Download as txt, pdf, or txt
Download as txt, pdf, or txt
You are on page 1of 2

የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነቸው ደቡብ አፍሪካ እየሠራችበት ያለውን ‘የቅኝ ግዛት’ የኢሚግሬሽን ሥርዓት ልታሻሽል

መሆኑን አስታውቃለች።
የደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የአገሪቱ የኢሚግሬሽን ሕግጋት ጠበቅ ያሉ እንዲሆኑ እና የዜግነት እንዲሁም የጥገኝነት ሂደቶችን
የሚያሻሽለውን አዲሱን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።
የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ሃሳቡ ይፋ በሆነበት ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ ዶ/ር አሮን ሞትሶአሌዲ አሁን አገሪቱ እየሠራችበት
ያለውን የኢሚግሬሽን ፖሊሲ “የቅኝ ግዛት ዘመን ውርስ” ሲሉ ገልጸውታል።
ከወራት የሕዝብ ምክክር በኋላ ይፋ የሆነው የአገሪቱ የኢሚግሬሽን ረቂቅ ዕቅድ በፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ካቢኔ ጸድቋል።
ነገር ግን ረቂቅ ሕግ ሆኖ ለመጽደቅ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማን ይሁንታ ያስፈልገዋል።
‘የዜግነት፣ የኢሚግሬሽን እና የስደተኞች ጥበቃ ረቂቅ’ የተባለው ረቂቅ ሕግ ይፋ የሆነው ደቡብ አፍሪካውያን በመጪው ግንቦት ብሔራዊ
ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።
በዚህም ምርጫ የስደተኞች እና የኢሚግሬሽን ጉዳይ ቁልፍ ርዕስ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በአገሪቱ ውስጥ በከፋ ሁኔታ እየጨመረ ያለው የሥራ አጥነት መጠን ወደ 32.6 በመቶ አሻቅቦ ከዓለም ከፍተኛው ከሚባሉት መካከል
አንዱ ሆኖም ተመዝግቧል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ለተሻለ ኑሮ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ስደተኞች ሥራ፣ መኖሪያ ቤት እና ሌሎች ዕድሎችን ከአገሬው እየነጠቁ ነው የሚሉ
ቁጣዎች በርትተው በተደጋጋሚ ይሰማሉ።
ደቡብ አፍሪካ ከሁለት ዓመት በፊት ባደረገችው የሕዝብ ቆጠራ መሠረት ቢያንስ 2.4 ሚሊዮን ከሌሎች አገራት የመጡ ስደተኞች አሏት።
ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ከጎረቤት አገር ዚምባብዌ ቢሆኑም ከኢትዮጵያ፣ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ከሶማሊያ፣ ከባንግላዴሽ እና
ከሌሴቶም የመጡ ስደተኞች ቁጥር በርካታ ነው።
ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተሻለ ሥራ እና ኑሮ ፈልገው የሄዱት ስደተኞች 62 ሚሊዮን ሕዝብ ካላት ደቡብ አፍሪካ አንጻር ሲሰላ 3 በመቶ
ብቻ ናቸው።
ሆኖም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ በርካታ ስደተኞች ሥራ እና የተለያዩ ዕድሎችን ተሻምተውናል በሚሉ መጤ ጠል (ዜኖፎቢክ) የአገሪቱ ዜጎች
ጥቃቶች ያጋጥማቸዋል።
በተለይም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች አፍሪካ አገራት የመጡ ስደተኞች ግድያ፣ ዝርፊያ እና የንብረት ውድመቶች አጋጥሟቸዋል።
ይህንን ሁሉ ከግምት ውስጥ ያስገባችው ደቡብ አፍሪካ በኢሚግሬሽን ፖሊሲዋ ልታሻሽል የምታስባቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
የፎቶው ባለመብት, AFP
የጨቋኙ፣ ዘረኛ እና አግላዩ የአፓርታይድ ሥርዓት መገርሰስን ተከትሎ በአውሮፓውያኑ በ 90 ዎቹ አጋማሽ ሥልጣን የተቆጣጠረው የአፍሪካ
ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) መንግሥት፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መፈረሙ ‘ትልቅ ስህተት’ እንደሆነ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሮን
ያስረዳሉ።
ሚኒስትሩ እንደሚሉት እነዚህ ስምምነቶች የተፈረሙት አዲሱ መንግሥት ስደትን በተመለከተ የራሱን ፖሊሲ ከማዘጋጀቱ በፊት ነው።
ሚኒስትሩ ከሚጠቅሷቸው ስምምነቶች መካከል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ 1951 የስደተኞች ስምምነት፣ የ 1967 ፕሮቶኮል እንዲሁም
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 1969 ስምምነቶች ናቸው።
ደቡብ አፍሪካ እነዚህን ስምምነቶች ስትቀበል የተወሰኑ አንቀጾች ተፈጻሚ የማይሆኑበት ወይም የሚቀሩበት መንገድን አላመቻችም ነበር ይላሉ
ሚኒስትሩ።
ደቡብ አፍሪካ ከእነዚህ ስምምነቶች እንድትወጣ ሃሳብ ያቀረቡት ሚኒስትሩ፣ እንደ መከራከሪያ የሚያቀርቡትም በስምምነቶች መሠረት በአገሪቷ
ላሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች የትምህርት እና መኖሪያ ቤቶችን የመስጠት ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ከለላዎችን የመስጠት አቅም
እንደሌላት በመጥቀስ ነው።
ደቡብ አፍሪካ ከስምምነቶቹ ውስጥ የተወሰኑትን አንቀጾች ማስቀረቷን ስታረጋግጥ እነዚህን ስምምነቶች እንደገና እንደምትፈርም ዶክተር አሮን
ተናግረዋል።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ ወደ 250 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች አሉ።
ከእነዚህም በተጨማሪ የተለያዩ የኢኮኖሚ ዕድሎችን የሚሹትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ሰነድ ያላቸው እና ሰነድ አልባ የውጭ
አገር ዜጎች ይኖራሉ።
በአዲሱ ረቂቅ መሠረት የስደተኛ ማዕከላት ወደ ድንበር አካባቢዎች እንዲጠጉ ይደረጋል። ይህም የኢኮኖሚ ስደተኞች እና ሕጋዊ ስደተኞች
ወይም የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመለየት እና ዝም ብለው ወደ አገሪቷ ገብተው ‘የሚጠፉ’ ሰዎችን ለማስቆም ያለመ ነው።
በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ‘የመጀመሪያው ደኅንነቱ የተጠበቀ አገር መርህ’ ('First Safe Country Principle')ን
ተግባራዊ ታደርጋለች። ይህ መርህ ጥገኝነት ጠያቂዎች ከትውልድ አገራቸው ከወጡ በኋላ በደረሱበት የመጀመሪያ ደኅንነቱ የተጠበቀ አገር
ለጥገኝነት እንዲያመለክቱ የሚጠይቅ ነው።
በዚህም መሠረት ስደተኞች ደቡብ አፍሪካ ከመድረሳቸው በፊት ባሉ አገራት ጥገኝነት ያልጠየቁ ስደተኞች ጥያቄያቸው ውድቅ ይሆናል።
ጥያቄያቸው ተቀባይነት የሚያገኘው ይህንን ላለማድረጋቸው “የተለየ አጥጋቢ ምክንያት ካላቸው” ብቻ ነው።
ነገር ግን ይህ የማይመለከታቸው ሊኖሩ እንደሚችሉ አዲሱ ረቂቅ አስፍሯል። የአገሪቱ የግብርና ዘርፍ ከውጭ አገራት በሚመጡ ሠራተኞች
ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የግብርና ሠራተኞችን ላይመለከት እንደሚችል ነው የተገለጸው።
በኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች ላይ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊነትን አጽንኦት የሰጡት ዶ/ር አሮን ደቡብ አፍሪካ ያሏትን 17 ዓይነት ቪዛዎች
‘አስተዳደራዊ ቅዠት” ሲሉ ገልጸውታል።
በአዲሱ አሠራር ከዚህ ቀደም ሲሰጡ የነበሩ የዘመድ ጥየቃ ቪዛ፣ የተቋማት ቪዛ፣ እንዲሁም የኩባንያዎች ቪዛ ሊሻሻሉ፣ ሊጠቃለሉ ወይም
ሊሰረዙ ይችላሉ።
ሌላኛው የቀረበው ማሻሻያ ‘ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የቋሚ ነዋሪ ቪዛን’ ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት ከማቅረብ ጋር አገናኝቶታል። በተጨማሪም
ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የተፈጸሙ የሐሰት ጋብቻዎች ላይም ቁጥጥር እንደሚያደርጉም ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል።
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በአገሪቷ በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ መጤ ጠል (ዜኖፎቢክ) ጥቃቶች በአብዛኛው ዒላማ ያደረጉት በአፓርታይድ ወቅት ጥቁሮች ተገልለው
እንዲኖሩ በተደረጉባቸው ‘ታውንሺፕ’ በመባል በሚጠሩት የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ሱቆች ላይ ነው።
እነዚህ መደበኛ ያልሆኑ ሱቆች ‘ስፓዛ’ የሚሰኙ ሲሆኑ፣ ባለቤቶቻቸውም አብዛኛውን ጊዜ የውጭ አገር ስደተኞች ናቸው። እነዚህን ሱቆች
ከሌሎች የችርቻሮ መሸጫ ቦታዎች ጋር በተመሳሳይ መንገድ እንዲሠሩ ለማድረግ የአገሪቱ መንግሥት ጥብቅ ደንቦችን ሊያወጣ ነው።
እነዚህ ሱቆች በየከተሞቹ ማዘጋጃ ቤቶች መመዝገብ እንዲሁም የባለቤቶቻቸው የስደት ሁኔታም ሊታወቅ ይገባል ይላል አዲሱ ደንብ።
ባለቤቶቹ ሰነድ አልባ ሆነው ከተገኙ ሱቆቹ ይዘጋሉ። ነገር ግን ትክክለኛ ሰነዶች ካሏቸው ግብር መክፈል እና በአገሪቱ የጤና እና የደኅንነት
ሕጎች ሊተዳደሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶ፤ በእነዚህ ሱቆች ምግብ ማብሰል፣ መተኛትም ሆነ ጸሎት ማድረግን ይከለክላል።
አዲሱ የመተዳደሪያ ደንብ እነዚህ ሱቆች የት አካባቢ ሊከፈቱ እንደሚገባ የሚደነግግ ሲሆን፣ የአገሪቱ ባህላዊ መሪዎች ማኅበረሰቡ በጋራ
በያዛቸው መሬቶች ላይ እንዲተዳደሩ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱም አስፍሯል።

You might also like