መዝሙር ክፍል ፪

You might also like

Download as pdf or txt
Download as pdf or txt
You are on page 1of 9

መዝሙር በመጽሏፍ ቅደስ

በመጽሏፍ ቅደስ የመዝሙር ታሪክ ከጥንት ጀምሮ ከእምነት ታሪክ ጋር አብሮ ተተርኳሌ፡፡
ከመጽሏፍ ቅደስም ውስጥ አንደ መጽሏፍ መጽሏፈ መዝሙር ነው፡፡ ይኸውም መዝሙረ
ዲዊት የሚባሇው ነው፡፡ መዝሙረ ዲዊት የተባሇው መጽሏፍ በውስጡ ከያዛቸው 150 ያህሌ
መዝሙሮች ብዙዎቹ (82ቱ) በዘማሪነት የሚታወቀው የቅደስ ዲዊት መዝሙራት ስሇሆኑ
ነው እንጂ በመጽሏፉ ውስጥ በላልች መዘምራን (ቆሬ፣ አሳፍ፣ ኤማንና፣ ሏጌ ዘካርያስ…)
ስም የተጠቀሱ መዝሙሮች ይዟሌ፡፡ በላልች የመጽሏፍ ቅደስ ክፍልች ብዙ የእምነት
ሰዎች በየምክንያቱ የዘመረቻቸው መዝሙሮች ከታሪኩ ጋር ተመዝግበው ታሪክ
እንዯሚከተሇው እናያሇን፡፡

በብለይ ኪዲን

ሀ) እስራኤሊውያን ከግብፅ ሲወጡ የዘመሩት መዝሙር

እግዚአብሔር በበረታች ክንዴ ከግብፅ ምዴር በከባርነት ቤት በሙሴ አማካይነት


እስራኤሊውያንን ነጻ ካወጣቸው በኋሊ ታሊቁን የእግዚአብሔርን ማዲን አዩ፡፡ ይኸውም
ሕዝቡን እስራኤሌን ባሕረ ኤርትራን ከፍል ቢብስ ካሻገረ በኋሊ የሚያሳዴዶቸውን
ግብፃውያንን ፈርኦንና ሠራዊቱን ፈረሱንና ፈረሰኞችን እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ
ጣሊቸው፡፡ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ አመኑ፡፡ (ዘጸ
14፡26-31) በዚያን ጊዜም ባሕሩን ከተሻገሩ በኋሊ ሙሴና የእስራኤሌ ሌጆች «bKBR kF
kF BÉaL³ lAGz^aBh_R እዘምራሇሁ» bìlT rJM mZmƒR zMr§L¥¥
ymƒs_³ yaÅN AUT nB‡t> ìR¶M kl_É{ s_Ä{ ¬R bmÒN YUNn& mZmƒR
bkbÅ Ayzmr{ mL±§l{¥¥ (z; 15¥1-21)

mƒs_ yHZB mÞ ÒÑ ±l kHZB ¬R AGz^aBh_RN amsgn¥¥ ºr_M b^ÒN


ታሊሊቆችም ታናናሾችም እግዚአብሔርን ሉያመሰግኑት ይገባቸዋሌ፡፡ (ራዕይ 19፡5) የአገር
ሽማግላ፣ አገረ ገዢ፣ የሕዝብ መሪ መሆን ከመዘመር ሉሇይ አይችሌም፡፡ ማርያምና
ላልችም ሴቶች በክብር መዝሙሩን መዘመራቸው ምስጋና በጾታም የማይገዯብ መሆኑን
ያሳየናሌ፡፡ ሴቶችም ቢሆኑ በሕዝብ ጉባኤ በአዯባባይ በከበሮ በሽብሸባ በጭብጨባ በእሌሌታ
እያዯመቁ ያሇፍርሃት መዘመር ይገባቸዋሌ፡፡ (መዝ 67፡25) እስራኤሊውያን የዘመሩት
መዝሙር ባሕሩን ከፍል ባሻገራቸው ጊዜ ያሳየውን የማዲን ኃይሌ እያወሳ እግዚአብሔርን
የሚያመሰግን ነው፡፡ ዛሬም ቢሆን በመዴኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሌ የኃጢያትና
የሞት ባሕር ተከፍል ዱያብልስም ወዯ ትሌቅ የእሳት ባሕር የተሻገረበትና እኛ የዲንበት ጊዜ
ነው፡፡ ከዚህም በሊይ እግዚአብሔርን ካመሇክነው ከፍ ከፍ ካዯረግንና ካከበርነው በኋሊ
ባዯረገሌን ነገር ምክንያት ዯግሞ እግዚአብሔርን ሌናመሰግን ይገባናሌ፡፡

