Download as txt, pdf, or txt
Download as txt, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ሩዋንዳ በጤና መስክ እጅግ ስኬታማ ጉዞ እያደረጉ ያሉ አገራት ብሎ የዓለም ጤና ድርጅት የመሰከረላቸው መካከል አንዷ ናት።

“የሺህ ተራራዎች ምድር” ተብላ የምትጠራው ትንሽዬዋ የምሥራቅ አፍሪካ አገር የሕዝብ ቁጥር ከ 15 ሚሊዮን ባይልቅም በጤናው ዘርፍ
ግንባር ቀደም ከሚባሉት ተርታ ተመድባለች።
የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም መረጃ እንደሚጠቁመው 90 በመቶ ሕዝቧ የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን አለው። ኤችአይቪ በደማቸው ካለ ሰዎች 90
በመቶው የመድኃኒት አቅርቦት አላቸው። 93 በመቶ ሕፃናት ደግሞ ተላላፊ በሽታዎችን ለመግታት ክትባት ወስደዋል።
በአውሮፓውያኑ 2000 የሩዋንዳውያን አማካይ የዕድሜ ጣሪያዋ 48 ነበር፤ አሁን ይህ ቁጥር ከ 67 በላይ ሆኗል።
እርግጥ ነው ሩዋንዳ አሁንም በምጣኔ ሀብት ዳበረች የምትባል አይደለችም። ነገር ግን ከ 2000 እስከ 2015 ባለው ጊዜ በድህነት ውስጥ
የሚኖሩ ሰዎችን ቁጥር ከ 40 በመቶ ወደ 16 በመቶ ዝቅ ማድረግ ችላለች።
የሩዋንዳ መንግሥት በጤና ዘርፍ ማሳካት የሚፈልገው ትልቁ ግብ የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ማዳረስ ነው። ለዚህ ግብ መሳካት ደግሞ
ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረጉ ይመስላል።
ለመሆኑ ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ሩዋንዳን የሚመርጡት ለምንድነው? እንዴትስ ነው ወደ ሩዋንዳ የሚያቀኑት?
ዶክተር የቆየሰው በለጠ ነዋሪነታቸውን በሩዋንዳ ካደረጉ አንድ ዓመት ተኩል ሆኗቸዋል። በክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሺየቲቭ የሄልዝ
ሲስተምስ ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
“በርካታ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ቦትስዋና በሚፈልሱበት ወቅት እኔ ተማሪ ነበርኩ” የሚሉት የሕብረተሰብ ጤና (ፐብሊክ ሄልዝ)
ባለሙያው አሁን ደግሞ ተራው የሩዋንዳ እንደሆነ ይመሰክራሉ።
እሳቸው እንደሚሉት መጀመሪያ አንድ ሰው ወደ አዲስ አገር በሕክምና ሙያ ካቀና በኋላ ዕድሉ እንዳለ ለሙያ አጋሮቹ ያሳውቃል፤ ይሄኔ ነው
ሐኪሞች ወደ ውጭ መውጣት የሚጀምሩት።
የፐብሊክ ሄልዝ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር የቆየሰው፣ በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከማገልገላቸውም በላይ በሙያቸው ምክንያት ዛምቢያን
መኖሪያቸው አድርገው ነበር።
የጤና ባለሙያው እንደሚሉት አብዛኞቹ ሩዋንዳ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች 'ሰብ-ስፔሻሊስቶች' ናቸው።
“ይህ ማለት ለምሳሌ አንድ ሐኪም በውስጥ ደዌ አሊያም በማህጸን ወይም በሕፃናት ሕክምና ስፔሻላይዝ ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ለምሳሌ
