Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 17

የአአትሪኮን ማህበር የእንጀራ መጋገር እና የዳቦ ሱቅ ስራ መመሪያ

ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም

አዲስ አባባ ኢትዮጵያ


መግቢያ

የአአትሪኮን ማህበር በ 2015 ዓ.ም የተመሰረተ የግል ማህበር ሲሆን የእንጀራ መጋገር ስራ በመጀመር ሲሰራ
የቆና እና ስራውን በማስፋት የዳቦ ጭርቻሮ ስራ በመጀመር በጠንካራ አባሎቹ ብርታትና ጥንካሬ ለአስር ወር
ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ሥራው ብዙ ውጣውረድ የሚጠይቅ እና የቅርብ ክትትል የሚፈልግ ከመሆኑ አንፃር የአባሉን
የስራ ጫና ለመቀነስ እና በድርጅቱ ለሚቀጠሩ ባለሙያዎች ቀልጣፋ የአሰራር ስልት እንዲኖር ለማድረግ፤

ማህበሩ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስችል የሰው ሃይል፣ ገንዘብ እና ንብረትን በስራ ላይ ማዋል
የሚያስችል የአደረጃጃት መዋቅርና የሰው ሃብት አስተዳደር ስርዓት ሊኖራቸው የሚገባ በመሆኑ፤

ማህበሩ ስራን በአግባቡ ለማቀድ፣ ለማደራጀት፣ ለመምራት፣ ለመቆጣጠር እና አስፈላጊ ውሳኔዎችን በወቅቱ
በመስጠት ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል በማስፈለጉ፤

ማህበሩ የሰራተኞችን አደረጃጀት በማዘመን እንደየስራው ስፋት እና ክብደት የሰው ሀይል አስተዳደር ስርዓትን
የተከተለ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤

ማህበሩ የሰራተኞችን ተጠያቂነትንና ግልጸኝነትን ያሰፈነ አሰራር እንዲኖር ለማስቻል ይህን መመሪያ
አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

የአአትሪኮን ማህበር የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር

1. የአአትሪኮን ማህበር የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር

1
ሀ. ማንኛውም በአአትሪኮን ማህበር ውስጥ የሚሰራ ሥራ የማህበሩን አሰራር ተከትሎ የተዘጋጀ የሰው ኃይል
ድርጅታዊ መዋቅር ይኖረዋል፡፡

ለ. በዚህ ክፍል የተዘጋጀውን መመሪያ ማህበሩ የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅሩን እና ተግባሩን ሲያሰፋ
ወይም ሲያጠብ በጥናት ላይ ተመስርቶ የሰው ኃይል መዋቅሩን ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

2. የአአትሪኮን ማህበር የሰው ሃይል አደረጃጀት መዋቅር በሚዘጋጅበት ወይም በሚሻሻልበት ወቅት
የሚከተሉትን ጉዳዮችን ታሳቢ ማድረግ አለበት፣

ሀ. የማህበሩን የካፒታል አቅም ወይም እድገት መሰረት ያደረገ፣

ለ. ማህበሩ የሚሠጣቸው የአገልግሎቶች አይነት፣ ስፋትና የሚጠይቀውን ጊዜ መሰረት ያደረገ፣

መ. አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የአሰራር ዘዴዎችን በመጠቀም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት


የሚያስችሉ አሰራሮችን የዳሰሰ፣

ሠ. ጊዜን እና ወጭን ቆጣቢ በሆነ መንገድ አገልግሎት መስጠትን መሰረት ያደረገ፣

ረ. ማህበሩ የሚጠብቀውን ውጤት የዳሰሰ ይሆናል፡፡

3. ማህበሩ የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር በሚያዘጋጅበት ወይም በሚያሻሽልበት ወቅት ባለሙያ ወይም
በሙያው የተሻለ ክህሎት ባላቸው ሰዎች የዳሰሳ ጥናት ተደርጎ በስራ አመራር ኮሚቴ ወይም ቦርድ
ተገምግሞ ትክክለኛነቱ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

4. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 ተጠንቶ የጸደቀው የማህበሩ የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር ተግባራዊ
የሚሆነው ከዚህ በታች የተገለጹ ነጥቦችን ማሟላት ይኖርበታል፣

ሀ. የማህበሩ የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር የጥናት ውጤት በጠቅላላ ጉባኤ ከጸደቀ በኋላ፤

ለ. የሰው ኃይል ድርጅታዊ መዋቅር የእያንዳንዱን ሠራተኞች የሥራ መደብ ተጠሪነት፣ መብት፣ ግዴታ፣
የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የደመወዝ ክፍያ መጠን በአንድ ላይ ማካተት ይኖርበታል፡፡

5. አስፈልጊ የሰው ኃይል እና ተጠሪነት

ሀ. ማህበሩ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ሰራተኞችን ቀጥሮ ማሰራት አለበት፡፡

ለ. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ ይሆናል፡፡

2
ሐ. የማህበሩ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለማህበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም ዋና ስራ አስኪያጅ
ይሆናል፡፡

ሐ. የማህበሩ ሰራተኞች ተጠሪነታቸው ለማህበሩ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይም ተወካይ ሥራ አስኪያጅ