ሇ) እግዚአብሔር ሇሙሴ የሰጠው የምስክር መዝሙር

ይህች መዝሙር ሙሴ የሚሞትበት ጊዜ ሲቃረብ እግዚአብሔር በእስራኤሌ ሌጆች ሊይ


ወዯፊት ምስክር እንዴትሆን የተሰጣት መዝሙር ናት፡፡ ከሙሴ በኋሊ ሕዝቡን በመሪነት
የሚረከበው ኢያሱ ከሙሴ ጋር በመገናኛው ዴንኳን ውስጥ አብረው እንዱቆሙ ከተዯረገ
በኋሊ ወዯፉት ሕዝቡ ላልች አማሌክትን ሲከተሌ ምስክር ትሆን ዘንዴ ይህችን መዝሙር
እንዱጽፍና ሇሕዝቡ እንዱያስተምሩ ተዯረገ፡፡ (ዘዲ 31፡14-30) ይህች መዝሙር የምስክር
መዝሙር ብቻ ሳይሆን የትምህርትና የመታሰቢያ መዝሙርም ናት፡፡ ላልች አማሌክት
ሲከተለ ከዚህች መዝሙር ትምህርት አግኝተው እንዱመሇሱና የቀዯሙትን እውነተኛ
የእምነት አባቶቻችንና መሪዎቻችን እንዱያስታውሱ እንዱያስቡ ታዯርጋቸዋሇች፡፡

መዝሙር እግዚአብሔር የሚመሰገንት ግጥምና ዜማ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርም ሇሕዝቡ


በከንፈሩ የሚተውሇት መሌዕክትና ትምህርት መሆኑን ከዚህ እንረዲሇን፡፡ ስሇዚህ ዛሬም
ቢሆን በተሇያየ ምክንያት አገር በመቀየር፣ በሞት … አገሌግልታችንን የምናጠናቅቅ ከሆነ
በሕዝቡ የሚቀር መታሰቢያና ትምህርት እንዱሁም ምስክር የሚሆን መሌዕክት ያሇው
መዝሙር ማስተማር ይገባናሌ፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑም ቢሆን ከጥንት ጀምሮ በተሇያዩ አባቶች
የተጻፉሇትን መሌዕክት አዘሌ መዝሙሮች እያስተዋሇ ተምሮ በማጥናት ሉመከርበት
ሉገሇጽበትና ሉሇወጥበት ይገባሌ፡፡

ሏ) በዘመነ መሳፍንት ነቢያት ዱቦራና ባርቅ የዘመሩት መዝሙር (መ.መሳ 5)

መዝሙር በዘመነ መሳፍንትም እግዚአብሔር የሚከበርበትና የሚመሰገንት መንገዴ ነበር፡፡


ነቢያት ዱቦራና ባርቅ በዘመነ መሳፍንት ሇአራተኛ ጊዜ በእስራኤሌ መስፍን የነበሩ ናቸው፡፡
እንዯሚታወቀው በዘመነ መሳፍንት በእስራኤሌ የነበረው መንግሥት መንግሥተ
እግዚአብሔር ስሇነበር እግዚአብሔር ሕዝቡን በቅርብ የሚረዲበት ዘመን ነበር፡፡ ሕዝቡም
ስሇሚዯረግሊቸው ነገር ያመሰግኑታሌ፡፡ በነቢዪት ዱቦራና ባርቅ ዘመን በአሶር የነገሰው
የከንዓን ንጉሥ ኢያቢስ ሃያ አመት በሊይ እስራኤሌን ባስጨነቀ ጊዜ እስራኤሌ ወዯ
እስራኤሌ ወዯ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ ነቢዪት ዱቦራ ባርቅን አስነስታ ከአሥር ሺህ ሰዎች
ጋር ወዯ ታቦር ተራራ አብራው ወጣች፡፡ የኢያቢስ ሠራዊት አሇቃ ሲሳራ ከነሠራዊቱ
በተንቀሳቀሰ ጊዜ እግዚአብሔር በባርቅ ፊት ወጣ፡፡ ሲሳራና ሠራዊቱ ዴሌ ተመቱ፡፡ (መ.ማ
4፡1-24)
ከዚህ በኋሊ ዱቦራና ባርቅ ሇእግዚአብሔር ክብር እየተቀኙ ዘምረዋሌ፡፡ ይኸው በመጽሏፈ
መሳፍንት ምዕራፍ አምስት ሊይ የሚገኘው መዝሙር ነው፡፡ ሲዘምሩም «እኔስ
ሇእግዚአብሔር እቀኛሇሁ ሇእስራኤሌ አምሊክ እዘምራሇሁ» (መ.ማ 5፡3) በማሇት ሲሆን
የዯረሰባቸውን መከራ በማስታወስ አሁን ዯግሞ ባገኙት ዴሌ እግዚአብሔርን በማመስገን
ነው፡፡