በውስጥ ደዌ ሕክምና የልብ ስፔሻሊስት ሊሆን ይችላል። እንግዲህ ምን ያክል ትልልቅ ባለሙያዎች እንደሆኑ ያሳየናል ማለት ነው።”
ዶክተር የቆየሰው እንደሚሉት ምንም እንኳ የሩዋንዳው ትልቁ ኪንግ ፋይሳል ሆስፒታል ዋነኛው የኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ቀጣሪ ቢሆንም
ሌሎች 'ተሪሻሪ ሆስፒታሎች' ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ተቀጥረው ይሠራሉ።
አክለው ኢትዮጵያውያን ሆስፒታሉን ከማስተዳደር ጀምሮ አንዳንዶቹ በስፔሻሊስት ሌሎቹ ደግሞ በሰብ-ስፔሻሊስት ደረጃ በማገልገል ላይ
ይገኛሉ።
ዶክተር ዘሪሁን አበበ የኪንግ ፋይሳል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፣ ዶክተር ሃና አበራ ደግሞ የጋስትሮኢንትሮሎጂ ክፍል ኃላፊ
ናቸው።
ዶክተር የቆየለት እንደሚሉት ቢያንስ ከ 20 አስከ 30 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ሩዋንዳ ውስጥ ያገለግላሉ።
የነርሶች እና የአንስቴዢያ ባለሙያዎች ቁጥር ግን እምብዛም አይደለም። ለሁለት እና ሦስት ወራት ወደ ሩዋንዳ መጥተው፤ በሙያቸው
ሠርተው፤ ልምዳቸውን አካፍለው የሚሄዱ ባለሙያዎችም አሉ።
ፐብሊክ ሄልዝን ጨምሮ በሌሎች መስኮች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ከ 10 እስከ 15 የሚሆኑ ስፔሻሊስቶችም እንዳሉ ዶክተሩ
ይናገራሉ።
“ኢትዮጵያ በቁጥርም በዓይነትም በጣም ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችን ስላሰጠነች እነዚህ ባለሙያዎች መጥተው እየሠሩም እያሠለጡንም ነው
ያሉት። እኛ የፐብሊክ ሄልዝ ባሙያዎች ደግሞ ስትራቴጂ የማውጣት እና የማማከር ሥራ እንሠራለን።”
የዓለም ጤና ድርጅት ቢያንስ አራት የሕክምና ባለሙያዎች ለአንድ ሺህ ሰው መድረስ አለበት የሚለውን ስትራቴጂ ካወጣ በኋላ የሩዋንዳ
መንግሥት በአራት ዓመት ውስጥ ይህን ለማሳካት እየተጋ ይገኛል።
በቅርቡ የተሾሙት የሩዋንዳ አዲሱ የጤና ሚኒስትር እና ዴኤታቸው ይህን ዕቅዳ ለማሳካት እየሠሩ መሆናቸውን የሚናገሩት የፐብሊክ ሄልዝ
ስፔሻሊስቱ፤ አገሪቱ እየሠራ የሚያስተምር ባለሙያ ትፈልጋለች ይላሉ።
“አንደኛው ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሩዋንዳ እየመጡ ያሉበት ምክንያት አገሪቱ ያወጣችው ስትራቴጂ የሥራ ዕድል መፍጠሩ
ነው። ሩዋንዳ ያወጣችውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ።”
ነገር ግን ይላሉ ለበርካታ ዓመታት በፐበሊክ ሄልዝ ሙያ ያገለገሉት ዶክተር የቆየሰው፤ “ነገር ግን መሠረታዊው ምክንያት ግን ሌላ ነው።”
እሳቸው እንደሚሉት “ኢትዮጵያ ለሕክምና ባለሙያዎች እጅግ ዝቅተኛ ገንዘብ ከሚከፍሉ የዓለማችን አገራት መካከል ናት። ያለው ሁኔታ
ብዙዎች ከአራቸው ወጥተው ያለውን ዕድል እንዲሞክሩ የሚያደርግ ነው።”
የቢቢሲ አማርኛ ዘጋቢ በቅርቡ ወደ ሩዋንዳ ተጉዞ የጤና ባለሙያዎች ወደ ኪጋሊ ለምን መምጣት እንደሚሹ ከራሳቸው አንደበት ለመስማት
ቢሞክርም የጤና ባለሙያዎቹ በይፋ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ዶክተር የቆየሰው እንደሚሉት ግን ሌላኛው ምክንያት “ሙያን ለማሳደግ የሚደረግ እንቅስቃሴ” ነው። ይህን ለማስረዳት የራሳቸውን ልምድ
