Final Urban Moblization Plan On To Beat Plastic Pollution Edited

You might also like

Download as doc, pdf, or txt
Download as doc, pdf, or txt
You are on page 1of 10

የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

“የፕላስቲክ ብክለትን በመከላከል አካባቢያችንን ንጹህ እና ጤናማ እናድረግ”

“በካይ ፕላስቲክ ከመጠቀም እንቆጠብ”


የከተማ አስተዳደሮች የህዝብ ንቅናቄ መድረክ
የድረጊት መርሃ ግብር

መጋቢት 2016
አዲስ አበባ

1. መግቢያ

1
በሀገራችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን የከተሞች ዕድገትና መስፋፋት የሚያበረክተው አዎንታዊ አስተዋጽኦ
እንደተጠበቀ ሆኖ ይኸው ዕድገት በአግባቡ ካልተያዘና ዘላቂነት ባለው መልኩ ካልተመራ ለሰው ልጅና ለአካባቢ
ችግሮች መባባስ ምክንያት ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ በከተሞች የሚታየው ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት በርካታ ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የአካባቢ
ጫናዎች የሚያስከትል ሲሆን በከተሞች ያለው ደካማ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓት ችግሮቹ እንዲባባሱ
አስተዋፆ ያደርጋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በገጠርም ሆነ በከተማ ከአካባቢ ብክለት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረው ችግር ከባድና ውስብስብ እየሆነ
መጥቷል፡፡የሰው ልጅ የመኖር ህልውናውንም የሚፈታተን ሆኗል፡፡በከተሞች ከብክለት ጋር ተያይዞው የሚስተዋሉ
ችግሮች፣ የአካባቢ ሙቀት መጨመር፣ የብዝሐ ሕይወት መመናመን እና የአካባቢ መራቆትን ሲያስከትሉ ይታያሉ፡፡
በመሆኑም የአካባቢን ውበትና ፅዳት ችላ ማለት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከማዛባቱም ባሻገር የከተማን
ብሎም የሀገርን ገፅታ በእጅጉ ያጎድፋል፡፡
ሀገራችን እያስመዘገበች የምትገኘውን ፈጣን የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የከተሞች
ፅዳት፣ ውበትና አረንጓዴ ልማት ስራዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ ይሆናል፡፡ ይህም ሊሳካ
የሚችለው በመንግስት ጥረት ብቻ ሳይሆን ሁሉም የባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና በመቀናጀት
በሚያካሂዱት የለውጥ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለሆነም በሃገር አቀፍ ደረጃ በፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል በከተሞች
የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለትን ለመከላከል ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በመፍጠር በዘርፉ በተገኙ
ውጤቶች፣ እየተስተዋሉ ባሉ ተግዳሮቶች እና ለወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ አንድ ወር የሚቆይ የግንዛቤ
ስራ እና ውይይቶችን በማድረግ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን ያስችል ዘንድ ይህ የድርጊት መርሃ ግብር
ተዘጋጅቷል፡፡
የድርጊት መርሃ ግብሩ መነሻ ሁኔታዎችን፣ ዓላማ፣ ግብ፣ የሚከናወኑ ተግባራት፣ ተግባሩን የሚያስተባብሩ ኮሚቴዎች
እና የአፈፃፀም አቅጣጫን ያመላከተ ነው፡፡
2. የእቅዱ መነሻ ሁኔታ
ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢኮኖሚ ዕድገት እድገት መመዝገቡ፣ ነጻ የገበያ ስርዓት መኖሩ፣ ምቹ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ሁኔታ መፈጠሩ፣
የግሉ ተዋንያን ተሳትፎ እያደገ በመምጣቱ፣ የፕላስቲክ ቆሻሻ በመልሶ ኡደት እና ዳግም በመጠቀም የአካባቢ ብክለትን በመከላከል
ለገቢ ምንጭ መሆኑ እየታወቀ መምጣቱና በዘርፉም በርካታ ኢንቨስትምንት መስፋፋት እና ለአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል የስራ
እድል በመፈጠሩ ከዘርፉ የሚመነጭን ብክለት በመቀነስ የአካባቢ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ወሳኝና አዎንታዊ አበርክትኦ አለው፡፡