ዛሬም ቢሆን በችግርና በጭንቅ ጊዜ ወዯ እግዚአብሔር መጮኽ ይገባናሌ፡፡ ጩኸታችንንም


በመዝሙር ሌንገሌት እንችሊሇን፡፡ (መዝ 119፡1) እግዚአብሔርም ይሰማናሌ
ይዯርስሌንማሌ፡፡ ታዴያ በመከራና በጭንቅ ጊዜ የሌቅሶ ቅኔ እየተቀኘን ያስታውስነውንና
የሇመነውን አምሊክና አባት በዴሌ ጊዜ በዯስታ ሌንዘነጋው አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር ኃይሌ
ባገኘነው ዴሌ ራሳችንን ማመስገን የሇብንም፡፡ በተሇይም የእግዚአብሔርን ሕዝብ የምናገሇግሌ
ሰዎች እግዚአብሔርን በሕዝቡ ውስጥ በዴሌ ስናየው በመቀኘትና በመዘመር ሌናመሰግነው
ይገባሌ፡፡ መዝሙራችንም ያሇፈውንና የአሁኑን፤ መከራውንና ዴለን የሚያስታውስ ሉሆን
ይገባሌ፡፡ እግዚአብሔር ሇዴሌ በዴሌ የተገሇጠባቸውን ሰዎችን ስም በመዝሙራችን ውስጥ
ማንሳት እንችሊሇን፡፡ ሇምሳላ በዚህ መዝሙር ውስጥ የዱቦራ፣ የባርቅ፣ የዛብልንና
የንፍታላም ነገዴ የሄሇር ሚስት ኢያኤሌ ተጠቅሰዋሌ፡፡ (መ. መሳ 5፡1፤ 5፡18፤ 5፡24)
እንዱህም ከሆነ በተሇይም በአዱስ ኪዲን በሰይጣን ሊይ ሇተገኘው ዴሌ እግዚአብሔር መሳሪያ
ያዯረጋቸውን ቅደሳን በመዝሙራችን ማንሳት ያስፈሌጋሌ፡፡ ዯግሞ በግሌና በማኅበር
በዯረሰብን መከራና ጭንቀት እግዚአብሔር ዴሌን ሲሰጠን በመሳሪያነት የተገሇጠባቸውን
እያወሱ መዘመር ምስጋናችንን በበሇጠ ያከብረዋሌ ያዯምቀዋሌም፡፡

መ) መዝሙር በዘመነ ነገሥት

በእስራኤሊውያን ዘንዴ መዝሙር በተዯራጀ ሁኔታ በመዘምራንና በዜማ ዕቃዎች በዕሇተ


ሰንበትና በተሇዩ በዓሊት ይዘመር የነበረው በዘመነ ነገሥት እንዯሆነ መጻሕፍተ ነገሥትን
ስናነብ እንረዲሇን፡፡ ከመዯበኛው የመዝሙር አገሌግልት ውጪም በተሇያዩ ምክንያቶች
ሇእግዚአብሔር ክብር ይዘመር ነበር፡፡ አሁን በመጠኑ የምንመሇከተው በሚከተለት አራት
ነገሥታት ዘመን በመጽሏፍ ቅደስ ውስጥ የተገሇጸሌንን የመዝሙር ታሪክ ይሆናሌ፡፡