ይሆናል፡፡

መ. የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤው ወይም ማናጀር ሊሆን ይችላል፡፡

6. ማህበሩ የሰው ኃይል ለማሟላት ዝርዝር መዋቅር እና የሰው ኃይል በማጥናት ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡

3
ክፍል ሁለት

የማህበሩ ዋና ሥራ አስኬያጅ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና የቅጥር ሰራተኛ ተግባርና ኃላፊነት

7. የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም ለጠቅላላ ጉባኤ ሆኖ የሚከተሉት
ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡

ሀ. የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ሥራውን በብቃት በመምራት የታቀደውን ግብ


ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ለ. የማህበሩን ሥራ ያስተባብራል፣ ያቀናጃል፣ ይቆጣጠራል፣ የተከሰቱ ስህተቶች በወቅቱ እንዲታሩሙ


ያደርጋል፡፡

ሐ. የሥራ አቅጣጫዎችን ሃሳቦችን ይተነትናል፣ የተሰጠውን ሥራ በሕጎች፣ በደንቦችና በመመሪያዎች


መሠረት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

መ. ቢዝነስ ፕላን ወይም የሥራ ዕቅድ፣ በጀትና የስራ መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ለሥራ አመራር ኮሚቴ
ወይም ዋና ስራ አስኬያጅ ያቀርባል፣ ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፤

4
ሠ. ሠራተኞችን ይቀጥራል፣ በሠራተኞች አደረጃጀትና አስተዳደር መመሪያ መሠረት ያስተዳድራል፣
ያሰናብታል፣ የሥራ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፤

ረ. ከሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የባንክ አካውንት ይከፍታል፣ በተሰጠው ኃላፊነትና ውክልና
መሠረት ክፍያ ይፈጽማል፤

ሰ. የማህበሩን የሂሳብ ሰነዶች በአግባቡ እንዲያዝና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል፤

ሸ. ማህበሩ በተጠናከረና በተስተካከለ ሁኔታ ሥራውን እንዲያከናውን የሥራ አመራር ኮሚቴውን ያማክራል
የተሻሻሉ የአሠራር ስልቶች እንዲቀየሱ ያደርጋል፡፡

ቀ. የማህበሩ ገንዘብ፣ ሀብትና ንብረት ምርታማነትን ለማሳደግ በአግባቡና በተገቢው መንገድ በሥራ ላይ
መዋሉን ይቆጣጠራል፤

በ. ወቅታዊ የሥራ ሪፖርት ለሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፤

ተ. ወቅታዊ የሥራ ሪፖርት እንደ አስፈላጊነቱ የሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም ቦርድ በማጸደቅ ሪፖርት
ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤

ቸ. በተጨማሪ ከሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም ቦርድ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

8. የዋና ሥራ አስኬያጅ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖሩታል፤

ሀ. ጠቅላላ ጉባኤው ወይም የቴክኒክ ኮሚቴው የሚያወጣቸውን መተዳደሪያ ደንብ እና መመሪያዎች


በሥራ ላይ የማዋል፣

ለ. ለማህበሩ መተዳደርያ ደንብ፣ የአሰራር መመሪያዎችንና ማኑዋሎች ተገዥ መሆን አለበት፤

ሐ. ሙሉ ችሎታውንና ያለውን አቅም በመጠቀም ማህበሩን ትርፋማነት ማሳደግ፤

መ. ስራውን በታማኝነት የመስራት፤

ሠ. በመጠጥ ወይም አእምሮን የሚያደነዝዝ እጽ ተጠቅሞ በስራ ገበታ ያለመገኘት፤ የማህበሩን የስራ ስዓት
የማክበር፣ እንዲሁም በመደበኛ የስራ ስዓት ከማህበሩ ስራ በስተቀር ሌላ የግል ስራ አለመስራት፤

ረ. የማህበሩን ንብረት ወይም በኃላፊነት የተረከበውን ንብረት በጥንቃቄ የመጠቀም እና የመጠበቅ፤

5
ሰ. የሚመለከተው ኃላፊ ሳይፈቅድ ማንኛውንም ንብረት፣ መሳሪያ ወይም ቁሳቁስ መውሰድ ወይም ለሌላ
አሳልፎ መስጠት ወይም ከማህበሩ ስራ ጋር ላልተያያዘ ተግባር አለማዋል እና ሌሎችም
እንዳይፈጽሙ መቆጣጠር፤

ሸ. ብክነትን፣ ምዝበራን፣ ዝርክርክነትን፣ አላግባብ በስልጣን መጠቀም ማስወገድ፤ ግደታ አለበት፡፡

ቀ. የማኅበሩን ስትራተጂክ ፕላን፣ ዓመታዊ ዕቅድና በጀት ያሻሽላል፣ ያፀድቃል፤


በ. በሚቀርቡለት ወርሀዊ እና ዓመታዊ የሥራ ክንውንና የኦዲት ሪፖርቶች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች
ላይ ይመክራል፣ ይወስናል፤
ተ. የማኅበሩን የስራ መዋቅር ያሻሽላል፣ ስራ አስኬያጅ፣ ፋይናንስ፣ ግዥና ኦዲተር ይሾማል፣ ያግዳል፣
ያሰናብታል፤
ቸ. ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ያልቻሉ የማኅበሩን ተመራጮች ከኃላፊነት ያሰናብታል፤
ኀ. ማህበሩ ንግድ ጋር የተያያዙ ማንኛውም የንግድ ልውውጥ በተመለከተ ከሶስተኛ ወገኖች

