥት ሽግግር[14]”
በሚል ድርሰታቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር [ኢ.ሕ.ዴ.ግ] በመባል
የሚታወቀው የወያኔ መንግሥት በዐዋጅ ኦሮሞ ብሎ በሠየመው ሕዝብ ላይ የጐሣው
አቀንቃኞች ደርሶበታል የሚሉትን ግፍና ሰቈቃ ይተርካሉ። ታሪክን በገለልተኛነት
ለሚመራመርና የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ ለሚያውቅ ምሁር፣ የሊቁ ንግግር የተለመደውን
ደጋግሞ ከመወሸከት ውጭ ምንም አዲስ ነገር ስለማያፈነጭ ጊዜ ላለመፍጀትና የጽሑፌን
አቅጣጫ ላለመለወጥ ስል አልፈዋአለሁ። ሁኖም ላነሣ የፈለግኋቸው ሁለት አውራ ነገሮች
አሉ።

Page 6 of 23
አንደኛ፣ እንዴት ሁለቱ የሴማውያን ዘሮች ማለትም ትግሬዎችና ዐማሮች፣ ኦሮሞችን
አገልለውና ካስፈለገም የሥልጣን ፍርፋሪ ብቻ በመወርወር ያስተዳደሩን ሥልጣን የግላቸው
ሀብት እንዳደረጉ፣ ምሁሩ አበክረው ይናገራሉ። እንዲህም ሲሉ፣ ሊቁ በጽሑፋቸው
የሚጠቅሱትን የእንደነጆን ማርካኪስ [John Markakis[15]] ዐይነቶቹን የግራዘመም
ጸሓፊዎችን አሳብ ከማንሸራሸር በስተቀር፣ ከማንም ታሪክ ጸሓፊ የሚጠበቁትን አመዛዛኝ
ልቡናና የማያዳላ አእምሮ በመጠቀም የኢትዮጵያን ታሪክ ያገናዘቡት አይመስሉም።
በመጀመርያ ደረጃ ከላይ ያየነው በዘመነ መሳፍንት አገሩን ይገዛ የነበረው የወረሼኮቹ ሥርወ
መንግሥትም ሆነ፣ ነጋሾቹ መሳፍንት እንደፍላጎታቸው የሚለዋዉጧቸው ነገሥታት በስም
ሰለሞናውያን ይሁኑ እንጂ፣ ከመላ ጐደል የኦሮሞ ዝርያ መሆናቸውን አይተናል። ስለዚህም
በኢትዮጵያ እየተፈራረቁ ከፍተኛ ሥልጣን ይዘው የነበሩት ትግሬዎችና ዐማሮች እንጂ ኦሮሞች
ለዚህ አልበቁም ማለት በጠራራ ቀን ፀሐይ የለችም ብሎ እንደመሟገት የሚቈጠር መስሎ
ይታየኛል።

በሁለተኛ ደረጃ የገረመኝ ነገር ቢኖር፣ ምሁሩ በምዕራባውያን ኀይሎች አነሣሽነትና በሥልጣን
ሽኩቻ፣ ባንድ በኩል በልጅ ኢያሱና በአባታቸው ንጉሥ ሚካኤል፣ በሌላው ደግሞ በልጅ
ተፈሪና (ኋላ አፄ ኀይለሥላሴ) በደጋፊዎቻቸው መካከል፣ እንደኢትዮጵያ አቈጣጠር [ኢ.አ.]
በመስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም. የተካሄደውን የሰገሌን ጦርነት በሚያስደንቅ ሁናቴ
በመተርጐም፣ በወሎ ኦሮሞችና በሸዋ ዐማሮች እንደሆነ አድርጎ ማቅረባቸው ነው። በሁለቱም
በኩል የሚዋጉትም ሆነ፣ ጦሩን በበላይነት የሚመሩት፣ አብዛኞቹ ኦሮሞች ወይንም የኦሮሞ ደም
ያላቸው ሲሆኑ፣ ምሁሩ እንዴት አድርገው እንደዚህ ለመደምደም እንደበቁ አይናገሩም።
ምናልባት ኦሮሞ ሲሉ፣ እንደነፃ አውጪ ነን ባዮቹ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የተወሰነ መስፈርት
ካላቸው ደግሞ ምሁሩ በጽሑፋቸው ውስጥ ይኸንን ግልጥ አያደርጉም። አባባላቸው ደግሞ
ኦሮሞች እርስበርሳቸው አይዋጉም የሚል ከሆነ፣ በጣም ሩቅም ሳይሄዱ የእረኝነትን ሥርዐት
ትተው፣ በኦሞ ወንዝ አካባቢ በመንግሥትነት ተቋቁመው የነበሩትን፣ የጅማ አባጅፋርን፣
የጉማንና የጐማን ከዚያም ባሻግር የለቃ-ነቀምትንና የለቃ-እናርያን ንጉሦች፣ እንዲሁም በወሎ
ውስጥ የየጁዎች ባላንጦች የነበሩትን የማመዶችን ሥርወ መንግሥት ማየት ይበቃል።
በአገዛዛቸው ጨካኝነት፣ በኦሮሞም ሆነ መሬታቸውን ከነጠቁ በኋላ “ባዕዳን” ብለው
በፈረጁባቸው ባገሩ ተወላጆች ላይ ያደርሱባቸው የነበረው ግፍና ሰቈቃ፣ የጐሣው ልሂቃን
’የአበሻ” ነገሥታት በሕዝባችን ላይ ፈጸሙበት ከሚሉት እጅግ ይከፋል እንጂ በምንም ረገድ
አያንስም ብዬ እገምታለሁ። ሊቅ ሕዝቅኤል በዚህ ድርሰትና በሌሎችም ጽሑፎቻቸው
ይልቁንም በጀርመን አገር ታትሞ በወጣው በEncyclopedia Aethiopiaca ኦሮሞ-ነክ
ዐምዶች [vol. 4 O-X] ላይ ከፖለቲከኞች እንጂ ካንድ ገለልተኛ የታሪክ ምሁር የማይጠበቁ
አያሌ የተዛቡ አስተያየቶች አስቀምጠዋል። እንደዚህ ዐይነቱ የታሪክ አተረጓጐም ቁልጭ አድርጎ
የሚያሳየው የኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክን የፖለቲካ ደንገጡር እንዳደረጓት ነው ብል ሐሰት
አይመስለኝም። በዚህ ረገድ ሊቅ ሕዝቅኤል ብቸኛ አይደሉም[16]፤ እንደጊዜው ፖለቲካ
የሚቀያየሩ የወረት-በላ ምሁራን የበዙበት ዘመን ስለሆነ፣ ነገሩ የሚገርም መስሎ አይታየኝም
በማለት አሳቤን ልቋጭና ወደዛሬው ጥያቄዬ ልመለስ።
Page 7 of 23
ዐማራን በተመለከተ በቂ ያልሁ ስለሚመስለኝ፣ ልቀጥልና ወደዐማርኛ ልሻገር። የዐማርኛ ቋንቋ
ምንጩና መነሻው ዐማራ ከተባለው ክልል እንደሆነ አይካድም። ልክ እንደዐማራ እሱም
በዘተለምዶ ተቈራኝቶ የሚገኘው ከገዢው መደብ ጋር ቢሆንም፣ ሐቁ ግን ቋንቋው በደምቡ
ያደገውና የዳበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው ያልተቈጠበና ሰፊ አስተዋፅኦ ነው ማለት
ይቻላል። ስሙ ከተወለደበት ምድር ጋር ተያይዞ ቢቀርም፣ እውነቱ ግን በየአካባቢው
የሚገኙትን የተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትንም ሆነ አገባብ በመከለስ፣ በማዳበልና በማቀያየጥ
አዋህዷቸውና አመሳስሏቸው ይገኛል። የቋንቋ ጥናት ምሁራን ሴማዊ ብለው ፈርጀውታል። በኔ
አመለካከት ይኸ ዐይነቱ አከፋፈል በርካታ ታሪካዊ ጥላሸት የለበሰ በመሆኑ እንደአስተያየት
እንጂ እንደዐምደ ሃይማኖት ሁኖ መወሰድ የለበትም። ያም ሁኖ ግን፣ ሐቁ ዐማርኛ
በኩሳውያንና በሌሎችም ባካባቢው ካሉት ቋንቋዎች ቃላትና አገባብ በሰፊው ከመደባለቁ
የተነሣ ሴማዊ ብሎ መጥራቱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የራሱን ስያሜ ሰጥቶ፣
“ኢትዮጵያዊ” ወይንም “አፍሪቃዊ” ማለቱ የሚቀል ይመስለኛል። በፊደልም ሆነ በአነባብ
ከማንኛውም ያለም ቋንቋ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙዎች ቋንቋዎች ንባባቸው በጽሑፍ
ተቀርጾ ካለው ፊደል ጋር በፍጹም አይጣጣምም። ለምሳሌ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሰበብ ባለም
እየተሰራጨ በመጣው የእንግሊዝኛ፣ አንድ ቊጥር ወይንም “One” ሲነበብ “ዋን” ብሎ እንጂ
እንደጽሑፉ “ዖንእ” አይደለም። እንዲሁም ከአውሮጳዉያን ቋንቋዎች መካከል ጽሑፉና አነባቡ
አገባቡን ተከትሎ ይሄዳል ከሚባሉት ቋንቋዎች መካከል ኢጣሊያንኛ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
አባባሉ እውነትነት ቢኖረውም፣ ሐቁ ግን እሱም ቢሆን መጠነኛ ሕገወጥነት ያጠቀዋል።
ለምሳሌ ያህል ኢጣሊያንኛ የዐማርኛ “ሸ” የሚል ፊደል ስለሌለው፣ የሚጻፈው ቢያንስ ሦስት
ፊደላትን በማቈራኘት ነው። “ሻ-ካሎ[17]” ለማለት “scia-callo” መጻፍ ይኖርበታል።
በዚህ መልክ ስናየው ያማርኛ ፊደል የተራቀቀና ዘመናዊነትን ያሟላ ነው ማለት ይቻላል።
ፊደሎቹ በዛ በማለታቸው፣ ለጥናት መጠነኛ ጊዜ ቢፈጁም፣ አንዴ ጠንቅቋቸው ላወቀ ግን
በቅልጥፈት፣ በቀላልነትና በይዘት ደረጃ ወደር የሚገኝለት ቋንቋ አይደለም ሊባል ይችላል።
በኮምፑቴር አገላለጽ “የሚነበበው እንደተጻፈው ነው[18]” የሚለው አባባል የሚገባው
ከማንኛዉም ቋንቋ ይልቅ ለዐማርኛ ነው ቢባል እውነትነት አለው::