1. በዲዊት 2. በሰልሞን 3. በኢዮሳፈጥ 4. በሕዝቅያስ


1. መዝሙር በዲዊት ዘመን
ቅደስ ዲዊት የሚታወቀው በንጉሥነቱ ብቻ ሳይሆን በዘማሪነቱም ጭምር ነው፡፡ በመጽሏፍ
ቅደስ ውስጥ ያሇው የመዝሙር መጽሏፍ በስሙ ተሰይሟሌ፡፡ ከመዝሙሮቹ ውስጥ
በሰማንያ ሁሇቱ ሊይ የእርሱ ስም ተጠቅሷሌ፡፡ ሌበ አምሊክ የተባሇው ቅደስ ዲዊት በገና
በመዯርዯር መዝሙር የጀመረው ከንጉሥነቱ በፊት ነው፡፡ ወዯ ሳኦሌ ቤተመንግሥት
እንዱገባ መሠረታዊ ምክንያት የሆነው ይኸው በገና የመዯርዯር ችልታው ነበር፡፡ በሳሙኤሌ
እጅ ሇንጉሥነት ከተቀባ በኋሊ በዲዊት ሊይ መንፈሰ እግዚአብሔር ሲያዴርበት በሳኦሌ ሊይ
ግን ክፉ መንፈስ አዯረበት፡፡ ስሇዚህ ክፉ መንፈስ እንዱርቅሇት ባሪያዎቹ ባቀረቡሇት ሃሳብ
መሠረት ሳኦሌ ዲዊትን አስመጥቶ በገና እንዱዯረዴርሇት አዯረገ፡፡ ክፉው መንፈስም ከሳኦሌ
እንዱርቅሇት አዯረገ፡፡ ክፉው መንፈስም ከሳኦሌ ራቀ ዲዊትም በሳኦሌ ፊት ሞገስን ስሊገኘ
ጋሻ ጃግሬ ሆነ፡፡ (1ኛ ሳሙ 16፡14-23) ነገር ግን ሳኦሌ እግዚአብሔር ከዲዊት ጋር እንዯሆነ
ሲያውቅ ፈራው፡፡ ብዙ ጊዜ ሉገዴሇው ፈሇገ፡፡ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ዴረስ ሇዲዊት ጠሊት
ሆኖ ቀረ፡፡ እግዚአብሔርም ግን ከሳኦሌና ከጠሊቶቹ ሁለ እጅ አዲነው፡፡ ይህን በተመሇከተ
2ኛ ሳሙ 22፡1-51 ያሇውን መዝሙር ዘምሯሌ፡፡

ዲዊት በእስራኤሌ ሊይ ከነገሰ በኋሊ በኤሉ ዘመን መጨረሻ ሊይ የተማረከው የእግዚአብሔር


ታቦት ከአሚናዲብ ቤት ተመሌሶ እንዱመጣ ባዲረገ ጊዜ ከእስራኤሌ ቤት ጋር በሙለ ኃይለ
ይዘምር ነበር፡፡ ይህንንም ሲገሌጽ «ዲዊትና የእስራኤሌ ቤት ሁለ በቅኔና በበገና በመሰንቆም
በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽሌ በእግዚአብሔር ፊት በሙለ ኃይሊቸው ይጫወቱ ነበር»
ይሊሌ፡፡ (2ኛ ሳሙ 6፡5) ከዚያም በአቢዲራም ቤት ሦስት ወር ከተቀመጠ በኋሊ ታቦቱ ወዯ
ዲዊት ከተማ ሲመጣ በብዙ ክብር ነበር፡፡ ዲዊትም በሙለ ኃይለ በእግዚአብሔር ፊት
ይዘፍን ነበር፡፡ የእስራኤሌ ቤትም ሆነ እያሱ ቀንዯ መሇከት እየነፋ እግኢአብሔርን
አክብረዋሌ፡፡ የሳኦሌ ሌጅ ሜሌኮሌ ግን ዲዊትን በእግዚአብሔር ፊት በሙለ ኃይለ ሲዘሌና
ሲዘፍን ባየችው ጊዜ በሌብዋ ናቀችው በቃሌዋም ተናገረችው፡፡ እርሱ ግን «በእግዚአብሔር
ፊት እጫወታሇሁ» ብል ሳያፍር ተናግራት፡፡ እርሷም እስከ ሞተች ቀን ዴረስ ሌጅ
አሌወሇዯችም፡፡ (2ኛ ሳሙ 6፡16-23)

ቅደስ ዲዊት በተከሇው ዴንኳን ውስጥ የሚያገሇግለ ሦስት መዘምራን አዯራጅቷሌ፡፡


የአቆችም ስም ኤማን፣ አሳፍ እና አይታም ነበር፡፡ ሇነዚም ከናንያ የሚባሌ የመዝሙር
(የዜማ) አስተማሪ ነበራቸው፡፡ አገሌግልታቸውም በተራ በሰልሞን ነበር፡፡ ዲዊት በአጠቃሊይ
288 መዘምራን ነበሩት፡፡ ዲዊትም በአዯባባይ ሳይውሌ ከእነርሱም ጋር እየተገኘ ይዘመር
ነበር፡፡ (1ኛ ዜና 15፡16-24፣ 1ኛ ዜና 25፡1-10)
ዛሬም ቢሆን እንዯ ቅደስ ዲዊት ሁሇገብ የሆነ የመዝሙር ሰው መሆን ይገባሌ፡፡ ቅደስ
ዲዊት በገና ይዯረዴር ነበር፤ እየተቀኘም ይዘምር ነበር፡፡ ከዚህም የምንረዲው ከመዝሙር
ጋር የዜማ መሳሪያዎችን የመምታት ችልታ ሉኖረን ያስፈሌጋሌ፡፡ በየጊዜውም በመቀኘትና
በመዘመር እግዚአብሔርን እንዴናመሰግን ሇላልችም ሰዎች እንዴንተርፍ ይገባሌ፡፡
የእግዚአብሔር ቃሌ «ተቀኙሇት ዘመሩሇት» ይሊሌ፡፡ (1ኛ ዜና 16፡9) በዚህም እግዚአብሔር
የሚመሰገንበት ብቻ ይሆን ዘንዴ ይባሌ፡፡ ያም ከሆነ ሊመስጋኙ እንዯ ሳኦሌ የክፋት መንፈስ
እንዲያዴርበት ክፉ መንፈስን ያርቅሇታሌ፡፡

