Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 4

በንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

የነዲጅና ኢነርጂ ባለሥሌጣን

በነዳጅ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ እና በነዳጅ አቅርቦትና ሎጅስቲክስ ዳይሬክቶሬት

ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማ ነዳጅ ቀጥታ ተጠቃሚ ላይ የተደረገ የመስክ ኢንስፔክሽን

ሪፖርት

ሚያዚያ 01/2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ
መግቢያ

ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን ነዳጅን ከኩባንያዎች በቀጥታ በመግዛት ለሚጠቀሙ ተቋማት በፈቃድ አሰጣጥ

መመሪያ ቁጥር 905/2014 መሰረት የነዳጅ ቀጥታ ተጠቃሚ ተቋማት የሚያቀርቡትን የነዳጅ ውጤቶች

ፍላጎት ተቋማቱ ከሚያከናውኑት ሥራ እና ከሚሰጡት የህዝብ አገልግሎት ጋር በማገናዘብ መጠኑን ይወስናል፣

የተጠቃሚነት ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ቀጥታ ተጠቃሚዎች የቀረበላቸውን የነዳጅ ውጤቶች ለተፈቀው ዓላማ ብቻ

ማዋላቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡ በመመሪያው ላይ የተቀመጡ ግዳታዎችንና ክልከላዎችን ያላከበረ

ወይም የጣሰ ቀጥታ ተጠቃሚ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዲሌ፡፡ እንደአጠቃላይ የነዳጅ ውጤቶች

ማከማቻ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርት ያወጣል፣ በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት መገንባታቸውን

በማረጋገጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ይሰጣል፣ ቀጥታ ተጠቃሚው ማሟላት የሚጠበቅበትን መስፈርት

አሟልቶ ማቅረቡ ሲረጋገጥ ጥያቄ ላቀረበው አካል ሽያጭ እንዲፈጸምለት ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ

ድርጅት፣ ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ በደብዳቤ መፈቀዱን ያሳውቃል፡፡

በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማ የነዳጅ ትስስር ፈቃድ
ለመ/ቤታችን ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አካባቢ
ለኮሜርሻል እና መኖሪ ቤቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ነዳጅ ለምን ዓላማ እንደሚጠቀሙበት፣
የተገነባውን የነዳጅ ማከማቻና ለመቅጃነት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ላይ ከደህንነት ሁኔታ፣ አካባቢ ጥበቃ እና
የማህበረሰቡን ጤና በማይጎዳ መልኩ መሰራቱን ለማረጋገጥ ከነዳጅ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት
እና ከነዳጅ አቅርቦት እና ሎጅስቲክስ ዳይሬክቶሬት ሁለት ባለሙያዎች በቦታው ላይ ተገኝተን የተከናወኑ
ስራዎችን ባየነው እና በያዝነው መረጃ መሰረት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ዓላማ
 ከፍተኛ የነዳጅ ውጤቶች ፍጆታ ያላቸው ተቋማትን ከጅምላ አከፋፋይ ኩባንያዎች በቀጥታ

በመግዛት እንዲጠቀሙ ማስቻል፤

 የነዳጅ ቀጥታ ተጠቃሚነት ፈቃድ የሚሰጥበትና ነዳጁ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ

የሚያስችል የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት፡፡

ግብ

 የነዳጅ ተቋማት በአካባቢና ህብረተሰብ ላይ ብክለቶችና ጉዳቶችን እንዳያደርሱ ተደርገው የተሰሩ


መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
 ነዳጅ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ፡፡

የተሰሩ ሥራዎች

ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አካባቢ ለኮሜርሻል
እና መኖሪ ቤቶች ግንባታው የሚከናወንበትን ቦታ የማስተካከልና የመሰረት (basement) ሥራ እየሰሩ እንደሆነ
የተረጋገጠ ሲሆን ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 580 ሺህ ሔክታር ስፋት ያለው ቦታ ሲሆን 60 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት

የታሰበ እና 30 ኪ.ሜ መንገዶችን የሚያገናኝ ግንባታ ያለው ፕሮጀክት ነው፡፡ በተደረገው የክትትልና የቁጥጥር

ሥራ ላይ የሚከተሉት ተግባራት ተከናውነዋል፡-

፡፡ አገልግሎት የሚውል ነዳጅ

 ሁለት ባለ 50 ሺህ ሊትር በድምሩ 100 ሺ ሊትር የመያዝ አቅም ያላቸው የነዳጅ ታንከሮች
አስፈላጊውን እስታንዳርድ አሟልተው የተገነቡ ሲሆን የነዳጅ ማከማቻው የተቀመጠበት ቦታ ከህዝብ
መገልገያ ስፍሪያ የራቀ ነው፡፡
 ድርጅቱ በዋነኛነት ነዳጅ የተፈለገው 488 ሄክታር ላይ የሚያርፉ 60,000 መኖሪያ ቤቶች ከግራውንድ
ፕላስ 33 እስከ ግራውንድ 8 ፍሎር ህንፃዎች እና በያንዳንዱ ህንፃ እስከ 4 ቤዝመንት ድረስ የመኪና
ማቆሚያ አገልግሎት ለሚሰጡ እንደሚገነቡ አሳውቀውናል፡፡
 በወር የነዳጅ ፍጆታው ከአንድ ነዳጅ ማመሊለሻ ቦቴ ወይም ከ 46,000 ሊትር በላይ መሆኑ
ተረጋግጧል፤
 የነዳጅ ፍላጎት ጥያቄ ካቀረቡት ቀጥታ ተጠቃሚ ተቋማት መካከል ኦላ አንዱ ተቋም ሲሆን የቀረበው

የነዳጅ ፍላጎት 200,000 ሊትር ነው፤ ነገር ግን ከሚያከናውኑት ሥራ ጋር በማገናዘብ መጠኑ የበዛ

መሆኑን እየገለጽን 150,000 ሊትር ቢፈቀድላቸው የተሻለ ይሆናል፤

 ቀጥታ ተጠቃሚዎች የሚቀርብላቸውን ነዳጅ ለተፈቀደው ዓላማ ብቻ ማዋል እናዳለባቸው

ማሳሰቢያ ተሰጧል፤

 የቀረቡትንና የተጠቀሙበትን የነዳጅ ዓይነትና መጠን፣ የተደራጀ መረጃ መያዝና በየ 3 ወሩ

ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ማቅረብ እናዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጧል፤

You might also like