Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 2

ቁጥር______________

ቀን_______________

ለ መንገድ ሀብት ማኔጅመንት ም/ዋ/ዳይሬክተር

ኢዲስ አበባ፤

ጉዳዩ፡- በባቱ ከተማ የሚገነባው የብስክሌት መንገድን ይመለከታል፤

እንደሚታወቀው የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በቀን 15/06/2015 ዓ.ም ደብዳቤ ቁጥር
ፅወዳ/1827/15 በፃፉት ደብዳቤ በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ ዋና መንገድ ላይ የብስክሌት መንገድ ለማሰራት
የቦታ ልየታ፤የጨረታ ግዥና ከከተማው መስተዳድር ጋር የጋራ ውይይት ማድረጋቸውንና ለግንባታ ስራው
በዋናነት የኛን ተቋም የሚመለከት መሆኑን በመግለፅ ድጋፍና ትብብር እንድናደርግላቸው ጠይቀውናል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በናንተ በኩል በተሰጠን አቅጣጫ መሰረት ግንባታው ወደሚከናወንበት ቦታ ባለሙያዎችን
በመላክ የመስክ ምልከታ ያደረግንና ከመንገድ ደህንነትና መንገድ ፈንድ አገልግሎት ተወካዮች ጋር ውይይት
አድርገናል፡፡

በመሆኑም የብስክሌት መንገዱ ቢገነባ ሊኖረው የሚችል ጠቀሜታና በመንገዱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን
ችግር ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

የብስክሌት መንገድ ግንባታው ሊኖረው የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖ

- በተለይ በስተግራ በኩል የሚሰራው የብስክሌት መንገድ የእግረኛ መሄጃ መንገድ (Shoulder)
ሙሉ በሙሉ የሚወስድ በመሆኑ ከተማው ላይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ሊያስከትል
ይችላል፤
- በስተቀኝ የሚገነባው የብስክሌት መንገድ ቦታው ላይ ባለው ኮብል ንጣፍ ድንጋይ ላይ የሚገነባ
በመሆኑ በቀጣይ የመፈራረስ ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡
- በብስክሌት መንገዱ ላይ በሚቀመጡት የአበባ ማስቀመጫዎች (Flower Pot) መካከል ክፍተት
ስለሚኖር ህገወጥ ሞተረኞች፤ ባጃጅና መኪኖች እየገቡ አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡

የብስክሌት መንገድ ግንባታው ሊኖረው የሚችለው አዎንታዊ ጥቅም

- በባቱ ከተማ ላይ ከፍተኛ ጭነት ጭነው የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ለረጅምና ለአጭር ጊዜ


እንዳይቆሙ የሚያደርግ ሲሆን ይህም በክብደት ምክንያት በእግረኛ መንገዱ፤በውሃ ቦይ (Ditch)
ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ያደርጋል፤
- በከተማው ላይ ብስክሌት በብዛት የሚንቀሳቀስ ከመሆኑ አንፃር በብስክሌት አሽከርካሪዎች ላይ
አደጋዎች እንዳይከሰቱ ያደርጋል፤
- በመንገዱ ግራ የሚገኘው ዲች ክዳን የሌለው በመሆኑ በዚህ ግንባታ ወቅት ዲች ክዳን (Ditch
Cover) ይገነባለታል፤

የመፍትሔ ሀሳቦች፡-

1. በብስክሌት መንገዱ ግራና ቀኝ ሌሎች ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ በብረት አጥር ማጠር፤


2. በስተቀኝ የሚገነባው የብስክሌት መንገድ ኮብል ድንጋይ (Cobble Stone) በማንሳት በጥሩ
ሁኔታ በአርማታ (Concrete) መገንባት፤
3. በአበባ ማስቀመጫዎች መካከል ያለውን ክፍተት በሰንሰለት እንዲታጠር ማድረግ፤
4. ከአካባቢው መስተዳደር ጋር በመነጋገር በከተማው ላይ የሚቆሙ ተሽከርካሪዎችን ከመንገድ
ወጪ እንዲቆሙ ማድረግ፤

በሌላ በኩል የቀረበው የብስክሌት መሄጃ መንገድ ንድፍ (Drawing) በጥልቀት የተመለከትነው ሲሆን
በኛ በኩል ምንም አይነት ጉድለት ያላገኘንበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር//

ግልባጭ:-

 ፋይል፤

You might also like