ዲዊት ከንጉሥነቱ በፊት ብቻ ሳይሆን በሹመቱና በንጉሥነቱም እያሇ ሇእግዚአብሔር


ዘምሯሌ፡፡ በግለ ብቻ ሳይሆን ከመዘምራኑ ጋር በቤቱም ብቻ ሳይሆን በአዯባባዩ
እግዚአብሔርን በመዝሙር አክብሯሌ፡፡ እኛም በሕጻንነታችን ሇእግዚአብሔር የመዘመር
ፍቅር የነበረንን ያህሌ በእዴሜ ከፍ ብንሌም ሥራ ብንይዝም ትዲር ብንመሰርትም ሹመትና
ሥሌጣን ብናገኝም የዚህ ሁለ ባሇቤት የሆነውንና ሇዚህ ያበቃንን ሌዑሌ አምሊክ በግሌና
በሕዝብ ፊት ሌናመሰግነውና በሙለ ኃይሊችን ሌናሸበሽብሇት ይገባሌ፡፡ በዲር ሆኖ
የሚዘምሩትን መናቅ እና መተቸት ግን እንዯ ሜሌኮሌ መሆን ነው፡፡ እግዚብሔር
የሚንቁትን ይንቃቸዋሌ የሚስቁትንም ይስቅባቸዋሌ ዯግሞም ይቀጣቸዋሌ፡፡ ስሇዚህ
በተሇይም ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ስሙ የተጻፈበት ጽሊት ወጥቶ እግዚአብሔር በሚከብርበት
በዓሇ ንግሥ ሊይ እግዚአብሔርን ከማመስገን ጋር ሳናፍር እምነታችንን ሌንመሰክር
ያስፈሌጋሌ፡፡

ከዚህም ላሊ የበዓሌ ቀን ዘማሪዎች ብቻ ሌንሆን አይገባም፡፡ ያ ከሆነ ሇተርዕዮ (ሇታይታ)


ብቻ ይሆናሌ ማሇት ነው፡፡ ስሇዚህ ቅደስ ዲዊት እንዲዯራጃቸው መዘምራን በሁሇት በሦስት
ቡዴን ከዚያም በሊይ ተዯራጅተን በሰንበት ትምህርት ቤትና በቤተክርስትያን በየሳምንቱ
በየተራ ቋሚ የመዝሙር አገሌግልት ሌንሰጥ ያስፈሌጋሌ፡፡

2) መዝሙር በሰልሞን ዘመን

ከዲዊት ጀምሮ በተዯራጁ መዘምራን የተጀመረው የመዝሙር አገሌግልት እንዯቀጠሇ ነው፡፡


በሰልሞን ዘመን በበሇጠና በተሻሻሇ ሁኔታ ይዘመር ነበር፡፡ አሁን በዚህ ርዕስ የምናየው ግን
በንጉሥ ሰልሞን ቤተመቅዯሱን ሠርቶ በጨረሰ ጊዜ እንዳት እንዯተዘመረ ይሆናሌ፡፡

የቤተ መቅዯሱ ሥራ እንዯተጨረሰ የእግዚአብሔር ታቦት በካህናት አማካይነት ወዯ ቅደሳኑ


እንዱገባ ተዯረገ፡፡ በዚህ ጊዜ በሰልሞን ሳይከፈለ ሦስቱንም ቡዴን መዘምራን ጥሩ በፍታ
ሇብሰው በጸናጽሌ በበገና በመሰንቆ በዜማ ዕቃ ሁለ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡
የሚዘምሩትም «እግዚአብሔር ቸር ነውና ምህረቱም ሇዘሇዓሇም ነውና እግዚአብሔርን
አመስግኑ» የሚሌ መዝሙር ነበር፡፡ ሇዴምቀቱም ካህናት መሇከት ይነፉ ነበር፡፡
የእግዚአብሔርም በክብር በዯመና ተገሌጦ ቤቱን ሞሊው፡፡ (2ኛ ዜና 5፡11-14)