በሌላ በኩል በማህበረሰቡ እና በባለድርሻ አካላት ዘንድ የግንዛቤ ችግር መኖሩ በፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ተፅዕኖ
ሲያሳድሩ ይታያሉ፡፡ በሌላ በኩል የኢኮኖሚ እድገት መኖሩ የፕላስቲክ ፍጆታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
የከተሞች መስፋፋትና የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሃ ህይወት መመናመን፣ እና የአካባቢ ብክለት የተነሳ
ለመስኩ ትኩረት እንዳያገኝ በማድረግ ችግሩን ሊያባብሰው መቻሉ ተጠቃሽ ስጋቶች ናቸው፡፡

በሀገራችን ሕገ መንግስት የተደነገገውን የዜጎችን በንጹህ እና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብት እውን ለማድረግ የአካባቢ ፖሊሲን
ጨምሮ በርካታ የህግ ማዕቀፎች ተደንግገው በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

በ 1986 ጸድቆ በስራ ላይ የዋለው የሀገራችን የአካባቢ ፖሊሲም ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አከባቢያዊ ጥቅሞች ላይ
ትኩረት በማድረግ የበከለ ይክፈል፣ የቅድመ ጥንቃቄ እንዲሁም ቆሻሻን አካባቢያዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ እስከ መጨረሻው
ማጥራት መርሆች ላይ እንዲመሰረት ተደርጓል፡፡

1
በአካባቢ ፖሊሲ ላይ የተገለጹ መርሆችን በመጠበቅ ለከተሞች ጽዳት፣ የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እንዲሁም ለአጠቃላይ
የአካባቢ ደህንነት መጠበቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አዋጆች እና ደንቦች እንዲሁም ደረጃዎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ
ተገብቷል፡፡

በብክለት ቁጥጥር አዋጅ 300/1995 ዓ.ም እንዲሁም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ 513/99 ዓ.ም ከደረቅ ቆሻሻ የሚከተልን
አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና ጠቃሚነቱን ለማጎልበት የማህበረሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የማህበረሰቡን ተሳትፎ
ለማሳደግ የሚያስችሉና ውጤታማነቱን የሚያረጋግጡ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ ድረጊት መርሃ ግብሮች በታችኛው የመንግስት
አስተዳደር እርከን ታቅደው እንዲተገበሩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በዚህም በተለያየ ደረጃ የሚገለጹ ውጤቶች የተመዘገቡ
ሲሆን የከተማ ቆሻሻ በተወሰነ መልኩ የመሰብሰብና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ከቆሻሻ ሊከሰት
የሚችልን ብክለትና ብክነት መቀነስ ተችሏል፡፡ በዚህም በከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር
በቆሻሻ አያያዝ ላይ እንዲሳተፉ ተችሏል፡፡ በተለያዩ ከተሞች የቆሻሻ አያያዝ ችግር ያለባቸውን ከተሞች በሚደረጉ የህዝብ
ንቅናቄ ቋሚ የከተሞች ማጽዳት ጊዜም ወስነው እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡

ሃገራችን ምንም ዓይነት የፕላስቲክ ምረት አታመርትም ከተለያዩ ሃገራት የማስገባት ስራን ትሰራለችየሃገሪቱ የፕላስቲክ መጠቀም
ባለፉት አስራ አምስት ዓመታ ከ 400 እጥፍ በላይ አድጓል፡፡ ከነዚህ ውሰጥ የአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ምርቶችን
በመቀነስ ወይም በማቆም የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ መጠናከር ወሳኝ ነው፡፡

የፕላስቲክ ቆሻሻ በስብሶ ከአፈር ለመዋሃድ ከ 400 እሰከ 1000 ዓመታት ይፈጅበታል፡፡ ወደ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶችም
ይቀየራል በማይክሮ እና ናኖ ደረጃ በመሆን በሰው ሥርዓት(በደም እና በምግብ) በማግባት መርዛማ ኬሚካ እንድንበከል በዚህም
ለተለያዩ የጤና ችግር፣ የሆርሞን እና የስርዓት መዘባትን ያስከትላ፡፡