ዐማርኛ ባገሪቷ ውስጥ ያሉትን የልዩ ልዩ ብሔረ-ሰቦችን ድምፅ ሊያስተናግድ ሲል፣ ጥንት
ከአባቱ ግእዝ በወረሳቸው ፊደላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ አዳዲስ ፊደል ሊፈጥርና ሊጨምር
በቅቷል። አብዛኛውም የቋንቋው ተናጋሪ የሚገኘው ከጥንት ትውልዱ ክልል ውጭ ነው።
የተለያዩ ማስረጃዎች እንደሚገልጹ ከሆነ፣ በሁሉም ዘንድ ባይሆን እንኳን በተወሰኑት በዛሬዎቹ
ሱማሌዎችም አካባቢ ተስፋፍቶ እንደነበር አል-ፋቂህ በመባል የሚታወቀው የግራኝ ታሪክ
ጸሓፊ እስላሙ ዐረብ በ“የአበሻ ወረራ” በሚል መጽሐፉ ከመዘገበው ፍንጭ እናገኛለን። አፄ
ልብነድንግልን በድንገት በሰፈሩበት ዐምባ ላይ ለመያዝ ዐቅዶ፣ ግራኝ ለወታደሮቹ በዐማርኛ
ብቻ እንዲናገሩ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጠ። ወታደሩም እንደታዘዘው አድርጎ፣ ሳይጠረጠር
የደኅንነቱን ጠባቂዎች ዐልፎ ንጉሥ ነገሥቱን ለመያዝ ምንም አልቀረውም ነበር። አፄውን
ሊያስመልጣቸው ያበቃው ምናልባት ግራኝ ራሱ ሳይታወቀው በራሱ [አደርኛ?] ቋንቋ መናገሩ
ይመስላል።
Page 8 of 23
ዐማርኛ ለተለያየ ብሔረሰብና አካባቢ የኢትዮጵያዊነቱ መግለጫ መሆኑ አይካድም። ከላይ
የጠቀስናቸው እንደነጐጃም ነጋሽ ክፍሎ፣ ጸሓፈላም ቡኮና ራስ ዘሥላሴ የዐማራ ተወላጆች
እንዳልሆኑ ይታወቃል። አጭር በመሆኔ “ጢኖ” የሚል የኦሮሞኛ ስም ተስጥቶኛል ባዩ ጸሓፌ
ትእዛዝ አዛዥ ተክለሥላሴም በጽሑፋቸው ስለቋንቋው ሲገልጡ፣ “ዐማርኛ ቋንቋችን” እያሉ
ኩራት በተሞላበት ስሜት ሲናገሩ ይታያሉ። በላስታና በሸዋ፣ በበጌምድርና በወሎ፣ እንዲህም
በጐጃም ግዛቶች አማርኛ የኩሳውያንን ቋንቋዎች ተክቶ ይገኛል። በአርጐባና ጋፋት በመሳሰሉት
አገሮች ደግሞ የሴማውያንን ቋንቋዎች ቦታ ወስዷል።

አማርኛ ያፋቸው መክፈቻ ቋንቋቸው ቢሆንም፣ እነዚህ እላይ የተጠቀሱ አገሮች እንደአ.አ.
በ፲፱፻፺ዎቹ ዓ.ም. ላይ፣ ዐማሮች ናችሁ የሚል ስያሜ በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት በግድ
በላያቸው ላይ እስከተለጠፈባቸው ጊዜ ድረስ፣ “ዐማራ” በመባል አይታወቁም። ራሳቸውን
ይጠሩ የነበሩት በሚኖሩበት አገርና ቦታ ስም ጐንደሬ፣ ጐጃሜ፣ መንዜ በመባል እንጂ በፈጠራ
በተሰጣቸው ዐማራ በሚል ብሔረሰብነታቸው አልነበረም። ታሪክም ራሱ የሚያመለክተው
ይኸንኑ ሐቅ ነው። ከ፲፬ኛ እስከ፲፰ኛ አዝማን ድረስ በተከትታይ ድረስ የተጻፉት የነገሥታቱ
የታሪክ ሰነዶች ዐማራ የሚለውን ቃል ከቦታ እንጂ ከብሔረሰብ ጋር አያቈራኙም። እንዲሁም
እስከ፲፱ኛ ዘመን ድረስ በተጻፉት የክርስቲያኖቹም ሆኑ የእስላሞቹ ዜና መዋዕል ውስጥ “ዐማራ”
የሚለው ቃል የሚያመለክተው፣ በአሁን ጊዜ በወሎ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስም እንጂ
ብሔረሰብን አይደለም[19]።
ጽሑፌ የሚያስረዳው አንድ መሠረታዊ ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያውያን ከገዢው መደብ ጀምሮ
እስከ ተራው ሕዝብ በጋብቻና በአምቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን ነው። ያገሩ አስተዳደሩም ሆነ
ቋንቋው በተለምዶ ዐማራና ዐማርኛ ቢባልም ሁሉም ኅብረተሰብ በባለቤትነት ከፍተኛ
አስተዋፅኦ አድርጎባቸው ያስመዘገባቸውና የገነባቸው መሆኑን የታሪክ ሰነዶች ይመሰክራሉ።
ዐማራ የሚያመለክተው የዚህ አስደናቂ ግንብ አሳቡንና መሠረቱን የጣለው ሕዝብ የሚኖርበትን
በጣም የተወሰነ ክልል እንጂ አሁን በሥልጣን ያለው መንግሥት ለጥቅሙ ሲል አብዛኛውን
የኢትዮጵያን ሕዝብ በገፍ በማግለል ጭብጥ የማይሞሉና ማንንም የማይወክሉ መሰሎቹን ብቻ
አሰባስቦ የፈጠረውን ኅብረተሰብ አይደለም።

Page 9 of 23
[1] . የወያኔ መሪዎች ስለዐማራ ተናግረዋል ከሚባሉት ንግግሮች አንዳንዱ ለጠላትም ጆሮ
እንኳን ይቀፋል። እዚህ ጥቂቶቹን ከነተናጋሪያቸው ጋር ልጠቅስ እወዳለሁ።

“ ዐማራ ጠላት ነው” (የሕ.ወ.አ.ት. ማእከላዊ አቋም – ሰነድ)።

“ዐማራ መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሲለምን ማየት እፈልጋለሁ” (መለስ ዜናዊ)።

“ዐማራን እንደ ሲጋራ ረግጠን ጥለነዋል” (ስዬ አብርሃ)።

“ገድለን የቀበርነውን ዐማራ አታንሱብን” (ሳሞራ ይኑስ)።

“ዐማራውንና ኦርቶዶክሱን ሰብረን ጥለነዋል” (አቦይ ስብሃት)።

“ዐማራ ትምክሕተኛ ነው” (ገብረኪዳን ደስታ)።

[2] . መጥሌነትና ድንቁርና ብዙውን ጊዜ ተያይዘው ናቸው የሚሄዱት። ኢጣሊያን አገር ተማሪ
ሳለሁ፣ አንድ ከደቡቡ [በሥልጣኔ ወደኋላ ከመቅረቱ የተነሣ “mezzo-giorno” ወይንም
“መንፈቀ-ዕለት” ይሉታል] በኩል የመጣ የደስደስ ከፊቱ ያለው ጓደኛችን ካገር ቤት
የተላኩልንን የውብ ቤቶች ሥዕል (ፎቶግራፍ) እያየን ሲንጯጯህ ሰምቶ መጣና፣ ሥዕሎቹን
ሲያይ ገርሞት፣ “እናንተ ጥቁርች፣ሥዕሎቹ ከየት ናቸው” ሲል ጠየቀን። “ካገራችን” ስንለው፣
ደጋግሞ ያየው የታርዛን ፊልም ትዝ ብሎት ነው መሰለኝ፣ “አፍሪቃ ውስጥ ሁሉም እዛፍ ላይ
የሚኖር መስሎኝ! ታዲያ ቤትም አለ እንዴ” ሲለን ከኛ አንዱ፣ “እውነትህን ነው ሁላችንም
የምንኖረው በዛፍ ላይ ነው። የኢጣሊያን አምባሳደር ደግሞ የሚኖረው ከሁሉም በረዘመው ዛፍ
ላይ ነው” ብሎ ባሽሙር ሲያሽማጥጥበት ነገሩ ያነውኑ ገባው።

[3] . ቃሉ መሻዘር “ዐም (ዕብራይስጥ)= ሕዝብ”፣ “ሐራ = ነፃ”

