Gospel For...

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 25

ወንጌል ለአብርሃም እና በአብርሃም በኩል ተሰብኳል

አብርሃም በቁርአንም በመጽሐፍ ቅዱስም ውሳኝ ቦታ አለው። እግዚአብሔር


ለአብርሃም «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ»(surah 2:124) ብሎ እንደነገረው
በቁራን ተጽፏል። ዘፍጥረት 22: 18 ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም "የምድር ሕዝቦች
ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ” ብሎ ቃል ገብቶለታል።

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃልኪዳን

እግዚአብሔር ለአብርሃም “እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት


ትሆናለህ።"(ዘፍ 17:4) ብሎ ነግሮታል። አብርሃምም ለሰው ልጆች ሁሉ በረከት፥
ለአህዛብም አባት የተደረገበትን ምክንያት ተረዳ። ስለዚህ አብርሃም በእግዚአብሔር
መመረጡን እና ከፍ ባለ ስፍራ መቀመጡን የእግዚአብሔር ታላቅ ሰማያዊ ክብር
ነጸብራቅ እንደሆነ አድርጎ ቆጠረ። አብርሃም የእግዚአብሔር አይነተኛ ሰዋዊ ምሳሌ
በመሆን ከሰማዩ አባት ጋር እንደተመሳሰለ አስተዋለ።

አብርሃም የይሰሀቅን ተዓምራዊ ልደት፥ መስዋዕትነት እና ከሞት መነሳት፥ እንዲሁም


እንደ አሸዋ ይበዛል ተብሎ ቃል የተገባለትን የትውልድ ዘር ገና ሊመጣ ያለ ታላቅ
እውነታ እንደሆነ አድርጎ እንደቆጠረም ማወቅ ይቻላል።

አብርሃም ስለ ታላቁ-መስዋዕትነት መልካም ዜና ቀድሞ አይቶ ነበር

ሰማያዊው አባት ተአምራዊ በሆነ መንገድ ወደዚች ምድር ልጅ እንዲወለድ


እንደሚያደርግ አብርሃም ተገንዝቧል። ከዚያም ያ ልጅ በገዛ አባቱ እጅ መስዋዕት ሆኖ
ይቀርባል፤ እንደገና ከሞት ይነሳል። ከሞት ከተነሳ በኋላ ለአለም በረከት ይሆናል።

እግዚአብሔር ለወዳጁ አብርሃም አለምን የማዳን እቅዱን እና ለሰው ልጅ ሊመጣ


ያለውን ታላቅ በረከት ነግሮት ነበር። አብርሃም አስቀድሞ የወንጌልን ዋና ፍሬ ሀሳብ
ተመልክቷል።እግዚአብሔር ለአይሁድ "አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት
አደረገ፥ አየም ደስም አለው።"(ዮሐ 8: 56) ብሎ ነግሮአቸዋል። አብርሃም በልቡ
"እግዚአብሔር እንዳደርግለት ያዘዘኝ ነገር እርሱ ለእኔ ሊያደርግልኝ ከሚችለው ፈጽሞ
ሊበልጥ አይችልም" ብሎ ማሰቡ የማይቀር ነው።

አብርሃም ሊመጣ ስላለው እውነተኛ ሀይማኖት የተወሰነ ያህል እውቀት ነበረው።


እግዚአብሔር ለወዳጁ አብርሃም ወደፊት የገዛ ልጁን ለአለም ሀጥያት መስዋዕት
እንዲሆን እንደሚልክ እና በእግዚአብሔር አዳኝ ጸጋ የሚያምን ማንም ሰው
እንደሚባረክ እና እንደሚድን በተወሰነ መጠን ገልጦለት ነበር።

በአይሁድ ቤተ መቅደስ ለብዙ ምዕተ አመታት የእንስሳት መስዋዕት ስርዐት ሲካሄድ


ቆይቷል፤ በመጨረሻም ነብዩ ዮሐንስ(በቁራን Yahya ይሰኛል) መጥቶ የኢየሱስን
መምጣት አወጀ። መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:16 ላይ እንዲህ ይላል፦ "በነገው ዮሐንስ
ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ። እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ
የእግዚአብሔር በግ።"

የክርስት ትምህርት በተለይም የወንጌል ማእከላዊ ሀሳብ በሁሉም የአይሁድ መጽሐፍት


ተጽፎ መገኘቱ የሚደንቅ እና መሠረታዊ ጉዳይ ነው።

የአብርሃም ጽድቅ የእምነቱ ውጤት ነው

አብርሃም የተለያዩ ሀጥያቶች እንደሰራ በመጽሐፍ ቅዱስም በቁራንም(surah 26:82)


ተጽፏል፤ ሆኖም እግዚአብሔር ይቅር ብሎታል፤ እንዲሁም ጻዲቅ መሆኑን መስክሯል።
አብርሃም በእግዚአብሔር ላይ እና እግዚአብሔር ለእርሱ የገባለትን ቃል የመፈጸም
ችሎታ እንዳለው ማመኑ እንደ ጽድቅ ተቆጥሮለታል። ዘፍ 15፥6 ላይ “አብራምም
በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።” ተብሎ ተጽፏል።

የአብርሃም እምነት እጅግ የሚደንቅ ነው፤ ምክንያቱም የአብርሃም እምነት


ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንዲሁ አሜን ብሎ ከመታዘዘ ያልፋል፤ አብርሃም
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እና የእግዚአብሔር ታማኝነት የተሳሰሩ እና አብረው የሚሄዱ
መሆናቸውንም አምኗል። አብርሃም በእግዚአብሔር ጽድቅ፣ መልካምነት እና ታማኝነት
ተደግፏል። ስሊዚህ አብርሃም በእምነቱ እግዚአብሔርን አክብሯል። የአብርሃም ጽድቅ
በጥረት የተገኘ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
አብርሃም በእግዚአብሔር ዘንድ የጸደቀው በቅድስናው ወይም በመልካም ስራው ብዛት
አይደለም፤ በዘር ሀረጉ ምክንያትም አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን እንደ ጻድቅ
የተቀበለው አብርሃም በእግዚአብሔር ስላመነ እና በእግዚአብሔር ሀይል፣ ጸጋ እና
ታማኝነት ስለተደገፈ ነው። የ"እምነት" መርህ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብራርቷል።

"ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል


አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ
ቃል አልተጠራጠረም። ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ነገር ግን፦ ተቈጠረለት
የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን
አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን
ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው።" ሮሜ 4: 20-25።

እውነተኞቹ የአብርሃም ልጆች እነማን ናቸው?

እውነተኞቹ የአብርሃም ልጆች የአብርሃም አይነት እምነት ያላቸው ናቸው፤ ዘራቸው


እና ጎሳቸው አንዳች ለውጥ አያመጣም። ይህ እውነታ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ
ተቀምጧል፤ አብርሃምን ተመለከቱት፦

"እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። እንኪያስ


ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ እወቁ። መጽሐፍም
እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ
ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። እንደዚህ ከእምነት የሆኑት
ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ።" ገላትያ 3: 6-9።

ቁጥር 13 እና 14 ላይ የእኛ ከአብርሃም ጋር አብሮ መቆጠር መሠረቱ እምነት መሆኑን


የበለጠ ያብራራል። "ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤
የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ
ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።" በሌላ አገላለጽ፥ አብርሃም በእምነት ድነትን እንዳገኘ
ሁሉ፥ እውነተኞቹ የእግዚአብሔር ልጆችም በእግዚአብሔር እና በተስፋ ቃሉ የሚያምኑ
ናቸው። የእግዚአብሔርን ህግጋት የመጠበቅ ችሎታቸው ላይ የሚተማመኑ እውነተኛ
የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም።
ይህ እምነት ያለው ማንኛውም ሰው የጽድቅን በረከት ያገኛል። “ስለዚህ ከሕግ ብቻ
ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ
ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ
ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት
በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።” ሮሜ 4፥16-17

መሲሁ የመጣው በአብርሃም ዘር በኩል ነው።

ዘፍጥረት 22፥18 ላይ እግዚአብሔር ለአብርሃም “የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ


ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።” ብሎ ቃል ገብቶለታል። ማቴዎስ 1:1 ላይ ኢየሱስ
የአብርሃም ልጅ ተብሎ ተጠርቷል። የሀዲስ ኪዳን መጽሐፍት ኢየሱስ የአብርሃም
ዘር(seed) እንደሆነ ያብራራሉ። “ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ
ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም
ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።” ገላትያ 3፥16።

