Professional Documents
Culture Documents
Aderejajet
Aderejajet
Aderejajet
2024 እ.እ.አ
ጀሙ
ይሁንታ የሚመሰረት ሀገር በቀል የልማት ተቋም ነው፡፡ ማህበሩ የሚቋቋምበትን ዓላማ መሰረት በማድረግ
በትምህርት፣ በጤና፣ በውሃ፣ በመንገድና በማህበረሰብ አቅም ግንባታ ላይ በርካታ ስራዎችን በመስራት ህዝብን
ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ተቋም ነዉ፡፡ በዚህ ሂደት በተለይም በአባላት ማፍራት ረገድ ያለውን ሥራ
ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራትና ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ የአባላት ክፍያ ትኩረት አድርገው መስራት
ለማህበሩ ቀጣይነት ስራ ወሳኝ በመሆኑ በየእርከኑ ባሉ የአባላት ክፍያ ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ይህ
መመሪያ ተዘጋጅተዋል፡፡
በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ የአካባቢው ህዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተቀርፈው መሰረተ ልማት
ተስፋፍተውና ህዝቡ የዘላቂ ልማት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡
የምዕራብ ኦሞ ህዝቦች ልማት ማህበር (ምኦህልማ) ህብተሰቡን በማስተባብር ከአባላት በሚሰበሰብ ገቢና
ፕሮጀክት ቀርፆ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተባብሮ በመስራት በሚገኘዉ ገቢ የአከባቢውን የልማት ክፍተት
በመሙላት የህዝብን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ተልዕኮ አለው፡፡
2.3 ዓላማ
የማህበሩን ገቢ አሁን ካለበት ከምንም ተነስተን ከፍ በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት የማህበረሰቦቻችንን
የልማት ፍላጎት በአፋጣኝና በተሳለጠ መልኩ ምላሽ መስጠት ነው፡፡
2.4. አስፈላጊነት
የውጭ ድጋፍ ሰጭና ረጂ ድርጅቶችን ብቻ ጠብቆ በልማት ጥማት ውስጥ ከመኖር ይልቅ የማህበረሰብ
አቅማችንን በማቀናጀትና ያሉንን ፀጋዎች ወደ ሀብት በመቀየር በርካታ ልማቶችን በማልማት አሁን የታዩ
የእድገት ደረጃዎቻችን ከፍ ለማድረግ ገቢያችን ወሳኝ ሚና ስላለው ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
3. የማህበሩ ገቢ ምንጭ
ከማህበሩ ገቢ ምንጮች አንዱ በአባላት ማፍራት ዘርፍ አማካኝነት የሚሰበሰብ የአባላት መዋጮ ክፊያ ገቢ
ሲሆን ማህበሩ ይህን ሀብት በመሰብሰብ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሁሉም በሚባል ደረጃ በወረዳዎችና
በከተማ አስተዳደር ያከናዉኗል፡፡
4. የተቋምና የአባላት የአባልነት ክፊያ እርከንን ቀመር
መምሪያ ኃላፊዎች በሚመሩት መድረክ 3(ሦስት) አባላት ያሉት ልማትና አባላት ማፍራት ኮሚቴ
በሠራተኛው ሙሉ ድምጽና ተሳትፎ እንዲመረጡና ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
የማህበሩን አባላት በማስተባበር የፋይናንስ ማቴሪያልና የእውቀት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራን ጨምሮ
ፕሮጀክት እስከ ማዘጋጀት የሚደርስ እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡
ተጠሪነትን በተመለከተ ኮሚቴው ለመ/ቤታቸው ኃላፊና ለልማት ማህበሩ ጽ/ቤት ተጠሪነት
ይኖራቸዋል፡፡
9. የግንኑነት ስርዓት
9.1 ወረዳ ልማትና አባላት ማፍራት ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት
የወረዳ ልማትና አባላት ማፍራት ኮሚቴ ተጠርነቱ ለዞን ልማት ማህበር ሥራ አመራር ኃላፊ ሆኖ የሚከተሉት
ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡
የቀበሌ ልማትና አባላት ማፍራት ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለወረዳ ልማትና አባላት ማፍራት ኮሚቴ ሆኖ የሚከተሉት
ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
o የቀበሌው አመታዊ የልማት ዕቅድ መዘጋጀቱን መከታተል ገምግሞ ወደ ስራ ማስገባት
o ፎካል በመደገፍና በማብቃት በየወሩን ስራ አፈጻጸም መገምገምና ግብረ መልስ መስጠት
o ከወረዳ ልማት ማህበር ጋር ግንኙነት በማድረግ የቀበሌውን ሪፖርት በየጊዜው መላኩን ማረጋገጥ
o ፎካሉ በአፈጻጸሙ ልክ ማትጋትና በጉድለቱ ልክ የማረም ስራ በመስራት በእጁ ያለውን የቀበሌዋ
የልማት እድገትና ኃላፊነት በጫንቃቸው ላይ የተጣለባቸው መሆኑን በማወቅ መረባረብ
ይኖርባቸዋል፡፡
9.4 የወረዳ ተወካይ ተግባርና ኃላፊነት
የወረዳ ተወካይ ጣምራ ተጠርነቱ ማለትም በአስተዳደራዊ ጉዳይ ለወረዳ ልማትና አባላት ማፍራት
ኮሚቴና ለዞን ልማት ማህበር ጽ/ቤት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡
የወረዳውን የአባላት ማፍራትና የልማት ዕቅድ አዘጋጅተው የማቅረብ የማስገምገምና ሲፈቀድ ወደ
ተግባር መግባት
ከማህበሩ አባላትና ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ገቢ በማህበሩ ገቢ ደረሰኝ ይሰበስባል ለዞን ምኦህልማ
ጽ/ቤት ቦርድ አካውንት በማስገባት ሪፖርት ያደርጋል፡፡
አቅሙን በመገንባት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አባላትን ለማፍራት ጥረት ማድረግና የልማት ስራዎችን
እንዲተግብሩ መደገፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
በየቀበሌ ያለውን አፈጻጸም በመከታተል ወራዊ ሪፖርት አዘጋጅተው በኮሚቴው ማስገምገም፡፡
በተገቢው መንገድ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት በኮሚቴው ማስገምገምና ለጽ/ቤት ሪፖርት ማድረግ
በአፈጻጸማቸው የተሻሉ ተቋማት፣ ፎካሎችና አደረጃጀቶችን በመለየት እውቅና እንዲያገኙ
ማድረግን ጨምሮ በኮሚቴው የሚሰጡትን ተግባራት በታማኝነትና በትጋት የሚያከናውን ይሆናል፡፡
በየተቋማትና በቀበሌ ያሉ ፎካል ፐርሰኖች በያሉበት አከባቢ የማህበሩን ተልዕኮዎች እንዲሳኩ ርብርብ
ያደርጋሉ ፡፡
የዞንና የወረዳ ሴክተር ፎካሎች የአባላት ማፍራት ስራው በአግባቡ እንዲመራ በማድረግ አባሉ
የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ ስለመሆኑ ከመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጋር በጋራ እየፈተሸና እየገመገመ
ለወረዳ ፎካል ፐርሰን መረጃ ይሰጣሉ
ከተቋሙ ሰራተኞች የአባልነት መዋጮ በማህበሩ የገቢ ደረሰኝ እንዲሰበስብ የዞን ተወካይ ለዞን የወረዳ
ተወካይ ለወረዳ ፋ/ኢ/ል/መ/ጽ/ቤት የአባል ዝርዘር ያስተላልፋል፡፡
የቀበለ ፎካል ፐርሰኖችም በቀበሌው አባላት ማፍራትና በልማት ስራ ዙሪያ ያለውን አፈጻጸም
እያስገመገመ ለወረዳ ሪፖርት በወቅቱ የሚልኩ ይሆናል፡፡
ከአባላትና ከተለያዩ ገቢ ምንጮች ገቢ በማህበሩ የገቢ ደረሰኝ ይሰበስባል ለወረዳው ያስገባል
በቀበሌው በልማት ቡድኖች መካከል ጤናማ የልማትና አባላት ማፍራቱን ስራ በንቅናቄ መንገድ
በፉክክር መንፈስ እንዲፈጸም ይሰራሉ የተሻሉትን እውቅና እንዲያገኙ ያድርጋሉ
በጥቅሉ ይች አጠር ያለች የአደርጃጀት አሰራርና በሰው ሀይል ምደባ ዙሪያ ያለብንን ክፍተት
ለመሙላት የተዘጋጀች ሰነድ በመሆኗ ወደ ተግባር እየተገባ በሚገኝ ተጨማሪ ግብዓት እንደምታዳብሩ
ታሳቢ በማድረግ ለተግባራዊነቱ በጋራ እንዲንረብርብ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
10. የሥራ ባለቤቶችና የባለድርሻዎች ሚና
ጀሙ