[4] . ትርጒሙ “የዐማራ ንጉሥ” ማለት ነው።

[5] . የጐጃም ነዋሪ አማራ እንዳልነበረ ዝቅ ብሎ ይታያል።

[6] . ትርጉሙ “የኢትዮጵያ የበላይ ገዢ”።


Page 10 of 23
[7] . ትንሹ ራስ አሊ በመባል የሚታወቀው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተፈራረመው የንግድ
ውል የንጉሡንና የራሱን ማኅተም በሰነዱ ላይ ቢያኖርም፣ ራሱን “የኢትዮጵያ ንጉሥ” ብሎ ነው
የፈረመው።

[8] ቃሉ ሙሻዘር ሲሆን ከኦሮሞኛ “ወረ = ቤተሰብ”፣ ከዐረብኛ “ሼኽ/ሸይኽ = ሼኽ”፣


ከአማርኛ “ኦች = የብዙ ምልክት” የተወጣጣ ነው። ባንድጋ ሲጋጠም “የሼይኽ/ሼኽ
ቤት/ቤተሰብ” ሲሆን፣ ስሙ የሚያመለክተው ሥርወመንግሥታቸው የኦሮሞ፣ የአማራ
ወይንም የአርጐባና የእስላም ቅልቅል መሆኑን ነው።

[9] . የአፄ ዮሐንስ ባለቤት እቴጌ ምሥጢረ ሥላሴ የአፋር ተወላጅ ነበሩ። አፄ ዮሐንስን
ያገቡት ከከረስተኑ በኋላ ነው።

[10] . አፄ ቴዎድሮስ የቋራ ብሔረሰብ ሲሆኑ፣ ባለቤታቸው እቴጌ ተዋበች የታናሹ ራስ አሊ


ልጅ ናቸው።

[11] ልጅ ኢያሱ የወሎው ገዢ የንጉሥ ሚካኤልና የወይዜሮ ሸዋረጋ ምኒልክ ልጅ ናቸው። አፄ


ኀይለሥላሴ ባያታቸው ኦሮሞ ሲሆኑ እናታቸው ጉራጌ ናቸው ይባላል፣ ባለቤታቸው እቴጌ
መነን አስፋው የልጅ ኢያሱ የእኅት ልጅ ናቸው።

[12] . በ እንግሊዝኛ ፊውዳሊዝም [feudalism] በመባል የሚታወቀው ሥርዐት ነው።

[13] . ጸሓፊው የራስ ዘሥላሴ አባቱ ከወረብ እናቱ ከጐናን ምድር ሲሆኑ የተወለደው
በመጤነት በደርኀ ምድር ነው ይላል። አንዳንድ ጸሓፊዎች ቦታዎቹ በወለጋ ውስጥ ይገኛሉ
ቢሉም የተረጋገጠ ነገር የለም።

[14] . Ethiopia: An Oromo Dilemma. The National Question and


Democratic Transition”

[15] . ጆን ማርካኪስም ሆኑ ብዙዎች እሳቸውን የመሰሉ የውጭ አገር ጸሓፊዎች እንደሊቅ


ሕዝቅኤል በኢትዮጵያ ምድር አልተወለዱም ብቻ ሳይሆን ቋንቋውንም አይናገሩም፤ ላገሩና
ለባህሉ ባዳ ናቸው፤ ግንኙነታቸው ደግሞ ከተማሪዎቻቸውና እንደነሱ በአውሮጳውያን ተቋማት
ከተማሩት ኢትዮጵያውያን የማያልፍ ስለሆነ ሕዝቡንም በቅርብ አያውቁትም። ስለዚህም
ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ታሪክና ባህል ያላቸው ግንዛቤ የሚያንፀባርቀው በትርጒም ካነበቡትና
በአካባቢያቸው ካሉት የቀሰሙት መሆኑ መካድ ያለበት አይመስለኝም።

[16] . በጣም የሚገርመው አብዛኞቹ የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች እንደፖለቲካ ልሂቃኖቻቸው


በታሪክና ተረት መካከል ያለውን ልዩነት የተገነዘቡ አይመስሉም። በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ብዙ
ምናቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የቦረንና የበርይቱማ ዝምድና እንደሐቅ አድርጎ መውሰድ
Page 11 of 23
ሮማውያን ገናናዋን የሮም ከተማ የቈረቈሩት ሮሙሉስና ረሙስ በጤግሮስ ወንዝ ከተጣሉ በኋላ
ተኲላ እያጠባቻቸው አሳደገቻቸው የሚለውን ምናብ ሐቅ አድርጎ እንደመቀበል ነው። በሌላው
ደግሞ በኦሮሞ ላይ የተፈጸመውን ግፍና ሰቈቃ ሲወሽክቱ፣ ኦሮሞች በሌሎቹ ላይ የፈጸሙትን
አያነሡም። አፄ ምኒልክ የገባር ሥርዐት በሕዝባችን ላይ ጣሉብን እያሉ ንጉሠነገሥቱን በግፍ
ሲወቅሱ፣ “ሕዝባቸው” በየወረረበት ሰፋሪውን ያገሩን ተወላጅ በአረመኔ መልክ
እንደጨፈጨፈ፣ ለባርነት እንደዳረገ፣ የባላይነቱን በተቀበለው ደግሞ የሃበታ፣ ጠለታ፣
ሞጋሳ/ⶁአሳ፣ ገበሮ እያለ የተለያዩ የጭቆና ሥርዐቶች እንደጫነባቸው ሊናገሩ አይፈልጉም።

[17] . ‘Sciacallo = ቀበሮ”

[18] . የእንግሊዝኛው፣ “What you read is what you see.”

[19] . እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የምጨምር ነገር ቢኖር፣ ባሁኑ አጠራር ኦሮሞ፣ ድሮ
ደግሞ ጋላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ሁናቴም ልክ ይኸንኑ የዐማራን ይመስላል። ጥንት
ቦረን፣ ሜጫ፣ ቱለማ፣ ኢቱና ጉጂ በመሳሰሉት ስሞች ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩትን ብሔረ-ሰቦች
፣ ኦሮሞ በሚባል በጋራ መጠርያ ስም ሥር እንዲካተቱ አስገድዷቸዋል[19]። ጉዳዩ ራሱን
የቻለ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ስለሚፈልግ ቦታው ስላልሆነ፣ አሁን ልለፈው። ሁኖም አንድ መሰመር
የሚገባ የማይካድ ሐቅ አለ።
ኀይሌ ላሬቦ

COMMENTS

... ሙሉውን ጽሁፍ ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።


... post your comment below↓

14 comments on “ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ”


1. tamene says:
August 13, 2016 at 11:59 am

Page 12 of 23
thank you prof. Haile Larebo
Ethiopia owe you a lot sir !

[Reply]
Reply
2. Getu says:
August 13, 2016 at 12:28 pm

በተለያየ አጋጣሚዎችና ስፍራዎች፡ ሰላማዊ ሰልፈኛው፡ ፖለቲካዊ ተንታኙ፡ የዜና ሰዎች…ወዘተ፣ ወልቃዪት
አማራ ነው የሚል መግለጫዎችና መፈክሮች እየተሰሙና እየታዩ ነው። ይሄ ደግሞ፡ በወያኔ ወጥመድ ውስጥ
እንደመጠመድ ነው። ወያኔ ተቃውሞ ቢገጥመውም፡ ይሄን ዘረኛ አስተሳሰብ በማስረጹ በኩል የተሳካለት
ይመስለኛል።
ወልቃይት አማራ አይደለም፡ ጎንደር ነው – ጎንደር ኢትዮጵያዊ -አለቀ።

ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በዚህ አገላለጽ ይስማማሉ። ወያኔ ቢጠላና መጠነ ሰፊ የሆነ ተቃውሞ
ቢያጋጥመውም፡ እሱ ያመጣውን ዘረኛ ፖሊሲ እሚቀበሉ፡ ላሁኑ ተቃዋሚዎች፡ ለነገ የወያኔ ፖሊሲ
አራማጆች እንዳሉ ማወቁና ለተራዘመ ትግል መዘጋጀቱ ሳይሻል አይቀርም። ወያኔ ዘረኛ ህገ-መንግስቱን መቼ
ብቻውን ቀረጸውና፡ ከጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር ሆኖ ነው የቀረጸው።
[Reply]
Reply
3. አለም says:
August 13, 2016 at 11:29 pm
አቶ ጌቱ እሾህን በሾህ ሲባል ሰምተዋል?
[Reply]
Reply
4. Mori says:
August 14, 2016 at 2:05 am
Indante Yale dear Zealabaj Terb defar tenkolengna mahaim aiche alawqm
Orono tlacha asaytahal dedebnethn lemsale Hochimin Hangariawi. Sayhon
Vetnamawi new. Ambassador zaf indeneberk argeh yemtaweraw ke20ametat
befit indeqeld be awropa yafrica tamariwoch well neber neber. Lela kftafneth..
Muhur nen bayous Orinowoch , dro gala yemibalu,h/slase promo new y ball,
abugida sainsawi new Latin yereqeqe blehal setun thche sntun qzet. Lawra.
INE Microsoft Yanten abugida yemiteqemew gn Iyandandu hzb yesedebkbet
debtera abath yenegereh teret teret aqaztoh inde awaqi lemehon mokrehal
[Reply]
Reply
5. ይሄም ያልፋል says:
Page 13 of 23
August 14, 2016 at 3:46 am
ሀይሌ ላሬቦ እውቀት ያብዛልን አንተ በገለልተኝትነት የምትጽፈውን የነጠረ ታሪክ እናነባለን እናስቀምጣለን
ታሪክን በዘረኝነት ተነሳስተው አቅጣጫ የሚያስቱትን ደግሞ ሀይሌ ላሬቦን ይዘዝባቸው እንላለን። እንግዲህ
እነዚህ ደካሞች ቀደም ሲልም ስለ ፈሩህ ሰይፋቸውን መዘውብህ ነበር ብቻህን አልነበርክም ለሀገርህ
ባደረግሀው አስተዋጽኦ የወገን ጦር ከፊትህ ወድቕል በርታ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ኢትዬጵያ ብድሩን
ትከፍልሀልች። ለፕሮፌሰርነትማ ሳያፍሩ በፈረንጅ ብስኩት ነው የተማርኩት ኢትዮጵያ ያደረገችልኝ የለም
እያሉ በድፍረት የሚነግሩን አሉ አይደል። እውነትም ላጲስ አሉት። እንግዲህ ህወእት ከላይ እናንተ ክታች
የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲያራግቡት የዘረፈውን ሴይበላ የሞሶኮኒ እጣ ይደርሰዋል።
[Reply]
Reply
6. Zeleke says:
August 14, 2016 at 5:25 am
Thank you dear Prof Haile Larebo. I really appreciate your contributions.
[Reply]
Reply
7. Bakalu says:
August 14, 2016 at 12:24 pm
yes yes yes amara for feture write his storey. thinkes Hiyela Larebo
[Reply]
Reply
8. ኀይሌ ላሬቦ says:
August 15, 2016 at 12:02 am