መሲሁ ኢየሱስ የድነታችንን ስራ ሊፈጽም በአብርሃም በኩል ወደ ምድር እንደመጣ


በማሻማ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጧል። የኢየሱስ ወደ ምድር መምጣት እና
መስዕዋትነት እግዚአብሔር ለአብርሃም "ለለዎች ሁል በረከት አደርግሃለሁ" ብሎ
የገባው ቃል ፍጻሜ ነው። በአለም ያለ ሰው ሁሉ ልክ እንደ አብርሃም በኢየሱስ በማመን
ድነትን እና የዘለአለም ህይወት በረከትን ያገኛል።

እርቅ የሚቻል ነገር ነው

በኢየሱስ በማመን በኩል የይስሐቅ እና የእስማኤል ልጆች ሰላማዊ ግንኙነት ሊመሰርቱ


ይችላሉ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር በረከት ለሁሉም የሰው ልጆች ነውና።
እግዚአብሔር የይስሐቅ እና የእስማኤል ልጆች በአንድ ደስተኛ ቤተሰብ አንድ እንዲሆኑ
እና ሰላም፣ ፍቅር፣ ሀሴት እና ደስታን እንዲያጣጣሙ ይፈልጋል ብዬ አምናለሁ።

እግዚአብሔር ለእኛ ያለው መስዋዕታዊ ፍቅር

«ለምንድነው እግዚአብሔር አብርሃምን ልጅህን ስጠኝ ያለው? ሌላ ነገር ያልጠየቀው


ለምንድነው? ልጁህን ስጠኝ በማለት ፈንታ ይህንን ያህል ቀን ጹም እና ጸልይ ሊለው
አይችልም ነበር?» ብላችሁ ጠይቃቹ ታውቃላቹ?

እግዚአብሔር አብርሃምን ንብረቱን ወይም መሬቱን አልጠየቀውም፤ የገዛ ልጅህን ስጠኝ


ነው ያለው። ምክንያቱም ሰው ከወለደው ልጁ አስበልጦ የሚወደው ምንም ነገር የለም።
አብርሃም የገዛ ልጁን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ፈቃደኛ በመሆን ያለውን ነገር ሁሉ
ለእግዚአብሔር ለመስጠት ፈቃደኛ እንደሆነ አረጋግጧል፤ ሙስሊም እህትና ወንድሞቼ
በዚህ ሀሳብ ከእኔ ጋር እንደምትስማሙ ተስፋ አደርጋለሁ።

እግዚአብሔር ይህንን የራሱን ባሀርይ እንድንረዳ ይፈልጋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ


እግዚአብሔር እንዲህ ተጽፏል፦ “ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ
የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?” ሮሜ
8፥32

እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ምሳሌ ልስጣችሁ። እኔ እና ሚስቴ ሀላ አንድ ሰው


ለአግሎታችን ህንጻ ወይም ቤት ስጦታ አድርጎ እንዲሰጠን እንጸልይ ነበር። ይህ ይሆናል
ብለን እናስብ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ለህንጻችን መቀመጫዎች ያስፈልጉናል። ይህንን ህንጻ
በስጦታ የሰጠንን ሰው መቀመጫዎችም አንዲሰጠን እጠይቃለሁ፤ እርሱም
መቀመጫዎችን ጨምሮ እንደሚሰጠን እርግጠኛ ነኝ፤ ምክንያቱም አስቀድሞ ትልቅ
የሆነውን ህንጻ ሰጥቶናልና።

ሙስሊም ወዳጆቼ ሆይ፥ አሁን በዚህ ሰዐት ንስሀ እንድትገቡ እና የኃጢአታቹን ዋጋ


ለመክፈል በሞተው በኢየሱስ ላይ እምነታቹን እንድታደርጉ አጥብቄ አበረታታችኋለሁ፤
በዚህም እግዚአብሔር በምድራዊም ሆነ በዘላለማዊ ህይወታቹ ሁሉ መልካም ነገርን
እንደሚያደርግላቹ በእርግጠኝነት አውቃቹ መኖር ትችላለህ።

አብርሃም ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር እና ለገዛ ልጁ ካለው ፍቅር አንዱን መምረጥ


ነበረበት። አብርሃም ልጁን ለእግዚአብሔር ለመሰዋት ፈቃደኛ መሆኑ ከልጁ እና
ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሔርን እንደሚወድ አረጋግጧል።

እግዚአብሔር አብርሃም ልጁን እንዲሠዋለት ባዘዘው ጊዜ አብርሃም እንደ አባት ብዙ


እንደተጨነቀና እንዳዘነ ምንም ጥርጥር የለውም። ሕያው ልጁን (ከእሱ የመጣውን)
በገዛ እጁ ሊሰዋ ይዞት ሲሄድ ነፍሱ በጥልቀት እንደተሰቃየ ግልጽ ነው።

ሙስሊም ወዳጄ ሆይ፣ አብርሃም እግዚአብሔርን ታዝዞ ልጁን ሊሠዋለት በተዘጋጀ ጊዜ፣
ለእግዚአብሔር ፍጹም የሆነ የመሥዋዕትነት ፍቅር እንዳለው በማያሻማ ሁኔታ
እንዳረጋገጠ ከእኔ ጋር የምትስማማ ይመስለኛል። እግዚአብሔርም ላንተ ያለውን
ፍጹም ፍቅር እንዲህ ባለ ተመሣሣይ መንገድ አረጋግጧል፤ ይህንንም ታውቅ ዘንድ
ይፈልጋል። ሮሜ 5፥8 ላይ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና
እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” ተብሎ ተጽፏል።
አንድ ጥያቄ መጠየቅ እንዲፈቀድልኝ በትህትና ልጠይቃቹ፦ እስልምና ውስጥ ያለው
እግዚአብሔር የአብርሃምን የፍጹም ፍቅር ተምሳሌት የሚስተካከል ፍቅር አሳይቶ
ያውቃል? ቁራን የእግዚአብሔርን ፍጹም መስዋዕታዊ ፍቅር ገልጦልናል?

አንድ መሠረታዊ ጥያቄ አለ፦ ሰዎች ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር (አብርሃም


ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር አይነት) እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካለው ፍቅር ሊበልጥ
ይችላል?

ቀላሉ እና ምክንያታዊው መልስ ይህ ነው፦ እግዚአብሔር አብርሃምን ጨምሮ ማንንም


ሰው እሱ ለሰዎች ሊያደርግ ከፈቀደው በላይ ሰዎች ለሱ እንዲያደርጉለት ጠይቆ
አያውቅም።

አብርሃም «እግዚአብሔር እንዳደርግለት ያዘዘኝ ነገር እሱ ለኔ ሊያደርግልኝ ከፈቀደው


ነገር ፈጽሞ ሊበልጥ አይችልም» ብሎ ማሰቡ ግድ ነው። እግዚአብሔር ከዘላለም ጀምሮ
አብሮት ያለውን፣ በአብሮነቱም የሚደሰተውን፣ አንዲያ ልጁን አሳልፎ ሰጠን፤ በዚህም
ከፍቅር ሁሉ የበለጠውን ፍቅር አሳየን። እግዚአብሔር መስዋዕት ያደረገው ከሁሉ
አስበልጦ የሚወደውን ነገር ነው። እግዚአብሔር ለአብርሃም እና ለእኛ ያለው ፍቅር
አብርሃም ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር በብዙ እንደሚልቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማየት
ይቻላል።

በመስዋዕታዊ ፍቅር መምራት

በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተከሰተ አንድ እውነተኛ ታሪክ አንብቤያለሁ፤ ይህ ታሪክ


የተለያዩ የመሪ አይነቶችን ያሳያል። የብሪቲሽ ጦር የሚመራ አንድ ኮማንደር ወታደሮቹ
ወደ ጦር ቀጠና እንዲያቀኑ አዘዛቸው። ወታደሮቹ ሲቆስሉ እና ሲሞቱ እየተመለከተ፥
ነገር ግን ከልበ ቀዝቃዛነቱ የተነሳ ወታደሮቹን ተቀላቅሎ ከመዋጋት ተቆጠበ።

ሌላኛውን የብሪቲሽ ጦር መሪ ጀምስ ይባላል። ጀመስ ወታደሮቹ በጠላት እንደተከበቡ


በተመለከተ ጊዜ ጦራቸውን አንስተው ጠላትን እንዲወጉ ትእዛዝ ሰጠ። እሱም
ወታደሮቹን ተቀላቅሎ ግንባር ላይ ይዋጋ ጀመር። ጦሩን በብቃት መርቶ ጠላትን ድል
አደረገ። ይህ የጦር መሪ የብዙ ወታደር ህይወት ታድጓል። ነገር ግን እሱ ክፉኛ ተጎድቶ
ነበር። ለወታደሮቹ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠ መሪ ይህ ነው።