ጋር ይዋዋላል፤
ነ. በማናቸውም ፍ/ቤት ማህበሩ ከሳሽ ተከሳሽ ወይም ጣልቃ ገብ በሚሆንበት ጉዳይ ለሚጠራው
የውጭ ስብሰባ ሁሉ ማህበሩን በመወከል አስፈላጊውን ይፈፅማል፤
ኘ. ጠቅላላ ጉባኤውን ስብሰባ ይጠራል በዕለቱ ጸሀፊ ይወክላል፤

9. የእንጀራ ቤት ምክትል ስራ አስኬያጅ ኃላፊነት

ሀ. ሙሉ ድርጅቱን በመቆጣጠር የማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፤


ለ. እለታዊ፣ ወርሃዊ እና አመታዊ እቅዶችን ያወጣል፤ በየጊዜው ጥናትና ምርምር በማድረግ የሚሰሩ
ስራወችን ፕሮፖዛል ይቀርፃል፤
ሐ. አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማናጀሩን ይጠይቃል፤ ድርጅቱን ትርፋማ ሊያደርጉ የሚችሉ

ልምድ ያላቸው ሰራተኞች እንዲቀጠሩለትያደርጋል(ይቀጥራል)

መ. በአግባቡ ኃላፊነታቸውን ለማይወጡ ሠራተኞች ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣

ያሠናብታል፤

ሠ. የድርጅቱን ትርፋማነት ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስጊ ሁኔታ ሲገጥመው ለኃላው

ያሳውቃል፤

ረ. በንቃት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ስራዎቹ በተፈለገው መጠን፣ ጥራት እና ጊዜ

እንዲካሄዱ ያደርጋል፤

6
ሰ. በስሩ ያሉ ሰራተኞችን በመከታተል ግልጸኝነትና ተጠያቂት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡

ሸ. እንዳስፈላጊነቱ የገበያ ጥናት በማድረግ በግዥ ክፍል የሚገዙ ቁሳቁሶችን የገበያ ጥናት

ያደርጋል፤
ቀ. የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
በ. የግዥ እና የወጪ ቅፆችን ያዘጋጃል፤

ተ. በስድስት ወር እና በዓመት ሪፖርት ያቀርባል፤

ቸ. ጥፋት በሚያጠፋ ሰራተኞች ላይ በተቀመጠው ህግ መሠረት ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ቅጣት

ይቀጣል።

ኘ. ሙሉ ወጭዎችን ይከፍላል፣ ይመዘግባል ቀሪውን ለፋይናንስ ያስረክባል።

አ. ግብዓቱንና አዋጭነቱን እየገመገመ ያስተካክላል፤

ከ. አስፈላጊ ነገሮችን እና አስቸኳይ ግዥዎችን ይገዛል

ወ. የሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና የኦዲት ይገመግማል

ዘ. ሰራተኞች በማኅበሩ ንብረት ላይ ወይም በሌላ ሠራተኛ ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት ሲያደርስ ወይም

ሲሰርቅ፣ ሲደባደብ በዝምታ ያለማለፍና ለማኅበሩ ኃላፊዎች የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፤

ዠ. ስራን በታማኝነት የመስራት እና በስራ ቦታ ብቁ ሆኖ መገኘት የተሻሉ የስራ አማራጮችን

ያስቀምጣል፤

የ. ምዝበራን፣ ብኩንነትን መከላለከል እና አላግባብ የሚወጡ ወጪዎችን መቆጣጠርና መመጠን

አለበት፡፡

ደ. እንጀራ ሲወጣ በትክክል ተቆጥሮ መውጣቱን ያረጋግጣል፤

ገ. ቡኮ ሲቦካ ከቦታው ተገኝቶ ያስቦካል ያስወቅጣል፤

10. የዳቦ ቤት ምክትል ስራ አስኬያጅ ኃላፊነት

ሀ. ሙሉ ድርጅቱን በመቆጣጠር የማህበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነው፤


ለ. እለታዊ፣ ወርሃዊ እና አመታዊ እቅዶችን ያወጣል፤ በየጊዜው ጥናትና ምርምር በማድረግ የሚሰሩ
ስራወችን ፕሮፖዛል ይቀርፃል፤
ሐ. አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማናጀሩን ይጠይቃል፤ ድርጅቱን ትርፋማ ሊያደርጉ የሚችሉ

ልምድ ያላቸው ሰራተኞች እንዲቀጠሩለትያደርጋል(ይቀጥራል)

7
መ. በአግባቡ ኃላፊነታቸውን ለማይወጡ ሠራተኞች ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፣

ያሠናብታል፤

ሠ. የድርጅቱን ትርፋማነት ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ አስጊ ሁኔታ ሲገጥመው ለኃላው