ሰላም አቶ ሞሪ፣
ኢጣልያን ከሚመስል ስምዎ ተባዕት (ወንድ) ይሆናሉ ብዬ ስላመንሁ ነው አቶ ያልክዎት። ከተሳሳትሁ
በትሕትና ይቅርታ እጠይቃለሁ።
እኔ እንደደምቡ በጻፍሁት ጽሑፍ ላይ በማቈላመጥም ሆነ በማጥላላት፣ በማወደስም ሆነ በማንቋሸሽ፣
በማመስገንም ሆነ በመሰዳደብ ለሚጽፍልኝ እንደደምቡ መልስ አልሰጥም። እርስዎ በጻፉት ላይ ግን
የሚታረም ግድፈት ስላለና አንባቢያንም እንዲማሩና እንዲታነፁበት፣ አሳብ ለአሳብ በመለዋወጥ ትምህርት
ቀስመው ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ስል መልስ ካለመስጠት ልቈጠብ አልቻልሁም። ብዙ ሐተታ ሳላበዛ
ወደ አውራ ነገሮቹ እንድሄድ ይፍቀዱልኝ።
ባንደኛ ደረጃ የአልባንያን መሪ ኤንቨር ሆሻ ከቬትናሙ ሆቺሚኒ የማዘባረቁ ግድፈት እኔም ከርስዎ በፊት
አስቀድሜ በታተመው ጽሑፍ ላይ አስተውዬው፣ ረቂቁን ደጋግሜ ሳነብ አለማየቴ ገርሞኝ ሲያበቃ፣
ወዲያውኑ ጽሑፉ ለተላከላቸው ድረገጾች አስፈላጊዉን እርማት አድርጌ፣ በፊተኛው ምትክ አዲሱን
በድረገጻቸው እንዲለጥፉ ደጋግሜ ልኬ ነበር። ግን ካንድ ድረገጽ አዘጋጅ በስተቀር፣ ሌሎቹ እንደተጠበቀ
አላደረጉም። እኔ እንደማውቀው ከሆነ፣ የድረገጾች አዘጋጆች አብዛኞቹ የቀን ተቀን ኑሮ ትግል እንደሁላችንም
የሚሯሯጡና፣ ሌላ ሥራ ያላቸው ናቸውና ያልናቸውን ሁሉ ለማስተናገድ ሥራ ይበዛባቸዋል። የድረገጹን
ሥራቸው፣ ባገራችን ጉዳይ ላይ እኛ አሳብ ለአሳብ እንድንለዋወጥና እንድንማማር፣ እርስ በርስ
እንድንተዋወቅና እንድንቀራረብ፣ ላገራቸውና ለወገናቸው ሲሉ የግላቸውንና የቤተሰባቸውን ድሎትና
Page 14 of 23
ቅንጦት ትተው፣ ገንዘባቸውንና ጊዜአቸውን በመሠዋት በትርፍ ጊዜአቸው የሚያካሄዱት ጉዳይ መሆኑ
መረሳት የሌለለበት ይመስለኛል። እነዚህን ዐይነቱ ታታሪዎች ፍላጐታችንን ባያሟሉ እንኳን፣ እንደዚህ
የመሰለ ምቹ መድረክ በመፍጠራቸው ልናመሰግናቸው፣ ልናደንቃቸው ይገባል እንጂ በምንም መልክ
መወቀስ የለባቸውም ብዬ በጽኑ አምናለሁ። እውነት ነው ባንድ ጽሑፍ ውስጥ ምንም ዐይነት ግድፈት ባይኖር
ይመረጣል። ይኸ ግን ምኞት እንጂ ብዙውን ጊዜ ተግባራዊ አይደለም። ምክንያቱ ግልጥ ይመስለኛል።
ከእኛም በጽሑፍም ሆነ በንግግር አስተዋፅዖ ከሚናደርገው መካከል ብዙዎቻችን እንደድረገጽ አዘጋጆቹ፣
እንደዚህ ዐይነቱን ሥራዎች የምንሠራ በትርፍ ጊዜአችን ነው። አንባቢው የሚያየው ጽሑፉን እንጂ የጽሑፉ
አሳብ በጸሓፊዎቹ ጭንቅላት ከተፀነሰበት ወቅት ጀምሮ፣ በድረገጾቹ እስከታተመበት ጊዜ ድረስ የሚፈጀውን
ሥራ፣ የሚከፈለውን መሥዋዕት፣ የሚጠፋውን ገንዘብና ጊዜ አይደለም። ለማስታወስ ያህል የመጻፉ አሳብ
ሲመጣ አርእስት ይፈለጋል፣ ቤተ መጻሕፍት ተኬዶ መጻፍቶችን አንብቦና አመሳክሮ ማስታወሻዎች ይያዛሉ፣
ነጥቦች ይፈለጋሉ፤ በዘርፍ ዘርፍ ይደረግና ረቂቅ ይጻፋል፤ ረቂቁ ተደጋግሞ ሦስቴም ዐራቴም ይከለሳል፣
ይታረማልም፤ ከዚያ በኮምፑተር ይተየባል። ከዚያም የመጨረሻ እርማት ይደረግና ለድረ-ገጾቹ ይላካል። ይኸ
ሁሉ የሚሠራው ከቤተሰብና ከግል ምቾት በመገለል በብቸኝነት ነው። እንደሚያዩት በጣን አድካሚ ሥራ
ነው።
“ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው” እንደሚባል ልፋቱንና ድካሙን የማያውቅ ገር አንባቢ፣ ብዙውን ጊዜ
የጽሑፉን አንኳር መልእክት ትቶ በጥቃቅን ዋጋ በሌላቸው ነጥቦች ያተኩራል። አሁንም እርስዎ ያነሡት
ግድፈት መደረግ ባይገባም ቅሉ፣ ዋናው የጽሑፉ መልእክት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዐማራ ምን እንደሆነ
በየዘርፉ ከነማስረጃው ማሳየት ነው። ጽሑፌ ይኸንን ተግባር አማልቷል ብዬ አምናለሁ፤ እርስዎም አላሟላም
ብለው አንድ ነጥብ እንኳን አላነሡም። እንደመሰለኝ የከነከነዎት የግድፈቱ ጉዳይ ነው። ስለግድፈቱ እንግዴህ
እርስዎ ከመናገርዎ በፊት እኔው ራሴ እንደደረስኩበትና፣ እንድታረም እንደጠየቅሁ ከዚህ በላይ
አወያይቼዎትአለሁና አምነው እንደሚቀብሉት ተስፋ ላድርግ።
ሁለተኛው እርስዎ የሚያነሡት ነጥብ “የጋላ ጥላቻ” አለብህ በማለት ነው። ይኸ ትልቅ ክስ ነው፤ ሁኖም ግን
ቃላት ከመወርወርዎ ውጭ፣ ጥላቻዬ እምኑ ላይ እንደሆነ፣ ምንስ በማለቴ እንደሆነ አልነገሩኝም። ቢነግሩኝ
ኖሮ መልስ በሰጠሁ ወይንም ተገቢ መስሎ ከታየኝ በታረምሁና ይቅርታ በጠየቅሁ። አሁን ግን ያንን ዕድል
ስላልሰጡኝ፣ አንዱንም ለማድረግ አልችልም። ከንግግርዎ እንደምረዳ ከሆነ ግን፣ ለምን ባገራችን ካለው
የፖለቲካ ነፋስ ጋር አብረህ አትሄድም መሰለኝ። ይኸም ማለት፣ የጐሣ ፓለቲካ አዳባሪዎች ልሂቃንና ምሁራን
የሚሉትን ለምን ዝምብለህ አትቀበልም የሚሉኝ ይመስላል። የጋላ ጥላቻዬ መግለጫው ይኸ ነው ካሉኝ
በጣም ይገርመኛል። ይበልጥ ደግሞ የሚገርመኝ እርስዎ እንደዚህ እያሉ ያሉት፣ ምናልባት የአሳብ ነፃነት በነፃ
እንዲንሸራርሸር አይዞህ አይዞህ በሚባልበት በምሥራቁ ዓለም እየኖሩ ከሆነ ነው። ከኢትዮጵያ ቢሆንማ
ምንም አይገርመኝ፤ ምክንያቱም አሳብ የሚታፈን አገር ስለሆነ የአሳብ ነፃነትና ጠላትነት ያው ናቸው ብዬ
ስለማምን።
እንግዴህ የጋላ ጠላትነቴ ምልክት እርስዎ በሚደግፉት ሰዎች አስተሳሰብ አለማሰቤ ከሆነ፣ እንደዚያ ዐይነት
ነገር ለማድረግ ዝንባሌዬም አይደለም፤ የሠለጠንኩበት ሙያዬም አይፈቅድልኝም። ገና ልጅ ሳለሁ አንድ ነገር
ካልጣመኝ የማልቀበል በተፈጥሮዬ ሽፍታ ነበርሁኝ። ስለዚህም ከዚህ የአሳብ ሽፍትነት የተነሣ፣ ያልወጣልኝ
ስም አልነበረም። አሁን የምሥራቃውያን ፓስፖርትና ሶሻል ሰኩሪቲ ባንድ ስም እንድጸና ታድጎኝ ነው እንጂ፣
ስሞቼ ከመብዛታቸው የተነሣ እውነተኛ ስሜን እንኳን እስከመርሳት ደርሼ ነበር። የተፈጥሮ ዝንባሌዬ አልበቃ
ብሎ፣ ሙያዬ ተጨመረበትና የመመራመሬን ዝንባሌን አሰላው። ሕይወታቸው ባጭሩ የተቀጨው
ገብረሕይወት ባይከዳኝ የማስተዋል ጸጋ የታደላቸው ታልቅ ምሁር ናቸው። ቶሎ ባያርፉ ኖሮ፣ ላገራችን ብዙ
ዕውቀት ባበረከቱ ነበር። እኚህ አስተዋይ ሰው፣ ስለታሪክ ጸሓፊነት አስፈላጊ መስፈርቶች ሲናገሩ፣ ታሪክ
Page 15 of 23
መጻፍ በጣም አስቸጋሪ ሙያ ነው ብለው አበክረው ካስገነዘቡ በኋላ፣ መሟላት አለባቸው የሚሉትን ሦስት
የሚቀጥሉትን ነገሮች ያማጥናሉ። አንደኛ፣ ድርጊቱን ለማስተዋል አመዛዛኝ ልቡና፤ ሁለተኛ፣ ድርጊቱን
ለመፍረድ የማያዳላ አእምሮ፤ ሦስተኛ፣ያመዛዘኑትንና የፈረዱትን ለማስታወቅ የጠራ የቋንቋ አገባብ ናቸው
ይላሉ። የታሪክ ባለሙያ በመሆኔ፣ እኔም የምከተለው የሳቸውን ምክር ነው። ታሪክን እንደብዙዎቹ የአገራችን
ምሁራን ነን ባዮች መጠቀሚያና የፖለቲካ ደንገጡር አድርጌ አልመለከትም። እርስዎ የሚያደንቋቸውን
የኢትዮጵያን የታሪክ ምሁራንን የሚተቸው በጣም በሚያሳዝን ሁናቴ የገብረሕይወትን ምክር ለማሟላት
ባለመቻላቸው ነው። በጽሑፌ ውስጥ ስለጋላ ያነሣሁት ነገር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ስለጋላ ታሪክና
በኢትዮጵያ ውስጥ ስለደረሰባቸው መከራ የሚያውቁና የሚናገሩ የታሪክ ምሁራን ነን ባዮች፣ የኢትዮጵያ
ነገሥታትና ገዢዎች በጋላ ላይ አደረሱ የሚሉትን ሐተታ ሲዘረዝሩ፣ ጋላውም ይልቁንም ከእረኝነት ሕይወት
ወደግብርና እስከገባ ጊዜ ድረስ፣ ባካባቢው ሕዝብና ባገሪቷ የፈጸመውን ጭቈናና ውድመት መርሳት
የለባቸውም። የአፄ ምኒልክን የኢትዮጵያን የጥንት አንድነቷን መልሶ የማደስ ሥራ እንደቅኝ ግዛትነት ካዩ፣
የጋላውንም ወረራ በዚያው መልክ ማየት አለባቸው ነው። ለርስዎ ግን ይኸ ሐቅ ልዋጥልዎት ስላልተቻለ፣
የጋላ ጥላቻ እንዳለብኝ አድርገው ፈርጀውኛል። ለኔ ፍርደገምደልነት ቦታ የለውም። እርስዎ አመዛዛኝ
ልቡናና የማያዳላ አእምሮ ባይኖርዎት ነው እንጂ፣ በጽሑፌ ውስጥ ጋላ የሚሉት ሕዝብ ከተራ ገበሬና ወታደር
እስከባለሙሉ ሥልጣን የመንግሥት የበላይ ጠባቂነት ደረጃ፣ ባለቤት ሁኖ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ
አስተዋፅዖ ያስመዘገበ መሆኑን ተናግሬአለሁ። ግን ግድ የሰጠዎት፣ የሙያቸውን ተልእኮ ረስተው፣ የተዛባና
አወናባጅ የተረት ታሪክ ምሁራንን መውቀሴ ነው። እንደምረዳው ከሆነ እርስዎ የጋላ ጥላቻ አለህ ሲሉኝ፣
መልእክትዎ ለምን የጋላን ታሪክ ለማንም በማያዳላ መንገድ አመዛዝነህ ታያለህ ማለት ስለሆነ አልቀበለውም።