ከዚህ በኋሊ ሰልሞን ረዘም ያሇ ጸልት አዴርጎ የሚቃጠሌ መስዋዕት ቀረበና ሕዝቡና ካህናቱ
ንጉሡም እግዚአብሔርን በመዝሙር አመሰገኑ፡፡ ላዋውያን የዘመሩትም «ምህረቱ ሇዘሊሇም
ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑት» የሚሇውን የዲዊትን መዝሙር ሲሆን የዘመሩትም
ንጉሥ ዲዊት እግዚአብሔርን ሇማስገን የሠራውን የእግዚአብሔርን የዜማ ዕቃ በመጠቀም
ነበር፡፡ (2ኛ ዜና 7፡4-7)

ዛሬም ቢሆን የቤተክርስቲያን ቅደስ ቤት ሲከበርም ሆነ ማንኛውም በዓሌ ሲከበር ሁለም


መዘምራን ዩኒፎርም ሇብሰው መዘመር ይገባቸዋሌ እንጂ እንዯ ዘወትር አገሌግልት ተራ
(ሰሞን) መጠበቅ አያስፈሌጋቸውም፡፡ ሕዝቡም ከመዘምራኑ ጋር በተሇዩ የዜማ ዕቃዎች
እያዯመቀ እግዚአብሔርን ማመስገን አሇበት፡፡

3) መዝሙር በኢዮሳፍጥ ዘመን

በአራተኛው የይሁዲ ንጉሥ በኢዮሳፍጥ ዘመን እግዚአብሔር ሇእስራኤሊውያን


በመዝሙራቸው ተገሌጦ ጠሊቶቻቸውን እንዲሸነፈሊቸው ተመዝግቧሌ፡፡ የሞዓብና የአሞን
ሌጆች ከእነርሱን ጋር ሞአባውያን ኢዮሳፍጥን ሉወጉ በመጡ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ከሕዝቡ ጋር
ሆኖ የእግዚአብሔርን ኃይሌ በጾምና በጸልት ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም መንፈሱን በሕዝቅኤሌ
ሊይ ገሌጾ ሰሌፉ የእግዚአብሔር ስሇሆነ እነርሱም ዝም ብሇው በመቆም የእግዚአብሔርን
መዴኃኒት እንዱያዩ እንዲይፈሩና እንዲይዯናገጡ ተናገራቸውም፡፡ ማሌዯውም በመነሳት
ከሕዝቡና ከሠራዊቱ ፊት መዘምራንን በእምነት አቆሙ፡፡ መዘምራኑም ጌጠኛ ሌብስ
ሇብሰው ነበር፡፡ እነርሱም «ምህረቱ ሇዘሊሇም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ» የሚሇውን
መዝሙር ገና ሲጀምሩ እግዚአብሔር ሉወጉዋቸው በመጡት ሊይ ዴብቅ ጦርን አመጣባቸው
እነርሱም ተመቱ፡፡ ከዚህ ዴሌ በኋሊ ይሁዲና የኢየሩሳላም ሰዎች በፊታቸውም ኢዮሳፍጥ
ዯስ እያሊቸው በበገና በመሰንቆ በመሇከትም ወዯ እግዚአብሔር ቤት ገቡ፡፡ (2ኛ ዜና 10፡1-
30)

ዛሬ ግን ምዴራዊ የሆነ የእግዚአብሔር ሰሌፍ አናይም፡፡ ብዙዎች ሰሌፈኞች በሽሇሊ በፉከራ


በዘፈን የሚገሌጹት የራሳቸውን ኃይሌ እንጂ የእግዚአብሔርን ኃይሌ አይዯሇም፡፡
ክርስትያኖች ግን ቅደስ ጳውልስ እንዯገሇጸሌን ከሰይጣንና ከሠራዊቱ ጋር በምናዯርገው
ሰማያዊ ሰሌፍ (ጦርነት) ውስጥ በራሳችን ጥበብና ኃይሌ ሳይሆን በመዝሙራችን
የእግዚአብሔርን ኃይሌ በመግሇጥ ሌንዋጋውና ሌናሸንፈው እንችሊሇን፡፡ ከዴሌ በኋሊም ዯስ
ብልን እየዘመርን በቤቱ እግዚአብሔርን ሌናመሰግን ይገባሌ፡፡ መዝሙራችንም ጌጠኛ ሌብስ
በሇበሱ መዘምራን ሉመራ እንዯሚገባ ከዚህ ታሪክ እንረዲሇን፡፡

4) መዝሙር በሕዝቅያስ ዘመን

ሕዝቅያስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ካህናቱንና ላዋውያንን ሰብስቦ የእግዚአብሔር ቤት