እንደ የተባባሩት መንግስታት የአካካቢ መርሃ ግብር በ 2023 ዘገባ መሰረት በየዓመቱ ከ 400 ሚሊዮን ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ
ይመነጫል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 19-23 ሚሊዮን ቶን በውሃማ አካለት ይወገዳል፡፡ በ 2022 እ.ኤ.አ የፕላስቲክ ቆሻሻ በኢትዮጵያ
ከተሞች የአካባቢ ችግር እያስከተሉ መሆኑን ተመላክቷል፣ በዚህም የአካባቢ እና የሰው የጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡

የፕላስቲክ ብክለት አካባቢን በተለያየ መንገድ ይጎዳል የአካባቢን ስርዓተንም ያዛባል የአየር ንብረት ለውጥን እንዳይቋቋሙም
መንስዔ ይሆናሉ፡፡ በዙህ በሃገራችን የሚሊዮኖችን ህይወት እንዲቃወስ ያደርጋል የምግብ እጥረት ያስከስታል፡፡

ቢሆንም በከተሞች ጽዳት እና ውበት ስራዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ እንዲሆን በማደረግ ዘርፉ የህዝብን እርካታ
ያረጋገጠ ያለመሆን፣ ሁሉንም ባለድረሻ አካላት ያሳተፈ እና ዘላቂነት የጎደለው የቆሻሻ አያያዝ ስርዓትን መከተል፣ ሁሉንም የህበተሰብ
ክፍል ባሳተፈ መልኩ ያለመከናወን እና በቆሻሻ ምክኒያት ከፍተኛ ችግሮች እያስከተለ መገኘት፣ በፕላስቲክ ቆሻሻ ምክኒያት ከተሞች
በክረምት የውሃ መውረጃ ቱቦዎችን በመድፈን የጎርፍ ስጋት በጋለጣቸው፣ የአካባቢ ውበት መበላሸት ፣ የተለያዩ እንስሳት መበላት፣
በመሬት ላይ በመዝረክረክ ለአፈር እና የአየር ብክለት መንስዓ እየሆኑ መምጣት፣ በዚህም ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ
ጉዳት ሊያስከትል በሚችል መልኩ ያለመያዝ ችግር እና የህግ ተከባሪነት ግቡን እንዳይመታ ተግዳሮት ሆኗል፡፡ በዚህም ላይ
በከተሞች የቆሻሻ አያያዝ በተለይም የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ግንዛቤ ገና ያልዳበረ እና በጅምር ላይ ያለ ነው፡፡ እንዲሁም የአካባቢን
እና የሰውን ጤና በሚያረጋግጥ መልኩ የፕላስቲክ ቆሻሻን የሚከሰትን ብክለት መከላከል ላይ የሚጠበቀውን ያህል
ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት አልተከናወነም፡፡

በአጠቃላይ ከተሞቻችን የሚያመነጩትን ከፕላስቲክ ቆሻሻ የሚመጣ ብክለትን ለመቀነስ፣ ከሌሎች ቆሻሻዎች በመለየት መልሶ
ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ፣ ለማጓጓዝ እንዲሁም ለማስወገድ የባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ የአሰራር ሥርዓት

1
አልተጠናከረም፡፡ ይህንንም ሁኔታ ደረጃ በደረጃ መቀየር እና ዘላቂነትን መረጋገጥ የሚቻለው መላውን ህዝብ ችግሩ ያለበትን ሁኔታ
ሲያውቅ እና የመፍትሄው አካል እንዲሆን ማድረግ ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም ይህ የድርጊት መርሃግበር በከተሞች እና ከተማ
አስተዳደሮች ዘንድ የሚስተዋለውን ከፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ሊከሰት የሚችልን ብክለት ለመከላከል የተዘጋጀ ነው፡፡
3. አስፈላጊነት
ከአካባቢ አያያዝ ጋር ተያይዘው ከፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ በከተሞች የሚከሰቱ ችግሮች ከባድና ውስብስብ እየሆኑ
መጥተዋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሐ ሕይወት መመናመን እና የአካባቢ ብክለት፣ በአካባቢ በሰው እና እንስሳት
ጤና ላይ ችግር በማስከትል የመኖር ህልውናን የሚፈታተን ሆኗል፡፡

የከተሞች ጽዳት በከተሞች ላይ የሚያሳድረው አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደተጠበቀ ሆኖ ለነዋሪዎች በማህበራዊ እና