የሁለተኛው መሪ ታሪክ እግዚአብሔር ህዝቡን ለድል የመራበትን እና ለእነርሱ ሲል


ራሱን አሳልፎ የሰጠበትን እውነት ያስታውሰናል። የእግዚአብሔር ፍቅር ፍጹም ነው።
እውነተኛ የፍቅር የሚፈተነው እና የሚለካው በመስዋዕትነት ነው። ኢየሱስ እንዲህ
ብሎ ነበር፦ “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም
የለውም።” ዮሐንስ 15፥13።
መስቀሉን ስትመለከት፣ በላዩ ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስን ስትመለከት፣ የእግዚአብሔርን
ወሰን የለሽ እና ዘላለማዊ ፍቅር ጥልቀት እና ጥንካሬ ትመለከታለህ። ኢየሱስ ለእኛ
የተሰጠን የእግዚአብሔር እጅግ ውድ ስጦታ ነው። አሁን ልብህን ለኢየሱስ በእምነት
በመክፈት ስጦታውን ለመቀበል ፈቃደኛ ነህ? እምነት እግዚአብሔር በአንተ ውስጥ
ለማግኘት የሚፈልገው ብቸኛው ምላሽ ነው።

እግዚአብሔር የአብርሃምን ልጅ ተቤዠ

ቁራን እግዚአብሔር አብርሃም ልጁን እንዲሰዋለት እንደጠየቀው እና አብርሃምም


ሊሰዋ ሲዘጋጅ ጣልቃ ገብቶ እንዳስቆመው ይናገራል። "... ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም
አበሰርነው፡፡ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ
ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡
አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም
ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!
ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ ይህ
እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡... "
(surah 37: 101-107)

እግዚአብሔር የምትክ መስዋዕት አዘጋጀ

ቁራን ሱራህ 37 ላይ በተቀመጠው የአብርሃም ታሪክ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ ተዘጋጅቶ


እንደነበርና ነገር ግን እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ልጁን እንዳአስለቀቀው ይናግራል።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ነብዩ አብርሃምን ልጁን ይዞ በነጻነት ወደ ቤቱ እንዲሄድ
ፈቅዷል? አልፈቀደም። አሁንም መስዋዕታዊ ስጦታ አስፈላጊ ነበር። እግዝአብሔር
የአብርሃምን ልጅ በነጻ ያሰናበተበት ብቸኛ መንገድ በልጁ ፈንታ ሌላ መስዋዕት
በመተካት ነበር። በዚህ ታሪክ የቤዝዎት መርህ በግልጽ ተቀምጧል፤ የአብርሃም ልጅ በነጻ
የተለቀቀው በእርሱ ምትክ በግ ከተሰዋ በኋላ ነው።

እግዚአብሔር የአብርሃምን ልጅ ወዶታል፤ ስለዚህም ታድጎታል ወይም ተቤዥቶታል።


በእርሱ ምትክ በግ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ እግዚአብሔር የመስዋዕት በግ አዘጋጀ(ዘፍ
22:13)። የምትክ መስዋዕት ያዘጋጀው እግዚአብሔር መሆኑን ልብ ልንል ይገባል።

ልክ እንደዚሁ፣ ራሱ ያዘጋጀውን መስዋዕት ሰውቶ እኛን የተቤዠን እግዚአብሔር ነው፥


ሙስሊም ወዳጆቼ። አላማውም ለእኛ ያለው ፍቅር ነው።

A “Momentous,” “Mighty,” and “Tremendous” Sacrifice

መጥመቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመልክቶ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት


የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ብሎ እንደተናገረ በመጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1፥29
ላይ ተጽፏል። የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ነው(ኢሳ)

ነብዩ ኢሳያስ በእግዚአብሔር መንፈስ ተነሳስቶ ሊመጣ ስላለው ነብይ ትንቢትን


ተናግሯል፤ በትንቢቱም ኢየሱስ የመስዋዕት በግ እንደሆነ አስተውሏል፦ “ተጨነቀ
ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም
እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።” ኢሳይያስ 53፥7።

አብዱላህ ዩሱፍ አሊ ሱራህ 37: 107 ላይ ያለውን ጥቅስ እንደሚከተለው ተርጉሟል፦


"we ransomed him a momentous sacrifice." ሌሎች በአለማቀፍ ደረጃ
የታወቁ ተርጓሚዎች ደግሞ ይህንን ክፍል "tremendous" እና "Almighty" ብለው
ተርጉመዋል።
የተሰዋዉ በግ እጅግ ታላቅ የሆነ እውነት ተምሳሌት ነዉ

አንድ ጥያቄ መጠየቅ አለብን፦ momentous፣ mighty እና tremendous ተብሎ


ሊጠራ የሚገባው መስዕዋት ምን አይነት መስዋዕት ነው? እግዚአብሔር ለአብርሃም
በልጁ ምትክ ያዘጋጀው የበግ መስዋዕት እንዲያ ያለ አገላለጽ እንደማይመጥነው ግልጽ
ነው። ያ የበግ መስዋዕት ሊመጣ ያለው ታላቅ መስዋዕት ተምሳሌት ነው፤ የኢየሱስ
ክርስቶስ።

መልሱ በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ተቀምጧል፦ “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ


ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው
እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።” 1 ኛ ጴጥሮስ
1፥18-19።

ሀልቬርሰን የተሰኘ የስነ መለኮት ሊቅ አንድ ሀሳብን የሚያጭር ጥያቄ ይጠይቃል። “ድነት
መልካም ስራ ለሚሰሩት እንደ ሽልማት የሚሰጥ ከሆነ፣ የእግዚአብሔር አላማ ደግሞ
የአብርሃምን ታዛዥነት ለመፈተን ብቻ ከሆነ፣ ለምንድነው ታድያ ‛momentous
መስዋዕትነት’ ያስፈለገው? አብርሃም እግዚአብሔርን ታዝዞ እስከሄደበት ድረስ መሄዱ
በቂ አልነበረምን?”

የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ወደእኛ የመጣው በኢየሱስ በኩል ነው።

እግዚአብሔር እኛን እጅግ አድርጎ እንደሚወደን እና መውደዱንም ኢየሱስን መስዋዕት


አድርጎ እኛን በማዳን እንደገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ቁራን አል-ማሲህ ኢሳን
“a Spirit proceeding from God” (ሱራህ 4:171) ብሎ ይገልጸዋል። ኢየሱስ
የእኛን ቦታ ወስዶ በእኛ ምትክ ተሰዋ። በመስቀል ላይ ሞት በሃጢአታችን ምክንያት
ከመጣብን የሞት ቅጣት ተቤዥቶናል። እየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “እንዲሁም የሰው ልጅ
ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
ማቴዎስ 20፥28።

እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጥ የሚችለው የመጨረሻው ውድ ነገር ራሱን ነው። ለዚህም


አላማ በኢየሱስ በኩል እኛን ሊያድነን ወደ ምድር መጣ። የበጉ መስዋዕትነት "እጅግ
የሚደንቅ" ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱን መስዋዕት ማድረጉን ያመለክታልና፤
ይህ የእግዚአብሔር መስዓትነት ወሰን የለሽ ዋጋ ያለው እና ለድነታችንም በቂ የሆነ
ነው።
ይህንን የፍጹም ፍቅር ተግባር በሌላ ታሪክ አማካኝነት ላብራራ። ከእለታት አንድ ቀን
አንድ ወጣት ግድያ ፈጸመ። ፖሊስ በምድር እና በአየር አባረረው፤ ነገር ግን እንደምንም
ብሎ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት ሊደርስ ቻለ።

የልጁ አባት የልጁ ልብስ በደም ተጨማልቆ በተመለከተ ጊዜ ደነገጠ። ልጁም ሰው ገድሎ
እንደመጣ እና የሚጮኹዉ የፖሊስ አምቡላንስ እና የጀት ድምጽ እርሱን የሚያሳድድ
እንደሆነ ተናዘዘ። አባቱም ልጁ በደም የተጨማለቀ ልብሱን በፍጥነት እንዲያወልቅ
ነገረው። አባት በደም የተጨማለቀ የልጁን ልብስ ለራሱ ለብሶ ንጹህ የሆነው የራሱን
ልብስ ለልጁ ሰጠውና እንዲለብስ ነገረው። ፖሊስ ቤታቸውን በሀይል ከደበደበ በኋላ
ሰብሮ ገባ። የአባትየው ልብስ በደም እንደተጨማለቀ በተመለከቱ ጊዜ ይዘው አሰሩት።
አባት ልጁ ለሰራው ወንጀል ዋጋ ከፈለ። እየሱስ ኢንዲህ ብሏል፦ “ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ
ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።” ዮሐንስ 15፥13።

የቤዝዎታችንን ዋጋ የሚከፍለው ማነው?