እርስዎ ተገንዝበው ከሆነ፣ ከዚህ በላይ አሁን በሥልጣን ያለው መንግሥት በዐዋጅ ያዘዘውን “ኦሮሞ”
የሚለውን ቃል ትቼ “ጋላ” የሚለውን ተጠቅሜአለሁ። አንደኛ “የኦሮሞ” ሳይሆን “የጋላ ጥላቻ” አለህ ብለው
ስለከሰሱኝ፣ እርስዎ ራስዎ የተጠቀሙትን ቃል ልጠቀም ብዬ ነው። ሁለተኛ፣ ከዚህ በላይ እንዳልኹዎት
ሌላው (መንግሥትም ይሁን ግለሰብ) ያደርገዋል ብዬ አላደርገውም። አንደኛ፣ ስም መቀየር ያለበት ተገቢው
ጥናት ተካሄዶ፣ ጥቅሙና ጉዳቱ ታይቶ፣ የስሙ ባለቤት ተመክሮ መሆን አለበት እንጂ፣ ራሳቸውን በማያውቁ፣
ተረትና እውነት በማይለዩ፣ በጥቂት ጥቅመኞች ግፊት መሆን የለበትም። አሁን በሥልጣን ያለው
መንግሥትም “ጋላ” የሚለውን ቃል፣ “ኦሮሞ” ወደሚለው ስያሜ የቀየረው፣ በዚያ መልክ ነው። የስም
አወጣጥ ታሪክ ቢያዩ ይረዳል በሚል አሳብ እስኪ አንዳንድ ነጥቦች ልዳስስና፣ በጥሙና እንደሚያነብቡት
ተስፋ አደርጋለሁ። ዋና መነሻዬ የስም መጥፎ የለም ነው። ጥሩና መጥፎ የሚያደርገው ተጠቃሚውና ሥራው
ነው ከሚል ልጀምር።

የስም አወጣጥ ታሪክ ካዩ፣ ለግለሰብም ሆነ ለእገርና ለተወሰነ ቡድን ወይንም ሕዝብ ሌላ ነው የሚያወጣው።
ወላጆች የልጆቻቸውን ስም ያወጣሉ። ያ ስም እንደሁናቴውና እንደኅብረተሰቡ ከግለሰቡ ጋር ተጣብቆ
ይቀራል፣ ካልሆነም በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀየርም ወይንም ሌሎች ስሞች ሊደራረቡበትም ይችላሉ።
በሠለጠነው በምዕራብ ዓለም፣ የግለሰቡ ስም አንዴ ከተመዘገበ፣ ሥርዐቱንና አገባቡን ተከትሎ ካልሆነ
(ለምሳሌ ፍርድ ቤት ሄዶ አመልክቶ) በስተቀር አይቀየርም። ዘመድ አዝማድና ጓደኞች የሚጠሩት
የቁልምጫ፣ የቅጽልና የብርቅዬ፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የክርስትና ስሞች፣ በተጨማሪ ሊሰጡ
ይችላሉ፤ ግለሰቡም በዚያ ስም ሊታወቅ ይችላል። በመንግሥት ደረጃ ግን ጸንቶ የሚቈየው ያው ሲወለድ
ያገኘው ስም ነው። በኢትዮጵያ በወላጅ የተሰጠ ስም እንደሁናቴውና እንደኅብረተሰቡ በየጊዜው ይቀየራል።

Page 16 of 23
ደብተሮች ብዙዉን ጊዜ በየሄዱበት ትምህርት ቤት ራሳቸውን የሚያስታውቁት በተለያየ ስም ነበር። ለምሳሌ
ያህል፣ በዋድላ የቅኔ ትምህርትቤት ስሙ ወልደብርሃን የነበረ፣ ወደደብረ ዐባይ መዝገበ ቅዳሴ ሊያጠና
ብሄድ፣ ስሜ ገብረክርስቶስ ይል ነበር። በተቀረ በወላጅ የተሰጠው ስም፣ በተለያየ በግለሰቡ የሕይወት
ደረጃም ሆነ፣ ባካበተው በሥራ ውጤት ምክንያት ሊቀየር ይችላል። ማለትም በቤተክህነት ከሆነ፣ ሲቀሰስ፣
ሲመነኰስ፣ ሲጳጳስ፣ በመንግሥት ደግሞ ሲሾም ወይንም ሲነግሥ፣ በኅብረተሰቡ እንደየባህሉና ቦታው፣
ሲገረዝ፣ ሲያገባ፣ ሲወልድና፣ ሸምግሎ ካባቢው በዕውቀቱና በፍርዱ ብስለትና አለማዳላት የክብር ቦታ
ሲሰጠው። ይኸ ሁሉ እንግዴህ በግለሰብ ደረጃ ነው።

