Professional Documents
Culture Documents
Advanced News
Advanced News
Advanced News
በ ሶስና አለሙ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስድስት ኪሎ ካምፓስ ውስጥ ያሉት መፀዳጃ ቤቶች በአብዛኛው የንፅህና ጉድለትና የአጠቃቀም
ችግር እንዳለባቸው ታወቀ።
መፀዳጃ ቤቶቹ ለተማሪዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የማይችሉና የተበላሹ መሆናቸውንም ለመገንዘብ
ተችሏል።ዝርዝሩን ሶስና አለሙ አዘጋጅታዋለች።
በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ ካሉት መፀዳጃ
ቤቶች መካከል ለተማሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡት አነስተኛ መሆናቸውን እንዲሁም ንፅህናቸው በአግባቡ እየተጠበቀ
እንዳልሆነ ተመልክተናል።
በተማሪዎች የመኝታ አገልግሎትና ቤተመፅሀፍት አካባቢ ያሉትን መፀዳጃ ቤቶች ሄደን የተመለከትናቸው ሲሆን
ለተማሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡት መጸዳጃ ቤቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የንፅህና ጉድለትና የአጠቃቀም ችግር
አስተውለናል።
ከተጠቃሚዎች ባገኘነው መረጃ መሰረትም ተማሪዎች በሚኖሩበት ስፍራ ያሉት መፀዳጃ ቤቶች ከፍተኛ የሆነ
የአጠቃቀም ጉድለትና የውሀ እጥረት እንደዳለባቸው ለማስተዋል ተችሏል።
በመማሪያ ህንፃዎች ላይ ያሉት መፀዳጃ ቤቶችም እቃዎቻቸው ያልታደሱና የተሰበሩ፤ ቧንቧዎቹም አገልግሎት
የማይሰጡ እንዲሁም መጥፎ ጠረን ጭምር ያላቸው መሆኑ ተማሪዎች የሚቸገሩበት ጉዳይ ነው።
በማንዴላና በቢሄቪሪያል ኮሌጆች ላይ የሚታየው የመፀዳጃ ቤት ዕጥረትና ንፅህና ጉድለት ደግሞ ከሁሉም ጎልቶ በይበልጥ
ይታያል።ይህም ለተማሪዎች ከፍተኛ ችግር እንደሆነባቸውና ከማንዴላ ህንፃ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ድረስ ሄደው
ለመጠቀም እንደተገደዱ ገልፀውልናል።
ይህ ለምን ሆነ ስንል የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ፋሲሊቲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዘላለም መላኩን አነጋግረናቸዋል።
በማንዴላ ህንፃ ውስጥ ስለተቆለፈባቸው መፀዳጃ ቤቶች አቶ ዘላለምን ባነሳንላቸው ጥያቄ ላይ በቂ ምላሽ ሳይሰጡ
አልፈዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በተማሪዎች የቤተመፅሀፍት አገልገሎት ህንፃ ላይ መፀዳጃ ቤት አለመኖሩ እንደትልቅ ችግር
ይነሳል።በግቢው ካሉት ሁለት ቤተመፅሀፍት መካከል በአንዱ መፀዳጃ ቤት ቢኖርም ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች
አገልግሎት እንደማይሰጥ ታውቋል።
ለአቶ ዘላለም በድጋሚ ባነሳንላቸው ጥያቄ ስለ ቤተ መጽሐፍቶቹ መፀዳጃ ቤቶች ይህን ብለውናል፡፡
በዲጂታል ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ያሉት መፀዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ክፍት እንዲሆን ታዞ ሳለ ለምን አገልግሎት
አልሰጡም ብለን በዲጂታል ቤተ መጽሐፍት የህግ ክፍል ሀላፊ የሆኑትን አቶ ወልደኪዳን ለማን ጠይቀናቸዋል ፡፡
የፅዳት ሠራተኞችም አብዛኛዎቹ በትጋት ስራቸውን ቢያከናውኑም ልክ እንዲሁ ደግሞ ስራቸውን በቸልተኝነት
የሚያልፉ መኖራቸውን ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል ለመረዳት ችለናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪዎች ላይ በራሱ የአጠቃቀም ችግር በሰፊው እንደሚስተዋል እኛም በቦታው ተገኝተን
ለመመልከት ችለናል፡፡
በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ መፀዳጃ ቤቶች የንፅህናቸው ችግር እንዲቀረፍና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ
አገልግሎት እንዲሰጥ መንግስት ተገቢውን በጀት በተገቢው ቦታ እንዲያከፋፍልና የአስተዳደር ሠራተኞችም ጉድለቱን
በየጊዜው በመፈተሽ ቸልተኛ የፅዳት ሠራተኞችንም እንዲሁ በመቆጣጠር ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው
ከወዲሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
ለዛሬ የያዝነው የዜና ትንታኔ ያደመጣቹትን ይመስል ነበር፡፡ በሌላ የዜና ትንታኔ እስከምንገናኝ ቸር ሰንብቱ፡፡
###