ሱራህ 10: 54 ላይ እንዲህ ተጽፏል፦ "ለበደለች ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ


ቢኖራት ኖሮ በርግጥ በተቤዠችበት ነበር።" 'ቤዝዎት' ማለት አንድን እስረኛ
ለማስለቀቀ ሊከፈል የሚገባው ዋጋ ነው። ከመንፈሳዊ ሞታችን እና ቅጣታችን ነጻ
የምንወጣበትን ዋጋ መክፈል የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

በኦሪት መጽሐፍት (ዘሌዋውያን 4) እግዚአብሔር ህዝቡን ሀጥአታቸው እንዲሸፈን


የበግ ጠቦት፣ በግ፣ ፍየል እና የመሳሰሉ ነውር እና እንከን የሌለባቸው ንጹሕ እንስሳትን
መስዋዕት አድርገው እይዲያቀርቡ እንዳዘዛቸው ተጽፎአል። ሀጥያት የሰራ ሰው ከነኚህ
እንሳሳት አንዱን ይዞ ወደ ካህን ይመጣል፤ ከዚያም ሀጥአተኛው እጁን የእንስሳው
ጭንቅላት ላይ ይጭናል(ራሱን ከእንስሳው ጋር አንድ እንዳደረገ ይቆጠራል)፤ ከዚያም
ሀጥያቱን ይናዘዛል፤ በዚህ አማካኝነት የሀጥአተኛው ሀጥያት ወደ እንስሳው ይተላለፍና
እንስሳው ይታረዳል። ከዚያም ካህኑ የእንስሳውን ደም ለኃጢአት ይቅርታ ይሆን ዘንድ
በመሠዊያው ላይ ይረጫል። በዚህም፥ የኃጢአት ቅጣት ንጹሕ እንስሳ ለኃጢአተኛው
ሰው ምትክ ሆኖ በመሞቱ ይከፈላል።

ንጹሕ የሆነው እንስሳ ከምንም ዓይነት ወንጀል ነጻ እንደሆነ ግልጽ ነው። ነገር ግን
አምላክ ኃጢአት በእርሱ ዓይን ምን ያህል ከባድና አደገኛ እንደሆነ ለሕዝቡ
ሊገልጽላቸው ፈልጎ ይህንን አደረገ። ብሉይ ኪዳን ለወንጌል ትምህርቶች መሠረትን
ጥሏል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን


ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን
ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን? ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና
ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል
እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።" ዕብራውያን 9: 14-15።

ውድ ሙስሊም ወዳጄ! የመስቀሉን ፋይዳ ተመለከትክ? ክርስቶስ ለዘላለም የመኖር


መብትን ሊሰጠን ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ ሰጠ፤ ካለብን የሞት እዳ ነፃ አወጣን፤
በእኛ ቦታ ኢየሱስ ተተካ፤ ዋጋችንን ከፈለልን።

የስነ መለኮት ሊቅ ጆን ስቶት ዋናውን የወንጌል ጭብጥ እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፦


"መለኮት ራሱን መስዋዕት በማድረጉ መለኮታዊ ፍቅር መለኮታዊ ቁጣን አሸነፈ"
ኢየሱስም እንዲህ ብሏል፦“ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ
ይህ ነው።” ማቴዎስ 26፥28።

ኢየሱስ "ስለ ብዙዎች... የሚፈስ... ደሜ ይህ ነው" ብሎ ሲል ህይወቱ ለብዙዎች


እንደሚሰጥ እያመለከተ ነው። የኢየሱስ ሞት በሰው እና በእግዚአብሔር መኻል አዲስ
ግንኙነት(ይህ ግንኙነት ኪዳን ይሰኛል) እንዲጀመር ምክንያት የሆነ ነው። ይህ ኪዳን
ሙሴ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል መሠዊያው ላይ የእንስሶችን ደም በመርጨት
ያተመውን አሮጌውን የሙሴ ኪዳን የሚተካ ነው (ዘጸአት 24፡6)።

የደም መስዋዕትነት ፋይዳ በእስልምና

ሙሴ ለህዝቡ እግዚአብሔር ንጹሕ እና ነውር የሌላት ጊደር እንዲሠዉ መናገሩ ቁራን


ውስጥ መጻፉ የሚገርም ነው። (ሱራህ 24: 6)

መሐመድ (በአል-ቡካሪ እንደተጻፈው) የእንስሳት መስዋዕት ተቀባይነት ያለው እና


መለኮት የወሰነው ከእግዚአብሔርን ተቀባይነት የማግኛ መንገድ እንደሆነ ይናገራል።
ሙስሊሞች "የመስዋዕት በዓል" (ኢድ አል-አድሃ) የተባለ ዓመታዊ ክብረ በዓል
አላቸው። በዚህ ቀን እንስሳትን ይሠዋሉ። ይህ በዓል በእስልምናው አለም አብርሃም
ልጁን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ያሳየውን ፈቃደኝነት የሚዘክር ነው
ተብሎ ይታመናል።

እግዝአብሔር ለእኛ ያዘጋጀው ቤዝዎት ምሳሌ

ሻሙኤል ስለተባለ የተከበረ ልዑል ያነበብኩትን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ። ሻሙኤል


ህዝቡንና መሬቱን ከክፉ ጎረቤት መንግስት ወረራ ለመከላከል እየሞከረ ነበር። አንድ
ምሽት ጠላቱ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመሰንዘር አቀደ። ነገር ግን ጠላት የሻሙኤልን
ሚስጥራዊ እቅዱ አስቀድሞ አውቆ የሳሙኤልን ጦር እየተጠባበቀ ነበር፤ ምክንያቱም
የሻሙኤል እቅድ በሰላዮች አማካኝነት ለጠላቱ ደርሶታል። በመጨራሻም አብዛኞቹ
ወታደሮቹ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ጦርነቱንም ሙሉ በሙሉ ተሸንፏል። ሻሙኤል
ሚስጥሩን አሳልፎ የሰጠ ከሀዲ መቶ ጅራፍ ግርፋት እንደሚቀጣ አስታወቀ።
የሻሙኤል ጦር ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ ሚስጥር ሌላ ጥቃት ሰነዘረ፤ ነገር ግን አሁንም
ጠላት የሻሙኤልን ጦር ዶግ አመድ ሊያደርግ አድፍጦ እየጠበቀ ነበር። ልዑሉ ይህንንም
ጦርነት ተሸነፈ፤ ነገር ግን በዚህኛው ጊዜ ከሃዲው ማን እንደሆነ አወቀ። ከሀዲዋ
የሻሙኤል እናት ነበረች። ከጠላት ወታደሮች ከአንዱ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ነበር።

እንዴት ያለ አጣብቂኝ ነው! ሻሙኤል ምን ማድረግ አለበት? እናቱን ከቅጣት ነፃ ካደረገ


ተከታዮቹ ፍትሃዊ ያልሆነ እና ለወገኖቹ ህይወት ደንታ የሌለው እንደሆነ አድርገው
ይከሱታል። ሌላኛው አማራጩ ለሻሙኤል የበለጠ ከባድ ነው። እናቱን አብዝቶ ይወድ
ስለነበር የሚወዳትን እናቱን ለሥቃይ እና ምናልባትም ለሞት የሚዳርግ ፍትሐዊ ፍርድ
እንዴት ይስጥ?

ሻሙኤል ለህዝቡ የሚከተለውን ንግግር አደረገ፦ “በክህደት ምክንያት ሁለት ጦርነቶች


ተሸንፈናል። ብዙ ወገኖቻችን ተገድለውብናል። ህጉ ተጥሷል፤ ቅጣቱም ተፈጻሚ ይሆን
ዘንድ ይገባል፤ አንድ መቶ ግርፋት! ጽድቅ እና ፍትህ ሊሰፍኑ ግድ ነው።"

የልዑሉ እናት ቅጣቷን የምትቀበልበት ቦታ በወታደር እየተመራች ስትወሰድ በታላቅ


ፍርሃት ተሞላች። ገራፊው ጅራፉን አነሳና የመጀመርያውን ግርፋት ሊያሳርፍ ሲዘጋጅ
ሻሙኤል ጩኾ “አቁም! በእሷ ፋንታ እኔ እቀጣለው” አለ። የንግሥና ልብሱን አውልቆ
ገራፊውን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ከሀዲውን ከምትገርፍበት ሀይል ባነሰ ሀይል
ብትገርፈኝ ውርድ ከራሴ! እኔ ነኝ የሷን ቅጣት የምቀጣው። ግዴታህን ተወጣ! በል
ቀጥል!"