ለኢኮኖሚያዊ ለውጥ የሚኖረው ሚና እጅጉን የጎላ ነው፡፡ በመሆኑም የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ለአካባቢ ለሰው እና
ለእንስሳት ጤና ጉድለት የተጋለጠ ነው፡፡

በሌላ በኩል የፕላስቲክ ውጤቶች ለሰው ልጅ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና የኢኮኖሚው ልማትን
ተከትሎ የመጣው የኑሮ ለውጥ፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የፕላስቲክ ውጤቶች ለአያያዝ ምቹ ከመሆናቸው ጋር
ተዳምሮ በመጠን በእጅጉ በመጨመራቸው ከፍተኛ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማስከተል ላይ
ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ችግሮቹ የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት በየደረጃው ህብረተሰቡን በማስተባበር የአንድ ጊዜ
አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ውጤቶች ከገበያ እንዲወጡ ማድረግና የተበከለውን አካባቢ በማጽዳት፣ መልሶ
ጥቅም ላይ መዋል የሚውሉትን በመልሶ ኡደት መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ አካባቢያችንን ለዜጎች ኑሮ
ምቹ በፅዱና ጤናማ አካባቢ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ ስለሆነም የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ችግር የአንድ ጊዜ
አገልግሎት የሚሰጡትን ፕላስቲክን ጨምሮ ከወዲሁ ትኩረት አግኝቶ በአፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጠው ጉዳይ መሆን
ይኖርበታል፡፡ የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ስርዓት የመዘርጋት እና የመተግበር ኃፊነት የሁሉም አካላት ኃላፊነት ነው፡፡
ከዚህም አኳያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትና የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ
ከተሞችና የከተማ አስተዳደሮች ችግሩን የጋራ በማድረግ በጉዳዩ ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማዳበር የችግሩና
የመፍትሄው ባለቤትነትነትን በማረጋገጥ የጋራ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በመሆኑም በሃገራችን የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች
መላው ህዝባችን በንቃት በማሳተፍ ችግሩን ለመፍታት የህዝብ ንቅናቄ ተግባራት የሚከናወንበት በከተማ
አስተዳደሮች ለአንድ ወር የሚቆይ የሚመራበት የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡

4. ዓላማ
በከተሞች እና የከተማ አስተዳደሮች የፕላስቲክ ቆሻሻ ሊመነጭ የሚችልን ብክለት ለመከላከል ዘላቂ የፕላስቲክ
ቆሻሻ አያያዝ እንዲኖር የከተማውን ነዋሪ እና የህብረተሰብ ግንዛቤን በማዳበር፣ ስርዓትን በመዘርጋት የህግ ተከባሪነት
ሥራን ማጠናከር ይሆናል፡፡

5. የዕቅዱ ዋና ግብ

በከተሞች እና ከተማ አስተዳደሮች ህዝብ ዘንድ የፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለትን መከላከያ መንገዶች ላይ ግንዛቤን
በማሳደግ የባለድርሻ አካላት እና ለህዝብ ዘላቂ፣ ንጽሁና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ መፈጠሩን ማረጋገጥ ነው፡፡
6. ኃላፊነቶች:

1
I. የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የክልል አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን/ቢሮዎች
1. ለግንዛቤ ንቅናቄው አጠቃላይ መመሪያ እና ስልታዊ አቅጣጫ ይስጣል፡፡
2. የግንዛቤ ንቅናቄውን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር፣ ከክልል የከተማና መሰረተ
ልማት ቢሮ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያስተባብራል.
3. ለመገናኛ ብዙሃን ማሰጨበጫ የሚሆኑ የግንዛቤ ንቅናቄ ጽሁፎችንና እና ግብዓቶችን
ያዘጋጃል.
4. የግንዛቤ ንቅናቄው እንቅስቃሴዎችን አፈፃፀም ይከታተላል እና ይገመግማል
5. የግንዛቤ ንቅናቄው ውጤት እና ለወደፊት ልምድ ሊሆኑ የሚችሉትን አጠቃላይ
የሪፖርት ያዘጋጃል ለሚመለከተው ተደራሽ ያደርጋል፡፡
II. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር እና የክልል ቢሮዎች
1. የግንዛቤ ንቅናቄው ስራ ወደ ከተሞች እና የከተማ አስተዳደር እንዲወርድ ይደግፋል ያመቻቻል፡፡
2. በየክልሉ ከሚገኙ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮዎች እና ጽ/ቤቶችን በማስተባበር ግንዛቤ ንቅናቄው
ትግበራ አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርጋል፡፡
3. ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለግንዛቤ ንቅናቄ የቴክኒክና የግብዓቶ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
4. የግንዛቤ ንቅናቄ ስራውን እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ያቅዳል አፈፃፀም ይከታተላል እና ይገመግማል
ለሚመለከተው አካል በሪፖርት ያቀርባል፡፡
III. ከተሞች እና ዝቅተኛው የከተሞች አደረጃጀት(ክፍለ ከተማ/ቀበሌ)
1. በከተሞቻቸው ውስጥ የግንዛቤ ንቅናቄውን አፈፃፀም አስተባባሪ ኮሚቴ ያደራጃሉ
2. በተሞች ከሚገኙ የአከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን
ያቅዳሉ፣ ያካሂዳሉ፣ ይገመግማሉ ዘገባ ለሚመለከተው ያቀርባሉ፡፡
3. የከተማ ነዋሪዎችን፣ የመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን
በየግንዛቤ ንቅናቄው ስራ ላይ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ ያስተባብራሉ፡፡
4. በከተሞቻቸው ውስጥ ዘላቂ የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አሰራሮችን ይዘረጋሉ፣
ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራሉ፡፡
5. በከተሞች አደረጃጀት ውስጥ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ተቋማት መለየትና እውቅና መስጠት፡፡
6. በከተሞች የከተማውን ማህበረሰብ እና ሌሎች ተቋማትን በማሳተፍ የከተማ ጽዳት ስራዎችን
ማከናወን፡፡
7. በከተሞች የሚገኙ የኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ሚዲያዎችን በመጠቀም ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል
የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ እና ብክለትን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራ ይሰራሉ፡፡
7. የሚጠበቅ ውጤት
1. በፌደራል እና ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ተቋማት፣ በከተሞች እና ከተማ አስተዳደሮች ስለ
ጉዳዮ ዙሪያ የተዘጋጀ ዝርዝር እቅድ፡፡
2. ከፕላስቲክ ብክለት ነጻ የሆኑ ተቋማት እና ከተሞች ብዛት፡፡
3. በፕላስቲክ ብክለት እና በዘላቂ የቆሻሻ አወጋገድ ልምዶች ላይ ተደረሻ የሆነ የህበረተሰብ
ክፍል እና መረጃ ፡፡