ያሳውቃል፤

ረ. በንቃት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ስራዎቹ በተፈለገው መጠን፣ ጥራት እና ጊዜ

እንዲካሄዱ ያደርጋል፤

ሰ. በስሩ ያሉ ሰራተኞችን በመከታተል ግልጸኝነትና ተጠያቂት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡

ሸ. እንዳስፈላጊነቱ የገበያ ጥናት በማድረግ በግዥ ክፍል የሚገዙ ቁሳቁሶችን የገበያ ጥናት

ያደርጋል፤
ቀ. የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል፣ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፤
በ. የግዥ እና የወጪ ቅፆችን ያዘጋጃል፤

ተ. በስድስት ወር እና በዓመት ሪፖርት ያቀርባል፤

ቸ. ጥፋት በሚያጠፋ ሰራተኞች ላይ በተቀመጠው ህግ መሠረት ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ቅጣት

ይቀጣል።

ኘ. ሙሉ ወጭዎችን ይከፍላል፣ ይመዘግባል ቀሪውን ለፋይናንስ ያስረክባል።

አ. ግብዓቱንና ውጤቱን እየገመገመ ያስተካክላል፤

ከ. እንደየ አስፈላጊነቱ ሠራተኞችን ሰብስቦ ያወያያል።

ክፍል ሦስት

የማህበሩ ዋና ሥራ አስኬያጅ፣ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና የቅጥር ሰራተኞች መብት እና ግዴታ

11. በሌሎች ህጎች የተሰጡ መብቶች እንደተጠበቁ ሆነው የማህበሩ ዋና ሥራ አስኬያጅ መብት የሚከተሉትን
ያካትታል፡-

ሀ. በሥራ ውሉ እና በሕጉ መሠረት የሠራተኛውን የሥራ እንቅስቃሴና ክንውን የመምራት፣ የማስተዳደርና


የመቆጣጠር፤

ለ. በዚህ መመሪያና ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎችን መሠረት በማድረግ የመቅጠር የመቅጣት፣ ከሥራ
የማገድ፣ ከሥራ የማሰናበትና በሠራተኛው ላይ ሕጋዊ የሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ የመውሰድ፤

8
ሐ. የሥራ መደቦችን የመሰረዝ ወይም የማሻሻል፣ በተጠኑ የሥራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን የመመደብ እና
የማሰናበት መብቶች አሉት፡፡

12. ሥራ አስኪያጆች እና ቅጥር ሰራተኞች ማንኛውንም ህገወጥ ድርጊቶች መፈጸም የተከለከለ ሆኖ


የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

ሀ. ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት በሕይወትና በንብረት ላይ አደጋ የሚጥል ድርጊት በሥራ ቦታ መፈጸም፤

ለ. የማህበሩ ዋና ኃላፊ ሳይፈቅድ ከሥራ ቦታ ንብረት መውሰድ፣

መ. ማጭበርበር፤

ሠ. በሥራ ቦታ ላይ መጠጥ ጠጥቶና ሰክሮ መገኘት፤

ረ. በሥራ ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ድርጊት መፈጸም፤

ሰ. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ጥቃት መፈፀም፤

ሸ. የማህበሩን ምስጢር ሳይፈቀድ ሌለላ አካል አሳልፎ መስጠት፤

ቀ. ከስራ ውጭ የሆኑ ጓደኛ ወይም ዘመድ ከዋና ሥራ አስኬያጁ ፍቃድ ውጭ ይዞመግባት፤

በ. ስራ እንቅስቃሴው የሚገድብ ወይም ስጋት ላጥ የሚጥል ድርጊትና እንዝላልነት ሲኖር፡፡

13. የቅጥር ሰራተኞች ግዴታ

ሀ. ለህግ፣ ለማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ፣ ለአሰራር መመሪያዎች ተገዥ የመሆን፤

ለ. ሙሉ ችሎታውንና ያለውን አቅም በመጠቀም የኅብረት ስራ ማህበሩን አባለት ተጠቃሚነት ለማሳደግ


ተገቢውን ጥረት የማድረግ፤

ሐ. ስራን በታማኝነት የመስራት እና በአካልና በአእምሮ በስራ ቦታ ብቁ ሆኖ መገኘት፤

መ. በመጠጥ ወይም አእምሮን የሚያደነዝዝ እጽ ተጠቅሞ በስራ ገበታ ያለመገኘት፤ የኅብረት ስራ


ማህበሩን የስራ መግቢያና መውጫ ስዓት የማክበር፣ ለስዓት ቁጥጥር በተዘጋጀው የስዓት ፊርማ
የመፈረም፣ እንዲሁም በመደበኛ የስራ ስዓት ከኅብረት ስራ ማኅበሩ ስራ በስተቀር ሌላ የግል ስራ
አለመስራት፤

9
ሠ. ሠራተኛው ራሱንም ሆነ የሥራ ጓደኞቹን አዳጋ ላይ የሚጥል ወይም የማኅበሩን ጥቅም የሚነካ ሁኔታ
ሲያጋጥመው ወዲያውኑ ለአሰሪው የማሳወቅና በሥራ ቦታ በህይወትና በንብረት ላይ አደጋ
ሲደርስ ተገቢውን ትብብር የማድረግ፤