ሻሙኤል ከግርፋቱ ብዛት ራሱን ስቶ መሬት ላይ እስኪወድቅ ጀርባውን ተቀጠቀጠ። ከዛ


ሁሉ ግርፋት በኋላ በህይወት ይተርፋል ብሎ ማንም አልጠበቀም ነበር፤ ነገር ግን ተረፈ።
ልዑል ሻሙኤል የሚወዳት እናቱን ነፃ ለማውጣት እሷ ለፈጸመችው ጥፋት ሙሉ ዋጋ
ከፍሏል!

በተመሳሳይ መንገድ፥ ኢየሱስ የሌለበትን ዕዳ ለመክፈል መጣ፤ ምክንያቱም እኛ መክፈል


የማንችለው ዕዳ ነበረብን። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ
እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል
ተፈወሳችሁ።” 1 ኛ ጴጥሮስ 2፥24። እንደገና ኢየሱስም እንዲህ አስተምሯል፦ “ነፍሱን
ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።” ዮሐንስ
15፥13።

ውድ ሙስሊም አንባቢዬ፥ እግዚአብሔርን “ምን ያህል ትወደኛለህ?” ብለህ


ብትጠይቀው እጁን በመስቀል ላይ ወደተሰቀለውን ኢየሱስ እየጠቆሞ “ይህንን ያህል
እወድሀለው” ይለሀል።
ኢየሱስ ማለት "አዳኝ" ማለት ነው

አልቃሲሚ የተባለ እውቅ የእስልምና ሊቅ "Mahasen at-Ta’aweel" በተኘ ታዋቂ


የማብራሪያ መጽሐፉ በሱራ 3፡45 ላይ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል፦ “ኢሳ
[ኢየሱስ] የሚለው ስም ወደ አረብኛ የተመለሰ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም አዳኝ
ማለት ነው።" መጽሐፍ ቅዱስ በማቴዎስ 1:21 እንዲህ ይላል፦ “ልጅም ትወልዳለች፤
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”

( -
ክርስቶስ ኢየሱስ አል ማሲህ፣ ኢሳ ) የተቀባ የእግዚአብሔር መሲህ

ቁራን ለኢየሱስ ሶስት የተለያዩ ማዕረጎች ይሰጣል፦ "የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ


የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ
ነው፡፡" ሱራህ 4: 171።

ኢየሱስ በቁርዓንም በሐዲስም መሲሕ ነው። በቁርአን ውስጥ አል-ማሲህ (መሲሁ)


ተብሎ የተጠቀሰው ኢየሱስ ብቻ ነው። its use of the definite article the
positively distinguishes Jesus from all other prophets. አልፎ አልፎ ስሙ
ሳይነሳ በዚህ ማዕረግ ብቻ ተጠቅሷል (በሱራ 4፡172)።

ኢየሱስ በቁርኣን ውስጥ ከአሥር ጊዜ በላይ መሲሕ በሚል ማዕረግ ተጠርቷል። ለምሳሌ
ሱራህ 3፡45 ላይ መልአኩ ገብርኤል ለማርያም ተገልጦ የልጇ ስም “ክርስቶስ ኢየሱስ”
(አል-ማሲህ፣ ኢሳ፤ ማለትም፥ መሲህ፣ ኢየሱስ) እንደሆነ ተናግሯል።

ኢየሱስ በሐዲስ አል-ማሲህ ይባላል። የእስልምና ሊቃውንት አል-ማሲህ የሚለው


የማዕረግ ቃል ከአረብ ቋንቋ የተገኘ እንደሆነ ይስማማሉ። አል-ባይዳዊ የተባለው
የእስልምና ምሁር፣ በሱራ 3፡45 ላይ አስተያየት ሲሰጥ፣ ክርስቶስ (አል-ማሲህ) የሚለው
ቃል በመሠረታዊነት የዕብራይስጥ ቃል (ማሺህ) እንደሆነ ይናገራል። ቁርኣን መሲሕ
የሚለውን ቃል ትርጉም እንደማያብራራ ልብ ይበሉ። የቃሉን ትርጉም ባለማብራራት
በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው መሲሕ የሚለው ቃል ማብራሪያ ጋር በተዘዋዋሪ
ይስማማል ማለት እንችላለን።

የወንጌል መጽሐፍት የተፃፉት በግሪክ ቋንቋ ነው። አል-ማሲህ ወይም "የተቀባው"


ለሚለው ቃል ዋናው የግርክ አቻ "ho Christos" ይሰኛል። ክርስቶስ የሚለው
የእንግሊዘኛ ቃል የመጣው ከዚህ የግሪክ ቃል ነው። ስለዚህ ክርስቶስ የሚለው
የእግሊዝኛው ትርጉም በእንግሊዝኛው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ውስጥ በተጠቀሰበት
ቦታ ሁሉ አል-ማሲህ የሚል ትርጉም ይዞ ነው። በዚህ ሀሳብ የሙስሊም ሊቃውንትም
ይስማማሉ።

ስለሚመጣው መሲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች

ብሉይ ኪዳን የተጻፈው ክርስቶስ ወደ ምድር ከመምጣቱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት


ነው። ብሉይ ኪዳን በውስጡ ብዙ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተነገሩ፣ ወደ ፊት አንድ ቀን
ከእግዚአብሔር ስለሚላከው እና "የተቀባ" (መሲሑ) ተብሎ ስለሚጠራዉ የተከበረ
አዳኝ የሚያወሱ ትንቢቶችን ይዟል።

በብሉይ ኪዳን ስለሚመጣው መሲህ ስልሳ አንድ ዋና ዋና ትንቢቶች አሉ፣ እነዚህም


በኢየሱስ ሙሉ በሙሉ በትክክል ተፈጽመዋል። በዚህ ርዕስ ብቻ ብዙ መጻሕፍት
ተጽፈዋል። ስለ መሲሐዊው ትንቢቶች ከተጻፉ መጽሐፍት ቀልፍ ተጠቃሽ የሆነው "all
the messianic prophecies of the Bible" የሚል መጠርያ ያለው የ ኸርበርት
ሎከር መጽሐፍ ነው።

የኢየሱስ የትውልድ ቦታ

ክርስቶስ ከመምጣቱ ሰባት መቶ ዓመታት በፊት በነቢዩ ሚክያስ በተነገረው ትንቢት


(ሚክያስ 5፡2) መሠረት ኢየሱስ በቤተልሔም ተወለደ። በማቴዎስ 2:1, 6 እና ዮሐንስ
7:42 ላይ ይህ ትንቢት ታሪካዊ ፍጻሜውን እንዳገኘ ተጽፎ እናነባለን።

ከድንግል መወለዱ

ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት በነቢዩ ኢሳይያስ በተነገረው ትንቢት መሠረት እየሱስ


ከድንግል ተወለደ። “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥
ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳይያስ 7፥14።
የዚህ ትንቢት ታሪካዊ ፍጻሜ በሀዲስ ኪዳን ተጽፎ ይገኛል።

"በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም


አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።" ማቴዎስ 1፥ 22-23።

በስቅላት መሞቱ

መዝሙረ ዳዊት 22 ላይ የኢየሱስ የመስቀል ላይ ምት ተገልጿል። ዳዊት (ዳውድ) ስለ


ስቅለቱ የጻፈው ክርስቶስ ከመምጣቱ ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት ነው። ቁጥር 16
እንዲህ ይላል፦ “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና
እግሮቼን ቸነከሩኝ።”

በወዳጆ ስለመከዳቱ

መዝሙር 41:9 ላይ መሲሑ በወዳጁ እንደሚከዳ የትንቢት ቃል ተጽፏል።

የዚህ ትንቢት ፍጻሜ በአዲስ ኪዳን በማቴዎስ 26፡47-50 ተመዝግቧል (ይህም ኢየሱስ
በይሁዳ ተከድቶ እና ለእስር ተላልፎ የተሰጠበት ሁኔታ ነው)።

በምድር ላይ ስላለው ተልእኮ

ኢሳያስ ኢየሱስ ከመወለዱ ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት ይህንን ትንቢት ተናግሯል፦


"እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ
አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም
አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል
በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።" ኢሳይያስ 53፥ 5-6።

በትንቢት የተነገረለት መሲሕ መለኮታዊ አካል እንደሆነ መጽሐፍ ቀዱስ በግልጽ


ይናገራል። ከትንቢቶቹ በአንዱ ላይ የሚመጣው መሲሕ መለኮታዊ ስሞች ተሰጥቶታል፦
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ
ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ
ይጠራል።” ኢሳይያስ 9፥6።