ባገርና በብሔረሰብ አኳያ ግን እነዚህ ራሳቸውን ከሚጠሩበት ከግል መጠርያቸው ውጭ፣ ሌሎችም
ጐረቤቶቻቸው የሚሰጡት ስሞች አሉ። ለምሳሌ ጀርመኖችን የወሰድን እንደሆነ፣ የጐረበታቸው አገሮች
በየቋንቋቸው እንዴት እንደሚጠሯቸው እስኪ እንይ። በአኳኋንዎ የላቲኖችን ፊደላት አድናቂ ስለሚመስሉ፣
በዚያው ልጻፍልዎት፡ ጀርመኖች ራሳቸውን የሚጠሩት Deutschen ሲሆን፣ እንግሊዞች (ከሮማውያን
ወስደው) Germans፣ ኢጣሊያኖች tedeschi፣ ፈረንሳዮች allemands፣ ዳቾች duitsers፣ ዳንሾች
tyskerne፣ እስዊድኖች tyskarna, የፊን ምድር ሰዎች saksalaiset፣ ሁንጋሮች nemetek፣
ሩሲያኖች Hemubi ይሉዋቸዋል። ጥቂት የሚቀራረበው ስም ቢኖር፣ የደንሾቹና የእስዊድኖቹ ነው።
እንግዴህ እያንዳንዱ የየራሱን ሰም ያወጣው ካንድ ግንዛቤ ተነሥቶ ነው። እኛንም የቅርብ ጐረቤቶቻችን
ዐረቦች፣ ካንድ ለየት ካለ ግንዛቤ ተነሥተው “ሐበሻ” ይሉናል፣ ፈረንጆችም “Abyssinians” የሚሉን ከነሱ
ተቀብለው ነው፣ ልክ እኛ ከዐረቦች ተበድረን ከጽርዖች {ማለትም የዛሬው ግሪኮች] በስተቀር፣ ሌሎቹን
አውሮጳውያን በሙሉ ፈረንጅ [ከFrance/Frank] እንደምንል ማለት ነው። ኢትዮጵያን ለማመልከት
“ሐበሻ” ወይንም “አበሻ” የሚል ቃል በየትም የኢትዮጵያ ታሪክ የለም። ያለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ዐረቦች
“ሐበሻ” የምትለውን ቃል ከየት እንዳመጧት አናውቅም። ግን ቃሉ በኛም መኻል ተዛምቶ ክርስቲያን ለሆኑት
ለሰሜኖቹ ብቻ የተሰጠ አስመስለን፣ እነዚህን የጠላቸውና ያኰረፈባቸው ሁሉ ቁጭቱንና ብሶቱን ሊወጣ
ሲፈልግ፣ ቃሉን ስድብ አለባብሶ፣ “እናንተ አበሾች” ሲባል ይሰማል። እንዳልክሁዎት ስድብ አድርጎ
የሚገምተው ተናጋሪው እንጂ፣ ቃሉ ገለልተኛ ነው። መጥፎነቱና ጥሩነቱ የሚወሰነው ካጠቃቀሙ እንጂ
ከቃሉ አይደለም።

ከዚህ በላይ ስም በዐዋጅ አይቀየርም ያልክሁት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አውሮጳውያንንና ሌላውን ዓለም
“አበሻ” አትበሉን፤ በስማችን ኢትዮጵያ ብላችሁ ጥሩን ሲል ቢያስታውቃቸውም፣ ዐረቦቹ ገና አበሻ እያሉን
ነው። “ጋላ”ም የሚለው ቃል እንግዴህ አመጣጡ በዚያ መልክ ስለሆነ፣ ስድብ አድርጎ መውሰዱ አያዋጣም።
ለመጀመርያ ስሙ የተሰጠው በሱማሌዎች ስለሆነ፣ እነሱም አለምክንያት ከመሬት ብድግ ብለው ሳይሆን፣
ባንድ ግንዛቤ ተመሥርተው ነው። ልክ ጋሎች ሌላውን በ አካባቢያቸው ያለውን የደቡብ ኢትዮጵያን ሕዝብ
“ሲዳማ” ብለው ይጠሩ እንደነበር ማለት ነው። “ሲዳማ” አሁንም ሆነ፣ ስሙን በሰጡት ጋሎችም ስድብ
አይደለም። ሰጪዎቹ ራሳቸውንና ቡድናቸውን፣ በባህልም በቋንቋም ከማይመሰስሏቸው፣ ለመለየት ሲሉ
የሠየሙት “ሌላ” እንደማለታቸው ነው። እንዲሁም እርግጠኛ ነኝ ሱማሌዎችም ‘ጋላ” የሚለውን ቃል
ሲሰጡ፣ በዚያው መልክ መሆን አለበት። ሱማሌዎቹ ራሳቸው እንደጋላው ሕዝብ እረኞች ቢሆኑም፣
እስላሞች በመሆናቸው፣ በቋንቋም በእምነትም፣ ክጐረቤታቸው “ጋላ” የሚል ስያሜ ከሰጡት ሕዝብ
ይለያሉ። እንግዴህ ለሱማሌ “ጋላ” ማለት “ሱማሌ” ያልሆነ፣ የሱማሌን ባህልና የእስልምናን እምነት
የማይከተል “ሌላ” ጐረቢታችን ማለት ነው።

Page 17 of 23
“ጋላ” ስድብ ቢሆን ኑሮ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መከሰስ ይኖርበታል። ይህቺ፣ የሰው ዘር በሙሉ በእግዜር
ምስል ነው የተፈጠረው፣ ሁሉም እኩል ነው የምትለው ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሏት ከዋናዎቹ
ሰበካዎች መካከል “የጋላ ሐዋርያዊ ሰበካ [በእንግሊዝኛ The Apostolic Vicariate of the Galla፣
በኢጣሊንኛ Vicariato Apostolico di Galla” ይገኝበታል። ስድብ ቢሆን እንግዴህ እንዴት ይህቺ
ከቅድሳትም ይበልጥ ቅድስት ናት የሚትባል ቤተክርስቲያን፣ የራሷን ታማኝ ምእመናን “ጋላ” ብላ
ትጠራለች። የማይታሰብ ነው። ዝቅተኝነት የሚያጠቃውና የእእምሮ ችግር ያለው ካልሆነ በስተቀር፣ ማንም
መጠርያ ስምን እንደስድብ አያስብም። ስለዚህ ጋላ የሚለው ቃል ችግር ባለባቸው በፓለቲከኞች ጭንቅላት
ካልሆነ በስተቀር፣ መጥፎነትን የማያመለክት ገለልተኛ መጠርያ ነው። ልክ ጋሎች ከእረኝነት ኑሯቸውና፣
ከሚያምኑበት እምነት የተለየ ኑሮና ሃይማኖት ያላቸውን የጐረቤታቸውን ሕዝብ “ሲዳማ” ብለው
ሲጠሯቸው እንዳልተቀየሙ ሁሉ፣ ሌሎችም እነሱን ጋሎች ቢሏቸው የሚቀየሙበት ምክንያት አይታየኝም።
እነሱም “ጋላ” ያሏቸው፣ ከባህላቸውና ከቋንቋቸው ጋር የማይጣጣም “ሌላ” ዐይነት ሕዝብ ስለሆኑ እንጂ
መሳደብ ፈልገው አይመስለኝም። እንደማንኛውም ሕዝብ፣ እነሱም ጐረቤታቸውን በቋንቋቸው ስም
የመሰየም መብት አላቸው። እርስዎ ከመሳደብ ውጭ፣ ለምን “ጋላ” የሚለውን ቃል መጠቀም ከጥላቻ
እንደሚቈጠር ከነማስረጃው አላቀረቡልኝምና እንግዴህ የኔን ትንተና እንደሚቀበሉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

በመጨረሻ ላነሣ የምፈልገው እርስዎ በንቀት አቡጊዳ የሚሉትን የአማርኛ ፊደል ነው። ላቲን ይበልጣል
ማለትዎ ብቻ የሚያጠግብ መልስ ሊሆን አይችልም። ከላቲን በምን እንደሚተናነስም ከነማስረጃው ማቅረብ
ይጠበቅብዎታል። ባያውቁት ይሆናል እንጂ፣ የላቲን ፊደል ራሱ ምንጩ ከአፍሪቃ ነው። በኔ በኩል የአማርኛ
ፊደል፣ ከማንኛውም አሁን ባለም ካሉት ፊደላት እንደሚሻል በጽሑፌ አሳይቻለሁ። ቫወል እያሉ ሁለት
ፊደል ከመጻፍ ባንድ ፊደል መገላገሉ እንደሚሻል፣ ዓለም በሙሉ ያውቃል። የተጻፈውን ፊደል አለአገባቡ
ከማንበብ፣ እንደተጻፈው ማንበብ እንደሚሻልም አስረድቻለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ ክብርና ኩራት አለ።
በፊደል ብዛት የሺኖች (ቻይናውያን) ከማንም ይበልጣል። ሲቀለድ ሺኖች ፊደላቸውን ሕይወታቸውን
በሙሉ አጥንተው ሳይጨርሱት ነው የሚሞቱ ይባላል። በአውሮጳ ተማሪ ሳለሁ በትርፍ ጊዜዬ ቋንቋ
እያስተማርሁ ትምህርቴን እደጉም ነበርና፣ ክፍያው ከቋንቋው አስቸጋሪነት መጠን ስለነበር፣ ከሁላችንም
ዕጥፍ የሚያገኝ የነበረው የሺኑ አስተማሪ ነበርና በጣም እቀናበት ነበር። ታዲያ ይኸንን ያነሣሁልዎት አንድ
ነገር ላሳስብዎት ነው። በቅርብ ጊዜ የአውሮጳ ጋዜጠኞች የጃፓንን መሪ፣ ለምን አገርዎ ውስብስቡንና
አስቸጋሪውን የሺን ፊደል ትቶ፣ የላቲን ፊደል አይጠቀምም ብለው ሲጠይቋቸው የሰጡት መልስ፣ “የሺን
ፊደል አስቸጋሪ መሆኑ ጠፍቶብን አይደለም፤ በደምብ እናውቃለን። ሺን የእስያ ሥልጣኔ ነው፤ ጃፓንም
የእስያ አካል ናት። ስለዚህ እኛም እስያዉያን ነንና የእስያን ሥልጣኔ እንጂ የአውሮጳውያንን ሥልጣኔ
የምንጠቀምበት ምክንያት አይታየኝም” የሚል ነበር።