በምሳሌ ያነሳሉ።
“እኔን ብጠየቅ የግሎባል ሄለዝ ስፔሻሊስት ነው መሆን የምፈልገው። ማንኛውም ባለሙያ ሙያውን ዓለም አቀፍ በሚባል ደረጃ ማሳደግ
ይፈልጋል። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ አፍሪካ አገራት ሄደው ሠርተው ራሳቸውን ያሳድጋሉ፤ በግሎባል ሄልዝ ላይ
አሻራቸውን ማሳረፍ ይፈልጋሉ። ፍልሰቱ ከችግር ብቻ ነው የሚመነጨው ብሎ ማሰብም ተገቢ አይደለም።”
በአንድ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ውጭ ተጉዘው እንዳያገለግሉ ያወጣውን መመሪያ የሚያነሱት
ዶክተር የቆየሰው “አስረን ልናስቀረው የሞከርንበት ጊዜም ነበር፤ ግን አይጠቅምም” በማለት ማንኛውም ባለሙያ ተንቀሳቅሶ የመሥራት መብቱ
ሊጠበቅለት ይገባል ባይ ናቸው።
የሩዋንዳ መንግሥት ጤናን ለሁሉም ለማዳረስ ያወጣውን ስትራቴጂ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እና የተራድዖ ድርጅቶች
ጋር እየሠራ ይገኛል።
የዓለም የጤና ድርጅት፣ ዩኤስኤአይዲ እና ክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሺዬትቭን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሩዋንዳ መንግሥት
ጋር ይሠራሉ።
ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች አገራት የሚመጡ የሕክምና ባለሙያዎች በእነዚህ ድርጅቶች አማካይነት ይመጣሉ የሚሉት ዶክተር የቆየሰው “ጥሩ
ጥቅማጥቅም፣ ጥሩ ደመወዝ እና መልካም የሥራ ሁኔታ አመቻችተው ነው ወደዚህ አገር የሚያስመጡት” ሲሉም ያስረዳሉ።
“እኛ [ኢትዮጵያ] በስትራቴጂ ብዙ ባንታማም ስትራቴጂዎችን ለማሳካት የሚሆን የተመቻቸ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር ላይ ግን ብዙ
ይቀረናል። የጤና ባለሙያው በትክክል ሥራውን እንዲሠራ የማያስችሉ ብዙ የምናውቃቸው ተግዳሮቶች አሉ።”
እሳቸው እንደሚሉት ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ውጭ አገራት ተጉዘው ልምድ መቅሰማቸው የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ
አይደለም።
“የጤና ባለሙያዎች አምርተናል፤ ሐኪሞቹ አገር ውስጥ አገልግለዋል፤ ሌሎችን ዕድሎችንም እንዲያዩ ማድረግ ለአገሪቱ ጠቃሚ ነው ብዬ
አስባለሁ። አንድ ወቅት ላይ ሁሉም ሰው ወደ አገሩ ይመለሳል። ወደ አገራቸው የተመለሱ የጤና ባለሙያዎች እየሠሩ ያሉትን ነገር ስንመለከት
በጣም የሚያኮራ ነው።”
የፎቶው ባለመብት, Dr. Yekoyesew/Linkedin
ከ 30 ዓመታት በፊት አስከፊ በሚባል የእርስ በርስ ጦርነት እና ድህነት ስትታመስ የነበረችው ሩዋንዳ ዘንድሮ በጤና እና ቱሪዝም እንዲሁም
በሌሎች መስኮች በአፍሪካ ምሳሌ ተብላ የምትጠራ አገር ሆናለች።
የዓለም ጤና ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2018 ባወጣው ሪፖርት ከ 1994 የሩዋንዳ ዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) በኋላ ባሉት 20 ዓመታት
የዜጎቿ አማካይ ዕድሜ ዘመን በእጥፍ አድጓል።
