Professional Documents
Culture Documents
21
21
የመ/ቁ 165381
በፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ለን/ስ/ላፍቶ ምድብ 2ኛ የውርስ ችሎት
አዲስ አበባ
አመልካች ፦1. አቶ ልዑል ሰገድ ጉደታ ለማ
ተጠሪ ፦ ወ/ሮ የሺ ጋረደው በላይነህ
አመልካች ወላጅ አባቴ የነበሩት አቶ ጉደታ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ባለቤታቸው የነበሩትን ወ/ሮ የሺ
ጋረደውን ተጠሪ በማድረግ በህይወት ዘመኑ ያፈራው ንብረቶች በውርስ ሀብትነት እንዲጣሩልኝ ማመልከቴ የሚታወቅ
ሲሆን ከእነዚህ ንብረቶች መካከል በባንክ ሊገኝ ይችላል የተባለ ገንዘብ ሲሆን በባንክ በሟች ስም ካለ እንዲታገድልኝ ጠይቄ
ዕግድ መቀበሌ ይታወቃል ። ይሁንና በተጠሪ ወይም ባለቤቱ ስም የሚገኝ ገንዘብ ካለም እንዲጣራልኝ ከጠቀስኩት የባንክ
ገንዘብ የሚካተት ወይም የውርስ ገንዘብ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም ተጠሪ በስሟ የሚገኝ ገንዘብ ባለመታገዱ በቀላሉ
ልታሸሸው ትችላለች ። ስለሆነም አመልካች የሟች አባቴ የውርስ ሀብት እንዲጣራልኝ ከጠቀስኩት ንብረቶች መካከል
በባንክ ሊገኝ የሚችል ገንዘብ እንዲሁም አክሲዮን በመሆኑ በተጠሪ ስም በባንክ ገንዘብ እንዲሁም አክሲዮን ካለ በቀላሉ
ገንዘቡን ወጪ በማድረግ ተጠሪ ልታሸሸው ስለምትችል በተጠሪ ስም በዳሽን ባንክ ፣ በብርሃን ባንክ ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
፣ ለንብ ባንክ ፣ ለወጋገን ባንክ ፣ ለዘመን ባንክ ፣ ለአዋሽ ባንክ ፣ ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፣ ለኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
፣ ለደቡብ ግሎባል ባንክ ፣ ለአቢሲኒያ ባንክ ፣ ለእናት ባንክ ፣ ለዓባይ ባንክ ፣ ለቡና ባንክ ፣ ለህብረት ባንክ ፣ ለአንበሳ
ባንክ እና ለአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ የሚገኝ ገንዘብ/የአክሲዮን ገንዘብ የቀረበው የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ ዕልባት
እስኪያገኝ ድረስ ወጪ ሆኖ ክፍያ እንዳይፈፀም የሚያዝ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲሰጠኝ በማለት አመለክታለሁ ።
አመልካች፦
1. አቶ ልዑል ጉደታ ለማ