ረ. አንድ ሠራተኛ በመደበኛ የሥራ ስዓት ከሥራ አካባቢው ላይ ተነስቶ ከመሄዱ በፊት ከቅርብ ኃላፊው
ፈቃድ የመጠየቅ፤

ሰ. በስራ ገበታው ላይ ያልተገኘን ሠራተኛ ሥራ ለማሟላት ከክፍል ኃላፊው ወይም ከበላይ ኃላፊው
የሚሰጠውን ተገቢ የጹሁፍም ሆነ የቃል ትዕዛዝ ተቀብሎ የመፈጸም፤

ሸ. በኃላፊነት የተረከበውን የኅብረት ሥራ ማህበሩ ንብረት በጥንቃቄ የመጠቀም እና የመጠበቅ፤

ቀ. በሠራተኛው ቸልተኝነት ወይም ግዴለሽነት በንብረቶች ላይ ለሚደርስ ጉዳት በዕዳ ተጠያቂ የመሆን፤

በ. የሚመለከተው ኃላፊ ሳይፈቅድ ማንኛውንም ንብረት፣ መሳሪያ ወይም ቁሳቁስ መውሰድ ወይም ለሌላ
አሳልፎ መስጠት ወይም ከማኅበሩ ስራ ጋር ላልተያያዘ ተግባር ማዋል እና ሌሎችም እንዳይፈጽሙ
መቆጣጠር፤

ተ. ምዝበራን፣ ብኩንነትን መከላለከል የተፈቀደን ግብአት አላግባብ ያለመጠቀም፤

ነ. የፈረቃ ሰራተኛ የቅርብ አለቃው እስካልፈቀደ ድረስ የተረከበውን የማምረቻ እና ሌሎች መሳሪያዎች
ለተተኪ ሰራተኛ ሳያስረክብ አለመሄድ፤

ኘ. ሌላው ሠራተኛ በማኅበሩ ንብረት ላይ ወይም በሌላ ሠራተኛ ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት ሲያደርስ ወይም
ሲሰርቅ፣ ሲደባደብ በዝምታ ያለማለፍና ለማኅበሩ ኃላፊዎች የማሳወቅ ኃላፊነት፡፡

አ. በቂ ባልሆነ ምክንያት የምርት ውስንነት ከታየና ድርጅቱ ስጋት ውስጥ ከገባ ይጠየቃሉ፡፡

14. የቅጥር ሰራተኞች መብት

ሀ. ማንኛውም ሠራተኛ ምንም አይነት አድሎዎ ሳይደረግበት በድርጅቱ የሚሰጡትን ጥቅማጥቅሞች እና


አገልግሎቶች የማግኘት፤

ለ. የዲሲፕሊን እርምጃዎችና በመሳሰሉት ጉዳዮች አፈጻጸም ሂደት ቅሬታ ካለው ስለአፈጻጸሙ የተወሰዱ
እርምጃዎችን ቀርቦ የመረዳትና የማስረዳት፤

ሐ. የሠራተኞች ስብሰባ ሲደረግ በዚህ ላይ የመሳተፍ ሙያዊ አስተያየት የመስጠት፤

10
መ. አድሎ ከተፈጸመበት ለማኅበሩ ቅሬታ የማቅረብ፣ በጹህፍ ወይም በቃል መልስ የማግኘት፡፡

15. የግዥ ኃላፊነት

ሀ. ከስራ አስኬያጁ የተላለፈለትን ትዕዛዝ በመጠበቅ አስፈላጊ ነገሮችን ይገዛል፤


ለ. የወጪ መጠየቂያ ቅፅ ያዘጋጃል ወጪ ይጠይቃል፤
ሐ. የገበያ ጥናት በማድረግ አስፈላጊ ነገሮችን ይገዛል፤
መ. ለሰራተኞች የተፈቀዱ ነገሮችን ይገዛል በሰነድ ያስቀምጣል ለኦዲተር ይሰጣል፤
ሠ. አጠቃላይ ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎችን ግዥ ይፈጽማል፤
ረ. ቀሪ ብር (ትርፍ ብር) ለፋይናንስ ክፍል ተመላሽ ያደርጋል፤
ሰ. የማህበሩን ንብረት መዝግቦ ይይዛል፡፡

16.የኦዲተር ኃላፊነት

ሀ. የማኅበሩ ገንዘብና ንብረት አስተዳደር በሕግና በማኅበሩ መመሪያ መሠረት መሆኑን ያረጋግጣል፣
ጉድለቶች ሲኖሩ በጊዜው እንዲታረሙ ያደርጋል፤
ለ. የማኅበሩ የሥራ እንቅስቃሴ በማህበሩ ሕግና መተዳደሪያ ደንብ፣ በወጡ ዕቅዶች መሠረት መካሄዱን
ያረጋግጣል፤
ሐ. በማኅበሩ ስብሰባና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ስብሰባ ቃለ-ጉባዔዎች በአግባቡ መያዛቸውን
ያረጋግጣል፤
መ. ዕለታዊ፣ ወርሀዊ እና ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል፤ ማነኛውንም የድርጅት
እንቅስቃሴ ኦዲት ያደርጋል፤
ሠ. ሰነዶችን፣ የግዥ እና ወጪ ደረሰኞችን ኦዲት ያደርጋል፤
ረ. እንደ አስፈላጊነቱ ከስራ አስኬያጅ የሚሰጠውን ስራ ይፈጽማል፡፡