እንዱታዯስ አዯረገ፡፡ ካህናቱንና ላዋውያኑን የእግዚአብሔርን ቤት ካነጹትና ከቀዯሱት በኋሊ
ሕዝቅያስ የተሇያየ ዓይነት መስዋዕት እንዱቀርብ አዯረገ፡፡ ይህ መስዋዕት ሲቀርብ መዝሙር
እየተዘመረ ነበር፡፡ ሕዝቅያስ ጸናጽሌና በገና መሰንቆም አስይዞ መዘምራን አቆመ
መስዋዕቱም ማረግ በጀመረ ጊዜ በእነዚህ የዜማ መሳሪዎች ታጅቦ የእግዚአብሔር መዝሙር
ተጀመረ፡፡ ሕዝቡ እየሰገዯ መሇከት እየነፋ በመዘመር መስዋዕቱን አቅርበው ሲጨርሱ ንጉሡ
ሕዝቅያስና አሇቆች በዲዊትና በአሊፍ መዝሙሮች እግዚአብሔር እንዱመሰገን አዯረጉ ሁለም
በዯስታ አመስግኑ፡፡

እኛም ዛሬ በስእሇታችን፣ በስግዯታችን፣ በምጽዋታችን፣ በጾማችን፣ በሌግስናችን …


የምናቀርበው መስዋዕት ሁለ እግዚአብሔርን በዝማሬ እያመሰገንን ሌናቀርብ ያስፈሌጋሌ፡፡
ሰዎች ራሳቸውን ከቀዯሱና ካቀረቡ በኋሊ የእግዚአብሔር መሆናቸውን የሚገሌጹ ሇስሙ
በመዘመራቸው ነው፡፡ ከዚህ ታሪክ እንዲየነው የቤተ መቅዯስ መታዴስ የሰዎችን መታዯስ
ያሳያሌ ከዚያ በፊት ያረከሱት ሰዎች ነበሩና፡፡ ይህንንም የገሇጡት በመዝሙርና በመስዋዕት
ነው፡፡ የዘመሩትም ቀዴሞ በዲዊት ዘመን የነበረውን ሥርዓተ መዝሙር ሌንከተሌ ይገባሌ፡፡
እንዯቀዴሞ አባቶች በገና በመዯርዯር ጸናጽሌና መሰንቆ በመምታት መሇከት በመንፋት
የተዘነጋውን የዲዊትን መዝሙር ሌናዲብር ይገባሌ፡፡

ሠ) መዝሙር ከባቢልን ምርኮ መሌስ

እስራኤሊውያን በባቢልን ምርኮ በነበሩ ጊዜ በባዕዴ ምዴር በምርኮ አገር መዝሙራቸውን


እንዲሌዘመሩ መጽሏፍ ቅደስ ያስረዲናሌ፡፡ (መዝ 136፡1-5) ከባቢልን ምርኮ መሌስ ግን
ሁሇት መቶ ወንድችና ሴቶች መዘምራን ነበሩ፡፡ (ዕዝራ 2፡65) በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ
ትእዛዝና ፍቃዴ መሠረት ፈርሶ በነበረው የሰልሞን ቤተ መቅዯስ ምትክ በዚያው ቦታ አዱስ
ቤተ መቅዯስ ሇመሥራት አናጢዎች መሠረት ሲጥለ ካህናቱና ላዋውያኑ በቀዴሞው
በንጉሥ ዲዊት ሥርዓት መሠረት ሌብስ ሇብሰው ጸናጽሌ ይዘው መሇከት እየነፉ
እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ የሚዘምሩትም «ቸር ነውና ሇእስራኤሌም ምህረቱ ሇዘሊሇም
ነውና» የሚሇውን በማስተዛዘሌ ነበር፡፡ ሕዝቡም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ዯስ ብሎቸው
በታሊቅ ዴምጽ ያሇቅሱ ነበር፡፡ በአንጻሩም ዯግሞ የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግላዎች በትዝታ
ተወስዯው በታሊቅ ዴምጽ ያሇቅሱ ነበር፡፡ በዚህም የእሌሌታውንና የሇቅሶውን ጩኸት
ሇመሇየት እስከሚያስቸግር ዴረስ በታሊቅ ፍቅር ይዘመር ነበር፡፡ (ዕዝራ 3፡1-13) አንዲንዴ
ፈተናዎችን አሌፎ የቤተ መቅዯሱ ሥራ በተጠናቀቀ ጊዜ ዯግሞ ቅዲሴ ቤቱን በታሊቅ ዯስታ
አክብረዋሌ፡፡ (ዕዝራ 6፡13-18) ከላልች የቤተ መቅዯሱ አገሌጋዮች ጋር መዘምራንም
ከግብርና ከቀረጥ ነጻ ሆነው እንዯ ቀዴሞው ሥርዓት እግዚአብሔርን ያገሇግለ ነበር፡፡

