Code Enforcement Notice

You might also like

Download as docx, pdf, or txt
Download as docx, pdf, or txt
You are on page 1of 1

ቀን፡- 01/09/2016 ዓ.


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽ/ቤት
ለአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ንብረትነቱ የራሴ የሆነውን እና በጽ/ቤታችሁ በኩል በቀን 18/08/2016 ዓ.ም የተወረሰብኝ 700 ከረጢት ከሰል
በ 03 ቀናት ውስጥ እንዲመለስልኝ ስለማሳዎቅ፡-

ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው እኔ አመልካች ብዛት 700 ከረጢት ከሰል በቀን 17/08/2016 ዓ.ም
ከክ/ሀገር አስመጥቼ ተከራይቼ የምኖርበት ግቢ ውስጥ አስቀምጨ የንግድ ስራ ፈቃድ ለማውጣት በሂደት ላይ
እያለሁ በቀን 18/08/2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 8፡00 ሰዓት ሲሆን የእናንተ ጽ/ቤት ባልደረቦች ከሰሉን በህገ-
ወጥ መንገድ እየነገድህ ተገኝተሃል በሚል ምክንያት አንስተው የወሰዱብኝ መሆኑ ይታዎቃል፡፡ ይህን
ተከትሎም በጽ/ቤታችሁ በተደጋጋሚ ጊዜ በአካል በመቅረብ ከሰሉን ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ከክፍለ ሀገር
አስመጥቼ ግቢየ ውስጥ አስቀምጨ የንግድ ፈቃድ ለማውጣት በቀን 18/08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
ጀምሮ ገቢዎች ጽ/ቤት ቀርቤ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን እንዳቀርብ ተነግሮኝ አስፈላጊ መረጃዎችን እና
ሰነዶችን እየሰበሰብሁ የነበርሁ መሆኑን፤ ምንም አይነት የንግድ ስራ ያልሰራሁ መሆኑን፤ በኋላም ቀደም ብየ
ጀምሬው በነበረው መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ ያወጣሁ መሆኑን በመግለፅ ከሰሉን እንድትመልሱልኝ ጠይቄ
የነበረ ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ አልተሰጠኝም፡፡ በመሆኑም ይህን የራሴ የሆነውን ከሰል በ 3 ቀናት ውስጥ
እንድትመልሱልኝ፤ ካልሆነ ግን በፍ/ቤት መደበኛ ክስ ለማቅረብ የምገደድ መሆኑን በትህትና አሳውቃለሁ፡፡

ገዳሙ መለስ -----------


ስለማስጠንቀቂያ ሰጭ:- ---------------------------
ፊርማ---------------------

You might also like