17. የፋይናንስ ኃላፊነት

ሀ. ስራ አስኬያጁ በጠየቀው መሰረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ደረሰኝ ለኦዲትር ይሰጣል፤


ለ. የዕለት ገንዘብ ይሰበስባል በዕለቱ ወደ ድርጅቱ አካውንት ያስገባል፤
ሐ. እንደ አስፈላጊነቱ ከስራ አስኬያጅ የሚሰጠውን ስራ ይፈጽማል፤
ረ. የስራ እቅድ ወይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ለሥራ እስኬያጅ ይሰጣል አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፣
ድጋፍ ይሰጣል፤
ሸ. የባለሙያዎችንና የስራውን ምጥጥን በማጤን የሰራተኞችን ቁጥር ይወስናል፤

11
ቀ. የሂሳብ ሰነዶች በመለየት ይመዘግባል፣ በቅደም ተከተል እንዲደራጅ ያደርጋል፣ በአግባቡ ተጠብቀው
መያዛቸውን ይከታተላል፤
በ. የሂሳብ አያያዝ እና የክፍያ አፈጻጸም በደንብና መመሪያ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፣
ይከታተላል፤
ተ. ያልተወራረዱ ክፍያዎችን ለይቶ ይከታተላል፣ እንዲወራረዱ ያደርጋል፤
ቸ. የተቋሙን የፋይናንስ አፈጻጸም መግለጫዎችና ሪፖርቶች በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል
በወቅቱ ያቀርባል፤
ኀ. በኦዲት ሪፖርት ግኝት መሠረት የማስተካከያ እርምጃ መግለጫዎች ለኃላፊ ያቀርባል፣ አፈፃፀሙን
ይከታተላል፤
ነ. የስራ ክፍሉ ተግባራት የሚመሩበትን መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ሲፀድቁም በአሰራሩ
መሠረት መፈጸማቸውን ያረጋግጣል፣ በየጊዜው እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤
ኘ. በስራ ክፍሉ ሰራተኞች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ጉዳዩን አጣርቶ ተጠያቂነት እንዲሰፍን
ያደርጋል(የዲስፕሊን ቅጣት እንዲኖር) ያደርጋል፤
አ. ተመላሽ የሆነን ብር በወቅቱ ወደ ማህበሩ አካውንት ያስገባል፡፡

18. የምርት ክፍል ሰራተኞች ኃላፊነት

18.1. የጋጋሪ ኃላፊነት


ሀ. በተቀመጠላቸው ሰዓት መሠረት በስዓታቸው ይወጣሉ ይገባሉ፤
ለ. ሰራ አስኪያጁ የሰጣቸውን አቅጣጫ ይፈፅማሉ፤
ሐ.ሊጋግሩ ተስማምተው በገቡበት መሰረት የሚጋግሩትን የእንጀራ ቁጥር ሙሉ መሆኑን ያረጋግጣሉ፤
መ. የቤቱን የራሳቸውን እና የእቃዎችን ፅዳት ይጠብቃሉ፤
ሠ. ቡኮው መቡካት አለመቡካቱን ያረጋግጣሉ፤
ረ. አስቸኳይ ትዕዛዝ ሲመጣ ከተመደበላቸው ስዓት በተጨማሪ ይገባሉ፤ አበል ይጠይቃሉ፤
ሰ. ችግሮች ሲኖሩ ለስራ አስኪያጁ ያቀርባሉ፤
ሸ. በቸልተኝነት ወይም ግዴለሽነት በንብረቶች ላይ ለሚደርስ ጉዳት በዕዳ ተጠያቂ ይሆናሉ፤
ቀ. የማኅበሩን ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም የውጭ ሰው ይዞ መግባት አይችልም።
በ. አስቤዛን በአግባቡ አለመጠቀምና ማባከን የሚሉት ናቸው፡፡