"ዘለአለማዊ አባት" የሚለው ሀረግ ይህ የሚወለደው ህጻን ዘለአለማዊ እንደሆነና


ለህዝቡም ፍጹም የሆነ አባታዊ ልብ እንዳለው ያመለክታል።

ነቢዩ ኢሳይያስ የሚመጣው መሲሕ አማኑኤል ተብሎ እንደሚጠራ ተንብዮአል፤ ይህ


ስም የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው።
በኢሳይያስ 7፡14 እንዱህ ተብሎ ተጽፏል፦ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤
እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች።" የዚህ ትንቢት ፍጻሜ በማቴዎስ 1፡21-23 ተመዝግቧል።

ኢየሱስ የሰው ልጅ - ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ

ኢየሱስ ራሱን "የእግዚአብሔር ልጅ" ብሎ ጠርቷል። “ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤


ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት
ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” ማቴዎስ 11፥27። ማቴዎስ 26: 63-64
ላይ የተጻፈውንም መመልከት ይቻላል።

እንዲሁም ኢየሱስ ራሱን "የሰው ልጅ" ብሎም ጠርቷል። ይህንንም ያደረገው መለኮት
እንደሆነው ሁሉ ሰውም መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ነው፤ ይህም መሲህ መሆኑን ያሳያል።

ነብዩ ዳንኤል "የሰው ልጅ" የተሰኘውን መሲሓዊ ማዕረግ ተጠቅሞ የሚመጣው መሲሕ
መለኮት ስለመሆኑ ትንቢት ተናግሯል

"በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ


በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ
ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም
የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።" ዳንኤል 7: 13-14።

በዚህ ክፍል ዳንኤል በራዕይ "የሰው ልጅ"ን የሚመስል አካል አይቷል፤ ገጽታውም ሰው
የሚመስል እንደሆነ አመልክቷል። በተጨማሪም ይህ ሰው ሉዓላዊ ስልጣን እንደተሰጠው
እና በሁሉም የሚመለክ እንደሆነ አይቷል። ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥
መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። ይህ የሰው ልጅን የሚመስል ሰው ብቻ እንዳልሆነና
ከሰው በላይ እንደሆነ ግልጽ ነው። ነቢያት በቅዱሳን ጽሑፎች የሚመጣው መሲሕ
እንዲሁ ነቢይ ብቻ እንዳልሆነና ከነብይ እጅግ የላቀ እንደሆነ በግልጽ ተናግረዋል።
የብሉይም ሆነ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት የመሲሑን (የክርስቶስን) መለኮታዊ-
ሰውነት በሚገባ ያስተምራሉ።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን እያረጋገጠ ባለበት በተለያዩ አጋጣሚዎች


“የሰው ልጅ” የሚለውን ሀረግ ራሱን ለመግለጽ ተጠቅሟል። ለምሳሌ ማቴዎስ 9፡6 ላይ
የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን የማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው ይናገራል። በሌላ
ክፍል ደግሞ በዓለም ላይ የሚፈርደው የሰው ልጅ እንደሆነ ተናግሯል። “የሰው ልጅ
ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው
ያስረክበዋል።” ማቴዎስ 16፥27። (በተጨማሪ የሚከተሉ ክፍሎችን ይመልከቱ፦
ዮሐንስ 3:16፣ ማቴዎስ 12: 8፣ ማቴዎስ 26:63-65።)

ስለዚህ “የሰው ልጅ” የሚለው ሀረግ ሰው'ነትን ብቻ ወይም መለኮት'ነትን ብቻ


የሚገልጽ አይደለም፤ የመለኮት እና የሰውነትን አንድነት የሚያሳይ ነው።

ኢየሱስ መሲሕ ስለመሆኑ ራሱ ተናግሯል

ሉቃስ 24:44-48 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦


"እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ
የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። በዚያን
ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ እንዲህም
አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም
ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ
ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።"

በዚህ ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳኑ የእግዚአብሔር መገለጥ እውነተኛ መሆኑን
አረጋግጧል። ደቀ መዛሙርቱን ለወደፊት መከራው እና ስቅለቱ አዘጋጅቷል። ስለ
ትንሣኤው ነግሯቸዋል።

"አይሁድም እርሱን ከበው፦ እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? አንተ ክርስቶስ


እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት። ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ
አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ እናንተ ግን
እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።" ዮሐንስ 10: 24-26።

“የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።” ዮሐንስ 1፥11።

መሲሑ የመጣው ለሁሉም ሰዎች እና ለሁሉም ዘሮች ነው።

እንደ አለመታደል ሆኖ ኢየሱስ በምድር ላይ ባለበት ዘመን ብዙ አይሁዶች


የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ለእነሱ ብቻ እንደሆኑ ያስባሉ። ተሳስተው ነበር።

እግዚአብሔር በወንጌል ሁሉም አማኞች በክርስቶስ አንድ እንደሆኑ ደንግጓል።


በክርስቶስ ማመን ሰዎች እርስበርስ ካላቸው ልዩነት ያልፋል። መጽሐፍ ቅዱስ በገላትያ
3:26-28 ላይ እንዲህ ያለ ማረጋገጫ ይሰጠናል፦ "በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ
የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥
ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ
አንድ ሰው ናችሁና።" (ሮሜ 3:29-30 ላይ የተጻፈውንም ያንብቡ)

የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች የሚመጣው መሲሕ ሕዝባቸውን እና ሀገራቸውን


ይታደጋል ብለው በመጠበቃቸው ተሳስተዋል። በተጨማሪም መሲሑ ራሱን ምድራዊ
ንጉሥ አድርጎ እንደሚያጸና በማመናቸውም ስህተት ሰርተዋልል። “ኢየሱስም መልሶ፦
መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም.... አለው።” ዮሐንስ 18፥36

ኢየሱስ አንዳንድ የአይሁድ መሪዎችን የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቋል፦ "ፈሪሳውያንም


ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ፦ ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ
ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን፦
ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት
በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል?
አላቸው። አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ
ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።"

ኢየሱስ መዝሙር 110: 1 ላይ ያለውን ክፍል በመጥቀስ በዚህ ክፍል ዳዊት


እግዚአብሔር ከመሲሁ ጋር ስለመነጋገሩ መጻፉን እና ዳዊት መሲሁን "ጌታይ" ብሎ
መጥራቱን አሳይቷል። ይህም እነሱ እንዳሰቡት መሲሁ ፖሌቲካዊ መሪ እንደማይሆን
አሳይቷል።

የመልካም ዜና ብስራት

የብሉይ ኪዳን ነቢያት የታላቁን መሲሕ መገለጥ በጉጉት ይጠባበቁ ነበር። ከሰው ልጅ
ታሪክ ሁሉ እንዴት ያለ ታላቅ ጊዜ ነው። መልካሙ ዜና ታወጀ! በመጨረሻም አል-
ማሲህ፣ የሰው ሁሉ አዳኝ መጣ። የመሲሑን መወለድ የእግዚአብሔር ቃል “መልካም
ዜና” ሲል ያውጃል። ይህ ታሪክ በወንጌል ውስጥ ተመዝግቧል። በቤተልሔም ሜዳ ላሉ
እረኞች መልአክ ታይቷል፤ የጌታም ክብር በዙሪያቸው አበራ። መልአኩ ይህን ድንቅ
አዋጅ አወጀ።

"መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች


እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ
ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ
ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም
እያመሰገኑ፦ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ
ፈቃድ አሉ።" ሉቃስ 2: 10-14።

ቁርኣን የኢየሱስን መወለድ “መልካም ዜና” ሲል ያረጋግጣል።

ቁርዓን አል-ማሲህ (መሲህ) ኢየሱስ የመርየም ልጅ ስለመሆኑ ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር


መስማማት ብቻ ሳይሆን የኢየሱስ መወለድ መልካም ዜና ስለመሆነ መጽሐፍ ቅዱስ
ከሚናገረው ጋርም ይስማማል። ሱራ 3፡45 ላይ "መላእክት ያሉትን (አስታውስ)፡-
«መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ
ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡»"
ሙስሊም ወንድሞቼ፣ ይህ መልካም ዜና ለእናንተ ነው።

መልካም ዜና ላይ የሚነሳ ተቃውሞ

ሰይጣን(በአርብኛ ሸይጣን) ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠውን የኢየሱስን


ማንነት እና ተልእኮ እንዳይረዱ በትጋት ይሰራል። የአይሁድ የሀይማኖት መሪዎች
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን "ለምን እሱ ከቀራጮች እና ከሀጥአተኞች ጋር ይበላል?"
ሲሉ ጠይቀዋል።

ኢየሱስም ሰምቶ "ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም


ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።” ማርቆስ 2፥17።
ኢየሱስ የመጣው ለሀጥአተኞች ነው።