እንደርስዎ ያለ ግን ወደሰባ ዓመት ገደማ፣ ባገኙት በዘመናዊ መሣርያ ኀይል ከሰው ዘር በሙሉ የበላይ ነን
በማለት በድፍኑ ዓለም እንደልባቸው እየፈነጩ በነበሩበት ጊዜ፣ እርስዎን የመሰለውን ጥቁር ሕዝብ በሙሉ፣
“ከዝንጀሮ” የማይሻሉ ፍጥረት ናቸው፤ ለሰው ዘር ሥልጣኔ ያደረጉት ምንም ዐይነት አስተዋፅዖ የለምና
መጥፋት ያለባቸው የጐሦች ጥርቅምቅም ናቸው፣” ይሉ የነበሩትን ነጮች ከሚያደንቁት ጥቁሮች አንዱ
ይመስሉኛል። “ላም ካራጇ ጋር ትውላለች” የሚለው ያገራችን ተረት ለርስዎ ዐይነቱ የተረተ ይመስለኛል።
የጃፓኑ መሪ ግን ይኸንን ታሪክ አብጠርጥረው ስለሚያውቁና፣ የሳቸውም አገር የነጮች ትዕቢትና

Page 18 of 23
ምንአለብኝነት ሰለባ እንደነበረች ስለተማሩ፣ የበቀል ስሜት ሳያሳዩ፣ ለጠያቂዎቻቸው የአውሮጳውያን
ጋዜጠኞች፣ በጣም ጨዋ መልስ ነው የሰጧቸው።

እርስዎም በጥቁርነትዎ ክብርና ኩራት እንደሚሰማዎት አልጠራጠርም። በአገርዎና በሕዝብዎ ግን የሚኰሩ


አይመስለኝም። እንግዴህ ነጮች ጥቁሮች አፍሪቃውያንን ጊዜአቸው ያለፈባቸው የጐሦች ጥርቅምቅም እንጂ
ሕዝብ ስላልሆኑ፣ ቀይ ህንዶች የሚባሉትን የአሜሪቃ ተወላጆችን እንዳደረጉ፣ አፍሪቃውያንንም አጥፍተው
በነጭ ሕዝብ ለመተካት ሲሉ ነው ክፍለ አገሩን ቅኝ ግዛት ያደረጉት። ዓላማቸውን ያከሸፈችባቸው ኢትዮጵያ
በልጆቿ ትብብር በአድዋ ላይ ባደረገችው ድል ነው። ያሸነፈችውም እንደሌላው የአፍሪቃ አገሮች የጐሣ
ጥርቅምቅም ጦር ሁና ተዋግታ አይደለም። ሁሉም ተባብረው በኢትዮጵያዊነታቸው ባንድ መሪ ባንድ ሰንደቅ
ዓላማ ሥር ተዋግተው ነው። አሜሪቃ የነጮች ሰለባ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ ተሸንፎ የማያውቀው የነጮች
የቅኝ ግዛት ጦር፣ አውሮጳዊ ባልሆነ ሕዝብ ለመጀመርያ ጊዜ በማያዳግም መልኩ ድል የሆነው በኢትዮጵያ
ብቻ ነው። ቀጥላ ጃፓን ደገመችው። ፊታውራሪዎች እንደመሆናችን፣ በዚህ መኩራት አለብን። ይበልጥ
ደግሞ የምንኰራው ሕዝቡን የሚያስተባብር ቋንቋ ባይኖር የኢትዮጵያም ድል አጠያያቂ ሁኖ በቀረ። ስለዚህ
የአማርኛ ፊደል የአንድነታችን መግለጫ፣ የሥልጣኔአችን መለዮ፣ የታሪካችን ኩራት ነው። እንደሺኖች
ፊደላት አስቸጋሪ አይደለም፤ እንደሮማውያን ከሌሎች አልተበደርንም። ጽሑፌ ሊያስረዳዎት የሞከረው፣
ለዕድገቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አስተዋፅዖ ያደረገበት አገርበቀል ፊደል ስለሆነ፣ ካስፈለገ አሻሽለነው መጠቀም
አለብን እንጂ መናቅ የለብንም ነው።

ከጽሑፍዎ እንደምረዳ ከሆነ፣ እርስዎ እንደጐረቤቶቻችን እንደኤርትራ መሪዎች፣ ትላንት ከእንስሳ እንጂ
ከሰው የማይቈጥርዎት የነበረውን ነጭ እንደሚመርጡ፣ ግን ከነጭ ጨቋኝ እጅ ታድጋዎት ለወግና ለማዕረግ
ያበቃችዎን አገርዎን ኢትዮጵያን እንደጨቋኝ በመቊጠር እንደሚሳደቡና እንደሚያዋርዱ ነው። ተረት
የሚባለው እንደዚህ ዐይነቱ አስተሳሰብ እንጂ፣ በሐቅ ላይ የተመሠረት የኔ ትንተና አይደለም። ሮም
አውሮጳውያንን ከአረመኔነት አወጥታ ለሥልጣኔ እንዳበቃቻቸው፣ ኢትዮጵያም ከሮም በምንም መልኩ
በማያንስ ሥልጣኔዋ፣ አብዛኛውን ሕዝብ ለታላቅ ሥልጣኔ አብቅታለች። እረኛ የነበረውን እርስ በርሱ ይፋጅ
የነበረውን የጐሦች ጥርቅምቅም፣ በማእከላዊ መንግሥት ሥር አደራጅታ፣ ለታላቅ ማዕርግና ወግ እንዲደርሱ
አድርጋለች። እንደዚህ ዐይነቱን እውነት የጐሣ ሥርዐት አራማጆች ሊዉጡት የማይችሉት፣ ሊናገሩት
የማይወዱት ሐቅ ነው። ግን ምን ይደረግ። ከመጮህና ከመሳደብ ውጭ ሌላ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር
የለም።

እርስዎ ከድፍረትዎ የተነሣ የትምህርቴንና የሙያዬን ብቃትንም እጥያቄ ውስጥ እስከማስገባት ደርሰዋል።
ማወቅ ያቃተዎት ነገር ቢኖር፣ ከተወለድህበት አገር ወጥተህ በተማርከው መስክና ሙያ መቀጠር የትም
አስቸጋሪ ነው። በምዕራብ ዓለም ከሆነ ደግሞ ያገሩን ተወላጅ ቢያንስ በዐምስት እጅ ካልበለጥህ ዞር ብሎ
የሚያይዎት እንደሌለ ማንም የውጭ አገር ምሁር ያውቃል። እንግዴህ እኔንም ማየት የሚገባዎት በዚያ
መልክ ይመስለኛል። እርስዎ ከሚያደንቁትም ከጐሣዎ ምሁራን ስማቸውን ባልነግርዎትም፣ ጥቂቶቹን አሁን
ወዳሉበት ደረጃ እንዲደርሱ በማድረግ የረዳሁኋቸው እንዳሉ እናዘዝልዎታለሁ። እንደርስዎና እንደአብዛኞቹ
እርስዎን ከመሰሉት ስሜን በብርዕ ስም ሽፋን ሳልደብቅ በግልጽ የምጽፈው በዕውቀቴና በሙያዬ
ስለምተማመን ነው። ዕውቀቴና ድግሬዬ መስፈርቶቹን በማትረፍረፍ አልፈው የተገኙ እንጂ እንደብዙዎቹ

Page 19 of 23
በሸቀጥ የተገዙ አይደሉም። በዚህ አይጠራጠሩ። በየሄድሁበት የሚመሰክርልኝ ሥራ ስለሠራሁ፣ የርስዎን
ስድብ ከምንም እንደማልቈጥር ይረዱኝ።