18.2. የአቡኪ ኃላፊነት

ሀ. በተቀመጠለት የዱቄት መለኪያ እና በተፈቀደለት ምጥጥን(ratio) መሰረት በትክክል ሰፍሮ ያቦካል፤

12
ለ. ቡኮውን ስራ አስኪያጁ በሚያስቀምጥለት የጊዜ ገደብ(ሰዓት) በደንብ አሽቶ ያቦካል፣ ያሻል ይወቅጣል፤

ሐ. አብሲት በወቅቱ ያዘጋጃል፤

መ. የቡኮ ማቡኪያ እቃዎችን ንፅህና ይጠብቃል፤

ሰ. ግብዓት መኖር አለመኖሩን ይቆጠራል በቶሎ ያሳውቃል፤

ረ. ውሐ ይቀዳል ሮቶ ይሞላል፤
ሸ. ችግሮች ሲኖሩ ለስራ አስኪያጅ ያሳውቃል፤
ቀ. በቸልተኝነት ወይም ግዴለሽነት በንብረቶች ላይ ለሚደርስ ጉዳት በዕዳ ተጠያቂ ይሆናል፤
በ. የሚመለከተው ኃላፊ ሳይፈቅድ ማንኛውንም ንብረት፣ መሳሪያ ወይም ቁሳቁስ መውሰድ ወይም ለሌላ
አሳልፎ መስጠት አይችልም፤
ተ. የማኅበሩን ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም የውጭ ሰው ይዞ መግባት አይችልም።
18.3. የአመላላሽ ኃላፊነት
ሀ. እንጀራ ሲወጣ ቆጥሮ አረጋግጦ ይወስዳል፤
ለ. የወሠዳቸውን እቃዎች በወቅቱ ይሰበስባል፤
ሐ. የእንጀራ መሸፈኛ ፌስታሎችን በወቅቱ ያጥባል፤
መ. የተቋሙን ንብረቶች በጥንቃቄ መጠቀም እና መጠበቅ አለበት፤
ሠ. ችግሮች ሲኖሩ ለስራ አስኪያጅ ያሳውቃል፤
ረ. በቸልተኝነት ወይም ግዴለሽነት በንብረቶች ላይ ለሚደርስ ጉዳት በዕዳ ተጠያቂ ይሆናል፤
ሰ.የማኅበሩን ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም የውጭ ሰው ይዞ መግባት አይችልም።
18.4. የዳቦ ቤት ሽያጭ ሰራተኛ ኃላፊነት
ሀ. በቀን የተሸጡ ነገሮችን በጊዜው መዝግቦ ያስቀምጣል፤
ለ. ፈጠን ብሎ በማግባባት ይሸጣል፤
ሐ. ዱቤ ከኃላፊው ካልተፈቀደለት በስተቀር ለማንም አይሸጥም፤
መ. በተፈቀደለት ጊዜ እና ሰዓት ብቻ ይወጣል ይገባል፤
ሠ. በመደበኛ የሥራ ስዓት ከሥራ አካባቢው ላይ ተነስቶ የሚሄደው ከቅርብ ኃላፊው ፈቃድ ካገኘ ብቻ ነው፤
ረ. የኃላፊውን ፈቃድ ሳያገኝ ማንኛውንም የውጭ ሰው ወይም ዘመድ ይዞ መግባት አይችልም።

13
የአአትሪኮን ማህበር ወርሀዊ የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ

ቃለ ጉባኤ

የስብሰባ ቦታ፡- ላፍቶ ክ/ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ቅ/ጽ/ቤት
የስብሰባ ቀን፡- 03/05/2016 ዓ/ም
የስብሰባ ሰዓት፡-ከምሽቱ 1፡30-7፡00
አወያይ፡- አቶ ይታያል ንብረቱ የማህበሩ ሰብሳቢ እና ዋና ስራ አስኬያጅ
በስብሰባው የተገኙ ስም ዝርዝር
1. አቶ ይታያል ንብረቱ………………..…..ዋና ስራ አስኬያጅ
2. አቶ ያስችላል እምቢአለ…………………የዳቦ ቤት ዋና ኦዲተር
3. አቶ ሲሳይ መለሰ ……………….….…..የእንጀራ ቤት ግዥና ፋይናንስ ኃላፊ

14
4. አቶ ተመስገን ሙሉ ……………….......የዳቦ ቤት ም/ስራ አስኬያጅ
5. አቶ ዳኛው ይመር ………………………የእንጀራ ቤት ዋና ኦዲተር
6. አቶ ደርብ ዘውዴ ……………………….የእንጀር ቤት ም/ኦዲተር
7. ወ/ሮ አያልነሽ ዋለ………………………..የዳቦ ቤት ም/ኦዲተር
8. ወ/ሪት አገርነሽ ያንበል………….………..የዳቦ ቤት ግዥና ፋይናንስ ኃላፊ
9. ወ/ሮ መቅደስ መኳንት………….………..አባል

የስብሰባው አጀንዳዎች
አጀንዳ 1:- የሥራ መዋቅርን እና መመሪያን ለማጽደቅ ጠቅላላ ጉባዔውን በማወያየት ግብዓቶችን ማካተት
በዚህ አጀንዳ ላይ የተነሱ አስተያየቶች፣ የተደረገ ውይይት እና ውሳኔዎች

 አቶ ይታያል ንብረቱ ስብሰባውን በመምራት ሀሳብ ለሚያነሱ ተሰብሳቢዎች እድል በመስጠት

ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡
 ማህበሩ ሥራ ከመጀመሩ በፊት የመመስረቻ ጽሁፍ(ደንብ) በማውጣትና በማጽደቅ ሲተዳደርና
ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ይሁን እነጂ ደንቡ እናዳለ ሆኖ የሥራ መመሪያ በማውጣት ማህበሩ ስራን
በአግባቡ ለማቀድ፣ ለማደራጀት፣ ለመምራት፣ ለመቆጣጠር እና አስፈላጊ ውሳኔዎችን በወቅቱ
በመስጠት ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ መዋቅር እንዲጸድቅ ተደርጓል፤
 ከስራ ዝርዝር አንፃር ሥራን መከፋፈልና በትብብር መስራት ቢቻል የሚል ሀሳብ ተነስቷል፡፡
 ሁሉም የራሱ የሆነ መክሊት እንዳለው እና በመክሊቱ መሰረት እሄን እሰራለሁ ብሎ ኃላፊነት
ቢወስድ የሚበረታታ መሆኑ ተገልፆ፤ በተዘጋጀው መዋቅር መሰረት በዕለቱ ለተገኙ አባላት
ኃላፊነት ተሰጥቷል፤
 ኃላፊነቱን ያልተወጣ ማነኛውም ሰው በጠቅላላ ጉባኤው እንደሚቀጣ ተወስኗል፡፡