ኢየሱስ የሰራቸው ተዓምራት የኢየሱስን መሲህነት የሚመሰክሩ ናቸው

የሚመጣው መሲህ ተአምራትን እንደሚያደርግ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል።(ኢሳያስ


35: 5-6)። ከብዙ ምዕተ አመታት በኋላ ኢየሱስ ወደ አለም መጥቶ እውራንን
አብርቷል፤ ሽባ ተርትሯል፤ መስለማት ለማይችሉ ጆሮዎቻቸውን ከፍቷል። ስለዚህ
ኢየሱስ በሰራቸው ተዓምራታት ይመጣል የተባለው መሲህ እና የአለም መድሐኒት
መሆኑን አረጋግጧል።

ቁራን ላይ የተጠቀሱ የኢየሱስ ተአምራታት

ቁራን ኢየሱስ የሰራቸው ተአምራታት የእግዚአብሔር ሀይል "ግልጽ ምልክቶች" ናቸው


ይላል። እነኚህ "ግልጽ ምልክቶች" ለሁሉም ነብያት አልተሰጡም። ቁራን በሱራህ 2:
253 ላይ እንዲህ ይላል፦ "እነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡
ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡
የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡" አል-ባይዳዊ በነኚህ ጥቅሶች
ላይ አስተያየት ሲሰጥ እንዲህ ብሏል፦ "እግዚአብሔር የኢየሱስን ተአምራት ኢየሱስ
ከሁሉም ነብያት የተመረጠ ስለመሆኑ ማስረጃ እንዲሆኑ አድርጓል። ኢየሱስ
የፈጸማቸውን ተዓምራት በጠቅላላ አንድ ላይ የፈጸም ሌላ ነብይ የለም።"

ቁራን ላይ በተጻፈው መሠረት ኢየሱስ ሕይወትን እንደሚፈጥር፣ ዕውሮችን


እንደሚፈውስ፣ ለምጻሞችን እንደሚፈውስ እና ሙታንን እንደሚያስነሳ አውጇል።

ታላቁ የእግዚአብሔር ሀይል የተገለጠው በኢየሱስ ብቻ ነው

ወንጌል እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ኢየሱስ ጋ


እንደሚመጡ ይናገራል።

"ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ


ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም
ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከርኵሳንም መናፍስት
ይሠቃዩ የነበሩት ተፈወሱ፤ ከእርሱም ኃይል ወጥቶ ሁሉን ይፈውስ ነበርና ሕዝቡ ሁሉ
ሊዳስሱት ይሹ ነበር።" ሉቃስ 6: 17-19።
መሐመድ ምንም ዓይነት ተአምር ወይም ምልክት እንዳደረገ በቁርኣን አንድም ቦታ ላይ
አለመጻፉ አስገራሚ እና እንዲሁም ለብዙ የሙስሊም ምሁራን ተስፋ አስቆራጭ ነው።
ሱራህ 28: 48 ላይ ይህ እውነት እንዲህ ተጽፏል፦ "እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው
ጊዜ «ለሙሳ የተሰጠው ብጤ አይስሰጠውም ኖሯልን» አሉ፡፡ «ከዚህ በፊት ሙሳ
በተሰጠው አልካዱምን የተረዳዱ ሁለት ድግምቶች ናቸው» አሉ"። ቁርአን ብዙ ሰዎች
መሐመድን ምንም አይነት ተአምር ባለማድረጉ እንዳላመነው ዘግቧል።(ሱራህ 20: 113
እና 29: 50 ጨምረው ይመልከቱ)

ኢየሱስ ብቻ ነው ታላቅ የእግዚአብሔር ኃይል ያለው፤ ኢየሱስ ብቻ ነው በእርሱ


የሚያምኑትን ሁሉ ከመንፈሳዊ እና አካላዊ በሽታ መፈወስ የሚችለው። ምናልባት
በህይወትህ ከገጠሙህ አሉታዊ ገጠመኞች የተነሳ በእረፍት ማጣት ውስጥ ልትሆን
ትችላለህ። ምናልባት ፈውስ ወይም እረፍት ያስፈልግህ ይሆናል፤ “እናንተ ደካሞች
ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ማቴዎስ 11፥28።

(
ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የእርሱ ቃል” ቃሊማቱሁ )

በቁርአን ኢየሱስ “የእርሱ ቃል” (Kalimatuhuu) ተብሎ ይጠራል፣ ትርጉሙም


የእግዚአብሔር ቃል ማለት ነው። ሱራህ 4:171 ላይ እንዲህ ተጽፏል፦ "... የመርየም
ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ
የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡"

ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ቃል" ስለመሆነ መጽሐፍ ቅዱስ እና ቁርአን ይስማማሉ

ቁራን ውስጥ መልኣኩ ለመሪያም የተናገራት እንደሚከተለው ተዘግቧል፦ "መላእክት


ያሉትን (አስታውስ)፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ
የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ
(ልጅ) ያበስርሻል፡፡»" ውድ አንባቢዬ፣ አምላክ ለማርያም የሰጣት ይህ “ቃል” እንዲሁ
የአገላለጽ ቃል እንዳልሆነ እና የክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ልብ በል።
ሱራህ 3:39 ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፦ "«አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል
የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል»"። አል ራዚ
የተሰኘው የእስልምና ሊቅ በዚህ ክፍል ላይ አስተያየት ሲሰጥ በዚህ ክፍል "ቃል"
የሚለው ቃል ኢየሱስን(ኢሳ) እንደሚያመለክት ይናገራል።

ቁርአን በሱራህ 3፡39 ላይ “ቃሉ” (ኢየሱስ) ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚመጣ


ያውጃል፤ በዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ(በቁርአን ነቢዩ ያህያ
ተብሎ የሚጠራው) ከተጻፈው ዘገባ ጋር ይስማማል።

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ ምጽአት መንገድ እንዲጠርግና


የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እንዲያበስር ከእግዚአብሔር የተላከ ነው። (ዮሐንስ 1:
23-27)።

መጽሐፍ ቅዱስ ለኢየሱስ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚለውን ማዕረግ በግልፅ ይሰጣል።


ራእይ 19፥13 ላይ እንዲህ ተጽፏል፦ “በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም
የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።”።

በቁርኣን እና በወንጌላት ውስጥ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚል ልዩ ማዕረግ የተሰጠው


ለኢየሱስ ብቻ ነው። ይህ ማዕረግ ከመለኮትነት ጋር የተያያዘ መሆኑ ግልጽ እና
ተቀባይነት ያለው ነው። ኢየሱስ ቃል ነው፤ የዚህ ቃል ምንጭ ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር
ነው። ምንም እንኳን ቁርኣን ለዚህ ማዕረግ ምንም ማብራሪያ ባይሰጥም፥ መጽሐፍ
ቅዱስ ግን ያብራራል።

ኢየሱስ(ቃል) ለሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ሙሉ መገለጥ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔር በራሱ "የእግዚአብሔር ቃል" ተብሎ


የተጠራው ኢየሱስ ብቻ መሆኑ እና ቁርኣንም በዚህ ሀሳብ መስማማቱ ኢየሱስ አንድ
እና ብቸኛው የእግዚአብሔር አእምሮ እና ፈቃድ ፍጹም መግለጫ መሆኑን በግልጽ
ያሳያል። ቆላስይስ 1፥15-16 ላይ እንዲህ ይላል፦ “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ
ነው፤ የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት
ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ
በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤”

ከውስጣችን የሚወጡ ቃላቶች ምን አይነት ሰው እንደሆንን እንደሚገልጡ ልናስተውል


ይገባል። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል (ኢየሱስ)
ለሰው ልጅ ሁሉ የተገለጠ የእግዚአብሔር አካላዊ መገለጥ ነው። ኢየሱስን ማወቅ
እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። ዮሐንስ 14፥9 ላይ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔን ያየ
አብን አይቶአል”። ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መገለጥ እና ቃል ለሰዎች ወደ ምድር
ማምጣቱ ብቻ ሳይሆን እርሱ ራሱ ከሰማይ ወደ ምድር የወረደ ቃል ነው። ዮሐንስ 1:
14።

የኢየሱስ ቃል ልእለ ተፈጥሮአዊ ነው

በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ የተናገራቸው ቃላት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆኑ ግልጽ


ነው። የኢየሱስ ቃል መለኮታዊ ሀይል እንዳለው ቁራን እንደሚያረጋግጥ ማስታወስ
አለብን። በቁርኣን እና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ የኢየሱስን ኃይል የተሞሉ ቃላት
ተመልከት።