(ዕዝራ 24፣ ነህምያ 11፡22-24)

በላሊ በኩሌ ዯግሞ በነህምያ መሪነት የኢየሩሳላም ቅጥር ከተሠራ በኋሊ ላዋውያኑና
መዘምራኑ ከሰፈሩበት ቦታ ተፈሌገው መጥተው የምረቃውን (የቅዲሴውን) በዓሌ በዯስታና
በምስጋና በመዝሙር አክብረዋሌ፡፡ አጥሩ ከመሠራቱ በፊት መዘምራኑ በኢየሩሳላም
መንዯሮች ሰርተው ነበር፡፡ ከዚያም ተሰብስበው ራሳቸውን ካነጹ በኋሊ አመስጋኞ በሁሇት
ተርታ ተከፈለ፡፡ አንደ በጸሏፊው በዕዝራ መሪነት አንደም በነህምያ መሪነት ቅጥሩን
እየዞሩ በእግዚአብሔር ሰው በዲዊት የዜማ ዕቃ በታሊቅ ዴምጽ ዘምሩ በዚህን ጊዜ
የመዘምራን አሇቃ ይዝረህያ ይባሌ ነበር፡፡ (ነህምያ 12፡ 27-43)

ከባቢልን ምርኮ በኋሊ በአጠቃሊይ የመዝሙር ሁኔታ እንዯቀዴሞው ሥርዓት ቀጥሎሌ፡፡


መዝምራኑም የዲዊትንና የሰልሞንን ትዕዛዝ ጠብቀዋሌ፡፡ ሌክ እንዯ ዲዊት እንዯ አሳፍ
ዘመንም የመዘምራን አሇቆች ነበሩ፡፡ መዘምራኑም በዘሩባቤሌና በነህምያ ዘመን እንዯላልች
አገሌጋዮች ሁለ በየዕሇቱ የሚገባቸውን ዕዴሌ ፈንታ ከእስራኤሊውያን ያገኙ ነበር፡፡ (ነህምያ
12፡44-46) በዚያ ዘመን ከነበሩት ነብያት የሏጌና የዘካርያስ መዝሙሮች በመዝሙረ ዲዊት
ውስጥ ተጠቅሰው ይገኛለ፡፡ (መዝ 145፡ 146-148)

ከዚህም ታሪክ ብዙ ነገሮችን እንገነዘባሇን በባዕዴ እንዯ አሕዛብ የሆኑ ዓሇማውያን ሰዎች
ሉያሾፉበት ሉዝናኑበት እንዴንዘምርሊቸው ቢጠይቁን መታዘዝ የሇብንም፡፡ መዝሙር
ምስጋና እንጂ መዝናኛና መታወቂያም መሆን አይዯሇምና፡፡ በቤተክርስቲያን ሇምናዯርገው
የመዝሙር አገሌግልት ግን ያሇጸታ ገዯብ መዘምራን በመሆን መዘመር እንችሊሇን፡፡ ፈርሶ
የነበረ የሰው ሌጆች ሕይወት፤ ፈርሶ የነበረ ጉባኤ፣ ረርሶ የነበረ ሥርዓት እንዯቀዴሞው
ሲመሇስ ሌክ እንዯ እስራኤሌ ወንደም ሴቱም ሌጆችም በአንዴ ዴምጽ ሌንዘምር ይገባሌ፡፡
ስንዘምርም ፍቅራችን የሚገሇጸው በዯስታ እሌሌ በማሇት ብቻ ሳይሆን በታሊቅ ሌቅሶም
ሉሆን ይችሊሌ፡፡ ከዚህም አንዲንዴ መዝሙሮችን በማስተዛዘሌ (በመቀባበሌ) መዝሙሩ
መጽሏፍ ቅደሳዊ መሆኑን እንረዲሇን፡፡
በሕዝብ ውስጥ ታሊቅ ቦታ የነበራቸው ከመዘምራን ዕዝራ፣ ከባሇሥሌጣን ነህምያ፣ ከነቢያት
ሏጌና ዘካርያስ አብረው ዘምረዋሌ፡፡ ዛሬም እንዱሁ ሉሆን ይገባሌ፡፡ በተሇይም በወንጌሌ
ሥራ ውስጥ መዝሙር ትሌቅ ቦታ ሉሰጠው ይገባሌ ሌክ እንዯ ነህምያ ዘመን በንጽሕና
ሇሚያገሇግለ መዘምራን ሉታሰብሊቸው ሉጸሇይሊቸው ይገባሌ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት በታሊቅ
አገሌግልት የተሰየሙ ናቸውና፡፡

You might also like