ጽሑፍዎ ብዙ አላስፈላጊ ስድብ አዝሏል። እኔ ግን ሙያዬም አስተዳደጌም የርስዎን ዐይነት የብልግና ንግግር
ስለማይፈቅዱልኝ፣ ከርስዎ ከፍ ብዬ እንጂ ዝቅ ብዬ ለመታየት ፍላጎት የለኝም። በኛ አገር እንደርስዎ ዐይነቱን
አሳዳጊ የበደለው ብለን እንደምናልፈው ያስታውሱ ይሆናል። በፈረንጅ አገርም ቢሆን የርስዎን ዐይነቱ ንግግር
አጸያፊ ነው። በነሱ አገር፣ ይልቅስ እያንዳንዱ ሰው እንደየዝንባሌውና የሙያ ብቃቱ የሚሠራበትና
የሚወዳደርበት መስክ አለ። ለሁሉም ዕድል የሚሰጥ አገር ነው። መማታትና ጡንቻ የሚያምረው
ወደBoxing ያመራል። ቊጣ ለሚያጠቃው ደግሞ የቊጣ መቈጣጠርያ ሰፈር አለ፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ
ባልሳሳት “Anger Management” ይሉታል። እዚያ ሄዶ ቊጣውን እንዴት መወጣት እንደሚገባው
ይማራል። ከባዶ ተነሥቶ ተሳዳቢም ወይ ሌላውን ስድብ እየተጠቀመ ለማዝናናት ወደኮሚክነት ይገባል፤
ካልሆነለት ደግሞ እንደአዲስ አበባው የአማኑኤል ሆስፒታል ወደመሰለ የአእምሮ ቀውሶች መታከሚያ ቤት
አለለት። ለርስዎም ስድብ ዐምልዎ ከሆነ ከነዚህ አንዱ ሳይስማማዎት አይቀርም ይሆናል። ምርጫው የርስዎ
ነው።

ከላይ እንደገለጽክሁልዎት ድረገጾች የተቋቋሙት፣ ባገር ጉዳይ አሳብ እንድንለዋወጥ፣ እንድንማማር እንጂ
ለመሰዳደብ አይደለም። ስድብ የደደቦች መሣርያ ነው። ፍራቻቸውንና የብቃት ጉድለታቸውን የሚወጡበት
በስድብ ስለሆነ፣ የተሳዳቢውን የብቃትና የችሎታ ማነስ ነው የሚያመለክተው። ለማዳ ያልሆኑ የዱር
እንስሶች የሚፈሩትን በጉልበታቸው ለማጥቃት እንደሚሮጡ ሁሉ፣ ደደቦችም የሚያደርጉት ልክ እንደነሱ
ነው። ጭንቅላት ያለውና በትምህርት የተገራ አእምሮ ያለው ግን መልሱን በጨዋነታና በብልሃት ይሰጣል።
ቸር ይግጠመን።
[Reply]
Reply
9. Mori says:
August 15, 2016 at 2:34 am
Ago Haile male Mnale sdbwon baidegmut. INE rasen gala bye alteram.
Lelawnm hzb bemktelaw sm alteram. INE yewesedkut kanuye Tshuf
Yalengehut(‘DRO Galloch yemibalu “Ahun ihadeg be awaj oromo blo
yesemew)Mangnwm hzb YEMITERAW RAsun bemiteraw inji betelat
betesetew qstl sm a, idelem. Amaran besomali aterar har(amhar har, jarer)
blew new, emiterut har besumalinga qalu kemolagodel yaw indeamarnga
new. Yih. Hzb nqetNew. Oromo qalu bihadeg yetaweje sahone meteriachn new
kaza yalefew sdb new . adis mehonun kante samahu inji lela sm yelenm.
Nsuhu Oromo abagochun qotro mechereshaw abatu oromo new. Man qsulun
sm indawetaw indabazaw metqesu waga yellewm. Whew s. One tells u that
u’ve done s. thing that hurts them, u don’t get to decide that u didn’t. Any how
I’m dude conserving my name. Don’t feel offended. It’s not personal. I’m cool .
take it easy . plz goof off using approbrious and disrespectful words towards

Page 20 of 23
any nation coz it’s harms & brings ding dong for its not take us anywhere
except flacky Destruction . let me put u in good words that u r a geek & change
into dynamite real unity. I love ethiopia, specially Oromo l love buried genioun
fabulous history of oromo, prey with me for its revival. mr Haile. Remember?
We r one.. Oromo amahara garage… Including z whole races of our planet
except those some fat headed goof sook individuals want to fill their belly with
blood of people and to make them. S. U.. C ya libora
[Reply]
Reply
10. Tola says:
August 15, 2016 at 9:22 am
ዶክተር ሃይሌ ላሬቦ የሰጥኡት አስተያየት በምርምርና በማስረጃ የተደገፈ በመሆኑ ትልቅ ትምህርት
ይስጥኣል::ነገር ግን አይምሮዋቸውን በጥልኣቻ ለደፈኑና ስድብ መልስ ለሚመስላችው የሃሳብ ደሃዎች መልስ
መስጤት አያስፈልግም ::ምክንያቱም ደጋግሞም ቢነገራቸው አይገባችውምና ::
[Reply]
Reply
11. Gemeda Boru says:
August 15, 2016 at 3:59 pm
None sense writing by Haile Larebo. You waste your time in writing none
sense. You are like a mad dog. Your writing is full of rubish. GIM CHINQLAT!
[Reply]
Reply
12. ሽማግሌ says:
August 15, 2016 at 9:17 pm
የሰው ልጅ የተፈጠረው ከ አዳምና ሔዋን ነው። ስለዚህ የ ሰው ፍጥረት ሁሉ አንድ ብሔር ነው ማለት ነው።
ነገር ግን ይህን ሃቅ አንቀበልም። በ አንፃሩ በ ቌንቋ ላይ የተመሠረተ ብሔርተኝነትን ተቀብለናል። ማንኛውም
ብሔር አሁን ከሚጠቀምበት ቋንቋ በፊት ሌላ ቋንቋ አልተጠቀመም ነበር ማለት አይቻልም። ስለዚህ አንድ
ህብረተሰብ የሚታወቀው በ አፍ መፍቻው ቋንቋ ነው። ስለሆነም ጎንደሬዎች፣ ጒጃሜዎች፣ ወሎዬዎችና
ሸዋዎች አማሮች ናቸው።
[Reply]
Reply
13. ወጣ says:
August 16, 2016 at 3:04 am
ለመሆኑ አማራ አለ እንዴ? ወያኔ እኮ አከርካሪው መቶታል አጥፍቶታል!
ወያኔ ስንት አማራዎችን ገደለ አስደገል ወደፊትስ ስንት አማራዎችን ይገድላሉ? መቼ ይገድላሉ? ነገሮች
እየተባባሰ ባለበት ለማን ይጠቅም ይሆን ?ወያኔስ ይኮራበት ይሆናል!
የእኛ ጉዳይ ፈጣሪ ከኢትዮጵያ ጋር ይሁን! እንጂ በጣም አሳሳቢና አስጀጋር ሁኔታ ላይ ያለነው እንደሰው
መታሰብ የሚጀመረው መቼና በማን ይሆን?
[Reply]
Page 21 of 23
Reply
14. Sidamaol says:
August 16, 2016 at 4:55 pm
Libora lemn buzu gizewon zmblo tera sewoch tesebsbew yemiawerut
yemimesl chweta ystfalu?1)..arswo sle amara kehone indetelemedew kalelaw
semi kagengu kebrhan new yeteseru ybelu.yeraswon yekereme inqulal wub
qelemoch qebtew yelelawn werq degmo aynemdr meqebatwo
germongal.ihadeg beawaj oromo yemil sm awetalachew yalut isti yeawajun
qenna qutr yngerun. wushet kehonem ihadigochn yemiaswqs
aidelem.2/mhuran tebyewoch oromowoch maletwo lemn alachebechebum
lewshet tari maletwo meselegn.wushet sidegagem….. 3/yejapan yaltefetseme
tarik.ketataroch yedro tarik gar kaltemtatabawot besteqer germen
ingliznga.taliangna.greek..mndnew buz awaqiwoch menorachewn
aizengu.4/mori indalew hochimin .. Uelem ststf tesasche indezi
indeza….5/somligna gal malet irso yalut saihon beteley leamhara yetesete
trgum islam yalhone malet new mknyatum gorebetochachew oromowoch
islam nachew..6/irson bgn yarogot fidelin yemichnubet sew matatwo new.ya
degmo latin behulum africa kale arab ager bemulu awropa..lemn keseletenew
alem kaleaqmwona mebto ymboracheqalu yemitequmubet new beagerachn
afar,oromo,somale..tesmamatuachewal tadia oromo lay bcha chuhet lemn
bereket?oromi gn amarochn belatin tsafu alza yamengal blo ayawqm.lelaw
sidama gorebetochn sayhon lewererwachew yetesete new.honom tsfwo
yerson asteyayet yemesele yalachewn biasdestm sle oromo yetenagere
tefetrwawi mebet tnsh yetenagere tsngegna zeregna befidelachew yetsafu
hulu iske ihadge wede sltan memtat dres yitadenu yegedelu neber.tadia yann
yenafequ ymeslalu.irson lelaw hzb fidel merch man aregot.fetari raiy
asaytowot indayhon?
[Reply]
Reply
4 Pings/Trackbacks for "ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ"
1. ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ – March 4 Freedom says:
August 13, 2016 at 10:36 am
[…] ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብ ላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ
እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ
በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው
የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ […]
2. ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ – March 4 Freedom says:
August 13, 2016 at 2:45 pm

Page 22 of 23
[…] Source Article from http://www.mereja.com/amharic/508921 […]
3. ይድረስ ለአቶ ሞሪ [ኀይሌ ላሬቦ] – ሳተናው – Latest Ethiopian News & Breaking
News says:
August 16, 2016 at 6:33 am
[…] August 14, 2016 at 2:05 am […]
4. ይድረስ ለአቶ ሞሪ [ኀይሌ ላሬቦ] – March 4 Freedom says:
August 16, 2016 at 10:45 am
[…] August 14, 2016 at 2:05 am […]

Page 23 of 23

You might also like