አጀንዳ 2:- ወርሀዊ የስራ ክንውን ማቅረብ እና በቀረበው ላይ አስተያየት መስጠት

በዚህ አጀንዳ ላይ የተነሱ አስተያየቶች፣ የተደረገ ውይይት እና ውሳኔዎች


 በመጀመሪያ የእንጀራ ቤት ኦዲት ሪፖርት በአቶ ያስችላል እምቢያለ የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱ አንዳንድ ግልፅ ያልሆኑ
ነገሮች እንዳሉበት ተጠቁሟል፡፡ በዚህም ላይ ብዙ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሪፖርቱ በቀጣይ ሳምን አብሮ
ለማየትና ለማጥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
 ከቀረበው ኦዲት በመነሳት እንጀራ ቤቱ ላይ ወጭዎች እንደበዙ እና በቀጣይ መቀነስ እንዳለባቸው የተነሳ ሲሆን
በዚህም ላይ ለእንጀራቤት ም/ስራ አስኬያጅ ኃላፊነቱን በመስጠት አላስፈላጊ የሆኑ ዎጭዎች መቀነስ እንዳለባቸው
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

15
 እንጀራ ቤት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች የተሰጣቸውን ሥራ አውቀው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ የተሻለ
የሥራ እንቅስቃሴ መኖር እንዳለበት የተነሳ ሲሆን በዚህም ላይ ኃላፊነታቸውን ለማይወጡ ሰራተኞች እርምጃ
መወሰድ እንዳለበትና የተሻለ የስራ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት ሥምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

አጀንዳ 3:- የወርሀዊ መዋጮ ክፍያ አከፍፈልን በተመለከተ

በዚህ አጀንዳ ላይ የተነሱ አስተያየቶች፣ የተደረገ ውይይት እና ውሳኔዎች


 ወርሀዊ ክፍያን በሰዓቱ ያልከፈሉ አባሎች ላይ ከጥር ወር ጀምሮ ወር በገባ በአስራ አምስት
ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያልከፈለ አባል መተዳደሪያ ደንባችን ላይ በተወሰነው መሰረት ቅጣቱ
ተግባራዊ እንደሚደረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
 ከየኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም የገባነውን የግዴታ ቁጠባ የስምንት ወር ክፍያ አልከፈላችሁም
ተብሎ 3200 ብር እዳ እንዳለብን በተገለጸው ላይ አቶ ይታያል ንብረቱ ኃላፊነቱን በመውሰድ
ማስተካከል እንደሚችሉ በሰጡት ሀሳብ መሰረት ማስተካከል እንደሚቻል ስምምነት ላይ
ተደርሷል፡፡

አጀንዳ 4:- የኃላፊዎችን እና የሰራተኖችን ደመወዝ በተመለከተ

በዚህ አጀንዳ ላይ የተነሱ አስተያየቶች፣ የተደረገ ውይይት እና ውሳኔዎች


 ለዋና ኃላፊ ለጊዜው አበልም ወይም ደመወዝ መታሰብ እንዳለበት የተነሳ ሲሆን በዚህም ላይ
ብዙ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለጊዜው ደመወዝም ሆነ አበል መከፈል እንደሌለበት ስምምነት
ላይ ተደርሷል፡፡
 አቶ ፈንታሁን ንብረቱ የእንጀራቤት ም/ስራ አስኬያጅ እና ወ/ሪት አበሩ እንጀራ ጋጋሪ ሰራተኛ
ባቀረቡት የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤው ጉዳዩ ላይ የሚከተሉትን ነጥቦች
በማስቀመጥ የደሞዝ ጭማሬ እንዲደረግላቸው ተወስኗል፡፡
 የሰራተኞችን ደመወዝ በመጨመር የሥራውን ቅልጥፍናና ውጤታማነት መጨመር
ይቻላላ ብሎ በማሰብ፤
 አሁን ካለው አሰራር በተሻለ መልኩ ሰርተው ጥሩ ውጤት ያስመዘግባሉ ብሎ በማሰብ፤
 የሚስተዋለውን የወቀጣና የቡኬት ማነስ፣ የእንጀራ ውጤት ማነስ፣ የቁጥር መጉደል እና
የተጋነነ የአስቤዛ ወጪን በማሻሻል ጥሩ ውጤት ያስመዘግባሉ ብሎ በማሰብ ደመወዝ
እንዲጨመርላቸው ተወስኗል፡፡

16

You might also like