- ኢየሱስ ለምጻሙን ሰውዬ “ንጻ” አለው፣ እንዳለውም ሰውየው ሙሉ በሙሉ ነጻ(ማር


1፡40–45፥ ሱራህ 3፡49 ይመልከቱ)።

- ኢየሱስ ሽባውን ሰውዬ “ኃጢአትህ ተሰረየችልህ” አለው እና የመራመድን ችሎታ


ሰጠው (ማርቆስ 2፡5)።

- ኢየሱስ የሞተችውን ልጅ “አንቺ ሴት ልጅ ሆይ ተነሺ” ባላት ጊዜ ከሞት


ተነስታለች(ማርቆስ 5፡21–43፥ ሱራህ 3፡49፥ ሱራ 5፡110 ይመልከቱ)።

- ኢየሱስ ማዕበሉን “ዝም በል! ጸጥ በል!" በማለት ጸጥ አሰኝቷል፤ በተፈጥሮ ላይ


ስልጣን እንዳለው አሳይቷል(ማርቆስ 4፡35-41)።

ልእለ-ተፈጥሮ የሆኑት የኢየሱስ ቃላት እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን


አድርገዋል። የታሪካዊው ኢየሱስ ቃላት ድውያንን ፈውሷል፤ ኃጢአትን አስተሰርዮአል፤
ሙታንን አስነስቷል። ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ዛሬም እንዲያ ያሉትን ቃላት
ይናገራል፣ ምክንያቱም እሱ አሁንም ሕያው ነው!

የእግዚአብሔር ቃል ዘለአለማዊነት

ውድ አንባቢዎቼ፥ አንድን ንግግር ስትናገሩ ይህ ንግግር ከእናንተ ውስጥ የወጣ ነው፤ ነገር
ግን ያ ራሱ ንግግር አሁንም እናንተ ውስጥ አለ። የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ
ከእግዚአብሔር ወጥቶ የመጣ ነው፤ ነገር ግን አሁንም በእግዚአብሔር ውስጥ ይኖራል።
ኢየሱስ ዮሐንስ 14፥10 ላይ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? ”
ይላል። እንዲሁም ዮሐንስ 10: 30 ላይ “እኔና አብ አንድ ነን።” ይላል።

"ቃሉ" ያለና የነበረ ነው

ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ማናቸው ነው ቀድሞ የመጣው? የእግዚአብሔር ቃል


የእግዚአብሔር ማንነት አካል እንደሆነ ግልጽ ነው። እግዚአብሔርን ከቃሉ ማንም ሊለይ
አይችልም።

በቁራንም በመጽሐፍ ቅዱስም ለኢየሱስ የተሰጠውን ይህንን "ቃል" የተሰኘውን


ማህረግ መጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ያብራራል።

"በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር


ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም
አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።" ዮሐንስ 1: 1-3።

ከላይ ከተቀመጡ ጥቅሶች እንደምንረዳው ቃል ከፍጥረት ሁሉ በፊት የነበረ ነው።


ኢየሱስ ለዘላለም የእግዚአብሔር ቃል ነበር። የቃሉ ምንነትና ተፈጥሮ መለኮት ነው፤
ይህም ኢየሱስ መለኮት መሆኑን ያሳያል።

ዘለአለማዊ ቃል ሰው ሆነ

በሰው አምሳል ወደ ምድር የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ብቻ ነው።


የእግዚአብሔር ሰው ህነ፤ የማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ። መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ
1:14 ላይ እንዲህ ይላል፦ “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥
አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”

ቃል ሰው ሆነ ማለት "ቃል"(ሎጎስ) ማንነቱን ለወጠ ወይም ቃል መሆንን አቆመ ማለት


አይደለም። "ሆነ" የሚለው ቃል "egeneto" ከተሰኘ የግሪክ ቃል የተተረጎመ ነው። ይህ
የግሪክ ቃል "ቃል" ተፈጥሮውን ቀይሮ ወደ ሰውነት እንደተለወጠ በፍጹም
አያመለክትም። ይልቅ፥ ተፈጥሮውን ሳይለውጥ ተጨማሪ ማንነትን እንዳገኘ ወይም
መለኮት'ነት ላይ ሰው'ነትን እንደጨመረ ነው የሚያሳየው።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚገናኘው በዘለአለማዊ ቃሉ አማካኝነት ነው

መለኮት ለሰው ልጆች በክርስቶስ አማካኝነት በሙላት ተገልጧል። እግዚአብሔር


ባህርይውን የሚገልጥልን እና በቀጥታ የሚገናኘን በቃሉ ወይም በኢየሱስ አማካኝነት
ነው ።

ወድ አንባቢዎቼ! አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ። እጅግ አብዝታቹ የምትወዱት ሰው


ቢታመም እንዴት ነው የምትጠይቁት? ደብዳቤ በመጻፍ ነው ወይስ በአካል በመሄድ?
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመገናኘት የመረጠው መንገድ የፍቅር እና የትህትና እንደሆነ
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስቀምጣል፤ ይሄውም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት በአካል
ወደ እኛ በመምጣት ነው።

ዶክተር ቃራዳዊ የተሰኘ እውቅ የእስልምና ሊቅ ስለ እግዚአብሔር ተፈጥሮ እንዲህ


ጽፏል፦ "የምናዳምጠው እንድናዳምጥ የሚረዳን የስሜት ህዋሳች ጋ በአየር አምካኝ
የድምጽ ሞገድ ሲደርስ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚያዳምጠው ከዚህ በተለየ
መንገድ ነው። የምናያው እንድናይ ወደሚረዳን የስሜት ህዋሳችን የብርሃን ጨረር
ሲደርስ ነው፤ እግዚአብሔር የሚያየው ግን ከዚህ በተለየ መንገድ ነው" የእግዚአብሔር
ቃል ከምናውቃቸው ማንኛውም ነገሮች የተለየ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል የተፈጠረ ነው ወይስ ያልተፈጠረ?

አል ባዳዊ የተሰኘው እውቅ ከሆኑ የእስልምና ሊቃውንት አንዱ ሰራህ 3: 39 ላይ


እንደሚከተለው አስተያየት ተሰጥቷል፦ "ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል የተባለው እሱ ልክ
እንደ እግዚአብሔር መጽሐፍ ስለሆነ ነው" ኢብኒ ሀዝም የተሰኘ ሌላኛው የእስልምና
ሊቅ ኢብኒ ሀንባል የተሰኘ የእስልምና ሊቅ ስለ እግዚአብሔር ቃል የሚከተለውን
እንደተናገረ ዘግቧል፦ "የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ እውቀት ነው፤
ስለዚህ የተፈጠረ አይደለም"

እግዚአብሔር ራሱ በአካል መጥት፥ የተጻፉ ትእዛዛትን ደግሞ ልኮልናል።


ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ፥ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ህመም ላይ ላሉት የሰው ልጆች
ካለው ጠንካራ ፍቅር የተነሳ ቅዱስ መጽሐፉን በመላክ ብቻ እንዳላበቃ እንዲገለጥላቹ
እጸልያለው፤ ከዚያም ባለፈ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የግል ሀኪማችን እና
አዳኛችን ለመሆን መርጧል።

ካሊፕ ማሞን(AD 786-833) የተሰኘ ከጥንታዊ የእስልምና መሪዎች አንዱ ለባግዳድ


አገረ ገዢ በጻፈው ደብዳቤ፥ ቁራን ያልተፈጠረ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች "እንደ
ክርስቲያኖች ናቸው፤ ክርስቲያኖችም የማርያም ልጅ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል
ስለሆነ የተፈጠረ አይደለም ብለው ያስባሉ" በማለት አጽንኦት ሰጥቶ ጽፏል።

ጥልቅ ውቂያኖስ ውስጥ ሊሰጥም የሚጣጣርን አንድ ሰው አስብ፤ ይህ ሰው ጨንቅላትን


ከውሀው ውስጥ አውጥቶ አየር መቀበል ፈተና ሆኖበት ይሰቃያል። ያ ሰው አንተ ብትሆን
ቢዚያ ሰዐት እጅግ በጣም የሚያስፈልግህ ነገር ምንድነው? ስለ ዋና የሚያስተምር
መጽሐፍ የሚወረውርልህ እና ጥረትህን እንድትጨምር የሚነግርህ ሰው? ወይንስ ዘሎ
ወደ ውሃው የሚገባ እና ከውሃው የሚያወጣህ ሰው? እግዚአብሔር የሰው ልጭ
በሀጥያት ጥልቅ ውስጥ እየሰጠመ እንዳለ እና እሱ ራሱ ሊታደገን በአካል እንደመጣ
በወንጌላት ይናገራል።

You might also like