1
4. የጽዳት ዘመቻ ያከናወኑ ከተሞች ዝርዝር እና የተገኘ ውጤት፡፡
5. የንቅናቄውን አፈጻጸም የሚገልጽ የክትትል እና የግምገማ ሪፖርት
6. እንደየ ከተሞች እና ተቋማት ነባራዊ ሁኔታ ውጤቶች ሊጨመሩ ይችላሉ
8. ኮሚቴው አደረጃጀት
እንደየ የከተሞች እና ተቋማት አደረጃጀት ስራውን የሚያስተባብሩ እና የሚከታተሉ ኮሚቴዎች
ይዋቀራሉ፡፡
8.1.1. የኮሚቴው ተግባር እና ኃላፊነት
 ማስፈጸሚያ እቅድ ያዘጋጃል
 መድረኮችን ያዘጋጅል ያስተባብራል
 በከተማው የጽዳጽ ስራዎችን ያስተባብራል
 የህዝብ ውይይት እና የግንዛቤ ስራዎችን ይመራል በተለያዩ መንገዶች መተላለፉን ይከታተላል፡፡
 የተግባራት አፈጻጸምን በመገምገም ዘገባ ያዘጋጃል
 የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ከተሞች/ተቋማት በመለየት እውቅና ይሰጣል
በክልል/ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ አስተባባሪ ኮሚቴ
6. ክትትል እና ድጋፍ
የግንዛቤ ንቅናቄውን ለማሳካት፣ በከተሞች አና ተቋማት በፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ተጽእኖ እና መፍትሄ
ላይ ግንዛቤ ተፈጥሮ፣ በከተሞች አና የከተማ አስተዳደሮች ተሳትፎውን በተግባር በማረጋገጥ ሁሉም
ከተሞች ከፕላስቲክ ብክለት የጸዳ ንጹህ እና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ክትትል እና ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡
 በፌደራል አስተባባሪ ኮሚቴ የንቅናቄውን አካሄድና ውጤት በሳምንት መገምገም
 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ የንቅናቄውን አካሄድና ውጤት በ የሁለት ቀናት መገምገም
 በከተሞች እና ከተማ አስረዳደሮች ደረጃ የንቅናቄውን አካሄድና ውጤት በየዕለቱ መገምገም
 በፌደራል እና የክልል አብይ ኮሚቴ ከተማ/ወረዳ እና በከተሞች አንድ ዙር በአካል በመገኘት
ድጋፍና ክትትል ማድረግ ሪፖርት ማዘጋጀት፡፡
9. የአፈጻጸም አቅጣጫ
 ለሁሉም ተግባራት አስፈጻሚ ኮሚቴ ይኖረዋል
 መድረኮቹ ሰነድ በማዘጋጀት ይከናወናል
 ሁሉም ተግባራት ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፣ ዘገባ ይዘጋጃል፣ በሰነድ ይያዛል፤
 የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ችግር ሊሻሻል የሚችለው የሁሉንም ተሳትፎ ሲኖር ሲሆን ተሳትፎን
በሚያጠናክር መልኩ መሆኑን ይረጋገጣል፡፡
 ለሁሉም ተግባራት የእቅዱን ያለመና በእቅዱ መሰረት መተግባር ይኖርበታል፡፡
10. የሚጠበቅ ውጤት
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአንድ ወር የሚቆይ የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ ላይ የተለያዩ የህዝብ ግንዛቤ በማሳደግ የህግ ተከባሪነትን ስራ
በማጠናከር ዘላቂ የአካባቢ አያያዝን ማረጋጥ የሚያስችል መነሻ ተግባረትን ማከናወን ሲሆን የሚከተሉት ውጤቶች
ይጠበቃሉ፡፡

1
1. ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እና የባለድርሻ አካለት የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ላይ የተዘጋጀ የውይይት
መድረክ፡፡
2. ጉዳዩ ለሚመለከታችው የባለድርሽ አካለት የፕላስቲክን ብክለት በተለመለከተ የተሰጠ ገለጻ እና ለህብረተሰቡ ተደረሽ
የተደረገ መልእክት፡፡
3. በቆሻሻ አያያዝ (ቆሻሻን መልሶ መጠቀም) ስራ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን የመስክ ጉብኝት በማድረግ ዘርፉ እንዲበረተታታ
ማስቻል፡፡
የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተቋማት እና ያደገ የግንዛቤ ሥራ በፕላስቲክ ብክለት መከላከል ላይ፡፡

1
11. በከተማ እና ከተማ አስተዳደሮች የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ የህዝብ ግንዛቤን ለመፍጠር የተዘጋጀ የማስፈጸሚያ መርሀ ግብር

ተ/ቁ ዋና ተግባር ተግባራት ፈጻሚ የጊዜ ሰሌዳ

1. ሀገር አቀፍ ደረጃ የግንዛቤ ንቅናቄ ለማዘጋጀት ኮሚቴዎች ማቋቋም በየፌደራል መ/ ቤቶች ከሚያዚያ1 እስከ 3 /2016 ዓ.ም
የግንዛቤ ንቅናቄ ስራ የሚቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ
የዝግጅት እና የተግባር ለግንዛቤ ንቅናቄው አጠቃላይ መመሪያ እና ስልታዊ አቅጣጫ ይስጣል፡፡ በየፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ንዑስ ከሚያዚያ1 እስከ 3 /2016 ዓ.ም
ምዕራፍ መደገፍ እና ኮሚቴ
መከታተል፡፡ የግንዛቤ ንቅናቄውን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር፣ ከክልል የከተማና በየፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ንዑስ ከሚያዚያ 1 እስከ 3 /2016 ዓ.ም
መሰረተ ልማት ቢሮ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያስተባብራል. ኮሚቴ
ለመገናኛ ብዙሃን ማሰጨበጫ የሚሆኑ የግንዛቤ ንቅናቄ ጽሁፎችንና እና ግብዓቶችን በየፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ንዑስ ከሚያዚያ 1 እስከ 5/2016
ያዘጋጃል. ኮሚቴ
የንቅናቄ መድረኩን ሎጀስትክ ማዘጋጀት የሚሳተፉ ከተሞች እና ተቋማትን በየፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ንዑስ ከሚያዚያ 1 እስከ 5/2016
መለየት ኮሚቴ
የግንዛቤ ንቅናቄው እንቅስቃሴዎችን አፈፃፀም ይከታተላል እና ይገመግማል የፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ንዑስ ኮሚቴ ከሚያዚያ 1እስከ 30 /2016
የግንዛቤ ንቅናቄው ውጤት እና ለወደፊት ልምድ ሊሆኑ የሚችሉትን አጠቃላይ በየፌደራል መ/ ቤቶች የሚቋቋም ከሚያዚያ 25 እስከ 30/2016ዓ.ም
የሪፖርት ያዘጋጃል ለሚመለከተው ተደራሽ ያደርጋል፡፡ አስተባባሪ ኮሚቴ