ሪፖርቱ አክሎም በሩዋንዳ የጤና አገልግሎት ከመሻሻሉም በላይ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ከፍ ብሏል፤ የእናቶች እና የሕፃናት ሞት ቁጥር
ደግሞ አሽቆልቁሏል ይላል።
ዶክተር የቆየሰው እንደሚሉት ሩዋንዳ በጤናው ዘርፍ ተጠቃሽ አገር ለመሆን የቻለችው “ግልፅ ስትራቴጂ እና ተጠያቂነት” ስላለ ነው።
“አንድ አገር፤ አንድ የጤና ፖሊሲ፤ አንድ ስትራቴጂ አላቸው። እሱን ተከትለው ነው የሚሠሩት” ይላሉ።
“አንድ ሰው በጤና ሚኒስቴር በኩል ወደ ሥልጣን ሲመጣ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት ነው። ኃላፊነቱን ካልተወጣ አይቆይም። ይህ
እጅግ በጣም ከሚያስቀኑኝ ነገሮች አንዱ ነው።”
በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ያገለገሉት ዶክተር የቆየሰው፤ በኢትዮጵያ ምንም እንኳ “ስትራቴጂው ቢኖረንም”
ተግባራዊ ማድረጉ ላይ ደካማ ነው ይላሉ።
እሳቸው በጤና ሚኒስቴር እየሠሩ ሳለ የሆነውን አውስተው ችግሩ ያለው ከፖሊስ ሳይሆን ከትግበራ መሆኑን ያስረዳሉ።
“በአንድ ወቅት ብዙ ሐኪሞች በዓለም ጤና ድርጅት መስፈርት እናሠልጥን ተባለ፤ ሠለጠኑ። ግን ሥራ አልነበራቸውም። በወቅቱ በርካታ
የጤና ባለሙያዎች አመጽ ወጥተው ነበር። ክልሎች ናቸው ሐኪም መቅጠር የሚችሉት። ፌዴራል መንግሥቱ መቅጠር የሚችለው
ለሆስፒታሎች እና ለፌዴራል ተቋማት ብቻ ነው። ነገር ግን የጤና ሚኒስቴር ያወጣው ስትራቴጂ ጥሩ ሆኖ ቀጣሪው ግን የፈለገውን የማድረግ
መብት አለው።”
ዶክተሩ ሌላኛው በሩዋንዳ ቆይታቸው ያስቀናቸው ጉዳይ ሰላም እና ደኅንነት መሆኑን ይናገራሉ። በተለይ የጤና ባለሙያዎች ሰላማዊ የሥራም
ሆነ የመኖሪያ ሥፍራ ያስፈልጋቸዋል የሚል እምነት አላቸው።
አክለውም ሩዋንዳውያን ለንጽህና ያላቸው አመለካከት ሌላኛው “ነቅለው ወደ ኢትዮጵያ ቢወስዱት” የሚመኙት ነገር ነው። ምክንያቱም ንጽህና
ለጤናውም መስክ አስተዋፅዖ አለውና ይላሉ።
ኪጋሊ በየወሩ በሦስተኛው ቅዳሜ “ኡሙጋንዳ”ን ታከብራለች። ይህ ቀን ሁሉም ሰው ወጥቶ አካባቢውን የሚያጸዳበት ቀን ነው። በየወሩ
በአራተኛው እሑድ ደግሞ “ካር ፍሪ ደይ” ነው። እስከ ጥዋቱ 5፡00 ድረስ መኪኖች መንገድ ላይ አይታዩም።
“እርግጥ እኛ አገር በተለያዩ ጊዜያት ብልጭ ብሎ አይተነዋል። እዚህ ግን ቀልድ የለም፤ ሁሉም ያከብረዋል።”
ዶክተር የቆየሰው “ሩዋንዳ ውስጥ ችግር የለም፤ ፍጹም አገር ናት እያልኩ አይደለም” ይላሉ። ነገር ግን ችግሮቻቸውን አውቀው እየሠሩበት
ነው። ለዚህ ነው ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የውጭ አገር ባለሙያዎች መጥተው እየሠሩ ያሉት።
እሳቸው እንደሚሉት ሩዋንዳውያን ለኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጡት ቦታ ደግሞ ከፍ ያለ ነው።
“ታድያ ጉምቱ የሕክምና ባለሙያ ሆነህ የምትናገረውን የሚያደምጥ፤ የምትጽፈውን የሚያነብ ከሌለ፤ እንዲህ ዓይነት ለሥራ ምቹ የሆነ አገር
እንዴት አትመጣ?
“እኛ አገር ያለው 'ሲስተም' ሥነ-ልቡናዊ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ ደኅንነት አይሰማም፤ ሙስናው እና የአሠራር ብልሹነት እንዲሁም ቢሮክራሲው፤
የሚባክነው ጊዜ፣ ጉልበት፣ ገንዘብ ጨለምተኛ እንደትሆን ያደርጋል።”

You might also like