2. በከተሞች የግንዛቤ የተቋማት የግንዛቤ ንቅናቄ መድረክ የሚመራበት እቅድ ማዘጋጀት የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 7 /2016 ዓ.ም
ንቅናቄ ስራዎችን
ማዘጋጀትና መፈጸም የንቅናቄ ስራ አዘጋጅ ኮሚቴ ማቋቋም የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 7 /2016 ዓ.ም
በከተሞች ተቋማት ግንዛቤ ማወያያ ሰነድ ማዘጋጀት የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 3 /2016 ዓ.ም
በከተሞች ውይይት የሚሳተፉ አካላት በመለየት ውይይት ማካሄድ የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ 7እስከ 15 /2016 ዓ.ም

በከተሞች እና ተቋማት የጽዳት ቀን ማስወሰን እና መተግበር የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ 7እስከ 15 /2016 ዓ.ም
በከተሞች ማህበረሰብ ተሳትፎ በከተሞች ተቋማት የማጽዳት ዘመቻ ማካሄድ የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ 10 እስከ 20/2016ዓ.ም
በከተሞች መለየትና እውቅና መስጠት የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ 25እስከ 30/2016 ዓ.ም
የግንዛቤ ንቅናቄ ስራዎች አፈጻጸም የሪፖርት ዘገባ ማዘጋጀት እና የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ 25 እስከ 27/2016 ዓ.ም
ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ
3. ከተሞች እና ከተሞቻቸው ውስጥ የግንዛቤ ንቅናቄውን አፈፃፀም አስተባባሪ ኮሚቴ የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 7 /2016 ዓ.ም
ዝቅተኛው የከተሞች ያደራጃሉ

1
ተ/ቁ ዋና ተግባር ተግባራት ፈጻሚ የጊዜ ሰሌዳ

አደረጃጀት(ክፍለ በተሞች ከሚገኙ የአከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር የግንዛቤ የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 27 /2016 ዓ.ም
ከተማ/ቀበሌ) ማስጨበጫ መድረኮችን ያቅዳሉ፣ ያካሂዳሉ፣ ይገመግማሉ ዘገባ
ለሚመለከተው ያቀርባሉ፡፡
የከተማ ነዋሪዎችን፣ የመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 27 /2016 ዓ.ም
እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በየግንዛቤ ንቅናቄው ስራ ላይ ውስጥ
በንቃት እንዲሳተፉ ያስተባብራሉ፡፡

በከተሞቻቸው ውስጥ ዘላቂ የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ1 እስከ 7 /2016 ዓ.ም
አሰራሮችን ይዘረጋሉ፣ ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራሉ፡፡

በከተሞች አደረጃጀት ውስጥ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ተቋማት የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ25 እስከ 27 /2016 ዓ.ም
መለየትና እውቅና መስጠት፡፡
በከተሞች የከተማውን ማህበረሰብ እና ሌሎች ተቋማትን በማሳተፍ
የከተማ ጽዳት ስራዎችን ማከናወን፡፡
በከተሞች የሚገኙ የኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ሚዲያዎችን በመጠቀም የከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ ከሚያዚያ12 እስከ 27 /2016 ዓ.ም
ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የፕላስቲክ ቆሻሻ አያያዝ እና ብክለትን
መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስራ ይሰራሉ፡፡

1
1

You might also like